በኢትዮጵያ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ከመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ጋር ሲነፃፀር በ10 እጥፍ መጨመሩ ተገለጸ፡፡
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ታማሚ ከተገኘ ዛሬ ሶስተኛ ወሩን ማስቆጠሩን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል። በመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ብዛት 250 የነበረ ሲሆን ባለፈው አንድ ወር ብቻ 2420 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተገልጿል። ይህም ማለት ባለፈው አንድ ወር ውስጥ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ከመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ጋር ሲነፃፀር በ10 እጥፍ ጨምሯል።
በመሆኑም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የወረርሽኙ መስፋፋት ግምት ወስጥ በማስገባት ከመቼውም ጊዜ በላይ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል፡፡“መከላከል ከመታከም ይበልጣል፣ ቤት መቆየት ሆስፒታል ከመተኛት ይሻላል፣ የአፍና የአፍንጫን መሸፈኛ አድርጎ መተንፈስ በማሽን ከመተንፈስ ይልቃል። ስለሆነም እነዚህን አንዲሁም ሌሎችን የመከላከያ መንገዶች ሳንዘናጋ በመተግበር እራሳችንን እና የምንወዳቸውን ከኮሮና ቫይረስ በሽታ እንጠብቅ።” በማለት ኢንስቲትዩቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡
#AMN
@YeneTube @FikerAssefa

የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር አክስዮን ማህበር ለመጀመሪያ ግዜ የባቡር ካፒቴኖች አስመረቀ፡፡
የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር አክስዮን ማህበር ላለፉት 6 ወራት በሃገረ ቻይና ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 34 ኢትዮጲያውያን የአዲስ አበባ- ጅቡቲ የኤሌክትሪክ የባቡር ካፒቴኖችን ለመጀመሪያ ግዜ አስመረቀ፡፡የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ተመራቂዎች ወደ ስራ ሲገቡ ህዝባቸውን በታማኝነት እነደሚያገለግሉ እምነታቸው መሆኑን ጠቅሰው የትራንሰፖርት ሚኒሰቴር በዘርፉ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሸግግርን እውን ለማድረግ እየሠራ መሆኑን መግለጻቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ስምንት (2658) ደርሷል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ አንድ (81) ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን በከተማዋ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ስምንት (2658) ደርሷል፡፡በአዲስ አበባ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በአስክሬን ምርመራ አንድ (1) ሰው የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት አንድ መቶ አስራ አምስት (115) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ ማገገማቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት በአዲስ አበባ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፤-
👉አዲስ ከተማ 40
👉ቦሌ 8
👉ጉለሌ 3
👉ልደታ 1
👉ኮልፌ ቀራንዮ 11
👉ቂርቆስ 0
👉አራዳ 4
👉የካ 2
👉ንፋስ ስልክ ላፍቶ 3
👉አቃቂ ቃሊቲ 0
👉አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ 9

በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 85 ሰዎች ቫይረሱ ተገኘባቸው፡፡
በከተማዋ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2743 ደርሷል፡፡በአዲስ አበባ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በህክምና ማዕከል ህክምና ሲከታተሉ የነበሩ 1 ሰው ህይወታቸው አልፏል፡፡በሌላ በኩል በትላንትናው እለት 109 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ አገግመዋል፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት በአዲስ አበባ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፤-
👉አዲስ ከተማ 18
👉ቦሌ 7
👉ጉለሌ 6
👉ልደታ 6
👉ኮልፌ ቀራንዮ 9
👉ቂርቆስ 3
👉አራዳ 12
👉የካ 4
👉ንፋስ ስልክ ላፍቶ 6
👉አቃቂ ቃሊቲ 9
👉አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ 5

ባለፉት ተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ ብቻ ግምታዊ ዋጋቸው ከ16 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ንግድ ማጭበርበር በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል የተለያዩ ዓይነት አዳዲስና አሮጌ አልባሳት፣ የአዋቂና የህፃናት ጫማዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ተሽከርካሪዎች፣ የተሸከርካሪ ጎማና መለዋወጫ (ስፔር ፓርት)፣ የምግብ ዘይት፣ ጫት፣ ሃሺሽ እና ልዩ ልዩ ዓይነት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች እንዲሁም በቦሌ፣ በሞጆ እና በአንዳንድ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ በተደረገው ከፍተኛ 120,000 ሀሰተኛ ዶላርም በሞያሌ ቅርንጫፍ መያዙ ተገልጿል።ህብረተሰቡ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ የሃገሪቱን እድገት የሚያቀጭጭ መሆኑን በመገንዘብ ጥቆማ በመስጠት ከጎኑ እንዲሆኑ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።

በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 144 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን በከተማዋ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2887 ደርሷል፡፡በአዲስ አበባ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በህክምና ማዕከል ህክምና ሲከታተሉ የነበሩ ሁለት (2) ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የከተማዋ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት ሰባ ሶስት (73) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ አገግመዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፤-
👉አዲስ ከተማ 18
👉ቦሌ 11
👉ጉለሌ 13
👉ልደታ 10
👉ኮልፌ ቀራንዮ 5
👉ቂርቆስ 7
👉አራዳ 10
👉የካ 9
👉ንፋስ ስልክ ላፍቶ 7
👉አቃቂ ቃሊቲ 54
#AMN
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፤-
👉አዲስ ከተማ 18
👉ቦሌ 11
👉ጉለሌ 13
👉ልደታ 10
👉ኮልፌ ቀራንዮ 5
👉ቂርቆስ 7
👉አራዳ 10
👉የካ 9
👉ንፋስ ስልክ ላፍቶ 7
👉አቃቂ ቃሊቲ 54
#AMN
@YeneTube @FikerAssefa
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በክ/ከተማው ለሚገኙ አርሶ አደሮች 1 ሺህ 85 ኩንታል ማዳበርያ ድጋፍ አደረገ፡፡
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በክ/ከተማው ለሚገኙ አቅም ለሌላቸው አርሶ አደሮች 1 ሺህ 85 ኩንታል ማዳበርያ ድጋፍ አድርጓል፡፡የከተማ አስተዳደሩ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ አንድም መሬት ጾም ማደር የለበትም በሚል ሁሉንም መሬቶች በዘር ለመሸፈን እየተሰራ እንደሆነ መግለጹ ይታወሳል፡፡በዚህም አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በክ/ከተማው ለሚገኙ የመግዛት አቅም ለሌላቸው 450 አርሶ አደሮች 1 ሺህ 85 ኩንታል ማዳበርያ ድጋፍ አድርጓል፡፡በተጨማሪም ክፍለ ከተማው 233 ኩንታል የጤፍ፤የስንዴ፤የሽንብራ፤የምስር እና የጤፍ ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሮቹ ድጋፍ አድርጓል፡፡ለአርሶ አደሮቹ ከተደረገው ድጋፍ በተጨማሪ በክ/ከተማው በግብርና ለተደራጁ 1ሺህ 500 ወጣቶችም የአትክልት ምርጥ ዘር ድጋፍ ተደርጓል፡፡በክፍለ ከተማው በተያዘው የክረምት ወር 2 ሺህ 300 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 101 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2988 ደርሷል፡፡
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በከተማዋ የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል።በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት 88 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ ማገገማቸውን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፤-
👉አዲስ ከተማ 17
👉ቦሌ 3
👉ጉለሌ 21
👉ልደታ 28
👉ኮልፌ ቀራንዮ 7
👉ቂርቆስ 6
👉አራዳ 0
👉የካ 2
👉ንፋስ ስልክ ላፍቶ 14
👉አቃቂ ቃሊቲ 1
👉አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ 2

የተሽከርካሪዎች የፍጥነት መገደቢያ መሣሪያ ከመጪው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገለጸ!
የተሽከርካሪዎች የፍጥነት መገደቢያ መሣሪያ ከመጪው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ356 ሰዎች በላይ በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ሲያልፍ ከ1,200 ደግሞ ለከባድ የአካል ጉዳት መዳረጋቸውን ገልጿል፡፡በመረጃ መሠረት ከአደጋዎቹ መንስኤዎች መካከል የከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው ደግሞ ከተፈቀደው ፍጥነት በላይ ማሽከርከር መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲም ለመንገድ ደህንነት፣ ለትራፊክ አደጋ እና ለትራንስፖርት ፍሰቱ ማነቆ የሆኑትን ችግሮችን በመለየትና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
በከተማዋ የትራፊክ አደጋን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል የተባለው የተሽከርካሪዎች የፍጥነት መገደቢያ መሣሪያ ከመጪው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡በአዲስ አበባ አስተዳደር ሥር የሚገኙ የአንበሳ ከተማ አውቶብስ እና የሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት እንዲሁም የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ተሽከርካሪዎች የፍጥነት መገደቢያ መሣሪያው ገጥመው ያጠናቀቁ ሲሆን፣ ሌሎች መንግስታዊ ተቋማትም በማስገጠም ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡በቀጣይም የአሰራር ሥርዓት መመሪያን በማዘጋጀትና የአፈጻጸም ሲስተሞችን በመዘርጋት የንግድ ትራንስፖርት እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል፡፡

የጀነራል ሰዓረ መኮንን 1ኛ ዓመት ዝክረ ሰማዕታት ፕሮግራም አምና ከመስዋዕትነቱ በፊት ችግኝ በተከሉበት ቦታ ተካሄደ፡፡
የጀነራል ሰዓረ መኮንን 1ኛ ዓመት ዝክረ ሰማዕታት ፕሮግራም አምና ከመስዋዕትነቱ በፊት በዛው እለት ከአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር ችግኝ በተከሉበት ቦታ ተካሄዷል፡፡በስነስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች፤የአዲስ አበባ ከንቲባ ም/ኢንጂነር ታከለ ኡማ ፤የአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ፤የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ እንዲሁም የጀነራሉ ቤተሰቦችና የስራ ባልደረቦቻቸው ተገኝተዋል።

YeneTube
የጀነራል ሰዓረ መኮንን 1ኛ ዓመት ዝክረ ሰማዕታት ፕሮግራም አምና ከመስዋዕትነቱ በፊት ችግኝ በተከሉበት ቦታ ተካሄደ፡፡ የጀነራል ሰዓረ መኮንን 1ኛ ዓመት ዝክረ ሰማዕታት ፕሮግራም አምና ከመስዋዕትነቱ በፊት በዛው እለት ከአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር ችግኝ በተከሉበት ቦታ ተካሄዷል፡፡በስነስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች፤የአዲስ አበባ ከንቲባ ም/ኢንጂነር ታከለ ኡማ ፤የአዲስ…
በተያያዘ ዜና ከሩዋንዳ ድልድይ እስከ አትላስ ያለው ጎዳና በጀነራል ሰዓረ መኮንን ስም ተሰየሟል፡፡በስነስርዓቱ ላይ ከሩዋንዳ ድልድይ እስከ አትላስ ያለው ጎዳና በጀነራል ሰዓረ መኮንን ስም መሰየሙ ተገልጿል፡፡በቀጣይም በጀነራሉ ስም ሃውልት እንደሚቆምላቸው እና በስማቸውም ፓርክ እንደሚሰራ የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡
#AMN
@YeneTube @FikerAssefa
#AMN
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ዘጠና ስምንት (98) ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን በከተማችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ሶስት (3203) ደርሷል፡፡ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በአዲስ አበባ ከተማ በተደረጉ የአስከሬን ምርመራዎች አንድ (1) ሰው ቫየረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት ሰባ ዘጠኝ (79) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ ማገገማቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡
አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፤-
👉አዲስ ከተማ 22
👉ቦሌ 20
👉ጉለሌ 4
👉ልደታ 3
👉ኮልፌ ቀራንዮ 4
👉ቂርቆስ 9
👉አራዳ 0
👉የካ 14
👉ንፋስ ስልክ ላፍቶ 21
👉አቃቂ ቃሊቲ 1
#AMN
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፤-
👉አዲስ ከተማ 22
👉ቦሌ 20
👉ጉለሌ 4
👉ልደታ 3
👉ኮልፌ ቀራንዮ 4
👉ቂርቆስ 9
👉አራዳ 0
👉የካ 14
👉ንፋስ ስልክ ላፍቶ 21
👉አቃቂ ቃሊቲ 1
#AMN
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ለጊዜያዊ የኮሮና ህሙማን ማገገሚያ ማእከልነት መዘጋጀቱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ለጊዜያዊ የኮሮና ህሙማን ማገገሚያ ማእከልነት መዘጋጀቱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።ስፖርት አካዳሚው 300 ቀላል ምልክት የሚያሳዩና ምንም ምልክት የሌላቸው ነገር ግን በቤታቸው ለመቆየት አመቺ ሁኔታ የሌላቸውን ታካሚዎች ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡ይህንን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲሳካ ላደረጉት የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ቡድንም ዶክተር ሊያ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 160 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡
ከነዚህም ውስጥ 55 ሰዎች አድራሻቸው አዲስ አበባ ሲሆን የቀሩት 105 ሰዎች ደግሞ በአዲስ አበባ በሚገኙ አስገድዶ ማቆያ ውስጥ ከሚገኙ የስደት ተመልሾች መሆኑን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡በሌላ በኩል በትላንትናው እለት 81 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ ማገገማቸው ተገልጿል፡፡
አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፤-
👉አዲስ ከተማ 15
👉ቦሌ 5
👉ጉለሌ 19
👉ልደታ 0
👉ኮልፌ ቀራንዮ 2
👉ቂርቆስ 6
👉አራዳ 0
👉የካ 2
👉ንፋስ ስልክ ላፍቶ 3
👉አቃቂ ቃሊቲ 2
👉አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ 1

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ እያደረጉ ያሉ የግል የጤና ተቋማት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰበ፡፡
ኢንስቲትዩቱ አንዳንድ የግል ጤና ተቋማት የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ እያደረጉ እንደሆነ ጥቆማ እንደደረሰው አስታውቋል፡፡ሆኖም በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ምርመራ ማድረግ የሚቻለው በrRT-PCR Machine ብቻ እና ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፍቃድ ሲገኝ መሆኑን ገልጾ ከዚህ ውጭ ሲሰራ የተገኘ የግል ጤና ተቋም አስፈላጊው ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድበት አሳስቧል፡፡የሚመለከታቸውም አካላት የክትትልና ቁጥጥር ስራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ኢንስቲትዩቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 13,497 ደርሷል፡፡
በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ ከተደረጉ 3,836 የላብራቶሪ ምርመራዎች 386 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ድረስ ከተደረጉ 265,747 የላቦራቶሪ ምርመራዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 13,497 መድረሱን የጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡በሌላ በኩል በ24 ሰዓታት ውስጥ የ ሃያ ሶስት (21 ከሬሳ ምርመራ፣2 ከጤና ተቋም) ሰዎች ህይወት በኮሮና ምክንያት አልፏል፡፡
#AMN
@YeneTube @FikerAssefa1

ከ46 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
ባለፉት አሥራ አንድ ቀናት ከ46 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ከሀገር ለማስወጣት እና ወደ ሀገር ለማስገባት ሲሞከር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ስማርት ስልኮች፣ የብር ጌጣጌጥ ፣ ካናቢስ ተብሎ የሚጠራ አደንዛዥ ፤ ልባሽ ጨርቆች ፣ሺሻ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የምግብ ዘይት፣ ሲጋራ፣ መድኃኒት የተያዙ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መሆናቸውን ሚኒስቴር መ/ቤቱ አስታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 13,826 ደረሰ፡፡
በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረጉ 4,516 የላብራቶሪ ምርመራዎች 329 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ድረስ በተደረጉ 270,263 የላቦራቶሪ ምርመራዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 13,826 ደርሷል፡፡በተጨማሪም በ24 ሰዓታት ውስጥ የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል።
#AMN
@YeneTube @FikerAssefa1
በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረጉ 4,516 የላብራቶሪ ምርመራዎች 329 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ድረስ በተደረጉ 270,263 የላቦራቶሪ ምርመራዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 13,826 ደርሷል፡፡በተጨማሪም በ24 ሰዓታት ውስጥ የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል።
#AMN
@YeneTube @FikerAssefa1
የጊቤ 3 የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግድብ እየሞላ በመምጣቱ ውሃ በየደረጃው ለመልቀቅ የሚያስችል የሙከራ ስራ መከናወኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታውቋል፡፡
ከግድቡ የሚለቀቀው ዉሃ ወደፊት በታችኛው ተፋስስ ላይ ጎርፍ እንዳይከሰት ለመቆጣጠር እና ውሃውን በተመጠነ መልኩ በመልቀቅ በክረምቱ መጨረሻ ላይ ግድቡ ሙሉ እንዲሆን ለማድረግ በማስፈለጉ እንደሆነ የጣቢያው ስራ አስኪያጅ አቶ ሃብታሙ ሰሙ ገልፀዋል፡፡ውሃ ከግድቡ በየደረጃው እንዲለቀቅ መደረጉ በተፋሰሱ ውስጥ የጎርፍ መቆጣጠር ስራ ለማከናወን እንደሚያግዝም ጠቁመዋል፡፡ግድብ የመጣውን ጎርፍ ሁሉ እንደመጣ ላለመልቀቅና የተመጠነ የውሃ ፍሰት እንዲኖር ለማድረግም በየጊዜው እየተቆጣጠሩ መልቀቅ ክረምቱ ሲጠነክር ሊከሰት የሚችለውን ጎርፍ ለመቆጣጠር እንደሚያግዝ አስረድተዋል፡፡
እንደ አቶ ሃብታሙ ገለፃ ግድቡ መያዝ ከሚችለው 15 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ ውስጥ 12 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ የያዘ ሲሆን በሴኮንድ በአማካኝ 800 ሜትር ኪዩብ ውሃ ለመልቀቅ እቅድ ተይዟል፡፡ግድቡ ባለፈው ዓመት ህዳር ወር ከባህር ጠለል በላይ 882 ሜትር ላይ በመድረስ ከፍተኛ ውሃ መያዝ የቻለ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ከዚህ መጠን ጋር ተመሳሳይ ውሃ መያዙን ተናግረዋል፡፡ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከሦስት ወር አስቀድሞ ከባህር ጠለል በላይ 892 ሜትር ላይ በመድረስ ሊሞላ እንደሚችል ያመለክታል፡፡ውሃው ከአሁኑ ካልተለቀቀ ነሐሴ 4 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ሙሉ በሙሉ ሊሞላ እንደሚችልም ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡

የጎረቤቷን የኤቲኤም ካርድ በመስረቅ ከ580 ሺህ ብር በላይ ወጪ አድርጋ ለግል ጥቅሟ ያዋለችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች::
በየካ ክፍለ ከተማ የጎረቤቷን የኤቲኤም ካርድ በመስረቅ ከ580 ሺህ ብር በላይ ወጪ አድርጋ ለግል ጥቅሟ ያዋለች ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ገለፀ፡፡የግል ተበዳይ ወ/ሮ ሰናይ ቦጋለ እና ወንጀሉን ፈፅማለች የተባለችው ግለሰብ የቅርብ ግንኙነት እና ጉርብትና አላቸው፡፡በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮተቤ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል መርማሪ ረዳት ሳጅን እስጢፋኖስ ገ/ታቲዎስ እንደገለፁት ተጠርጣሪዋ ከግል ተበዳይ ጋር ያላትን ቅርበት ተጠቅማ ወደ ወ/ሮ ሰናይ ቦጋለ መኝታ ክፍል በመግባት ቁም ሳጥን ውስጥ ተቀምጦ የነበረ የዘመን ባንክ ኤቲኤም ካርድ ከነ ሚስጥር ቁጥሩ ሰርቃ በመውሰድ እና በተለያዩ ጊዜያት ከ5መቶ 80 ሺ ብር በላይ ከባንኩ ወጪ በማድረግ ለግል ጥቅሟ አውላች፡፡
የግል ተበዳይ ከሀገር ውጭ የሚኖሩ መሆናቸውን የገለፁት ተወካያቸው አቶ ወርቁ ለገሰ ወይዘሮ ሰናይ ቦጋለ የኤቲኤም ካርዱን ከባንኩ ከወሰዱበት ጊዜ ጀምሮ ተጠቅመውበት እንደማያውቁ እና ባላወቁት ሁኔታ ገንዘቡ ከባንክ ወጪ መደረጉን ባወቁ ጊዜ ለፖሊስ ማመልከታቸውን ተናግረዋል።ፖሊስ ከባንኩ ባገኘው መረጃ መሰረት በተጠርጣሪዋ ላይ ክትትል በማድረግ በየካ ክፍለ ከተማ ክልል ውስጥ በቁጥጥር ስር እንዳዋላት እና በአሁኑ ወቅትም ምርመራ እየተጣራባት እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡