YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#update
በምድር፣ በአየር፣ በባህር እና በህዋ ዝግጁ የሆነ የመከላከያ ሰራዊት ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን የኢፌዲ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #አብይ አህመድ አስታወቁ።

በመከላከያ ሰራዊት በየደረጃው እየተደረገ የነበረው ውይይት ማጠቃለያ መድረክ ላይ ጠ/ር ዶ/ር #አብይ አህመድ እንደተናገሩት፤ ዘመናዊ ዐውደ ውጊያ በሚጠይቃቸው አምስቱም ምህዳሮች ዝግጁ የሆነ #መከላከያ ሰራዊት የመገንባቱ ሂደት ተጀምሯል።

የአሰራር መመሪያዎች እንዲዳብሩና ዘመናዊ ሰራዊት ሊኖረው በሚገባው ደረጃ እንዲሆኑ #ከፍተኛ ጥረት መደረጉንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር የገለጹት።

መከላከያ የሀገሪቱ አቅም በፈቀደ መጠን ቴክኖሎጂን የሚታጠቅ፣ #በራሱ አቅም መጠገን፣ ማሳደግ ብሎም መፍጠር የሚችል እንዲሆን በርካታ የአቅመ ግንባታ ስራዎች #እየተሰሩ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሰራዊቱ እነደሌሎች አገራት ከራሱም አልፎ ለሌሎች ዘርፎች ምንጭ መሆን የሚችል የቴክኖሎጂ ማዕከል እንዲሆን እየተሰራ ይገኛል ሲሉም ነው የገለጹት።

ምንጭ ፦የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
@yenetube @mycase27