በአማራ ክልል ኤፍራታና ግድም ወረዳ አጣዬ ከተማ ላይ ባልታወቁ ሰዎች ተፈጥሮ የነበረው ግጭት መረጋጋቱን የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳር አስታወቀ።
የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ተፈራ ወንድምአገኘሁ ዛሬ በሰጠት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት የተፈጠረውን አለመረጋጋት በዘላቂነት ወደ ነበረበት ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ የሚያስችሉ ስራዎች በቅንጅት እየተከናወኑ ነው።
በክልሉ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አዋሳኝ ቦታዎች አካባቢ የተከሰተው ግጭት በጸረ-ሰላም ኃይሎች ምክንያት እንጂ በህዝቦች መካከል የተነሳ እንዳልሆነም አስረድተዋል።
ከአራት ወራት በፊት በነዚህ አካባቢዎች በተመሳሳይ መልኩ በተከሰተ ግጭት የአጣየና አካባቢው ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አውስተዋል።
“ከዛ ጊዜ ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው የአስፓልት መንገድ ግራና ቀኝ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መቀሳቀስ ክልክል መሆኑ በኮማንድ ፖስት ታውጆ ነበር” ብለዋል።
ይሁን እንጂ ሰሞኑን የጦር መሳሪያ የታጠቁ ሁለት ግለሰቦች አጣየ ከተማ ገበያ ሊገቡ ሲሉ በአካባቢው በጥበቃ ላይ በነበሩ የክልሉ ልዩ ሀይል አባላት ሊያዙ ሲሉ ተኩስ በመክፈታቸው ግጭት መፈጠሩን ተናግረዋል።
በእለቱም ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ሀይሎች የአጣየን ከተማ ለመውረርና ግጭቱን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማስፋት ያደረጉት ሙከራ በክልሉ ልዩ ሃይል፣ በፌደራል ፖሊስና በመከላከያ ሰራዊት በተደረገ ጥረት መክሸፉን ገልጸዋል።
ይሔንን ተከትሎ በነበረው የተኩስ ልውውጥም አምስት ሰዎች ሲሞቱ አራት መቁሰላቸውን ገልጸው ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሁለቱም ዞኖች አመራሮች፣ ህዝቡና የሚመለከታቸው አካላት በጋራ እየሰሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
#ENA
@YeneTube @Fikerassefa

“የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የኖቤል የሰላም ሽልማት የአፍሪካውያን ሽልማት ነው” አፍሪካውያን አምባሳደሮች
ተቀማጭነታቸውን ኬንያ ናይሮቢ ያደረጉ የአፍሪካ አምባሳደሮች ዶክተር አብይ አህመድ የኖቤል ሽልማት ማሸነፋቸው ለኢትዮጵያ ለውጥ እና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አመራር የተሰጠ እውቅናና የአፍሪካውያን ሽልማት ነው ብለዋል።
አምባሳደሮቹ ትናንት በኢትዮጵያ ኤምባሲ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይን መሸለም በማስመልከት ባደረጉት ዝግጅት የኖቤል ሽልማቱ ለኢትዮጵያ የሚመጥን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚገባ መሆኑን ገልጸዋል።
ሽልማቱ ሁሉንም የአፍሪካ ሀገራት ያኮራ እና አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው መፍታት መቻላቸውን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
በኬንያ የኤርትራ አምባሳደር እና የአፍሪካ አምባሳደሮች ዲን አምባሳደር በየነ ርእሶም በበኩላቸው ዶ/ር አብይ የሁላችንም ኩራት ናቸው ብለዋል።
አምባሳደር መለሰ አለም ሽልማቱ ለአፍሪካውያን የተሰጠ እንደሆነ ገልጸው አፍሪካውያን ላሳዩት ድጋፍና ወገንተኝነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በመጨረሻም አምባሳደሮቹ ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስትን እንኳን ደስ አላቹ ብለዋል።
Via:- #ENA
@YeneTube @FikerAssefa

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ስር በሚገኘው የሚሌኒየም ማገገሚያ ማዕከል ውስጥ ከኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ያገገሙ 87 ሰዎች ከማዕከሉ መውጣታቸው ተገለጸ።
የማዕከሉ ክሊኒካል ዳይሬክተር ዶክተር ውለታው ጫኔ እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት በማዕከሉ ውስጥ 656 ኮሮናቫይረስ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ህክምናቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ።ከነዚህ ውስጥ 157 ሰዎች የመጀመሪያ የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤታቸው ከኮሮናቫይረስ ማገገማቸውን (ኔጋቲቭ) ያሳየ መሆኑን ገልጸው፤ 87 ሰዎች ዛሬ ከማዕከሉ እንዲወጡ መደረጉን አመልክተዋል።

በህንድ በአንድ ቀን ብቻ 12 ሺህ 881 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ!
በህንድ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 12 ሺህ 881 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።ይህም በአገሪቱ በአንድ ቀን ውስጥ እስካዛሬ ድረስ ከተመዘገበው ከፍተኛው ቁጥር መሆኑን አናዶሉ ኤጀንሲ ዘገቧል።በአለም አቀፍ ደረጃ በአንድ ቀን ውስጥ ከተመዘገበው ቁጥርም በሶስተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በመረጃው ሰፍሯል።ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የ334 ሰዎች ህይወት በማለፉ የሟቾች ቁጥር 12 ሺህ 237 መድረሱም ተገልጿል።በአገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 366 ሺህ 946 የደረሰ ሲሆን 194 ሺህ 324 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን መረጃው አስታውሷል። እስካሁን በዓለም ከ 8 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን 451 ሺህ 463 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።

ኬኒያ የፀጥታው ምክር ቤት መቀመጫን አሸነፈች!
ኬኒያ ጂቡቲን በድምፅ ብልጫ አሸንፋ አፍሪካን በመወከል የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት የተለዋጭ አባልነት ማግኘቷ ተዘገበ።የምሥራቅ አፍሪካወዊቷ ሀገር ኬኒያ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ያልሆነ መቀመጫ የነበራትን ደቡብ አፍሪካን ትተካለለች።ኬኒያ 129 ድምፅ ያገኘች ሲሆን የጅቡቲ ደግሞ 62 ነው። ኒጀርና ቱኒዚያ ሌሎች የአፍሪካ አህጉር ተወካዮች ናቸው ሲል ቢቢሰ ዘግቧል ፡፡የኬኒያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ሀገራቸው ማሸነፏንም ተከትሎ እንደተናገሩት ሀገሪቷ እያደገችና በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በልማት አጋርነቷ እየፈጠረች ያለውን እመርታ የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱም አያይዘው ጅቡቲንም በጥሩ ተፎካካሪነቷ አመስግነው የአፍሪካ ኅብረትም ድጋፍ ስለቸራቸው አመስግነዋል።ጅቡቲና ኬኒያ በአንደኛው ዙር ምርጫ ሁለት ሦስተኛውን (128 ድምጾች) አላገኙም ነበር ፡፡ፕሬዚዳንት ኡሁሩ እንዳሉት አፍሪካ እንደ አህጉር በፀጥታው ምክር ቤት ያላትን ተሰሚነት መጨመሩን ገልጸው ፤ለጉባኤው ምርጫ ሲንቀሳቀሱበት የነበረውን ባለ አሥር ነጥብ አጀንዳም እንደሚያስተዋውቁ መናገራቸውን መረጃው አስታውሷል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ የሚተኛበት ስፍራ ደን ምንጣሮ ስራ ትናንት ተጀመረ፡፡
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የስራ እድል ፈጠራና ኡንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ በሽር አብዱራሂም እንደገለፁት ክልሉ በኢንተርፕራይዞች አማካኝነት የሚመነጠር 1 ሺህ ሔክታር መሬት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ተረክቦ ትናንት የምንጣሮ ስራው እንዲጀመር አድርጓል።ግድቡ በመጪው ሐምሌ ውሃ ለመሙላት የተያዘውን እቅድ እንዲሳካ ከወዲሁ የደን ምንጣሮ ስራውን ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ 2ሺህ አባላት የያዙ ኢንተርፕራይዞች ወደ ስራው ገብተዋል። ኤጀንሲው የምንጣሮ ስራውን በፍጥነትና በጥራት እንዲከናወን የቅርብ ክትትል ያደርጋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የጤና፣ የጸጥታ እና ሌሎችም ቡድኖች ምንጣሮውን ከሚያካሂዱ ኢንተርፕራይዞች ጋር አብረው ወደ ስፍራው ገብተዋል ብለዋል፡፡ለስራው የሚያስፈልግ በጀት እና ሌሎች ግብአቶች ለኢንተርፕራይዞቹ መቅረቡን አቶ በሽር ተናግረዋል።አጠቃላይ ለምንጣሮ ስራው 32 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት እንደተያዘለትም ከዋና ዳሬክተሩ ገለጻ ለማወቅ ተችሏል፡፡በደን ምንጣሮ ስራው መሳተፍ የጀመሩ ኢንተርፕራይዞች በበኩላቸው ስራውን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቅቀው ለማስረከብ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በአማራ ክልል ውስጥ የሽብር ተግባር ለመፈጸም ተልእኮ ተቀብለው ወደ ክልሉ ሰርገው የገቡ 85 "የጥፋት ሃይሎች" በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁ፡፡
ርእሰ መስተዳድሩ በማእከላዊና በሰሜን ጎንደር ዞኖች የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን ትናንት በመረቁበት ወቅት እንደተናገሩት የጥፋት ሃይሎቹ የክልሉን ሰላም በማደፍረስ ክልሉን የግጭት ቀጠና ለማድረግ ተልእኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው፡፡እነዚህ ጸረ-ሰላም ሃይሎች በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ሰርገው የገቡት ጸበልተኛ፣ መነኩሴና የአዕምሮ ህሙማን በመምሰል እንደሆነ የጠቆሙት ርእሰ መስተዳድሩ እኩይ አላማቸውን ሳያሳኩ በህብረተሰቡ ትብብርና ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡የጥፋት ተልእኮ በመቀበል ወደ ክልሉ ገብተው የነበሩት እነዚህ ጸጉረ ልውጥ ግለሰቦች ታዋቂ ሰዎችንና ከፍተኛ አመራሮችን የመግደል፤ በሃይማኖት ተቋማትና በታሪካዊ ቅርሶች ላይ ጉዳት ለማድረስ እቅድ ይዘው የገቡ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
#ENA
@YeneTube @FikerAssefa1

በኢትዮጵያ በመኸር እርሻ 7 ነጥብ 75 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በሰብል መሸፈኑን ግብርና ሚኒስቴር ገለጸ!
በዚህ ዓመት በመኸር እርሻ 12 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለማረስ የታቀደ ሲሆን ከዚህ ውስጥ እስከ አሁን 7 ነጥብ 75 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ታርሶ በተለያዩ ሰብሎች መሸፈኑን የግብርና ሚኒስቴር ገልጿል።
#ENA
@YeneTube @FikerAssefa
በዚህ ዓመት በመኸር እርሻ 12 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለማረስ የታቀደ ሲሆን ከዚህ ውስጥ እስከ አሁን 7 ነጥብ 75 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ታርሶ በተለያዩ ሰብሎች መሸፈኑን የግብርና ሚኒስቴር ገልጿል።
#ENA
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የትራፊክ አደጋን በ17 በመቶ መቀነሱን የትራንስፖርት ሚኒስቴር ገለፀ!
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የትራፊክ አደጋን በ17 በመቶ መቀነሱን የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ገለጹ።አዲስ አበባ- አዳማ የፍጥነት መንገድ መግቢያ ላይ “የትራፊክ አደጋ ሰለባዎችን እያሰብን አረንጓዴ አሻራችንን እናኑር!” በሚል መሪ ቃል ደም የመለገስ የአረንጓዴ አሻራ ማኖር መርሐ ግብር ተከናውኗል።በመርሐ ግብሩ የትራፊክ አደጋ የደረሰባቸው ሰዎችና የተጎጂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት በ2011 በጀት ዓመት የተመዘገበው 4ሺህ 597 ሞት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ወደ 3ሺህ 400 ቀንሷል ብለዋል።

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ለ2013 ዕቅድ ማስፈጸሚያ 3 ነጥብ 377 ቢሊዮን ብር በጀትና የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ!
በክልሉ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ውጤታማ በማድረግ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላት ጠንክረው እንዲሰሩም የምክር ቤቱ አፈጉባኤ አቶ ላክደር ላክባክ ጠይቀዋል።ጉባኤው በሁለት ቀናት ቆይታው በክልሉ የ2012 የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንዲሁም የጠቅላይ ፍርድ ቤትና የኦዲት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ አጽድቋል።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እናቶችን ልጆቻቸውን ጡት ከማጥባት እንደማያግዳቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
28ኛው ዓለም ዓቀፍ ጡት የማጥባት ቀን ከሐምሌ 25 እስከ ነሐሴ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ”ለአገር ጤና ጡት ማጥባትን እንደግፍ” በሚል መሪ ሃሳብ ይከበራል።በጉዳዩ ላይ ለጋዜጠኞች የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ያዘጋጀው የጤና ሚኒስቴር በዓሉ በኢትዮጵያ ለ12ኛ ጊዜ እንደሚከበር አስታውቋል።የሚኒስቴሩ የእናቶችና ሕፃናት ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት ዘላለም አንዳንድ እናቶች በኮሮና ቫይረስ ስጋት ሳቢያ ለልጆቻቸው የቆርቆሮ ወተት እያጠጡ መሆኑን ተናግረዋል።ነገር ግን እስካሁን ድረስ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት እናቶች ልጆቻቸውን እንዳያጠቡ የሚል ጥናት አልተካሔደም ነው ያሉት።በመሆኑም እናቶች ከጤና ባለሙያዎች የሚሰጡ ምክሮችን በአግባቡ በመተግበር ልጆቻቸውን ያለተጨማሪ ምግብ ለስድስት ወራት ጡት ማጥባት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

በአፋር ክልል የአዋሽ ወንዝ በመሙላቱ 32ሺህ ሰዎች ተፈናቀሉ!
በአፋር ክልል የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ በተለያዩ ወረዳዎች 32 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸዉን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋሰትና ማስተባባሪያ ጽህፈት ቤት ገለፀ።በአፋር ክልል ክረምቱን ተከትሎ እየጣለ ባለው ዝናብ የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ በ6 ወረዳዎች 32 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን በፅህፈት ቤቱ የቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ዳይሬክተር አቶ አይዳሂስ ያሲን ገልፀዋል።ዳይሬክተሩ እንዳሉት በክልሉ በአዋሽ ወንዝ ዳርቻ የሚገኙ 7 ወረዳዎች ከፍተኛ የጎርፍ ስጋት ተጋላጭ ናቸው።ይህን ችግር ለመቅረፍ የአዋሽ ተፋሰስ ባለስልጣን ከሚመለከታቸው የፌዴራልና የክልሉ መንግስት አካላት ጋር በመቀናጀት የጎርፍ መከላከል ስራዎች ሲያከናውን ቢቆይም የዘንድሮው ክረምት ጠንከር ያለ በመሆኑ በ6 ወረዳዎች የጎርፍ አደጋ አጋጥሟል።
ጎርፉን ተከትሎ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም 32 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውንና ግምቱ በመጣራት ላይ የሚገኝ ሰብልና እንስሳት ላይ ጉዳት ማድረሱን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።እስከ አሁን ድረስ በአይሳኢታ ወረዳ በጎርጉም ሁለት ቀበሌዎች ለሚገኙ ከ1 ሺህ100 በላይ ሰዎች የፌዴራል መንግስት በሄሊኮፕተር ምግብ የማቅረብ ስራዎች በማከናወን ላይ ነው።ከተፈናቃዮች መካከል 17 ሺህ 450 ሰዎች በአይሳኢታ ወረዳ የ5 ቀበሌ ነዋሪዎች ናቸው።በተለይም ካለፈው እሁድ ጀምሮ በወረዳው ኮሎዱራና ገለአሊ ቀበሌዎች የአዋሽ ወንዝ ሰብሮ ወደ ቀበሌዎቹ በመግባጋቱ 1ሺህ 126 ሰዎች በውሃ ተከበው ይገኛሉ ብለዋል።
ለጊዜው ክልሉ የምግብና ምግብ-ነክ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ በማድረግ የህይወት አድን እርዳታ ለማቅረብ እየሞከረ ቢሆንም ከችግሩ ስፋትና አሳሳቢነት አንፃር የፌዴራል መንግስት እገዛ መጠየቁን አቶ አይዳሂስ ተናግረዋል።በመሆኑም ከሰላም ሚኒስቴርና ከሚመለከታቸው የፌዴራል አካላት ጋር በመተባባር ከዛሬ ጀምሮ በሄሊኮፕተር አስቸኳይ የምግብ አቅርቦት ስራዎችን ለማከናወን ዝግጅት መደረጉን አስረድተዋል።በውሃ የተከበቡት ሰዎች በሔሊኮፕተርና በሞተር ጀልባ በማውጣት ወደ ሌላ አካባቢዎች ለማስፈር የሚያስችል ዝግጅት መደረጉንም ከዳይሬክተሩ ገለፃ ለማወቅ ተችሏል።በአፋር ክልል በታችኛውና መካከለኛው አዋሽ 63 ሺህ ሰዎች የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ሲሆኑ 44 ሺህ ሰዎች በመፈናቀል ስጋት ላይ የሚገኙ ናቸው ተብሏል።