#የአንድ_አፈር_አፈሮች
•
ፍቅራችንን
ድንበር ወሰን ላይገድበው
ሁለት ክልል ላይመጥነው
መገዳደል ፍት' ላይሆነው
በሽንፈትህ እሠይ ላልል
በሽንፈቴ እፎይ ላትል
ከቂም በቀል ፍቅር ላይበቅል
ልጅህ በእጄ ለምን ይሙት
ልጄስ በእጅህ ለምን ትሙት
እኔና አንተ እኮ
የአንድ እናት ልጆች
ወንድማማቾች
ያንድ አፈር አፈሮች
ርስት አፈሩማ
ይቅርም ከወደዚህ ይሂድም ወደዚያ
ያው ነው የኢትዮጵያ ያንድ አፈር መጠሪያ
ወዲያ ካለው የቀድሞዋ ወዲህ ካለው የእስካሁኗ
ግዳይ ጥዬ በልጅህ ደም በጀግንነት ላልጠራ
ግዳይ ጥለህ በልጄ ደም ላትፎክር ላታቅራራ
ወንድም ገድለው ላይፎክሩ
ጀብዱ ሰርተው ላይኩራሩ
ያዘን ሙሾ ሊዘምሩ
እንደ ማተብ የእምነት ክር ፍቅር ድሩ ላይበጠስ
ባዘናችን ላትዘፍኑ በሞታችሁ ላንደንስ
ስሙር አይሁን ነጭ ሴራው ደስ አይበለው የጠላት ነፍስ
ልጅህ አይሙት በልጄ ጣት
ልጄም አይሙት በልጄ ቀስት
እኔና አንተ እኮ
ከዘመናት በፊት
በታሪክ በሃይማኖት
በባህል በትውፊት
በደስታ በችግር
ስም የለሽ ስመ-ጥር
በጋሻና በጦር ጀብደኛ ባላገር
ያንድ አያቶች ዘር የሁለት አፈር ሠፈር
ስም የለሽ በጥጋብ
ስመ-ጥር በረሃብ
እያሉ ሲተቹህ እያሉ ሲተቹን
በሙጫ ስድብ አጣብቀውን
ሲተቹን መተቸት ሲተቹን መተቸት
እንዳለ ስናውቀው እንዳለ ስታውቁት
ካንድ እናት ተወልደን በሁለት አባት አድገን
አንድ ውሃ ተራጭተን አንድ አፈር አቡክተን
ቃታ ስንሳሳብ
እሺ ላይለው ልብህ ደስ ላይለው ልቤን
እኮ እንዴት እኔና አንተ ዛሬ እንዲህ እንጫከን
እኔና አንተ እኮ
ያንድ እናት ልጆች
ወንድምና እህቶች
ያንድ አፈር አፈሮች
እናም ወንድም ስማኝ ልስማህ
ደስ አይበለው ነገር ሰሪ አንተን ከኔ ጸብ ሲያቃባ
እንዘምር ባንድ እንዝለል ወሰን አይኑር የደም ካባ
በመሞትህ ደስ ላይለኝ ውስጥ ልቤ እዥ ሊያነባ
የናቱ ልጅ ልጅህ ገድሎ ላያሰማ ጉሮ ወሸባ
ፍቅር እንጂ ግድባችን ወሰን አይኑር የደም ካባ
ይልቅስ ልንገርህ
ኩራቴ ኩራትህ
ታሪኬ ታሪክህ
የሚያመጻድቀኝ የሚያመጻድቅህ
የኔም ያባቴ ነው ያንተም የአባትህ
ከቢዘን ባስቀድስ ከግሸን ብትሰልስ
በአክሱም ብትኮራ
ብሸልል በአስመራ
ያንተ አባት አባቴ አባቴ አባትህ
የሚያመያጻድቀኝ የሚያጻድቀኝ ታሪኬ ታሪክህ
መሆኑን ስናውቀው መሆኑን ስታውቁት
በደምና ባጥንት በስጋ በጅማት በታሪክ በትውፊት
መንታ ናቸው ሲሉን
እኮ እንዴት እኔና አንተ ዛሬ እንዲህ እንጫከን
በብቀላ ጸጸት በቀር ወንድም ጥሎ ላይፎክር
ጀግና ተብሎ ሜዳይ ላይኖር
በናቴ ልጅ በመጨከን እሺ ላይለኝ የልቤ በር
ወንድ ልጄን ግዳይ ጥለህ ላይፈታ የደምህ ስር
ካንድ ደብር አድገን በአንድ አስቀድሰን አንድ ዳዊት ደግመን
ካንድ መስጊድ ኖረን ባንድ ሰላት አድገን አንድ ቁርዓን ቀርተን
እኮ እንዴት እኔና አንተ ዛሬ እንዲህ እንጫከን
ለጉዳትህ ተሰዉቼ
ላንተ ክብር ብዙ ሞቼ
ስላንተ ነጻነት ካገርህ ደሜ አለ
በናቕፋ ተራሮች እቅፍ የታዘለ
መጎዳቴን እምቢ ብለህ
ስለ ክብሬ ተሰውተህ
የሰጠኸኝ ክቡር ደምህ
ያንተም አጽም ዓድዋ አለ
ለጦቢያ ነጻነት ስለኔ የዋለ
መንታ ናቸው ሲሉን
ፍቅር ናቸው ሲሉን
እያወቁት ልቦናችን
ሁለት ክልል ላይመጥነን
ድንበር ወሰን ላይገድበን
መገዳደል ፍት' ላይሆነን
በሽንፈትህ ስንዘምር "በለው" ያሉን ሊታዘቡን
ነጭ ሴራ ወጣው ሊሉን
ስጋ ክንድህ ሲደማብህ ልቦናችን ሊያዝብን
ባለም ዜና ድላችንን ደም ጥማት ነው ብለው ሊሉን
ልጅህ በጄ ለምን ይሙት
ልጄስ በእጅህ ለምን ይሙት
ስማኝ ወገን
ደስ አይበለው ነገር ሰሪ አንተን ከኔ ጸብ ሲያቃባ
እንዘምር ባንድ እንዝለል ወሰን አይኑር የደም ካባ
ርስት አፈሩማ
ይቅርም ከወደዚህ ይሂድም ወደዚያ
ያው ነው የኢትዮጵያ ያንድ አፈር መጠሪያ
ወዲያ ካለው የቀድሞዋ ወዲህ ካለው የእስካሁኗ
እናም በሞቱት ሞት
እኔና አንተ አንሙት
እኔና አንተማ
የአንድ እናት ልጆች
ወንድምና እህቶች
ያንድ አፈር አፈሮች
#ኤፍሬም_ስዩም
@getem
@getem
@getem
•
ፍቅራችንን
ድንበር ወሰን ላይገድበው
ሁለት ክልል ላይመጥነው
መገዳደል ፍት' ላይሆነው
በሽንፈትህ እሠይ ላልል
በሽንፈቴ እፎይ ላትል
ከቂም በቀል ፍቅር ላይበቅል
ልጅህ በእጄ ለምን ይሙት
ልጄስ በእጅህ ለምን ትሙት
እኔና አንተ እኮ
የአንድ እናት ልጆች
ወንድማማቾች
ያንድ አፈር አፈሮች
ርስት አፈሩማ
ይቅርም ከወደዚህ ይሂድም ወደዚያ
ያው ነው የኢትዮጵያ ያንድ አፈር መጠሪያ
ወዲያ ካለው የቀድሞዋ ወዲህ ካለው የእስካሁኗ
ግዳይ ጥዬ በልጅህ ደም በጀግንነት ላልጠራ
ግዳይ ጥለህ በልጄ ደም ላትፎክር ላታቅራራ
ወንድም ገድለው ላይፎክሩ
ጀብዱ ሰርተው ላይኩራሩ
ያዘን ሙሾ ሊዘምሩ
እንደ ማተብ የእምነት ክር ፍቅር ድሩ ላይበጠስ
ባዘናችን ላትዘፍኑ በሞታችሁ ላንደንስ
ስሙር አይሁን ነጭ ሴራው ደስ አይበለው የጠላት ነፍስ
ልጅህ አይሙት በልጄ ጣት
ልጄም አይሙት በልጄ ቀስት
እኔና አንተ እኮ
ከዘመናት በፊት
በታሪክ በሃይማኖት
በባህል በትውፊት
በደስታ በችግር
ስም የለሽ ስመ-ጥር
በጋሻና በጦር ጀብደኛ ባላገር
ያንድ አያቶች ዘር የሁለት አፈር ሠፈር
ስም የለሽ በጥጋብ
ስመ-ጥር በረሃብ
እያሉ ሲተቹህ እያሉ ሲተቹን
በሙጫ ስድብ አጣብቀውን
ሲተቹን መተቸት ሲተቹን መተቸት
እንዳለ ስናውቀው እንዳለ ስታውቁት
ካንድ እናት ተወልደን በሁለት አባት አድገን
አንድ ውሃ ተራጭተን አንድ አፈር አቡክተን
ቃታ ስንሳሳብ
እሺ ላይለው ልብህ ደስ ላይለው ልቤን
እኮ እንዴት እኔና አንተ ዛሬ እንዲህ እንጫከን
እኔና አንተ እኮ
ያንድ እናት ልጆች
ወንድምና እህቶች
ያንድ አፈር አፈሮች
እናም ወንድም ስማኝ ልስማህ
ደስ አይበለው ነገር ሰሪ አንተን ከኔ ጸብ ሲያቃባ
እንዘምር ባንድ እንዝለል ወሰን አይኑር የደም ካባ
በመሞትህ ደስ ላይለኝ ውስጥ ልቤ እዥ ሊያነባ
የናቱ ልጅ ልጅህ ገድሎ ላያሰማ ጉሮ ወሸባ
ፍቅር እንጂ ግድባችን ወሰን አይኑር የደም ካባ
ይልቅስ ልንገርህ
ኩራቴ ኩራትህ
ታሪኬ ታሪክህ
የሚያመጻድቀኝ የሚያመጻድቅህ
የኔም ያባቴ ነው ያንተም የአባትህ
ከቢዘን ባስቀድስ ከግሸን ብትሰልስ
በአክሱም ብትኮራ
ብሸልል በአስመራ
ያንተ አባት አባቴ አባቴ አባትህ
የሚያመያጻድቀኝ የሚያጻድቀኝ ታሪኬ ታሪክህ
መሆኑን ስናውቀው መሆኑን ስታውቁት
በደምና ባጥንት በስጋ በጅማት በታሪክ በትውፊት
መንታ ናቸው ሲሉን
እኮ እንዴት እኔና አንተ ዛሬ እንዲህ እንጫከን
በብቀላ ጸጸት በቀር ወንድም ጥሎ ላይፎክር
ጀግና ተብሎ ሜዳይ ላይኖር
በናቴ ልጅ በመጨከን እሺ ላይለኝ የልቤ በር
ወንድ ልጄን ግዳይ ጥለህ ላይፈታ የደምህ ስር
ካንድ ደብር አድገን በአንድ አስቀድሰን አንድ ዳዊት ደግመን
ካንድ መስጊድ ኖረን ባንድ ሰላት አድገን አንድ ቁርዓን ቀርተን
እኮ እንዴት እኔና አንተ ዛሬ እንዲህ እንጫከን
ለጉዳትህ ተሰዉቼ
ላንተ ክብር ብዙ ሞቼ
ስላንተ ነጻነት ካገርህ ደሜ አለ
በናቕፋ ተራሮች እቅፍ የታዘለ
መጎዳቴን እምቢ ብለህ
ስለ ክብሬ ተሰውተህ
የሰጠኸኝ ክቡር ደምህ
ያንተም አጽም ዓድዋ አለ
ለጦቢያ ነጻነት ስለኔ የዋለ
መንታ ናቸው ሲሉን
ፍቅር ናቸው ሲሉን
እያወቁት ልቦናችን
ሁለት ክልል ላይመጥነን
ድንበር ወሰን ላይገድበን
መገዳደል ፍት' ላይሆነን
በሽንፈትህ ስንዘምር "በለው" ያሉን ሊታዘቡን
ነጭ ሴራ ወጣው ሊሉን
ስጋ ክንድህ ሲደማብህ ልቦናችን ሊያዝብን
ባለም ዜና ድላችንን ደም ጥማት ነው ብለው ሊሉን
ልጅህ በጄ ለምን ይሙት
ልጄስ በእጅህ ለምን ይሙት
ስማኝ ወገን
ደስ አይበለው ነገር ሰሪ አንተን ከኔ ጸብ ሲያቃባ
እንዘምር ባንድ እንዝለል ወሰን አይኑር የደም ካባ
ርስት አፈሩማ
ይቅርም ከወደዚህ ይሂድም ወደዚያ
ያው ነው የኢትዮጵያ ያንድ አፈር መጠሪያ
ወዲያ ካለው የቀድሞዋ ወዲህ ካለው የእስካሁኗ
እናም በሞቱት ሞት
እኔና አንተ አንሙት
እኔና አንተማ
የአንድ እናት ልጆች
ወንድምና እህቶች
ያንድ አፈር አፈሮች
#ኤፍሬም_ስዩም
@getem
@getem
@getem
👍1
ድሮና ዘንድሮ...
#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ )
ድሮ....
ሀበሻ በሚሉት ፥ የአማኞች አገር
በሊቅ በመሀይም
ከካባ ተንዶ
በእጅ የሚሰበር
ከለታት ባዱ ለት ፥ ድንጋይ ዳቦ ነበር
ለጥቂት አመታት ፥ በዘለቀው ደቦ
ስንቱ ኮብል ራስ ፥ ምስያውን ጠርቦ
ንጣፍ ረብርቦ ፥ መንገዱን አስውቦ
በሽ ዳቦ በላ ፥ ድንጋዩን ሰብስቦ
ዛሬ...
በዝችው ሀገር ላይ ፥ ተረት ተለወጠ
ተበልቶ አለቅ መሰል ፥ ገበታው አረጠ
ድንጋይ.... ድንጋይ ሆኖ ፥የትም ተቀመጠ
አልፎ ይባስ ብሎ....
እንደፊት ሊበላው
ስራ በማጣቱ
አይቶት የቋመጠ
በተገላቢጦሽ
በጌጠኛው ኮብል
ስንቱ ተፈለጠ
#የሚገርመው
የያኔን ዳቦነት
አሁን ለመታዘብ
ዘመን ላቋረጠ
የዛሬ ትጥቅ ነው
በነብስ ወከፍ መንገድ
ለነብስ የተሰጠ ።
@Abrsh
@getem
@getem
#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ )
ድሮ....
ሀበሻ በሚሉት ፥ የአማኞች አገር
በሊቅ በመሀይም
ከካባ ተንዶ
በእጅ የሚሰበር
ከለታት ባዱ ለት ፥ ድንጋይ ዳቦ ነበር
ለጥቂት አመታት ፥ በዘለቀው ደቦ
ስንቱ ኮብል ራስ ፥ ምስያውን ጠርቦ
ንጣፍ ረብርቦ ፥ መንገዱን አስውቦ
በሽ ዳቦ በላ ፥ ድንጋዩን ሰብስቦ
ዛሬ...
በዝችው ሀገር ላይ ፥ ተረት ተለወጠ
ተበልቶ አለቅ መሰል ፥ ገበታው አረጠ
ድንጋይ.... ድንጋይ ሆኖ ፥የትም ተቀመጠ
አልፎ ይባስ ብሎ....
እንደፊት ሊበላው
ስራ በማጣቱ
አይቶት የቋመጠ
በተገላቢጦሽ
በጌጠኛው ኮብል
ስንቱ ተፈለጠ
#የሚገርመው
የያኔን ዳቦነት
አሁን ለመታዘብ
ዘመን ላቋረጠ
የዛሬ ትጥቅ ነው
በነብስ ወከፍ መንገድ
ለነብስ የተሰጠ ።
@Abrsh
@getem
@getem
…እኔ አንችን ስወድሽ😋
(አብርሃም ሙሉ)
እኔ አንችን ስወድሽ፤ ብሄሩ የጠላኝ
ድምርሽን ስደመር፤ ድምበሬን ያሳጣኝ😂
ነኝ።
"በፍቅር እንመን" ስትይ፤ ያመንኩሽ ታምኜ
መች መስሎኝ ነበረ፤
"ግራ የሚገባኝ፤ የሚጠፋ ቀኜ"😱
እኔ አንችን ስወድሽ፤ ሲጥመኝ ነገርሽ
በምላስሽ ስወቅስ፤ ያለኝን እን-ሽሽ
መቼ መስሎኝ ነበር፤ የሚቆጨኝ ዛሬ
ድምርሽን ሳሰላ፤ ተቀነሰ ዘሬ🙄
እኔ አንችን ስወድሽ፤ ጠላትሽን መክሬ
ብሄሬን ስከዳ፤ ሳምን በሀገሬ
መቼ መስሎኝ ነበር፤ ወገኔ የሚያለቀስ
ሄደ ያልኩት ሀዘን፤ አይሎ ሚመለስ😭
አሁን ግን ስጠላሽ
ደም ብዛት ሲሆነኝ፤ የመግለጫሽ ብዛት"
ድሮ የቀረውን፤ የሴት ልጅ ግርዛት
"ለምላስሽ ያርገው"
አልልሽም እኔ፤ አልጨክንም በሰው😂
@getem
@getem
(አብርሃም ሙሉ)
እኔ አንችን ስወድሽ፤ ብሄሩ የጠላኝ
ድምርሽን ስደመር፤ ድምበሬን ያሳጣኝ😂
ነኝ።
"በፍቅር እንመን" ስትይ፤ ያመንኩሽ ታምኜ
መች መስሎኝ ነበረ፤
"ግራ የሚገባኝ፤ የሚጠፋ ቀኜ"😱
እኔ አንችን ስወድሽ፤ ሲጥመኝ ነገርሽ
በምላስሽ ስወቅስ፤ ያለኝን እን-ሽሽ
መቼ መስሎኝ ነበር፤ የሚቆጨኝ ዛሬ
ድምርሽን ሳሰላ፤ ተቀነሰ ዘሬ🙄
እኔ አንችን ስወድሽ፤ ጠላትሽን መክሬ
ብሄሬን ስከዳ፤ ሳምን በሀገሬ
መቼ መስሎኝ ነበር፤ ወገኔ የሚያለቀስ
ሄደ ያልኩት ሀዘን፤ አይሎ ሚመለስ😭
አሁን ግን ስጠላሽ
ደም ብዛት ሲሆነኝ፤ የመግለጫሽ ብዛት"
ድሮ የቀረውን፤ የሴት ልጅ ግርዛት
"ለምላስሽ ያርገው"
አልልሽም እኔ፤ አልጨክንም በሰው😂
@getem
@getem
#የኔ_ሌላ_ምስል
:
እንቅፋት አግኝቶኝ ፥ ስጓዝ በዱር በመንገድ
ከወገቤ ቢያጥፈኝ ፥ ሰላምታ እንደ መስገድ፣
ዘመዴ እጄን ሲይዝ ፥ 'እኔን!' ሲለኝ ፈጥኖ
'ይድፋህ!' ሲል ጠላቴ ፥ ሲረግመኝ ጨክኖ፣
ጓዴ ግን ሳቀብኝ ፥ አንጀቱ እስኪቆስል
እርሱ ነው ወዳጄ ፥ የኔው ሌላ ምስል።
--------------------//--------------------------
( በርናባስ ከበደ )
@getem
@getem
@lula_al_greeko
:
እንቅፋት አግኝቶኝ ፥ ስጓዝ በዱር በመንገድ
ከወገቤ ቢያጥፈኝ ፥ ሰላምታ እንደ መስገድ፣
ዘመዴ እጄን ሲይዝ ፥ 'እኔን!' ሲለኝ ፈጥኖ
'ይድፋህ!' ሲል ጠላቴ ፥ ሲረግመኝ ጨክኖ፣
ጓዴ ግን ሳቀብኝ ፥ አንጀቱ እስኪቆስል
እርሱ ነው ወዳጄ ፥ የኔው ሌላ ምስል።
--------------------//--------------------------
( በርናባስ ከበደ )
@getem
@getem
@lula_al_greeko
****ትዝብት************
በፈጣሪ ድርሠት;በአለም ልብወለድ ላይ
የሠው ደሥታ ሣይሆን;ሀዘን ነው የሚታይ
፦፦፦፦
እንጀራ የሌለው;መ ሶብ እና ክዳን
የተራበች እናት;ጡት ያልጠባ ህፃን
ደጋግ የሚመሥሉ!!!
አምነው ያላመኑ;እልፍ ምእመናን
የተገፋ አዛውንት;ያልታመነ ድርሣን
፦፦፦++++++++
ተሥፋ ያጣ ወጣት;ምርት ያጣ ገበሬ
ወተት የማትሠጥ;ላም ያልታረሠ በሬ
እልፍ ሣቂታወች!!!
ከለቅሶአቸው ብዛት...
የፊታቸው ፀዳል;መልካቸው የጠፋ
የተከፋ ሠማይ;ደምኖ ያካፋ
፦፦፦+++++++++++
መድረሻው የጠፋው;እልፍ መንገደኛ
ምቾት ያሠቃየው;ውሥኪ ጠጭ መናኛ
እልፍ ታማሚወች;በሽተኛ አካሚ
ከጫጫታ መሀል;የሚፅፍ ገጣሚ
ዘለፋ መፅዋች ህዝብ;ምሥኪን የኔ ቢጤ
እልፍ ኮረዳወች;ያላገባ ላጤ
፦፦፦++++++++++
ሸክም የበዛበት;አሣዛኝ ሠአሊ
ከወጠረው ሸራ ትንሽ ዝቅ ብሎ
እሩቅ እያለመች;ግን እዛው ላይ ያለች
................የምትሣብ ኤሊ
.................<><><>.............................
በፈጣሪ ድርሠት;በአለም ልብወለድ ላይ
የሠው ድሥታ ሣይሆን;ሀዘን ነው የሚታይ
ሀ..ዘ...ን...ነ...ው....የ....ሚ....ታ......ይ.....
//ኅይሌ//
@yasteseryall
@getem
@getem
በፈጣሪ ድርሠት;በአለም ልብወለድ ላይ
የሠው ደሥታ ሣይሆን;ሀዘን ነው የሚታይ
፦፦፦፦
እንጀራ የሌለው;መ ሶብ እና ክዳን
የተራበች እናት;ጡት ያልጠባ ህፃን
ደጋግ የሚመሥሉ!!!
አምነው ያላመኑ;እልፍ ምእመናን
የተገፋ አዛውንት;ያልታመነ ድርሣን
፦፦፦++++++++
ተሥፋ ያጣ ወጣት;ምርት ያጣ ገበሬ
ወተት የማትሠጥ;ላም ያልታረሠ በሬ
እልፍ ሣቂታወች!!!
ከለቅሶአቸው ብዛት...
የፊታቸው ፀዳል;መልካቸው የጠፋ
የተከፋ ሠማይ;ደምኖ ያካፋ
፦፦፦+++++++++++
መድረሻው የጠፋው;እልፍ መንገደኛ
ምቾት ያሠቃየው;ውሥኪ ጠጭ መናኛ
እልፍ ታማሚወች;በሽተኛ አካሚ
ከጫጫታ መሀል;የሚፅፍ ገጣሚ
ዘለፋ መፅዋች ህዝብ;ምሥኪን የኔ ቢጤ
እልፍ ኮረዳወች;ያላገባ ላጤ
፦፦፦++++++++++
ሸክም የበዛበት;አሣዛኝ ሠአሊ
ከወጠረው ሸራ ትንሽ ዝቅ ብሎ
እሩቅ እያለመች;ግን እዛው ላይ ያለች
................የምትሣብ ኤሊ
.................<><><>.............................
በፈጣሪ ድርሠት;በአለም ልብወለድ ላይ
የሠው ድሥታ ሣይሆን;ሀዘን ነው የሚታይ
ሀ..ዘ...ን...ነ...ው....የ....ሚ....ታ......ይ.....
//ኅይሌ//
@yasteseryall
@getem
@getem
ሰውን...እንደ ሀገር
.
.
እግሬ ልራመድ ብቻ
እጄም ልዳብስ ብቻ
ጆሮዬም ላድምጥ ብቻ
አፌም ልጎረስ ብቻ
ጥርሴም ልሳቅ ብቻ
ፀጉሬም ልበጠር ብቻ
ኑሮን ካዩት በኀላ ብቻ ለብቻ
እግሬና እጄ በአንድነት ጎዳና ነጎዱ
ጆሮዬና ምላሴ በእርቅ ኮሚቴ ሰላም አወረዱ
አፌ ከጥርሴ ጋር
በፓናል ውይይት ሁለት ቀን መከረ
ፀጉሬ ብቻ
የመዋሃድ ቀመር ሳይገባው አደረ
===========
ከአካሎቹ(ከአጋሮቹ) ጋራ
የአብሮነትን ሀሳብ እያቀነቀነ
ተላጭቶ ሲቀመጥ፣ሀሳብ እያፈነ
የማያልፉት የለም እያለ ዘፈነ
===========
እናም....
ልምከርህ ፀጉሬ አትሁን መደ-ነስ
ዛሬ ተደምረ ነገ አትቀነስ
አካል ክፍል ሆነ
ፀጉር ነፃ አውጪ(ፀ.ነ.አ) የሚል ግንባር ፈጥረ ብታመጣ
ሰውነት ይኖራል..በራስ ቅል መላጣ
==========
መደ-ነስ=(መደ)መር ና መቀ(ነስ)
✍ሳሙኤል አለሙ
@Sazi5
@getem
@getem
.
.
እግሬ ልራመድ ብቻ
እጄም ልዳብስ ብቻ
ጆሮዬም ላድምጥ ብቻ
አፌም ልጎረስ ብቻ
ጥርሴም ልሳቅ ብቻ
ፀጉሬም ልበጠር ብቻ
ኑሮን ካዩት በኀላ ብቻ ለብቻ
እግሬና እጄ በአንድነት ጎዳና ነጎዱ
ጆሮዬና ምላሴ በእርቅ ኮሚቴ ሰላም አወረዱ
አፌ ከጥርሴ ጋር
በፓናል ውይይት ሁለት ቀን መከረ
ፀጉሬ ብቻ
የመዋሃድ ቀመር ሳይገባው አደረ
===========
ከአካሎቹ(ከአጋሮቹ) ጋራ
የአብሮነትን ሀሳብ እያቀነቀነ
ተላጭቶ ሲቀመጥ፣ሀሳብ እያፈነ
የማያልፉት የለም እያለ ዘፈነ
===========
እናም....
ልምከርህ ፀጉሬ አትሁን መደ-ነስ
ዛሬ ተደምረ ነገ አትቀነስ
አካል ክፍል ሆነ
ፀጉር ነፃ አውጪ(ፀ.ነ.አ) የሚል ግንባር ፈጥረ ብታመጣ
ሰውነት ይኖራል..በራስ ቅል መላጣ
==========
መደ-ነስ=(መደ)መር ና መቀ(ነስ)
✍ሳሙኤል አለሙ
@Sazi5
@getem
@getem
በግ ተራ!!!!!!!!
ዮኒቨርስቲ ሳለን በግ ተራ ወርደን፤
እንመለስ ነበር የዋህ በግ አርደን፤
ዛሬማ የጉድ ነው፤
የዘመኑ ተሜ፤
ወግ ይድረሰኝ ብሎ፤ በግ ተራ ሲጋፋ፤
ሁሉም አራጅ ሆነ ፤ በግ የሚሆን ጠፋ።
(( ጃ ኖ ))💚💛❤️
@getem
@getem
@balmbaras
ዮኒቨርስቲ ሳለን በግ ተራ ወርደን፤
እንመለስ ነበር የዋህ በግ አርደን፤
ዛሬማ የጉድ ነው፤
የዘመኑ ተሜ፤
ወግ ይድረሰኝ ብሎ፤ በግ ተራ ሲጋፋ፤
ሁሉም አራጅ ሆነ ፤ በግ የሚሆን ጠፋ።
(( ጃ ኖ ))💚💛❤️
@getem
@getem
@balmbaras
ለጁምኣችን!
💚
በዱኒያ እሽቅድድም፤
በልፊያው በግፊያው እየተራመዱ፤
እንደ ቢላል ልጆች ፤
ከመንገዱ በፊት፤
አድርሰኝ እያሉ፤ ስጁድ ካልወረዱ
ምን ቢሽቀዳደሙት፤
ምን ቢንደረደሩት ፤
አይሞላው ጎተራው አይሰልጥም መንገዱ።
(( ጃ ኖ ))💚💛❤
ሸጋ ጁምኣ!💚
@getem
@getem
@balmbaras
💚
በዱኒያ እሽቅድድም፤
በልፊያው በግፊያው እየተራመዱ፤
እንደ ቢላል ልጆች ፤
ከመንገዱ በፊት፤
አድርሰኝ እያሉ፤ ስጁድ ካልወረዱ
ምን ቢሽቀዳደሙት፤
ምን ቢንደረደሩት ፤
አይሞላው ጎተራው አይሰልጥም መንገዱ።
(( ጃ ኖ ))💚💛❤
ሸጋ ጁምኣ!💚
@getem
@getem
@balmbaras
መሄድ.. መሄድ... መሄድ...
"""""""""""""""""""""""
እኔን ተሸክሜ እራሴን በኔው ክንድ
በወደድኩት መንገድ ዝም ብየ ስሄድ
ዝም ብየ ስሄድ... በመረጥኩት መንገድ
እንደው ስሄድ ስሄድ...
እንደው ብሄድ ብሄድ
አልደርስ አልኩኝሳ
ምነው እየሄድኩኝ
ሳልደርስ እየመሸ ሳልደርስ ነጋሳ
""""""""""""""""""""""""""""
ወሳጅ ነው መሰለኝ የወደድኩት መንገድ
ጫፍ የለውም መሰል የመረጥኩት መንገድ
ለመድረስ እያልኩኝ ይሄው አለሁ ስሄድ
እደርሳለሁ እያልኩ ከረምኩኝ በመንገድ
ከረርኩኝ በመንጎድ
ቢሆንም መሄድ ነው፤ የልቤ ቁም ነገር
ወትሮም መድረሻየ፤ መጀመሪያ ነበር
"""""""""""""""""""""""""""
ዮሐንስ ፍቃዴ
@getem
@getem
@getem
"""""""""""""""""""""""
እኔን ተሸክሜ እራሴን በኔው ክንድ
በወደድኩት መንገድ ዝም ብየ ስሄድ
ዝም ብየ ስሄድ... በመረጥኩት መንገድ
እንደው ስሄድ ስሄድ...
እንደው ብሄድ ብሄድ
አልደርስ አልኩኝሳ
ምነው እየሄድኩኝ
ሳልደርስ እየመሸ ሳልደርስ ነጋሳ
""""""""""""""""""""""""""""
ወሳጅ ነው መሰለኝ የወደድኩት መንገድ
ጫፍ የለውም መሰል የመረጥኩት መንገድ
ለመድረስ እያልኩኝ ይሄው አለሁ ስሄድ
እደርሳለሁ እያልኩ ከረምኩኝ በመንገድ
ከረርኩኝ በመንጎድ
ቢሆንም መሄድ ነው፤ የልቤ ቁም ነገር
ወትሮም መድረሻየ፤ መጀመሪያ ነበር
"""""""""""""""""""""""""""
ዮሐንስ ፍቃዴ
@getem
@getem
@getem
ቅዳሜ እና ናፍቆት !!!!!!
ከቅዳሜ መሃል፣ አንዳንዱ ቅዳሜ፣
አልጠገብኩም ይላል፣
እንደ ሙና ከንፈር፣ ተስሜ ተስሜ።
ይኸውልሽ ውዴ፣
ብዙ ቀን አለፈኝ፣
የሚሳም ቅዳሜ፣
ፍልቅልቅ ቅዳሜ፣ ከኔ ማጀት ወጥቶ፣
ፈልገኝ ይለኛል፣
ከነምናምኑ ካንች ጉያ ገብቶ።
እንደ በትረ ሎሚ፣ ተንቦክቦክ እያለ፣
ሉባንጃ ያወደው፣ ብርጉድ የታጠነ፣
ለጀማ እሚበቃ፣
ሙት የሚቀሰቅስ፣
ዘበናይ ቅዳሜ ካንች ከንፈር አለ???
ግን ውዴ፣
አንዳንዱ ቅዳሜ፣
ቀን አይወጣለትም፣
አያገማሸርም አያሞቅም ማጀት፣
ልክ እንደ አቦል ቡና፣
ውል ባለ ጊዜ ፣
ይዘውራል ራስ፣ ይፈትናል አንጀት።
እናም ሸጋዬዋ፣
ደማቁ ቅዳሜ፣
ሁሌ እንደለመድኩት ፣
ፍልቅልቅ፣
ፍንድቅድቅ፣
ሽሙንሙን እያለ፣ ቀኔ እንዲደምቅልኝ፣
የምወድሽዋ፣
ፍ .ል.ቅ.ል.ቅ.ል.ቅ ብለሽ፣ እባክሽ ሳቂልኝ።
ሳቂልኝ!!!!
((( ጃ ኖ )))💚💛❤️
ሸጋ ሸግዬ ቅዳሜ ትሁንላቹ!!!!
@balmbaras
@getem
@getem
ከቅዳሜ መሃል፣ አንዳንዱ ቅዳሜ፣
አልጠገብኩም ይላል፣
እንደ ሙና ከንፈር፣ ተስሜ ተስሜ።
ይኸውልሽ ውዴ፣
ብዙ ቀን አለፈኝ፣
የሚሳም ቅዳሜ፣
ፍልቅልቅ ቅዳሜ፣ ከኔ ማጀት ወጥቶ፣
ፈልገኝ ይለኛል፣
ከነምናምኑ ካንች ጉያ ገብቶ።
እንደ በትረ ሎሚ፣ ተንቦክቦክ እያለ፣
ሉባንጃ ያወደው፣ ብርጉድ የታጠነ፣
ለጀማ እሚበቃ፣
ሙት የሚቀሰቅስ፣
ዘበናይ ቅዳሜ ካንች ከንፈር አለ???
ግን ውዴ፣
አንዳንዱ ቅዳሜ፣
ቀን አይወጣለትም፣
አያገማሸርም አያሞቅም ማጀት፣
ልክ እንደ አቦል ቡና፣
ውል ባለ ጊዜ ፣
ይዘውራል ራስ፣ ይፈትናል አንጀት።
እናም ሸጋዬዋ፣
ደማቁ ቅዳሜ፣
ሁሌ እንደለመድኩት ፣
ፍልቅልቅ፣
ፍንድቅድቅ፣
ሽሙንሙን እያለ፣ ቀኔ እንዲደምቅልኝ፣
የምወድሽዋ፣
ፍ .ል.ቅ.ል.ቅ.ል.ቅ ብለሽ፣ እባክሽ ሳቂልኝ።
ሳቂልኝ!!!!
((( ጃ ኖ )))💚💛❤️
ሸጋ ሸግዬ ቅዳሜ ትሁንላቹ!!!!
@balmbaras
@getem
@getem
\\__ሀገር እንደ ሰይ-ብል__//
በታሪኩ ገላሼ
(@ዘሩባቤል ዘወርቅያንጥፉ)
አዎን ወንድማለም!
ያኔ ለጋ ሳለን ለማንም ከንቱ ሀሳብ ሳንሞላ በፊት፥
ፍቅር አጠራርቶን
ያለማንም ውስዋስ ያለማንም ግፊት፥
ጮሮቃ ጨልፈን አብረን እየጠጣን በዕንቁላል ቅርፊት፥
እንዲህ ተጫውተናል!
፥
እኩል አፈር ገፍተን እኩል ምድሩን ገምሰን፥
እሰይ የምንልበት አምስት ጉርጓድ ምሰን፥
ብይ ለገባለት ጎሽ እሰይ እያልን፥
ያበሸቀን ወዳጅ ብይ ሲስት ሲሰብር
ጎሽ እሰይ እያልን፥
ስለወንድማዊ አፍቅሮት ነበረ
ከአቧራው መሀል የተንከባለልን።
፥
ትዝ ይልሃል አይደል
ቼቼ ማለት አሊያም
ብይ ማሲያዝ በሚል ለዘብተኛ ቁማር፥
በሰይብላችን ህግ ፍቅርን ስንማማር፥
ያቸነፈ ቼቼ ሲባል እስከሰፈር፥
አልወርድም አይልም በልጅ አተፋፈር።
፤
ከአንድ ለአምስት በፊት እንደተማማርነው፥
በአምስት እንዲፀና ነገራችን ሁሉ
አምስት የቆፈርነው፥
ስድስት እና ሰባት ስላልሆኑ አይደለም፥
ስምምነት ካለ ሺም ጉድጓድ ብንቆፍር ትበቃለች አለም፥
ዳሩ ግን
ሰይ ባንከረባብት
ሰይ ለሁሉም ስንባባል፥
ከእሰያቻን ፊት ላይ ክብር እና ፍቅር እኩል ይነበባል።
።
የለም የለም
ወንድም ጋሼ
ዛሬስ አልጣመኝ ሰይ አባባላችን ድምፁ ጎረነነ፥
ለፍቅር የማስነው ለጥላቻ ሆነ።
እይ እስኪ ግንባሬን የፊቴን መቋጠር፥
ሰው እንዴት ይነቅዛል በጉድጓድ በጠጠር።
እይ እሰይ ስንባባል
ጎሽ ስንባባል
ለአንዳችን መሠበር ለአንዳችን መቸነፍ፥
አንዳችን ስንስቅ ስናቀብል ሰደፍ፥
እይ የዘመንን መዛግ በግፍ መተዳደፍ፥
፤
ወንደማልምዬ
ይሄ ነው ጨዋታው ያስተማረን እኛን?
ይሄን ሊያባብል ነው ያሳደገን እኛን?
የለም የለም
ፀብ አይደል ፍቅር ነው ካቧራው ያላፋን ከትቢያው ያስተኛን።
፤
ወንድማለም ውዴ
ያልተስተማርከውን በሰይ ብል ጨዋታ፥
ወንድምህ በሰይብል በጠጠሯ ፈንታ፥
ጎሽ እሰይ አትበል አናቱን ሲመታ፥
አንተም ባንተ አቅም አንተም ባንተ ፈንታ፥
ማሊያ እየለወጥህ ምሽግ እየቀየርክ አሳደህ ልትመታ፥
በአጉል ዝልልፍ በአጓጉል ጥልልፍ አፍህን አትፍታ።
፤
አዎን ወንድምዬ
በጉርጌ እንደለመድህ መገለባበጡን፥
የብብትህን አትጣል ስታወርድ የቆጡን።
፤
እባክህ ወንድሜ
ፎቅ እየሰራራን በሀገር መሬት ላይ
ብይ የተጫወትነው፥
ሊመታ የነበር ተመቺ እንዲሆንልን
ያንከረባበትነው፥
ሰላም መከባበር ፍትህ እንዲሰፍን
ስለናፈቀን ነው፥
እናም
ህጋችን ተጥሶ መሆንን እንዳንሆን አይሆኑ የምንሆነው፥
ያለወግ ብንጋጭ ትርፋችን ምንድነው?
እባክህ ወንድሜ
ሆድ ሲብሰን ደርሰን ልናደርገው ምሽግ፥ ጉድጓዱን አንማስ መቀበሪያችንን በጃችን ኣናድርግ፥
ካልተስማማን ይቅር ጨዋታውን እንበትነው ጉድጓዱንም ይድፈን፥
ለሰኞ ማክሰኞ
ጨዋታ እንዲሆን
መሬትም ባናገኝ መቀበሪያ ይትረፈን። አደራ!!!
ህዳር 20, 2012 ዓ.ም
አዳማ ኢትዮጵያ
የግርጌ ማስታወሻ!
ስለመነሻ ሀሳቡ የ90s እድምተኛ ሁሉ የዚህ ግጥም ባለቤት ነው
@getem
@getem
በታሪኩ ገላሼ
(@ዘሩባቤል ዘወርቅያንጥፉ)
አዎን ወንድማለም!
ያኔ ለጋ ሳለን ለማንም ከንቱ ሀሳብ ሳንሞላ በፊት፥
ፍቅር አጠራርቶን
ያለማንም ውስዋስ ያለማንም ግፊት፥
ጮሮቃ ጨልፈን አብረን እየጠጣን በዕንቁላል ቅርፊት፥
እንዲህ ተጫውተናል!
፥
እኩል አፈር ገፍተን እኩል ምድሩን ገምሰን፥
እሰይ የምንልበት አምስት ጉርጓድ ምሰን፥
ብይ ለገባለት ጎሽ እሰይ እያልን፥
ያበሸቀን ወዳጅ ብይ ሲስት ሲሰብር
ጎሽ እሰይ እያልን፥
ስለወንድማዊ አፍቅሮት ነበረ
ከአቧራው መሀል የተንከባለልን።
፥
ትዝ ይልሃል አይደል
ቼቼ ማለት አሊያም
ብይ ማሲያዝ በሚል ለዘብተኛ ቁማር፥
በሰይብላችን ህግ ፍቅርን ስንማማር፥
ያቸነፈ ቼቼ ሲባል እስከሰፈር፥
አልወርድም አይልም በልጅ አተፋፈር።
፤
ከአንድ ለአምስት በፊት እንደተማማርነው፥
በአምስት እንዲፀና ነገራችን ሁሉ
አምስት የቆፈርነው፥
ስድስት እና ሰባት ስላልሆኑ አይደለም፥
ስምምነት ካለ ሺም ጉድጓድ ብንቆፍር ትበቃለች አለም፥
ዳሩ ግን
ሰይ ባንከረባብት
ሰይ ለሁሉም ስንባባል፥
ከእሰያቻን ፊት ላይ ክብር እና ፍቅር እኩል ይነበባል።
።
የለም የለም
ወንድም ጋሼ
ዛሬስ አልጣመኝ ሰይ አባባላችን ድምፁ ጎረነነ፥
ለፍቅር የማስነው ለጥላቻ ሆነ።
እይ እስኪ ግንባሬን የፊቴን መቋጠር፥
ሰው እንዴት ይነቅዛል በጉድጓድ በጠጠር።
እይ እሰይ ስንባባል
ጎሽ ስንባባል
ለአንዳችን መሠበር ለአንዳችን መቸነፍ፥
አንዳችን ስንስቅ ስናቀብል ሰደፍ፥
እይ የዘመንን መዛግ በግፍ መተዳደፍ፥
፤
ወንደማልምዬ
ይሄ ነው ጨዋታው ያስተማረን እኛን?
ይሄን ሊያባብል ነው ያሳደገን እኛን?
የለም የለም
ፀብ አይደል ፍቅር ነው ካቧራው ያላፋን ከትቢያው ያስተኛን።
፤
ወንድማለም ውዴ
ያልተስተማርከውን በሰይ ብል ጨዋታ፥
ወንድምህ በሰይብል በጠጠሯ ፈንታ፥
ጎሽ እሰይ አትበል አናቱን ሲመታ፥
አንተም ባንተ አቅም አንተም ባንተ ፈንታ፥
ማሊያ እየለወጥህ ምሽግ እየቀየርክ አሳደህ ልትመታ፥
በአጉል ዝልልፍ በአጓጉል ጥልልፍ አፍህን አትፍታ።
፤
አዎን ወንድምዬ
በጉርጌ እንደለመድህ መገለባበጡን፥
የብብትህን አትጣል ስታወርድ የቆጡን።
፤
እባክህ ወንድሜ
ፎቅ እየሰራራን በሀገር መሬት ላይ
ብይ የተጫወትነው፥
ሊመታ የነበር ተመቺ እንዲሆንልን
ያንከረባበትነው፥
ሰላም መከባበር ፍትህ እንዲሰፍን
ስለናፈቀን ነው፥
እናም
ህጋችን ተጥሶ መሆንን እንዳንሆን አይሆኑ የምንሆነው፥
ያለወግ ብንጋጭ ትርፋችን ምንድነው?
እባክህ ወንድሜ
ሆድ ሲብሰን ደርሰን ልናደርገው ምሽግ፥ ጉድጓዱን አንማስ መቀበሪያችንን በጃችን ኣናድርግ፥
ካልተስማማን ይቅር ጨዋታውን እንበትነው ጉድጓዱንም ይድፈን፥
ለሰኞ ማክሰኞ
ጨዋታ እንዲሆን
መሬትም ባናገኝ መቀበሪያ ይትረፈን። አደራ!!!
ህዳር 20, 2012 ዓ.ም
አዳማ ኢትዮጵያ
የግርጌ ማስታወሻ!
ስለመነሻ ሀሳቡ የ90s እድምተኛ ሁሉ የዚህ ግጥም ባለቤት ነው
@getem
@getem
የነበረኝ የለም፣ያለኝ አልነበረም!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ወደ ውስ ጤ ገባሁ. . .
የውስጤ ውስጥ ላይ ዘልቄ ተገኘሁ!
ያገኘሁት ገረመኝ. . .
ያጣሁት አመመኝ!
ድር የዋጠው ትዝታ፤
ያልበላሁት ገበታ፤
የተረሱ ሰዎች፣
የአደራ ልቦች፣
ዳር-አልባ ናፍቆት፤
ያልታቀደ ስርቆት፣
ያልተፈታ እንቆቅልሽ፣
'ሚያስፈራ አባርሮሽ፣
ያላለቀ መንገድ፤
የፈረሰ መውደድ፣
ቆራሌው ማንነት፣
ውሸት ብቻ እውነት!
የነበረኝ የለም
ያለኝ አልነበረም፣
ሊኖረኝ የቃጣው መኖር አልጀመረም!
በዚህ ሁሉ መሐል. . .
ያጣሁት ምን ቢያመኝ
የቀረው ቢገርመኝ፣
ቁም-ነገር ፍለጋ፣
የውስጠኛዬን ባሕር፣ቀዝፌ ስዋኘው፣
እንደ ክራር ክሮች፣ድርድሩን ስቃኘው፣
የሚረባኝ ነገር ራሴን ብቻ አገኘሁ!
.
@huluezih
@getem
@getem
@getem
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ወደ ውስ ጤ ገባሁ. . .
የውስጤ ውስጥ ላይ ዘልቄ ተገኘሁ!
ያገኘሁት ገረመኝ. . .
ያጣሁት አመመኝ!
ድር የዋጠው ትዝታ፤
ያልበላሁት ገበታ፤
የተረሱ ሰዎች፣
የአደራ ልቦች፣
ዳር-አልባ ናፍቆት፤
ያልታቀደ ስርቆት፣
ያልተፈታ እንቆቅልሽ፣
'ሚያስፈራ አባርሮሽ፣
ያላለቀ መንገድ፤
የፈረሰ መውደድ፣
ቆራሌው ማንነት፣
ውሸት ብቻ እውነት!
የነበረኝ የለም
ያለኝ አልነበረም፣
ሊኖረኝ የቃጣው መኖር አልጀመረም!
በዚህ ሁሉ መሐል. . .
ያጣሁት ምን ቢያመኝ
የቀረው ቢገርመኝ፣
ቁም-ነገር ፍለጋ፣
የውስጠኛዬን ባሕር፣ቀዝፌ ስዋኘው፣
እንደ ክራር ክሮች፣ድርድሩን ስቃኘው፣
የሚረባኝ ነገር ራሴን ብቻ አገኘሁ!
.
@huluezih
@getem
@getem
@getem
👍1