ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ተነስ !

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።።።።።።።

ወንድሜ ሆይ !

ይኸው እንዳየሁህ ፥ የጫማህ መርገጫ 

ምላስ ሆኖ ሳስቷል

አካልህ ኮስምኖ ...

ኑሮ የደበተው ፥ አይንህ እንባን አዝሏል ።

#ከዚህ ሁሉ ጀርባ 

ቅዱስ ፍጥረትህን ፥ ሰውነትህን ሽሮ

በብሄር ቱማታ ፥ በቃሉ ጠፍሮ 

በል ... በል በሚል ድንፋት ፥ በፌስቡክ ፉከራ 

ግለሰብ አያለሁ !

ከዳር ተቀምጦ ፥ ስሙን የሚሰራ ።

።።።።።።

#አያለሁ ከጀርባህ !

ባንተው ተጠልሎ ፥ ተስፋ ጓዙን ጥሎ

አንጓች ቅቤ አዝሎ ...

ዘር እየቆጠረ ፥ ዘመድ እያስጠቃ

ባንተ ጉስቁልና ፥ ኪሱን ያጠረቃ 

።።።።።።

#አያለሁ ከጀርባህ !

ደጀን ሁነኝ ብሎ ፥ ደረት የለመነ 

አንተ ስትቆስል ፥ እርሱ የጀገነ

የጥል እርሾ ቅመም ፥ ፅዋውን ጠማቂ

ባንተ እሪታ ጩኸት ፥ ከጠርዝ ቆሞ ሳቂ

።።።።።

#አያለሁ አንድ ሰው !

አያለሁ ታዋቂ ....

ውብ ቃላት አርቃቂ 

የሰይጣን ውልድ ጭፍራ

መሬቱ ልብህ ላይ ስሜት የሚዘራ 

በል ተዋጋ 'ሚልህ

መንገድ ዝጋ 'ሚልህ 

ከእህትህ ድርሻ ፥ ቆርሰህ ጉረስ 'ሚልህ

የህሊና ስንኩል!

ዛሬም ይታየኛል.. .

በሞትህ ሀውልት ገፅ  ፥ ስሙን ቀርፆ ሲውል ።

።።።።

#እንግዲያስ ወንድሜ 

የእናቴ ልጅ ደሜ ...

ፌዝ ቧልቱ አይጣለን ፥ በዚህች አጭር ዕድሜ

እኔም ቁርሾ ልፋቅ ፥ ከጥል ቀን ቀድሜ

ቀሰቀስሁህ ተነስ ፥ ማሸለቡ ይብቃን

የወጣት ደም ፍላት ፥ ስሜት እንዳይገዛን

በክልል ሲያጠቡን.. .

ሀገር ሆነን ሰፍተን ፥ ከመሞት እንዳን ።

@getem
@getem
@getem