ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ውሰት
ለይቶ ላይለየን ወስዶ ላያስቀርሽ
ከሌቱ ጅማሬ ከምሽቱ አጋማሽ
ልዉሰድሽ ማለቱን በፍፁም አልፈቅድም
አንድ ያለኝን ነገር መስጠት እኔ አልወድም።

(እንደኔ ውዱን እንቅልፍ ለነጠቀው ሁሉ)
#ሳሚ

@getem
@getem
@getem
አምሣለ ዮርዳኖስ


ስለ ፍቅር ብዬ
 ሁሉን ነገር ችዬ 
ባበዛ ዝምታ 
ንቀቱ በረታ
 ንፁህ ልቤን ወግቶ 
ውስጠቴን አድምቶ 
ጥሎኝ ከመንገዱ 
ጊዚያት ነጎዱ
 በጥላቻው ጥልቀት
 በበደሉም ር'ቀት
 ዓይኔ እንባ አፈለቀ
 አካሌን ጠመቀ
 ሠው በሚሉት ካህን 
ዙሪያውን ሲታጠን 
 ገብቼ ከወንዙ ሕይወት ከሚሉቱ 
ዕንባ ሆኖኝ ጠበል ተነከርኩኝ ውሥጡ
 ጠልቄ ብወጣ 
አዲስ ፀሐይ ወጣ 
 ዛሬ እኔም ተካንኩ
 ደግነትን ጣልኩ 
 ሥለ ሠው-ልጅ ክፋት ውሥጤ ተሠበረ
 እርኩሠት ተረጨ ክፋትን ዘመረ


@getem
@getem
@getem

#ሳሚ ዘ ሆህተ ምስራቅ
ጨረቃ ና ናፍቆት


እቱ የጥንቲቱ
የጥርስሽ ንጣቱ 
የጉንጭሽ ቅላቱ 
ውል ይለኛል ዛሬም የገላሽ ሙቀቱ 
የእግሮችሽ ኮሽታ 
የፍቅርሽ ሹክሹክታ 
ያ የሣቅሽ ዜማ የበዛው ክትክታ 
ይሠማኛል ዛሬም ናፍቆት ሲበረታ
እቱ የጥንቲቱ 
አንቺም ትዝ ካለሽ ካለብሽ ናፍቆቱ 
ይህ ነው መዳኒቱ 
ባስለመድኩሽ ሰዓት ባለሽበት ቦታ 
ቀና በይ ላንድ አፍታ
እኔም ባለሁበት ባስለመድሽኝ ሰዓት
ዓይኖቼን አቅንቼ
ጨረቃን አይቼ  ልግባ ተፅናንቼ 
አንቺም በዚያች አፍታ 
ጨረቃዋን ፈክታ 
ካየሻት ተጽናኚ 
በይ ቃሌን እመኚ 
ምንም ብንራራቅ ካንድ ሰማይ ሥር ነን
  ነገ አብረን ለመኖር ታላቅ ተሥፋ አለን

@getem
@getem
@getem

#ሳሚ ዘ ሆህተ መስራቀ