።።።።።።የምርቃና ግፉ።።።።።።
የሙዚቃ ሊቁ፣
ሙዚቃ ቀማሚው ዜማ እየቀመረ
ጠባቧ "ስቲዲዮ " ጫት ሞልቷት ነበረ።
ሳተናው ነጋዴ ትርፉን እያሰላ
ሊቅም ቁርሱን በላ።
ሹማምንቶቻችን ፣
ገንቢ አፍራሾቻችን ፣
ዕቅዱን ሲጽፉ ፣
በትዕዛዝ ያደገ አወደይ ቀጠፉ።
ጎረምሳው አፍቃሪሽ ጫት በዱቤ ቅሞ፣
ደብዳቤ ጻፈልሽ ከገረባ መሃል
ምርቅን ቃላት ለቅሞ።
እናስ!
መሪ ከተከታይ፣
ፍትህ ከተበዳይ፣
ጥበብ ከአድናቂው፣
መላሽ ከጠያቂው
የነቃ ከእውኑ
የተኛ ከሕመሙ
ውበት ከቀለሙ
እኮ በምን ስሌት? እንደምን ይስማማ?
ሰጪና ተቀባይ እኩል አልቃሙማ።
በረከት.በ
@getem
@getem
@gebriel_19
የሙዚቃ ሊቁ፣
ሙዚቃ ቀማሚው ዜማ እየቀመረ
ጠባቧ "ስቲዲዮ " ጫት ሞልቷት ነበረ።
ሳተናው ነጋዴ ትርፉን እያሰላ
ሊቅም ቁርሱን በላ።
ሹማምንቶቻችን ፣
ገንቢ አፍራሾቻችን ፣
ዕቅዱን ሲጽፉ ፣
በትዕዛዝ ያደገ አወደይ ቀጠፉ።
ጎረምሳው አፍቃሪሽ ጫት በዱቤ ቅሞ፣
ደብዳቤ ጻፈልሽ ከገረባ መሃል
ምርቅን ቃላት ለቅሞ።
እናስ!
መሪ ከተከታይ፣
ፍትህ ከተበዳይ፣
ጥበብ ከአድናቂው፣
መላሽ ከጠያቂው
የነቃ ከእውኑ
የተኛ ከሕመሙ
ውበት ከቀለሙ
እኮ በምን ስሌት? እንደምን ይስማማ?
ሰጪና ተቀባይ እኩል አልቃሙማ።
በረከት.በ
@getem
@getem
@gebriel_19
#የ 4 ኪሎ ተጓዥ!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
ተስፈኛ ወያላ ፥ የሹፌር ረዳት
ታክሲ ተደግፎ ፥
እንድረስ እያለ ፥ አራት ኪሎን ጠራት።
"አራት ኪሎ የሞላ !
አንድ ሰው የቀረው ...
አራት ኪሎ ሊሄድ ፥ ልቡ የከጀለው
አራት ...አራት ኪሎ
ከቤተመንግስቱ ከፓርላማው ሰፈር
ጠጋ ጠጋ ብለን በአጀብ እንብረር"
በሚል ጥዑም ዜማ በስልተኛ ቃላት
አራት ኪሎ ባሉ ተስፈኛ ፊደላት
ታክሲ ተደግፎ
በፅኑ ለፍፎ
በጩኸት ይጣራል.. .
አራት ኪሎ ሊደርስ ልቦናው የመራው ተጓዥ ይሳፈራል ።
አንድ ሰው የሞላ !
አራት ...አራት ኪሎ
ሲሻው ከጆሊ ባር
ቆንጆ ሴት ከጅሎ
እንደው ለአፉ ደንብ ማክያቶ አዝዞ
ሲሻው ከመንገድ ዳር
የወሬ ሰሌዳ ጋዜጣውን ይዞ
መቀመጥ የሚሻ ...
ሲሻው ከድልት ሀውልት
ግርጌ አረፍ ብሎ ለታሪክ ሟሟሻ
መጣፍ የሚከትብ...
አንድ ሰው የሞላ !
አራት ኪሎ እንሂድ ከመንግስቱ ግድም።"
አንድ ሰው የሞላ !
አራት ... አራት ኪሎ ...
መንጋው ይሳፈራል ለመድረስ ተቻኩሎ ።
ደግሞም ወዲያ ያለው...
የ አራት ኪሎ ተጓዥ መብዛት ያስገረመው
ጥርሱን እየፋቀ ከጠርዝ ዳር ቆሞ
የቱ ይደርስ ይሆን? እያለ ያስባል ብቻውን ቆዝሞ
አንድ ሰው የሞላ !
አራት ...አራት ኪሎ
ወያላው ይጣራል...
በየፌርማታው ላይ
መንገዱ አታክቶት
መድረስ የቸገረው አንድ ሰው ይወርዳል ።
አራት...አራት ኪሎ
ይጣራል ወያላው!
...
ኸረ መንገድ ስጡኝ ?
እያለ ይለፍፋል ሹፌሩ በተራው.. .
።።።።።
ደግሞም ሌላ ተጓዥ...
ከችኩል በራሪው ... መንጋ ተነጥሎ
በቀስ ... ቀስ እርምጃ መንደሩን አካሎ
ወያላ ሳይጠራው ካልተሳፈርህ ብሎ
ሳይዋከብ ይደርሳል.. .
የጉዞውን ማብቂያ እድሉ ላይ ጥሎ ።
ደግሞም ወዲያ ያለው ...
ከዚህ ሁሉ መንጋ የትኛው ይደርሳል? ብሎ የጠየቀው
ከ አራት ጎማ ታክሲ ቀድሞ የደረሰ
እግረኛ አለ ሲሉት ተዐምር ያፈሰ
እንዴት ሆነ ሳይል ? ጥያቄ ቀጥሎ
ፈገግ ብሎ ያልፋል መፋቂያውን ጥሎ።
አንድ ሰው የሞላ...
@getem
@getem
@getem
(ሚካኤል አስጨናቂ)
ተስፈኛ ወያላ ፥ የሹፌር ረዳት
ታክሲ ተደግፎ ፥
እንድረስ እያለ ፥ አራት ኪሎን ጠራት።
"አራት ኪሎ የሞላ !
አንድ ሰው የቀረው ...
አራት ኪሎ ሊሄድ ፥ ልቡ የከጀለው
አራት ...አራት ኪሎ
ከቤተመንግስቱ ከፓርላማው ሰፈር
ጠጋ ጠጋ ብለን በአጀብ እንብረር"
በሚል ጥዑም ዜማ በስልተኛ ቃላት
አራት ኪሎ ባሉ ተስፈኛ ፊደላት
ታክሲ ተደግፎ
በፅኑ ለፍፎ
በጩኸት ይጣራል.. .
አራት ኪሎ ሊደርስ ልቦናው የመራው ተጓዥ ይሳፈራል ።
አንድ ሰው የሞላ !
አራት ...አራት ኪሎ
ሲሻው ከጆሊ ባር
ቆንጆ ሴት ከጅሎ
እንደው ለአፉ ደንብ ማክያቶ አዝዞ
ሲሻው ከመንገድ ዳር
የወሬ ሰሌዳ ጋዜጣውን ይዞ
መቀመጥ የሚሻ ...
ሲሻው ከድልት ሀውልት
ግርጌ አረፍ ብሎ ለታሪክ ሟሟሻ
መጣፍ የሚከትብ...
አንድ ሰው የሞላ !
አራት ኪሎ እንሂድ ከመንግስቱ ግድም።"
አንድ ሰው የሞላ !
አራት ... አራት ኪሎ ...
መንጋው ይሳፈራል ለመድረስ ተቻኩሎ ።
ደግሞም ወዲያ ያለው...
የ አራት ኪሎ ተጓዥ መብዛት ያስገረመው
ጥርሱን እየፋቀ ከጠርዝ ዳር ቆሞ
የቱ ይደርስ ይሆን? እያለ ያስባል ብቻውን ቆዝሞ
አንድ ሰው የሞላ !
አራት ...አራት ኪሎ
ወያላው ይጣራል...
በየፌርማታው ላይ
መንገዱ አታክቶት
መድረስ የቸገረው አንድ ሰው ይወርዳል ።
አራት...አራት ኪሎ
ይጣራል ወያላው!
...
ኸረ መንገድ ስጡኝ ?
እያለ ይለፍፋል ሹፌሩ በተራው.. .
።።።።።
ደግሞም ሌላ ተጓዥ...
ከችኩል በራሪው ... መንጋ ተነጥሎ
በቀስ ... ቀስ እርምጃ መንደሩን አካሎ
ወያላ ሳይጠራው ካልተሳፈርህ ብሎ
ሳይዋከብ ይደርሳል.. .
የጉዞውን ማብቂያ እድሉ ላይ ጥሎ ።
ደግሞም ወዲያ ያለው ...
ከዚህ ሁሉ መንጋ የትኛው ይደርሳል? ብሎ የጠየቀው
ከ አራት ጎማ ታክሲ ቀድሞ የደረሰ
እግረኛ አለ ሲሉት ተዐምር ያፈሰ
እንዴት ሆነ ሳይል ? ጥያቄ ቀጥሎ
ፈገግ ብሎ ያልፋል መፋቂያውን ጥሎ።
አንድ ሰው የሞላ...
@getem
@getem
@getem
👍1
ለወርቃችን
❤
ድንቁርናችንን ይቅር በለው
-----------------------------------
(ደበበ ሰይፉ)
ወንድምዬ፤
እንደወጣህ ባትመለስ፣
በዋል ፈሰስ አትከሰስ።
በዋልጌነት አትጠቀስ።
የመንፈስህ ብርታት ንቃቱ
የድምፅህ ውበት ጥራቱ፤
ሥዕል ነው
ነድፈን እማናኖረው።
… ግን ምነው
እመለሳለሁ ብለህ ሄደኸው
እንደወጣህ ቀረኸው?
----- ማለት መቼም ልማድ ነው። ----
መንገድ መኖሩን እንጂ
መንገዳችንን ላላወቅነው
ጊዜ መኖሩን እንጂ
ጊዜያችንን ላላየነው፤
አንተ አውቀሃልና ወንድምዬ፣
ድንቁርናችንን ይቅር በለው።
ይቅር በለው።
-----------
1963
(ይህ ደበበ ሰይፉ "ለተረፈ ኩራባቸው መታሰቢያ" ብሎ የፃፈው ግጥም፣ ለኤልያስ መልካም
ህልፈት የሚገጥም ሆኖ ባገኘውና ቢሰማኝም ነው - እዚህ መለጠፌ። “ ገና መሥራት
በሚችልበት ዕድሜው ምነው በለጋነቱ ተቀጨ? ፣ ለአድማጭ
ጆሮ የሚያበቃቸውን ሥራዎች እያሰናዳ ነው ’ የሚል ወሬን ብዙ እንደነበረው ሰምተን? ምነው?
” የሚለውን ሞቱ የፈጠረብንን የ"ምነው? ፣ ምነው? " ስሜትም ጋር ይተያያል! )
"ናካይታ"!💚
@getem
@getem
@balmbaras
❤
ድንቁርናችንን ይቅር በለው
-----------------------------------
(ደበበ ሰይፉ)
ወንድምዬ፤
እንደወጣህ ባትመለስ፣
በዋል ፈሰስ አትከሰስ።
በዋልጌነት አትጠቀስ።
የመንፈስህ ብርታት ንቃቱ
የድምፅህ ውበት ጥራቱ፤
ሥዕል ነው
ነድፈን እማናኖረው።
… ግን ምነው
እመለሳለሁ ብለህ ሄደኸው
እንደወጣህ ቀረኸው?
----- ማለት መቼም ልማድ ነው። ----
መንገድ መኖሩን እንጂ
መንገዳችንን ላላወቅነው
ጊዜ መኖሩን እንጂ
ጊዜያችንን ላላየነው፤
አንተ አውቀሃልና ወንድምዬ፣
ድንቁርናችንን ይቅር በለው።
ይቅር በለው።
-----------
1963
(ይህ ደበበ ሰይፉ "ለተረፈ ኩራባቸው መታሰቢያ" ብሎ የፃፈው ግጥም፣ ለኤልያስ መልካም
ህልፈት የሚገጥም ሆኖ ባገኘውና ቢሰማኝም ነው - እዚህ መለጠፌ። “ ገና መሥራት
በሚችልበት ዕድሜው ምነው በለጋነቱ ተቀጨ? ፣ ለአድማጭ
ጆሮ የሚያበቃቸውን ሥራዎች እያሰናዳ ነው ’ የሚል ወሬን ብዙ እንደነበረው ሰምተን? ምነው?
” የሚለውን ሞቱ የፈጠረብንን የ"ምነው? ፣ ምነው? " ስሜትም ጋር ይተያያል! )
"ናካይታ"!💚
@getem
@getem
@balmbaras
ጠርጥሪኝ
""""""""""""
በስልኬ ደውዬ
እንገናኝ ብዬ ከቀጠርኩሽ ቦታ
ውዴታ አስቸኩሎኝ
ከ አንድ ሰዓት በፊት ቀድሜ ብመጣ
በሰአትሽ መጥተሽ
ለምን ቆየሽ ብዬ እንዲያው ብንጨረጨር
አስቀድሞ አምጥቶ
እዚህ የጎለተኝ ያንቺው ፍቅር ነበር።
(እናማ አንቺዬ)
ቁጣዬ አይታይሽ
ብበሳጭ ብናደድ እኔ ባንቺ ዛሬ
ፊትሽ ቢለዋወጥ
ውስጥሽ ፈካ ይበል ደስ ይበልሽ ፍቅሬ
ይግባሽ አሁን እስቲ
በዚች ብስጭቴ እኔ አንቺን ማፍቀሬ
አትከፋም አንዳንዴ
የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ
"ምን ሆነ?" እስቲ በይ
......ተይ ጠርጥሪኝ ፍቅሬ 🤔
@getem
@getem
@getem
#አብርሃም
""""""""""""
በስልኬ ደውዬ
እንገናኝ ብዬ ከቀጠርኩሽ ቦታ
ውዴታ አስቸኩሎኝ
ከ አንድ ሰዓት በፊት ቀድሜ ብመጣ
በሰአትሽ መጥተሽ
ለምን ቆየሽ ብዬ እንዲያው ብንጨረጨር
አስቀድሞ አምጥቶ
እዚህ የጎለተኝ ያንቺው ፍቅር ነበር።
(እናማ አንቺዬ)
ቁጣዬ አይታይሽ
ብበሳጭ ብናደድ እኔ ባንቺ ዛሬ
ፊትሽ ቢለዋወጥ
ውስጥሽ ፈካ ይበል ደስ ይበልሽ ፍቅሬ
ይግባሽ አሁን እስቲ
በዚች ብስጭቴ እኔ አንቺን ማፍቀሬ
አትከፋም አንዳንዴ
የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ
"ምን ሆነ?" እስቲ በይ
......ተይ ጠርጥሪኝ ፍቅሬ 🤔
@getem
@getem
@getem
#አብርሃም
#ጭብጨባ
(በተመስገን መሰረት)
.
ጭብጨባ አትውደድ፣ አይምሰልህ የብርታት
ከመውደቋ በፊት......
ቢንቢም መስሏት ነበር፣ አድናቆት የሰጧት፡፡
@getem
@getem
@gebriel_19
(በተመስገን መሰረት)
.
ጭብጨባ አትውደድ፣ አይምሰልህ የብርታት
ከመውደቋ በፊት......
ቢንቢም መስሏት ነበር፣ አድናቆት የሰጧት፡፡
@getem
@getem
@gebriel_19
እንዴት እረሳሁሽ
ብሎ በማሰብ ውስጥ
..............አንቺን ማለም አለ
ደርሶ ሚታገለኝ
መገረም ሚመስል
..............ናፍቆትን ያዘለ።
/አዱኛ አስራት/
@getem
@getem
@lula_al_greeko
ብሎ በማሰብ ውስጥ
..............አንቺን ማለም አለ
ደርሶ ሚታገለኝ
መገረም ሚመስል
..............ናፍቆትን ያዘለ።
/አዱኛ አስራት/
@getem
@getem
@lula_al_greeko
\\__ነፀብራቅ__//
በታ.ገ.ኃ (ዘሩባቤል ዘወርቅያንጥፉ)
፤
እንደሙሴ ፅላት
ለድሂን አብጅቶ ቢሰራሽ እዝጌሩ፥
እፀድቅ ብዬ ባዝላት
ቀረች ተንጠልጥላ ይልሻል ሀገሩ፥
እንዳስመሳይ ጠላት
ለፅድቅ ብተኛት
ጥላቻ አረገዘች ሆነና ነገሩ፥
ከኣባይሽ ዳርታ
ይናዳል ድልድይሽ
አስፈርቷል መሻገሩ።
፥
አንቺ የጠብ ቀዬ፥
አንቺ እና ውሽማ አንድ የሚያረጋቹ፥
ውርጃ ሞያቹ ሆኗል፥ ውርደት ማዕረጋቹ።
፤
ተከዜ ዳር ሆኖ
በዘመን ትካዜ
እንደዚ የሚያዜም ህዝቤ ገራገሩ፥
ተኳርፈው እያየ
ጎሪጥ ሲታያዩ እግዜሩ እና ሀገሩ፥
ህሊናው ነቅርሶ
ስጋው ተመናምኖ ነፍሱ ብትደኸይም፥
ለተኳረፈ ህዝብ
ለጨለመ ሌሊት ሰማይ አይፀኸይም፥
ብሎ ያሟርታል
በድንግዝግዝ መሀል
ሻማ እንኳን ሳይለኩስ፥
ሌላውን አንቋሾ
በመነነች ቀዬ ራሱን ሲያመነኩስ።
፤
ፃፊ እንዲህ ይላል!
ከመርገሟ አበዛዝ
እግዜር ፅድቁን ተወ
እርሷም እርቁን ጠላች፥
ከላላ አገዛዝ
አገር በገፍ ሟሙታ
በግፍ እየተላች፥
ካለማንም ትዕዛዝ
ከራሷ ገላ ላይ ትል
ለቅማ እየበላች፥
የለችም እንዳይሏት
አለሁ ምትል አገር አለሁ ያለች ቀዬ፥
ታሪኳ ሲጀመር
እህህም ባይኖረው
የታሪኳ ማብቂያ ይመስላል እዬዬ።
፥
አንቺዬዋ!
ከያዘሽ ነቀርሳ
ለሚከሳ ገላሽ፥
ለሚቀጭጭ ቆሌሽ
ለሚሸሽሽ ጥላሽ፥
በምን እንዳስማረሽ¡
ማን እንዳስተማረሽ¡
ባላውቅም ጠቢቡን፥
እንደቀሚስሽ ወግ
እንደመፍቴሽ ስራይ
ይዘሻል መጥበቡን፥
፥
አየሽ እታለሜ!
እኔ የዋህ ሆዬ ፥
አገር አማን ብዬ፥
እዝጌር ሲያስታብይሽ፥
እሽኮለል ሲያስብልሽ፥
አንቺው በጠራሽው
የይምሰል ጉባኤ፥
አንቺው ባሳወጅሽው
የቁርሻ ሱባኤ፥
ተፅድቅሽ ልቋደስ
እፀድቅ እንደሁ ብዬ፥
እንደመታበይሽ
ብገዘት ታ'ብዬ፥
ብውል ታደባባይ
እጅ አመሳቅዬ፥
ይኸው አለሁ ራሴ በራስ ተኮነኜ
ተመሰቃቅዬ፥
ለፍቅር ካልሁት ልብ ንቃቃት አብቅዬ።
፤
አየሽ እናት ሀገር!
ግዞት ሲወድልን እንፀድቅ እንደው ብለን፥
የማይፀድቅ ሀሳብ ስናፀድቅ ውለን፥
በኑባሬ ማሳ ዣንጥላ አቃጥሎን
ጣይ ስር ተጠልለን፥
ላለመኖር አለን ላለመሞት ገድለን።
፤
በታሸገ ጓሮሾ
የታሸገ ውሃ የምትጎነጪ ምን ተዳሽ አንቺማ፥
ይብላኝስ ለኔ ነው
ማልቀስስ ለኔይ ውሃ ላይ ተኝቼ ጠላ ለምጠማ።
፤
ህዳር 12, 2012
አዳማ
ኢትዮጵያ
@getem
@getem
@getem
በታ.ገ.ኃ (ዘሩባቤል ዘወርቅያንጥፉ)
፤
እንደሙሴ ፅላት
ለድሂን አብጅቶ ቢሰራሽ እዝጌሩ፥
እፀድቅ ብዬ ባዝላት
ቀረች ተንጠልጥላ ይልሻል ሀገሩ፥
እንዳስመሳይ ጠላት
ለፅድቅ ብተኛት
ጥላቻ አረገዘች ሆነና ነገሩ፥
ከኣባይሽ ዳርታ
ይናዳል ድልድይሽ
አስፈርቷል መሻገሩ።
፥
አንቺ የጠብ ቀዬ፥
አንቺ እና ውሽማ አንድ የሚያረጋቹ፥
ውርጃ ሞያቹ ሆኗል፥ ውርደት ማዕረጋቹ።
፤
ተከዜ ዳር ሆኖ
በዘመን ትካዜ
እንደዚ የሚያዜም ህዝቤ ገራገሩ፥
ተኳርፈው እያየ
ጎሪጥ ሲታያዩ እግዜሩ እና ሀገሩ፥
ህሊናው ነቅርሶ
ስጋው ተመናምኖ ነፍሱ ብትደኸይም፥
ለተኳረፈ ህዝብ
ለጨለመ ሌሊት ሰማይ አይፀኸይም፥
ብሎ ያሟርታል
በድንግዝግዝ መሀል
ሻማ እንኳን ሳይለኩስ፥
ሌላውን አንቋሾ
በመነነች ቀዬ ራሱን ሲያመነኩስ።
፤
ፃፊ እንዲህ ይላል!
ከመርገሟ አበዛዝ
እግዜር ፅድቁን ተወ
እርሷም እርቁን ጠላች፥
ከላላ አገዛዝ
አገር በገፍ ሟሙታ
በግፍ እየተላች፥
ካለማንም ትዕዛዝ
ከራሷ ገላ ላይ ትል
ለቅማ እየበላች፥
የለችም እንዳይሏት
አለሁ ምትል አገር አለሁ ያለች ቀዬ፥
ታሪኳ ሲጀመር
እህህም ባይኖረው
የታሪኳ ማብቂያ ይመስላል እዬዬ።
፥
አንቺዬዋ!
ከያዘሽ ነቀርሳ
ለሚከሳ ገላሽ፥
ለሚቀጭጭ ቆሌሽ
ለሚሸሽሽ ጥላሽ፥
በምን እንዳስማረሽ¡
ማን እንዳስተማረሽ¡
ባላውቅም ጠቢቡን፥
እንደቀሚስሽ ወግ
እንደመፍቴሽ ስራይ
ይዘሻል መጥበቡን፥
፥
አየሽ እታለሜ!
እኔ የዋህ ሆዬ ፥
አገር አማን ብዬ፥
እዝጌር ሲያስታብይሽ፥
እሽኮለል ሲያስብልሽ፥
አንቺው በጠራሽው
የይምሰል ጉባኤ፥
አንቺው ባሳወጅሽው
የቁርሻ ሱባኤ፥
ተፅድቅሽ ልቋደስ
እፀድቅ እንደሁ ብዬ፥
እንደመታበይሽ
ብገዘት ታ'ብዬ፥
ብውል ታደባባይ
እጅ አመሳቅዬ፥
ይኸው አለሁ ራሴ በራስ ተኮነኜ
ተመሰቃቅዬ፥
ለፍቅር ካልሁት ልብ ንቃቃት አብቅዬ።
፤
አየሽ እናት ሀገር!
ግዞት ሲወድልን እንፀድቅ እንደው ብለን፥
የማይፀድቅ ሀሳብ ስናፀድቅ ውለን፥
በኑባሬ ማሳ ዣንጥላ አቃጥሎን
ጣይ ስር ተጠልለን፥
ላለመኖር አለን ላለመሞት ገድለን።
፤
በታሸገ ጓሮሾ
የታሸገ ውሃ የምትጎነጪ ምን ተዳሽ አንቺማ፥
ይብላኝስ ለኔ ነው
ማልቀስስ ለኔይ ውሃ ላይ ተኝቼ ጠላ ለምጠማ።
፤
ህዳር 12, 2012
አዳማ
ኢትዮጵያ
@getem
@getem
@getem
👍1
#መስታወት_ልግዛልሽ
:
:
መቼስ በዚች ዓለም
አምናለው አልክድም
የሰው ፍፁም የለም።
፡
፡
ሰው ስህተት ይሰራል
ከዚያም ይታረማል
ከስ'ተቱ ይማራል።
፡
፡
ያንቺ ግን ፍቅርዬ መሳሳትሽ ወዛ
በ'ኔና አንቺ መሀል ምንም ሰው ሳይበዛ
እራስሽ የጣድሺው ጎመንም ጠነዛ።
፡
፡
ከሰራሺው ስህተት ትማሪያለሽ ብዬ...
...በተስፋ ስጠብቅ ወይ ዛሬ ወይ ነገ
እንኳን ልትማሪ ጥፋትሽ ስር ሰዶ...
ቅርንጫፍ አውጥቶ ይባሱን አደገ።
፡
፡
እናምልሽ ፍቅሬ...
ትናንት በመቅረዜ ደቂቅ ተስፋን ይዤ
ሁሉን ለ አምላክ ጥዬ እሱን ተመርኩዤ
አጣጥቤ ልኬሽ ጨቅይተሽ ስትመጪ
ፍቅርሽ እንዳይርቀኝ ከልቤ እንዳትወጪ
መውደድ አስገድዶኝ ዳግም እንደገና
አምጥቼልሽ ነበር ውሀና ሳሙና።
፡
፡
ዛሬ ግን ታከተኝ ዛሬማ በቅቶኛል
ጭቃሽን ለማንፃት ውሀ ምቀዳበት...
ጉልበቴም ከድቶኛል።
፡
፡
እናም ካሁን ወዲህ ለኔም እንዲቀለኝ...
...ላንቺም እንዲበጅሽ
በሳሙና ፈንታ ጭቃሽን እንድታይ...
...መስታወት ልግዛልሽ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
to inbox & send ur poems @Henokbirhanu
:
:
መቼስ በዚች ዓለም
አምናለው አልክድም
የሰው ፍፁም የለም።
፡
፡
ሰው ስህተት ይሰራል
ከዚያም ይታረማል
ከስ'ተቱ ይማራል።
፡
፡
ያንቺ ግን ፍቅርዬ መሳሳትሽ ወዛ
በ'ኔና አንቺ መሀል ምንም ሰው ሳይበዛ
እራስሽ የጣድሺው ጎመንም ጠነዛ።
፡
፡
ከሰራሺው ስህተት ትማሪያለሽ ብዬ...
...በተስፋ ስጠብቅ ወይ ዛሬ ወይ ነገ
እንኳን ልትማሪ ጥፋትሽ ስር ሰዶ...
ቅርንጫፍ አውጥቶ ይባሱን አደገ።
፡
፡
እናምልሽ ፍቅሬ...
ትናንት በመቅረዜ ደቂቅ ተስፋን ይዤ
ሁሉን ለ አምላክ ጥዬ እሱን ተመርኩዤ
አጣጥቤ ልኬሽ ጨቅይተሽ ስትመጪ
ፍቅርሽ እንዳይርቀኝ ከልቤ እንዳትወጪ
መውደድ አስገድዶኝ ዳግም እንደገና
አምጥቼልሽ ነበር ውሀና ሳሙና።
፡
፡
ዛሬ ግን ታከተኝ ዛሬማ በቅቶኛል
ጭቃሽን ለማንፃት ውሀ ምቀዳበት...
ጉልበቴም ከድቶኛል።
፡
፡
እናም ካሁን ወዲህ ለኔም እንዲቀለኝ...
...ላንቺም እንዲበጅሽ
በሳሙና ፈንታ ጭቃሽን እንድታይ...
...መስታወት ልግዛልሽ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
to inbox & send ur poems @Henokbirhanu