YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ሱዳን-ኢትዮጵያ በምዕራብ ጎንደር ዞን ኢትዮጵያን ከሱዳን በሚያዋስነው ደንበር አካባቢ በተከሰተው ግጭት በሰው ህይዎት እና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡

•የግጭቱ ምክንያትም የእርሻ መሬት ይገባኛል ጥያቄ መሆኑን ሰምተናል፡፡

•ሱዳንን ከኢትዮጵያ በሚያዋስነው የምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ አካባቢ በሚገኝ የኢትዮጵያ መሬት ላይ ሱዳኖች የይገባኛል ጥያቄ አንስተዋል፡፡

•የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘላለም ልጃለም እንደነገሩን መሬቱ የኢትዮጵያ ነዉ፤ ስለሆነም ሱዳኖች የሚያነሱት ጥያቄ ትክክል አይደለም፡፡

•ይሁን እንጅ የእርሻ ስራ በሚያከውኑ የአካባቢው የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ላይ ትንኮሳ በመፈጸማቸው ምክንያት ግጭቱ ተከስቷል፡፡

•የአካባቢው አርሶ አሮችም የመከላከል አጸፋ መውሰዳቸዉን አቶ ዘላለም ተናግረዋል፡፡

•አሁን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በቋራ እና መተማ ጥበቃ እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

•የዞኑ አስተዳዳሪ እና አርሶ አደሮቹ እንደነገሩን አሁን ላይ ግጭቱ የተረጋጋ ቢመስልም በሱዳን ወታደሮች ትንኮሳ ምክንያት በአካባቢዉ ባሉ ሌሎቹ የኢትዮጵያ መሬቶች ላይ የእርሻ ስራ ማከናወን አልተቻለም ፡፡

•በግጭቱ ምክንያት በመተማ ደለሎ በኩል የሚገኝ የሱዳን ጦር ተደምስሷል፤ አንድ የሱዳን ሻለቃ አመራር ህይዎቱ አልፏል፡፡

•በቋራ ነብስ ገበያ በኩል በተፈጠረው ግጭት ደግሞ 7 የሱዳን ወታደሮች ሞተዋል፤ 2 መኪና እና 7 የጦር መሳሪያዎችም ተማርከዋል፡፡

•ሶስት የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እና ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ህይዎታቸዉ ማለፉንም ሰምተናል፤ 6 ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዉ ሆስፒታል መግባታቸው ታዉቋል፡፡ ከነዚህ መካከል ሁለቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ናቸዉ፡፡

•በቋራ ነብስ ገበያ በኩል የይገባኛል ዉዝግብ ያስነሳዉ ቦታ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ከ1996 በፊት ጀምሮ በህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ የያዙት ነዉ ብለዋል አቶ ዘላለም፡

•ለጣምራ የጸጥታ ቁጥጥር በሚል በአካባቢዉ የሰፈረው የሱዳን ጦር በተለያዩ ጊዜያት ትንኮሳ እንደሚፈጽም የአካባቢው ነዋሪዎች እና ዋና አስተዳሪው አስረድተዋል፡፡

•በተደጋጋሚ በሰላማዊ መንገድ ቦታዉን ለቀው እንዲወጡ ጥረት ቢደረግም ፈቃደኛ አለመሆናቸዉንም ነግረዉናል ፡፡

ምንጭ፦አማሚ

@Yenetube @Fikerassefa
#ኢትዮጵያ እና #ሱዳን የድንበር ቁጥጥር የሚያደርግ ጥምር ጦር ለማስፈር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

የኢትዮጵያ እና የሱዳን ጦር በትናንትናው እለት በደረሱት ስምምነት መሰረት ሁለቱም ሀገራት በድንበር አቅራቢያ ያላቸውን የየራሳቸውን ጦር ከስፍራው ለማንሳት ተስማምተዋል።

በምትኩም ሽብርተኝነትን፣ ህገ ወጥ የሰው ዝውውርን እና ሌሎች በሀገራቱ ላይ የሚቃጡ የደህንነት ስጋቶችን የሚከላከል ጥምር ጦር ለማስፈር ከስምምነት ደርሰዋል።

©FBC
@YeneTube @Fikerassefa
ድምፃችን ለግድባችን #ሱዳን አብዬ ግዛት
Via:- በሱፍቃድ የኔቲዩብ
@Yenetube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ እና በጎረቤት ሀገሮች የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ -19) ወቅታዊ ሁኔታ

#ኢትዮጵያ

በበሽታው የተያዙ - 26,204
ህይወታቸው ያለፈ - 479

#ሱዳን
በበሽታው የተያዙ - 12,115
ህይወታቸው ያለፈ - 792

#ደቡብ ሱዳን

በበሽታው የተያዙ - 2,478
ህይወታቸው ያለፈ - 47

ኤርትራ
በበሽታው የተያዙ - 285
ህይወታቸው ያለፈ - 0

#ሶማሊያ

በበሽታው የተያዙ - 3,227
ህይወታቸው ያለፈ - 93

#ኬንያ

በበሽታው የተያዙ - 28,753
ህይወታቸው ያለፈ - 460
@Yenetube @Fikerassefa
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኤርትራ የሚገኘውን ጨምሮ አስር ኤምባሲዎችን ለመዝጋት ማቀዱ ተገለጸ

የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር #በኤርትራ እና ደቡብ #ሱዳን የሚገኙትን ጨምሮ 10 የአሜሪካ ኤምባሲዎችን ለመዝጋት ማቀዱ ተገለጸ።

ከኤምባሲዎቹ በተጨማሪ 17 ቆንስላዎቹንም ለመዝጋት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ማቀዱን ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ተመለከትኩት ያለው ያስተዳደሩን ማስታወሻ ዋቢ በማድረግ ባቀረበው ዘገባው ጠቁሟል።

የትራንፕ አስተዳደር እንዲዘጉ በሚል በእቅድ በያዛቸው ሀገራት ውስጥ በሚገኙ ኤምባሲዎች ይከናወኑ የነበሩ ስራዎች በአጎራባች ሀገራት ባሉ ኤምባሲዎች ለማከናወን ማቀዱንም ዘገባው አስታውቋል።

የኤምባሲዎቹ እና ቆንስላዎቹ መዘጋት የትራንፕ አስተዳደር የፌደራል መንግስትን ባጀት ለመቀነስ እየወሰደ ያለው እርምጃ አካል ነው ተብሏል።

የትራንፕ አስተዳደር ከሚዘጋቸው አስር ኤምባሲዎች መካከል ስድስቱ በአፍሪካ የሚገኙ መሆናቸውን ዘገባው አስታውቋል።

የአስተዳደሩ እቅድ ዩናይትድ ስቴትስ የነበራት የዲፕሎማሲ የበላይነት ያሳጣታል፣ ለቻይና አዲስ እድል ይፈጥርላታል የሚሉ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ እንደሚገኙም ዘገባው አመላክቷል።

እቅዱ ተግባራዊ ከሆነ ቻይና በአፍሪካ ያላትን የዲፕሎማሲ የበላይነት ይበልጥ ያጠናክርላታል መባሉን ዘገባው አካቷል።

ጋዜጣው በተጨማሪም በሶማሊያ ሞቃዲሾ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ካልሆነ ደግሞ በከፍተኛ ቁጥር ሰራተኞቹ እንዲቀነሱ ሃሳብ መቅረቡን አመላክቷል።


@Yenetube @Fikerassefa
👍141🔥1