ለባለ ልደቷ (የልቤ ሰው )❤
🎂🎂🎂
መወለድ በብርሃናማ ገፁ የተገለጠባት ኪነት.... ፍቅር በእያንዳንዷ ህዋሳቷ ሰርፆ ሰው
የመሆንን ዜማ የተቀኘችልን ጥዑም ልሳን..... ሳምሶን ያልተሰናከለባት ደሊላዊ ጥፍጥና.....
እስራኤላውያን ያላመፁባት ሲጳራዊት ንቃት..... ግብፃውያን ያላስመረሯት ራሔላዊት
ቅንነት..... ፍርኦነች ያላሳደዷት ማሪያማዊት ብፅእና.... እነኋት የቅን መንገድ።
ሰላማዊቷ ርግብ..... የፍቅር እጣነ ሞገር..... የውበት ሸማ ፈታይ..... ጥዑም ፈትለ ወርቅ
ዜማ..... ጂጂ ነፍሴ ....ልባሟ ወለተ ፃድቅ.... እዝን ማርካ፥ አንጀትን ፈልፍላ በልብ
የነገሰች የንጋት ትፍስህት!! ከመወለዷ አብራክ ፀንሳ የወለደችኝ አማልክቴ!!! አፈቅርሻለሁ
የኔ እመቤት።አንቺ በእያንዳንዷ ቅፅበት በልብ ሰማይ ላይ የምትወለጅ የማትጠልቂ ፀሓይ
ነሽ።እንኳንም ተወለድሽልኝ!!!
በአንቺ መወለድ
የፈገግታን ጣእም.... የህይወትን አይጠገቤ ገፅ አጣጣምንና እንኳንም ተወለድን አልን!!!!
------------------------------------------------
በመኪናው መንገድ በተወለወለው ፤
በሎንችን አውቶብስ ነይ ድረሽ በሚለው ፤
ታዲያ ይኸ ቀልቤ፤
ምን አይቶ መስሎህ ነው የሚንጦለጦለው ፤
አልገባህ አለ እንጂ ፤
አንተን አይደል እንዴ ልቤ የከጀለው።
ዘለቀ ይሉኛል ያ ባለጎፈሬው ያ ባለድምድሙ ፤
ኧረ ድረሱልኝ ፤
ጎፈሬው ጋረደኝ ሊጠፋኝ ነው ስሙ ።
አባይን በዋና ወጥቼው ላይደክመኝ ፤
ጣናን በታንኳየ ዋኝቼው ላይገርመኝ ፤
ሌት ከቤትህ መጣሁ እኔ ደግሞ አያርመኝ ።
እዚያ ማዶ ጋራ ያለሽው ጋጋኔ ፤
የናፍቆት ሊጋባ የፍቅር ምስለኔ፤
ውሃ ከዳኝ ብለሽ ፤ ከፍቶሻል እንደኔ ።
ውሃ ከዳኝ ብሎ ሰው ለምን ይቆጣል ፤
ቁልቁለት ካገኘ ፤
ውሃ ዝቅዝቅ እንጅ መች ሽቅብ ይወጣል ።
አያና ደማሙ ያባይ ዳሩ ቃንቄ የሰከላው ዳገት ፤
ምንድር ይሆን መላው ፤
ምን ይሆን መሻሪያው ፤ ውሃ የከዳለት ።
አሁንም ዘለቀ ፤
ያንን ሸጋ ይዞ ፤
ረጅሙ አውቶብስ አለፈ ነጎደ ሄደ ወደፊት፤
መሆኑን ቢያውቅ ነው ፤
መዋያው ዳንግላ ማደሪያው ዳሞት ፤
አወይ አጨካከን ፤
ምነው ጥሎኝ ሄደ ፤ እኔ እንዲህ ስሞት ።
አባ አለም ለምኔ አባ አለም ለምኔ ፤
እንኳንስ ሰውና ፤
ማልመድ አይጠፋኝም ወፍና ቀጭኔ ።
የራያውን ቀሚስ ሸብ አድርጌዋለሁ ፤
መልጎም ብር አምባሩን በጄ ሰክቻለሁ ፤
በተረከዜ ላይ አልቦ ገጥሜያለሁ ፤
ባለ አልቦ ባል አልቦ ቢለኝ መንገደኛ ፤
እንዴት እንዴት እንዴት ፤
ባል አልቦይቱ ልጅ ባል አልቦ ልተኛ ??
የመልከፄዴቅ ልጅ ጦቢያ ላይ ስትዘልቅ ፤
እኔ ግብር ላግባ እጣንና ወርቅ ፤
በጉባኤ ቃና በአጀብ ልራቀቅ ፤
ቢጠጡት አይጠግቡት ቅኔና መረቅ ።
#እማፈቅርሽዋ መልካም ልደት!🎂
@getem
@getem
@balmbaras
🎂🎂🎂
መወለድ በብርሃናማ ገፁ የተገለጠባት ኪነት.... ፍቅር በእያንዳንዷ ህዋሳቷ ሰርፆ ሰው
የመሆንን ዜማ የተቀኘችልን ጥዑም ልሳን..... ሳምሶን ያልተሰናከለባት ደሊላዊ ጥፍጥና.....
እስራኤላውያን ያላመፁባት ሲጳራዊት ንቃት..... ግብፃውያን ያላስመረሯት ራሔላዊት
ቅንነት..... ፍርኦነች ያላሳደዷት ማሪያማዊት ብፅእና.... እነኋት የቅን መንገድ።
ሰላማዊቷ ርግብ..... የፍቅር እጣነ ሞገር..... የውበት ሸማ ፈታይ..... ጥዑም ፈትለ ወርቅ
ዜማ..... ጂጂ ነፍሴ ....ልባሟ ወለተ ፃድቅ.... እዝን ማርካ፥ አንጀትን ፈልፍላ በልብ
የነገሰች የንጋት ትፍስህት!! ከመወለዷ አብራክ ፀንሳ የወለደችኝ አማልክቴ!!! አፈቅርሻለሁ
የኔ እመቤት።አንቺ በእያንዳንዷ ቅፅበት በልብ ሰማይ ላይ የምትወለጅ የማትጠልቂ ፀሓይ
ነሽ።እንኳንም ተወለድሽልኝ!!!
በአንቺ መወለድ
የፈገግታን ጣእም.... የህይወትን አይጠገቤ ገፅ አጣጣምንና እንኳንም ተወለድን አልን!!!!
------------------------------------------------
በመኪናው መንገድ በተወለወለው ፤
በሎንችን አውቶብስ ነይ ድረሽ በሚለው ፤
ታዲያ ይኸ ቀልቤ፤
ምን አይቶ መስሎህ ነው የሚንጦለጦለው ፤
አልገባህ አለ እንጂ ፤
አንተን አይደል እንዴ ልቤ የከጀለው።
ዘለቀ ይሉኛል ያ ባለጎፈሬው ያ ባለድምድሙ ፤
ኧረ ድረሱልኝ ፤
ጎፈሬው ጋረደኝ ሊጠፋኝ ነው ስሙ ።
አባይን በዋና ወጥቼው ላይደክመኝ ፤
ጣናን በታንኳየ ዋኝቼው ላይገርመኝ ፤
ሌት ከቤትህ መጣሁ እኔ ደግሞ አያርመኝ ።
እዚያ ማዶ ጋራ ያለሽው ጋጋኔ ፤
የናፍቆት ሊጋባ የፍቅር ምስለኔ፤
ውሃ ከዳኝ ብለሽ ፤ ከፍቶሻል እንደኔ ።
ውሃ ከዳኝ ብሎ ሰው ለምን ይቆጣል ፤
ቁልቁለት ካገኘ ፤
ውሃ ዝቅዝቅ እንጅ መች ሽቅብ ይወጣል ።
አያና ደማሙ ያባይ ዳሩ ቃንቄ የሰከላው ዳገት ፤
ምንድር ይሆን መላው ፤
ምን ይሆን መሻሪያው ፤ ውሃ የከዳለት ።
አሁንም ዘለቀ ፤
ያንን ሸጋ ይዞ ፤
ረጅሙ አውቶብስ አለፈ ነጎደ ሄደ ወደፊት፤
መሆኑን ቢያውቅ ነው ፤
መዋያው ዳንግላ ማደሪያው ዳሞት ፤
አወይ አጨካከን ፤
ምነው ጥሎኝ ሄደ ፤ እኔ እንዲህ ስሞት ።
አባ አለም ለምኔ አባ አለም ለምኔ ፤
እንኳንስ ሰውና ፤
ማልመድ አይጠፋኝም ወፍና ቀጭኔ ።
የራያውን ቀሚስ ሸብ አድርጌዋለሁ ፤
መልጎም ብር አምባሩን በጄ ሰክቻለሁ ፤
በተረከዜ ላይ አልቦ ገጥሜያለሁ ፤
ባለ አልቦ ባል አልቦ ቢለኝ መንገደኛ ፤
እንዴት እንዴት እንዴት ፤
ባል አልቦይቱ ልጅ ባል አልቦ ልተኛ ??
የመልከፄዴቅ ልጅ ጦቢያ ላይ ስትዘልቅ ፤
እኔ ግብር ላግባ እጣንና ወርቅ ፤
በጉባኤ ቃና በአጀብ ልራቀቅ ፤
ቢጠጡት አይጠግቡት ቅኔና መረቅ ።
#እማፈቅርሽዋ መልካም ልደት!🎂
@getem
@getem
@balmbaras
👍1
. ተ ረ ት ተ ረ ት .
(ሜሮን ጌትነት)
-----------------------------
ተረት ተረት
የላም በረት
አንድ ሰው ነበረ
በሀብቱ የከበረ
ውልደቱም እድገቱም የሆነ አሜሪካ
ባለው ነገር ሁሉ ጭራሽ የማይረካ
ሲሞላለት ሆዱ 'ሀምበርገሩን' በልቶ
'ጋዴሚት' ይለዋል አልጋው ላይ ተኝቶ።
ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
በጣም የተማረ
በቃኝን የማያውቅ የጣልያን ተወላጅ
ሁሌም ለአዲስ ነገር ጠዋት ማታ 'ሚባጅ
'ፒዛና ፓስታውን' ጥርግርግ አድርጎ
ይተኛል ጥሩ እንቅልፍ 'ባፋንኩሎ' ብሎ።
ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
ህልሙ የሰመረ
ጀርመን ነው ሀገሩ
'ምርጥ ዘር' ነው ዘሩ
'ቮግ ቮረስቱን' በልቶ ሞልቶለት አዱኛ
'ሻይሰ' ብሎ ነው ሁሌም የሚተኛ።
ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
የተመራመረ
ጃፓን ተወለደ
በሮቦት አደገ
ቀን ሲሰራ ውሎ
ሩዙን ቀቅሎ
'ሱሺ' ጠግቦ በልቶ
'ባጋይሮ' ብሎ ያነጋል ተኝቶ።
ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
አጥቶ የተቸገረ
ኢትዮጵያ ተወልዶ ኢትዮጵያ ያደገ ኩራት ነው 'ራቱ ዛሬም ሆነ ነገ
ቢጠግብም ባይጠግብም ቆሎውን ቆርጥሞ
'ተመስገን' ይለዋል መደብ ላይ ተጋድሞ።
ተረት ተረት ...
እግዜር ከመንበሩ ወደ ምድር ወርዶ
ይጎበኝ ነበረ በየቤቱ ሄዶ
ከእነኚያ ከአራቱ ቆዳቸው ከነጣ
ከየአንደበታቸው መልካም ነገር ቢያጣ
ጥቁሩ ሲያመሰግን የፈለገው ሞልቶ
ያጎደለባቸው አንድ የሆነ ነገር እንዳለ ገምቶ
ሊጨምርላቸው ነጮቹጋ ሄደ አበሻውን ትቶ።
ተረቴን መልሱ
አፌን በዳቦ አብሱ።
-------------------------------
@getem
@getem
@stupid_world_1
(ሜሮን ጌትነት)
-----------------------------
ተረት ተረት
የላም በረት
አንድ ሰው ነበረ
በሀብቱ የከበረ
ውልደቱም እድገቱም የሆነ አሜሪካ
ባለው ነገር ሁሉ ጭራሽ የማይረካ
ሲሞላለት ሆዱ 'ሀምበርገሩን' በልቶ
'ጋዴሚት' ይለዋል አልጋው ላይ ተኝቶ።
ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
በጣም የተማረ
በቃኝን የማያውቅ የጣልያን ተወላጅ
ሁሌም ለአዲስ ነገር ጠዋት ማታ 'ሚባጅ
'ፒዛና ፓስታውን' ጥርግርግ አድርጎ
ይተኛል ጥሩ እንቅልፍ 'ባፋንኩሎ' ብሎ።
ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
ህልሙ የሰመረ
ጀርመን ነው ሀገሩ
'ምርጥ ዘር' ነው ዘሩ
'ቮግ ቮረስቱን' በልቶ ሞልቶለት አዱኛ
'ሻይሰ' ብሎ ነው ሁሌም የሚተኛ።
ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
የተመራመረ
ጃፓን ተወለደ
በሮቦት አደገ
ቀን ሲሰራ ውሎ
ሩዙን ቀቅሎ
'ሱሺ' ጠግቦ በልቶ
'ባጋይሮ' ብሎ ያነጋል ተኝቶ።
ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
አጥቶ የተቸገረ
ኢትዮጵያ ተወልዶ ኢትዮጵያ ያደገ ኩራት ነው 'ራቱ ዛሬም ሆነ ነገ
ቢጠግብም ባይጠግብም ቆሎውን ቆርጥሞ
'ተመስገን' ይለዋል መደብ ላይ ተጋድሞ።
ተረት ተረት ...
እግዜር ከመንበሩ ወደ ምድር ወርዶ
ይጎበኝ ነበረ በየቤቱ ሄዶ
ከእነኚያ ከአራቱ ቆዳቸው ከነጣ
ከየአንደበታቸው መልካም ነገር ቢያጣ
ጥቁሩ ሲያመሰግን የፈለገው ሞልቶ
ያጎደለባቸው አንድ የሆነ ነገር እንዳለ ገምቶ
ሊጨምርላቸው ነጮቹጋ ሄደ አበሻውን ትቶ።
ተረቴን መልሱ
አፌን በዳቦ አብሱ።
-------------------------------
@getem
@getem
@stupid_world_1
እረፉ!
“ዘመመ!” ብላችሁ የሰው ቤት አትግፉ
እሾህ ለማሳመር አበባ አታርግፉ።
እረፍ!
“ቆሜያለሁ!” ለማለት አጥሬን አትደገፍ
ለአመዳም ወዘናህ ቆዳዬን አትግፈፍ።
እረፍ!
በመስመርህ ፍካ በድንበርህ ለምልም
በየአልጋህ እደር በየእንቅልፍህ አልም።
እረፊ!
በኩረጃ ንባብ ትርጉም አትግደፊ
በሰባራ መርፌሽ የሰው ልክ አትስፊ።.
...ማን አንደጠለፈኝ ማን እንደሰበረኝ
ጠያቂ አጣሁ እንጂ መልስማ ነበረኝ።
(በረከት በላይነህ)https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFA2weUHLJRi_HLwlQ
@getem
@getem
“ዘመመ!” ብላችሁ የሰው ቤት አትግፉ
እሾህ ለማሳመር አበባ አታርግፉ።
እረፍ!
“ቆሜያለሁ!” ለማለት አጥሬን አትደገፍ
ለአመዳም ወዘናህ ቆዳዬን አትግፈፍ።
እረፍ!
በመስመርህ ፍካ በድንበርህ ለምልም
በየአልጋህ እደር በየእንቅልፍህ አልም።
እረፊ!
በኩረጃ ንባብ ትርጉም አትግደፊ
በሰባራ መርፌሽ የሰው ልክ አትስፊ።.
...ማን አንደጠለፈኝ ማን እንደሰበረኝ
ጠያቂ አጣሁ እንጂ መልስማ ነበረኝ።
(በረከት በላይነህ)https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFA2weUHLJRi_HLwlQ
@getem
@getem
እማራለሁ ብዬ - ወጥቼ ነበረ -
ቦርሳዬን ሸክፌ፥
ዳሩ ምን ያደርጋል?
የእውቀቱን ጎዳና - ድንጋዩ ዘጋብኝ -
እንድቀር ከሽፌ፤
#SyriaInMyMind
(ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ)
@getem
@getem
ቦርሳዬን ሸክፌ፥
ዳሩ ምን ያደርጋል?
የእውቀቱን ጎዳና - ድንጋዩ ዘጋብኝ -
እንድቀር ከሽፌ፤
#SyriaInMyMind
(ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ)
@getem
@getem
~አንዳንዴ እንዲህ ነው ~
እርሜን እግር አውጥቼ ብሄድ ከዚያ መንደር
ከልለሃል አሉ አበጅተህ ድንበር
አወይ የሞኝ ዕጣ ያለማወቅ ነገር
እንዴት ሊቆም ብለህ ጎጆ ያለ ማገር
...............................
ለካስ...
አንዳንዴ እንዲህ ነው ...
የጨነቀው ንጉስ ዳኛዉን ይከሳል
ያደለው ባላባት በአያቱ ይጎርሳል
...............................
አንዳንዴ እንዲህ ነው ...
ከአፈር መሠራቱን ላፍታ የዘነጋ
ገልን ያራክሳል የመኖሩን ዋጋ
...............................
አንዳንዴ እንዲህ ነው...
ገዳይ በዋለበት ሟች ገነት ይወርሳል
ገላ ያሉት ስጋ እያደር ይማሳል
............................
እንዲህ ነው አለሜ
ፅድቅ ይሉት ኩነኔ በውል ያልተለየ
ቀረበን ያልነው ነው እውነት የዘገየ
...............................
ድንገት ስትነቃ ባልዋልክበት ውሎ
እውነትህ ቢዘገይ ሐሰት ቢያሳንሰው
ሳትሮጥ አንጋጠህ ዕምነትክን መልሰው
...............................
አየህ...
ዕምነትህ ሲመለስ
የመርፌ ቀዳዳ ግመል ያሾልካል
ቀን የጣለው ወስፌ ከጅማት ይረክሳል
...............................
አንዳንዴ እንዲህ ነው...
እጅ ይዞ ያስገባ እጅ ይዞ ያስወጣል
የሞኝ ሙክት ታርዶ ብልጥ ቤት ይገባል
...............................
አንዳንዴ እንዲህ ነው
ላም ነጂዋን እንጂ ጌታዋን አታውቅም
የጨረቃ ውበት በፀሐይ አይደምቅም
.................................
አየህ...
አንዳንዱ ሞኝ ነው
የሩቅ ጮማ ናፍቆ ቆሎውን ይረሳል
በፍቅር የተኳለ ሀገር ይፈውሳል
.................................
አንዳንዴ.....
ልብህ ልብ አግኝቶ በፅናት ቢታከም
መርከብ ያድንሃል ከጥፋቱ አለም
................................
አንዳንዴ እንዲህ ነው ።
~~~~~~//~~~~~~~
በ ሔለን ፋንታሁን
ጥበብና ማስተዋልን ያድለን
@getem
@getem
@getem
እርሜን እግር አውጥቼ ብሄድ ከዚያ መንደር
ከልለሃል አሉ አበጅተህ ድንበር
አወይ የሞኝ ዕጣ ያለማወቅ ነገር
እንዴት ሊቆም ብለህ ጎጆ ያለ ማገር
...............................
ለካስ...
አንዳንዴ እንዲህ ነው ...
የጨነቀው ንጉስ ዳኛዉን ይከሳል
ያደለው ባላባት በአያቱ ይጎርሳል
...............................
አንዳንዴ እንዲህ ነው ...
ከአፈር መሠራቱን ላፍታ የዘነጋ
ገልን ያራክሳል የመኖሩን ዋጋ
...............................
አንዳንዴ እንዲህ ነው...
ገዳይ በዋለበት ሟች ገነት ይወርሳል
ገላ ያሉት ስጋ እያደር ይማሳል
............................
እንዲህ ነው አለሜ
ፅድቅ ይሉት ኩነኔ በውል ያልተለየ
ቀረበን ያልነው ነው እውነት የዘገየ
...............................
ድንገት ስትነቃ ባልዋልክበት ውሎ
እውነትህ ቢዘገይ ሐሰት ቢያሳንሰው
ሳትሮጥ አንጋጠህ ዕምነትክን መልሰው
...............................
አየህ...
ዕምነትህ ሲመለስ
የመርፌ ቀዳዳ ግመል ያሾልካል
ቀን የጣለው ወስፌ ከጅማት ይረክሳል
...............................
አንዳንዴ እንዲህ ነው...
እጅ ይዞ ያስገባ እጅ ይዞ ያስወጣል
የሞኝ ሙክት ታርዶ ብልጥ ቤት ይገባል
...............................
አንዳንዴ እንዲህ ነው
ላም ነጂዋን እንጂ ጌታዋን አታውቅም
የጨረቃ ውበት በፀሐይ አይደምቅም
.................................
አየህ...
አንዳንዱ ሞኝ ነው
የሩቅ ጮማ ናፍቆ ቆሎውን ይረሳል
በፍቅር የተኳለ ሀገር ይፈውሳል
.................................
አንዳንዴ.....
ልብህ ልብ አግኝቶ በፅናት ቢታከም
መርከብ ያድንሃል ከጥፋቱ አለም
................................
አንዳንዴ እንዲህ ነው ።
~~~~~~//~~~~~~~
በ ሔለን ፋንታሁን
ጥበብና ማስተዋልን ያድለን
@getem
@getem
@getem
ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ኝ
--------------------------
ኑሮ ቢገፋኝ ፥ የማልወድቅለት
እንዳክሱም ድንጋይ ፥ እንደሮሐ አለት
የጊዜ ሞገድ ፥ ያላደቀቀኝ
የመከራ ዶፍ ፥ ያልነቀነቀኝ
ለሙሾ ሲያጩኝ ፥ ቅኔ የምቀኝ
በግራ ሲሉኝ ፥ የምገኝ በቀኝ
ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ኝ ፤
ከዋርካ ባጥር ፥ ከምቧይ ተልቄ
ከፀሀይ ባንስም ፥ ከኩራዝ ልቄ
ተምድረበዳ ፥ ጅረት አፍልቄ
ጥሜን የምቆርጥ ፥ በፍኝ ጠልቄ
ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ኝ ፤
ግትር ጠላቴን ፥ ባጭር አንካሴ
ራስ ምታቴን ፥ በዳማከሴ
ነቅዬ ምጥል
ነገር በነገር ፥ የማብጠለጥል
ለወዳጆቼ ፥ ዓደይ ምነቅል
በጠላቴ ፊት ፥ ቀንድ የማበቅል
ልክ እንደዋልያ ፥ ተራራ መራጭ
ልክ እንዳሞራ ፥ ብርንዶ ቆራጭ
ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ኝ ፤
እንደመሀረብ ፥ ቤቴን በኪሴ
እንደንቅሳት ፥ ተስፋን በጥርሴ
ይዤ የምዞር
ከቦታ ቦታ
በዘብ በኬላ ፥ የማልገታ
ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ኝ ።
===============
📙 የማለዳ ድባብ
✍ በዕውቀቱ ስዩም
📖 📖 📖 📖 📖 📖
@getem
@getem
@getem
--------------------------
ኑሮ ቢገፋኝ ፥ የማልወድቅለት
እንዳክሱም ድንጋይ ፥ እንደሮሐ አለት
የጊዜ ሞገድ ፥ ያላደቀቀኝ
የመከራ ዶፍ ፥ ያልነቀነቀኝ
ለሙሾ ሲያጩኝ ፥ ቅኔ የምቀኝ
በግራ ሲሉኝ ፥ የምገኝ በቀኝ
ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ኝ ፤
ከዋርካ ባጥር ፥ ከምቧይ ተልቄ
ከፀሀይ ባንስም ፥ ከኩራዝ ልቄ
ተምድረበዳ ፥ ጅረት አፍልቄ
ጥሜን የምቆርጥ ፥ በፍኝ ጠልቄ
ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ኝ ፤
ግትር ጠላቴን ፥ ባጭር አንካሴ
ራስ ምታቴን ፥ በዳማከሴ
ነቅዬ ምጥል
ነገር በነገር ፥ የማብጠለጥል
ለወዳጆቼ ፥ ዓደይ ምነቅል
በጠላቴ ፊት ፥ ቀንድ የማበቅል
ልክ እንደዋልያ ፥ ተራራ መራጭ
ልክ እንዳሞራ ፥ ብርንዶ ቆራጭ
ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ኝ ፤
እንደመሀረብ ፥ ቤቴን በኪሴ
እንደንቅሳት ፥ ተስፋን በጥርሴ
ይዤ የምዞር
ከቦታ ቦታ
በዘብ በኬላ ፥ የማልገታ
ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ኝ ።
===============
📙 የማለዳ ድባብ
✍ በዕውቀቱ ስዩም
📖 📖 📖 📖 📖 📖
@getem
@getem
@getem
❤1
ቸኩሎ ሟችና፤ የሃምሌ ደመና፤
ከእንጣል በስተቀር፤
ከእንውረድ በስተቀር፤ ሌላ ምን ያውቁና።
ስማኝማ ጓዴ፤
ኧረ ገዳይ ሲሉህ ፤
ሰማይ ሸና ሲሉህ ፤ ደንብረህ አትፍለስ፤
አህላቁ ከነዳው፤
ችኩልም ይቻኮል፤ ደመናውም ይፍሰስ፤
እኔ የቱፍታው ልጅ፤
እኔ የጉፍታው ልጅ፤
ሶብር እንዲሆነኝ፤ የዱኣ ገሳየን ብርድልብሴን ልልበስ፤
አላየሁምና ፤
ተቻኩሎ የሞተ፤ አይለምደኝም ብሎ ከቀብር ሲመለስ።
እመዋ! እመዋ!!!
እነየ እነየ!!!
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
ከእንጣል በስተቀር፤
ከእንውረድ በስተቀር፤ ሌላ ምን ያውቁና።
ስማኝማ ጓዴ፤
ኧረ ገዳይ ሲሉህ ፤
ሰማይ ሸና ሲሉህ ፤ ደንብረህ አትፍለስ፤
አህላቁ ከነዳው፤
ችኩልም ይቻኮል፤ ደመናውም ይፍሰስ፤
እኔ የቱፍታው ልጅ፤
እኔ የጉፍታው ልጅ፤
ሶብር እንዲሆነኝ፤ የዱኣ ገሳየን ብርድልብሴን ልልበስ፤
አላየሁምና ፤
ተቻኩሎ የሞተ፤ አይለምደኝም ብሎ ከቀብር ሲመለስ።
እመዋ! እመዋ!!!
እነየ እነየ!!!
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras