YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
"ለሼህ አላሙዲ #መፈታት የጠቅላይ ሚንስትሩ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበር" አቶ ተካ


በትውልድ ኢትዮጵያዊ እና የሳዑዲ ዜግነት ያላቸው ቢሊየነሩ ሼህ ሞሐመድ ሁሴን አሊ-አላሙዲ ትናንት ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ከሪያድ ወደ ጅዳ በማቅናት ከቤተሰባቸው ጋር ተቀላቅለዋል።

የሳዑዲ መንግሥት ያካሄደውን የፀረ-ሙስና ዘመቻን ተከትሎ ከበርካታ ንጉሣዊ ቤተሰቦች እና ከበርቴዎች ጋር ተይዘው ከ14 ወራት በላይ በእስር ያሳለፉት አላሙዲ እንዲፈቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ጠበቃቸው አቶ ተካ አስፋው ለቢቢሲ ተናገረዋል።

አቶ ተካ ''ትናንት (እሁድ) በስልክ ተገናኝተናል። ጤናቸው በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል። ከቤተሰቦቻቸው ጋርም ተቀላቅለዋል'' ያሉ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ መቼ ሊመጡ ይችላሉ ተብለው ለተጠየቁት ''ወደ ኢትዮጵያ መምጣቸው አይቅርም፤ ነገር ግን መቼ እንደሚመጡ በእርግጠኝነት መናገር አልችልም'' ሲሉ የአላሙዲ ጠበቃ አቶ ተካ አስፋው ተናግረዋል።

ካለፈው ግንቦት 2009 ዓ.ም ጀምሮ አሊ-አላሙዲ ከእስር እንዲፈቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጥረቶችን ሲያደርጉ እንደቆዩ የሚናገሩት አቶ ተካ ''ጠቅላይ ሚንስትራችን ከአንዴም ሁለቴ ቦታው ድረስ ተገኝተው ከሳዑዲ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድረገዋል። ከዚያም በኋላ በነበራቸው ግንኙነት ከፍተኛ ጥረት እንዳደረጉ ነው የምናውቀው። ለመፈታታቸው የእሳቸው ጥረት እንዳለበት ነው የተረዳነው'' ብለዋል።

የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት የፌስቡክ ገጽ የባላሃብቱን ከእስር መፈታት ይፋ ባደረገበት ጽሁፍ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ግንቦት 2010 ዓ.ም ሞሐመድ ሁሴን አሊ-አላሙዲ ከእስር ለማስፈታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን እና በቅርቡም ወደ አገራቸው ይመለሳሉ በማለት በሚሊኒያም አደራሽ ያደረጉትን ንግግር አስታውሷል።

የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ጨምሮም አሊ-አላሙዲ በሰላም እንዲመለሱ መልካም ምኞታችንን አንገልጻለን በማለት አስፍሯል።

ከ14 ወራት በፊት ከአላሙዲ ጋር በሙስና ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው ከነበሩት መካከል ጥቂት የማይባሉ ከበርቴዎች መጠኑ በይፋ ያልተገለጸ ነገር ግን ካላቸው ሃብት ከፍተኛ መጠን ያለውን ገንዘብ ለሳዑዲ መንግሥት ሰጥተው ከወራት በፊት ከእስር መውጣታቸው ይታወሳል።

ከዚህ አንጻር ሼህ አላሙዲንም ከእስር ለመፈታት #ከፍተኛ_ገንዘብ_ከፍለዋል ወይ ተብለው የተጠየቁት ጠበቃቸው አቶ ተካ ''ከፍለዋል ብዬ ለመናገር ይከብደኛል።

የተፈቱበትን አኳኋን ዝርዝር ሁኔታ ሰለማላውቅ ይሄ ነው ብዬ መናገር አልችልም። እኔ ግን ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለዋል ብዬ አላምንም። ጠቅላይ ሚንስትሩ ግን ለመፈታታቸው የማይናቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል'' ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@YeneTube @Fikerassefa