YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኅብረተሰቡ መጪውን የፀሐይ ግርዶሽ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲመለከት ጥሪ ቀረበ!

ኅብረተሰቡ ሰኔ 14 ቀን 2012 ዓ.ም የሚጠበቀውን የፀሐይ ግርዶሽ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲመለከት ለማድረግ በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች እና በመገናኛ ብዙኃን በኩል መልእክቶች እያስተላለፈ መሆኑን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ጥሪ አቅርቧል።ሶሳይቲው በፌስቡክ ገጹ ባስተላለፈው መልእክት የፀሐይ ግርዶሽ ለማየት ያስችላል፣ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተመስክሮለታል በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዋወቀ የሚገኘው መመልከቻ መነጽር እውቅና እንደሌለው አስታውቋል።የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲም ሆነ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለየትኛውም ዓይነት የግርዶሽ መመልከቻ መነጽር ማረጋገጫ እውቅና አልሰጡም ብሏል።እውቅና ለሚሰጣቸው አካላት ሕጋዊ ማረጋገጫ ደብዳቤ የሚይዙ መሆኑን ኅብረተሰቡ ተገንዝቦ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የሀገር ሽማግሌዎች መማክርት በጋራ በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መካከል « ጥሩ ያልሆነ ግንኙነት» ያሉትን በንግግር እንዲፈታ ለማድረግ ነገ ወደመቀሌ ሊጓዙ ነው። የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የሀገር ሽማግሌዎች መማክርት ከዚህ ቀደምም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሰላም ጉዞ እንቅስቃሴ ያደርጉ እንደነበር ያመለከቱት የጉባኤው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሀጂ…
ወደ መቐለ ነገ በሚጓዘው ቡድን ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ አባ ማቲያስ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር ኢድሪስ እና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ ሱራፌልን ጨምሮ የሰባት የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች እንደሚሳተፉ ተሰምቷል፡፡

ከሃይማኖት መሪዎቹ በተጨማሪ፣ የሀገር ባለውለታ የሆኑ ታዋቂ ሰዎችና የሀገር ሽማግሌዎች በቡድኑ ውስጥ እንደሚሳተፉ ሸገር ኤፍ ኤም ሰምቻለው ብሏል፡፡የቡድኑን የጉዞ ወጪ በተመለከተ፣ ሙሉ ወጪው ጉዳዩ ያገባናል ባሉ ባለሀብቶች እንደተሸፈነ፣ ከዚያም ውስጥ ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሤ የቡድኑን የመጓጓዣ ወጪ እንደሸፈነ ተሰምቷል።

ቡድኑ ነገውኑ ጉዳዩን ጨርሶ ይመለሳል ተብሏል፡፡የሃይማኖት አባቶቹና የሀገር ሽማግሌዎቹ ለተመሳሳይ ተልዕኮ ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የመጓዝ ዕቅድ እንዳለውም ተሰምቷል፡፡ስለ ጉዳዩ ያውቁ እንደሆነ የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አወሉ አብዲ ስለዚህ ጉዳይ ፓርቲያችን የሚያውቀው ነገር የለም ብለዋል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ ስምንት ሚሊየን ማለፉን አንድ የዓለም አቀፍ መረጃ መዘርዝር አመለከተ።

እስካሁን ከኮቪድ 19 ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከአራት ሚሊየን፣ አንድ መቶ ሺህ በላይ ሆንዋል።ኮሮና ባስከተለዉ ሕመም በዓለም ላይ እስካሁን ከ435 ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአሜሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም ከሁለት ሚሊየን በልጦአል ፤ ከ870 ሺህ በላይ ታማሚዎች ደግሞ አገግመዋል። በአሜሪካ እስካሁን በኮቪድ 19 ፤ 118 ሺህ ገደማ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በአፍሪቃም የኮሮና ተኅዋሲ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ246 ሺህ በላይ ሆኗል። 113 ሺህ አፍሪቃውያን ደግሞ ከኮቪድ 19 ሕመም አገግመዋል፤ ከ6500 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa
ሦስት የንግድ ድርጅቶች በአዲስ አበባ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት እና በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ላይ የሁከት ይወገድልኝ ክስ እንደመሠረቱ ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ ከሳሾቹ ከማዘጋጃ ቤት እስከ መስቀል አደባባይ በሚሰራው የልማት ፕሮጀክት ሳቢያ፣ ለበርካታ ዐመታት ለንግድ የሚጠቀሙባቸውን ይዞታዎቻቸውን ባስቸኳይ እንዲለቁ የታዘዙ ንግድ ድርጅቶች ናቸው፡፡

#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ መካከል በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚካሄደው ድርድር ትናንትም ቀጥሎ ውሏል።

የኢፌዴሪ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ድርድሩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፥ በትናንትናው ስብሰባ ሶስቱ ሀገራት በህዳሴ ግድብ ውሃ አሞላል እና ዓመታዊ የስራ ክንውን ጋር በተያያዘ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው መደራደራቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቅዋል።በትናንትናው ውሎ ውይይት የተደረገባቸውም የመጀመሪያ የውሃ አሞላል ሂደት ህግና መመሪያዎች፣ ከድርቅ ጋር የተያያዙ የድርቅ ወቅት አስተዳደር፣ የግድቡ ደህንነት እና የግድቡ አካባቢያዊና ማህበራዊ ተጽዕኖ ጥናት ናቸው።

በግድቡ ዙሪያ ሶስቱ ሀገራት እያደረጉት ያለው ድርድር ዛሬም ቀጥሎ የሚውል ሲሆን፥ በዛሬው ውሎም ግድቡ ውሃ በሚይዝበት ወቅት እና ወደ ስራ ሲገባ ድርቅ ቢያጋጥም ምን አይነት የድርቅ ወቅት አስተዳደር ሊኖር ይገባል በሚለው ላይ ድርድሮች ይካሄዳሉ።የድርቅ ወቅት አስተዳደርን በተመለከተ ኢትዮጵያ ግድቡ ውሃ ይዞ ወደ ስራ በሚገባበት ውቅት ድርቅ ካጋጠመ የሶስቱ ሀገራት የጋራ ኃላፊነት ሊሆን ይገባል የሚል አቋሟን አንፀባርቃለች። በውሃ ሚኒስትሮች ደረጃ የሚካሄደው ድርድር ዛሬም በኢትዮጵያ ሊቀመንበርነት ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን፥ ከዚያ ቀደም ብሎ ግን የህግ ባለሙያዎች ቡድን በህግ ነክ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርግም ተገልጿል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የኮሮናቫይረስ እንዳለባቸው ከተረጋገጡ 16 አሽከርካሪዎች መካከል ስድስቱ መገኘታቸውን ጤና መምሪያው አስታወቀ፡፡

የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸው ወደ ለይቶ ማከሚያ ያልገቡትን አሽከርካሪዎች እና ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የማፈላለጉ ሥራ መቀጠሉን የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ አስታውቋል፡፡በሰሜን ሸዋ ዞን 22 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የዞኑ ጤና መምሪያ ትናንት መግለጹ ይታወሳል፡፡ በ79 ሰዎች ላይ ምርመራ ተደርጎ ነበር 22 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው፡፡ከ79 ተመርማሪዎች 36 አሽርካሪዎች እንደነበሩና ከእነዚህ መካከል 16 የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸውም ዘግበን ነበር፡፡

ቫይረሱ ከተገኘባቸው 22 ሰዎች መካከል 16ቱ አሽከርካሪዎች እየተፈለጉ እንደሚገኙ የዞኑ ጤና መምሪያ ለአብመድ ገልጾ ነበር፡፡ አሁን በደረሰን መረጃ መሠረት ደግሞ ስድስት አሽከርካሪዎች ተገኝተዋል፤ ወደ ለይቶ ማከሚያ ማዕከልም ተወስደዋል፡፡ ሌሎችን አሽከርካሪዎች እና ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የማፈላለጉ ሥራ መቀጠሉንም ጤና መምሪያው አስታውቋል፡፡በአማራ ክልል ትናንት ሰኔ 8/2012 ዓ.ም ይፋ የተደረገ መረጃ እንደሚያሳየው ከ624 የላቦራቶሪ ምርመራ በ33 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡በክልሉ እስከ ትናንት ሰኔ 8/2012 ዓ.ም ድረስ ለ5 ሺህ 590 ሰዎች የናሙና ምርመራ ተደርጎ በ231 ሰዎች ቫይረሱ መገኘቱን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ በክልሉ አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 44 መድረሱን መዘገባችን ይታወቃል፡፡

#AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
ኮሮናን ድል ነስቻለሁ በሚል አውጃ የነበረችው ኒውዚላድ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ አገኘች፡፡

ሀገሪቱ ምንም አይነት የኮሮና ቫይረስ ታማሚ አለመኖሩን ካወጀች ከ24 ቀናት በኋላ 2 አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎችን ማግኘቷን አስታውቃለች፡፡2ቱም የቫይረሱ ተጠቂዎች ከእንግሊዝ ወደ ኒውዚላንድ ያቀኑ ሲሆን የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ለመታደም በልዩ ፍቃድ ወደ ሀገሪቱ የገቡ ናቸው ተብሏል፡፡ባለፈው ሳምንት ኒውዚላንድ አገሪቱ ከቫይረሱ ነፃ የሆነች መሆኗን በመግለፅ ሁሉንም የአገር ውስጥ ገደቦችን አንስታ ነበር ፡፡

ሆኖም ግን ፣ ጥብቅ የድንበር ገደቦች በቦታው መኖራቸውን ቀጥለዋል - ዜጎች እና አስፈላጊ ሠራተኞች ብቻ ተፈቅዶላቸዋል፡፡በኒውዚላንድ የመጡ ሁሉም ሰዎች ኮቪድ -19 ምርመራ ይደረግባቸዋል እናም ለ 14 ቀናት ብቸኛ ወይም ገለልተኛ ሆነው ማለፍ አለባቸው። በሀገሪቱ ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ባለፉት 24 ሰዓት ቫይረሱ ከተገኘባቸው አዲስ 2 ሰዎች ጋር ተደምሮ በአጠቃላይ 1ሺ 506 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡የሟቾች ቁጥርም 22 መሆኑን ቢቢዚ ዘግቧል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሳተላይት በቀን 40 ሺህ ዶላር ግምት ያለው መረጃ አንደምትልክ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡ሳተላይቷ በሚሰጣት ትዕዛዝ መሠረት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ ክትትል በማድረግ መረጃ እንደምታደርስ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬተር ሰሎሞን በላይ (ዶክተር) ለአብመድ ተናግረዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ወደ ትግራይ ያቀናው የሽምግልና ቡድን መቀለ ገባ!

ፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መንግሥት መካከል ያለውን አለመግባባት በሽምግልና መፍትሔ እንዲያገኝ ለማገዝ ዛሬ ወደ መቀለ የተጓዙት የሐይማኖት መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎች መቀለ አሉላ አባ ነገ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደርሰዋል።የሽምግልና ቡድኑ ወደ መቀለ የሚሄድበት ዋና ዓላማ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው አለመግባባት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተካረረ መሄዱ እና ችግሩ እንዲፈታ ደግሞ መቀራረብና መነጋገር አስስፈካጊ በመሆኑ እንደሆነ ተገልጿል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የተባበሩት መንግስታት ደርጅት ሜጀር ጄነራል ከፍያለው አምደተሰማን በአብዬ ለሚገኘውን የመንግስታቱ የፀጥታ ኃይል ሃላፊ አድርጎ ሾመ!

የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሜጀር ጄነራል ከፍያለው አምደተሰማን በአብዬ ለሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ኃይል ዋና ሃላፊ አድርጎ መሾሙን አስታውቀዋል፡፡ሜጀር ጄነራል ከፍያለው በሐምሌ ወር ስራቸውን በሚያጠናቅቁት ሜጀር ጄኔራል መሃሪ ዘውዴ ገብረማሪያም ቦታ መሾማቸውን የገለፁት ዋና ፀሃፊው ሜጀር ጄነራል መሃሪ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እስካሁን ላከናወኑት ውጤታማ አመራራዊ ሚና የመንግስታቱ ድርጅት ምስጋናው ላቅ ያለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ሜጀር ጄነራል ከፍያለው አምደተሰማ ከ30 ዓመት በላይ የኢትዮጵያ ጦር ኃይል ውስጥ ልዩ የወታደራዊ ሙያ ልምድ ያላቸው ሲሆን ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የምክር ቤት አባል ሆነው አገልግለዋል፡፡በቅርብ ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሰራዊት የምህንድስና ክፍል ዋና ሃላፊ ሆነው አገልግለዋል ፡፡

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የቤት እድሳት መርሀግብር በይፋ ተጀመረ!

የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የቤት እድሳት መርሀግብር በይፋ ተጀመረ። ኢንጂነር  ታከለ ኡማ በሚኖሩበት አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ቀነኒ ሁንዴ መኖሪያ ቤት በመገኘት የቤት እድሳት መርሀግብሩን አስጀምረዋል።

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
የኮሮናቫይረስ እንዳለባቸው ተረጋግጦ ሲፈለጉ ከነበሩት አሽከርካሪዎች መካከል 15 መገኘታቸውን ጤና መምሪያው አስታወቀ፡፡

የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸው ወደ ለይቶ ማከሚያ ያልገቡትን አሽከርካሪዎች እና ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የማፈላለጉ ሥራ መቀጠሉን የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ አስታውቋል፡፡በሰሜን ሸዋ ዞን22 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የዞኑ ጤና መምሪያ ትናንት መግለጹ ይታወሳል፡፡ በ79 ሰዎች ላይ ምርመራ ተደርጎ ነበር 22 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው፡፡ ከ79 ተመርማሪዎች 36 አሽርካሪዎች እንደነበሩና ከእነዚህ መካከል 16 የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸውም ይታወቃል፡፡ቫይረሱ ከተገኘባቸው 22 ሰዎች መካከል 16ቱ አሽከርካሪዎች እየተፈለጉ እንደሚገኙ የዞኑ ጤና መምሪያ ገልጾ ነበር፡፡አሁን በደረሰ መረጃ መሠረት ደግሞ 15 አሽከርካሪዎች ተገኝተዋል፤ ከእነዚህ ውስጥ አስራ ሁለቱ ወደ ደብረ ብርሃን ለይቶ ማከሚያ ማዕከል ተወስደዋል፡፡ ሦስቱ ደግሞ አዲስ አበባ ወደ ሚገኝ ለይቶ ማከሚያ ማዕከል እንዲገቡ ሊደረግ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡ አንድ አሽከርካሪ ተንቀሳቃሽ ስልኩ ጥሪ ባለመቀበሉ እስካሁን እንዳልተገኘና ፍለጋው መቀጠሉንም ጤና መምሪያው አስታውቋል፡፡

#AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ3ሺ 6መቶ በላይ የትራፊክ ደንብ ተላላፊ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ፡፡

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ በከተማዋ ባሉት አምስት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ስር ባሉ የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች በተሰሩ የክትትል እና ቁጥጥር ስራዎች በአንድ ሳምንት ጊዜ 3657 የትራፊክ ደንብ ተላላፊ አሽከርካሪዎች ላይ የቅጣት እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡በቅርቡ ኤጀንሲውን የተቀላቀሉ ከአንድ ሺህ በላይ የትራፊክ ቁጥጥር ሰራተኞች በከተማዋ የሚስተዋሉ የትራፊክ ህግ እና ደንብ ጥሰቶች ላይ ተገቢውን ክትትል እና ቁጥጥር እያደረጉ በመሆኑ በመንገድ ትራፊክ ደህንነት እና ፍሰት ላይ አበረታች ውጤቶች እየተመዘገበ እንደሚገኝ ኤጀንሲው ገልጿል፡፡

የትራፊክ ደንብ ተላላፊ አሽከርካሪዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ የሚያመላክተው በከተማዋ በርካታ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግ ጥሰቶችን የሚፈፅሙ መሆኑን ሲሆን ችግሩን ለመቅረፍ ተገቢውን ክትትል እና ቁጥጥር ከማድረግ ባሻገር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በልዩ ትኩረት ይሰራል ተብሏል፡፡ኤጀንሲው ከመንገድ ትራፊክ ክትትል እና ቁጥጥር ባሻገር የመንገድ ደህንነት እና ወቅታዊ የሆነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ላይ ያተኮረ የጎዳና ላይ ቅስቀሳ እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ከከተማዋ ፕሬስ ሴክሬታሪያት የተገኘ መረጃ ያሳያል፡፡

Via AMN
@YeneTube @FikerAssefa
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ስር በሚገኘው የሚሌኒየም ማገገሚያ ማዕከል ውስጥ ከኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ያገገሙ 87 ሰዎች ከማዕከሉ መውጣታቸው ተገለጸ።

የማዕከሉ ክሊኒካል ዳይሬክተር ዶክተር ውለታው ጫኔ እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት በማዕከሉ ውስጥ 656 ኮሮናቫይረስ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ህክምናቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ።ከነዚህ ውስጥ 157 ሰዎች የመጀመሪያ የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤታቸው ከኮሮናቫይረስ ማገገማቸውን (ኔጋቲቭ) ያሳየ መሆኑን ገልጸው፤ 87 ሰዎች ዛሬ ከማዕከሉ እንዲወጡ መደረጉን አመልክተዋል።

#ENA
@YeneTube @FikerAssefa
በኮሮና ቫይረስ መከሰት ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረው የውጭ ሃገራት የአበባ ግብይት እየተሻሻለ በመምጣቱ ምርቱን እየላከ መሆኑን በባህር ዳር የሚገኘው የጣና ፍሎራ አበባ ልማት ድርጅት አስታወቀ።የአበባ ገበያው በመሻሻሉ ምርት ወደ ውጭ እየላክን ነው፣ በግንቦት ወር ብቻ ከ3 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ የአበባ ዘንግ ለውጭ ገበያ አቅርበናል ብለዋል የድርጅቱ ማርኬቲንግ የስራ ክፍል ስራ አስኪያጅ አቶ አብነት በላይነህ።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 109 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።የ1 ሰው ህይወት አልፏል።

ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5102 የላብራቶሪ ምርመራ 109 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ሚንስትር አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ትናንት ተጨማሪ የ1 ሰው ህይወት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ አልፏል፤

የሟች ሁኔታ የ45 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ ስትሆን፣ ቫይረሱ እንደነበረባት የታወቀው በአስከሬን ምርመራ ነው። ይህንንም ተከትሎ አጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች 61 ደርሷል።

በተጨማሪም በትናንትናው ዕለት 118 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ብዛት 738 አድርሶታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 109 ሰዎች ሲሆኑ በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(60) ሴት(49) ናቸው!

➡️ዕድሜያቸው ከ1-78 አመት የሆኑ

➡️ተጨማሪ 118 ሰዎች(115 ከአዲስ አበባ፣ 3 ከትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 738 ነው።

➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(81)፣ ከኦሮሚያ ክልል(9)፣ከአማራ ክልል(3) ፣ ከትግራይ ክልል(3)፣ከደቡብ ክልል(4)፣ ከሀረሪ ክልል(2)፣ ከሶማሌ ክልል(4) እና ከአፋር ክልል(3) በድምር 109 ሰዎች ናቸው።

➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3630 ደርሷል።

➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 32 ነው።

➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 1 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፣ እስካሁን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 61 ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር አክስዮን ማህበር ለመጀመሪያ ግዜ የባቡር ካፒቴኖች አስመረቀ፡፡

የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር አክስዮን ማህበር ላለፉት 6 ወራት በሃገረ ቻይና ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 34 ኢትዮጲያውያን የአዲስ አበባ- ጅቡቲ የኤሌክትሪክ የባቡር ካፒቴኖችን ለመጀመሪያ ግዜ አስመረቀ፡፡የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ተመራቂዎች ወደ ስራ ሲገቡ ህዝባቸውን በታማኝነት እነደሚያገለግሉ እምነታቸው መሆኑን ጠቅሰው የትራንሰፖርት ሚኒሰቴር በዘርፉ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሸግግርን እውን ለማድረግ እየሠራ መሆኑን መግለጻቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#AMN
@YeneTube @FikerAssefa