ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ተነስ !

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።።።።።።።

ወንድሜ ሆይ !

ይኸው እንዳየሁህ ፥ የጫማህ መርገጫ 

ምላስ ሆኖ ሳስቷል

አካልህ ኮስምኖ ...

ኑሮ የደበተው ፥ አይንህ እንባን አዝሏል ።

#ከዚህ ሁሉ ጀርባ 

ቅዱስ ፍጥረትህን ፥ ሰውነትህን ሽሮ

በብሄር ቱማታ ፥ በቃሉ ጠፍሮ 

በል ... በል በሚል ድንፋት ፥ በፌስቡክ ፉከራ 

ግለሰብ አያለሁ !

ከዳር ተቀምጦ ፥ ስሙን የሚሰራ ።

።።።።።።

#አያለሁ ከጀርባህ !

ባንተው ተጠልሎ ፥ ተስፋ ጓዙን ጥሎ

አንጓች ቅቤ አዝሎ ...

ዘር እየቆጠረ ፥ ዘመድ እያስጠቃ

ባንተ ጉስቁልና ፥ ኪሱን ያጠረቃ 

።።።።።።

#አያለሁ ከጀርባህ !

ደጀን ሁነኝ ብሎ ፥ ደረት የለመነ 

አንተ ስትቆስል ፥ እርሱ የጀገነ

የጥል እርሾ ቅመም ፥ ፅዋውን ጠማቂ

ባንተ እሪታ ጩኸት ፥ ከጠርዝ ቆሞ ሳቂ

።።።።።

#አያለሁ አንድ ሰው !

አያለሁ ታዋቂ ....

ውብ ቃላት አርቃቂ 

የሰይጣን ውልድ ጭፍራ

መሬቱ ልብህ ላይ ስሜት የሚዘራ 

በል ተዋጋ 'ሚልህ

መንገድ ዝጋ 'ሚልህ 

ከእህትህ ድርሻ ፥ ቆርሰህ ጉረስ 'ሚልህ

የህሊና ስንኩል!

ዛሬም ይታየኛል.. .

በሞትህ ሀውልት ገፅ  ፥ ስሙን ቀርፆ ሲውል ።

።።።።

#እንግዲያስ ወንድሜ 

የእናቴ ልጅ ደሜ ...

ፌዝ ቧልቱ አይጣለን ፥ በዚህች አጭር ዕድሜ

እኔም ቁርሾ ልፋቅ ፥ ከጥል ቀን ቀድሜ

ቀሰቀስሁህ ተነስ ፥ ማሸለቡ ይብቃን

የወጣት ደም ፍላት ፥ ስሜት እንዳይገዛን

በክልል ሲያጠቡን.. .

ሀገር ሆነን ሰፍተን ፥ ከመሞት እንዳን ።

@getem
@getem
@getem
ለውብ ቀን!
💚

#ለምን ዛሬ ውብ ቀናችንን ለየት አናረገውም.....#ቅኔ ያለው ትውልድ የሚል እዚሁ ቴሌግራም መንደር የሚገኝ ቻናል እና የመወያያ ግሩፕ አለ .....ሁለቱም ጋር ብትገቡ በብዙ ታተርፋላቹ ነብስ ያላቸው ሀሳቦች ይነሱበታል.....እናም ለውይይት በሚነሱ ሀሳቦች ላይ እኔም መሳተፍ እፈልጋለው ፣ እኔም የዚህ ቤተሰብ አባል መሆን እሻለው ፣ ማን እንደዚህ አይነት እድል ገጥሞት እንቢ ይላል .....ይኼ አይደለም ወይ የተጠፋው የምትሉ ከሆነ ደስ ደስ እያላቸው ያስተናግዳሉ።

# የናንተን ምርጥ ምርጥ ሀሳቦች ይፈልጋሉ እና አካፍሏቸው።

#ከዚህ በታች ወደ ቴሌግራም ቤቱ የሚያደርሰውን ሊንክ ጀባ እላለሁኝ....መሄድና መግባት ለፈለገ ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው.....

ውብ ቀን!💚
👇👇👇👇
ጀመኣው ነገ ቅዳሚትም አይደለች.. እና ለቅዳሚት ድምቀት "ሰው ፍቅር ናፍቆት" የተሰኘ ቅዳሜን የመሰለ የግጥም መድብል ወጥቷል ለግጥም አፍቃሪያን......#መፅሐፉ በጃፋር መፅሐፍት መደብር እና በኤዞፕ (ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ወረድ ብላቹ ይገኛል )....

#ከዚህ በታች የወሎው አድባር ሙሀመድ ሙፍቲ ስለ ፀሐፊው የከተበው አለው...እንካቹ...


ግጥምን ቅኔን እንዲሁ በያዝ ለቀቅ እንደቧልት የሚገጠም የሚዘረፍ ሳይሆን ፣ ለአፈር ገላችን ምንዳ (በረካ) ይሆነን ዘንድ ለነፍሳችን በነፍሳችን ቀለም የሚከተብ የህወይት ግብራችን ነው ። ስንፈቅድ ሲሻን የምናነሳው ፣ ሳይሻን የምንተወው አንድ የፊዚካል እንቅስቃሴ ዘርፍ እይደለም ። ይልቅ ጌትዬው ደጅ የሚፈስ የፍቅር ወንጌል ፣ በሓድራ እየከነፉ በሙሃባ እየሰገሩ ተውበትና ንስሃን አዝለው የሚንዘምትበት ላይታገድ እስካለይኛው ቀዬ የሚዘረጋ ዘላለማዊ ኪታብ ነው ። ለዚህም ከፍታ ባለቅኔው ሙሉጌታ ተስፋዬ ያበክራል ።
.
እኔም ቅኔ ልዝረፍ ... እስኪ ይመርብኝ
ያፈር ግብር አስራት ... የሥጋ‘ዳ አለብኝ...
.
ገጣሚ በሀይማኖት አጥር ሳለ ፣ ግን ሰውነትን ፍቅር ትተው የሀይማኖት ንፅፅር ተጠምደው የሰውን ልብ ገመና ከሚያዜሙ ከንቱ ሰባኪዎች የማይወረስ ፣ ለጀሊሉ ያደረውን ልብህን ነፍስህን ገፍተው በወሎህና ባዳርህ የሚተምኑ ፣ የጀነትን ቁልፍ በእጃቸው ያለ ይመስል ጀነትን እና ጀሀነምን ከሚተምኑ ቀድሞ ቀመስ ዳኢዎች ሸውራራ ተፍሲር የማይማርከው ነው ። ገጣሚው ገና በጥንስሱ ኪነትን ለፍቅር በፍቅር ብሎ በመውላናው የታደለች ናት ። ነፍሱእንደ ቧልት እንዲሁ ስሜቱን ሊሸነግለው አይቻለውም ። ብርቱ የነፍስ ጥሪ ጥበበ ደወል አድያው ከላይ ነውና ።
ይልቁን ያየውን ሀቅ ላያፈገፍግ በቀለሙ ሊገስፅ ይታገላል ። ለሌላው ሊጠቁም በቅኔ መሰላል ይሻገራል ።

ቅንነት ነው ቅኔው ፣ ቅንነት ነው ቀኑ ፣ ሰው ቂም ውሎ ካሳደረ ጀባ ያሉት አወል ቡና እንኳን አይሰባም ። ቢመርቅ ላያደርስ ፣ ቢለግስ በረከት ላይገመጥመው ፣ በሊግስ እንኳ ቂም ካለ በውስጡ እንኳም ለእሱ ለተመፅዋቹም አይበረክትለትም ። ባብጀው የሀጃ ሰታቴ ምን ቢያንፈቀፍቁ የሻቱት ላይበስል አሻዋ ነው የጣዱት ሙራድ ። የከፈተው ላይከድን አድሮ ገርበብ ነው ። ኢማን እንደዋዛ አሉ ... ወዲህም ለውስጣችን ለነፍስ ተክህኖ ( ካባ ) እንጂ ለፈራሽ ገላ መልበሱ ክንቱ ነው ። ይህን የሰውነት ድካ አይያ ሙሌም ሲለኩሰው እንዲህ ነው ። አዎና « ቁርሾ ያዘለች ነፍስ ቅኔ አይቀናትም ። »
.
ጠኔ ሲያጥመነምን ...
መገን ይሄ ቅኔ ... በምን ይገለጣል
ስትሹ " እሹ ! " እያለ የወዳጃ አበጋር ...
ቁርሾ ካንቀራጨ ... መች ሓጃ ያወጣል ።
.
.
.
ሊቀ ካህናቱ ... በከንቱ ውዕቱ ፣
መርተው ሲነርቱ ...
በብር መቋሚያ ፣ በወርቅ ፅናጵል
ደበሎ ለብሼ ...
ሚስጥረ ህቡኀን ድጎን ብቀጵል..
" በህግ አምላክ ብሎ !" ብሎ ማን ሊያቆመኝ ኑሯል?
ለራሱ ሊወናኝ ... ዘርፎ ቢቀኝ እንጂ
በነብሱ " ተክህኖ " ማን ማንን አስምሯል !
.

.
----
እናም ይህንን አይነት ሀቅ ከብላቴናው ገጣሚ ዳግም ደጀኔ (ሔራን) የፊታችን አርብና ቅዳሜ ገደማ ከምትወጣው ( ሰው - ፍቅር - ናፍቆት ) አድስ የግጥም መድብል ላይ አየናትና ነው ብዙ ማለቴ ።
.
የለምን ጥያቄ
።።

የያመነው ኪዳን
ባልታመነ ካህን በአማኝ ነኝ ልሳን ፣
በአርጅቷል ማዘዣ
ሰርክ እየታደሰ አውደ ‘ዳሱ ድርሳን ።
እውነት ቅቡ ሃሰን
ገዝፎ ለመታየት የክፍ እርካብ ሽቶ ፣
ከመሆን ዘመን ላይ
ወደ ቅጥፈት ደጃፍ
ሀቅ ይንከባለላል በመምሰል ተገፍቶ ።

በገፊዎች ግፊት
የእውነት እውነት ወዙ ሲገረጣ ፣
እውነት አምላኪ ሰው
በሀሰት ገዢዎች ሰውነቱን አጣ ።
.
ታዳ እንድህ እንዳለ ...
ተገፊው ይሄ ሰው ፣
ለምን ነው እምገፋ
ብሎ ለመጠየቅ ለ ማለት ሲጀምር ፣
ዝምበል አትናገር
የሚል መልስ ያገኛል ከገፊው መምህር ።

ለምን ሲል ለእንደዚህ
እንደት ሲል እንደዚህ
ምድራዊ መገፋት
አየለማዊ ልፋት
ሩህን ቢያርዳት የልፋቱ ቀንበር ፣
ዝም ብለህ አትናገር
የፈተነህ ጌታ
አንተን ሊመርጥ ነው ለሰማዩ መምበር ።
ይህ ማለት ምንድን ነው ...
.
.
.
.
ታዳ ልክ እንደዚህ
አማኝ አለማኙም
እውነት ለመቀርጠፍ ቅጥፈት ከታቀፈ ፣
አምንም ያለ ሰው
በአማኞች ህብረት ለምን ተነቀፈ ።
.
.
.
.
-----
( ሰው ፍቅር ናፍቆት )ገፅ 83
ሰኞም ትወጣለችና እንሸምታት ።
---
በመጨረሻም.
--
በሰው ልጅ የሕይወት ሂደት ውስጥ ጥበብ ወይም የእርሱ ዘርፍ ውስጥ የሆነው ልክ እንደ ግጥም ቋሚ ቅርሶች ሁሉ የማህበረሰቡን ወግ ፣ ልማድ ፣ ባህል ... ወ ዘ ተ ይዞ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ ይኖራል ። እስልምናም ለዚህ የጥበብ ዘርፍ የራሱ የሆነ አስተዋፅኦ አለው ። ከረሱል አሚን ( ሶ ዐ ወ ) መላክ በስተፊት አንስቶ ድንቅ ገጣሚያን በአረቢያን ምድር ነበሩ ። ግጥም እጅግ ትልቅ ሀይል እንደነበረው የተለያዪ የታሪክ መዛግብት ይናገራሉ ። እጅግ ያማረና ውብ የሆኑ ግጥሞችን ያስነበበ ደግሞ ለክብሩ ሲባል በካዕባ ይንጠለጠል እንደነበር ታሪክ ያስረዳል ። ሲለኝ በአደብ አደምጨዋለሁ " ኪታቡን " የግጥም መፅሓፍ መግቢያ ።
-
አሁን አሁን የግጥም መፀሐፍ በየወሩ ቢወጡም ሳለ ፣ በእርቃን የታጀበ ክሊፕ ብቻ ሰርተው " ዘፈን ነው አደምጡ " ብለው ጆሯችንን እንደሚቀልዱበት ሙዚቃ ተብዬ ግርግር አይደለም ። አዎ አንድ የግጥም መፀሐፍ ሲወጣ ተነቦ እንደገጣሚው አቅምና መድረስ እንጂ የሚለካው ከሌሎች ከፍ ካሉ ስራዎች ጋር አይወደዳደርም ። ሲጀመር ያን መፀሀፍ ይጣፍ አይጣፍጥ መች ገዝተን አንብበንው ነው ። ይህ ትልቅ በሽታ ነው ። ስም ያላቸውን ገጣሚያን ግን ሳናነበው ለማድነቅ መሯሯጡ ነው አመላችን ። በተዋቂ ስም ለመድመቅ ከጀርባ ከፊት ሽፋን መለጠፉ ክፉ በሽታ ነው ። በዛው ልክም ሳያነቡ የማይመሰክሩ ሸጋ አንባቢም አሉ ። አዎ ለነፍስ ወደ ነፍስ የነፍስን ስራ የሚያደርሱ የሚጀቡ እንደነ Shalom Desalegn Fuddy Man Cj አይነትም አይነት የለሽ አሉ ።
.
እንጂማ ...
የነ YadEl Tizazu -- ( ሕልም ብሀርን አድሜ )
የነ ዲበኩሉ ጌታ --( የምድር ዘላለም )
የነ Andualem Mesfin ... ( ሰበከት )



ሸጋ የግጥም መፀሓፍ ተነቦ ሊገን ሊከበር በተገባው ነበር ። ግን ስንገዛ ፣ ስንጋብዝ አልታየንም ።
---
ምን ማለት ፈልጌ ነው -- እንግዛ እናንብብና ይውደቅ ። " አንባቢ ከብዶታል " አንበል መጀመሪያ እናድርስው ። #ኸላስ
---

ሸጋ የቅዳሚት መዳረሻ ምሽት

@getem
@getem
@Nagayta
👍2