በአዲስ አበባ ከተማ የፊታችን ሰኞና ማክሰኞ በአንዳንድ አካባቢዎች ለማሻሻያ ሥራ ሲባል የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ይቋረጣል!
👉ሰኞ ሐምሌ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ፤ በወሰን ግሮሰሪ፣ በሲኤምሲ ሚካኤል፣ በየካ አባዶ፣ በሳሪስ አቦ ቤተ-ክርስትያን፣ በቦሌ ቡልቦላ ኮንደሚኒየም፣ በቡልቡላ ማርያም ማዞርያ፣ በክሬሸር፣ በኦሎፕያ፣ በፍላሚንጎ፣ በደንበል፣ በኦሮሚያ ቢሮ፣ በሰንሻይን ጀርባ እና አካባቢዎቻቸው፤
👉ማክሰኞ ሐምሌ 28 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 4፡30 ሰዓት ድረስ፤ በፊጋ፣ በእፎይታ ሰፈር እና አካባቢዎቻቸው፤
👉እንዲሁም በተመሳሳይ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ፣በቀጨኔ 8 ቁጥር መዞርያ፣ በአመሃ ደስታ ትምህርት ቤት፣ በመቀጠያ፣ በታቦት ማደርያ እና አካባቢዎቻቸው፤
👉በተጨማሪም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ፤ በየረር፣ በጎሮ ሰፈራ፣ በጎሮ ገብርኤል፣ በየረር ድልድይ፣ በወሰን ግሮሰሪ፣ በሲኤምሲ ሚካኤል፣ በየካ አባዶ እና አካባቢዎቻቸው፤በመካከለኛ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኤሌክትሪክ የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ፣ ክቡራን ደንበኞቻችን ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
@YeneTube @FikerAssefa1

በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ ከተደረጉ 4,347 የላብራቶሪ ምርመራዎች 295 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን በከተማው እስከ ዛሬ ድረስ ከተደረጉ 257,633 ምርመራዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 12,623 ደርሷል።
@YeneTube @FikerAssefa1
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 469 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል!
ባለፉት 24 ሰአታት ለ7358 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 469 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡ዶክተር ሊያ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት 24 ሰአታት የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል፡፡245 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 17,999፣ ያገገሙት 7195፣ የሟቾች ቁጥር 284 ሲደርስ ፣በፅኑ ህክምና ክፍል ያሉ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ወደ 68 ዝቅ ብሏል።

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው ከሰሞኑ በኮንሶ እና አሌ ማህበረሰቦች መካከል በተፈጠረው ግጭት የደረሰውን ጉዳት በዛሬው ዕለት በአካባቢው በመገኘት ተመልክተዋል።
21 ሰዎች የሞቱበት ይህ ግጭት የተቀሰቀሰው በሁለት ጎረቤታሞች መካከል በተፈጠረ የመሬት ይገባኛል ጥያቄ እንደነበር የአካባቢው አስተዳዳሪዎች በዛሬው መርሃ ግብር ላይ ተናግረዋል።እስካሁን 7 የአካባቢው አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።
Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa1
21 ሰዎች የሞቱበት ይህ ግጭት የተቀሰቀሰው በሁለት ጎረቤታሞች መካከል በተፈጠረ የመሬት ይገባኛል ጥያቄ እንደነበር የአካባቢው አስተዳዳሪዎች በዛሬው መርሃ ግብር ላይ ተናግረዋል።እስካሁን 7 የአካባቢው አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።
Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa1
በነሀሴ ወር የመጀመሪያ ሁለት ሳምንታት ለ 200 ሺህ ዜጎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ለማድረግ ታቅዷል።
ለአንድ ወር የሚቆይ የኮሮና ቫይረስ ማኅበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና የምርመራ ዘመቻ ዛሬ ይፋ ተደርጓል።መርሀ ግብሩ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶክተር) በተገኙበት ነው ይፋ የተደረገው።በዘመቻው በነሀሴ ወር የመጀመሪያ ሁለት ሳምንታት 200 ሺህ ዜጎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ይደረግላቸዋል ተብሏል።በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ መሰራጨቱም ተገልጿል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር የመጀመሪያው 1 ሺህ ለመድረስ 79 ቀናትን እንደወሰደ፣ አሁን ላይ ግን በሁለት ቀናት ብቻ 1 ሺህ ሰዎች መያዛቸው ተገልጿል።ማኅበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና የምርመራ ዘመቻው ይፋ የተደረገውም የስርጭቱን መጠን ለማወቅና ለመቆጣጠር ታልሞ እንደሆነ ታውቋል።በቅርቡ በአዲስ አበባ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት የማስክ አጠቃቀም 76 በመቶ ፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ 38 በመቶ፣ የእጅ ንጽህና አጠባበቅ 28 በመቶ መሆኑ እንደተመላከተም ነው የተገለጸው።
#AMMA

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በድጋሚ በጸጥታ ኃይሎች ወደ ቤታቸው መወሰዳቸውን ግንባሩ አስታወቀ።
አቶ ዳውድ በጸጥታ ኃይሎች ተገደው ወደ ቤት እንዲመለሱ የተደረጉት «ለደህንነታቸው ሲባል ነው» የሚል ምላሽ ማግኘታቸውን የግንባሩ ቃል አቃባይ ቀጄላ መርዳሳ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።የግንባሩ ሊቀመንበር በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ጥብቅ ቁጥጥር ስር መሆናቸው በዕለት ተዕለት ስራቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩንም አቶ ቀጄላ ተናግረዋል። «ባለፈው ጊዜም እንደተነገረው ከእርሳቸውም አንደበትም የሰማነው ለደህንነታቸው ተብሎ ነው። ነገር ግን ይሄ ጉዳይ በስራቸው ላይ ቢሮአቸው ለመሄድ ተጽዕኖ አለው»ቀደም ሲል የግንባሩ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ባልተገኙበት በተወሰኑ የስራ አስፈጻሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አማካኝነት ተከናውኖ የነበረው ስብሰባ ዓላማውን ባልተረዱ ሰዎች የስም ማጥፋት ዘመቻ ተካሂዶበት በግንባሩ ላይ ብርቱ ጉዳት ማስከተሉን አቶ ቀጄላ ተናግረዋል።«አሁን ከስብሰባው ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ውዥንብር ብዙ ጥፋት ተከስቷል።መጠነ ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ሲከፈት ነበር። በስብሰባው ላይ የተሳተፉትን ሁሉ በጠላትነት የመፈረጅ ስራዎች ሀገር ባሉ በግንባሩ አባላት እና ደጋፊዎች ሲከናወን ቆይቷል። «አንዳንድ ሰዎች የሚጽፉትን እያየን ነው በጣም አጥፊ ተግባር ነው » በግንባሩ ውስጥ ተፈጠረ ችግርም አቶ ዳውድ ኢብሳ ወደ መደበኛ ስራቸው ሲመለሱ ሁሉም ነገር በንግግር ይፈታልም ብለዋል አቶ ቀጄላ ።አያይዘውም አቶ ዳውድ ኢብሳ ዛሬ ወደ መኖርያ ቤታቸው ከተወሰዱ በኋላ ከግንባሩ ምክትል ሊቀመንበር አራርሶ ቢቂላ ጋር መወያየታቸውን ቃል አቃባዩ ተናግረዋል።
#DW

ግብፅ በሶማሌላንድ የጦር ሠፈር ለማቋቋም የምታደርገውን ጥረት ኢትዮጵያ በትኩረት እንደምትከታተል አስታወቀች!
ግብፅ የኢትዮጵያ ጎረቤት በሆነችውና ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሕጋዊ ዕውቅና ባላገኘችው ሶማሌላንድ የጦር ሠፈር ለመመሥረት እያደረገች ያለውን ጥረት፣ ኢትዮጵያ በትኩረት እየተከታተለች መሆኑን አስታወቀች። የግብፅ ባለሥልጣናት ካለፈው አንድ ዓመት ወዲህ ከሶማሌላንድ መንግሥት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን በስፋት ሲያደርጉ እንደነበር፣ ከሳምንት በፊት ከፍተኛ የግብፅ መንግሥት ልዑካን በሶማሌላንድ ከፕሬዚዳንት ሙሳ አብዲ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ተዘግቧል።በዚህ ውይይት ወቅትም የግብፅ መንግሥት በሶማሌላንድ ሰሜን ምዕራብ ቀጣና የጦር ሠፈር ለማቋቋም ያለውን ፍላጎት በመግለጽ፣ ለፕሬዚዳንት ሙሳ አብዲ ጥያቄ ማቅረቡ ተሰምቷል።
ይህንን የግብፅ አዲስ እንቅስቃሴ በተመለከተ የተጠየቁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ (አምባሳደር)፣ የግብፅ ፍላጎት ምን እንደሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት በአንክሮ እየተከታተለ መሆኑን አስታውቀዋል። ‹‹ግብፅ በሶማሌላንድ የጀመረችው እንቅስቃሴ ምንም ይሁን ምን፣ በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎቹ የኢትዮጵያ ጎረቤት አገሮች ላይ አሉታዊ ጉዳት እንደማያስከትል ተስፋ እናደርጋለን። ከዚህ ውጪ ከሆነ ሕጋዊነት አይኖረውም፡፡ ከሆነ ግን ሰብዓዊነትንም ሆነ ዓለም አቀፍ የሰላምና የደኅንነት መርህን ይቃረናል፤›› ሲሉ ቃል አቀባዩ ለኬንያ ዴይሊ ኔሽን ጋዜጣ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇👇👇👇
https://telegra.ph/-08-02-95

ዘንድሮ የአሸንድዬ፣ ሻደይና ሶለል በዓላት እንደበፊቱ በደመቀ ሁኔታ እንደማይከበሩ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አሳወቀ፡፡
የኮሮና ተህዋሲያን (ቫይረስ) ወረርሽኝ እየተስፋፋ መምጣቱ ስነ ስርዓቱ እንዳይካሄድ አድርጓል፡፡በዘንድሮ ዓመት የአሸንድዬ፣ ሻደይና ሶለል በዓላት እንደ በፊቱ በደመቀ ሁኔታ እንደማይከበሩ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አሳውቋል፡፡ ይህም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት እንደሆነ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኃይለየሱስ ፍላቴ ጠቁመዋል፡፡በዓሉ በፓናል ውይይት፣ በፎቶ ማሳያ (ኤግዚቢሽን)፣ በደም ልገሣና ችግኝ ተከላ ታስቦ እንደሚውል ኃላፊው አመላክተዋል፡፡ የሻደይ አሸንድዬ ባህላዊ ትውፊት በ“ዶክሜንታሪ” በብዙኃን መገናኛ አውታሮች በተለይም በቴሌቪዥንና በሬድዮ ተዘጋጅተው እንደሚቀርቡ አቶ ኃይለየሱስ ጠቅሰዋል፡፡

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ረጅም ጊዜ ሊቆይ ስለሚችል አገሮች የሚሰጡት ደካማ ምላሽ ከፍተኛ መዘዝ ሊያስከትል እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት ቅዳሜ ዕለት አስጠንቅቋል።
የድርጅቱ ኮሚቴ ከስድስት ወር በፊት በሽታውን የዓለም ወረርሽኝ ብሎ ከፈረጀ ወዲህ ባካሄደው ግምገማ ላይ በሰጠው መግለጫ፣ በተለይ ቫይረሱ በአገሮች ላይ በሚያደርሰው ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጫና የተነሣ “የሚሰጠው ምላሽ ደካማነት” የከፋ መዘዝ ሊያመጣ ይችላል ብሏል።
ኮሚቴው ዓርብ ዕለት ያካሄደው ስብሰባ ወረርሽኙ ተከስቶ ዓለም አቀፍነቱ ከታወጀ እ.አ.አ ጥር 2020 ወዲህ አራተኛው ነው።
“የዓለም ጤና ድርጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ኮቪድ-19 ያለው አደጋ በጣም ከፍተኛ ነው ማለቱንም” መግለጫው አመልክቷል።
“ወረርሽኙ ረጅም ጊዜ ሊቆይ ስለሚችል በሽታውን ለመከላከል በዓለም አቀፍ ደረጃ ማኅበረሰቡ ዘላቂ የሆነ ጥረት ማድረግ እንደሚገባም” መግለጫው ጠቁሟል።
ኮሚቴው አገራት የተረጋገጡ የኮቪድ-19 መከላከለያ መድኃኒቶች እና ክትባቶች ማዘጋጀት እንዲችሉ የዓለም ጤና ድርጅት እገዛ እንዲያደርግ አሳስቧል።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ወደ ስብሰባው ሲገቡ የወረርሽኙ ተፅዕኖ ለረጅም ጊዜ ሊቆይ የሚችል ነው ማለታቸው ተዘግቧል።
በምዕተ ዓመት አንዴ የሚከሰት ይህን መሰል ወረርሽኝ ተፅዕኖ በሚቀጥሉት #አሥርት_ዓመታት ውስጥ የሚዘልቅ ነው ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ኮቪድ-19 ከ680 ሺህ በላይ ሰዎችን ሕይወት የነጠቀ ሲሆን፣ ከ18 ሚሊየን በላይ ሰዎች ደግሞ በበሽታው መያዛቸውን እስራኤል ናሽናል ኒውስ ዘግቧል።
Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa

መንግሥት የውጭ የቴሌኮም መሠረተ ልማት ኩባንያዎች እንዳይገቡ ወሰነ!
በመካሄድ ላይ ባለው የቴሌኮም ዘርፍ የለውጥ ትግበራ፣ የውጭ የቴሌኮም መሠረተ ልማት ኩባንያዎች እንዳይገቡ መንግሥት እንደወሰነ ታወቀ፡፡የቴሌኮም ዘርፍን ገበያ በመክፈት የውጭ ኩባንያዎች እንዲገቡ ለመፍቀድ መንግሥት በዝግጅት ላይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡የቴሌኮም ዘርፍ የለውጥ ትግበራ ሁለት ክፍሎች አሉት።የመጀመርያው በገንዘብ ሚኒስቴር የሚመራው ለ126 ዓመታት በብቸኝነት የቴሌኮም አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው በአፍሪካ አንጋፋው ኢትዮ ቴሌኮም ኩባንያ፣ 40 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ለውጭ ኩባንያ ለመሸጥ የሚደረገው ጥረት ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን ሁለት ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኩባንያዎች ወደ አገር ውስጥ ገብተው፣ የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት የሚያስችላቸውን ፈቃድ ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡የለውጥ ትግበራው ቀልባቸውን ከሳበው የውጭ ኩባንያዎች መካከል፣ የቴሌኮም መሠረተ ልማት ገንብተው የሚያከራዩ ኩባንያዎች ይገኙበታል፡፡እንደ ሞባይል ምሰሶዎች ያሉ መሠረት ልማቶች የሚያከራዩ ኩባንያዎች ኃላፊዎች ወደ አዲስ አበባ ሲመላለሱ ከርመዋል፡፡
ጉዳዩ ባለፉት ዓመታት በቢሊዮን ዶላሮች ወጪ በማውጣት የቴሌኮም መሠረተ ልማቶች በመላ አገሪቱ ሲዘረጋ የቆየውን ኢትዮ ቴሌኮምን አስቆጥቷል፡፡‹በቂ መሠረተ ልማት ገንብተናል፣ ለሚገቡት ኩባንያዎች አከራይተን ከፍተኛ ገቢ ማስገባት እንችላለን› ያሉት የኢትዮ ቴሌኮም ማኔጅመንት አባላት ያቀረቡትን አቤቱታ መንግሥት ተቀብሎ፣ የውጭ የቴሌኮም መሠረተ ልማት ኩባንያዎች ላለማስገባት እንደወሰነ ታውቋል፡፡
የ2012 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ፣ የውጭ የቴሌኮም መሠረተ ልማት ኩባንያዎች እንዳይገቡ እንደተወሰነ አስታውቀዋል፡፡ ‹‹የውጭ የቴሌኮም መሠረተ ልማት ኩባንያዎች እንዳይገቡ መንግሥት ወስኗል፣ አይገቡም፡፡ የሚገቡት ኦፕሬተሮች ወይ ከእኛ ይከራያሉ ወይም የራሳቸውን ይገነባሉ፤›› ያሉት ወ/ሪት ፍሬሕይወት፣ ኩባንያዎቹ የኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ምሰሶዎችንና የፋይበር ኦፕቲክስ መስመሮችን መከራየት እንደሚችሉ አስረድተዋል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በሊበራላይዜሽን ሒደቱ ላይ ያሉትን ሥጋቶችና ቅሬታዎች በጽሑፍ ለኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን አስገብቶ፣ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ እንደሆነ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ ‹‹ባለሥልጣኑ የኢትዮ ቴሌኮምን ህልውና የሚጎዳ አካሄድ ይከተላል ብለን አናምንም፡፡ ነገር ግን ከስምምነት ላይ ያልደረስንባቸው ቀሪ ጉዳዮች አሉ፤›› ብለዋል፡፡በተያያዘ ዜና የኢትዮ ቴሌኮም የንብረት ትመና ሥራ በማከናወን ላይ የሚገኘው ኬፒኤምጂ (KPMG) የተሰኘው ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት፣ ሥራውን በማጠናቀቅ ላይ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የንብረት ትመና ሥራውን አጠናቆ ሁለት ዙር ሪፖርት ለኢትዮ ቴሌኮም ማኔጅመንት እንዳቀረበ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ተናግረዋል፡፡በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ በዓለም አቀፍ የፋይናንስ አሠራር ሥርዓት ሪፖርት እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡
#Reporter

በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ በርካታ ክልሉ የልዩ ኃይል አባላትና ታጣቂ ሚሊሻዎች በዛሬው ዕለት ወታደራዊ ሰልፍ በማካሄድ ትዕይንት አድርገዋል።
በሰልፉ ላይ የተሳፉት የልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላቱ ቀላልና ከባድ የጦር መሳርያዎችን ታጥቀው መታየታቸውን የቢበሲ ዘጋቢ ከመቀለ ገልጿል።ዛሬ ረፋድ ላይ በክልሉ ዋና ከተማ በመቀለ ጎዳናዎች ላይ በሰልፍ ሲጓዙ የታዩት ወታደራዊ የደንብ ልብስ የለበሱት የልዩ ኃይሉ አባላትና ሚሊሻዎች በከተማው ወደሚገኘው ስታድየም በመጓዝ ተሰብስበው ታይተዋል።በመቀለ ከተደረገው ከዚህ ወታደራዊ የሰልፍ ትዕይንት ባሻገር በሌሎችም የክልሉ ከተሞች ጭምር መደረጉ ለማወቅ ተችሏል።ቢሆንም ይህ ዛሬ የተካሄደው ወታደራዊ ሰልፍ ዓላማው ምን እንደሆነ የትግራይ ክልል መንግሥት የገለጸው ነገር የለም።ነገር ግን የትግራይ ክልል የጸጥታ ቢሮ ፌስቡክ ገጹ ላይ "ለሰላም ሲባል ለሚከፈል ዋጋ ሁሌም ዝግጁ ነን" የሚል መልዕክት አስፍሯል።ቢሮው አክሎም "የአንድ ሕዝብ የሰላሙ ዋስትና ውስጣዊ አቅሙ እንጂ የማንም የውጭ ኃይል ድጋፍና ጥበቃ ሆኖ አያውቅም" ሲል ገልጿል።
#BBC

ኢትዮጵያዊያን በያሉበት ሆነው በዛሬው ዕለት ከ10 ሰዓት(ከ7 ደቂቃዎች በኋላ) ጀምሮ ለታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ያላቸውን ድጋፍ ያሰማሉ።
ድምፃችን ለግድባችን በሚል መሪ ቃል በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያን ለግድቡ ያላቸውን ድጋፍ ያሰማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት እና ሊፍት ኢትዮጵያ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ያዘጋጁት ይህ መርሃ ግብር ኢትዮጵያን የህዳሴ ግድብ ለደረሰበት ደረጃ ምስጋና ለማቅረብ ነው።

አንድነታችን ለግድባችን!
ከቀኑ 10: ሰአት ዛሬ ሀምሌ 26,2012 የመጀመርያ የአባይ ግድብ ውሀ ሙሌትን በማስመልከት ዛሬ በአዲስ አበባ መኪኖች በክላክስ እግረኞች በፉጨትና በጭብጭባ ድጋፋቸውን ለደቂቃዎች አሰምተዋል። ይሄ ፎቶ ደታስ ሆስፒታል አካባቢ የተነሳ ነው።
#FidelPost

“ድምፃችን ለግድባችን” በሚል ለሕዳሴው ግድብ ኢትዮጵያውያን ድምፅ የሚያሰሙበት መርሐ ግብር እየተከናወነ ነው!
“ድምፃችን ለግድባችን” የተሰኘ እና በመላው ዓለም ያሉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ውኃ ሙሌትን በተመለከተ ደስታቸውን እንዲገልጹ ለማድረግ ያለመው ዝግጅት በመከናወን ላይ ይገኛል።ዝግጅቱን ሊፍት ኢትዮጵያ የተሰኘ ድርጅት ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል።በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ በሚገኘው መርሐ ግብር ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር በት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ ወ/ሮ ሮማን ገብረ ሥላሴን ጨምሮ በርካታ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና የክብር እንግዶች በመታደም ላይ ናቸው።
#ETV

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንድነታችን ለግድባችን!
ለቡ መብራት ሃይል አካባቢ ፣
የአባይ ግድብ ውሀ ሙሌትን በማስመልከት መኪኖች በክላክስ እግረኞች በፉጨትና በጭብጭባ ድጋፋቸውን አሰምተዋል።
Via ChuChu/Yenetube
@YeneTube @FikerAssefa1
ለቡ መብራት ሃይል አካባቢ ፣
የአባይ ግድብ ውሀ ሙሌትን በማስመልከት መኪኖች በክላክስ እግረኞች በፉጨትና በጭብጭባ ድጋፋቸውን አሰምተዋል።
Via ChuChu/Yenetube
@YeneTube @FikerAssefa1
ጎሮ አከባቢ ድምፃችን ለግድባችን በማለት ድምፃቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።
#ግድቡ_የኔ_ነው
#itsmydam
Via:- ኦዚል የኔቲዩብ
@Yenetube @Fikerassefa
#ግድቡ_የኔ_ነው
#itsmydam
Via:- ኦዚል የኔቲዩብ
@Yenetube @Fikerassefa