YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በተፈጠረ ግጭት የሰዎች ህይወት አለፈ።

ግጭቱ የተፈጠረው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ኦዳ ቤልዲግ ወረዳ ደላቲ ከተማ መሆኑንም ቢሮው አስታውቋል።

በተፈጠረው ግጭት በክልሉ ይኖሩ የነበሩ የ10 የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች ህይወት ማለፉም ነው የተመለከተው።

ከዚህ በተጨማሪም አራት ሰዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በመንዲ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ ይገኛሉ።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ባወጣው መግለጫም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጋር በመሆን የግጭቱን መንስኤ በማጣራት አጥፊዎች ለህግ እንዲቀርቡ እየሰራ መሆኑን የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ።

በተጨማሪም ለዘመናት በወንድማማችነት የኖሩት የሁለቱ ክልሎች ህዝብ በቀጣይም አብሮነታቸው በሚጠናከርበት ላይ በትኩረት እስራለሁ ሲልም አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅትም የፀጥታ አካላት እና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን አካባቢውን ለማረጋጋት እየሰሩ ነው።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በመግለጫው በክልሉም ይሁን በሌላ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች እንዲረጋጉ አሳስቧል።
©fbc
@yenetube @mycase27
የተጠናከረ የአቶ ዳውድ ኢብሳ ለዋልታ ቲቪ የተናገሩት ቅንጫቢ⤵️

📌"ኦነግ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው ከኢትዮዽያ መንግስት ጋር ትጥቁን #ፈቶ #በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ነው ተብሎ የሚነገረው መሰረተ ቢስ ወሬ ነው"

📌"እኛ ትጥቅ እንድንፈታ የተስማማንበት #ስምምነት_የለም። የታጠቀው ኣአካል ትጥቅ ይዞ እያለ እኛ ትጥቅ የምንፈታበት ምክን ያት የለም።"

📌"ትጥቅ መፍታት የሚባል #sensitivity ጥያቄ ነው። ትጥቅ ፈቱ መባልም አንፈልግም። ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጣው አንዱ ትጥቅ የሚፈታ አንዱ ትጥቅ የሚያስፈታ ይመስላል። የሀገሪቱ ሰላም እንዲጠበቅ ኦነግ ያለው ሚና ምን እንደሚሆን ነው የተስማማነው።"

📌አቶ ዳውድ #ሰኔ_16 በጠቅላይ ሚንስትሩ ላይ በተደረገው የግድያ ሙከራ ድርጅታቸው እንዳልተሳተፈ ገልፀዋል። #በቡራዩና_በአዲስ አበባ በተፈጠሩ ግጭቶችም ኦነግ #አለመሳተፉን ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።

📌#በቤኒሻንጉል#በወለጋና #በከፋ በተፈጠሩ ግጭቶች #ኦነግ መሳተፉንና አለመሳተፉን ለማረጋገጥ ማጣራት እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

📌አቶ ዳውድ በበደኖና በአርባ ጉጉ #በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ #በገለልተኛ አካል እንዲጣራ የኦነግ ፍላጎት መሆኑን ገልጸዋል።
@YeneTube @Fikerassefa