ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
የሙዚቃው ፈርጥ

ገና በአፍላነቱ ለጥበብ የተጠራ
የኢትዮጵያን ሙዚቃ ወደፊት የመራ፤
ግጥምና ዜማን አርቅቆ የደረሰ
የጥበብን እንባ በእጁ ያበሰ፤
ፒያኖና ጊታርን ከልቡ ተጫውቶ
እልፍ ስራዎቹን ለሰሚ አበርክቶ
ዛሬ እሱ አለፈ አብይ ታሪክ ትቶ፤
የአምላክ ፍቃድ ሆኖ ከኛ ብትለይም
ህያው ስራዎችክ ፈፅሞ አይሞቱም፤
ኤልያስ መልካ የሙዚቃው ብስራት
ነብስህን ያኑራት በአፀደ ገነት።

ተፃፈ በኤርሚያስ(የእገሌ ልጅ)
መስከረም 24 - 2012 ዓም
@getem
@getem
@getem
@Eromaa
ነብስ ይማር

@getem
ቀጥታ ግጥም(live poem)
(ልዑል ኃይሌ)
..
የሐበሻ ቀጠሮ
ይለመድ በዓለሙ ይለመድ በሐገሩ፤
ሞትም አርፋጅ ይሁን
ሚወዱትን አጥተው እንዳይቸገሩ፤
ሞት እንደተማሪ
ቢያረፍድ ቢዘገይም
ስለማይቀጣ፤
ለሚወዱት ሲባል
ሞት ዘግይቶ ይምጣ፤
24-01-12ዓ.ም.
ከምሽቱ 4:31


@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
የጥበብ ዋርካ

ብሩህ ልቦና እግዜር የሰጠው
ለኪነ ጥበብ የተገለጠው
ትጉህ ታታሪ አያውቅም ድካም
ዘመን 'ሚሻገር ሳይከትብ አይረካም
የሀገሬ ኮከብ የሀገሬ ፈርጧ
በእውነት የወጣ ካ'ብራክ ከውስጧ
አዳዲስ ሀሳብ የሚበረብር
በተለየ ስልት የሚያቀናብር
የሙዚቃው ሊቅ ኤልያስ መልካ
የጥበብ አድባር የጥበብ ዋርካ
ሞተ ይላሉ ሞት ለ'ሱ ምኑ
ሕይወት ለዘራ በእድሜ ዘመኑ

ሁሌም ይወሳል በፍቅር አድባር
በሰላም አድባር
በኪነት አድባር
ሕያው በስራው ሕያው በተግባር ! ።

((የአስራትፍሬ))

ደምቆ ያደመቀን አበባ 'ረገፈ
የሀገሬ የጥበብ ቆሌ ተገፈፈ !።

@getem
@getem
@getem
ወዮ አለም
#_______ሲራክ__________
የዘመነ ርሑቅ ንዑሰ ወሬዛ
ቀዳማይ የሆንከው የጦቢያችን ቤዛ
በልመና ቅኔ ሆዴን ሙላ ያልከው
ሀበሻው ሰማና ጎረቤቱን ጠራው
----------------//----------------
ሲራክ
መስከረም ፪፼፲፪ ዓ.ም
ሚዛን ተፈሪ
ኢትዮጵያ

@getem
@getem
ጭፍን አማኝ !!

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።።።።።።።።።።።።

እኔማ...

የሕይወት ስሌቴ ፥ መተንፈሻ በሯ 

የጎጆዬ ደጀን ፥ ምሰሶ ማገሯ 

የግቢዬ ፍካት ፥ አበባና ስሯ 

እሷ ናት እያልሁኝ

እንዲህ እያሰብሁኝ

ስንት ዘመን ቀርጥፌ

ዓመታትን ኖርሁኝ።

ይብላኝ እንጂ ለኔ!

መገን የሷ ፍጥረት

የውበት ሰገነት

ዓይኗ ጠሀይ ሆኖ ፥ በዓለም የሚያበራ

ሽንጧ የሺህ ግምት ፥ ዳሌዋ ተራራ

ተረከዘ ሎሚ ፥ ጣቶቿ አለንጋ

ጡቷ የንጉስ ጦር ፥ ደረት የሚወጋ

እያልሁ ለምፎክር 

መንደር ለማሸብር

በመልክሽ ምጥማጥ ውስጥ

እግሬን ቀብድ አሲዤ

እዛዉ ለምዳክር ።

ልቤን ኸሌማቱ ፥ ከበላይ አኑሬ

ቁረሺ ለምልሽ ፥ ሥጋዬን ደርድሬ

ይብላኝ እንጂ ለኔ!

ሀገሬዉ በስላቅ ፥ እሳት ለገረፈኝ

በከንፈሩ ምፀት 

አልሰማም እያለ ፥ ሀዘኑን ለቸረኝ

ይብላኝ እንጂ ለኔ!

ጣዖቴ ነሽ ብዬ ፥ ሰግጄ ሳልጨርስ

መልክዐ ስምሽን ፥ ቀድሼ ሳልጨርስ

ንፁህ ናት እያልሁኝ ፥  ለማድር ፎክሬ

ጆሮዬን ላሸሸሁ ፥ ከመንደሩ ወሬ።

ይብላኝ እንጂ ለኔ!

በዘመናት ማምሻ ፥ ሀቅ አገኘሁ ብዬ ፥ ስለት ለገበርሁኝ

ከፀሎቴ ማግስት ...

ከሰው ጋር ተኝተሽ ፥ የቀኑ ቅዠቴን ፥ በቁም ለተጋትሁኝ።

@getem
@getem
@getem
በአንድ ሰከንድ ወርቅ ይወሰዳል
በአንድ ቃል ጠብ ይበርዳል
በአንድ ጎል ዋንጫ ይበላል
በአንድ ቃል ፍቅር ይጸናል
በአንድ ቃል ቤት ይቆማል
አንድ ትንሽ አይደለችም ፣

((ራስን ፍለጋ)) fb

@getem
@getem
የትዝታ ፈውስ(ልዑል ኃይሌ)

'ታማለች' ሲሉኝ ነው
ከየስራስሩ
ከየዛፉ ዞሬ ቅጠል መበጠሴ፤
ርቀሺኝ ለመሄድ
ሰበብ መሆኑን ሳውቅ
ታጠንኹት ለራሴ፤
.
ደስ ሲል ባሕር ዛፍ
ደስ ሲል ያ ቅጠል፤
አዳነኝ ከሕመም ባንቺ ከመቃጠል፤
.
ይኸው ከዚያ ወዲያ
ኑሮዬን መስርቼ
በየቅጠሉ ስር በየስራስሩ፤
ታጥኜ እንደወጣሽ ታጠነ ሠፈሩ፤
እኔ እንደረሳሁሽ
ዘንግቶሽ ጎዳናው፤
እንደቆረጠልኝ
ቆረጦለት ደመናው፤
ማጉረምረሙን ተወ
ጭፍግግ ሰማይ በራ፤
እኔን ያዳነ ፈውስ
አንቺን ለሚያስታውስ ሕመምተኛ ሠራ፤
....
እሰይ!
ይታጠን ያ 'ካፌ'
ይታጠን 'ሲኒማ'ው
ይታጠን ይታጠን የሄድንበት ቦታ፤
ትርፉ መታመም ነው
እቴ ያንቺ ትዝታ፤
24-01-2012ዓ.ም.
ከሌሊቱ 7:12

@getem
@getem
@getem
****ከሀሳብ በፊት**

ለውሳኔ ከባድ ~ግራ የሚያጋባ
ላሳብ የሚገፋ ~እልክ የሚያስገባ
በትዕዛዝ ተሰርቶ
በፍቅር በርክቶ
በደስታ ተሞልቶ ፥
መጠየቅን ወልዶ ~ፍቅርን የሰበረ
ዛሬ ማንገምተው ~ድንቅ አለም ነበረ።
*
ከሀሳብ በኃላ
*
ገነትም ተዘጋ~ ሁሉም እረከሰ
ፍጥረትም ተርግሞ ~ሐጥያትን ወረሰ
ከሀሳብ በኃላ ~ጥላቻ ነገሰ።
*
እናም
*
ከሀሳብ መንገድ ላይ ~ በፊት የተገኘ
ከሃሳቡ ቀድሞ ~ ሀሳብ ካላገኘ
ሀሳብ ሆኖ ይቀራል~ በጣም የተሞኘ።
*
*
ሃሳብ ግን ምንድን ነው?
*
እሑድ መስከረም 25 /2012
#መልካም_ሰንብት
~~~~~~~~~~~~~~
እሱባለው የቡዜ ልጅ💚💛❤️
❤️ሰላም❤️

@getem
@getem
👍2
ኑ እናበጥረው ፤ ህግንም በቁና
መቼም በህግ አምላክ ፤ ተዘንግቷልና
ጌታየን ስጠብቅ ፤ ህጉን ይዤ በጄ
ያቅራራብኝ ገባ ፤ ያ ሽንታም በደጄ
ሁለት ነብር በዱር ፤ ሁለት ንጉስ በሀገር
ከቶ አይነግሱምና ፤ ታሪክ ቢመረመር
ትውልድ እንዳይወቅስ ፤ አብይ መላ ፍጠር፡፡

@getem
@getem
@getem

#መብረቁ ጥቁር ሰው(መባ)
"ኤሊያስ ነው መልካ"

ጀንበሯ ጠለቀች
ምንም ሳይመሽባት እንዲያው በጠዋቱ፤
ወይኑም ደረቀ
ተንዠርግጎ አምሮ ሳይደርስ መበላቱ።
ሀቅም ከእውነቷ
ሀሰት ከውሸቷ እልገናኝ አለች፤
በድካም ያለች ነፍስ
በምድር እፎይ ሳትል በሰማይ አረፈች፤
ለሙዚቃ ህይወት
ባህር፣ ውቂያኖሷ ፣ መልካዋ ነበረች፤
በደንብ ሳንጎነጫት
እንደልብ ጠጥተን ሳንጠግባት ደረቀች።

ዓይን ብሌኗን አጣች
አፍን አንደበቷን ጆሮም መስሚያዋን
ፈልጋ እየሻተች
አምጡ አምጡ እያለች ኤልያስ መልካን!

ነገር ግን... ነገር ግን
እንዲያው ሞተ ብለን ልባችን ቢነካ፤
ህያው ነው ዘላለም
ቀድተን አንጨርሰው ኤሊያስ ነው መልካ።

አብርሃም

@Run_Viva_Run

@getem
@getem
@getem
የጥበብ ዋርካ

ብሩህ ልቦና እግዜር የሰጠው
ለኪነ ጥበብ የተገለጠው
ትጉህ ታታሪ አያውቅም ድካም
ዘመን 'ሚሻገር ሳይከትብ አይረካም
የሀገሬ ኮከብ የሀገሬ ፈርጧ
በእውነት የወጣ ካ'ብራክ ከውስጧ
አዳዲስ ሀሳብ የሚበረብር
በተለየ ስልት የሚያቀናብር
የሙዚቃው ሊቅ ኤልያስ መልካ
የጥበብ አድባር የጥበብ ዋርካ
ሞተ ይላሉ ሞት ለ'ሱ ምኑ
ሕይወት ለዘራ በእድሜ ዘመኑ

ሁሌም ይወሳል በፍቅር አድባር
በሰላም አድባር
በኪነት አድባር
ሕያው በስራው ሕያው በተግባር ! ።

((የአስራትፍሬ))

ደምቆ ያደመቀን አበባ 'ረገፈ
የሀገሬ የጥበብ ቆሌ ተገፈፈ !።

@getem
@getem
@getem
ዳሪክ የጥበብ ምሽት

በዚህ ምሽት
❖☞የአዳማ ሆስፒታል ሳይኮሎጂስት መኮንን አነቃቂ ንግግር ያደርጋል
❖☞የአምራን ፎቶ ስራ አስኪያጅ ወይዘሪት የሺ ስለፎቶ ንግድ የስራ ልምዳን ታካፍላላች
❖☞ተስፋሁን ከበደ (ፍራሽ አዳሽ)
❖ ☞ኤፍሬም መኮንን (ኤፊ ማክ)
❖☞እሱቤ ኮብላዩ
❖☞ያብስራ ካሲ
❖☞ ሊንዳ
❖☞ ኑሃሚን ዮናታን
የግጥም እና የወግ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡

ሐሙስ መስከረም 29 / 2012 ዓ/ም ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ በዳሪክ ቡና አዳማ ( አዳማ ዪኒቨርሲቲ ፊት ለፊት)

@getem
[#ፋሲል_ስዩም ]
©
እንግዳ አለብኝ ቤቴን ላሳምረው፣
አፈር ሊገባበት ባፈር ልደልድለው፡፡
እንግዳዬ ብናኝ፣የኔ መልከ መልካም
አግረ ነፋስ ጥሎት እኔም ቤት ይገባል፡፡
(በሚል)
የአዝማሪ ግጥም...
የአዝማሪ ዜማ...
ስንት እንግዳ ነኝ ባይ
ደጅ ደጄን ሲጠና...
(እኔ)
ከአዝማሪው ቅኝት፣ዜማውን ተውሼ፣
በመነን ምናኔ፣እምባዬን አብሼ፣
ቅኝቴን በማጣት፣በጉስቁል ስልና፣
የግጥሜን ፍሰት፣በድሎት ፅፍና፣
(ሙዚቃ)
(ሳበቃ)
እንግዳዬ ቆሟል፣ግራም ቀኝም ገብቶት፣
ቤቴ ሸራ ሆኖ መቆርቆሪያው ጠፍቶት፡፡
(ሙሾ)
ዋይ ዋይ ቤቴ ሳንቃ የለሽ
በሲቃ የታነቅሽ...
እንግዳ ቢመጣ ሳታስገቢ ሸኘሽ፡፡
ዋይ ዋይ ሸራ ቤቴ፣አፈር አይደርስባት፣
እራሷም ብናኝ ናት፣ብናኝ አይገባባት፡፡
(...///...)
ስም አልባ ቀን ላይ የተጫረች...

@getem
@getem
@gebriel_19
🔥1
ቀረሽ እንደ ዋዛ
--------------------
(ገብረ ክርስቶስ ደስታ)
እንደ ድመቶቹ
የትም እንደሚያድሩት
እንደ ዛፍ ሐረጎች፣
እንደ ቤት ክዳኖች
ብርድ አቆራመደኝ።
ስጠብቅ ----- ስጠብቅ
“ትመጫለሽ ብዬ ሳይ ማዶ፣
ሳይ ማዶ፣
የልጅነት ዓይኔ ሟሟ እንደ በረዶ።”
ትመጫለሽ ብዬ ደቂቃ ስቆጥር፣
ትመጫለሽ ብዬ ሰዓቱን ስቆጥር፣
ትመጫለሽ ብዬ ባዘን ሳንጎራጉር
ትመጫለሽ ብዬ በበራፍሽ ስዞር
ብርድ አቆራመደኝ።
የመንገድ መብራቶች አይተው አፌዙብኝ
ውርጩ ቀለደብኝ፣
ጨለማው ሳቀብኝ።
አለመምጣትሽን
አውቀዋል ----- ያውቃሉ።
መስኮቶች ጨልመው፣
ቤቶች ተቆልፈው፣
ከተማው ሲተኛ
አይተዋል ----- ያያሉ።
አለመምጣትሽን
አውቀዋል ---- ያውቃሉ።
* * *
ከ"መንገድ ስጡኝ ሰፊ" የግጥም መድብሉ የተጨለፈ

@getem
@getem
@getem
ሀገር የሞተች ቀን !
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።
ይኸው ከዓመታት.. . ከጊዜያት በፊት
የተጣባን ደዌ ፥ የለከፈን ግፊት
ዘር ጎሳ ቆጠራ የሚል ህመም ወልዶ
ሰው ባይተዋር ሆነ ...ስጋ ደሙን ክዶ
ይኸው ተመልከቺ !
መወለድ ቋንቋ ነው ...
ወንድም ከለላ ነው ...
ይሉት የነበረ የአያቶች ብሂል ቃሉ ተዘንግቶ
ቋንቋ ገደል ሆነ ወንድም መሀል ገብቶ ።
አሁን በዚች ምድር...
በእናቶች ቀዬ ፥ በአባቶች ርስት
ቃየር ድንጋይ ይዟል አቤልን ሊነርት
አሁን በዚች ምድር
ኢትዮጵያ በሚሏት ፥ የምድሪቷ ክፋይ
መሪ እስስት ሆኗል ፥
ቁርሾ የሚዘራ ፥ የቃልኪዳን አባይ
አሁን በዚች ምድር.. .
የሚጋባ የለም ፥ ድንኳን ዳሱን ጥሎ
የሚጨፍር የለም ፦
በሆይታ ሙዚቃ ፥ ከበሮውን አዝሎ
ይኸው ተመልከቺ !
ሁሉ ዘቅዛቂ ነው ፥ የነጠላ ጥለት
ሳቅ መቧለት ሆኗል ..
ሀገር መቃብር ላይ ፥ የሚያናውር ሁነት ።

@getem
@getem
@getem
አፍ መፍቻ
----//----

መሰረቱ ሆኖ ፥ . .ግንዱን ካዘለ ሥር
በገንጣዮች ስለት ፥ ገዝፎ ሳይመተር
እንዳሜባ ቅንጣት...
ሁሉ በየጉልቱ ፥ .. . ....ሳይራባ በዘር

የምላሱ ፍሬ
እንዳበደ ውሻ ፥ ሳያደርገው አውሬ
ካካሉ መቋሚያ
.…ከመሰሉ ጉያ
ፊደል ካራ ሆኖ ፥ ..ገንጥሎ ሳይለየው
ሳይከፈል ያ..ኔ ፥ የሰው ልጅ በቋንቋው
በለቅሶ ነበረ ፥. . . . . .አፉን የሚፈታው

«ሚኪ እንዳለ»


@getem
@getem
@MMIKU
አንቺን እንዲያስረሳኝ
ስለት ልገባለት ከደጁ እንዳልመጣው
ዛሬ አንቺን ቢያስረሳኝ
ስለቴን ለመክፈል ትንሽ ገንዘብ አጣው
አሁን በዚህ ጉዳይ
እግዜር ወይስ እኔ ማን ይሆን ሚቀጣው

(ልብ አልባው ገጣሚ)
@getem
@getem
# አርምሞ
|
የላይ ሰፈር ልጆች ፡ መፈንደቅ ያውቃሉ
ምክንያት ፈልገው ፡ በሳቅ ይወድቃሉ፨
|
የታች መንደር ልጆች ፡ ሐዘን ያበዛሉ
ድንኳን ባዩ ቁጥር ፡ ልቅሶ ይቀመጣሉ፨
|
የ'ኛ መንደር ልጆች ፡ ኣንቺን ይመስላሉ
ሁሉን በአርምሞ ፡ ታዝበው ያልፋሉ ፨
|||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||
|| በርናባስ ከበደ ||

@getem
@getem
@getem
👍1