YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
"ሙሶሎኒ በኢትዮጵያ የመርዝ ጋዝ አልተጠቀመም" ያለው ጋዜጠኛ ሐውልት እንዲፈርስ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ!

ኤርትራዊቷን በባርነት ገዝቶ የኖረው እና "ሙሶሎኒ በኢትዮጵያ የመርዝ ጋዝ አልተጠቀመም" ያለው ጋዜጠኛ ሐውልት እንዲፈርስ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ።ኢንድሮ ሞንታኔሊ ጣሊያናዊ ጋዜጠኛ ነበር። የዚህ ሰው ችግር ቅኝ ግዛት እጅግ አስፈላጊም ተገቢም ነበር ብሎ ማመኑ ነው።ሰሞኑን በዚህ ሰውዬ ላይ ቂም የያዙ ሰዎች ለእርሱ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የቆመን ሐውልት በቀለም ፊቱን አበለሻሽተውታል። "አንተ ሴት ደፋሪ፣ አንተ ዘረኛ" ብለውም በሚላን ከተማ የቆመውን ሐውልቱን በቀለም ቸክችከውበታል።የጣሊያን ፖሊስ ይህን ደርጊት ማን ነው የፈጸመው ብሎ ሲጠይቅ ጸረ ዘረኝነትን ያነገቡ ሰልፈኞች "እኛ ነን ሐውልቱን ያበላሸነው" ብለዋል። ይህ ሐውልት ቆሞ የሚገኘው በጣሊያን ሚላን ፓርክ ውስጥ ነው።ተቃዋሚዎች ይህ ሐውልት በአስቸኳይ መፍረስ አለበት ብለው ተነስተዋል።ሞንታኔሊ የሞተው እንደ አውሮፓዊያኑ በ2001 ነበር።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የወላይታ ህዝብ እራሱን በራሱ የማስተዳደር ህገ-መንግስታዊ በክልል የመደራጀት የመብት ጥያቄ በምክር ቤቱ ተገቢው ምላሽ ባለመሰጠቱ በደ/ብ/ብ/ህ/ ክልል ም/ቤት የወላይታ ህዝብ ተመራጮች እራሳቸውን ከምክር ቤት አባልነት ማግለላቸውን የወላይታ ዞን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ምክር ቤቱ በዛሬው ቀን በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ምንጭ: የዞኑ መ/ኮ/ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ከ205 ሺህ በላይ ሕጻናት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚኖሩ የክልሉ ሴቶች፣ ሕጻናትና፣ ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ የአፍሪካ ሕጻናት ቀንን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሰኔ 9/1984ዓ.ም በየዓመቱ ሰኔ 9 ቀን የአፍሪካ ሕጻናት ቀን ሆኖ እንዲከበር ወስኗል፡፡ ኢትዮጵያም ዕለቱን በተለያዩ ዝግጅቶች ታከብረዋለች፡፡ዘንድሮውም “ሕጻናትን ከወረርሽኝና ከጥቃት በመታደግ የአረንጓዴ ልማት ባህሉ ያደገ ትውልድ መፍጠር” በሚል መሪ ሐሳብ ይከበራል፡፡ ነገ ሰኔ 9/2012 ዓ.ም የሚከበረውን የአፍሪካ ሕጻናት ቀንን ምክንያት በማድረግ መግለጫ የሰጡት የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሰላማዊት ዓለማየሁ ከወቅቱ አንጻር ሕፃናት ለተለያዬ ችግር እንደሚጋለጡ ተናግረዋል፡፡ ከልጅነት ጋብቻ በመጠበቅ፣ ወላጆቻቸውን ያጡ፣ ከስደት የተመለሱና ሌሎችም ድጋፍ የሚሹ ሕጻናት በየአካባቢው እንክብካቤ እየተደረገላቸው ሰብዓዊ መብታቸውና ደኅንነታቸው ተጠብቆ እንዲያድጉ ለማስቻል ቀኑ እንደሚከበር አስታውቀዋል፡፡ ሕጻናቱ ከችግር ተላቅቀው ሕይወታቸውን እንዲመሩ ቀጣይነት ያለው ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ትኩረት ሰጥቶ ለመሥራትም እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ቢሮው መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በማድረግ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሕጻናትን ድጋፍ እና እንክብካቤ እንዲደረግላቸው እየሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ በተደረገ የመረጃ ማሰባሰብ ሥራ በተለይም በዚህ ወቅት በክልሉ 205 ሺህ 134 ሕጻናት በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ወይዘሮ ሰላማዊት ተናግረዋል፡፡ እንደ መግለጫው ባሕር ዳር፣ ጎንደር እና ደሴ ከተሞች በጎዳና ይኖሩ የነበሩ 6 ሺህ 348 ሕጻናትን ወደ ቤተሰቦቻቸው የማቀላቀል ሥራ እየተሠራ ነው፡፡ የልጅነት ጋብቻ የተከሰተባቸውን ፈጻሚዎቹን በሕግ የመጠዬቅ ሥራም ተሠርቷል፡፡

 በክልሉ 13 የሚደርሱ የሕጻናት ማዕከላት እንዳሉ የተናገሩት ምክትል ቢሮ ኃላፊዋ በማዕከላቱ 573 ሕጻናት እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡ ሕጻናቱ በቅርብ የሚከታተላቸው ያለ ቢሆንም ከወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ችግር እንዳይገጥማቸው ቢሮው እየሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ የሕጻናት ችግር በርከት ያለ በመሆኑ በአንድ ተቋም ብቻ የሚሠራ እንዳልሆነና የሚመለከታቸው አካላትም ቀኑን ከማክበር ባለፈ የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡም ጥሪ ቀርቧል፡፡

 የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ የሕጻናት ችግር ሰፋ ያለ መሆኑን ያነሱት ወይዘሮ ሰላማዊት ልጆች በቤታቸው ሲውሉ የተሻለ ደኅንነት ላይ ያሉ ቢመስልም ለተለያዩ ችግሮች እንደሚጋለጡም ተናግረዋል፡፡ ሕጻናት በቤት ሲውሉ ተገድዶ መደፈርን ጨምሮ ለሥራ እና ሥነ ልቦናዊ ጫና ተጋላጭ መሆናቸውን ምክትል ኃላፊዋ ተናግረዋል፡፡ በወቅቱ የተፈጸሙ ችግሮችን ለመለዬት ጥናት ባይደረግም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ ያለው ጥቃት ከፍ ያለ እንደሆነ ወይዘሮ ሰላማዊት ጠቁመዋል፡፡በክልሉ የኮሮናቫይረስ ከተከሰተ ወዲህ 63 የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች መፈጸማቸውንም አስታውቀል፡፡ ይህ ቁጥርም ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር ከፍ ያለ ነው ተብሏል፡፡ ጥቃቶቹ የሚፈጸሙት በአቅራቢያ ባለ ሰው መሆኑም ተገልጿል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
የናይጄሪያ ሀኪሞች የሥራ ማቆም አድማ ሊመቱ ነው!

የጤና ባለሙያዎቹ የደሞዝ እጥረት እና የሀኪሞች መገልገያ ቁሳቁስ (ፒፒኢ) አለመሟላትን ይቃወማሉ።ማኅበሩ እንዳለው፤ ሀኪሞች የድንገተኛ እንዲሁም የኮሮናቫይረስ ሕክምናም ያቋርጣሉ።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ባለፉት ሁለት ቀናት በተከሰቱ ሁለት አደጋዎች ከ180 ሺ ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገለጸ።

በአዲስ አበባ እሳት አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የመጀመሪያው አደጋ በአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በቀን 6 2012 ዓ.ም ከ ቀኑ 8 ሰዓት የተከሰተ፤ 250 ካሬ ሜትር የሚሸፍን ድንገተኛ የሼድ ቃጠሎ ነው፡፡በአደጋውም 30 ሺ ብር የሚገመት ንብረት የወደመ ሲሆን 500 ሺ ብር የሚገመት ንብረት ማትረፍ ተችሏል፡፡

ሌላኛው አደጋ የተከተው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ትናንት ምሽት ላይ 5 ሰዓት በሲሊንደር ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካ ላይ የደረሰ ቃጠሎ ነው፡፡ወደ 200 ካሬ ሜትር የሸፈነው የሲሊንደር ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካ ቃጠሎው 150 ሺህ ብር የሚጠጋ ንብረት እንዲወድም ምክንያት የሆነ ሲሆን 15 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ደግሞ ማትረፍ መቻሉን አቶ ጉልላት ተናግረዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮርቤቲ የኃይል ግዢ ስምምነት እና ረቂቅ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ እንዲሁም ሁለተኛውን የኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አጸደቀ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ጣዋት ባካሄደው ስብሰባ ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል።በዚህም የኮርቤቲ የኃይል ግዢ ስምምነት እና ረቂቅ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ እንዲሁም ሁለተኛውን የኢትዮጵያ የንግድ ሕግ ማጽደቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፌስ ቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ በጣም ሰፊ ሀገር በመሆኗ ተጨማሪ ወደቦች እንደሚያስፈልጓት በኬኒያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም ገለጹ።

ኢትዮጵያ የላሙ ፕሮጀክት መጠናቀቅን በጉጉት እየጠበቀች መሆኑንም አምባሳደር መለስ አስረድተዋል። አምባሳደሩ አያይዘውም የላፕሴት ኮሪደር ለደቡባዊ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን አመልክተዋል።የጅቡቲ፣ የሱዳንና የኤርትራ ወደቦችን መጠቀም ለደቡባዊ የኢትዮጵያ ክፍሎች ካላቸው ርቀት አኳያ አዋጭ አለመሆኑንም አምባሳደር መለስ አብራርተዋል።ኢትዮጵያ ወደቡን የምትፈልገው ኬኒያን ለማስደሰት ሳይሆን ለራሷ ጥቅም ብላ መሆኑን አምባሳደር መለስ መናገራቸውን በኬኒያ የሚታተመው ዘስታር ዘግቧል። የፕሮጀክቱ አካል የሆነው የወደብ ግንባታ ተጠናቆ ወደ ሥራ እስኪገባ በጉጉት እየጠበቁ መሆኑንም አንስተዋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) የትግረኛ ቋንቋ ክፍል ሀላፊ አቶ ኃ/ማሪያም ገ/እግዚአብሔር እየደረሰብኝ ነው ባሉት ጫና ምክንያት ሀላፊነታቸውን መልቀቃቸውን ገለጹ።

Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 176 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5636 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰባ ስድስት (176) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3521 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ የ3 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ፣ ባጠቃላይ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 60 ደርሷል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ያለፈ 3 ሰዎች ሁኔታ

1.በህክምና ላይ የነበሩ የ60 አመት የአማራ ክልል ነዋሪ (ወንድ)

2.በህክምና ላይ የነበረ የ19 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

3.በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘበት የ32 አመት የአማራ ክልል ነዋሪ

@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 176 ሰዎች ሲሆኑ በዜግነት 175 ኢትዮጵያውያን፣ አንዱ የውጭ ሀገር ዜጋ ነው። በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(116) ሴት(60) ናቸው!

➡️ዕድሜያቸው ከ5-90 አመት የሆኑ

➡️ተጨማሪ 75 ሰዎች(31 ከአዲስ አበባ፣ 5 ከአማራ፣ 1 ከአፋር፣ 28 ከሶማሊ ክልሎች) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 620 ነው።

➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(98)፣ ከኦሮሚያ ክልል(3)፣ከአማራ ክልል(33) ፣ ከትግራይ ክልል(31)፣ ከሶማሌ ክልል(7)፣ከድሬዳዋ(2) እና ከአፋር ክልል(2) በድምር 176 ሰዎች ናቸው።

➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3521 ደርሷል።

➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 29 ነው።

➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 3 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፣ እስካሁን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 60 ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር መናኸሪያ ውስጥ አገልግሎት ከሚሰጡ 36 ግለሰቦች ለ(covid-19) ቫይረስ ምርመራ ናሙና ተወስዶ በ16ቱ ላይ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተገለፀ፡፡

በከተማ አስተዳደሩ 36 ከሚሆኑ በመናኸሪያ ውስጥ አገልግሎት ከሚሰጡ ሰራተኞ፣ሹፌሮችና ረዳቶቸ ላይ ለ(covid-19) ቫይረስ ምርመራ ናሙና ተወስዶ በ16ቱ ላይ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ማሞ እንደገለፁት በ06/10/2012 ዓ.ም ቅዳሜ ዕለት በጽህፈት ቤቱ የጤና ባለሙያዎች ከ36 የደብረ ብርሃን መናኸሪያ ሰራተኞች፣ሹፌሮችና እረዳቶች ላይ ናሙና ተወስዶ ናሙና ከሰጡት 36 ሰዎች ውስጥ 16ቱ የ(covid-19) ቫይረስ የተገኘባቸው በመሆኑ በደብረ ብርሃን ከተማ በተዘጋጀው ጠባሴ ጤና ጣቢያ የህክምና ማዕከል እንዲገቡ መደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ከነዚህ ግለሰቦች ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች እየተለዩ መሆናቸውን የገለፁት ኃላፊው በተመሳሳይ ዛሬም በዚያው በደብረ ብርሃን ከተማ መናኸሪ አካባቢ የ70 ሰዎች ናሙና ተወስዶ ውጤት እየተጠበቀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ኃላፊው አክለው ማህበረሰቡ በተደጋጋሚ ቢነግርም የባህሪ ለውጥ ባለማምጣቱ በከተማው ከመቸውም ጊዜ በበለጠ የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተስፋፋ ይገኛል፡፡

ምንጭ፡- Debre Birhan city Communication Affairs Office
@YeneTube @FikerAssefa
በሰሜን ሸዋ ዞን የኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው 22 ሰዎች መካከል 16 ሰዎች እየተፈለጉ መሆኑን መምሪያው አስታውቋል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ኬዝ ቲም አስተባባሪ አቶ አውላቸዉ ታደሰ ለአብመድ እንደተናገሩት በ79 ሰዎች ላይ ምርመራ ተደርጎ 22 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡አስተባባሪ እንዳሉት ከ79 ተመርማሪዎች 36 አሽርካሪዎች ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል 16 የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በቫይረሱ ከተያዙ ግለሰቦች መካከል አንደኛው በሞጃና ወደራ ወረዳ በአስከሬን ምርመራ መገኘቱም ታውቋል፡፡ ከሳምንት በፊት በእንሳሮ ወረዳ በቫይረሱ ተይዞ ሕይወቱ ካለፈ ሰው የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙና ከግለሰቡ ጋር የቀጥታ ንክኪ ከነበራቸዉ 45 ሰዎች መካል አራቱ በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡንም መምሪያው አስታውቋል፡፡

አንድ ግለሰብ ደግሞ ከጣርማበር ወረዳ ደብረሲና ከተማ ቫይረሱ ተገኝቶበታል፤ ግለሰቡ በአስተናጋጅነት ሥራ ላይ የተሰማራ እንደሆነም አስተባባሪው ለአብመድ ተናግረዋል፡፡እንሳሮ ወረዳ ላይ የተገኘባቸዉ አራት ግለሰቦች ወደ ደብረ ብርሃን ለይቶ ሕክምና መስጫ እንዲመጡ እየተደረገ መሆኑም ታውቋል፡፡ ቫይረሱ ከተገኘባቸዉ 22 ሰዎች መካከል 16ቱ አሽከርካሪዎች የት እንዳሉ እንደማይታወቅና እየተፈለጉ እንደሚገኙ አስተባባው ለአብመድ ተናግረዋል፡፡ ከግለሰቦቹ ጋር የቀጥታ ንክኪ ያላቸዉ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የማግኘቱ ሥራ እንደተጀመረም ታውቋል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ ምርመራ 98 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው!

በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ዘጠና ስምንት (98) ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን በከተማችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሁለት ሺህ አምስት መቶ ሰባ ሰባት (2577) ደርሷል፡፡ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በአዲስ አበባ አንድ (1) በህክምና ማዕከል ውሰጥ ህክምና ሲከታተል የነበረ የ አስራ ዘጠኝ (19) አመት ወጣት ህይወቱ አልፏል።በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት ሰላሳ አንድ (31) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ አገግመዋል፡፡

በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፦
አዲስ ከተማ 37፤
ልደታ 13፤
ጉለሌ 4፤
ኮልፌ ቀራንዮ 8፤
ቦሌ 4፤
አራዳ 7፤
የካ 2፤
ንፋስ ስልክ ላፍቶ 4፤
አቃቂ ቃሊቲ 2፤
ቂርቆስ 16፤
የ1 ሰው አድራሻ በመጣራት ላይ ይገኛል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአውሮፓ ኅብረት ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መቋቋም እንድትችል 19 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ሊያደርግ ነው!

የአውሮፓ ኅብረት ኢትዮጵያ ላጋጠማት የኮሮናቫይረስ ቀውስ ምላሽ መስጠት እንድትችል የጤና ሥርዓቷን ለመደገፍ፣ የማቆያ ማእከላት እንድትገነባ፣ የኑሮ እና ኢኮኖሚ መነሣሣት እንድትፈጥር የሚያስችል የ487 ሚሊየን ዩሮ (19 ቢሊዮን ብር) ድጋፍ ሊሰጥ ነው።ኅብረቱ ድጋፉን የሚያደርገው አጋር አገራት ወረርሽኙን ለመቋቋም እንዲችሉ መሆኑን ከኅብረቱ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የሀገር ሽማግሌዎች መማክርት በጋራ በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መካከል « ጥሩ ያልሆነ ግንኙነት» ያሉትን በንግግር እንዲፈታ ለማድረግ ነገ ወደመቀሌ ሊጓዙ ነው።

የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የሀገር ሽማግሌዎች መማክርት ከዚህ ቀደምም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሰላም ጉዞ እንቅስቃሴ ያደርጉ እንደነበር ያመለከቱት የጉባኤው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሀጂ መስዑድ አደም አሁን በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ የሃይማኖት አባቶችንና የሀገር ሽማግሌዎችን ጣልቃ ገብነት የሚፈልግ መሆኑን ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። «አንዳንድ ወገኖች ሽማግሌም ሆነ ትልቅ ሰው የለም ወይ?» እንደሚሉ የጠቀሱት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ክልላዊ መንግሥት መካከል የሚታየውን አተካሮ አለዝቦ የማስታረቁ ሃሳብ ሁለቱም ተቋማት በየበኩላቸው ተነጋግረው ከሁለቱም ወገን የመነጨ መሆኑም አመልክተዋል። ዋና ዓላማቸው ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር በጉዳዩ ላይ መነጋገር መሆኑን በማመልከትም ለዚህም ይሁንታቸውን ማግኘታቸውን ገልጸዋል። በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ምርጫ መራዘሙን የፌደራል መንግሥት ምክር ቤት በአብላጫ ድምፅ ደግፏል፤ የትግራይ ክልል ምክር ቤት ምርጫውን ለማካሄድ ወስኗል። የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰባት የሃይማኖት ድርጅቶች የተካተቱበት ሲሆን የሀገር ሽማግሌዎች መማክር ደግሞ ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦችን የያዘ ስብስብ መሆኑ ታውቋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የኬንያ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ሠራተኞች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

የኬንያ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አራት ሠራተኞች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ጽህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ አስታወቀ።ለፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚሰሩት እነዚህ አራት ሠራተኞች በበሽታው በመያዛቸው ሁሉም በአቅራብያው ወደ ሚገኝ ሆስፒታል ተወስደዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa