YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በአማራ ክልል፣ ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን፤ ደዋ ጨፋ ወረዳ በታጠቁ ሰዎችና በጸጥታ አካላት በተካሄደ ግጭት የሰው ሕይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡

በኢንቨስትመንት የተያዘ መሬት በአግባቡ ልማት ላይ አልዋለም በሚል ቅሬታ ግጭቱ ነሐሴ 25 እና 26 ቀን 2010 ዓም መከሰቱን ነው የወረዳው ጸጥታ ኃላፊ የተናገሩት፤ በድርጊቱ ተሳታፊ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
ምንጭ ፦ ዋዜማ ራዲዮ
@Yenetube @mycase27
#በአማራ ክልል አፈ ጉባኤ ወሮ.ወርቅሰሙ ማሞ የሚመራው ልዑክ ዛሬ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገናኝቷል፡፡

በቆይታቸውም ሁለቱ ሀገራት የጀመሩትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር የአማራ ክልል የተወሰነ ርቀት እንደተጓዘ ገልጾ፤ምክር ቤቱ ያለውን ልምድ እንደሚያካፍልም ተናግሯል፡፡
ምክር ቤቱ ሁለቱ ሀገራት የጀመሩትን ግንኙነት አድንቋል፡፡

የተጀመረውን ግንኙነት ለማጠናከርም ሁለቱም አካላት በጋራ እንደሚሰሩም አስታውቀዋል፡፡
የአማራ ክልል ምክር ቤት ልዑካን ቡድን ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ስጦታም አበርክቷል፡፡

በምክር ቤት አፈ ጉባዔ የሚመራ የሃይማኖት አባቶችን ያካተተ ልዑክ ወደ ኤርትራ የሚያቀናው የሁለቱን አገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና ትስስርን ለማጠናከር ነው፡፡
©Amma
@yenetube @mycase27
የተጠናከረ የአቶ ዳውድ ኢብሳ ለዋልታ ቲቪ የተናገሩት ቅንጫቢ⤵️

📌"ኦነግ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው ከኢትዮዽያ መንግስት ጋር ትጥቁን #ፈቶ #በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ነው ተብሎ የሚነገረው መሰረተ ቢስ ወሬ ነው"

📌"እኛ ትጥቅ እንድንፈታ የተስማማንበት #ስምምነት_የለም። የታጠቀው ኣአካል ትጥቅ ይዞ እያለ እኛ ትጥቅ የምንፈታበት ምክን ያት የለም።"

📌"ትጥቅ መፍታት የሚባል #sensitivity ጥያቄ ነው። ትጥቅ ፈቱ መባልም አንፈልግም። ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጣው አንዱ ትጥቅ የሚፈታ አንዱ ትጥቅ የሚያስፈታ ይመስላል። የሀገሪቱ ሰላም እንዲጠበቅ ኦነግ ያለው ሚና ምን እንደሚሆን ነው የተስማማነው።"

📌አቶ ዳውድ #ሰኔ_16 በጠቅላይ ሚንስትሩ ላይ በተደረገው የግድያ ሙከራ ድርጅታቸው እንዳልተሳተፈ ገልፀዋል። #በቡራዩና_በአዲስ አበባ በተፈጠሩ ግጭቶችም ኦነግ #አለመሳተፉን ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።

📌#በቤኒሻንጉል#በወለጋና #በከፋ በተፈጠሩ ግጭቶች #ኦነግ መሳተፉንና አለመሳተፉን ለማረጋገጥ ማጣራት እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

📌አቶ ዳውድ በበደኖና በአርባ ጉጉ #በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ #በገለልተኛ አካል እንዲጣራ የኦነግ ፍላጎት መሆኑን ገልጸዋል።
@YeneTube @Fikerassefa
ቤተክርስቲያን እንዲሁም ቤቶች ተቃጥለዋል‼️‼️

#በአማራ_ክልል_ኦሮሞ_ብሄረሰብ አስተዳደር ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ከብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤት መግለጫ ተሰጥቷል። መግለጫው በአካባቢው የተፈጠረውን አለመረጋጋት ጠቅሶ "የተከሰተውን የሰላም መደፍረስ ለማረጋጋትና የሚመለከታቸው የፌደራልና የክልል የፀጥታ አስከባሪ ተቋማት አስፈላጊውን ሕጋዊና ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ" ትእዛዝ አስተላልፏል።

ከሰሞኑ በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የተከሰተው አለመረጋጋት ወደ ሰሜን ሽዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ተሸጋገሮ የሰው ህይዎት መጥፋቱ፣ ንብረት መውደሙ እና ዝርፊያ መፈፀሙ ተነግሯል።

አቶ ሰማቸው የተባሉ የማጀቴ ከተማ ነዋሪ እንደተናገሩት ከትናንት ጀመሮ በተደራጀ መልኩ የቡድን መሳሪያ የታጠቁ አካላት በንጹሃን ዜጎች ላይ ሲተኩሱ ውለዋል፤ በዚህም 14 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ሁለቱ የፖሊስ አባላት ናቸው ብለዋል።

አሁንም ስጋት በመኖሩ ነዋሪው አካባቢውን ለቅቆ ወደ ገጠር ቀበሌዎች እየተሰደደ ነው ያሉት አቶ ሰማቸው በዚህ ሰአት የሚካሄድ ተኩስ የለም ነገር ግን የጸጥታ አካላት ባለመድረሳቸው ስጋት አለን ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ሌላኛው የአካባቢው ነዋሪና ስሙን መግለጽ ያልፈለገው ግለሰብ ደግሞ "ከትናንት ጀምሮ ባልተዘጋጀንበት ሁኔታ ከቀያችን ድረስ መጥተው ተኩስ ከፈቱብን ባለን አቅም ስንከላከል ለጊዜው ከሁለታችንም ወገን ቁጥራቸውን የማላውቃቸው ሰዎች ሞተውብናል" ብሏል።

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ አቶ ካሳሁን እምቢአለ እንደገለጹት ደግሞ የጸጥታ አካላት በሁሉም ቦታ ደርሰዋል። አስፈላጊ ከሆኑ አካላት ጋርም እየተነጋገርንና ነገሮች ወደ ቀደመ ሰላማቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ እያመቻቸን ነው ሲሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ትናንት በነበረው ግጭት አንድ ቤተ ክርስቲያን የተቃጠለ መሆኑን የተናገሩት የመምሪያው ኃላፊው በሌላ አካባቢ ቤተክርስቲያንም የማቃጠል ሙከራ ተካሂዶ ባይሳካም በዙሪያው የሚገኙ ቤቶች ግን ተቃጥለዋል ብለዋል። አጣዬ ላይ የግለሰብ ቤቶች እንደተቃጠሉና ዝርፊያም እንደተፈጸመ አብራርተዋል።

"ኦነግ ያደራጃቸው ናቸው ይህን የፈጸሙት" የሚሉት አቶ ካሳሁን "አላማቸውም ሽብር መፍጠርና ዝርፊያ ማካሄድ ነው" ብለዋል። በዚህ ወቅት በስፍራው የሚገኙት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ እንደገለጹት ደግሞ በአሁኑ ወቅት ሁሉም አካባቢዎችን ማረጋጋት ተችሏል።

አክለውም ሁኔታውን ዘላቂ ሰላም እንዲኖረው ለማድረግም ከሃይማኖት አባቶችና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እየተደረገ ነው ብለዋል።

ትናንት የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ደብረ ብርሃንም ከፍተኛ የሆነ ህዝብ ጎዳና ወጥቶ ችግሩን ሲቃወም መስተዋሉን ከስፍራው ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ነግረውናል።

ዛሬ በአጣዬ ማጀቴና ካራቆሬ አንጻራዊ መረጋጋት የታየ መሆኑን የተናገሩት አቶ ካሳሁን ከባንኮችና አንዳንድ ተቋማት ውጭ ሌሎች አገልግሎቶች መደበኛ ስራቸውን በመስራት ላይ ናቸው ብለዋል። በስፍራው የመከላከያ ሠራዊትም ደርሷል ብለዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ የሚገኙ 500 የሚሆኑ የአካባቢው ተወላጆች ድርጊቱን በማውገዝ ዛሬ ጠዋት ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥተዋል።

መግለጫውን የሰጡት ተሰብሳቢዎች ተወካይ አቶ ደጀን መንገሻ በአካባቢው የተፈጠረ ግጭት አነሳስቷቸው መሰባሰባቸውን ጠቅሰው መግለጫው በቦታው ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግድያ፣ አፈናና ዘረፋን አስመልክቶ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራና ሠላም እንዲመጣ ለመጠየቅ ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል።

ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ በአጣዬ፣ ማጀቴ፣ ካራ ቆሬ፣ እና በአካባቢው በንፁሃን ላይ የተከፈተው ተኩስ፣ ግድያ፣ ዘረፋና አፈና እንዲቆም መንግስት ፈጣን እርምጃ እንዲወስድ፣ በሕይወትና ንብረት ላይ አደጋ ያደረሱ የተደራጁና የታጠቁ ኃይሎች በአፋጣኝ ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ ጥቃቱን በማውገዝ መንግስት ከህዝብ ጎን እንዲቆም፣ በቦታው በቂ የፀጥታ አካላት ተመድቦ ቦታውን እዲያረጋጋ፣ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አፋጣኝ ሰብዓዊና ቁሳዊ እርዳታ እንዲደርሳቸው ጥሪ ለማቅረብና ሟቾቹንም በፀሎት ለማሰብ ነው ሲሉ ዐብይ የመግለጫውን ይዘቶች ዘርዝረዋል።

አቶ ደጀኔ እንዳሉት በተለይ በማጀቴ፣ ካራ ቆሬ፣ አንፆኪያ አካባቢዎች ከዚህ ቀደምም በግጦሽም ሆነ በውሃ ሲጋጩ፣ በሽማግሌ ሲፈታ የኖረ ነው በማለት ሕዝቦቹ ተሳስበውና ተከባብረው የሚኖሩ ናቸው፤ ነገር ግን "አሁን የተፈጠረው ግን ታስቦበት፣ ታቅዶና ተጠንቶ የተደረገ ነው፤ ተራ ግጭት አይደለም" ሲሉም ያክላሉ።

ስልጠና ተካሂዶ፣ ከግለሰብ የማይጠበቅ መሳሪያ ተታጥቀው፣ ቦታና ምሽግ ይዘው ህዝቡን ሲያጠቁ ነበር የሚሉት ተወካዩ የተደራጀና ሌላ ዓላማ ያለው ኃይል እንዳለ ተረድተናል ብለዋል።

"የክልሉ ልዩ ኃይልም ሆነ መከላከያም የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ገብተዋል ፤ነገር ግን ቦታው ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት የክልሉም ሆነ የፌደራል መንግስት በሚገባው ልክ የተረዱት አይደለም፤ የተላከውም ኃይል በቂ አይደለም" ሲሉ የጉዳዩን አሳሳቢነት ያስረዳሉ።

አሁንም በአጣዬ ዙሪያ አላላ የተባለው አካባቢ የታጠቁ ኃይሎች ጥቃት እያደረሱ እንደሆነ መረጃ እንደደረሳቸውም ነግረውናል።

"ሕዝቡ ከኖረበት፣ ከአገሩ፣ ከርስቱ ነው እየተፈናቀለ ያለው" የሚሉት አቶ ደጀን መንግስት ይህንን ኃይል ያደራጀው አካል በመመርመር ሥር ነቀል ለውጥ እንዲያመጣ አሳስበዋል።

በቀጣይም ኮሚቴ አዋቅረው ለኢህአዴግ ፅ/ቤት፣ ለአዴፓ ፅ/ቤትና ለጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት ኃሳባቸውን ለማቅረብ እንደተዘጋጁ ገልፀውልናል።

ምንጭ:- ቢቢሲ
@YeneTube @FikerAssefa
አማራ ክልል የሚገኙ ዩንቨርስቲዎች የትግራይ ክልል ተማሪዎች እስከ ህዳር 5 ድረስ በልዩ ሁኔታ እንደሚመዘገ ታዋቀ።

#በአማራ ክልል ወደሚገኙ ዩንቨርስቲዎች የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ተማሪዎችን አልክም ማለቱ የክልሉን ትምህርት ቢሮ ጠቅሰው መገናኛ ብዙሃን ከዘገቡ በኋላ በትናንትናው እለት ማስተባበያ መስጠቱ ይታወሳል። በዚው መግለጫ ተዘናግተው ወደ ዩንቨርስቲዎቹ ያላመሩ ተማሪዎችን በልዩ ሁኔታ እስከ ህዳር 05/2012 ዓም ድረስ ተገኝተው እንዲመዘገቡ እድል መመቻቸቱን ሰምተናል።

@Yenetube @FikerAssefa
በባህር ዳር ከተማ ሊካሄድ የነበረው 11ኛው የጣና ፎረም ለሶስተኛ ጊዜ ተራዘመ!

የአፍሪካ ሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ የሚመክረው እና #በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ የሚካሄደው ዓመታዊው የጣና ፎረም ጉባኤ ለሶስተኛ ጊዜ ተራዘመ።11ኛው ጉባኤ መጀመሪያ ሊካሄድ ቀን ተቆርጦለት የነበረው ባለፈው ዓመት ከጥቅምት 2-4 ቀን 2016 ዓ.ም ነበር።

ሆኖም ጉባኤው “ባልተጠበቁ ሁኔታዎች ምክንያት” እንደተራዘመ የፎረሙ ጽህፈት ቤት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላም እና ደህንነት ጥናቶች ተቋም አስታውቆ ነበር።ጉባኤው ሚያዚያ ወር 2016 ዓ.ም. እንደሚካሄድ ጽህፈት ቤቱ በጊዜው አስታውቆ የነበረ ቢሆንም በተባለው ጊዜ ሳይካሄድ ለሁለተኛ ጊዜ ተራዝሟል።

“አፍሪካ እየተሻሸለ በመጣው የዓለም ሥርዓት ውስጥ” የሚል መሪ ቃል የያዘው 11ኛው ጉባኤ ከጥቅምት 15-17 2017 ይካሄዳል ተብሎ ተጠብቆ ነበር።ነገር ግን ፎረሙ በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ “11ኛው የጣና ከፍተኛ የጸጥታ ጉዳዮች ፎረም [እ.ኢ.አ] ወደ 2025 መተላለፉን የጣና ፎረም ሴክሬታሪያት ለማሳወቅ ይወዳል” ብሏል።

ፎረሙ አክሎም የጣና ፎረም ሴክሬታሪያት ከጣና ፎረም ቦርድ ጋር በመሆን ፎረሙ የሚካሄድበትን ቀጣይ ቀን ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።የጣና ፎረም የሚካሄድበት የአማራ ክልል ላለፈው አንድ ዓመት በፌደራል መንግስቱ እና በፋኖ ኃይሎች መካከል ውጊያ እየተካሄደበት ይገኛል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ትናንት መስከረም 27/ 2017 ዓ.ም አመሻሽ ባወጣው መግለጫ የጣና ፎረምን በምታስተናግደው ባህርዳር ከተማ “ተጠምዶ የነበረ ፈንጂ ጉዳት ሳያደርስ” መምከኑን አስታውቋል።የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በዚሁ መግለጫው ፈንጂው የመከነው በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 13 በተለምዶ ኪቤአድ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ መሆኑን ጠቁሟል።ፖሊስ ኮሚሸኑ “ጽንፈኛው ኃይል ያጠመደው” ሲል በክልሉ የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን ተጠያቂ ማድረጉን ከቢቢሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@YeneTube @FikerAssefa
😁17👍142😭1
ዜና፡ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ #በትግራይ የተፈናቃይ መጠለያዎች በርሃብ ሳቢያ ስምንት ሰዎች ሞተዋል ተባለ

በተመሳሳይ
#በአማራ ክልል የእርዳታ መቋረጥ ችግር እየፈጠረ መሆኑም ተገልጿል

በትግራይ እና በአማራ ክልሎች ከቀያቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ለሚገኙ ነዋሪዎች የሰብአዊ እርዳት መስጠት ከተቋረጠ ወዲህ ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸው ተገለጸ።

በትግራይ አክሱም ከተማ በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው ከሚገኙ ተፈናቃዮች መካከል ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ስምንት ሰዎች በረሃብና በመድሃኒት እጦት መሞታቸውን የምዕራብ ትግራይ ዞን የአክሱም ክላስተር ተፈናቃዮች አስተባባሪ አቶ ካህሳይ አሳየሀኝ አስታውቀዋል።

በተያያዘ ዜና በአማራ ክልል አዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ይሰጥ የነበረ እርዳታ መቀነስና በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ መቋረጥ በክልሉ በሚገኙ ተፈናቃዮች ዘንድ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ እንደሆነ ተፈናቃዮች ገልጸዋል።

ተፈናቃዮቹ ምግብ የለም፣ የመጠለያ ድንኳኖች ፈርሰዋል፣ የህክምና ባለሙያዎች ከመጠለያዎች ወጥተዋል፤ “ይደረጉ የነበሩ የዱቄት፣ የዘይትና አልባሳት ድጋፎች የሉም” ማለታቸውም ታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
😭21👍102😁2