ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
........... #አጀብ !

ስብራት አካሚ ፥ የፍቅር ወጌሻ
አናቱ ተቆርጦ ፥ ልክ እንደ እብድ ውሻ
ጥንብ
እርኩስ ተደርጎ
ካገር ጠፋ መሰል
ከጥላቻ ቅዠት ፥ መንቃት የተሳነን ፥ መፋቀር ቸልሰል
በአፅም የሾረ ፥ እንዝርት እያጦዝነ
ሀገር ይሉት ካባ ፥ በጋራ ለብሰነ
ከምቾቱ በላይ
እንደ ሱፍ ላይ ጭገር ፥ የኮሰኮሰነ
ምን ነካው ዘመኑ ?
እኛስ ምን ነካነ ?

#አብርሀም_ተክሉ

@getem
@getem