YeneTube
120K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.84K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
"በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት ያደረሰው ታጣቂ ኃይል በህውሓት ስልጠናና የገንዘብ ድጋፍ ያገኙ ነበር።"
-አቶ አገኘሁ ተሻገር

በ አማራ ብ/ክ/መ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈትቤት ኃላፊ አቶ አገኘው ተሻገር በጥቃቱ ዙሪያ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ጥቃቱን የፈጸመው ኃይል በአካባቢው የብሔር ግጭት የመቀስቀስ ዓላማ በመያዝ ተደጋጋሚ የጥፋት ሙከራ ሲያደርግ የቆየ ነው።ታጣቂ ኃይሉ በህውሓት የስልጠናና የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግለት አመልክተው፤ "ህውሓት ሀገርን ለማተራመስ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ አካል ነው" ብለዋል።ድርጊቱ ከተፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ አጥፊዎችን ፈልጎ ለመያዝና አስፈላጊውን ዕርምጃ ለመውሰድ የፀጥታ መዋቅሩ የተጠናከረ ጥረት እያደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል ።በአሁኑ ጊዜም አካባቢው ላይ ሰላም ሰፍኗል።አርሶአደሩም የእርሻ ሥራውን በማከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል።

ምንጭ: ኢፕድ
Photo: AMMA
@YeneTube @FikerAssefa1
የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ለ2013 ዕቅድ ማስፈጸሚያ 3 ነጥብ 377 ቢሊዮን ብር በጀትና የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ!

በክልሉ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ውጤታማ በማድረግ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላት ጠንክረው እንዲሰሩም የምክር ቤቱ አፈጉባኤ አቶ ላክደር ላክባክ ጠይቀዋል።ጉባኤው በሁለት ቀናት ቆይታው በክልሉ የ2012 የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንዲሁም የጠቅላይ ፍርድ ቤትና የኦዲት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ አጽድቋል።

#ENA
@YeneTube @FikerAssefa1
በዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር 4.1 ቢሊዮን ችግኞች ተተክለዋል ተባለ!

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ለመትከል ከተያዘው 5 ቢሊዮን ችግኞች ውስጥ እስካሁን 4.1 ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን ዛሬ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ባቀረቡት ሪፖርት እስካሁን የተተከለው ችግኝ ከዕቅዱ ውስጥ 83 በመቶ መሆኑን ገልጸዋል።በዚህ መርሐ-ግብር የደቡብ ክልል እና የቤኒሻንጉል ክልል ከዕቅዳቸው በላይ ያሳኩ መሆኑን አቶ ዑመር ተናግረዋል።

ምንጭ: ኢቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa1
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በእስር ላይ የነበሩ 5 የህወሓት አመራሮችን በዋስ እንዲለቀቁ ወሰነ!

የአመራሮቹ ጠበቃ ታደለ ገ/መድህን ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገረው የአቃቂ ክፍለ ከተማ የደህንነት ቢሮ ሃላፊና የመረጃና ደህንነት ኤጀንሲ(INSA) ሰራተኛ የነበሩት አቶ አፅበሃ አለማየሁ በ6,000 ብር ዋስ እዲለቀቁ ተበይኗል። እንዲሁም አቶ ተወልደ ገ/ፃድቃን (የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የአዲስ አበባ ቅ/ዋ/አስተባባሪ) እና አቶ ተስፋለም ይህደጎን (የፌዴራል ህግና ፍትህ ጥናት ኢንስቲትዩት ሃላፊና የቀድሞ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል) ጨምሮ 4 አመራሮችን በ5,000 ብር ዋስትና እዲለቀቁ መወሰኑን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2012 በጀት ዓመት 40.2 ሚሊዮን ብር በጀት በመመደብ 6309 የመንገድ መብራት ምሰሶዎች አዲስ ተከላ እና ጥገና እንዲሁም 4,864 አምፖሎች የመቀየር ስራ አከናውኛለው ብሏል፡፡

የጥገና ስራው በተሽከርካሪ አደጋ ግጭት ምክንያት ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ ምሰሶዎችን በሌላ መተካት' የተበጣጠሱ የመንገድ መብራት ኬብል መቀየር፣ በረጅም ጊዜ አገልግሎት በመስጠት ለብልሽት የተዳረጉትን የመጠገን እና ሌሎች ተዛማጅ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡በተጨማሪም የመንገድ ዳር መብራት ችግር በስፋት የሚታይባቸውና ከህብረተሰቡ ተደጋጋሚ ጥያቄ የቀረበባቸውን አካባቢዎች በተለይም የቀለበት መንገድ ላይ በስፋት የጥገና ስራ ተከናውኗል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተቋራጮች አስገንብቶ በበጀት ዓመቱ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት በሆኑት አምስት መንገዶች ላይ 982 የመንገድ መብራት ተከላ ስራ ተከናውኗል፡፡ እነዚህ የመንገድ ዳር መብራቶች አብዛኞቹ ስራ የጀመሩ ሲሆን የተወሰኑት በቅርቡ የኤሌክትሪክ ሀይል ተለቆላቸው ስራ የሚጀምሩ ይሆናሉ፡፡
በበጀት ዓመቱ የመንገድ ዳር መብራቶችን ከዘመኑ ጋር አብሮ ለማሳደግና ለማሻሻል፣ የትራፊክ እንቅስቃሴን ለማሳለጥና ለከተማዋ ውበት አስተዋፅኦ ባላቸው ሀይል ቆጣቢ ኤል.ኢ.ዲ (LED) መብራቶች ነባሮቹን የመቀየር እና አዲስ በሚገነቡ መንገዶች ላይ የመትከል ስራዎች ተከናውኗል፡፡

ምንጭ:የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን
@YeneTube @FikerAssefa1
በፎገራ ወረዳ የጎርፍ አደጋው ቢቀንስም ስጋቱ እንደቀጠለ ነው ተባለ፡፡

በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ ትናንት የተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅ በተወሰነ ደረጃ ቢቀንስም ስጋቱ ግን እንደቀጠለ ነው፡፡ በፎገራ እና ሊቦከምከም ወረዳዎች የርብ ወንዝ ከመጠን በላይ ሞልቶ በዘጠኝ ቀበሌዎች ላይ የጎርፍ መጥለቅለቅ ተከስቷል፡፡የፎገራ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አለባቸው ደጀን እንዳሉት ከሰዓት በኋላ የጎርፉ መጠን ቀንሶ ተሽከርካሪዎች ተንቀሳቅሰዋል፡፡ የየአካባቢው ነዋሪዎችም ወደየቤታቸው ተመልሰው ገብተዋል፡፡ መጠኑ ምን ያህል እንደሆነ ባይታወቅም በሰዎች ቀለብ ላይ ጉዳት እንዳደረሰም ምክትል አስተዳዳሪው አስታውቀዋል፡፡ ወንዙ እንደሞላ በመሆኑ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርስም ሥጋት አለ፡፡ ቀደም ብሎ የጎርፍ አደጋን ለመከላከል በመሠራቱ ከዚህ በላይ ይደርስ የነበረውን አደጋ ማስቀረት እንደተቻለ የተናገሩት አቶ አለባቸው በአፋጣኝ የማስተካከል ሥራ ካልተሠራ ስጋቱ ሊያሻቅብ እንደሚችል አስታውቀዋል፡፡

#AMMA
@YeneTube @FikerAssefa1
በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ የመሬት መንሸራተት/ ናዳ/ ተከስቶ ከ70 በላይ አርሶአደሮች ከቤትና ንብረታቸው ተፈናቀሉ።

የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ጽ/ቤት እንዳስታወቀው በዘንድሮው ዓመት እየጣለ ባለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በርካታ የህብረተሰብ ክፍል ለዚህ ዓይነት አደጋ ተጋላጭ መሆናቸውን ተናግረው አሁን ላይ ጉዳት የደረሰባቸውን አርሶ አደሮች በመለየት ጊዜያዊ መጠለያ እንዲቆዩ መደረጉን አስታውቀዋል። አርሶአደሮች በመንግሥት ትምህርት ቤት ፣ በቀበሌ ጽ/ቤቶች እና ግለሰቦች ጋር ተጠልለው ህይወታቸውን አንዲታደጉ እየተደረገ ያለ ሲሆን በዘላቂነት እነዚህን ተፈናቃዮች ጨምሮ ስጋት ያሉትን ለማስነሳትና ተለዋጭ ቦታ ላይ ለማስፈር ከወረዳው መንግሥት አቅም በላይ ሊሆን ስለሚችል የሚመለከተው ሁሉ የሰው ህይወት የማትረፍ ስራን እንዲተባበር ተጠይቋል።

ምንጭ: የወረዳው መንግሥት ኮምኒኬሽን
@YeneTube @FikerAssefa1
በአማራ ክልል 1 ሺህ 244 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ ተለቀቁ!

በአማራ ክልል 1 ሺህ 244 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ መለቀቃቸውን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ። የአቃቤ ሕጉ ህዝብ ግንኙነት ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አለምሸት ምህረቴ ለኢዜአ እንደገለጹት የህግ ታራሚዎቹ በይቅርታ የተለቀቁት ከሐምሌ 21/2012 ዓ.ም ጀምሮ ነው።ይቅርታ የተደረላቸውም በመደበኛው የይቅርታ አዋጅ ቁጥር 136/1998 መሰረት እና በልዩ ይቅርታ ቦርድ ጉዳያቸው ተጣርቶ የቀረቡ ናቸው ብለዋል።
የዕድሉ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከልም ዕድሜያቸው የገፋ፣ የጤና ችግር ያለባቸው፣ አንድ ሶስተኛውን እስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁና የባህሪ ለውጥ ያመጡ ይገኙበታል።በይቅርታ ከተለቀቁት ውስጥ 22 ሴቶች መሆናቸውንም አመልክተዋል።

በሙስና ፣ በጠለፋና አስገድዶ መድፈር ወንጀል የተፈረደባቸው በይቅርታው አለመካተታቸውን ነው ኃላፊው ያሰረዱት።ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ የበደሉትን ህዝብ በልማት ለመካስ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው ያሳሰቡት ደግሞ የክልሉ ይቅርታ ቦርድ ጽህፈት ቤት ተወካይ ኃላፊ አቶ አምባው አስረስ ናቸው።ህብረተሰቡም በጥፋታቸው የተፀፀቱና ታርመው የተለቀቁ መሆኑን ተገንዝቦ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሊደግፋቸውና ሊያግዛቸው እንደሚገባም አመልክተዋል።በክልሉ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም መንግስት በልዩ ሁኔታ ባደረገው ይቅርታ ከ7 ሺህ የሚበልጡ የህግ ታራሚዎች እንዲለቀቁ መደረጉ ይታወቃል።

#ETV
@YeneTube @FikerAssefa1
ትራምፕ ምርጫው እንዲዘገይ ጠየቁ!

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዘንድሮው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲዘገይ ጥያቄ አቀረቡ።ፕሬዘዳንቱ ጥያቄውን ያቀረቡት በፖስታ የሚላኩ ድምጾች ላይ መጭበርበር መኖሩን የሚያሳይ መረጃ መኖሩን በማጣቀስ ቢሆንም፤ ስለዚህ ጉዳይ ምንም ማስረጃ የለም።የአሜሪካ ግዛቶች በፖስታ ድምጽ እንዲሰጥ የሚፈልጉት ማኅበረሰቡን ለኮቪድ-19 ላለማጋለጥ ነው።ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው፤ በፖስታ ድምጽ ቢሰጥ “በታሪካችን እጅግ የተሳሳተ እና የተጭበረበረ ምርጫ ይሆናል” ብለዋል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
በቤንሻንጉል ጉሙዙ ጥቃት የተጠረጠሩ 20 ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

ሐምሌ 20/2012 በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ ጥቃት የፈጸሙ 20 ታጣቂዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ።የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱላዚዝ መሃመድ በተለይ ለቢቢሲ እንደገለጹት ግለሰቦቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ትናንት ነው።እንደ ምክትል ቢሮ ኃላፊው ከሆነ ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ከመፈጸማቸው በፊት የመንግሥት የጸጥታ ኃይል እርምጃ እየወሰደባቸው ነበር።እርምጃውን ተከትሎ ተበታትነው በመንቀሳቀስ 13 ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸማቸውን ጠቁመዋል።

ከጥቃቱ በኋላ በተደረገ የክትትልና የቁጥጥር ሥራ 20 ሰዎች ትናንት መያዛቸውን አቶ አብዱላዚዝ አስታውቀዋል።ግለሰቦቹ ሲጠቀሙባቸው የነበሩ 12 መሣሪያዎችም መያዙን ነው የተናገሩት። በአሁኑ ጊዜ አካባቢው ወደ ሠላማዊ ሁኔታ መመለሱን የገለጹት አቶ አብዱላዚዝ የክልሉን የሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊን እና የክልሉን የፖሊስ ኮሚሽነር ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችም ወደ ቦታው በማቅናት ሕዝብን የማራጋጋት እና ችግር ፈጣሪዎቸን በቁጥጥር ስር እያዋሉ ነው ብለዋል።በጥቃቱ ላይ የተሳተፉ ሁሉም ተጠርጣሪዎች ስለመያዘቸው በተመለከተም፤ የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ እየሠራ መሆኑን ተናግረው በውጤቱ መሠረት ተጨማሪ ሰዎች በቁጥጥር ስር ሊውሉ ይችላሉ ብለዋል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
ዐለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይኦኤም 116 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው እንደመለሰ በትዊተር ገጹ አስፍሯል፡፡ ስደተኞቹ በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ በቀላሉ ወደ ሀገራቸው መመለስ ያልቻሉ ናቸው፡፡ ስደተኞቹን ወደ ሀገራቸው ማጓጓዝ የተቻለው፣ አይኦኤም ከአውሮፓ ኅብረት ባገኘው ድጋፍ ነው፡፡

#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1
የተለያዩ ባለሙያዎችን #ትብብር ስለመጠየቅ!

- በአቤሴሎም መለሰ
👇👇
#በዚህች_የበጎ_አድራጎት_ግሩፕ_ታሪክ_እንስራ!!

#የተከበራችሁ የምህንድስና ባለሙያዎች አርክቴክቶች እና ባለሀብቶች ። በአማራ ክልል ከፍተኛ የኩላሊት በሽታ እየተስፋፋ ህዝባችን አቅም(ገንዘብ) በማጣት እየሞቱ ይገኛሉ። ይህን ችግር ለመቅረፍ ዛሬ ከአማራ ክልል የኩላሊት ማህበር የበጎአድራጉት ስራ አስፈጻሚ ዶክተሮች ጋር ውይይት አድርገናል።
የስራ አስፈጻሚዎች ወደ ባህርዳር ከንቲባ ሄደው መሬት ጠይቀው ፕሮፖዛል አቅርቡ ተብለዋል።
👉ከምህንድስና አባላት ጋር እንድሰራ የተሰጠኝ የቤት ስራ ሁለት ሄክታር ለመቀበል
🙏
1. G+12 ሆስፒታል መነሻ ዲዛይን ቢያንስ 1500 - 2000ካሬ ላይ የሚያርፍ የስብሰባ ከአዳራሽ አስተዳደር ቢሮ የበሽተኛ ማረፊያ ያለው እና ሌሎችም

2. ዘመናዊ እንግዳ መቀበያ የ15 ሰው መኖሪያ ቤት ያካተተና ለሃምሳ ከፍተኛ ባለሙያዎች መኖሪያ ቤት አንድ G+6 ህንጻ 1000 ካሬ
3.የስልጠና ማእከላት ያለው የምርምር ቦታ የጂምናዚየም ማእከል ያለው G+3 2000ካሬ ላይ የሚያርፍ

4.ጊቢው ለህንጻ ፣ ለፓርኪንግ ለመወጫቻ እና ለአረንጓዴ ተክሎች የሚያስፈልጉትን Land Scape design የመሬት አጠቃቀም የሚገልጽ (Site plan) አይነት ፈልገዋል

ከኛ በፍላጎት የሚጠበቀው
👉የመጀመሪያውን ህንፃ ዲዛይን እና መነሻ ዋጋ ድራፍት በፈቃደኝነት ለፕሮፖዛል ማስገቢያ ሰርተን ብናግዛቸው
👉የመሬቱን አጠቃቀም የሚልገጽ site plan ብንሰራላቸው

ለህዝብ የሚጠቅም ስራ በግልም በጋራም ብንሰራ የሚኖረን እርካታ ከፍተኛ ነው።
የምትችሉትን በሙያ ስራ ለማገዝ ቃል ግቡልን

መሳተፍ የምትፈልጉ በሚከተለው Group በመግባት አስተዋጽኦ ማበርከት ትችላላችሁ👇👇👇

@bdkidney
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 805 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል!

ባለፉት 24 ሰአታት ለ9786 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 805 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡ዶክተር ሊያ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት 24 ሰአታት የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል፡፡78 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 16,615፣ ያገገሙት 6763፣ የሟቾች ቁጥር 263 ፣በፅኑ ህክምና ክፍል ያሉ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 134 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ቁጥር በ24 ሰአት ውስጥ በእጥፍ ጨመረ!

በትናንትናው የጤና ሚንስቴር እለታዊ ሪፖርት በቫይረሱ ተይዘው በፅኑ ህሙማን ማከሚያ ክፍል የነበሩ ሰዎች ቁጥር 66 የነበረ ሲሆን በዛሬው እለት ግን ከእጥፍ በላይ በመጨመር 134 መድረሱ አሳሳቢ ሆኗል። በሚቀጥሉት ቀናት ይህ ቁጥር እየጨመረ የሚመጣ ከሆነ የሟቾች ቁጥር አሁን ካለው በበለጠ ሊጨምር የሚችልበት እድል እየሰፋ ይሄዳል። ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር እስከዛሬ ከነበረው ሁሉ ትልቁ መሆኑን ሳንረሳ ማለት ነው።

#ለራሳችንና_ለምንወዳቸው_ስንል_እንጠንቀቅ !

@YeneTube @FikerAssefa1
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል መንግስትን አስጠነቀቀ!

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል መንግስት ምርጫ ለማካሄድ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ “በአፋጣኝ እንዲያቆም” አሳሰበ። ክልሉ “ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን አደጋ ላይ በሚጥል” ድርጊቱ የሚቀጥል ከሆነ፤ ምክር ቤቱ “በሕገ መንግስቱ እና ሌሎች ሕጎች የተሰጠውን ስልጣን ለመተግበር እንደሚገደድ” አስጠንቅቋል።ምክር ቤቱ ማስጠንቀቂያውን የሰጠው ለትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ከቀናት በፊት በላከው ደብዳቤ ነው። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተመልክቼዋለው እንዳለችው ባለ ሶስት ገጽ ደብዳቤ “የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ እንዲከበር ስለማሳሰብ” የሚል ርዕስ ይዟል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa1
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ድባቲ እና ቡለን ወረዳዎች ዉስጥ ሠላም ለማወክ ሞክረዋል ወይም ከሰላም አዋኪዎች ጋር ተባብረዋል የተባሉ 20 ሰዎች ታሰሩ።

የታሳሪ ቤተሰቦች እና የሁለቱ ወረዳዎች ነዋሪዎች እንደሚሉት ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት የኦነግ ሸኔ ከተባለዉ አማፂ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸዉ በሚል ነዉ። ከታሰሩት ሰዎች መካከል በመተከል ዞን የሚኖሩ አባገዳዎች ሰብሳቢ ደበሎ ሒካን፣ የሆቴል ባለቤቶችና ነጋዴዎች ይገኙበታል።ዶይቸ ቨለ ያነጋገራቸዉ፣ የመተከል ዞን አስተዳዳሪ አትንኩት ሽታዉ እንዳሉት ሰዎቹ የታሰሩት በአካባቢዉ ለሸመቁ ደፈጣ ተዋጊዎች የጦር መሳሪ፣ ስንቅና ከለላ ሰጥተዋል ተብለዉ የተጠረጠሩ ናቸዉ።የታሰሩትን ሰዎች ብዛት ግን አስተዳዳሪዉ «ጥቂት» ከማለት በስተቀር ትክክለኛ ቁጥራቸዉን መናገር አልፈቀዱም።በመተከል ዞን የጎሳ ልዩነትን መሠረት ያደረገ በሚመስል ተደጋጋሚ ጥቃት በየጊዜዉ ሰላማዊ ሰዎች ይገደላሉ።በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ብቻ ጉባ በተባለዉ ወረዳ ታጣቂዎች በትንሽ ግምት 13 ሰላማዊ ነዋሪዎች መግደላቸዉ ተዘግቧል።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
በትግራይ ክልል ምርጫ ለመወዳደር 5 የፖለቲካ ድርጅቶችና 11 የግል እጩዎች መመዝገባቸው የትግራይ ምርጫ ኮምሽን አስታወቀ፡፡ ምርጫ የሚደረግበት ዕለት በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግም ኮምሽኑ ጨምሮ ገልፆል፡፡

Via Million HaileSelasie
@YeneTube @FikerAssefa1
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አል አድሀ በአል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

ኢድ ሙባረክ!

@YeneTube
ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባ የታሳሪዎችና የቤተሰቦቻቸው የባንክ አካውንት መታገዱ ተሰማ!

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች እና የቤተሰብ አባላት የባንክ አካውንት እንዲታገድ በመደረጉ የቤተሰብ አባሎቻቸው ገንዘብ ማንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ለችግር መጋለጣቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።የተጠርጣሪዎች ጠበቃ በበኩላቸው የባንክ አካውንቶቹ እንዳይንቀሳቀሱ የተደረገው ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ነው በሚል ቅሬታ አሰምተዋል።የባንክ አካውንታቸው እንዳይንቀሳቀስ ከተደረገባቸው ሰዎች መካከል የአቶ ጃዋር መሐመድና ቤተሰባቸው፣ የአቶ በቀለ ገርባ እና የቤተሰባቸው እንዲሁም የጋዜጠኛ መለሰ ዲሪብሳ እና ባለቤቱ እንደሚገኙበት ተገልጿል።

የአቶ ጃዋር መሐመድ እህት የሆነችው ራዲያ ሲራጅ፤ የእሷን ጨምሮ የአምስተ ወንድሞቿ የባንክ አካውንቶች እንዳይንቀሳቀስ መደረጉን ለቢቢሲ ተናግራለች።"አጠቃላይ የስድስት ሰዎች አካውንትን ነው የተዘጋው። የእኔንም አካውንት ዘግቷል። የአዋሽ እና የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አካውንቶች ናቸው የተዘጉት። ለምን እንደተዘጋ ስንጠይቃቸው እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ ስልክ ተደውሎ ነው ዝጉ የተባልነው አሉን።የሚያደርጉትን ያድርጉት ብለን ትተነዋል" ብላለች። በተመሳሳይ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋዜጠኛ መለሰ ዲሪብሳ ባለቤት የሆነችው ታደለች መርጋ፤ የእርሷ እና የባለቤቷ የቁጠባ ሂሳብ እንዳይንቀሳቀስ መደረጉን ለቢቢሲ ተናግራለች።ታደለች በትናንትናው እለት የቤት ኪራይ ለመክፈል በማሰብ ገንዘብ ለማውጣት ወደ ባንክ መሄዷን ጠቅሳ ማውጣት እንደማትችል ከባንኩ ሠራተኞች ሲነገራት ለምን እንደሆነ መጠየቋን ገልጻለች።

ለተጨማሪ ንባብ👇👇👇

https://telegra.ph/Detainees-Bank-account-blocked-07-31
“አቶ ሽመልስና ብልፅግና ፓርቲያቸው የህዝብ ጥያቄ መመለስ ሲያቅታቸው ህወሓትን እየወነጀሉ ነው-“ አቶ ጌታቸው ረዳ

አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ፓርቲያቸው ብልፅግና የህዝብ ጥያቄ መመለስና ሰላም ማስፈን ሲያቅታቸው ህወሓትን እየወነጀሉ መቀጠልን መርጠዋል ብሏል የህወሓት ስራ አስፈፃሚ አባል ጌታቸው ረዳ። አቶ ጌታቸው ረዳ ከአቶ ሽመልስ አብዲሳ ለተነሳው ውንጀላ ትናንት በሰጠው ምላሽ፤ በጨፌ ኦሮሚያ ባደረጉት ንግግር በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ውስጥ እየተፈጠሩ ላሉት ችግሮችና በህዝቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሁሉ ህወሓትና ኦነግ-ሸኔን ተጠያቂ ናቸው ሲል መወንጀሉን ጠቅሷል።

አያይዞም “ከዚህ ቀደም ከተጠያቂነት ለማምለጥ ‘የህወሓት ተላላኪ ነበርን’ ሲሉ የነበሩት አቶ ሽመልስ አብዲሳ አሁንም ደግሞ “ህወሓት ኦሮሚያ ውስጥ በመለመላቸው ፈረሶች የሚፈጥረው ችግር እንደቀጠለ ነው የሚል አዲስ ለቅሶ ጀምሯል” ሲል ተናግሯል።አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ፓርቲያቸው ብልፅግና የህዝብ ጥያቄ መመለስና ሰላም ማስፈን ሲያቅታቸው ህወሓትን እየወነጀሉ መቀጠልን መርጠዋል ብለዋል።

“የኦሮሚያ ፈረስ ጋልበው የሚጠቀሙ ሰዎች ከነበሩ ከአሁን በፊት የመጀመሪያ ተጠያቂ ፈረስ ሆኖ ያገለገለው ሰው ነው ካለ በኋላ ለምሳሌ አቶ ሽመልስ የሚመሩት መንግስት ከአሁን በፊት እንደሚሉት ህወሓት ጋልቦ ከሆነ እነ ሽመልስ ነበሩ ፈረሶቹ ማለት ነው፤ ብለዋል።“ስለዚህ የራሳቸው ጉዳይ ነው!” ያሉት አቶ ጌታቸው ኦሮሚያን የሚያስተዳድሩት እነሱ ናቸው፤ ራሱ ሲያስተዳድር ኖሮ ሲሳሳት ‘አይ እገሌ ብሎኝ ነው’ ካለ ያኔ ጥፋት ነው፣ አሁንም ኦሮሚያ ውስጥ ለሚፈጠር ማንኛውም እንቅስቃሴ የኦሮሚያ ክልል መንግስት የኦሮሚያን ህዝብ ጥያቄ መልሶ ሰላምና መረጋጋት የመፍጠር ኃላፊነት የኦሮሚያ መንግስት መሆኑን መታወቅ አለበት ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa1