ሱባኤ!!!!!
ካልረባ ጉባኤ ፤
ይሻላል ሱባኤ ፤
ብየ በአቴ ውስጥ
ተመስጥኦ ስመገብ ተመስጥኦ ስጠጣ፤
እርሜን ሱባይ ብይዝ አዲስ አዋጅ መጣ፤
እንዲህ የሚል፤
በሱባኤው ጉዳይ ስብሰባ ስላለን ከሱባኤህ ውጣ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
@getem
@getem
@balmbaras
ካልረባ ጉባኤ ፤
ይሻላል ሱባኤ ፤
ብየ በአቴ ውስጥ
ተመስጥኦ ስመገብ ተመስጥኦ ስጠጣ፤
እርሜን ሱባይ ብይዝ አዲስ አዋጅ መጣ፤
እንዲህ የሚል፤
በሱባኤው ጉዳይ ስብሰባ ስላለን ከሱባኤህ ውጣ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
@getem
@getem
@balmbaras
እዘኝ አዛኝቱ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ወሩ መሥከረም ነው...
ቀኑ በሃያ አንድ ፣ በኢትዮጵያ አቆጣጠር
ግሸን ደብረ ከርቤ...
የ'መብርሐንን ፣ በአሏን ለማክበር
ከክርስቲያኖች ቤት...
አርፍጄ እንደደረስሁ ፣ታቦት ወጥቶ ነበር፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ከታቦቱ አጠገብ...
አውደ ምህረቱ ላይ ፣ ካህኑ ይሰብካል
አንዳንዱ ምእመን ፣
ተአምር ያዘለ ..
ብጫቂ ወረቀት ፣ ለካህኑ ይልካል
ደግሞ ሌላ ተአምር...
ለካህኑ ጆሮ ፣ ዲያቆኑ ያንሻኩካል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ካህኑ!
"ታ'ምር ነው ምእመናን ፣ አንድዜ እልል በሉ
አንኳኩ ይከፈታል ፣
ጠይቁ ይሰጣል ፣ ይላልና ቃሉ
"አፀደ ማርያም"
የተባለች እናት ፣ የማርያም ምስክር
ልጇን አስተምራ ፣ በስቃይ በችግር
ካንዱ ይንበርስቲ...
ተመርቆ ወጥቶ ፣ ያለ ሥራ ሲኖር
አምና በዚህ ሰዓት...
ከደጇ መጥቼ ፣ ተማፅኛት ነበር
ፀሎቴን ሰምታለች!
ልጄም ሥራ ይዞ ...
መቶ ዶላር ልኳል ፣ ካሜሪካን ሀገር፡፡"
ስብከቱን አቋርጦ ፣ ተአምር ሲናገር...
በሴቶች እልልታ ፣ በወንዶች ጭብጨባ
የኢትዮጵያዊት ስለት...
ካሚሪካን ሀገር ፣ ተልኮ ሲገባ
ጥያቄ አምጣለሁ ፣ ዐይኔ እስኪያረግዝ እንባ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
አላለሁ...
ምንድነው እዚህ ሀገር ፣ ተምሮ መመረቅ?
እርግማን አይደል ወይ...
ሰው ሀገር ለመሥራት ፣ ተቸግሮ ማወቅ?
።፣፣፣፣፣።።።፣።፣፣
ምኑ ነው እውቀቱስ...
የተማሩት ነገር ፣ ላገር ካልጠቀመ
ምንስ ነው መቸገር....
ወድቀው ከፍ ያረጉት ፣ ሰው ሀገር ከቆመ?
ወይስ አልተቻለም...
እዚሁ ተምሮ ፣ እዚሁ ሀገር መስራት?
የተማረው ሁሉ...
ጥሏት ከነጎደ ፣
ማነው ይችን ሀገር ፣ የሚያስተዳድራት?
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ምንድነው እማምላክ
የሠው ሀገር ገንዘብ ፣ የሰው ሀገር ፍራንክ
በእልልታ ታጅቦ ፣ ከደጅሽ ሚመጣ?
በማለት እያማጥኩ...
ጥያቄ እየወረድኩ ፣ ጥያቄ ስወጣ...
።።።።፣፣።።።።
አውደ ምህረቱ ላይ ፣ የካህኑ ስብከት
ከታቦቱ ፊት ላይ....
"ተቃጠልኩኝ " የሚል
"አሰናብቺኝ " የሚል
በሰው ላይ ያደረ ፣ ያጋንንት ጩኸት
ከታቦቱ ዙርያ...
"አይኔ ነሽ ብርሃኔ
እመቤቴ ማርያም ፣ አብሶማ ለኔ"
እያለ ሚዘምር ፣ ክብ የሰራ ወጣት
ይህንን እያየሁ
ብዙ ጥያቄዎች ፣ ሳምጥ ሳጠራቅም
አንድ አይነ ስውር ሰው...
ፊቴ ተደቀነ ፣ ምፅዋት ሊለቅም፡፡
፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ምነው እመብርሀን
ታደዪ ይመሥል...
አይኔ ነሽ እያለ
አብሶማ እያለ ፣ ወጣቱ ሲዘምር
ምን ይሰማው ይሆን...
ከደጅሽ የመጣ ፣ ምስኪን አይነስውር?
ስል እጠይቃለሁ ፣ ደግሞ እታዘባለሁ
ጥያቄ እያማጥሁ ፣ እንባ እወልዳለሁ፡፡
እዘኝ አዛኝቱ!!!!!
@getem
@getem
@getem
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ወሩ መሥከረም ነው...
ቀኑ በሃያ አንድ ፣ በኢትዮጵያ አቆጣጠር
ግሸን ደብረ ከርቤ...
የ'መብርሐንን ፣ በአሏን ለማክበር
ከክርስቲያኖች ቤት...
አርፍጄ እንደደረስሁ ፣ታቦት ወጥቶ ነበር፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ከታቦቱ አጠገብ...
አውደ ምህረቱ ላይ ፣ ካህኑ ይሰብካል
አንዳንዱ ምእመን ፣
ተአምር ያዘለ ..
ብጫቂ ወረቀት ፣ ለካህኑ ይልካል
ደግሞ ሌላ ተአምር...
ለካህኑ ጆሮ ፣ ዲያቆኑ ያንሻኩካል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ካህኑ!
"ታ'ምር ነው ምእመናን ፣ አንድዜ እልል በሉ
አንኳኩ ይከፈታል ፣
ጠይቁ ይሰጣል ፣ ይላልና ቃሉ
"አፀደ ማርያም"
የተባለች እናት ፣ የማርያም ምስክር
ልጇን አስተምራ ፣ በስቃይ በችግር
ካንዱ ይንበርስቲ...
ተመርቆ ወጥቶ ፣ ያለ ሥራ ሲኖር
አምና በዚህ ሰዓት...
ከደጇ መጥቼ ፣ ተማፅኛት ነበር
ፀሎቴን ሰምታለች!
ልጄም ሥራ ይዞ ...
መቶ ዶላር ልኳል ፣ ካሜሪካን ሀገር፡፡"
ስብከቱን አቋርጦ ፣ ተአምር ሲናገር...
በሴቶች እልልታ ፣ በወንዶች ጭብጨባ
የኢትዮጵያዊት ስለት...
ካሚሪካን ሀገር ፣ ተልኮ ሲገባ
ጥያቄ አምጣለሁ ፣ ዐይኔ እስኪያረግዝ እንባ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
አላለሁ...
ምንድነው እዚህ ሀገር ፣ ተምሮ መመረቅ?
እርግማን አይደል ወይ...
ሰው ሀገር ለመሥራት ፣ ተቸግሮ ማወቅ?
።፣፣፣፣፣።።።፣።፣፣
ምኑ ነው እውቀቱስ...
የተማሩት ነገር ፣ ላገር ካልጠቀመ
ምንስ ነው መቸገር....
ወድቀው ከፍ ያረጉት ፣ ሰው ሀገር ከቆመ?
ወይስ አልተቻለም...
እዚሁ ተምሮ ፣ እዚሁ ሀገር መስራት?
የተማረው ሁሉ...
ጥሏት ከነጎደ ፣
ማነው ይችን ሀገር ፣ የሚያስተዳድራት?
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ምንድነው እማምላክ
የሠው ሀገር ገንዘብ ፣ የሰው ሀገር ፍራንክ
በእልልታ ታጅቦ ፣ ከደጅሽ ሚመጣ?
በማለት እያማጥኩ...
ጥያቄ እየወረድኩ ፣ ጥያቄ ስወጣ...
።።።።፣፣።።።።
አውደ ምህረቱ ላይ ፣ የካህኑ ስብከት
ከታቦቱ ፊት ላይ....
"ተቃጠልኩኝ " የሚል
"አሰናብቺኝ " የሚል
በሰው ላይ ያደረ ፣ ያጋንንት ጩኸት
ከታቦቱ ዙርያ...
"አይኔ ነሽ ብርሃኔ
እመቤቴ ማርያም ፣ አብሶማ ለኔ"
እያለ ሚዘምር ፣ ክብ የሰራ ወጣት
ይህንን እያየሁ
ብዙ ጥያቄዎች ፣ ሳምጥ ሳጠራቅም
አንድ አይነ ስውር ሰው...
ፊቴ ተደቀነ ፣ ምፅዋት ሊለቅም፡፡
፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ምነው እመብርሀን
ታደዪ ይመሥል...
አይኔ ነሽ እያለ
አብሶማ እያለ ፣ ወጣቱ ሲዘምር
ምን ይሰማው ይሆን...
ከደጅሽ የመጣ ፣ ምስኪን አይነስውር?
ስል እጠይቃለሁ ፣ ደግሞ እታዘባለሁ
ጥያቄ እያማጥሁ ፣ እንባ እወልዳለሁ፡፡
እዘኝ አዛኝቱ!!!!!
@getem
@getem
@getem
👍1
የሞት ተራራ ይደርመስ!!!!!!!
ጅል ያመረረ ቀን፤
ድንበርና አገሩን፤
ላፍርሰው ያለ እንደሁ፤
ሰው ይሞታል እንጅ፤ አገር አትሞትም፤
ሙት የጀለ ለታ፤
የጣለውን ሃገር ፤
ደግሞ ባለተራ መጥቶ ያበጀዋል ከየትም ከየትም።
በአድዋ በማይጨው፤
ሙቶ አገርን መስራት ፤ ነበር ትውፊታችን፤
ምነው በስተማታ፤
ሙቶ አገር ለመግደል መሽቀዳደማችን??
ይልቅ፤
በአምላክነት መልክህ፤
በሰው መሆን ልክህ፤
ዙፋንህ ላይ ወጥተህ፤
ህያው ህልም ገልጠህ፤
ከሞት ወዲህ ማዶ፤ ስምህ እንዲጠራ፤
በህይወት ድንበር ላይ፤
ሞት የሚደረምስ ፤
ህይወት የሚሞሽር፤ ምሽግህን ስራ፤
ልብ በል አንተ ሰው፤
ለሙት ህልም መሞት፤
የለውም ትንሳኤ፤ የለውም አሻራ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
ትላንት እዚህ ቻናል ላይ የተለቀቀው የምዕልቲ ኪሮስ "ኧረ አምሳለ " የምትለው ሸጋ ግጥም ደግሜ ደጋግሜ ባነባት ልጠግባት አልቻልኩም ለምን በሚጎመዝዘው ድምፄ አልሞክረውም አልኩኝና ግጥሙን ስለወደድኩት ብቻ አነበብኩት !
"ናካይታ"💚
@getem
@getem
@balmbaras
ጅል ያመረረ ቀን፤
ድንበርና አገሩን፤
ላፍርሰው ያለ እንደሁ፤
ሰው ይሞታል እንጅ፤ አገር አትሞትም፤
ሙት የጀለ ለታ፤
የጣለውን ሃገር ፤
ደግሞ ባለተራ መጥቶ ያበጀዋል ከየትም ከየትም።
በአድዋ በማይጨው፤
ሙቶ አገርን መስራት ፤ ነበር ትውፊታችን፤
ምነው በስተማታ፤
ሙቶ አገር ለመግደል መሽቀዳደማችን??
ይልቅ፤
በአምላክነት መልክህ፤
በሰው መሆን ልክህ፤
ዙፋንህ ላይ ወጥተህ፤
ህያው ህልም ገልጠህ፤
ከሞት ወዲህ ማዶ፤ ስምህ እንዲጠራ፤
በህይወት ድንበር ላይ፤
ሞት የሚደረምስ ፤
ህይወት የሚሞሽር፤ ምሽግህን ስራ፤
ልብ በል አንተ ሰው፤
ለሙት ህልም መሞት፤
የለውም ትንሳኤ፤ የለውም አሻራ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
ትላንት እዚህ ቻናል ላይ የተለቀቀው የምዕልቲ ኪሮስ "ኧረ አምሳለ " የምትለው ሸጋ ግጥም ደግሜ ደጋግሜ ባነባት ልጠግባት አልቻልኩም ለምን በሚጎመዝዘው ድምፄ አልሞክረውም አልኩኝና ግጥሙን ስለወደድኩት ብቻ አነበብኩት !
"ናካይታ"💚
@getem
@getem
@balmbaras
🔥1
የስጁዱ ሜዳ! !!!!!!
ይህ የሜዳ ጎበዝ ፤
ገምባሌውን ታጥቆ ፤
ማልያውን ለብሶ፤
እርም እርም ሲል፤
ለኳሱ ለጡንቻው ሲያረገርግ ውሎ፤
ደግሞ በርከክ ይላል ፤
ከስጁዱ ሜዳ አሏህ አክበር ብሎ ።
ከሜዳው መሃከል ፤
አዛን የወጣ እለት ፤
ስጁድ የወረደ ብሎ መርሃባ ፤
አይተናል ሰምተናል ፤
እንኳን በዱንያ ቤት ፤
በአኬራውም ሜዳ ብዙ ጎል ሲያስገባ ።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤️
ሸጋ ጁምኣ!💚
@getem
@getem
@balmbaras
ይህ የሜዳ ጎበዝ ፤
ገምባሌውን ታጥቆ ፤
ማልያውን ለብሶ፤
እርም እርም ሲል፤
ለኳሱ ለጡንቻው ሲያረገርግ ውሎ፤
ደግሞ በርከክ ይላል ፤
ከስጁዱ ሜዳ አሏህ አክበር ብሎ ።
ከሜዳው መሃከል ፤
አዛን የወጣ እለት ፤
ስጁድ የወረደ ብሎ መርሃባ ፤
አይተናል ሰምተናል ፤
እንኳን በዱንያ ቤት ፤
በአኬራውም ሜዳ ብዙ ጎል ሲያስገባ ።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤️
ሸጋ ጁምኣ!💚
@getem
@getem
@balmbaras
👍1
#የስደተኛ_ስንቅ
ቢጠበኝ ጎዳናው ፥ ቢቀጥን መስመሩ
ለፌሽታና ሀዘን
የሰው ልጅን እድሜ ፥ ቀናት ቢወጥሩ
መስሎ ማደር መልካም ፥ ለምዶ ማለፍ ጥሩ
አልጋ እንደሁ ፥ አልጋ ነው ፥ መርጠው ቢሳፈሩ
መጥፎ ሆነ መልካም ፥ ሳይተኙም አያድሩ
ቀን ሰጥቶ ማለፊያ ፥ ቦታ እስኪቀይሩ።
✍ #አብርሀም_ተክሉ
@getem
@getem
@getem
ቢጠበኝ ጎዳናው ፥ ቢቀጥን መስመሩ
ለፌሽታና ሀዘን
የሰው ልጅን እድሜ ፥ ቀናት ቢወጥሩ
መስሎ ማደር መልካም ፥ ለምዶ ማለፍ ጥሩ
አልጋ እንደሁ ፥ አልጋ ነው ፥ መርጠው ቢሳፈሩ
መጥፎ ሆነ መልካም ፥ ሳይተኙም አያድሩ
ቀን ሰጥቶ ማለፊያ ፥ ቦታ እስኪቀይሩ።
✍ #አብርሀም_ተክሉ
@getem
@getem
@getem
👍1
"ወርቅ ቅብ"
#ሚካኤል ኤርሚያስ
***
እኔማ.......
ወርቅ መምሰያ ቅብሽ
ጥቂት አየለና አይኔን ቢጋርደው
በቀይ እንቁው ሚዛን
አንቺን ቅባቅቧን እመዝንሻለው
ከዛ.....
ላላፊ አግዳሚው
እሳቱን ይመስል ወርቅ ናት እላለው
ምንም ቢገዝፋ ቅባቅብሽ
ወርቅ እማ ወርቅ ነሽ ለኔለአፍቃሪሽ
እስኪ አስቢው .....አሁን ምን ይሉታል......?
በቀይ እንቁ ሚዛን ቅባ ቅብ መመዘን
በይሁንታ ምኞት
ወርቅ ናት እያሉ በአንደበት ማላዘን
ልብን እያራዱ በልበ ኦና ማዘን
ንፍገተ ክብርሽን በላይሽ ላይ መድፍት
በፍቅርሽ ታፍሮ
ሀሰትሽን ታቅፎ ሀቅ ላይ መደንፍት
እኮ ይሄን ምን ይሉታል......?
በእሳቤ ጥጋጎት ወደላይ ማንጋጠጥ
የፈጠረሽ ጌታን
ወርቅ አድርግልኝ ብሎ ዘውትር መለማመጥ
እስኪሰማኝ ድረስ ሌላ አለማዳመጥ
በህላዌ አንድምታ
በጥቀርሻ ጥፍር አይምሮንመቧጠጥ
ወርቀ ቅባ ቅብነትሽ ታጥቦ እንዲለቅሽ
ማሳበቅ ላምላኬ ማሳበቅ ላምላክሽ
እሱ..ምንም ማይሳነው ..
ወርቁን እንዲያደርግሽ
መማፀን በእግዜሩ ቤት ስምሽ
:
ይሄ ብቻ መስሎሽ........
:
የኔ የልብ መሻት....
ከምመዝንበት
ከቀይ እንቁ አክብሬሽ በጥበብ ሰውሬሽ
እስከ ዐለም እጥፍት ነበር ፍላጎቴ በልቤ ላኖርሽ
ይሄ የኔ መሻት ነው .........
እሷ ግን ......
አሁን ያልኩት ሁሉ ለሷ እንዲሆንላት
ማንጋጠጤን አይቶ እንዲፈፅምላት
ቅባቅቧን ነስቶ ወርቁን እንዲያለብሳት
በጥበብ ሞሽሮ ከልቤ እንዲያውላት
ምለምንበትን ልብ ምልበትን
እኔነቴን ሰልባህቃቆቴን ነስታ
ቀልበ ቢስ ትላለች ማረሻ ስለቴን
አቀቀርቅራ እያየች ከጎኔ ተኝታ።
@getem
@getem
@getem
#ሚካኤል ኤርሚያስ
***
እኔማ.......
ወርቅ መምሰያ ቅብሽ
ጥቂት አየለና አይኔን ቢጋርደው
በቀይ እንቁው ሚዛን
አንቺን ቅባቅቧን እመዝንሻለው
ከዛ.....
ላላፊ አግዳሚው
እሳቱን ይመስል ወርቅ ናት እላለው
ምንም ቢገዝፋ ቅባቅብሽ
ወርቅ እማ ወርቅ ነሽ ለኔለአፍቃሪሽ
እስኪ አስቢው .....አሁን ምን ይሉታል......?
በቀይ እንቁ ሚዛን ቅባ ቅብ መመዘን
በይሁንታ ምኞት
ወርቅ ናት እያሉ በአንደበት ማላዘን
ልብን እያራዱ በልበ ኦና ማዘን
ንፍገተ ክብርሽን በላይሽ ላይ መድፍት
በፍቅርሽ ታፍሮ
ሀሰትሽን ታቅፎ ሀቅ ላይ መደንፍት
እኮ ይሄን ምን ይሉታል......?
በእሳቤ ጥጋጎት ወደላይ ማንጋጠጥ
የፈጠረሽ ጌታን
ወርቅ አድርግልኝ ብሎ ዘውትር መለማመጥ
እስኪሰማኝ ድረስ ሌላ አለማዳመጥ
በህላዌ አንድምታ
በጥቀርሻ ጥፍር አይምሮንመቧጠጥ
ወርቀ ቅባ ቅብነትሽ ታጥቦ እንዲለቅሽ
ማሳበቅ ላምላኬ ማሳበቅ ላምላክሽ
እሱ..ምንም ማይሳነው ..
ወርቁን እንዲያደርግሽ
መማፀን በእግዜሩ ቤት ስምሽ
:
ይሄ ብቻ መስሎሽ........
:
የኔ የልብ መሻት....
ከምመዝንበት
ከቀይ እንቁ አክብሬሽ በጥበብ ሰውሬሽ
እስከ ዐለም እጥፍት ነበር ፍላጎቴ በልቤ ላኖርሽ
ይሄ የኔ መሻት ነው .........
እሷ ግን ......
አሁን ያልኩት ሁሉ ለሷ እንዲሆንላት
ማንጋጠጤን አይቶ እንዲፈፅምላት
ቅባቅቧን ነስቶ ወርቁን እንዲያለብሳት
በጥበብ ሞሽሮ ከልቤ እንዲያውላት
ምለምንበትን ልብ ምልበትን
እኔነቴን ሰልባህቃቆቴን ነስታ
ቀልበ ቢስ ትላለች ማረሻ ስለቴን
አቀቀርቅራ እያየች ከጎኔ ተኝታ።
@getem
@getem
@getem
ኢሬቻ ሀቻምና
# ዋቃ # ዝም # አትበል
ሙስዓብ ዑመይር
ምርቃት ያወዛው ቂቤ የጠገበ ዱላ ተመርኩዞ...፣
ዋቃን ሊለማመን ሚስት ልጁን ይዞ....፣
ኢሬቻን ሊያደምቅ ለምለም ሳሩን መዞ....፣
ፀብ ጥላቻን ሊሽር መከራን ሊከላ....፣
ለምለም አመት ሊመኝ ኪዳኑን ሊሞላ....፣
አማን ሰላም ብሎ ዋቃን ተወክሎ....፣
ከቀዬው ለራቀ ሁሉን ለሱ ጥሎ....፣
የስቃይ ጣር ማሾር የሞት ሾተል መምዘዝ....፣
ቀጤማውን አጭዶ ሬሳን መጎዝጎዝ....፣
ሀጫ ንክር ሸማን በደም አጨማልቆ....፣
እናትን ጉድጓድ ስር በአፍጢሟ ዘቅዝቆ....፣
አባት ከነ ዱላው በጥይት ታምሶ በጥይት ሲደቆስ....፣
አንዲት ፍሬ ጨቅላ አባቷን በለቅሶ የምትቀሰቅስ .....፣
በዚህ ሁላ መሀል ዋቃ ዝም ብሏል ...፣
ለግፈኞች ምላሽ ለምንዱባን ጋሻ ከመሆን ቦዝኗል...፣
በዚህ ሁሉ መሀል አንድ ጩኸት ሰማሁ....፣
ሚስት ልጄን አጣሁ ሁሉንም ተቀማሁ....፣
ኢሬቻ ምንድነው ዋቃ የት ነህ አንተ....፣
ለክብርህ ምስጋና ከደጅህ ለሞተ....፣
ማእረጉ ምንድነው ሁሉን ለተቀማ.....፣
የበዳዬስ እጣ ?? ተናገር ወይ ስማ....፣
ያዋቃ!! ዝም አትበል ዝምታህ ያመኛል....፣
የበደነ አካሌን በደንዝ ያርደኛል ....፣
ዋቃ ዝም አትበል.....፣
አዎ ዝም አትበል...፣
.
.
.
በደም የላቆጠ ሌጣ አካሉን ይዞ....፣
እሳት የሚተፋ በቀልን አርግዞ....፣
ሲጮህ ይሰማኛል....፣
ዋቃ ዝም አትበል ዝምታህ ያመኛል....፣
የበደነ አካሌን በደነዝ ያርደኛል......፣
#አሁን ያ ሁሉ አልፏል !!
"ናካይታ" 💚 ነጋቲ ቡላ!💚
@getem
@getem
@balmbaras
# ዋቃ # ዝም # አትበል
ሙስዓብ ዑመይር
ምርቃት ያወዛው ቂቤ የጠገበ ዱላ ተመርኩዞ...፣
ዋቃን ሊለማመን ሚስት ልጁን ይዞ....፣
ኢሬቻን ሊያደምቅ ለምለም ሳሩን መዞ....፣
ፀብ ጥላቻን ሊሽር መከራን ሊከላ....፣
ለምለም አመት ሊመኝ ኪዳኑን ሊሞላ....፣
አማን ሰላም ብሎ ዋቃን ተወክሎ....፣
ከቀዬው ለራቀ ሁሉን ለሱ ጥሎ....፣
የስቃይ ጣር ማሾር የሞት ሾተል መምዘዝ....፣
ቀጤማውን አጭዶ ሬሳን መጎዝጎዝ....፣
ሀጫ ንክር ሸማን በደም አጨማልቆ....፣
እናትን ጉድጓድ ስር በአፍጢሟ ዘቅዝቆ....፣
አባት ከነ ዱላው በጥይት ታምሶ በጥይት ሲደቆስ....፣
አንዲት ፍሬ ጨቅላ አባቷን በለቅሶ የምትቀሰቅስ .....፣
በዚህ ሁላ መሀል ዋቃ ዝም ብሏል ...፣
ለግፈኞች ምላሽ ለምንዱባን ጋሻ ከመሆን ቦዝኗል...፣
በዚህ ሁሉ መሀል አንድ ጩኸት ሰማሁ....፣
ሚስት ልጄን አጣሁ ሁሉንም ተቀማሁ....፣
ኢሬቻ ምንድነው ዋቃ የት ነህ አንተ....፣
ለክብርህ ምስጋና ከደጅህ ለሞተ....፣
ማእረጉ ምንድነው ሁሉን ለተቀማ.....፣
የበዳዬስ እጣ ?? ተናገር ወይ ስማ....፣
ያዋቃ!! ዝም አትበል ዝምታህ ያመኛል....፣
የበደነ አካሌን በደንዝ ያርደኛል ....፣
ዋቃ ዝም አትበል.....፣
አዎ ዝም አትበል...፣
.
.
.
በደም የላቆጠ ሌጣ አካሉን ይዞ....፣
እሳት የሚተፋ በቀልን አርግዞ....፣
ሲጮህ ይሰማኛል....፣
ዋቃ ዝም አትበል ዝምታህ ያመኛል....፣
የበደነ አካሌን በደነዝ ያርደኛል......፣
#አሁን ያ ሁሉ አልፏል !!
"ናካይታ" 💚 ነጋቲ ቡላ!💚
@getem
@getem
@balmbaras
የ # ኢሬቻ ግብዣ
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
ኢልማ ገልማ
አባ ገዳ ርቱእ ጀማ
ብፁእ ጀማ
ለካ አንተ ነህ
አባ ገዳ ኢልማ ገልማ
ያደ ኦሮሞ ሻማ
ዋቃ ገዲ ነማ ኦሊን ሱማ
አከ ሱማ
የተሰኘዉ እንደ አክሱም
የተባልከዉ ፍፁም ጀማ
ለካ አንተ ነህ
አገ ኦጋ
ጂገ ሎጋ
አባ ሰርዳ
አባ ገዳ
አባ ፈርደ ነበልባሉ
እም ቅድመ ኦሪት ባህሉ
ያኢ ቢያ አባ ቃሉ
የማይቀለበስ ቃሉ
ለካ አንተ ነህ
ሴራ አርካ ኦገ ገዳ
የአድባር ዋርካ
ያዴ እናቴ
ያዴ እስቴ
ያዴ አተቴ
ያዴ እቴቴ
ያቴ ሆራ የኩሽ ነዶ
አባ ቦኩ አከም ኢዶ
በአናትህ ፀሃይ ከለቻ
የምትጠልቅ አንተ ብቻ
የካም ኢደ ኢዶ ምድር
ተነባቢ የአስር ሚስጥር
አባ ወሮ አባ ወራ
አባ ባሮ አባ በራ
የጅቡቲም ጀበ ዲሾ
የመቅዲሾም መቀ ዲሾ
የነሙንቴሳ ካም በልአ
እንደ ብራቡ ከምፐላ
መነ ደላ አከ መንደላ
መቀ ደላ አከ መቅደላ
የፊላኒ ካኖደላ
የምትሰኝ የምታሰኝ
የጎና ቤት አባ ወራ
የላሊ ቤት ላሊበላ
በጎፈሬህ ስሪት ላባ
አዶ አዶየ ዉብ ቀዘባ
አዳ የከለቻ ተሸላሚ
ያዱ ግንባር ተቀዳሚ
የአዲስ ዘመን መፀዉ አደይ
አዳ...አዱኛን እልል እሰይ
የምታሰኝ...የምትሰኝ
አዱ አዱኛ
አባ ቢሌ
የአካ ኪሌ
የአባ ቢሌ
ለካ አንተ ነህ
ገዳ ገዳም
የአለም ሰላም
ገዳ ቢሊሱማ ሳቃ
ፈካ ጉራቻ አካ ዋቃ
የመፀሃፍት አምላኩ አኒ
ያለበሰህ ድርብ ካኒ
የጥቁር ፈርኦን ልሳን
የአዴ አዳ ፀሃይ ብርሃን
የአዱሊስ አዱኛ ኪዳን
አባ ገዳ አባ በአል
የቅድመ አክሱማዊት ቃል
የአስርቱ በሮች መሰላል
የማለዳ ንጋት ፀዳል
የኦሩስ ኦሪሳ ተምሳል
ለካ አንተ ነህ
አገ ኦጋ
ጂገ ሎጋ
ያኢ ቢያ አባ ቃሉ
የማይቀለበስ ቃሉ
ርቱእ ጀማ
የተባልከዉ አባ ሱማ
እንደ አክሱማ
ያደ ኦሮሞ ሻማ
አባ ገዳ ኢልመ ገልማ
ለካ አንተ ነህ::
፨ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን፨
ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሚት!❤❤
"ናካይታ" 💚💚💚
@getem
@getem
@balmbaras
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
ኢልማ ገልማ
አባ ገዳ ርቱእ ጀማ
ብፁእ ጀማ
ለካ አንተ ነህ
አባ ገዳ ኢልማ ገልማ
ያደ ኦሮሞ ሻማ
ዋቃ ገዲ ነማ ኦሊን ሱማ
አከ ሱማ
የተሰኘዉ እንደ አክሱም
የተባልከዉ ፍፁም ጀማ
ለካ አንተ ነህ
አገ ኦጋ
ጂገ ሎጋ
አባ ሰርዳ
አባ ገዳ
አባ ፈርደ ነበልባሉ
እም ቅድመ ኦሪት ባህሉ
ያኢ ቢያ አባ ቃሉ
የማይቀለበስ ቃሉ
ለካ አንተ ነህ
ሴራ አርካ ኦገ ገዳ
የአድባር ዋርካ
ያዴ እናቴ
ያዴ እስቴ
ያዴ አተቴ
ያዴ እቴቴ
ያቴ ሆራ የኩሽ ነዶ
አባ ቦኩ አከም ኢዶ
በአናትህ ፀሃይ ከለቻ
የምትጠልቅ አንተ ብቻ
የካም ኢደ ኢዶ ምድር
ተነባቢ የአስር ሚስጥር
አባ ወሮ አባ ወራ
አባ ባሮ አባ በራ
የጅቡቲም ጀበ ዲሾ
የመቅዲሾም መቀ ዲሾ
የነሙንቴሳ ካም በልአ
እንደ ብራቡ ከምፐላ
መነ ደላ አከ መንደላ
መቀ ደላ አከ መቅደላ
የፊላኒ ካኖደላ
የምትሰኝ የምታሰኝ
የጎና ቤት አባ ወራ
የላሊ ቤት ላሊበላ
በጎፈሬህ ስሪት ላባ
አዶ አዶየ ዉብ ቀዘባ
አዳ የከለቻ ተሸላሚ
ያዱ ግንባር ተቀዳሚ
የአዲስ ዘመን መፀዉ አደይ
አዳ...አዱኛን እልል እሰይ
የምታሰኝ...የምትሰኝ
አዱ አዱኛ
አባ ቢሌ
የአካ ኪሌ
የአባ ቢሌ
ለካ አንተ ነህ
ገዳ ገዳም
የአለም ሰላም
ገዳ ቢሊሱማ ሳቃ
ፈካ ጉራቻ አካ ዋቃ
የመፀሃፍት አምላኩ አኒ
ያለበሰህ ድርብ ካኒ
የጥቁር ፈርኦን ልሳን
የአዴ አዳ ፀሃይ ብርሃን
የአዱሊስ አዱኛ ኪዳን
አባ ገዳ አባ በአል
የቅድመ አክሱማዊት ቃል
የአስርቱ በሮች መሰላል
የማለዳ ንጋት ፀዳል
የኦሩስ ኦሪሳ ተምሳል
ለካ አንተ ነህ
አገ ኦጋ
ጂገ ሎጋ
ያኢ ቢያ አባ ቃሉ
የማይቀለበስ ቃሉ
ርቱእ ጀማ
የተባልከዉ አባ ሱማ
እንደ አክሱማ
ያደ ኦሮሞ ሻማ
አባ ገዳ ኢልመ ገልማ
ለካ አንተ ነህ::
፨ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን፨
ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሚት!❤❤
"ናካይታ" 💚💚💚
@getem
@getem
@balmbaras
ባለ ቤት አልባ ገፅ
©
የእፎይታሽ ግኝት፣
የ'ስትንፋስሽ ድሪት
ጠያይም ልጆችሽ፣
በስሪያ ንድ መንገድ፣አልፈው የተጓዙ፣
ቅያም...
ጥያም...
ቃልን በአፈር እያዋዙ፣
•
•
(ማሌ...ሱርጳ...ይላሉ)
ግልድም ዝር ዘመንን፣
በዘመን መንዝረው፣ጥበብ ይፈትላሉ፡፡
•
(ማሌ)
•
ሹል...ውብ...እርሳስ፣
ከውጥር ሸራ ላይ
'ባሳብ ሚርመሰመስ፣
በ'ውነት ድሳስ ላይ፣
ቅላሙን የሚያፈስ...
በድብዛዝ ቀለሙ፣መንፈስን እሚያድስ፡፡
የረጠበ ብሩሽ...
በቀለም ንክሩ...
ነፍስ አልባውን ገላ
በስልቱ የሚያሻሽ፣
•
(ሱርጳ)
•
በነጭ ወረቀት ላይ
በስራር ሚሰደር ...
ቀይ...ጥቁር...ቀለም፣
ከብዕር ገላ ላይ
ሲማልል የሚውል
ተንከራታች ፊደል፡፡
ጥሉል ጠበብተኛ...ብሶተኛ አገር፣
አ
.
ገ
.
ር
.
እንደ ፊደል!
•
(ማሌ...ሱርጳ)
•
የነፍስሽ ውብ ጊጠት፣
የሕይወትሽ ቃማ፡፡
በንቅስ የጠቆረ...
የጠይም ልጆችሽ
አስደናቂ ገላ፡፡
...///....
29/12/2010
ሻሸመኔ...ባዶ ምናምን ላይ
@getem
@getem
@gebriel_19
©
የእፎይታሽ ግኝት፣
የ'ስትንፋስሽ ድሪት
ጠያይም ልጆችሽ፣
በስሪያ ንድ መንገድ፣አልፈው የተጓዙ፣
ቅያም...
ጥያም...
ቃልን በአፈር እያዋዙ፣
•
•
(ማሌ...ሱርጳ...ይላሉ)
ግልድም ዝር ዘመንን፣
በዘመን መንዝረው፣ጥበብ ይፈትላሉ፡፡
•
(ማሌ)
•
ሹል...ውብ...እርሳስ፣
ከውጥር ሸራ ላይ
'ባሳብ ሚርመሰመስ፣
በ'ውነት ድሳስ ላይ፣
ቅላሙን የሚያፈስ...
በድብዛዝ ቀለሙ፣መንፈስን እሚያድስ፡፡
የረጠበ ብሩሽ...
በቀለም ንክሩ...
ነፍስ አልባውን ገላ
በስልቱ የሚያሻሽ፣
•
(ሱርጳ)
•
በነጭ ወረቀት ላይ
በስራር ሚሰደር ...
ቀይ...ጥቁር...ቀለም፣
ከብዕር ገላ ላይ
ሲማልል የሚውል
ተንከራታች ፊደል፡፡
ጥሉል ጠበብተኛ...ብሶተኛ አገር፣
አ
.
ገ
.
ር
.
እንደ ፊደል!
•
(ማሌ...ሱርጳ)
•
የነፍስሽ ውብ ጊጠት፣
የሕይወትሽ ቃማ፡፡
በንቅስ የጠቆረ...
የጠይም ልጆችሽ
አስደናቂ ገላ፡፡
...///....
29/12/2010
ሻሸመኔ...ባዶ ምናምን ላይ
@getem
@getem
@gebriel_19
‹‹ሴት ሀገር›› የእንክብል ግጥሞች መጽሐፍ ዓርብ መስከረም 30 ቀ ን 2012 ዓ .ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ 5 ኪሎ በሚገኘው በቅርስና ጥናት ባለስልጣን አዳራሽ አንጋፋ ደራሲያንና ስመጥር የኪነ ጥበብ ሰዎች በተገኙበት ይመረቃል፡፡
በሥነ ሥርዐቱ ላይ፡- ዶ/ር ንጉሤ ተፈራ፣ ወንድም ንጉሤ ቡልቻ፣ ደራሲ ጌታቸው በለጠ - እንዲሁም ገጣሚያኑ፡- ወንድዬ አሊ(አንጋፋው ገጣሚ)፣ ረድኤት ተረፈ፣ ሰይፉ ወርቁ፣ በቃሉ ሙሉ እንዲሁም ምኒልክ ብርሃኑ እንደሚገኙ ሰም እና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት አስታውቋል፡፡
መጽሐፉን አስቀድመው ለመግዛት ከሥር ባለው አድራሻ ይከተቱ . . .
አ ከ ፋ ፋ ዮ ች -
- ጃዕፋር የመጻሕፍት መደብር /የድሮው ለገሀር መኪና ተራ ፊት ለፊት/
- ጸጋዬ የመጻሕፍት መደብር /ጉርድ ሾላ ሆሊ ሲቲ ሴንተር/
+𝟚𝟝𝟙 𝟡𝟙𝟛𝟛𝟙𝟝𝟡𝟚𝟛
+𝟚𝟝𝟙 𝟡𝟜𝟟𝟡𝟘𝟙𝟟𝟟𝟘
ለበለጠ መረጃ - +𝟚𝟝𝟙 𝟡𝟚𝟝𝟚𝟝𝟛𝟟𝟜𝟛
🤙
#ℤ𝕖𝕞𝕒𝕥
#𝕊𝕚𝕖𝕥ℍ𝕒𝕘𝕒𝕖𝕣
#𝔽𝕖𝕖𝕝𝕚𝕥
በሥነ ሥርዐቱ ላይ፡- ዶ/ር ንጉሤ ተፈራ፣ ወንድም ንጉሤ ቡልቻ፣ ደራሲ ጌታቸው በለጠ - እንዲሁም ገጣሚያኑ፡- ወንድዬ አሊ(አንጋፋው ገጣሚ)፣ ረድኤት ተረፈ፣ ሰይፉ ወርቁ፣ በቃሉ ሙሉ እንዲሁም ምኒልክ ብርሃኑ እንደሚገኙ ሰም እና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት አስታውቋል፡፡
መጽሐፉን አስቀድመው ለመግዛት ከሥር ባለው አድራሻ ይከተቱ . . .
አ ከ ፋ ፋ ዮ ች -
- ጃዕፋር የመጻሕፍት መደብር /የድሮው ለገሀር መኪና ተራ ፊት ለፊት/
- ጸጋዬ የመጻሕፍት መደብር /ጉርድ ሾላ ሆሊ ሲቲ ሴንተር/
+𝟚𝟝𝟙 𝟡𝟙𝟛𝟛𝟙𝟝𝟡𝟚𝟛
+𝟚𝟝𝟙 𝟡𝟜𝟟𝟡𝟘𝟙𝟟𝟟𝟘
ለበለጠ መረጃ - +𝟚𝟝𝟙 𝟡𝟚𝟝𝟚𝟝𝟛𝟟𝟜𝟛
🤙
#ℤ𝕖𝕞𝕒𝕥
#𝕊𝕚𝕖𝕥ℍ𝕒𝕘𝕒𝕖𝕣
#𝔽𝕖𝕖𝕝𝕚𝕥
❤1
፩ ናታን ዬ ፩
/ዳንኤል ሉሌ/
ቃላቶች ሊፅፉሽ፤
ፊደላት ሊገልፁሽ።
፡
በፍቅር የታጠርሽ ፍቅር ተጎናፅፈሽ፤
ከቃላት በላይ ነሽ።
፡
ደግነትሽ ብዙ ውለታሽ እልፋ ነው፤
አንቺን የሚገልፁሽ የትኛው ቃላት ነው።
፡
ማሬ እዳልልሽ እሱም አይመጥንሽ፤
ፋቅር እዳልልሽ የፍቅር ሚዛን ነሽ።
፡
ውዴም እዳልልሽ ከውድም በላይ ነሽ፤
ኪያዬ እዳልልሽ እሱም አነሰብሽ፤
የልቤ እዳልልሽ የአካላቶቼ ነሽ፤
ቁጣየን አብርደሽ ፋቅር መግበሽ፤
ፋቅር አስተምረሽ ኩርፊያየን ያስቀረሽ፤
አቺን ማለት ለኔ በቃ ናታኔ ነሽ።
፡
አወ ናታኔ ነሽ የእ/ር ስጦታ እ/ር የሰጠኝ፤
አቺን ከሰው መሐል መርጦ የሸለመኝ።
፡
ባቺ ኮነው ናታን ሙሉ ሰው የሆኩኝ።
ፍቅርን የተማርኩኝ፤
ትግስትን ያወኩኝ፤
ኩርፊያየን የተውኩኝ፤
ከልቤ ልንገርሽ እውነቱን ካመሽኝ፤
እኔን ካፈቀርሽኝ እውነቱን እመኝኝ።
፡
አንደበቴ አይገልፅሽ፤
ቃላት አይመጥንሽ፤
የሂወቴ አንድ አካል እስትፋሴ እኮ ነሽ።
፡
ይን ፍቀጂልኝ ዘላለም ላፍቅርሽ፤
ናታንዬ ብዬ ስጦታየ ላርግሽ።
@getem
@getem
@gebriel_19
/ዳንኤል ሉሌ/
ቃላቶች ሊፅፉሽ፤
ፊደላት ሊገልፁሽ።
፡
በፍቅር የታጠርሽ ፍቅር ተጎናፅፈሽ፤
ከቃላት በላይ ነሽ።
፡
ደግነትሽ ብዙ ውለታሽ እልፋ ነው፤
አንቺን የሚገልፁሽ የትኛው ቃላት ነው።
፡
ማሬ እዳልልሽ እሱም አይመጥንሽ፤
ፋቅር እዳልልሽ የፍቅር ሚዛን ነሽ።
፡
ውዴም እዳልልሽ ከውድም በላይ ነሽ፤
ኪያዬ እዳልልሽ እሱም አነሰብሽ፤
የልቤ እዳልልሽ የአካላቶቼ ነሽ፤
ቁጣየን አብርደሽ ፋቅር መግበሽ፤
ፋቅር አስተምረሽ ኩርፊያየን ያስቀረሽ፤
አቺን ማለት ለኔ በቃ ናታኔ ነሽ።
፡
አወ ናታኔ ነሽ የእ/ር ስጦታ እ/ር የሰጠኝ፤
አቺን ከሰው መሐል መርጦ የሸለመኝ።
፡
ባቺ ኮነው ናታን ሙሉ ሰው የሆኩኝ።
ፍቅርን የተማርኩኝ፤
ትግስትን ያወኩኝ፤
ኩርፊያየን የተውኩኝ፤
ከልቤ ልንገርሽ እውነቱን ካመሽኝ፤
እኔን ካፈቀርሽኝ እውነቱን እመኝኝ።
፡
አንደበቴ አይገልፅሽ፤
ቃላት አይመጥንሽ፤
የሂወቴ አንድ አካል እስትፋሴ እኮ ነሽ።
፡
ይን ፍቀጂልኝ ዘላለም ላፍቅርሽ፤
ናታንዬ ብዬ ስጦታየ ላርግሽ።
@getem
@getem
@gebriel_19