ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#በድጋሚ ከመሸ ብንከሰት ማን ከልካይ አለን ?....አንዳንዴ በማታ ሳታስበው ከሰማከው በጣም ረጅም ጊዜ የሆነክ #ሀሳብ ብቅ ይልልሃል ....... እንዴት ትዛለህ ዛሬ..?ለምን አትለኝም.? እሱን ለኔ ተወዉ ዝም ብለህ ወደ ሀሳቡ ግባ እልሃለው!



በድሮ ግዜ ነው አሉ(ድሮ የሚባለው ከመቼ በኋላ እንደሆነ ባይገባኝም)....እናም አንዲት
እናት የስለት ልጅ ነበራት... በስንት ልመና በስንት ስለት የወለደችው ...ከቤት ወጣ ሲል
ምን ይሆንብኝ ይሆን እያለች የምትሳሳለት ፤ ወደሆነ ነገር ልካው ባይዘገይም የዘገየ
እየመሰላት .... ምነው ቆየብኝ ምን አጋጥሞት ይሆን እያለች የምትጨነቅለት ልጅ ነበራት
።... እናም ይህ የስለት ልጇን በድንገት ይሞትባታል .... በጣም አዘነች እንዴት ፈጣሪ
ለሌላው ሰው አስር ፣ ዘጠኝ ልጅ ሰጥቶ ምንም ሳያደርግ እንዴት አንድ ልጄ የነጥቀኛል
በማለት በፈጣሪዋ ፍርድ መዛባት አዘነች። እናም ሀዘኑን ሲበረታባት ሙሾ ለማውረድ
አስገደዳት....


እንዲህም አለች
አስሩ ተቀምጠው አንዱን ትገድላለህ
ዘጠኙ ተቀምጠው አንዱን ትገድላለህ
ስምንቱ ተቀምጠው አንዱን ትገድላለህ
መቼስ የሴት ልጅ ነህ መች ፍርድ ታውቃለህ
አለችው በምሬት


.... አጠገቧ የነበሩት የንስሀ አባትዋም "ተይ ልጄ አይባልም እሱ ሰጠ እሱ ነሳ" ብለው
አወገዟት ....
እሷም እንዲህ በማለት መለሰችላቸው ...
እርሷ እማ ምን ሊሉ
ቄሴ እማ ምን ሊሉ
ለምን አያደሉ
እርሱ እየገደለ ተዝካሮ ሊበሉ.....


ናካይታ💚!

@getem
@balmbaras
👍2