YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ልደታ ኮንዶሚንየም ድምፃችን ለግድባችን!!

Via:- Lidia - Yenetube
@Yenetube @Fikerassefa
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ድምፃችን_ለግድባችን በማለት ኢትዮጵያዊያን በያሉበት ድምፃቸውን አሰምተዋል።

[32mb] በዋይፋይ ተመልከቱት
Via:- ማስተዋል- የኔቲዩብ
@Yenetube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ድምፃችን ለግድባችን!

አዲስ ከተማ፣ ሰባተኛ አካባቢ የነበረው ድባብ

#ግድቡ_የኔ_ነው
#itsmydam

Via King/YeneTube
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በተመሳሳይ ቃሊቲ 40/60 ኮንዶሚንየም ድምፃቸውን አሰምተዋል።

#ግድቡየኔነው💪
#Itsmydam💪🏻
Via:- Beza (Yenetube)
@Yenetube @Fikerassefa1
ድምፃችን ለግድባችን!

በተመሳሳይ ቦሌ አራብሳ አካባቢ የነበረው ድባብ በፎቶ

#ግድቡየኔነው
#Itsmydam

Via Bezawit[YeneTube]
@YeneTube @FikerAssefa
ድምፃችን ለግድባችን!

ሐምሌ19 አካባቢ የነበረው ድባብ በፎቶ

#ግድቡየኔነው
#Itsmydam

Via SAM[YeneTube]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል ከተሞች የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ አስገዳጅ ድንጋጌ ተግባራዊ ሆኗል። በተለይም የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ ይታይባታል በተባለችው መቐለ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ መንቀሳቀስ ቅጣት ያስከትላል።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ በ1 ቀን የ28 ሰዎች ህይወት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ አለፈ!

ባለፉት 24 ሰአታት ለ7607 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 707 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡ዶክተር ሊያ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት 24 ሰአታት የ28 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል፡፡406 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 18,706፣ ያገገሙት 7601፣ የሟቾች ቁጥር 310 ሲደርስ ፣በፅኑ ህክምና ክፍል ያሉ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ወደ 153 ከፍ ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa1
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በትናንትናው እለት ማለትም በ25/11/2012 ሪፖርቱ የ10 ሰው ህይወት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ማለፉን ያስታወቀ የነበረ ቢሆንም፣ ይህ ቁጥር ስህተት በመሆኑ ይቅርታን ጠይቆ በእለቱ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች 8 እንደነበርና እስከ ትናንት ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 282 እንደሆነ አሳውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa1
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ እውነታዎች!

👉የግንባታው የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠበት እለት - መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም፤
👉የግንባታው ስፍራ፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጉባ ወረዳ፤
👉የዋናው ግድብ ከፍታ -145 ሜትር፤
👉የዋናው ግድብ ርዝመት -1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር፤
👉የዋናው ግድብ ውፍረት - የግድቡ ግርጌ 130 ሜትር ሲሆን የግድቡ ጫፍ ወይም የላይኛው ክፍል 11 ሜትር፤
👉ግድቡ የሚይዘው የውሃ መጠን -74 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር፤
👉ግድቡ የሚሸፍነው የቦታ ስፋት -1 ሺህ 680 ስኩዌር ኪሎ ሜትር፤
👉ሲጠናቀቅ ውሃ የሚተኛበት መሬት ርዝመት 246 ኪሎ ሜትር፤
👉የኮርቻ ግድብ /Saddle Dam/ ከፍታ- 50 ሜትር፤
👉የኮርቻ ግድብ /Saddle Dam/ ርዝመት 5.2 ኪ.ሜ
👉ግድቡ16 የኃይል ማመንጫ ዩኒቶች አሉት፤
👉እያንዳንዱ ዩኒት የሚያመነጨው የኃይል መጠን ከ375 እስከ 400 ሜጋ ዋት፤
👉ጠቅላላ ግድቡ ሲጠናቀቅ የሚያመነጨው ኃይል መጠን፡ 6 ሽህ 450 ሜጋ ዋት
👉ከ500 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ማልማት ያስችላል፤
👉ከ10 ቶን በላይ ዓሳን ማምረት ያስችላል፤
👉ከ40 በላይ ደሴቶች ይኖሩታል።
👉ከግድቡ የውሃ ላይ የትራንስፖርት፣ የአሳ ልማትና ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ አገልግሎት ይውላል።
👉ታዳሽ ኃይል በመሆን የከባቢ ብክለትን ይከላከላል።
👉የከተሞችን ተሞክሮ በመቀመር በአዲሱ የህዳሴ ሐይቅ ዙሪያ ዘመናዊ ከተማ ለመመስረት ያስችላል።
👉አጠቃላይ ግንባታው የደረሰበት ደረጃ- 74.26%፤
👉ግድቡ በትልቅነቱ በአፍሪካ አንደኛ ደረጃን ይዟል።

ምንጭ፡- የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ
ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት/Prosperity Party Official FB page
@YeneTube @FikerAssefa1
👍1
ተመድ በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞችን ፍላጎት ለማሟላት ገንዘብ እንዳጠረው አስታወቀ!

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ766 ሽ በላይ ለስደተኞቹ ፍላጎት ለማሟላት ገንዘብ እንዳጠረው አስታወቀ። ተመድከሚያስፈልገው 385 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 72 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ማግኘት ማግኘቱን ገልጿል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ)የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞችን ፍላጎት ለማሟላት ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት እንዳጋጠመው አስታውቋል።ኮሚሽኑ ለስደተኞች አስፈላጊ የሆኑ የምግብ፣የትምህርት፣ የጤናና የመጠለያ ፍላጎቶችን ለማሟላት ከሚያስፈልገው 385 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 72 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ማግኘት መቻሉን ሮይተርስ ዘግቧል።

ከፈረንጆቹ ሰኔ 30 ጀምሮ ኮሚሽኑ ከ766ሺ በላይ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በኢትዮጵያ በስተኞች ካምፕና በስድስት ክልሎች ይገኛሉ።ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከኡጋንዳ ቀጥሎ በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ እያስተናገደች ትገኛለች።በኢትዮጵያ ያሉ ስደተኞች በአብዛኛው ከኤርትራ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከሶማሊያና ከሱዳን የመጡ መሆናቸውን የኢትዮጵያ መንግስት መረጃን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።ስደተኞችን በማስተናገድ የቆየ ልምድ ያላት ኢትዮጵያ በጎረቤት ሀገር በሚፈጠር ግጭትና ረሀብ ብዙዎች ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ። ኢትዮጵያ ከየመንና ከሶሪያ የመጡ ስደተኞችን ጭምር እያስተናገደች ትገኛለች።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa1
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።በአሁን ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከሉ ኡማ የ2012 ዓ.ም በጀት አፈፃፀምን ለምክር ቤቱ እያቀረቡ ይገኛል።ምክትል ከንቲባው የ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫን አቅርበው ውይይት እንደሚደረግበት ተጠቁሟል። በተጨማሪም የ2013 ዓ.ም የካፒታል በጀት እና መደበኛ በጀት ፣የ2012 የዋና ኦዲተር እና ፍርድ ቤቶች ሪፖርት እንዲሁም ልዩ ልዩ ሹመቶችን እንደሚያጸድቅ አቶ አዲስአለም ገልጸዋል፡፡በዛሬው ዕለት የተጀመረው ጉባኤው ነገም እንደሚቀጥል ነው የተነገረው።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
ኢራን በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ቁጥርን ማሳነሷን አንድ ሾልኮ የወጣ መረጃ አጋለጠ!

በኢራን በኮሮናቫይረስ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር መንግሥት በይፋ ከገለጸው በሶስት እጥፋ እንደሚበልጥ የቢቢሲ ፐርሺያ ምርመራ አረጋገጠ።ለህዝብ ይፋ ያልሆነ የኢራን መንግሥት አሃዝ የሚያሳየው በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ወደ 42ሺህ የሚጠጋ ነው። ይሁን እንጂ የአገሪቱ ጤና ሚንስቴር እስካሁን በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 14ሺህ 405 ነው ይላል።ይህም ብቻ ሳይሆን ከኢራን መንግሥት የተገኘው መረጃ በቫይረሱ ስለመያዛቸው በይፋ የተነገረው ቁጥር በግማሽ እንዲቀንስ መደረጉን አመልክቷል።

ጤና ሚንስቴር እስካሁን በቫይረሱ ተይዘዋል ያላቸው ሰዎች ቁጥር 278 ሺህ 827 ነው። ይሁን እንጂ የአገሪቱ መንግሥት 451ሺህ 024 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን አረጋግጧል። የኢራን መንግሥት በቫይረሱ የተያዙ እና የሞቱ ሰዎች ቁጥርን ከማሳነሱም በተጨማሪ በቫይረሱ ሳቢያ ህይወት ማለፍ ከጀመረ ከአንድ ወር በኋላ ነበር የአገሪቱ የጤና ሚንስቴር በቫይረሱ ሳቢያ የሰው ህይወት ማለፉን ሪፖርት ያደረገው።ይህ መረጃ እንዳረጋገጠው፤ መንግሥት የመጀመሪያውን ሟች ይፋ በሚያደርግበት ወቅት 52 ሰዎች ቀድመው በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።

ማንነቱ ይፋ ያልሆነው ምንጭ ለቢቢሲ የላከው መረጃ በመላው ኢራን በየዕለቱ በኮቪድ-19 ተይዘው ወደ ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎችን ዝርዝር መረጃ የያዘ ነበር።ሥም፣ እድሜ፣ ጾታ፣ ታማሚው የሚታይበት ምልክት፣ ቀን እና ተጠቂው የተጓዳኝ በሽታ ታማሚ ስለመሆኑ እና ሌሎች መረጃዎች ተካተውበታል። መረጃውን ለቢቢሲ የላከው ምንጭ “እውነቱ መታወቅ ስላለበት” እና “በወረርሽኙ የፖለቲካ ጥቅም ለማግኘት የሚደረገው ጥረት መቆም አለበት” በሚሉ ምክንያቶች መረጃውን ለቢቢሲ ለማጋራት መወሰኑ ተመልክቷል።ለቢቢሲ ቃላቸውን የሰጡ የኢራን የጤና ባለሙያዎች እንዳሉት የአገሪቱ ጤና ሚንስቴር በኢራን መንግሥት የደህንነት አገልግሎት ጫና ይደረግበታል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
ከክረምት መግባት ጋር ተያይዞ መንገድ ላይ የሚደረጉ ማንኛውም ቁፋሮዎች እንደማይከናወኑ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ!

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የክረምት መግባት ጋር በተያያዘ በመንገድ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚካሄዱ የቁፋሮ ስራዎችን ከግንቦት 30 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ማስቆሙን ገልፆ ለተግባራዊነቱም የክትትልና ቁጥጥር ስራ እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል፡፡የክረምት ወራት መግባትን ተከትሎ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከመሰረተ ልማት አቅራቢ ተቋማትና ግለሰቦች ለተለያዩ የልማት ስራዎች የሚቀርቡለትን የመንገድ መሰረተ ልማት ቁፋሮ ፈቃድ ማቆሙ ይታወቃል፡፡ከመንገድ መሰረተ ልማት ጋር ተያይዞ የቁፋሮ ፈቃድ ይሰጥባቸው ከነበሩት ውስጥ የመጠጥ ውሃ ዝርጋታ፣ የዝናብ ውሃ ከድሬኔጅ መስመር ጋር ይገናኝልኝ ጥያቄ፣ የፍሳሽ መስመር ለማገናኘት፣ የመግቢያ መውጫ ይከፈትልንና ከመሰረተ ልማት ዘርጊ ተቋማት የሚቀርቡ የመንገድ መቁረጥ ፈቃድ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ባለስልጣኑ በክረምት የሚደረጉ ቁፋሮዎች በነዋሪው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ እክል እንዳይፈጥር፣ ከአደጋ ለመጠበቅና የትራፊክ ፍሰት እንዳይስተጓጎል የቁፋሮና የአስፋልት መቁረጥ ፍቃድ መስጠት እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ማቆሙን ገልጿል፡፡ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2012 በጀት ዓመት በቁጥር 443 የሚሆኑ ከተለያዩ አካላት የቀረቡለትን የመንገድ መቁረጥ ጥያቄ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡በተጨማሪም የመንገድ ሃብት ላይ ህገወጥ ድርጊቶችን በመፈጸም ጉዳት የሚያደርሱ አካላት ላይ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የመንገድ መብት ጥሰቶችና ጉዳቶች ለመከላከል የሚያስችል አሰራርን በመዘርጋት እየሰራ ይገኛል፡፡

ምንጭ: የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን
@YeneTube @FikerAssefa1
በአፍሪካ ህብረት የሚመራውና ለጊዜው ተቋርጦ የነበረው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ዛሬ ይቀጥላል!

በአፍሪካ ህብረት መሪነት ለ11 ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ ከሁለት ሳምንታት በፊት እ.አ.አ ሐምሌ 13/2020 የተቋረጠው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ከሳምንት በፊት ሊቀጥል የነበረ ቢሆንም በሱዳን በኩል በቀረበው ለአንድ ሳምንት የይዘግይልኝ ጥያቄ መሠረት ለአንድ ሳምንት ዘግይቷል፡፡ ከዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ለቀጣዩ አንድ ሳምንት ድርድሩ ይቀጥላል፡፡የዚህ ሳምንቱ ድርድር ቀደም ሲል ከተካሄደው የ11 ቀናቱ ድርድር በኋላ ለመሪዎች በቀረበው ሰነድ መሠረት መሪዎቹ ባስቀመጠጡት አቅጣጫ የሚቀጥል ሲሆን ኢትዮጵያ እንደ ከዚህ ቀደሙ ፍትሓዊና ምክንያታዊ ተጠቃሚነትን መሠረት ባደረገ ሁኔታ ሁሉንም ወገን ተጠቃሚ ባደረገ መልኩ ድርድሩን ለመቋጨት ትሠራለች፡፡

#MoWIEE
@YeneTube @FikerAssefa1
ኢ/ር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩን 2012 የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በመጠናቀቅ ላይ ያለውን አመት የተዛነፉ አሰራሮችን በማስተካከል እንዲሁም የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል ላይ አተኩሮ መንቀሳቀሱን ገልፀዋል ኢ/ር ታከለ ኡማ።የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መቅረፍ የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች በበጀት ዓመቱ መከናወናቸውንም ኢንጅነር ታከለ በሪፖርታቸው አስታውቀዋል፡፡ለአብነትም የሸገር ዳቦ ፣ እንሥራ የሸክላ ማዕከል፣ የሸማ ማዕከል፣ የተማሪዎች ምገባ፣ ዩኒፎርም እና የትምህርት ቁሳቁስ፣ የትምህርት ቤቶች እድሳት፣ የእንጦጦ እና የሸገር ማስዋብ ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ደረጃና ፍጥነት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል።

የኮሮና ቫይረስን ከመከላከል ጋር በተያያዘም በሰው ህይወት እና ኢኮኖሚ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ በሙሉ አቅም የተሰራበት ዓመት መሆኑን ኢ/ር ታከለ ገልጸዋል፡፡በከተማዋ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የአትክልት፣ ፍራፍሬ እና መሰል ሰብሎች ላይ በማተኮር በትምህርት ቤቶች፣ በመንግሥት ተቋማት እና በተለያዩ ክፍት ቦታዎች በ600 ሄ/ር ቦታ ላይ የከተማ ግብርና ላይ ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል።በተጨማሪም የመኖርያ ቤት ጥያቄ ለመመለስ በ20/80 እና 40/60 መርሃግብር በጠቅላላው 125 ሺህ የጋራ መኖርያ ቤቶች በግንባታ ላይ መሆናቸውን ኢ/ር ታከለ ገልጸዋል፡፡

በጋራ መኖርያ ቤቶች ግንባታ ሂደት ላይ የሚስተዋሉ ከባንክ ብድርና ከወሰን ማካለል ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮችን በአፋጣኝ በመፍታት የቤት ችግርን ለማቃለል በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።በተጨማሪም በአዲስ እና ነባር ስራ ፈላጊዎችን አጥርቶ በመመዝገብ በተደረገው ስራም ለ250 ሺህ በላይ ስራ ፈላጊዎች ሥራ ዕድል መፈጠሩን ኢ/ር ታከለ ኡማ በሪፖርታቸው አመልክተዋል፡፡በከተማዋ ስር ከሰደዱ ችግሮች መካከል አንዱ የትራንስፖርት አቅርቦት እና ስምሪት ችግር ነው ያሉት ኢ/ር ታከለ ችግሩን ለመፍታት የትራፊክ መቆጣጠሪያ ከመገንባት ጀምሮ የትራንስፖርት ስርአቱን ለማስተካከል በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጨምረው ገልጸዋል፡፡በዚህም መንገዶችን ለትራፊክ ፍሰት ምቹ እንዲሆኑ ለማድረግ ለዋና ዋና እንዲሁም ለመጋቢ መንገዶች ከፍተኛ መዋለ ንዋይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን ኢ/ር ታከለ ገልጸዋል፡፡

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa1
የዩኬ ዜጎች ከወትሮው በግማሽ ባነሰ ዋጋ ምግብ ሊበሉ ነው!

ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ያሉ የምግብ ቤት ተጠቃሚዎች ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ ከወትሮው ዋጋ ሃምስ በመቶ ቅናሽ ይደረግላቸዋል። ግማሹን ወጭ መንግሥት የሚሸፍን ሲሆን ዓላማውም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ አቅማቸው የተዳከመ ምግብ ቤቶችን መደገፍ ነው። የመንግሥት ድጎማ ተግባራዊ የሚሆንባቸው ከ72 ሺህ በላይ ምግብ ቤቶች ሲሆኑ ድጎማው ለአንድ ወር የሚቆይ ነው።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
በመጪዎቹ 10 ዓመታት የኢትዮጵያን የመንገድ ሽፋን ወደ 225 ሺህ ኪ.ሜ ለማሳደግ ታቅዷል!

በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ኢትዮጵያ አሁን ያላትን ከ140 ሺህ ኪ.ሜ ያልበለጠ የመንገድ ሽፋን ወደ 225 ሺህ ኪ.ሜ ለማሳደግ መታቀዱን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ገልጿል። ባለሥልጣኑ ይህን የገለጸው የትራንስፖርት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ላይ በቢሾፍቱ ከተማ እያካሄዱት ባሉት የውይይት መድረክ ላይ ነው።በዕቅዱ መሠረት ከ10 ዓመታት በኋላ ከመሃል ከተማ ተነስቶ ወደ የትኛውም የኢትዮጵያ ጫፎች ለመድረስ የአንድ ቀን ጉዞ ብቻ እንደሚጠይቅ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኘ፣ ሁሉም የወረዳ ማዕከላት በአስፋልት ይገናኛሉ ብለዋል።የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የትራንስፖርት ዘርፉን በ10 ዓመት ውስጥ ለማሳደግ በተያዘው ዕቅድ ቀጠናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ታሳቢ ተደርገው እንደተሠሩ ገልጸዋል።የኢቢሲ ዘገባ እንዳመለከተው ዕቅዱ ኢትዮጵያ አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን የሚያስችል መመሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ፣ ለዕቅዱ ትግበራ እና ስኬት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

@YeneTube @FikerAssefa1
ኢትዮጵያዊ ፕሮግራሞችን በአገራዊ ቋንቋ ለኢትዮጵያ ተመልካቾች ለማቅረብ ያቀደው ግዙፉ የፈረንሳይ ሚዲያ ተቋም ካናል ፕሉስ ግሩፕ በቀጣዩ መጋቢት ወደ ስርጭት እንደሚገባ አስታወቀ፡፡

ለክፍያ ስርጭቱ ኢትዮጵያዊ አጋር የሆኑት የብሩህ ኢንተርቴመንት ባለቤት አቶ ቴዎድሮስ አብርሃም እንደተናገሩት ስርጭት ሲጀመር 50 በሚሆኑ ቻናሎች ይጀመራል ብለዋል፡፡ከነዚህም መካከል አብዛኞቹ በአማርኛ ቋንቋ የሚተላለፉ ኢትዮጵያዊ ቻናሎች ናቸው ብለው፡፡ ቻናሎችን ለማስገባት ካሉ የሚዲያ ተቋማት፣ ከፊልም አዘጋጆች፣ ባለሞያዎች እና ሃሳብ ካላቸው ጋር በመነጋገር ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡የልጆች ቻናሎች፣ ፊልም፣ ዶክመንተሪ እና ሌሎች ቻናሎች እንደሚኖሩት የሚጠበቀው አዲስ የክፍያ ስርጭት፡፡ ስርጭቱን ተደራሽ ለማድረግ ዲኮደር እና ወርሃዊ ክፍያ እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ማጋ ይቀርባል ብለዋል አቶ ቴዎድሮስ፡፡

የሃይ ዴፍኔሽን ጥራት የሚኖራቸውን ስርጭቶች የጥራት ደረጃ ከመጠበቅ አንፃር ካናል ፕሉስ ግሩፕ በሌሎች አፍሪካ አገራት እንዳደረገው የአቅም ግንባታ እና የቴክኖሎጂ ድጋፍ ያደርጋል ያሉት የብሩህ ኢንተርቴመንት ባለቤት ይህም ከስርጭት ባለፈ ለዘርፉ እድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ የሚያደርግ ነው ሲሉ ይገልፃሉ፡፡አሁን ላይ በኢትዮጵያ ዲኤስ ቲቪ እና ሰታር ታይምስ የተባሉ የአሜሪካ እና ቻይና የክፍያ ቴሌቭዥን ስርጭቶች ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ሆኖም ኢትዮጵያዊ የሆነ ቻናል የላቸውም፡፡
እ.ኤ.አ ከ1997 አንስቶ ካናል ፕሉስ ግሩፕ ሲስኮም ኃ/ተ/ግ/ኩ ከተባለ የአገር ውስጥ ድርጅት ጋር በመሆን ካናል ፕሉስ ሆራይዘንስ ስርጭትን በክፍያ ለፈረንሳይና ተናጋሪዎች ያቀርብ ነበር፡፡ ሆኖም ካናል ፕሉስ ግሩፕ ትኩረቱን ወደ ፈረንሳይኛ ተናጋሪ አፍሪካ አገራት ትኩረቱን ለማድረግ በመወሰኑ ከኢትዮጵያ ወጥቶ ቆይቷል ሲሉ የሲስኮም ባለቤት ወ/ት ትእግስት ይልማ ያስታውሳሉ፡፡

#Capital
@YeneTube @FikerAssefa1