YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የተጠናከረ የአቶ ዳውድ ኢብሳ ለዋልታ ቲቪ የተናገሩት ቅንጫቢ⤵️

📌"ኦነግ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው ከኢትዮዽያ መንግስት ጋር ትጥቁን #ፈቶ #በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ነው ተብሎ የሚነገረው መሰረተ ቢስ ወሬ ነው"

📌"እኛ ትጥቅ እንድንፈታ የተስማማንበት #ስምምነት_የለም። የታጠቀው ኣአካል ትጥቅ ይዞ እያለ እኛ ትጥቅ የምንፈታበት ምክን ያት የለም።"

📌"ትጥቅ መፍታት የሚባል #sensitivity ጥያቄ ነው። ትጥቅ ፈቱ መባልም አንፈልግም። ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጣው አንዱ ትጥቅ የሚፈታ አንዱ ትጥቅ የሚያስፈታ ይመስላል። የሀገሪቱ ሰላም እንዲጠበቅ ኦነግ ያለው ሚና ምን እንደሚሆን ነው የተስማማነው።"

📌አቶ ዳውድ #ሰኔ_16 በጠቅላይ ሚንስትሩ ላይ በተደረገው የግድያ ሙከራ ድርጅታቸው እንዳልተሳተፈ ገልፀዋል። #በቡራዩና_በአዲስ አበባ በተፈጠሩ ግጭቶችም ኦነግ #አለመሳተፉን ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።

📌#በቤኒሻንጉል#በወለጋና #በከፋ በተፈጠሩ ግጭቶች #ኦነግ መሳተፉንና አለመሳተፉን ለማረጋገጥ ማጣራት እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

📌አቶ ዳውድ በበደኖና በአርባ ጉጉ #በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ #በገለልተኛ አካል እንዲጣራ የኦነግ ፍላጎት መሆኑን ገልጸዋል።
@YeneTube @Fikerassefa