ሸጋ ጁምኣ!!!!
💚
ነጃ በለን ነጃ!!!!
ነጃ በለን ነጃ!!!!
ታውቀዋለህና ያገሬን ሰው ሃጃ።
ነጃ በለን ነጃ!!!!!
ነጃ በለን ነጃ!!!!
እስቲ በጁምኣው፤
ጨዋታው ይቅርብኝ፤
እኔም ብላቴናው፤
ሶላቴን ልፈጥም፤
ብዬ ዱኣ ላድርግ፤ """ነጃ በለን ነጃ፤"""
አውቃለሁ አውቃለሁ፤
ከሞት ይጋርዳል፤
በልኣ ይሸፍናል፤ ያንተ መጋረጃ።
ነጃ በለን ነጃ!!!!!!
((( ጃ ኖ ))(💚💛❤️
ሸጋ ጁምኣ!!!!💚
@balmbaras
@getem
@getem
💚
ነጃ በለን ነጃ!!!!
ነጃ በለን ነጃ!!!!
ታውቀዋለህና ያገሬን ሰው ሃጃ።
ነጃ በለን ነጃ!!!!!
ነጃ በለን ነጃ!!!!
እስቲ በጁምኣው፤
ጨዋታው ይቅርብኝ፤
እኔም ብላቴናው፤
ሶላቴን ልፈጥም፤
ብዬ ዱኣ ላድርግ፤ """ነጃ በለን ነጃ፤"""
አውቃለሁ አውቃለሁ፤
ከሞት ይጋርዳል፤
በልኣ ይሸፍናል፤ ያንተ መጋረጃ።
ነጃ በለን ነጃ!!!!!!
((( ጃ ኖ ))(💚💛❤️
ሸጋ ጁምኣ!!!!💚
@balmbaras
@getem
@getem
👆👆👆👆👆👆
#የሥነ_ጽሑፍ_ምሽት_ለምዕመናን_በሙሉ
👉በገዳሙ ዐውደ ምሕረት
👉ጥቅምት 16/2012 ዓ.ም
👉ከቀኑ 10:00 ሰዓት እስከ ምሽት 02:00 ሰዓት ድረስ
በትምህርተ ወንጌል ፤ በግጥምና በመነባንብ እንዲሁም በመንፈሳዊ ወግ ስለ ቅድስት #ቤተ_ክርስቲያን በሚወሳበት በዚህ ልዩ የሥነ ጽሑፍ ምሽት ላይ እንድትገኙ በአክብሮት ጋብዘናል።
#የገዳሙ_ስብከተ_ወንጌል_ከሰ_ት_ቤቱ_ጋር_በመተባበር
#share #share #share
(ጊዜው ያስገድደናልና ሁላችንም ለቤተ ክርስቲያናችንና ለተዋህዶ እምነታችን በመቆርቆር ለሁሉም በማጋራት መልእክቱን እናዳርስ)
ጥቅምት 2012 ዓ.ም
@getem
@getem
#የሥነ_ጽሑፍ_ምሽት_ለምዕመናን_በሙሉ
👉በገዳሙ ዐውደ ምሕረት
👉ጥቅምት 16/2012 ዓ.ም
👉ከቀኑ 10:00 ሰዓት እስከ ምሽት 02:00 ሰዓት ድረስ
በትምህርተ ወንጌል ፤ በግጥምና በመነባንብ እንዲሁም በመንፈሳዊ ወግ ስለ ቅድስት #ቤተ_ክርስቲያን በሚወሳበት በዚህ ልዩ የሥነ ጽሑፍ ምሽት ላይ እንድትገኙ በአክብሮት ጋብዘናል።
#የገዳሙ_ስብከተ_ወንጌል_ከሰ_ት_ቤቱ_ጋር_በመተባበር
#share #share #share
(ጊዜው ያስገድደናልና ሁላችንም ለቤተ ክርስቲያናችንና ለተዋህዶ እምነታችን በመቆርቆር ለሁሉም በማጋራት መልእክቱን እናዳርስ)
ጥቅምት 2012 ዓ.ም
@getem
@getem
ጫማ ሰሪው በዛ!!!!!
ይችን የኔን አገር፤
የቢቸግር ሊቆች ፤
ከጫማዋ በፊት፤ ልኳን ሳያጠሩ፤
ይወዘውዟታል፤
በራሳቸው ኮቴ ፤
ጫማ ልበሽ ብለው፤
በምኞታቸው ልክ መጫሚያ እያሰሩ።
እነ ልክ አያውቁ፤
ልካቸውን እንጅ፤ልኳን እየካዱ ፤
በነርሱ ጫማ ልክ ፤
ያገሬን ቁመና ወርድ እየከነዱ፤
ተረከዝ ጣቶቿን፤
ከውራጅ ጫማቸው፤
ግቢ ግባ ብለው ከወዲያ ከወዲህ እየገደገዱ፤
ይኸው ዛሬ ድረስ፤
እንደው እምቡፍ እምቡፍ
እንደው ተንቦክ ተንቦክ ሆነባት መንገዱ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
ናካይታ!💚
@getem
@getem
@balmbaras
ይችን የኔን አገር፤
የቢቸግር ሊቆች ፤
ከጫማዋ በፊት፤ ልኳን ሳያጠሩ፤
ይወዘውዟታል፤
በራሳቸው ኮቴ ፤
ጫማ ልበሽ ብለው፤
በምኞታቸው ልክ መጫሚያ እያሰሩ።
እነ ልክ አያውቁ፤
ልካቸውን እንጅ፤ልኳን እየካዱ ፤
በነርሱ ጫማ ልክ ፤
ያገሬን ቁመና ወርድ እየከነዱ፤
ተረከዝ ጣቶቿን፤
ከውራጅ ጫማቸው፤
ግቢ ግባ ብለው ከወዲያ ከወዲህ እየገደገዱ፤
ይኸው ዛሬ ድረስ፤
እንደው እምቡፍ እምቡፍ
እንደው ተንቦክ ተንቦክ ሆነባት መንገዱ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
ናካይታ!💚
@getem
@getem
@balmbaras
#በድጋሚ ከመሸ ብንከሰት ማን ከልካይ አለን ?....አንዳንዴ በማታ ሳታስበው ከሰማከው በጣም ረጅም ጊዜ የሆነክ #ሀሳብ ብቅ ይልልሃል ....... እንዴት ትዛለህ ዛሬ..?ለምን አትለኝም.? እሱን ለኔ ተወዉ ዝም ብለህ ወደ ሀሳቡ ግባ እልሃለው!
በድሮ ግዜ ነው አሉ(ድሮ የሚባለው ከመቼ በኋላ እንደሆነ ባይገባኝም)....እናም አንዲት
እናት የስለት ልጅ ነበራት... በስንት ልመና በስንት ስለት የወለደችው ...ከቤት ወጣ ሲል
ምን ይሆንብኝ ይሆን እያለች የምትሳሳለት ፤ ወደሆነ ነገር ልካው ባይዘገይም የዘገየ
እየመሰላት .... ምነው ቆየብኝ ምን አጋጥሞት ይሆን እያለች የምትጨነቅለት ልጅ ነበራት
።... እናም ይህ የስለት ልጇን በድንገት ይሞትባታል .... በጣም አዘነች እንዴት ፈጣሪ
ለሌላው ሰው አስር ፣ ዘጠኝ ልጅ ሰጥቶ ምንም ሳያደርግ እንዴት አንድ ልጄ የነጥቀኛል
በማለት በፈጣሪዋ ፍርድ መዛባት አዘነች። እናም ሀዘኑን ሲበረታባት ሙሾ ለማውረድ
አስገደዳት....
እንዲህም አለች
አስሩ ተቀምጠው አንዱን ትገድላለህ
ዘጠኙ ተቀምጠው አንዱን ትገድላለህ
ስምንቱ ተቀምጠው አንዱን ትገድላለህ
መቼስ የሴት ልጅ ነህ መች ፍርድ ታውቃለህ
አለችው በምሬት
.... አጠገቧ የነበሩት የንስሀ አባትዋም "ተይ ልጄ አይባልም እሱ ሰጠ እሱ ነሳ" ብለው
አወገዟት ....
እሷም እንዲህ በማለት መለሰችላቸው ...
እርሷ እማ ምን ሊሉ
ቄሴ እማ ምን ሊሉ
ለምን አያደሉ
እርሱ እየገደለ ተዝካሮ ሊበሉ.....
ናካይታ💚!
@getem
@balmbaras
በድሮ ግዜ ነው አሉ(ድሮ የሚባለው ከመቼ በኋላ እንደሆነ ባይገባኝም)....እናም አንዲት
እናት የስለት ልጅ ነበራት... በስንት ልመና በስንት ስለት የወለደችው ...ከቤት ወጣ ሲል
ምን ይሆንብኝ ይሆን እያለች የምትሳሳለት ፤ ወደሆነ ነገር ልካው ባይዘገይም የዘገየ
እየመሰላት .... ምነው ቆየብኝ ምን አጋጥሞት ይሆን እያለች የምትጨነቅለት ልጅ ነበራት
።... እናም ይህ የስለት ልጇን በድንገት ይሞትባታል .... በጣም አዘነች እንዴት ፈጣሪ
ለሌላው ሰው አስር ፣ ዘጠኝ ልጅ ሰጥቶ ምንም ሳያደርግ እንዴት አንድ ልጄ የነጥቀኛል
በማለት በፈጣሪዋ ፍርድ መዛባት አዘነች። እናም ሀዘኑን ሲበረታባት ሙሾ ለማውረድ
አስገደዳት....
እንዲህም አለች
አስሩ ተቀምጠው አንዱን ትገድላለህ
ዘጠኙ ተቀምጠው አንዱን ትገድላለህ
ስምንቱ ተቀምጠው አንዱን ትገድላለህ
መቼስ የሴት ልጅ ነህ መች ፍርድ ታውቃለህ
አለችው በምሬት
.... አጠገቧ የነበሩት የንስሀ አባትዋም "ተይ ልጄ አይባልም እሱ ሰጠ እሱ ነሳ" ብለው
አወገዟት ....
እሷም እንዲህ በማለት መለሰችላቸው ...
እርሷ እማ ምን ሊሉ
ቄሴ እማ ምን ሊሉ
ለምን አያደሉ
እርሱ እየገደለ ተዝካሮ ሊበሉ.....
ናካይታ💚!
@getem
@balmbaras
👍2
በመጀመሪያ እምወድሽዋ እንኳን ደህና መጣሽልኝ❤️❤️ ቅዳሜዋ❤️❤️
ነፍፍፍፍ የሚያስጠሉኝ ነገሮች ቢኖሩም እነኚህ ግን በጣም ያስጠሉኛል ፦
* ጨው የሌለው ወጥ
* ወተት የተጠጣበት ብርጭቆ ሽታ
* የዘመድ ሰርግ መታደም
* የማያልቅ ሲዝን ያለው ሲርየስ ሙቪ
* የዘነጠ እና ያነጠነጠ ቄስ
* የተለያየ አይነት ጫት መቃም
* የሚገላመጥ የከተማ ፖሊስ
* የማይስቅ አስተናጋጅ
* የስጋ ቤት ቆራጭ ጋውን
* በጥቅስ የተጨመላለቀ አሮጌ ታክሲ
* የማያነብ መምህር
* ጧት ታክሲ ውስጥ ያለ ጠንካራ ዝምታ
* የወያላ እድፋም ቂጥ
* ቆንጆ ሴትን መረጃ መጠየቅ[ለከፋ ያስመስሉታል]
* የፌስቡክ ጯሂዎች
* በየመንገዱ እናቶች እየተሳቀቁ ሲለምኑ ማየት
* በጫት የናወዘ ወጣት
* በየሰፈሩ ያለ ስራ ተጎልተው የሚውሉ ስማርት የሸገር ልጆች['ስራ-አጥ' የምትሏቸው ]
* ቅጥልጥሉ አቶቢስ
* አማራሪ ሽማግሌ
* የተበላሸ ኦቾሎኒ በስህተት ሳኝከው
* ሃሳቤ ተለዋዋጭ እንደሚሆን የማይገባው - ዱዝ !
*ፊለፊቴ 'ደም ለግሱ' እያለ ሞንታርቦውን ወደኔ አዙሮ የከፈተው 'ደም-ሰብሳቢ'
* ለመቅጣትና ለመቅጣት ብቻ ፊሽካውን የሚነፋ ቦርጫም ትራፊክ
* በባንዲራ የሚነታረክ ኩታራ
* የመስታወት ፎቅ[የምወዳቸው እንዳሉ ሆነው]
* ራስታ ሁላ ጡዘታም የሚመስለው
* እንግሊዝኛ የእውቀቱ ማሳያ የሚመስለው
* ሳያነብ ላይክ የሚገጭ
* ሁሌ ክፋት የሚታየው - አማራሪ
* ህጻናትን የማይወድ
* ካልመነተፈ የወሰደ የማይመስለው
* የመንገድ ላይ ዘግናኝ ቁስሎች - ተሽሞንሙነውና ይበልጥ ዘግናኝ! ሆነው ቢዝነስ
ሲሰራባቸው ማየት
* ይሄንን ሁሉ ጽፌለት ሪአክት የማያደርግ
* ወሬ እያወራ ፂሜን የሚላጨኝ ፀጉር ቆራጭ
* ፈረንጅ የማይፈትሽ ዘበኛ
* አቡሽ አያሌው
* ሽቀላ ተባጥሶ ለማሚ ነጠላ የማይገዛ ሱሳም
* ከቆርቋሳዋ ማሚ ጋር አብሮ ለመሄድ የምታፍር ሂውማን ሄራም - ቁሌታም
* ቤስት ጓደኛውን በነጋታው ሲያገኘው እንደ ሩቅ ሰው አጥብቆ ሰላምታ የሚያቀርብ
* እሑድ
* መርቅኜ ሊያወራኝ የሚሞክር አዝግ
* ጨብሲ ላይ በሲርየስ ጨዌ የሚያደርቀኝ
* ቦሌ አከባቢ ያለ የታይታ ፉክክር - ለቡም እንደዚያው እየሆነ ነው
* ሃይገር ባስ እና ጥሩምባው
* ሸገር ባስ ውስጥ መዝሙር ጮክ አድርጎ የሚከፍት ሹፌር
..... እናንተም የተሰማችሁ ካለ አክሉበት ። ከኔ ጋር መነታረክ ግን ፈጽሞ ክልክል ነው ።
በተረፈ ቻው ።
ሸጋ ቅዳሜ!❤ ናካይታ!💚
@getem
@balmbaras
ነፍፍፍፍ የሚያስጠሉኝ ነገሮች ቢኖሩም እነኚህ ግን በጣም ያስጠሉኛል ፦
* ጨው የሌለው ወጥ
* ወተት የተጠጣበት ብርጭቆ ሽታ
* የዘመድ ሰርግ መታደም
* የማያልቅ ሲዝን ያለው ሲርየስ ሙቪ
* የዘነጠ እና ያነጠነጠ ቄስ
* የተለያየ አይነት ጫት መቃም
* የሚገላመጥ የከተማ ፖሊስ
* የማይስቅ አስተናጋጅ
* የስጋ ቤት ቆራጭ ጋውን
* በጥቅስ የተጨመላለቀ አሮጌ ታክሲ
* የማያነብ መምህር
* ጧት ታክሲ ውስጥ ያለ ጠንካራ ዝምታ
* የወያላ እድፋም ቂጥ
* ቆንጆ ሴትን መረጃ መጠየቅ[ለከፋ ያስመስሉታል]
* የፌስቡክ ጯሂዎች
* በየመንገዱ እናቶች እየተሳቀቁ ሲለምኑ ማየት
* በጫት የናወዘ ወጣት
* በየሰፈሩ ያለ ስራ ተጎልተው የሚውሉ ስማርት የሸገር ልጆች['ስራ-አጥ' የምትሏቸው ]
* ቅጥልጥሉ አቶቢስ
* አማራሪ ሽማግሌ
* የተበላሸ ኦቾሎኒ በስህተት ሳኝከው
* ሃሳቤ ተለዋዋጭ እንደሚሆን የማይገባው - ዱዝ !
*ፊለፊቴ 'ደም ለግሱ' እያለ ሞንታርቦውን ወደኔ አዙሮ የከፈተው 'ደም-ሰብሳቢ'
* ለመቅጣትና ለመቅጣት ብቻ ፊሽካውን የሚነፋ ቦርጫም ትራፊክ
* በባንዲራ የሚነታረክ ኩታራ
* የመስታወት ፎቅ[የምወዳቸው እንዳሉ ሆነው]
* ራስታ ሁላ ጡዘታም የሚመስለው
* እንግሊዝኛ የእውቀቱ ማሳያ የሚመስለው
* ሳያነብ ላይክ የሚገጭ
* ሁሌ ክፋት የሚታየው - አማራሪ
* ህጻናትን የማይወድ
* ካልመነተፈ የወሰደ የማይመስለው
* የመንገድ ላይ ዘግናኝ ቁስሎች - ተሽሞንሙነውና ይበልጥ ዘግናኝ! ሆነው ቢዝነስ
ሲሰራባቸው ማየት
* ይሄንን ሁሉ ጽፌለት ሪአክት የማያደርግ
* ወሬ እያወራ ፂሜን የሚላጨኝ ፀጉር ቆራጭ
* ፈረንጅ የማይፈትሽ ዘበኛ
* አቡሽ አያሌው
* ሽቀላ ተባጥሶ ለማሚ ነጠላ የማይገዛ ሱሳም
* ከቆርቋሳዋ ማሚ ጋር አብሮ ለመሄድ የምታፍር ሂውማን ሄራም - ቁሌታም
* ቤስት ጓደኛውን በነጋታው ሲያገኘው እንደ ሩቅ ሰው አጥብቆ ሰላምታ የሚያቀርብ
* እሑድ
* መርቅኜ ሊያወራኝ የሚሞክር አዝግ
* ጨብሲ ላይ በሲርየስ ጨዌ የሚያደርቀኝ
* ቦሌ አከባቢ ያለ የታይታ ፉክክር - ለቡም እንደዚያው እየሆነ ነው
* ሃይገር ባስ እና ጥሩምባው
* ሸገር ባስ ውስጥ መዝሙር ጮክ አድርጎ የሚከፍት ሹፌር
..... እናንተም የተሰማችሁ ካለ አክሉበት ። ከኔ ጋር መነታረክ ግን ፈጽሞ ክልክል ነው ።
በተረፈ ቻው ።
ሸጋ ቅዳሜ!❤ ናካይታ!💚
@getem
@balmbaras
........... #አጀብ !
ስብራት አካሚ ፥ የፍቅር ወጌሻ
አናቱ ተቆርጦ ፥ ልክ እንደ እብድ ውሻ
ጥንብ
እርኩስ ተደርጎ
ካገር ጠፋ መሰል
ከጥላቻ ቅዠት ፥ መንቃት የተሳነን ፥ መፋቀር ቸልሰል
በአፅም የሾረ ፥ እንዝርት እያጦዝነ
ሀገር ይሉት ካባ ፥ በጋራ ለብሰነ
ከምቾቱ በላይ
እንደ ሱፍ ላይ ጭገር ፥ የኮሰኮሰነ
ምን ነካው ዘመኑ ?
እኛስ ምን ነካነ ?
✍ #አብርሀም_ተክሉ
@getem
@getem
ስብራት አካሚ ፥ የፍቅር ወጌሻ
አናቱ ተቆርጦ ፥ ልክ እንደ እብድ ውሻ
ጥንብ
እርኩስ ተደርጎ
ካገር ጠፋ መሰል
ከጥላቻ ቅዠት ፥ መንቃት የተሳነን ፥ መፋቀር ቸልሰል
በአፅም የሾረ ፥ እንዝርት እያጦዝነ
ሀገር ይሉት ካባ ፥ በጋራ ለብሰነ
ከምቾቱ በላይ
እንደ ሱፍ ላይ ጭገር ፥ የኮሰኮሰነ
ምን ነካው ዘመኑ ?
እኛስ ምን ነካነ ?
✍ #አብርሀም_ተክሉ
@getem
@getem
ምስጉን ነው !!!
።።።።።።።።።።፡
ምንም አይናቅም - ሁሉም ይከበራል
ቅንጣት የነበረው - ደርሶ ይከመራል
ትንሽ ብሎ ነገር - እያደር ይበዛል
አንድ ሳንቲም'ኳ - ያቅሙን ይገዛል
አይቸኩልም እውነት - በሂደት ነው ለውጡ
ኮተት ነው ትርፋቸው - ለሚያፈነግጡ
የፈለገ ቢሆን - አያልፍም ከልኩ
ሕሊና የሌለው - ሆዱ ነው አምላኩ
እግራችን ስንት ነው
እጃችን ስንት ነው
ሳንባችን ስንት ነው
ልባችን ስንት ነው
ኩላሊት ስንት ነው ...
ቢተመን በዋጋ
አሜንን እንወቅ - ለፈጣሪ ፀጋ
ለዚህ ምስክር ነኝ
ከሌለኝ ይበልጣል - የሰጠኝ አብዝቶ
ሕያው አድርጎኛል - ሞቴን በሞት ገዝቶ
ከወርቅም እጅግ 'ሚልቅ - ከዕንቁም የተወደደ
ለጠቢብ ብቻ የሚታይ - ለሰነፍ የተጋረደ
ከማንም በላይ 'ሚጠቅም - ከምንም በላይ አገልጋይ
ማስተዋል የጎደላቸው - ግንበኞች የናቁት ድንጋይ
የሰላማችን ዋርዲያ - በደስታ 'ሚያስፈነጥዘን
የተወደደ ጌጣችን - መገኛው በ'የ ማህዘን
የሀዘናችን መፅናኛ - በርህራሄው አባባይ
ምህረቱ ዘላለማዊ - በ'የ ቅፅበቱ ይቅር ባይ
በምኑም ዓይነት 'ሚገደው - ስለልጆቹ ጉዳይ
የኀያላኖች ኀያል - አልፋ
ኦሜጋ
ኤልሻዳይ ! ።
ማራናታ
መስከረም 25/2012
የአስራትፍሬ
ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ ፤ ይህች ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆነች ፤ ለዓይናችንም ድንቅ ናት ፡፡
መዝ 117 ፥ 22
@getem
@getem
@gebriel_19
።።።።።።።።።።፡
ምንም አይናቅም - ሁሉም ይከበራል
ቅንጣት የነበረው - ደርሶ ይከመራል
ትንሽ ብሎ ነገር - እያደር ይበዛል
አንድ ሳንቲም'ኳ - ያቅሙን ይገዛል
አይቸኩልም እውነት - በሂደት ነው ለውጡ
ኮተት ነው ትርፋቸው - ለሚያፈነግጡ
የፈለገ ቢሆን - አያልፍም ከልኩ
ሕሊና የሌለው - ሆዱ ነው አምላኩ
እግራችን ስንት ነው
እጃችን ስንት ነው
ሳንባችን ስንት ነው
ልባችን ስንት ነው
ኩላሊት ስንት ነው ...
ቢተመን በዋጋ
አሜንን እንወቅ - ለፈጣሪ ፀጋ
ለዚህ ምስክር ነኝ
ከሌለኝ ይበልጣል - የሰጠኝ አብዝቶ
ሕያው አድርጎኛል - ሞቴን በሞት ገዝቶ
ከወርቅም እጅግ 'ሚልቅ - ከዕንቁም የተወደደ
ለጠቢብ ብቻ የሚታይ - ለሰነፍ የተጋረደ
ከማንም በላይ 'ሚጠቅም - ከምንም በላይ አገልጋይ
ማስተዋል የጎደላቸው - ግንበኞች የናቁት ድንጋይ
የሰላማችን ዋርዲያ - በደስታ 'ሚያስፈነጥዘን
የተወደደ ጌጣችን - መገኛው በ'የ ማህዘን
የሀዘናችን መፅናኛ - በርህራሄው አባባይ
ምህረቱ ዘላለማዊ - በ'የ ቅፅበቱ ይቅር ባይ
በምኑም ዓይነት 'ሚገደው - ስለልጆቹ ጉዳይ
የኀያላኖች ኀያል - አልፋ
ኦሜጋ
ኤልሻዳይ ! ።
ማራናታ
መስከረም 25/2012
የአስራትፍሬ
ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ ፤ ይህች ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆነች ፤ ለዓይናችንም ድንቅ ናት ፡፡
መዝ 117 ፥ 22
@getem
@getem
@gebriel_19
❤1
..... ነፍፍፍፍፍፍፍ እጅግ ነፍፍፍፍፍፍፍፍ የምወዳቸው ነገሮች በዙሪያዬ ቢኖሩም እንደው
በሚጢጢው የሚከተሉትን እዩልኝማ ፦ [በርግጥ ሰዎች ስንባል ሁሌ ለኔጌቲቭ ነገሮች
ትኩረት እንሰጣለን ። .........ለዚሁም የየትኛውንም ነጻ ፕሬስ የፊት ገጽ ማየት ይበቃል ።
'ታሰሩ' - 'ተከለከሉ'- 'አመጹ' - 'አስጠነቀቁ' - 'ሞቱ' -'ተሰደዱ' - ...... በሚሉ ቃላት
የተሞሉ ናቸው ። እኔም ቀጥዬ ለምዘረዝራቸው የሚያስደስቱኝ ነገሮች እንደ ቀደመው ጊዜ
አሪፍ አተያይና አመለካከት ላይኖራችሁ ይችላል ። በተቻለኝ ግን ከደረቅና የሞኞች አገላለጽ
ይልቅ እንደወረደ እና Odd በሆነ አገላለጽ ላፍታታችሁ እሞክራለሁ ። እነሆ የምወዳቸው
ነገሮች ፦
* እራሴን [ሁሉ ነገሬን]
* መጻሕፍት
* ስራዬን/መተዳደሪያዬ
* አዳም ረታ
* የእናቴን እጅ
* ጉራጌ
* የረጠበ አፈር
* አጸድ
* የቤተሰቦቼን ቡሌ/ትርፍራፊ[በተለይ በዛች አንድ ጆሮ በሌላት ጠቋራና ጠማማ ድስት
ውስጥ ሲሆን ]
* የመንደር እግር ኳስ ማየት
* ፒቲ ጎል ፣ መሃል በገባ ወይም ፍጥር
* ለዛ ያለው ሼባ ዘመኑን በሃቅ ሲነግረኝ ማዳመጥ
* ቤተክርስቲያን በር ስር ያሉ ቢጫ የለበሱ ኦልዶች
* አጭቤ የሆነ ጩጬ ሊሸውደኝ ሲጥርና ስሸወድለት
* ኢድ ሙባረክ - የሰፈር ልጆች ፓርኪንግ ሽቀላ - ቀሽቶች እነ አሚና እነ ሰሚራ እነ ከድጃ
ሽክ ብለው
* የዶሮ እግር
* የመክሰስ ሰዓት የቱም አይነት ምግብ
* ትምህርት ቤት የመጨረሻው ደወል
* "አባታችን ቀኑን በሰላም እንዳዋልከን
የሰላም ሌሊት አድርግልን " የሚለውን መዝሙር ። ምክንያቱም ከዚህ በሗላ ስብከት
የለም ቀጥታ ወደቤት
* ኒቪያ ክሬም
* ጥቁሩ የስንዴ ቂጣ
* የጆሊ ጁስ ዱቄት ስቅመው የሚጎመዝዘኝ
* ከሸበሌ በር ስር የምንለቃቅመው ጥሬ ቴምር
* ዛፍ ላይ መውጣት
* በክረምት የውሃ ቦይ መቅደድ
* ኒያላ - ጥምብዬ
* የጥላሁን ገሰሰ ዘፈኖች
* እጅጋየሁ ሽባባው
* ቴዲ አፍሮ
* መርካቶዬ
* አዳም ረታ [በድጋሚ ]
* ጎላ ሚካኤል
* ባዕታ ማርያም
* አርክቴክት
* ሙዚቃ
*ጃዝ
* የዴፖ ድራፍት
* የሰንጋተራ ወመኔ
* ቀይይይይ ፍርፍር በሻይ - በጧቱ
* Ma Hi የጨርቆሷ
* በሶ ጭብጥ በሻይ
* የብሔራዊ ቴአትር አካባቢ ወክ
* ሬጌ
* የገጠር ሰው የዋህነት
* አሪፍ ቀፋይ -"የጠጅ አምጣ ፣ ያውም ሃያ ብር !" ብሎ አስደንግጦኝም አስቆኝም ዴች
የሚፈልጠኝ
* የናፍታ መኪና ጢስ ሽታ - አቧራ ላይ ውሃ ሲርከፈከፍ የሚሸተው ሽታ - የክብሪት ሰልፈር
ሽታ - የቤንዚን ሽታ - የትኩስ እንጀራ ሽታ
* የህጻን ንጹህ አይን
* ብይ አሁንም መሬት ላይ ወድቆ ሳገኝ ልቤ ይመታል !
* ሽበት
* ክራንቻ ላይ የበቀለ ድርብ ጥርስ
* በራሱ ጊዜ የሚታይ ዲምፕል
* የሴት ልጅ ስስ የጆሮ ስር ጺም
* ፈልፈላ ከማሚው ጋር ሲጨቃጨቁ
*ግራጫ ቃጭሎች
* ሂጃብ
* ፌስቡክ እና እናንተ
* እናቴ ሒሳብ ስታስብ
* ክበበው ገዳ
* ቶተንሃም እና ኬን
* ጮራ እና ወጋገን
* አራዳ ወያላ
* የአሮጌ መጽሐፍ ሽታ
* ለወመዘክር የመለስናቸው ዘግናኝ መጻሕፍት/ቅርስ
* ሐመሮ ሐ
* ቾ [የሆነች የ15 ዓመት ልጅ ትመስለኛለች- ጸጉሯን ግራና ቀኝ በፖኒተር ያያዘች ነገር ...]
* ሰራዊት ፍቅሬ ሲተረብ መስማት
* አሰፋ ጫቦ
* ሙላቱ አስታጥቄ
* ሃፒ ሃወር
* ይሄንን የያዝኩትን ሸቃባ ስልክ የሚገላግለኝ ምርጥ ስልክ የሚሸልመኝ
* የተረሳ ብድር አስታውሶ የሚመልስ
* የለቅሶ ቤት ምስር ወጥ
* ፊክሽን የሚገዛኝ ፖሊስ ወይም ወታደር
* ለስጦታ መጽሐፍ የሚመርጥ
* ጅንስ ሱሪ
* ነጩን ሲሊፐር
* የመቀሌ ፈታ
* የስንብት ቀለማት
* የመቀሌ ሰው ትህትና
* እማዬና አባዬ[ሲስተሯ] ሁለት ቢራ ሲጠጡ
* ቲቸር መሐመድ [ኢንግሊሽ ቲቸር - ኢትዮጵያ እርምጃ ት/ቤት]
* ቅርጫ - ጥሬ ጉበት -አረቄ-ሻኛ-ትኩስ ስጋ
* የጠጅ ቤት ጫጫታ ዝዝዝዝዝዝዝዝዝዝ
* የ derfek ግሮሰሪ
* ድርቆሽ ፍርፍር
* ኮሬንቲ ሻይ
* ጉንፋን ያለዘዘው ድምጽ
* ኦሪጂናል ትሪደንት
* አዳም ረታ [ስሰልስ ]
* የረመዳን ወር
* አፍጥር - ሾርባ - የስጋና የሩዝ ሳምቡሳ - ቴምር
* ጩጬ እጆቹን በፓንቱ ውስጥ ከቶ ቂጡን ያለማፈር ሲያክሙና
* ለሚስቱ ጓደኛ የሆነ ባል ማየት
* ታክሲው አንድ ሰው ሲቀረው ስደርስ
* አቶቢስ ለአሮጊቷ/ሽማግሌው ብሎ ካለቦታው አቁሞ ሲያሳፍራቸው ማየት
* ተስፋዬ ካሳ
* አለቤ ሾው
* አበባ ከነ ስሩ
* ዶት እርሳስ
* የአተር ክክ አልጫ
* ጥሬ ስጋ
* ተልባ ፍትፍት
* አይነ ስውር ሰውን ለረጅም ርቀት እየሸኘሁት የተሰማኝን በነጻነት መቀደድ - ጸጉሬን
እስከማስነካት ስለራሴ መግለጽ
* አርብ ምሽትና ቅዳሜን
* ነጠላ ለብሳ ላንድሮቨር የምታሽከረክር እንስት
* ሸኖ ክላስ ደቅ ብዬ የሚነበብ ነገር ይዤ ኩሴን ስጥል
ኸረ የምወዳቸው ነገሮችማ አያልቁም ........ እነሆ ኮሜንት መስጫው የናንተው ነው ።
ያላችሁን ጨማምሩበትማ ኤክሴፕት ሁ ዋንትስ ቱ ክሪቲሳይድ ማይ አይዲያስ
..... ሸጋ የቅዳሜ ምሽት💚 "ናካይታ"!
@getem
@getem
@balmbaras
በሚጢጢው የሚከተሉትን እዩልኝማ ፦ [በርግጥ ሰዎች ስንባል ሁሌ ለኔጌቲቭ ነገሮች
ትኩረት እንሰጣለን ። .........ለዚሁም የየትኛውንም ነጻ ፕሬስ የፊት ገጽ ማየት ይበቃል ።
'ታሰሩ' - 'ተከለከሉ'- 'አመጹ' - 'አስጠነቀቁ' - 'ሞቱ' -'ተሰደዱ' - ...... በሚሉ ቃላት
የተሞሉ ናቸው ። እኔም ቀጥዬ ለምዘረዝራቸው የሚያስደስቱኝ ነገሮች እንደ ቀደመው ጊዜ
አሪፍ አተያይና አመለካከት ላይኖራችሁ ይችላል ። በተቻለኝ ግን ከደረቅና የሞኞች አገላለጽ
ይልቅ እንደወረደ እና Odd በሆነ አገላለጽ ላፍታታችሁ እሞክራለሁ ። እነሆ የምወዳቸው
ነገሮች ፦
* እራሴን [ሁሉ ነገሬን]
* መጻሕፍት
* ስራዬን/መተዳደሪያዬ
* አዳም ረታ
* የእናቴን እጅ
* ጉራጌ
* የረጠበ አፈር
* አጸድ
* የቤተሰቦቼን ቡሌ/ትርፍራፊ[በተለይ በዛች አንድ ጆሮ በሌላት ጠቋራና ጠማማ ድስት
ውስጥ ሲሆን ]
* የመንደር እግር ኳስ ማየት
* ፒቲ ጎል ፣ መሃል በገባ ወይም ፍጥር
* ለዛ ያለው ሼባ ዘመኑን በሃቅ ሲነግረኝ ማዳመጥ
* ቤተክርስቲያን በር ስር ያሉ ቢጫ የለበሱ ኦልዶች
* አጭቤ የሆነ ጩጬ ሊሸውደኝ ሲጥርና ስሸወድለት
* ኢድ ሙባረክ - የሰፈር ልጆች ፓርኪንግ ሽቀላ - ቀሽቶች እነ አሚና እነ ሰሚራ እነ ከድጃ
ሽክ ብለው
* የዶሮ እግር
* የመክሰስ ሰዓት የቱም አይነት ምግብ
* ትምህርት ቤት የመጨረሻው ደወል
* "አባታችን ቀኑን በሰላም እንዳዋልከን
የሰላም ሌሊት አድርግልን " የሚለውን መዝሙር ። ምክንያቱም ከዚህ በሗላ ስብከት
የለም ቀጥታ ወደቤት
* ኒቪያ ክሬም
* ጥቁሩ የስንዴ ቂጣ
* የጆሊ ጁስ ዱቄት ስቅመው የሚጎመዝዘኝ
* ከሸበሌ በር ስር የምንለቃቅመው ጥሬ ቴምር
* ዛፍ ላይ መውጣት
* በክረምት የውሃ ቦይ መቅደድ
* ኒያላ - ጥምብዬ
* የጥላሁን ገሰሰ ዘፈኖች
* እጅጋየሁ ሽባባው
* ቴዲ አፍሮ
* መርካቶዬ
* አዳም ረታ [በድጋሚ ]
* ጎላ ሚካኤል
* ባዕታ ማርያም
* አርክቴክት
* ሙዚቃ
*ጃዝ
* የዴፖ ድራፍት
* የሰንጋተራ ወመኔ
* ቀይይይይ ፍርፍር በሻይ - በጧቱ
* Ma Hi የጨርቆሷ
* በሶ ጭብጥ በሻይ
* የብሔራዊ ቴአትር አካባቢ ወክ
* ሬጌ
* የገጠር ሰው የዋህነት
* አሪፍ ቀፋይ -"የጠጅ አምጣ ፣ ያውም ሃያ ብር !" ብሎ አስደንግጦኝም አስቆኝም ዴች
የሚፈልጠኝ
* የናፍታ መኪና ጢስ ሽታ - አቧራ ላይ ውሃ ሲርከፈከፍ የሚሸተው ሽታ - የክብሪት ሰልፈር
ሽታ - የቤንዚን ሽታ - የትኩስ እንጀራ ሽታ
* የህጻን ንጹህ አይን
* ብይ አሁንም መሬት ላይ ወድቆ ሳገኝ ልቤ ይመታል !
* ሽበት
* ክራንቻ ላይ የበቀለ ድርብ ጥርስ
* በራሱ ጊዜ የሚታይ ዲምፕል
* የሴት ልጅ ስስ የጆሮ ስር ጺም
* ፈልፈላ ከማሚው ጋር ሲጨቃጨቁ
*ግራጫ ቃጭሎች
* ሂጃብ
* ፌስቡክ እና እናንተ
* እናቴ ሒሳብ ስታስብ
* ክበበው ገዳ
* ቶተንሃም እና ኬን
* ጮራ እና ወጋገን
* አራዳ ወያላ
* የአሮጌ መጽሐፍ ሽታ
* ለወመዘክር የመለስናቸው ዘግናኝ መጻሕፍት/ቅርስ
* ሐመሮ ሐ
* ቾ [የሆነች የ15 ዓመት ልጅ ትመስለኛለች- ጸጉሯን ግራና ቀኝ በፖኒተር ያያዘች ነገር ...]
* ሰራዊት ፍቅሬ ሲተረብ መስማት
* አሰፋ ጫቦ
* ሙላቱ አስታጥቄ
* ሃፒ ሃወር
* ይሄንን የያዝኩትን ሸቃባ ስልክ የሚገላግለኝ ምርጥ ስልክ የሚሸልመኝ
* የተረሳ ብድር አስታውሶ የሚመልስ
* የለቅሶ ቤት ምስር ወጥ
* ፊክሽን የሚገዛኝ ፖሊስ ወይም ወታደር
* ለስጦታ መጽሐፍ የሚመርጥ
* ጅንስ ሱሪ
* ነጩን ሲሊፐር
* የመቀሌ ፈታ
* የስንብት ቀለማት
* የመቀሌ ሰው ትህትና
* እማዬና አባዬ[ሲስተሯ] ሁለት ቢራ ሲጠጡ
* ቲቸር መሐመድ [ኢንግሊሽ ቲቸር - ኢትዮጵያ እርምጃ ት/ቤት]
* ቅርጫ - ጥሬ ጉበት -አረቄ-ሻኛ-ትኩስ ስጋ
* የጠጅ ቤት ጫጫታ ዝዝዝዝዝዝዝዝዝዝ
* የ derfek ግሮሰሪ
* ድርቆሽ ፍርፍር
* ኮሬንቲ ሻይ
* ጉንፋን ያለዘዘው ድምጽ
* ኦሪጂናል ትሪደንት
* አዳም ረታ [ስሰልስ ]
* የረመዳን ወር
* አፍጥር - ሾርባ - የስጋና የሩዝ ሳምቡሳ - ቴምር
* ጩጬ እጆቹን በፓንቱ ውስጥ ከቶ ቂጡን ያለማፈር ሲያክሙና
* ለሚስቱ ጓደኛ የሆነ ባል ማየት
* ታክሲው አንድ ሰው ሲቀረው ስደርስ
* አቶቢስ ለአሮጊቷ/ሽማግሌው ብሎ ካለቦታው አቁሞ ሲያሳፍራቸው ማየት
* ተስፋዬ ካሳ
* አለቤ ሾው
* አበባ ከነ ስሩ
* ዶት እርሳስ
* የአተር ክክ አልጫ
* ጥሬ ስጋ
* ተልባ ፍትፍት
* አይነ ስውር ሰውን ለረጅም ርቀት እየሸኘሁት የተሰማኝን በነጻነት መቀደድ - ጸጉሬን
እስከማስነካት ስለራሴ መግለጽ
* አርብ ምሽትና ቅዳሜን
* ነጠላ ለብሳ ላንድሮቨር የምታሽከረክር እንስት
* ሸኖ ክላስ ደቅ ብዬ የሚነበብ ነገር ይዤ ኩሴን ስጥል
ኸረ የምወዳቸው ነገሮችማ አያልቁም ........ እነሆ ኮሜንት መስጫው የናንተው ነው ።
ያላችሁን ጨማምሩበትማ ኤክሴፕት ሁ ዋንትስ ቱ ክሪቲሳይድ ማይ አይዲያስ
..... ሸጋ የቅዳሜ ምሽት💚 "ናካይታ"!
@getem
@getem
@balmbaras
👍2
ክብራት እና ክቡራን ጤና ይስጥልኝ፡፡
ነገ እሁድ ከ 7 እስከ 11 ባለው ሰዓት ዉስጥ በብስራት ቲቪ ከ ሀና ከተማ ጋር ስለ ቅርፃ ቅርፅና ስለ አቢቹ ያደረግነዉን ቆይታ ስለሚቀርብ እንድትመለከቱ በአክብሮት ተጋብዛችዋል
@artbekiyechalal
@artbekiyechalel
ነገ እሁድ ከ 7 እስከ 11 ባለው ሰዓት ዉስጥ በብስራት ቲቪ ከ ሀና ከተማ ጋር ስለ ቅርፃ ቅርፅና ስለ አቢቹ ያደረግነዉን ቆይታ ስለሚቀርብ እንድትመለከቱ በአክብሮት ተጋብዛችዋል
@artbekiyechalal
@artbekiyechalel
፠፠እመን ሲሉህ ጠርጥር፠፠
(ሩታ ዘ ሀረር)
ገና ሲነጋጋ ጀንበር ስትፈነጥቅ፣
ጨለማ ተገፎ ለቀን ቦታ ሲለቅ፣
ህልሜን ከደገምኩት በአይኖቼ አይቼ፣
ራሴን ካገኘሁት ከ እቅፍህ ገብቼ፣
በጤናዋ አይደለም! አትበል ወዳጄ፣
በጓደኝነት ነው ካንተ ጋር መዋሉን ብዙ ተላምጄ።
በጠራራ ፀሀይ ፍቅርህ ጥላ ሆኖኝ፣
ባለህበት ሁሉ ድንገት ካገኘኸኝ፣
የእግሮችህን ዳና ተከትዬ እኔ፣
ብርሀን ከረጨ አንተን ያየ አይኔ፣
አሁንም አታስብ ልብህ ጭንቅ አይግባው፣
በጓደኝነት ነው የሚል ቃሌን ስማው።
በድቅድቅ ጨለማ ብርሀኔ ካልኩህ፣
በከፋው ዘመንህ መከታ ከሆንኩህ፣
ሲከፋህ ከከፋኝ ካዘንኩኝ አምርሬ፣
አፌ ሳይናገር አይኔ ላይ ከታየ ግልፅ ሆኖ ፍቅሬ፣
የልብ ወዳጅነት ጥግ የለውምና፣
በሌላ አትየው ጓደኛህ ነኝና።
ግና.......
ቃልህ እንደ ዜማ ልቤን ከሰረቀ፣
ደበረኝ ያልኩት ቀን አንተን እንዳገኘው ፈክቶ ከደመቀ፣
ያልተናገርከው ቀልድ እንደ ጉድ ካሳቀኝ፣
ልሙትልህ ጓዴ ይሄን ጠርጥረኝ።
ለካ አፍቅሬሀለው!!!
@getem
@getem
@getem
(ሩታ ዘ ሀረር)
ገና ሲነጋጋ ጀንበር ስትፈነጥቅ፣
ጨለማ ተገፎ ለቀን ቦታ ሲለቅ፣
ህልሜን ከደገምኩት በአይኖቼ አይቼ፣
ራሴን ካገኘሁት ከ እቅፍህ ገብቼ፣
በጤናዋ አይደለም! አትበል ወዳጄ፣
በጓደኝነት ነው ካንተ ጋር መዋሉን ብዙ ተላምጄ።
በጠራራ ፀሀይ ፍቅርህ ጥላ ሆኖኝ፣
ባለህበት ሁሉ ድንገት ካገኘኸኝ፣
የእግሮችህን ዳና ተከትዬ እኔ፣
ብርሀን ከረጨ አንተን ያየ አይኔ፣
አሁንም አታስብ ልብህ ጭንቅ አይግባው፣
በጓደኝነት ነው የሚል ቃሌን ስማው።
በድቅድቅ ጨለማ ብርሀኔ ካልኩህ፣
በከፋው ዘመንህ መከታ ከሆንኩህ፣
ሲከፋህ ከከፋኝ ካዘንኩኝ አምርሬ፣
አፌ ሳይናገር አይኔ ላይ ከታየ ግልፅ ሆኖ ፍቅሬ፣
የልብ ወዳጅነት ጥግ የለውምና፣
በሌላ አትየው ጓደኛህ ነኝና።
ግና.......
ቃልህ እንደ ዜማ ልቤን ከሰረቀ፣
ደበረኝ ያልኩት ቀን አንተን እንዳገኘው ፈክቶ ከደመቀ፣
ያልተናገርከው ቀልድ እንደ ጉድ ካሳቀኝ፣
ልሙትልህ ጓዴ ይሄን ጠርጥረኝ።
ለካ አፍቅሬሀለው!!!
@getem
@getem
@getem
"ወርቅ ሲመሰጠር"
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።።
ጭንቁ አልባስ ሆኖት ፥ ሜዳ ለወደቀ
ሆዱን እህል ናፍቆት ፥ አካሉ ላለቀ
ተስፋው ለደቀቀ!
እሳት ላደባየው ፥ ህላዌው ተማግዶ
አመዱ ለሚታይ ፥ ምጥን ስጋው ነዶ
ለዛ ምስኪን ነዳይ !
"ጌታን ካልተቀበልህ ፥ እሳት ይበላሀል"
ብለህ ስትሰብከው ፥ ቆመህ ካደባባይ
የቃል ዛቻ ቆጥሮ
ለነፍሱ ደንብሮ
ጌታውን ባይቀበል
ለምን ሳተ ? አትበል
ከሚዛን አትቅለል።
.
አንተ ባለ ስንጥር!
ቁስል ባየህ ቁጥር ፥ የ'ጅህን አትወርውር።
ይልቅ መጣፍ ግለጥ...
ድፍኑ ተስፋውን ፥ በቃል ምሳር ፍለጥ ።
ይሄ ያልኩህ ንጉስ!
የሰበክሁህ ጌታ !
እንኳን ክቡሩን ሰው ፥ መልኩን ለወረሰው
በአርያው በአምሳሉ ፥ ፈጥሮ ላበጃጀው
ተከፍቶ የቆየ ፥ ጉሮሮውን አይቶ
አሞራ ይመግባል ፥ ህብስቱን አብዝቶ።
ብለህ ተናገረው...
ተስፋውን ቀጥለው
አስፈራርተህ ሳይሆን ፥ ፍቅርን ችረህ ሳበው።
ደግሞም ይሄ ምስኪን!
ያልከው ውሉ ጠፍቶት ፥ ዳግም ከጠየቀ
ከሠሙ አንደበትህ...
ወርቁን ማወቅ ሽቶ ፥ ምናቡን ካራቀ
አሞራ የምልህ ...
አይደለም በራሪው !
አይደለም አዕዋፉ !
አሞራው እኛ ነን ፥ አዳም ባለ ክንፉ
ሁሉ ምሉዕ ሆኖ ፥ አንዳች ሳይጎልበት
በሄዱበት መክሰም ፥ 'መልመድ ልምድ ' ሆኖበት
ለመልዕክት ሲሰዱት ...
እሺ ብሎ በሮ ፥ መምጣት ያልቻለበት
ብለህ መልስለት! !
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።።
ጭንቁ አልባስ ሆኖት ፥ ሜዳ ለወደቀ
ሆዱን እህል ናፍቆት ፥ አካሉ ላለቀ
ተስፋው ለደቀቀ!
እሳት ላደባየው ፥ ህላዌው ተማግዶ
አመዱ ለሚታይ ፥ ምጥን ስጋው ነዶ
ለዛ ምስኪን ነዳይ !
"ጌታን ካልተቀበልህ ፥ እሳት ይበላሀል"
ብለህ ስትሰብከው ፥ ቆመህ ካደባባይ
የቃል ዛቻ ቆጥሮ
ለነፍሱ ደንብሮ
ጌታውን ባይቀበል
ለምን ሳተ ? አትበል
ከሚዛን አትቅለል።
.
አንተ ባለ ስንጥር!
ቁስል ባየህ ቁጥር ፥ የ'ጅህን አትወርውር።
ይልቅ መጣፍ ግለጥ...
ድፍኑ ተስፋውን ፥ በቃል ምሳር ፍለጥ ።
ይሄ ያልኩህ ንጉስ!
የሰበክሁህ ጌታ !
እንኳን ክቡሩን ሰው ፥ መልኩን ለወረሰው
በአርያው በአምሳሉ ፥ ፈጥሮ ላበጃጀው
ተከፍቶ የቆየ ፥ ጉሮሮውን አይቶ
አሞራ ይመግባል ፥ ህብስቱን አብዝቶ።
ብለህ ተናገረው...
ተስፋውን ቀጥለው
አስፈራርተህ ሳይሆን ፥ ፍቅርን ችረህ ሳበው።
ደግሞም ይሄ ምስኪን!
ያልከው ውሉ ጠፍቶት ፥ ዳግም ከጠየቀ
ከሠሙ አንደበትህ...
ወርቁን ማወቅ ሽቶ ፥ ምናቡን ካራቀ
አሞራ የምልህ ...
አይደለም በራሪው !
አይደለም አዕዋፉ !
አሞራው እኛ ነን ፥ አዳም ባለ ክንፉ
ሁሉ ምሉዕ ሆኖ ፥ አንዳች ሳይጎልበት
በሄዱበት መክሰም ፥ 'መልመድ ልምድ ' ሆኖበት
ለመልዕክት ሲሰዱት ...
እሺ ብሎ በሮ ፥ መምጣት ያልቻለበት
ብለህ መልስለት! !
ተነስ !
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።
ወንድሜ ሆይ !
ይኸው እንዳየሁህ ፥ የጫማህ መርገጫ
ምላስ ሆኖ ሳስቷል
አካልህ ኮስምኖ ...
ኑሮ የደበተው ፥ አይንህ እንባን አዝሏል ።
#ከዚህ ሁሉ ጀርባ
ቅዱስ ፍጥረትህን ፥ ሰውነትህን ሽሮ
በብሄር ቱማታ ፥ በቃሉ ጠፍሮ
በል ... በል በሚል ድንፋት ፥ በፌስቡክ ፉከራ
ግለሰብ አያለሁ !
ከዳር ተቀምጦ ፥ ስሙን የሚሰራ ።
።።።።።።
#አያለሁ ከጀርባህ !
ባንተው ተጠልሎ ፥ ተስፋ ጓዙን ጥሎ
አንጓች ቅቤ አዝሎ ...
ዘር እየቆጠረ ፥ ዘመድ እያስጠቃ
ባንተ ጉስቁልና ፥ ኪሱን ያጠረቃ
።።።።።።
#አያለሁ ከጀርባህ !
ደጀን ሁነኝ ብሎ ፥ ደረት የለመነ
አንተ ስትቆስል ፥ እርሱ የጀገነ
የጥል እርሾ ቅመም ፥ ፅዋውን ጠማቂ
ባንተ እሪታ ጩኸት ፥ ከጠርዝ ቆሞ ሳቂ
።።።።።
#አያለሁ አንድ ሰው !
አያለሁ ታዋቂ ....
ውብ ቃላት አርቃቂ
የሰይጣን ውልድ ጭፍራ
መሬቱ ልብህ ላይ ስሜት የሚዘራ
በል ተዋጋ 'ሚልህ
መንገድ ዝጋ 'ሚልህ
ከእህትህ ድርሻ ፥ ቆርሰህ ጉረስ 'ሚልህ
የህሊና ስንኩል!
ዛሬም ይታየኛል.. .
በሞትህ ሀውልት ገፅ ፥ ስሙን ቀርፆ ሲውል ።
።።።።
#እንግዲያስ ወንድሜ
የእናቴ ልጅ ደሜ ...
ፌዝ ቧልቱ አይጣለን ፥ በዚህች አጭር ዕድሜ
እኔም ቁርሾ ልፋቅ ፥ ከጥል ቀን ቀድሜ
ቀሰቀስሁህ ተነስ ፥ ማሸለቡ ይብቃን
የወጣት ደም ፍላት ፥ ስሜት እንዳይገዛን
በክልል ሲያጠቡን.. .
ሀገር ሆነን ሰፍተን ፥ ከመሞት እንዳን ።
@getem
@getem
@getem
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።
ወንድሜ ሆይ !
ይኸው እንዳየሁህ ፥ የጫማህ መርገጫ
ምላስ ሆኖ ሳስቷል
አካልህ ኮስምኖ ...
ኑሮ የደበተው ፥ አይንህ እንባን አዝሏል ።
#ከዚህ ሁሉ ጀርባ
ቅዱስ ፍጥረትህን ፥ ሰውነትህን ሽሮ
በብሄር ቱማታ ፥ በቃሉ ጠፍሮ
በል ... በል በሚል ድንፋት ፥ በፌስቡክ ፉከራ
ግለሰብ አያለሁ !
ከዳር ተቀምጦ ፥ ስሙን የሚሰራ ።
።።።።።።
#አያለሁ ከጀርባህ !
ባንተው ተጠልሎ ፥ ተስፋ ጓዙን ጥሎ
አንጓች ቅቤ አዝሎ ...
ዘር እየቆጠረ ፥ ዘመድ እያስጠቃ
ባንተ ጉስቁልና ፥ ኪሱን ያጠረቃ
።።።።።።
#አያለሁ ከጀርባህ !
ደጀን ሁነኝ ብሎ ፥ ደረት የለመነ
አንተ ስትቆስል ፥ እርሱ የጀገነ
የጥል እርሾ ቅመም ፥ ፅዋውን ጠማቂ
ባንተ እሪታ ጩኸት ፥ ከጠርዝ ቆሞ ሳቂ
።።።።።
#አያለሁ አንድ ሰው !
አያለሁ ታዋቂ ....
ውብ ቃላት አርቃቂ
የሰይጣን ውልድ ጭፍራ
መሬቱ ልብህ ላይ ስሜት የሚዘራ
በል ተዋጋ 'ሚልህ
መንገድ ዝጋ 'ሚልህ
ከእህትህ ድርሻ ፥ ቆርሰህ ጉረስ 'ሚልህ
የህሊና ስንኩል!
ዛሬም ይታየኛል.. .
በሞትህ ሀውልት ገፅ ፥ ስሙን ቀርፆ ሲውል ።
።።።።
#እንግዲያስ ወንድሜ
የእናቴ ልጅ ደሜ ...
ፌዝ ቧልቱ አይጣለን ፥ በዚህች አጭር ዕድሜ
እኔም ቁርሾ ልፋቅ ፥ ከጥል ቀን ቀድሜ
ቀሰቀስሁህ ተነስ ፥ ማሸለቡ ይብቃን
የወጣት ደም ፍላት ፥ ስሜት እንዳይገዛን
በክልል ሲያጠቡን.. .
ሀገር ሆነን ሰፍተን ፥ ከመሞት እንዳን ።
@getem
@getem
@getem