YeneTube
120K subscribers
31.2K photos
482 videos
79 files
3.83K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የፌዴራል ስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን 3 ሚሊየን የስራ እድሎችን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት መፍጠሩን ተናገረ፡፡

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ደግሞ 330 ሺ ስራዎች ከስመዋል ብሏል፡፡ባለፈው ዓመት ከተፈጠሩት የስራ እድሎች 62 በመቶዎቹ ቋሚ ሲሆኑ 38 በመቶዎቹ ጊዜያዊ ናቸው ተብሏል፡፡ከተፈጠሩት የስራ ዕድሎች ውስጥ የኢንዱስትሪው ዘርፍ 1.1 ሚሊየን የስራ ዕድሎችን በአነስተኛና ግዙፍ ማኒፋክቸሪ ዘርፍ በመፍጠር ከፍተኛውን ደረጃ ይዟል፡፡ግብርና ደግሞ በአነስተኛ መስኖ በሚመረቱ የአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ 900 ሺህ የስራ ዕድሎችን በመፍጠር ተከታዩን ደረጃ ይዟል፡፡በስራ እድል ተጠቃሚነት ደረጃ ባለፈው ዓመት የሴቶች ተጠቃሚነት ዝቅተኛ እንደነበር ኮሚሽኑ ዛሬ ከሰጠው መግለጫ ሰምተናል፡፡የኢፌድሪ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን በቀጣይ 5 ዓመታት 14 ሚሊየን የስራ ዕድሎችን ለመፍጠር ውጥን መያዙን ተናግሯል፡፡

#Sheger
@YeneTube @FikerAssefa1
የሰሞኑ ከባድ ቅዝቃዜ ለተከታታይ ቀናት ሊዘልቅ እንደሚችል ብሄራዊ ሜትሪዮሎጂ ኤጀንሲ ተናገረ፡፡ የቅዝቃዜው ምክንያትም የሆነው ከደቡብ ህንድ እና ከደቡብ አትላንቲክ ውቅያኖሶች የሚገባው እርጥበት አዘል ከባድ ነፋስ ነው ተብሏል፡፡

#Sheger
@YeneTube @FikerAssefa1
የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ 250 የመተንፈሻ አጋዥ ቬንቲሌተሮችን እያሰራጨሁ ነው አለ፡፡

ተቋሙ ከአሜሪካ መንግስት በድጋፍ ያገኘሁት ነው ያለውን ቬንቲሌተር ለኮሮና ቫይረስ የህክምና መስጫዎች እያሰራጨ መሆኑን ተናግሯል፡፡በጤና ሚኒስቴር ድልድል መሰረት 55 ቬንቲሌተሮች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ የጤና ተቋማት እየተሰራጩ ነው ተብሏል፡፡ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 4፣ ለትግራይ ክልል 12፣ ለአማራ ክልል 40፣ ለኦሮሚያ ክልል 62፣ ለደቡብ ክልል 30፣ ለሲዳማ ክልል 7፣ ለሶማሌ ክልል 14፣ ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 4፣ ለጋንቤላ ክልል 2፣ ለአፋር ክልል 6፣ ለሐረር ክልል 4 ቬንቲሌተሮችን እንደሚያሰራጭ ኤጀንሲው ተናግሯል።ለመከላከያና ለፖሊስ ሆስፒታሎች ደግሞ5፣ 5 ቬንቲሌተሮች እየተሰራጩ ነው ተብሏል፡፡የመተንፈሻ አጋዥ ቬንቲሌተሮች ለኮሮና ፅኑ ህሙማን በእጅጉ የሚረዱ መሆናቸውን ኤጀንሲው በላከው መረጃ ጠቅሷል፡፡ከአሜሪካ መንግስት በድጋፍ የተሰጡትን ቬንቲሌተሮች የኤጀንሲው ዋና ዳሬይክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ በአሜሪካ ኤምባሲ ተገኝተው መረከባቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡

#Sheger
@YeneTube @FikerAssefa1
የኦዴሳ ጦርነት

ፕሬዝዳንት ፑቲን ከወጣትነት ዕድሜያቸው ጀምሮ የሶቪየት መፈራረስና የሩሲያ ልዕልና ማነስ ሲያንገበግባቸው ማደጋቸውን የሚያውቋቸው ይመሰክራሉ፡፡ በተለይ የዩክሬይን አገር መሆን ውስጥ ውስጡን ይበላቸዋል፡፡ የፑቲንን ስነልቦና እናውቃለን የሚሉ በርካቶች የአሁኑ ጦርነት የሩሲያን ክብር ለመመለስ የሚደረግ ነው ይላሉ፡፡ ነገር ግን ይህን ለማሳካት ዋነኛዋ ቁልፍ የጥቁር ባህር ፈርጥ የሆነችውን ኦዴሳን መቆጣጠር ግዴታ ነው፡፡ ዩክሬኖቹ ኦዴሳን አሳልፈን አንሰጥም ብለዋል፡፡ በፑቲን ህልምና በዩክሬይኖች መካከል ስለሚደረገው የኦዴሳ ጦርነት ይህን አስደናቂ ቪዲዮ ይከታተሉ!!!

https://youtu.be/sW0rM_nr8Uo

ለመሆኑ ቅጥረኛ ወታደሮች በወር ምን ያህል ይከፈላቸዋል???
============
ከሰሞኑ በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በዩክሬይኑ ጦርነት ከሩሲያ ጎን ለመዋጋት ተሰልፈው ታይቷል። ወዶ መዝመት ከጥንት ጀምሮ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ የወጣቱን ልብ ያሸፈተው የርዕዮተ ዓለም ፍቅር አይደለም። አማላይ ክፍያው እንጂ። ለመሆኑ ቅጥረኛ ወታደሮች ምን ያህል ይከፈላቸዋል??? የሚሰጣቸው ስልጠና እና ዋነኛ ስራቸው ምንድነው? ይህን አጭር ቪዲዮ ይመልከቱ። ቻናሉን ሰብስክራይብ ያድርጉ!!!

https://youtu.be/Q0Uj40oaOho
ኦዴሳ

ፑቲን ኦዴሳ ከተማን ሳይቆጣጠር የዩክሬይን ዘመቻው ስኬታማ ሊሆንለት አይችልም። ኦዴሳን ከተቆጣጠረ ግን በአውሮፓ ትልልቅ ጂኦፖለቲካዊ ለውጦች ይጠበቃሉ። ለምን? ኦዴሳ ይህን ያህል ጥቅሟ ምንድነው?? ይህን አጭር ቪዲዮ ተከታተሉ