ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ድብቅ
""""""""
እኔው ባንደበቴ
ሀቁን ተናግሬ ከምገባ ጣጣ፥
ወርቄን ስትፈልጉ
እወቁት ቅኔዬን
ከፍርሃት ነው እንጂ ከየትም እንዳልመጣ!


@getem
@getem
@paappii

#አብርሃም
ይግባኝ
""""""""""
ይግባኝ ፈጣሪ ሆይ
ጥፋቴ አልገባኝም የኔ የክስ ዶሴ፤
ማንንም የማላቅ
ያሉኝን የማምን ምስኪን ነኝ ለራሴ።
አትብላ ብትለኝ
እርኩሰት ያላትን ያቺን እፀ በለስ፤
ከጉያህ ወጥቼ በጥፋት እንዳል'ረክስ፤
ያጥንቴ ፍላጭ ናት የስህተቴ ምክንያት፤
በእሷም አልፈርድም
የራሷ የሆን እሷም ምክንያት አላት።

ይግባኝ ፈጣሪ ሆይ
ጥፋቴ አልገባኝም የኔ የክስ መዝገብ፤
እኩል ፍርድ ተላልፏል
እንደ አንድ ተወስዶ ቅምሻና መመገብ።
እሷ በበኩላ ከፍሬው ቀንጥሳ፤
ከአንድም ሁለት ስትል
ከሁለትም ሶስቴ በልታ ስታገሳ፤
እኔ በበኩሌ
ከምላሴ ወርዶ ትዕዛዙም ቢረሳ፤
ሆዴን ቁልቁል አይቶ
ሳልበላው ሳይበላኝ ከአንገቴ ቀረሳ።

አልክድም እርግጥ ነው
ጥፋቴን በጉልህ በግልፅ አምኛለው፤
ነገር ግን ብይኑ ስህተት ነው እላለሁ፤
ይግባኝ አንተን ማለት
መልሶ መጠየቅ ያስፈራል አውቃለሁ፤
ፍርድ ያጣሁ ሲመስለኝ
መቼም ሰው ነኝና እንቆጠቆጣለሁ።

ግና እውቀልኝ
የድፍረት አይደለም ነፍሴን ብጠይቃት፤
አምናለሁ አያስቆጣም
ፈራጅን ለፍርዱ ፍርድህ ይግባኝ ማለት!

እናም ፈጣሪ ሆይ

ፈራጅ ፍትህ ይዞ ፍርድ ካላዘጋጀ
ቀማሹም በይውም እኩል ከፈረጀ
ውረዱ ወደመሬት ብሎ እንደታወጀ
ሚዛን ተጓደለች ቅጣቱም አልበጀ!

ያም ሆነ ይህም ሆነ
ግን ተርቤ ነበር ስትጥለኝ ከምድር፤
የበላሁት ፍሬ
እሆዴ ጋ ሳይደርስ አንገቴ ጋ ነበር..!


@getem
@getem
@getem

#አብርሃም
አንዳንድ ገፅ
"""""""'''''''''''''''""

የኔነቴ ምዕራፍ
ልክ እንደ መፅሀፍ
ጠፍተው የተረፉ ሰባት ገፆች አሉት፤
የኔና አንቺን ህይወት በግልፁ የሚያትት።

ማውጫ የለው መግቢያ
ጥራዝ የለው ሽፋን
ወና ....ቤት አልባ ገፅ፤
እንዲህ ይነበባል
በባለ ታሪኩ ታሪኩ ሲገለ'ፅ።

(ገፅ አንድ)

በሰፈሬ መንገድ ቁልቁለቱን ስወርድ፤
አንቺ ደሞ ወደላይ ስትወጪ አቀበት፤
እንቅፋት ሳይነካኝ ልቤ አለ ሸርተት፤
አልገባኝም ነበር?
ከየት አመጣጡ? ደርሶ ይሄ ስሜት።

አቀበት ሆኖብሽ
ደካክሞሻል አንቺ ያለሽበት መንገድ፤
ድካም ነው ቁንጅናሽ?
አልገባኝም ከቶ ደርሶ የልቤ መራድ።

መንገዱ ሲወስደኝ የልቤ መረበሽ፤
መንገዱ ሲይለፋሽ እንዲያ ተደካክመሽ፤
ድጋሚ አልገባኝም?
ጎን ለጎን ስንደርስ
ለምን ተሽኮረመምሽ? ለምን ስቀሽ አለፍሽ?

(ገፅ ሁለት)

እኔ እንቅልፋሙ
የሞትኩ የምመስለው ጎኔ ሲነካ አልጋ፤
አልገባኝም ዛሬም?
አልጋው ኮሰኮሰኝ ስገላበጥ ነጋ።

ውሎዬ አላማረ
እንዲሁ ስነጫነጭ ባህሪዬ ከፍቶ፤
"ምን ሆነሀል?" ሲለኝ
መጤ ባህሪዬን ሰዉ ተመልክቶ።
አላውቅም ምንድነው?
ልገልፀው አልቻልኩም ያናደደኝ ነገር፤
ቆይቼ ሲገባኝ
ገፅ አንድ ላይ ያለው አሳሳቅሽ ነበር!

(ገፅ ሶስት)

ድንገት ያየሁሽ ቀን
በደስታ ባህር ውስጥ ልቤ ሲረግጥ ጮቤ፤
ያላየሁሽ ለታ
ተከፍቼ ስገኝ ሀዘኔን ደርቤ፤
ለተመልካች ሁሉ
እኔ አንቺን መውደዴ አሳበቀ ቀልቤ፤
ልቀርብሽ ፈለኩኝ
የወንድነት ወኔ ድፍረቴን ሰብስቤ።

(ገፅ አራት)

ሰላም ተባባልን
ትንሽ ተንተባተብኩ አንቺም ተዋወቅሽኝ፤
ፍርሃቴም ቀነሰ
ተለማመድንና ቀርቤሽ ቀርበሽኝ፤
ግን ሌላ ምጥ ያዘኝ
እንደ ጓደኛ እንጂ በፍቅር አላየሽኝ፤
ድጋሚ አማጥኩኝ
ትንሽ ጉድጓድ ስዘል ትልቅ ገደል ሆንሽኝ።

(ገፅ አምስት)

ምንም አይገባሽም
ላሳይሽ ብሞክር ፍቅሬን በተግባር፤
የፍቅር አኩኩሉ
እየተጫወትኩኝ ተደብቄ ነበር፤
ደንታም አልነበረሽ
በስስት ማየቴ ለማሳይሽ ነገር፤
ግን ስፈራ ስቸር
ልነግርሽ ወሰንኩኝ በቃል የኔን ፍቅር።

(ገፅ ስድስት)

የነገርኩሽ ለታ
እንደ መሳቅ እያልሽ
"እንዴት ነው ያየከኝ?" የሚል ወጣ ካፍሽ
"ስሜት የለኝ ላንተ"
በምትለዋ ቃል በሰቀቀን ጥለሽ መንፈሴን አደማሽ
ታዲያ ገፅ አንድ ላይ
ምን አሽኮረመመሽ?...ለምን ስቀሽ አለፍሽ?

(ገፅ ሰባት)

ገብቶሻል ስሜቴ
አትምሰይ እባክሽ ይሄ የማይገባሽ፤
ጨንቆኝ የቀረብኩሽ
እህት ፈልጌ አይደል
ያልገባው አትምሰይ ገብቶሻል እባክሽ።

አሁን በይምሰልሽ አውቀሽ ልትመልሽኝ፤
ሳቅሽ ቀመር ነበር
ዳገቱም ነው ቀመር
አካሄድሽ ቀመር አውቀሽ ነው የታየሽኝ።

(ገፅ ስምንት)

ገፅ ስምንት ላይ
"አውቀሽ ነው የታየሽኝ..." በከፊሉ ይላል.....

የወረቀቱ ገፅ በግማሽ ተቀዷል
.
.
.
.
ውድቆ ቀርቷል እንጂ ታሪኩ ይቀጥላል

@getem
@getem
@getem

#አብርሃም
👍1
ልንገርሽ
#####

ልንገርሽ አንቺዬ
ትንሽ ካሰብኩበት ነገር በኔ ይብሳል፤
ገጣሚ ደንቡ ነው
ከአንገቱ ጎንብሶ ስንኝ ይቀልሳል።

ስንኝ ሌላ አይደለም
አንቺው ነሽ ስንኟ በኔ ድርሰት ዓለም፥
እሩቅ አታስቢ
ይኸው ካንቺ ውጪ ሌላ ማንም የለም።

ልንገርሽ አንቺዬ
ልብ ብለሽ ስሚኝ ብትሰሚ ይበጅሻል፣
አንቺ ካነሽበት
ብዕሬ ክፉ ነው አሳንሶ ያይሻል፤
ከስንኝ ወደ ሀረግ
ከሀረግ ወደ ቃል
ከቃል ወደ ፊደል ቁልቁል ያ




ል።

@getem
@getem
@paappii

#አብርሃም
ጠርጥሪኝ
""""""""""""
በስልኬ ደውዬ
እንገናኝ ብዬ ከቀጠርኩሽ ቦታ
ውዴታ አስቸኩሎኝ
ከ አንድ ሰዓት በፊት ቀድሜ ብመጣ
በሰአትሽ መጥተሽ
ለምን ቆየሽ ብዬ እንዲያው ብንጨረጨር
አስቀድሞ አምጥቶ
እዚህ የጎለተኝ ያንቺው ፍቅር ነበር።

(እናማ አንቺዬ)

ቁጣዬ አይታይሽ
ብበሳጭ ብናደድ እኔ ባንቺ ዛሬ
ፊትሽ ቢለዋወጥ
ውስጥሽ ፈካ ይበል ደስ ይበልሽ ፍቅሬ
ይግባሽ አሁን እስቲ
በዚች ብስጭቴ እኔ አንቺን ማፍቀሬ
አትከፋም አንዳንዴ
የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ
"ምን ሆነ?" እስቲ በይ
......ተይ ጠርጥሪኝ ፍቅሬ 🤔


@getem
@getem
@getem
#አብርሃም
ይማርህ
""""""""""
በአፍንጫ ቀዳዳ
በሰርኔ ጎድጓዳ
ትንሽ ብናኝ ገብታ፤
አሀ..ን..ጥ..ሼ ብዬ
አይኖቼን ጨፍኜ
ለጥቂት ሰኮንዶች ትንፋሼ ቢገታ።

ግድም የማይሰጠው
ባጠገቤ እያለ ተመልካቼ በዝቶ
ወገን እንደሌለው
በንጥሻ ሞትኩኝ ይማርህ ባይ ጠፍቶ..!

@getem
@getem
@getem

#አብርሃም
እድል
"""""""
ችለው አይጋፉት
እንዴት ያደርጉታል የእድልን ጠማማ
እንዲያው ዘመም ያለ
አሮጌ ቤት አይደል በባላ አይቃና!

@getem
@getem
@getem

#አብርሃም
አይቆጡም ጌታ
"""""""""""""""""""
የአለም መድህን ቤዛ የፈጠረን ጌታ፤
ከሰው ተራ ውሎ
በሰው ተመስሎ ተወልዶ ከመጣ፤
ዛሬ ምን ብጫወት
ብቀብጥ ብሽቀናጣ፤
ገርምመው አያዩኝ አይቆጡም ጌታ፤
ከእርሳቸው የበላይ
ከበላይም በላይ ጌታ ስለመጣ።

@getem
@getem
@getem
#አብርሃም
2
ሌባ
''''''''''

ቄጤማ እ'ማይሆን
የበቃቀለው ፥ ከሰርዶም ሙጃ፤
ሲዋትት ዋለ
የኔን ፈልጎ ፥ ህልሜን ኩረጃ።

@getem
@getem
@getem

#አብርሃም
ሁለት ገፅ
"''""""""""""

መራራና ጣፋጭ በአንድ ፅዋ መቅመስ
በግማሽ ፊት ስቀው በግማሽ ፊት ማልቀስ
በአንድ ጎን በርትተው በአንድ ጎን መቅለስለስ
በአንድ ልብ ኩሩ ሆነው በአንድ ልብ መልከስከስ
እልልታና ሙሾ በአንድ ላይ መዋረስ።

@getem
@getem
@getem
#አብርሃም
በስንት ምህላ
በፆም በሱባኤ...
ፅደቅብኝ ያልኩት ፥ ካልሳበሽ መድኔ
ሰይጣንሽን ጥሪው ፥ ይነጥልሽ ከኔ ።

#አብርሃም_ተክሉ

@Abrham_teklu
@Getem
@getem
@getem
#ድኩም_ምርጫ

ሰው ሲኖረው እንጂ ፥ ነብስ ሲዘ'ራበት
ብቻውን ኦና ነው ፥ተክል እና ዳገት
ሰው ነው ያገር ጥንሱ
ሰው ነው ያገር ዳሱ
ሀገር የት ይቆማል ፥ ሰብ እያፈረሱ ?

ብዬሽ እንዳልነበር
ብል በልቶት ጭንቅላት
አልቅት ጎጠኝነት ፥ ተጣብቶን ለቅጣት
ማዘን ተጠይፈን
ከገቢሩ ዘለል ፥ አዳም ላወረሰን ፥ የሰውነት ቅንጣት
ከሰው ሰው መረጥን
ከጣትም ልዩ ጣት !!

ፐ !!!
#ም_ይ_ም_ና

#አብርሃም_ተክሉ
ጳጉሜ / 4/ 2013 ከምሽቱ 3:00
አዲስ አበባ


@Getem
@getem
1👍1
ፀሎተ ገና

ፊኛ...ማንነቶች
ማንም ...እየነፋ
የሚወጥራቸው
ለገባሽ ሆዳቸው
የሚዘላብዱ ...
በመላ አካላቸው...
እግዜር ሰርቶ...ሰርቶ
ሰይጣን የነፋቸው
የደም ጅረት መኋል ...ሀሴት የሚያደርጉ
ምድር ቋያ ስትሆን ...
አየር ተወጥረው ፥ ሰማይ የሚያረግዱ
ነጥረው...




ነጥረው
ቀን የጎደለ ቀን ...በሳር የሚጎዱ
ለእስላም ...ለክርስቲያን
ለሴት ወይ ለወንዱ
ከማንቧቸር ሌላ ፥ ምንም ያልፈየዱ
ንፍፊታም ፊኞች .... ለገና ይፈንዱ !!!

#አብርሃም_ተክሉ

@Abrham_teklu
@Getem
@getem
👍257🔥7🤩2
ካንቺ ካፈቀርኩሽ
እልፍ አእላፍ ግዜ፣ ትዝታሽ ተሻለ
ርቀሽ ሄደሽ እንኳን፣
ረስተሺኝ እንኳን፣
ጥሎኝ ግን አልሄደም፣ ዛሬም አብሮኝ አለ።

@getem
@getem
@paappii

#አብርሃም ተስፋዬ
👍52🔥3327😢9👎5😱4