ህዝበ ሙስሊሙ የአረፋ በአልን ሲያከብር ለኮሮና ቫይረስ በማያጋልጥ መልኩ ሊሆን እንደሚገባ የጤና ሚኒስተሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ሚኒስትሯ በነገው ዕለት የሚከበረውን ኢድአልድሃ (አረፋ) በዓል አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህዝበ መስሊሙ በቀደሙ በአላት ሲያከናውናቸው የነበሩ ማህበራዊ መስተጋብሮችን ማድረግ የማይችልበት መሆኑን ሚኒስተሯ አንስተዋል፡፡ህዝበ ሙስሊሙ የአረፋ በአልን ሲያከብር ለኮሮና ቫይረስ በማያጋልጥ መልኩ ሊሆን እንደሚገባ የጤና ሚኒስተሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ጥሪ ማቅረባቸውን አዲስ ሚድያ ኔትዎርክ ዘግቧል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa1

የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒሰቴር ፈጣንና ወቅታዊ ድጋፍ አስረከበ፡፡
ሚኒስቴር መ/ቤቱ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አንዳንድ ቦታዎች በተነሳዉ ሁከት ቤት ንብረታቸዉ ለወደመባቸዉ ወገኖች የሚዉል ድጋፍ በትናትናዉ ዕለት በባቱ(ዝዋይ) በመገኘት አስረክቧል፡፡ድጋፉን በከተማዋ በመገነኘት ያስረከቡት የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒሰቴር ሚንስትር ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ ናቸው።በዕለቱም ግምታቸዉ ከ620,000 ብር በላይ የሚገመት በግ፣ ሩዝ፣ የህጻናት ወተት፣ አልሚ ምግቦች፣ ዱቄት፣ ፓስታና አልባሳት ቁጥራቸዉ ከ75 ለሚሆኑ አባወራዎች ድጋፍ እንደተደረገ ታዉቋል፡፡ 12 በጎች በአዲስ አበባ ከሚገኙ ከሱማሌ ከልል ተወላጅ ሴት ነጋዴዎች ማህበር በዛሬዉ የሚከበረዉን የአረፋ በዓል በማስመልከት የተደረገ ድጋፍ ሲሆን፣ ሌሎች ድጋፎች ከአክሽን ኤይድ ኢትዮጵያ እና ከሜሪ ጆይ ተገኝተዋል፡፡
ምንጭ: የሴቶች ህፃናትን ወጣቶች ሚኒስቴር

ግንባታው የተጓተተው የነቀምቴ-ቡሬ መንገድ ለቻይናው ቾንግኪንግ ኢንተርናሽናል የግንባታ ተቋራጭ ተሰጠ። ይህ የተደረገው ግንባታውን በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ እያካሄደ ባለመሆኑ IL & FS Transportation Network and Eslamex ከተባለው የስፔን ተቋራጭ ጋር የነበረውን ኮንትራት በማቋረጥ መሆኑን ፎርቹን ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa1
@YeneTube @FikerAssefa1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኬንያ በረራ ሊጀምር ነው!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት አቋርጦ የነበረውን በረራ እ.ኤ.አ ኦገስት 1 ቀን 2020 (ሀምሌ 25 ቀን 2012 ዓ.ም) ጀምሮ ወደ ኬንያ ናይሮቢና ሞምባሳ ከተሞች በረራውን ይቀጥላል።ተጓዦች ኬንያ ሲደርሱ ከ96 ሰዓት ወይም 4 ቀን ያልበለጠው ከኮሮና ቫይረስ ነጻ ወረቀት ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን፤ ይህንኑ ያሟሉ እና የሙቀት መጠናቸው ከ37.5°C ያልበለጠ እንዲሁም የመተንፈስ ችግር የሌለባቸው መንገደኞች ወደ ማግለያ ጣቢያ እንዲገቡ የማይገደዱ ይሆናሉ።ኬንያ ከኢትዮጵያ፣ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን፣ ካናዳ፣ ዚምባብዌ፣ ስዊዘርላንድ፣ ሩዋንዳ፣ ዩጋንዳ፣ ሞሮኮና ናሚቢያ የሚነሱ ተሳፋሪዎች ወደ አገሯ እንዲገቡ ፈቅዳለች።
ምንጭ: በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እናቶችን ልጆቻቸውን ጡት ከማጥባት እንደማያግዳቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
28ኛው ዓለም ዓቀፍ ጡት የማጥባት ቀን ከሐምሌ 25 እስከ ነሐሴ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ”ለአገር ጤና ጡት ማጥባትን እንደግፍ” በሚል መሪ ሃሳብ ይከበራል።በጉዳዩ ላይ ለጋዜጠኞች የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ያዘጋጀው የጤና ሚኒስቴር በዓሉ በኢትዮጵያ ለ12ኛ ጊዜ እንደሚከበር አስታውቋል።የሚኒስቴሩ የእናቶችና ሕፃናት ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት ዘላለም አንዳንድ እናቶች በኮሮና ቫይረስ ስጋት ሳቢያ ለልጆቻቸው የቆርቆሮ ወተት እያጠጡ መሆኑን ተናግረዋል።ነገር ግን እስካሁን ድረስ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት እናቶች ልጆቻቸውን እንዳያጠቡ የሚል ጥናት አልተካሔደም ነው ያሉት።በመሆኑም እናቶች ከጤና ባለሙያዎች የሚሰጡ ምክሮችን በአግባቡ በመተግበር ልጆቻቸውን ያለተጨማሪ ምግብ ለስድስት ወራት ጡት ማጥባት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
#ENA

የዚምባብዌ ሚኒስትር በኮሮናቫይረስ ሕይወታቸው አለፈ!
የዚምባብዌ የግብርና ሚኒስትር ፔሬንስ ሺሪ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ገልፀዋል።ሚኒስትሩ በኮሮናቫይረስ መሞታቸው የተረጋገጠው በምርመራ መሆኑንም የአገሪቱ መንግሥታዊ ጋዜጣ ሄራልድ ፕሬዚዳንቱን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።ሚኒስትሩ የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት በሚያዘው በኮሮናቫይረስ ለሞቱ ሰዎች የሚደረገው የቀብር ስነ ስርዓት መመሪያ መሰረት በነገው እለት እንደሚቀበሩም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።የ65 አመቱ ሚኒስትር በመዲናዋ ሃራሬ በሚገኝ የግል ሆስፒታል ረቡዕ እለት ሕይወታቸው ማለፉ ተዘግቧል።
#BBC

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 915 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል!
ባለፉት 24 ሰአታት ለ8957 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 915 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡ዶክተር ሊያ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት 24 ሰአታት የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል፡፡187 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 17,530፣ ያገገሙት 6950፣ የሟቾች ቁጥር 274 ፣በፅኑ ህክምና ክፍል ያሉ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 138 ደርሷል።

የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራር ልደቱ አያሌው ጤንነታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ እንደሆነ ፓርቲው በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡
በቢሾፍቱ ከተማ መርማሪያቸው ፖሊስ ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መስማታቸውን ልደቱ ተናግረዋል ተብሏል፡፡ ልደቱ የአስም በሽተኛ ሲሆኑ፣ አምና ደሞ የልብ ቀዶ ሕክምና አድርገዋል፡፡ ይሄ ሁኔታ ይበልጥ ለኮሮና ቫይረስ ያጋልጣቸዋል- ብሏል ፓርቲው፡፡ እናም መንግሥት ወደ አዲስ አበባ እንዲያዛውራቸው፤ ይህ ካልሆነ ግን በታሳሪው ሕይወት ላይ ለሚደርስ አደጋ መንግሥት ተጠያቂ እንደሚሆን ፓርቲው አስጠንቅቋል፡፡
#Wazema

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከደቡብ ክልል አራት ዞኖች አመራሮች ጋር ሊወያዩ ነው!
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከደቡብ ክልል አራት ዞኖች አመራሮች ጋር ነገ ቅዳሜ ሐምሌ 25፤ 2012 ዕለት እንደሚወያዩ ምንጮቹን ጠቅሶ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።ውይይቱ፤ ከክልል አደረጃጀት ጋር በተያያዘ በወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ እና ዳውሮ ዞኖች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለማርገብ ያለመ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል።በውይይቱ ላይ እንዲገኙ ለአራቱም ዞኖች አስተዳዳሪዎች እና የድርጅት አመራሮች ጥሪ እንደተላለፈ ምንጮች ገልጸዋል። የስብሰባው ዋና አጀንዳ “የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ማጠናከር ነው” የተባለ ሲሆን በውይይቱ ላይ “የደቡብ ክልል አወቃቀር ጉዳይ በተጨማሪ አጀንዳነት ሊቀርብ ይችላል” ተብሏል።
Via Ethiopia Insider

በድሬዳዋ ከተማ አሽከርካሪዎች ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በማስታከክ ከትራፊክ ፖሊሶችና የፀጥታ አካላት እንግልት እየደረሰብን ነው ሲሉ ለየኔቲዩብ ቅሬታቸውን አሰሙ።
ቅሬታቸውን የነገሩን አሽከርካሪዎች እንዳሉን በከተማዋ እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት አገልግሎት መስጠት እንደምንችል የታወቀ ቢሆንም የተቀመጠው ሰአት ሳይደርስ ይዘውን እየቀጡን ለአላስፈላጊ ወጪ እየዳረጉን ነው ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከአድማ ብተና ጋር በመሆን በፍተሻ ሰበብ ድብደባ ይደርስብናልም ብለዋል። ይህ ጫና በዋናነት የሚደርሰው በባለ3 እግር ተሽከርካሪዎች ላይ እንደሆነ የነገሩን ሲሆን የእለት ተዕለት ስራቸውን ለማከናወን ትልቅ እንቅፋት እንደፈጠረባቸው ነግረውናል።እኛም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም ለመገምገም የተቋቋመው ኮሚቴም ሆነ ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ጉዳዩን እንዲያጣራና ማስተካከያ እንዲወስድ ስንል እንጠይቃለን።

በአማራ ክልል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መጠቀም አስገዳጅ እንደሚሆን የክልሉ የኮሮና ቫይረስ መከላከልና መቆጣጠር ግብረ ኃይል አስታውቋል።
የአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስ መከላከልና መቆጣጠር ግብረ ኃይል ሰብሳቢ ዶክተር ሙሉነሽ አበበ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መልበስ ግዴታ ሆኗል ብለዋል።የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በሀገሪቱ እና በክልሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የገለፁት ዶክተር ሙሉነሽ ማኅበረሰቡ በአንፃሩ በአሳሳቢ ደረጃ እየተዘናጋ መሆኑን ነው ያነሱት።በክልሉ ያለው የኮሮና ቫይረስ መከላከልና መቆጣጠር ዋጋ በሚያስከፍል ሁኔታ እንደተፋዘዘም ተናግረዋል። "ከበሽታው መራቅ ሲገባን ወደ በሽታው እየቀረብን ነው" ያሉት ዶክተር ሙሉነሽ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተከለከሉ መመሪያዎች እየተጣሱ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ከመልበስ ይልቅ አለመልበስ እየተበራከተ መሆኑንም አመላክተዋል። በባሕርዳር ከተማ አስተዳደር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል መልበስ አስገዳጅ መሆኑን ያስታወሱት ዶክተር ሙሉነሽ መግለጫው ከተሰጠበት ከዛሬ ሐምሌ 24/2012 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ መልበስ ግዴታ መሆኑንም አስታውቀዋል። የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ባላደረገ ሰው ላይ እርምጃ እንደሚወሰድም ተናግረዋል።የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሚያዚያ 12 ቀን 2012 ዓ.ም የወጣውን አዋጅ በትኩረት መተግበር እንደሚገባም አሳስበዋል።የፀጥታ አካለትም ተግባራዊነቱን አስገዳጅ እንዲያደርጉት መልዕክት አስተላልፈዋል።
#AMMA

Audio
ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ከ2 ሺህ በላይ ሰው አካባቢውን ለቅቆ መውጣቱ ተገለፀ!
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጉባ ወረዳ አልመሀል ቀበሌ ውስጥ የሚኖሩ የአማራ ብሄር ተወላጆች በማንነታችው ላይ ያተኮረ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ተናግረዋል።የቀበሌዋ ነዋሪዎች ከትናንት በስቲያ ከረፋዱ 5 ሠዓት ላይ በእርሻ ማሳዎቻችው ላይ እንዳሉ የታጠቁ ሰዎች ጥቃት ሊያደርሱባቸው ሲሉ ሸሽተው እንዳመለጡና ታጣቂዎቹ ንብረታቸውን በእሳት እንዳወደሙባቸው ገልፀዋል።ከሁለት ሺህ በላይ ሰው አካባቢውን ለቅቆ ለመውጣት መገደዱን አመልክተዋል።የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አስተዳደርና የፀጥታ ጉዳዮች ምክትል ቢሮ ኃላፊ ስለጥቃቱ መረጃ አልደረሰኝም ብሏል።የድምፅ ዘገባው ከላይ ተያይዟል።
#VoA

ቲክቶክ በአሜሪካ ሊታገድ መሆኑን ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ!
ቲክቶክ የተባለው ማዕከሉን ቻይና ያደረገው የተንቀሳቃሽ ምስል ማጋሪያ ማህበራዊ ሚድያ በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ተጠቃሚዎችን ማግኘት የቻለ መሆኑ ይታወቃል።ነገር ግን ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ ሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት የቻይና መንግሥት ለስለላ ይጠቀምበታል የሚል ስጋት ስላደረባቸው በተቻለ ፍጥነት ከዛሬ (ቅዳሜ) ጀምሮ ለማገድ ማቀዳቸውን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል። ቲክቶክ ግን ከቻይና መንግስት ጋር ሚያነካካኝ ምንም ነገር የለም ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
ምንጭ:አጃንስ ፍራንስ ፕረስ
@YeneTube @FikerAssefa

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ድጋፍና ትብብር ያዘጋጀውን አሰራሩን ለማዘመን የሚያስችል የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት መመሪያ ማክሰኞ ሐምሌ 28 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር አዳራሽ ያስመርቃል፡፡በተጨማሪም በዕለቱ የከፍተኛ ትምህርትን በኢንተርኔት መስመር ኦንላይን (Online) ለመስጠት የተዘጋጀ መመሪያ ይፋ ይደረጋል፡፡
#MoSHE
@YeneTube @FikerAssefa1
#MoSHE
@YeneTube @FikerAssefa1
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት መምህራንና ተመራማሪዎች የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ።
ዩኒቨርሲቲው በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሰጠው ለፕሮፌሰር አሰፋ አባሁና እና ለፕሮፌሰር አማን ደቀቦ ነው።አሁን ሙሉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው ምሁራን በረጅም ጊዜ ማስተማር፣ ጥናትና ምርምሮቻቸውን በዓለም አቀፍ ጆርናሎች በማሳተምና በማህበረሰብ አገልግሎት አበርክቶዎቻቸው ማዕረጉ እንደተሰጣቸው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ለሚ ጉታ ተናግረዋል።
#FBC

የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ከ1 ሺህ በላይ ተማሪዎቹን አስመረቀ ::
የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰተማራቸውን ከ1 ሺህ በላይ የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎቹን በኢንተርኔት በተካሄደ የቀጥታ ሥርጭት (በቨርቹዋል ) ዛሬ አስመርቋል። ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ዲግሪ 685 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ከእነዚህም 418 ሴቶች እና 267 ወንዶች ናቸው። በሁለተኛ ዲግሪ ደግሞ 317 ተማሪዎችን አስመርቋል ፤ ከእነዚህ መካከል 76ቱ ሴቶች ሲሆኑ 241ዱ ደግሞ ወንዶች ናቸው።
በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ በተደረገው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ብርሃነ መስቀል ቀና እንዲሁም 50 ተማሪዎች ተሳትፈዋል።
ሌሎች ተመራቂ ተማሪዎቹ የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱን በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ እና በፌስቡክ ቀጥታ ሥርጭት ተከታትለዋል።ዩኒቨርሲቲው ዘንድሮ እስከ 3 ሺህ የሚደርሱ ተማሪዎችን የሚያስመርቅ የነበረ ቢሆንም በኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ምክንያት የተመራቂዎቹን ቁጥር ለመቀነስ መገደዱ በዝግጅቱ ላይ ተገልጻል።
ምንጭ: የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

ከቀናት በፊት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ ጃዲያ ቀበሌ ጥቃት በመፈጸም የ14 ዜጎችን ህይዎት ያጠፉ ታጣቂዎች እጃቸው እየሰጡ መሆናቸውን፣ እጅ ለመስጠት ፍቃደኛ ያልሆኑት እየተደመሰሱ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታወቀ።ቀሪዎችን ለመያዝ በመከላከያ ሰራዊትና በፀረ ሽምቅ ሀይል የተጀመረው "ኦፕሬሽን" መቀጠሉንም ክልሉ ገልጿል። ወንጀለኞች በቁጥጥር ሥር ሳይውሉ ወደሌላ ሥራ መሠማራት እንደማይቻል የክልሉ መንግሥት አቋም መውሰዱም ተነግሯል።
Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa1
Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa1
በፍርድ ቤት ውሎ ዘገባ ህብረተሰቡ ተገቢና ሚዛናዊ መረጃ ሊቀርብለት እንደሚገባ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ገለፁ።
የችሎት ዘገባ የሙያ ስነምግባርን እና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ለማስቻል በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ÷ የፍርድ ቤቶችን ነጻና ገለልተኛነት ያላማከለ፣ የተጠርጣሪዎችን ንጹህ ሆኖ የመገመት መብትን የሚጋፉ የችሎት ዘገባዎች በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን እየቀረቡ መሆኑን ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ ሰለሞን አረጋ ተናግረዋል።ዛሬ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዘጋጅነት ከመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ጋር በተደረገ ውይይት÷ ከኢትዮጵያ ህግ አንጻር የሚገደቡና የማይገደቡ የችሎት ውሎ ዘገባዎች ምን መምሰል አለባቸው በሚለው ጉዳይ ላይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት እና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ቃል አቀባይ አቶ ተስፋዬ ነዋይ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል።
በዚህ ጥናታዊ ጽሁፋቸው ተጠርጣሪዎችን ወንጀል እንደፈጸሙ አድርገው የሚዘግቡ አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን እንዳሉ አመላክተዋል።ይሁንና በሚዘገቡ የፍርድ ቤት ዘገባዎች ላይ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሀገርን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ እና መሰል ዘገባዎችን ከማስተላለፍ መቆጠብና በጥንቃቄ ሊዘገብ እንደሚገባ ተገልጿል።ከዚያም ባለፈ ዘገባዎች ፍሬ ነገርን የማያዛባ የዳኝነት አካሉን ተጽኖ ስር የማይከቱ ሊሆኑ እንደሚገባቸው ተጠቅሷል።ይሁንና በአንዳንዶች በኩል ተጠርጣሪዎች የሚናገሩትን ብቻ የሚዘግብ ሚዲያ ሚዛናዊነት የሚጎለው እንደሆነ የገለጹት አቶ ተስፋዬ በተቻለ መጠን የሁሉም አካል በሚዛናዊነት ሊካተት እንደሚገባ ጠቅሰዋል። በውይይቱ ላይ የተጠያቂነት ደረጃዎች እስከምን ድረስ የሚለውም የተነሳ ሲሆን÷በሚቀርቡ ሚዛናዊ ባልሆኑ ዘገባዎች ላይ ተጠያቂነት ማስፈን እንደሚገባ ተጠቅሷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በካቢኔው የቀረበለትን የ61 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ሐምሌ 27 እና 28 ቀን 2012 ዓ.ም በሚያካሂደው 7ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባው በካቢኔው የቀረበለትን የ61 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ለሁለት ቀናት የሚካሄደው ስብሰባው በአምስት አጀንዳዎች ላይ የሚያተኩር መሆኑን የምክር ቤቱ የፕሬስ እና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አዲስዓለም እንቻለው አስታውቀዋል።የከተማ አስተዳደሩ የ2012 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ዋና ዋና ዕቅዶች በምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ አማካኝነት ይቀርባሉ፤ ውይይትም ይካሄድባቸዋል።
የ2012 ዓ.ም የኦዲት ሪፖርት በከተማ አስተዳደሩ ዋና ኦዲተር ቀርቦም ውይይት ይደረግበታል።ሌላው የስብሰባው አጀንዳ በከተማ አስተዳደሩ የ2013 ዓ.ም ረቂቅ በጀት ላይ መወያየት እና ማጽደቅ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የ61 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ ለምክር ቤቱ መምራቱንም አቶ አዲስዓለም ገልጸዋል።ምክር ቤቱ በከተማዋ የሚገኙ ፍርድ ቤቶችን የ2012 ዓ.ም አፈጻጸም በማድመጥ እንደሚወያይ ይጠበቃል።በምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ አማካኝነት ልዩ ልዩ አጀንዳዎች በሚል በሚቀርቡ ጉዳዮች ላይ የሚደረገው ውይይት የምክር ቤቱ ስብሰባ የመጨረሻ አጀንዳ እንደሚሆንም ዳይሬክተሩ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በ750 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የፌዴራል ዳኞች የጋራ መኖሪያ ቤት ተመረቀ!
በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የፌዴራል መንግስት ህንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በ750 ሚሊዮን ብር ወጪ ተገንብቶ የተጠናቀቀው የፌዴራል ዳኞች የጋራ መኖሪያ ቤት ተመርቋል።በምርቃት ስነ-ስርአቱ ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የጋራ መኖሪያ ቤቱን ቁልፍ ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሯ ኢ/ር አይሻ መሀመድ ተረክበዋል።ግንባታው ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተይዞለት የተጀመረ ቢሆንም ከታሰበለት በታች 750 ሚሊዮን ብር ባልበለጠ በጀት ለማጠናቀቅ እንደተቻለ ተነግሯል፡፡በዛሬው ዕለት 80 ቤቶች የተላለፉ ሲሆን የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ግንባታ ፕሮጀክት በልዩ ልዩ ምክንያቶች መጠናቀቅ ከነበረበት ጊዜ ዘግይቶ የተጠናቀቀ ቢሆንም በጥራትና በበጀት አፈፃፀም በኩል በስኬት የተጠናቀቀ ነው ማለታቸውን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በማህበራዊ ገጹ ዘግቧል፡፡
#ETV