YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሦስት የንግድ ድርጅቶች በአዲስ አበባ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት እና በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ላይ የሁከት ይወገድልኝ ክስ እንደመሠረቱ ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ ከሳሾቹ ከማዘጋጃ ቤት እስከ መስቀል አደባባይ በሚሰራው የልማት ፕሮጀክት ሳቢያ፣ ለበርካታ ዐመታት ለንግድ የሚጠቀሙባቸውን ይዞታዎቻቸውን ባስቸኳይ እንዲለቁ የታዘዙ ንግድ ድርጅቶች ናቸው፡፡

#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ሐሙስ ወይም ዐርብ በሕዳሴው ግድብ ላይ ይወያያል ተብሎ እንደሚጠበቅ አሕራም ድረገጽ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ የጸጥታው ምክር ቤት ምንጮች ግን ዘገባውን አላረጋገጡም፡፡ አሜሪካ ጸጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ እንዲወያይ ትፈልጋለች፡፡ ተለዋጭ መቀመጫ ያላት ደቡብ አፍሪካ በበኩሏ፣ ጉዳዩ ጊዜ እንዲሰጠው ፍላጎት አላት፡፡ የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሴሪል ራማፎዛ፣ በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ እና ግብጽ መሪዎችን እያነጋገሩ ነው ተብሏል፡፡

#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልላዊ መንግስት በአዲስ ዐለም ባሌማ የሚመራ ልዑክ ወደ አዲስ አበባ እንደላከ ማወቃቸውን በኬንያ የኤርትራ አምባሳደር በየነ ርዕሶም በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡ ልዑኩ የተላከው ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ለመነጋገር እንደሆነም ጠቅሰዋል። ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ መንግሥትም ሆነ ከትግራይ ክልል መንግሥት ስለመረጃው እውነተኛነት የተሰማ ነገር የለም፡፡

#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1
ለሽብርተኞች መረጃ በማቀበል የተጠረጠሩት የሕወሃት አባላት ተወልደ ገ/ጻዲቅ እና ተስፋለም ይኸድጎ ትናንት ለ3ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት እንደቀረቡ የዋዜማ ሪፖርተሮች ከሥፍራው ዘግበዋል፡፡ተስፋለም በሚመሩት የሕግ ጥናት እና ምርምር ማዕከል የሚሰሩ ሁለት ሹፌሮችም አብረው ቀርበዋል፡፡ ፖሊስ በተስፋለም መኖሪያ ቤት ያገኘሁት ክላሽንኮቭ መሳሪያ በፌደራል ፖሊስም ሆነ በአዲስ አበባ ፖሊስ ዕውቅና የለውም- ብሏል ለችሎቱ፡፡ ፖሊስ ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ እና የጀመራቸውን ምርመራዎች ለማጠናቀቅ 14 ተጨማሪ ቀናት ጠይቋል፤ ችሎቱ ብይን ለመስጠጥ ለነገ ቀጥሯል፡፡

#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1
ዐለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይኦኤም 116 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው እንደመለሰ በትዊተር ገጹ አስፍሯል፡፡ ስደተኞቹ በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ በቀላሉ ወደ ሀገራቸው መመለስ ያልቻሉ ናቸው፡፡ ስደተኞቹን ወደ ሀገራቸው ማጓጓዝ የተቻለው፣ አይኦኤም ከአውሮፓ ኅብረት ባገኘው ድጋፍ ነው፡፡

#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1
የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራር ልደቱ አያሌው ጤንነታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ እንደሆነ ፓርቲው በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡

በቢሾፍቱ ከተማ መርማሪያቸው ፖሊስ ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መስማታቸውን ልደቱ ተናግረዋል ተብሏል፡፡ ልደቱ የአስም በሽተኛ ሲሆኑ፣ አምና ደሞ የልብ ቀዶ ሕክምና አድርገዋል፡፡ ይሄ ሁኔታ ይበልጥ ለኮሮና ቫይረስ ያጋልጣቸዋል- ብሏል ፓርቲው፡፡ እናም መንግሥት ወደ አዲስ አበባ እንዲያዛውራቸው፤ ይህ ካልሆነ ግን በታሳሪው ሕይወት ላይ ለሚደርስ አደጋ መንግሥት ተጠያቂ እንደሚሆን ፓርቲው አስጠንቅቋል፡፡

#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከብሮድካስት ባለሥልጣን ማስጠንቀቂያ እንደደረሰው ዋዜማ ዘግቧል፡፡መንግሥታዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ ማስጠንቀቂያ የደረሰው፣ በቅርቡ ያስተላለፋቸው ፕሮግራሞች የስነ ምግባር ጉድለት የታየባቸው፣ የሕግ ጥሰት ያለባቸው እና የብሮድካስት አዋጁን የጣሱ ሆነው በመገኘታቸው ነው፡፡ ጣቢያውን ለማስጠንቀቂያ የዳረጉት፣ በተለይ የድምጻዊ ሐጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ በሠራቸው ፕሮግራሞች እና ባቀረባቸው ቃለ ምልልሶች ነው፡፡

#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1
ብሄራዊ ባንክ ለብድር እና ተቀማጭ ገንዘብ ወለድ የምጣኔ ፖሊሲ ሊያወጣ እንደሆነ ፎርቹን አስነብቧል፡፡ምጣኔው ወቅታዊ የገንዘብ የመግዛት አቅምን መሠረት ያደረገ ይሆናል፡፡ፖሊሲው አሁን ያለውን አሠራር በ3 ዐመታት ውስጥ ይተካል፡፡አዲሱ ፖሊሲ ለቁጥጥር አመች ቢሆንም፣ አስገዳጅ ግን እንደማይሆን ዘገባው ጠቁሟል፡፡ እስካሁን ባለው አሠራር ባንኮች ለቁጠባ የሚሰጡት ዝቅተኛው ወለድ 7 በመቶ ሲሆን፣ የብድር ወለድ ደሞ በባንኮች እንደ ሁኔታው የሚወሰን ነው፡፡

#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1
አማራ ክልል ከትግራይ ክልል ላይ ምንም ሊያነሳ የሚችለው የግዛት ጥያቄ እንደሌለ ባይቶና የተሰኘው የክልሉ ተቃዋሚ ፓርቲ ዛሬ በፈስቡክ ገጹ ባሰራጨው መግለጫ ገልጧል፡፡እንዲያውም በአማራ ክልል ስር ያሉ አንዳንድ የትግራይ ግዛቶችን ለማስመለስ እታገላለሁ- ብሏል ፓርቲው፡፡ፓርቲው አክሎም፣ ትግራይ ዘንድሮ የምታካሂደው ክልላዊ ምርጫ የሕዝበ ውሳኔ አንድምታ ያለው በመሆኑ፣ ማንም ሊያሰናክለው እንደማይችል እና የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ለክልሉ ምክር ቤት የጻፉት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤም ተቀባይነት እንደሌለው አውስቷል፡፡

#Wazema
Photo: VoA
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮ ቴሌኮም ከፊል ሽያጭ ላይ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ ባዘጋጀው ምጥን የፖሊሲ ሃሳብ ላይ ውይይት እንዳዘጋጀ ፓርቲው በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡ በመጭው ቅዳሜ በሚካሄደው ውይይት፣ አንጋፋዎቹ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች በፍቃዱ ደግፌ (/ዶ/ር) እና ዐለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ጥናታዊ ወረቀቶችን ያቀርባሉ፡፡ ፓርቲው በዚሁ ጉዳይ ላይ ያዘጋጀውን ምጥን የፖሊሲ ሃሳብ ቀደም ብሎ ይፋ ያደርጋል፡፡

#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1
ፌደራል ፖሊስ ትናንት ሦስት ጋዜጠኞቹን እንዳሰረበት አሥራት ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡ ታሳሪዎቹ ጋዜጠኞች በላይ ማናየ፣ ሙሉጌታ አንበርብር እና ምስጋናው ከፈለኝ ናቸው፡፡ ከጣቢያው ቀደም ሲል የለቀቀው የካሜራ ባለሙያ ዮናታን ሙሉጌታም እንደታሠረ ዘገባው ጠቅሷል፡፡

#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1
በዋስ ከተለቀቁ በኋላ ይግባኝ ተጠይቆባቸው እስር ቤት ያሉት የሕወሃት አባላት ዛሬ እንደገና ፍርድ ቤት እንደቀረቡ የመንግሥት ዜና አውታሮች ዘግበዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ የሀገር ሚስጢርን ለአሸባሪዎች አሳልፈው ስለመስጠጣቸው ማስረጃ እንዳሰባሰበ ፖሊስ ለችሎቱ በማስረዳት፣ የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡ ችሎቱም በፖሊስ ጥያቄ ላይ ነሐሴ 11 ውሳኔ እሰጣለሁ ብሏል፡፡ እስር ላይ ያሉት ተጠርጣሪዎች፣ አዲስ አበባ የሕወሃት ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ተወልደ ገብረ ጻዲቅ፣ የደኅንነቱ መስሪያ ቤት ባልደረባ አጽብሃ አለማየሁ፣ የሕግ ጥናት እና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ተስፋለም ይኸድጎ እና የማዕከሉ 2 ሹፌሮች ናቸው፡፡

#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1