ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
175 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ለሰንበታችን!
💚

ጉራማይሌ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከ 8 ወራት በላይ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ሲያግዝ እንደነበር እዚህ ላይ ፎቶዎችን በመለጠፍ ስናሳውቃችሁ ቆይተናል።




ሆኖም ህጋዊ ሰውነታችን ጥቅምት 13/2012 በመሰጠቱ አሁን ላይ የራሳችን ቋሚ ቦታ ኖሮን በጎ ስራችንን ለማካሄድ ነገን እየጠበቅን ነው!!

ቦታ ፡ መገናኛ ቦሌ ክፍለ ከተማ ህንፃ በር ላይ
ሰዓት ፡ ከ3:00-8:00

የስራ ግብዓቶቻችን ከስር ዘርዝረናል ከቻሉ ያምጡሉን ካልቻሉ በአካል በመገኘት በጉልበት ያግዙን ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን!!

1 የገላም የፊትም ሳሙና
2 መታሻ ግላብ እና ግላብ
3 ያገለገሉም ይሁን ያላገለገሉ አልባሳት እና ጫማዎች
4 ማበጠሪያ
5 ጥፍር መቁረጫ
6 ሞዴስ
7 የወንዶች ጸጉር ማስተካከያ ማሽን
8 በርሚል እና ውሃ ማመላለሻ ባልዲዎች
9 ቅባት
10 ስፒከር ከእነማይኩ ለፕሮሞሽን ያስፈልገናል
11 ውሃ መቅጃ ጆክ

ለበለጠ መረጃ
+251955431015
+251912319263
+251988342836
+251931823235

"ጉራማይሌ የበጎ አድራጎት ድርጅት"

"ናካይታ"!💚
@Hab_G
@Guramayelie
*ህመም ፩***
በአንዲት ትንሽ ቅፅበት
በትንሽ መንደር ውሥጥ
ዙሪያየን ሥቃኘው
ይህ ነው የሚታየኝ.....
ሢጠጡ ያደሩ የጀዘቡ ነፍሶች
የተበታተኑ የቢራ ጠርሙሶች
ከበሩ ፊት ለፊት....
ሀገር የገነቡ ድንበር ያሥከበሩ
ጊዜ የጣላቸው ሠው ያላነሣቸው
ንፋሥ ላይ ተቀምጠው የሚራቡ ፊቶች
.....ትንሽ ዝቅ ብሎ...
ሁለት ልጅ ያዘለች
ከጡአት እሥከ ማታ ላፍታ ያላረፈች
የተጎሣቆለች ቆሎ ምትሸጥ እናት
ምንገድ ዳር ላይ ውላ ምንገድ የምታድር
..........................ማረፊያ የሌላት
ከዚህ አለፍ ብሎ...
ሽቶ ተርከፍክፈው ድሀ ተፀይፈው
የሚጉአዙ ጥንዶች..
ከነሡ ከፍ ብሎ
አየር ላይ ሚበሩ ጥንብ አንሣ ጭልፊቶች
..
ዱላ የጨበጠ ጋንጃ መቶ አዳሪ
ከቅርብ እርቀት ላይ..
እንዳላየ የሚያልፍ ሠላም አሥከባሪ
..
የተበታተኑ መፈክር የያዙ በጭሥ የታፈኑ
ሥራ አጥ ወጣቶች...
ከነሡ ፊት ለፊት...
ጥይት የታጠቁ እልፍ ወታደሮች
ከዚህ ሁሉ ጀርባ...
ግርማ የሌላቸው የፈረሡ ግንቦች።

#ኅይሌ

@getem
@getem
👍1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
//ላጣህ አቅም አጣሁ//

ዓለማዊ ልቤ ለበሰልህ ዳባ ምናኔ ተመኘ
በናቴ ቀብር ላይ የጠፋብኝ እንባ ፊቴ ላይ ተገኘ
ላጣህ አቅም አጣሁ፤

የሳምሶንን ገድል
ያላዛርን እድል
ያቡየን ተአምር
ተቀብዬ ነበር ቄስ እንዳስተማረኝ
አንተን አጣሁ ብየ ማመኑ ቸገረኝ

ክረምቱ ጨከነ
ጨላለመ ጋራው
በረዶና ጭፍራው
ከዋሻቸው ወጡ
ዛፎች ተመለጡ
ከምልአት ጎደሉ
ላባቸውን ያጡ
አሞሮች መሰሉ፤

ልረሳህ አልቻልኩም ልረሳህ እልና
ፊትህን አትመህ በየብስ በደመና
ከንፈርህ ያውና
ፈገግታህ ያውና
ውብ ዓይንህ ያውና ።


ግጥሙ ላይ የፆታ ለውጥ ተደርጓል
ገጣሚ:- በዕውቀቱ ሥዩም
@getem
@getem
@gebriel_19
#ከሠዓሊው_ደጃፍ

አይቀድምም ሰዕሉ ከምኖር ላይ ባለም
ከዚች ግዙፍ ምድር ያልተቀዳ የለም
በተመስጦ ጋሪ መምሰልን ሰግሮ እውነትን ሚጋልብ
አያውቁም ብሎ ነው የተኖረ ሰዕል ለሰው የሚያስነብብ

አትስጡ ድማሜ ላረንጓዴ ቅጠል እውነትነት ላጣ
ዛፉን ሰብሮ ሰብሮ ብሩሽ ባደረገው በሠዐሊው ተንኮል ሸራ ላይ በወጣ

ምድር ትግስተኛ ምንም አትናገር ውበቷን ሲሰርቁ
ገብቷት ይሆን መሰል ዘመኗን ሲጨርስ ዘመኑ ማለቁ

አትስጡ ድማሜ ሳርሳሩን የሚግጥ በሬውን አየታችሁ
በተሳለ ቢላ ስጋውን በልቶ ነው ቆዳውን ወጥሮ ሳልኩት የሚላችሁ

እንዲ ነው ሰዐሊ በወጠራት እውነት ውሸቱን ይኖራል
ያደነቁት አይኖች በጨመቁት እንባ ቀለሙን ይሰራል
አትስጡ ድማሜ በሰፊው ጎዳና ነፋስ ተንተርሶ
ገላውን ሚመስል ጠባብ ሱሪ ለብሶ
ሆዱን በእግሩ ቀብሮ የተራበ አንድ ሰው
ከመቀመጥ ብዛት መነሳት ያነሰው

ሳንቲም አየሰጠ መውደቁን የገዛው ይህ ሰዓሊ ነበር
ከደጃፉ አንስቶ ሸራ ላይ ጥሎት ነው ሚፎክረው ላገር

ይህ ነው መጨረሻው አይን እየከፈቱ አዕምሮ የዘጉ ለት
ዝም ብሎ መመሰጥ ዝም ብሎ ማጨብጨብ ሲቸረቸር አውነት
ስዕል
የሚቀበባበት ብሩሽ ላጣ ቆሌው ከጥበብ ለመነነ
እውነት መስረቅ ለሱ ስዕል መሳል ሆነ ፡፡

ተፃፈ 6-09-2010
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
#ቀንዲል

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።

መጣች አሉኝ ደግም !

ቀኔ ላይ ፅልመቷን ፥ እንዳልነበር ጥላ

ላምናው ልምምጤ ፥ 

መልሷን ለማበደር ፥ እንዳላለች ችላ

ንፁህ ነኝ ለማለት እጇን ውሀ ነክራ 

ለመናኙ ልቧ

የደፋችውን ቆብ ፥ ስፌቱን ተርትራ 

በከተማው አጀብ.. .

አሸወይና ልትል ፥ ዳግም ተሞሽራ

መጥታለች ይላሉ.. .

ያቺ ለምዳም ተኩላ ፥ የዋሁ በግ ነኝ ባይ

መጥታለች ይላሉ.. .

ያቺ ቄሳሪያዊ ፥ ባለ ጭንብላም ቄስ ፥ የመሲህ አታላይ

መንታ ጥያቄዋን ልትዘነዝር ቀርባ 

ረጭታ ልትጮህ የአዞንቷን እንባ

በቀል ባጀገነው

ሽንፈት በማያውቀው 

አጥፍቶ ባፈረ ፥ ባደፈ ህሊና

እውነቷን ልትቀብር ፥ እሳቱን አዳፍና

መታለች ይላሉ

እንዲህ ያወራሉ ... 

በበደሏ ቆስሎ ለላላው አንጀቴ ነገር ይፈትላሉ። 

።።።።

እኔም ደግሞ እላለሁ!

መምጣቱንስ ትምጣ

የመሸገችበት ጥሻውን ገላልጣ

ቀርባም ትናገረኝ.. .

በዳይ ነህ ትበለኝ.. .

እንባዋንም ታፍስስ ፥ ደረት እየደቃች ፥  ያለ ስስት ትዝራ

ጨለማ ሲኖር ነው ... 

የቀንዲሌ ፋኖስ ፥ አልነግቶም እያለ መንገድ 'ሚያጠራ

👇

።።።። የቀንዲል የጥበብ ምሽት መዳረሻ ስራ ነች ።።።።።

( ...መጭው..አርብ  .ፓናሮማ ሆቴል ከ11፡00 ጀምሮ ....መግቢያ 100 ብር ነው ጓዶች ...ሼር ይደረግ) 

@getem
@getem
@getem
((ሰለሞን ሳህለ))

"እናትሽ..." ይሰኛል የግጥሜ ርእሱ
እናትሽ...
እናትሽ ምን ትሁን ?
ሶስት ነጥብ አለዉ ከእናትሽ ቀጥሎ
ቀጣዩን ሊነግርሽ ጅማሬዉን ጥሎ
እናትሽ . . .(ሶስት ነጥብ ያዉም በዝግታ)
እናትሽ ትባረክ ትዉለድ መንታ መንታ
አንዷን ትሞሽራት አንዷን አስጠቅታ
እናትሽ...(አሁንም ሶስት ነጥብ)
እናትሽ ትባረክ ትዉለድ ሁለት ቀና
አንዷ ለቁም ነገር አንዷ ለሽፍድና
እናትሽ...አሁንም ሶስት ነጥብ
ለፍቅር አይደለም ወይም ደግሞ ለጠብ
አንቺ ግን እንዴት ነሽ ከናትሽ ምናለኝ
ሰይጣን አፈር ይብላ እናትሽ ያስባለኝ
በነገራችን ላይ ሶስት ብየ አንድ አለኝ
ርእሴን ልጻፍ
ፍርሃት ከከበበሽ ጠብ ጠብ ከሸተተኝ
ርእስ
ይቅርታ
ፖራምፖ ድርጭታ
አሲምባ ወዲባ
ዱደቢት ደዲባ
ደዱዲ ዲዲዳ
ባገራችን እዳ
በሸንኮር አገዳ
በግድብ በግምቡ
ባሸሸዉ ፈረንካ ያበጠበት ልቡ
ባየር ላይ ጨዋታ
ባየር ላየር ንግዱ
አፍራሽ አስራ ሀንዱ
እድገት አስራ አንዱ
ወይ አንዱን አይጠሉ
ወይ አንዱን አይወዱ
ሸጋ ሰዉ ሸሽገዉ
ፉንጋ አያስወርዱ
እናትሽ ይግባቸዉ
እናትሽ ይረዱ
ሶስት ነጥብ አለኝ
ሶስት ግዜ ይዉለዱ

@lula_al_greeko
@getem
@getem
👍1
#ህልሜና ~ትርታሽ

በሰመመን ጉዞ
እርቄ ከትሜ ውን አለሜን ትቼ
ከመዳፍሽ እቅፍ
በጡችሽ መሀል ልብሽ ላይ ተኝቼ
ለምን እንደው እንጃ
በትርታሽ ምናብ እቁነጠነጣለሁ
ከሀሳብሽ ሞገድ
ግራ የተጋቡ ቃላት አደምጣለሁ፡፡

መሄድ ነው ውጥንሽ
ከ'ኔነቴ መራቅ መልመድ ከሌላ ሰው
ታዲያ በምን አቅሜ
ከ'ንቅልፌ ነቅቼ ህልምሽን ላፍረሰው?

አልችልም ታውቂያለሽ
የማፍቀሬ ጣራ ነፃነት ነው ጥጉ
መሻትሽ ቢያመኝም
ከጉዞ አይገታሽም አንቺን መፈለጉ

እናም በሃሳብሽ
እርቀሻል ብዬ አልነቃም ከ'ንቅልፌ
ነግቶ እስክትለይኝ
በእጆችሽ ላይ ልደር እቅፍሽ ነው ትርፌ፡፡


(ልብ አልባው ገጣሚ)

@getem
@Getem
@gebriel_19
"ተስፋ ያለው ግጥም"

© በታመነ መንግስቴ

አዛን አለ ሀረር
ጎንደር ይቀደሳል
ኢሉ አባቦራ ላይ
"ኢትዮጵያ" የሚለው
ስምሽ ይወደሳል፡፡

በአርያም አንች አለሽ
በጀነት ፣በገነት
በየደማችን ነው
ዛርና መንፈሱ
የኢትዮጵያዊነት፡፡

አክሱም ፅዮን ጫፍላይ
ሠንደቅሽ ተተክሎ
ወሎየ ሲመርቅ
ዘይር ጀባ ብሎ፣
አክሊልሽ ጋምቤላ
በወርቅ ሲሰራ
ሽናሻ ይፈታል
ሰይጣን ያሰረውን
ጠልፎ 'ሚጥል ሴራ፡፡

ክበሪልኝማ ፦
ራስ ደጀንሽ ላይ
ከፍፍፍፍ ወደ ማማ
ልክሽ ዛግዌ ናት
አክሱም ላሊበላ
ልዩ ነሽ እማማ፡፡

እመኝኝ እናቴ ፦
ሰው ይሞታል እንጅ
የአንች አይቀርም ቃልሽ
ያለውን አይረሳም
በጨነቀሽ ጊዜ
ዘርጊልኝ የሚልሽ፡፡

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ሕዳር 14 /2012 ዓ.ም...ሌሊት በአስራ አንድ ሰዓት ተፃፈ

ነጋችን ከዛሬ የተሻለ ነው፡፡

@getem
@getem
1
፨፨፨፨፨፨
የጥላቻሽ ሚስጥር


በክፋት በቅናት ብቃይ የተሞላው


የጥላቻሽ ስሜት፣ ብዙ ሚስጥር አለው።


ስልኬ ላይ አቃጭለሽ ፣ ደውለሽ ስጠሪኝ

ፍቅራችን
ይታደስ፣ ቶሎ 'ና' ስትይኝ

ያኔ የዛን ምሽት፣ የጠራሺኝ ለታ

ድረስልኝ ብትይ፣ ካለሁበት ቦታ

አይገቡ ገብቼ፣ ገንዘብ ተበድሬ

እሮጬ ብመጣ ለጥሪሽ በርሬ

ዙርያ'ዬን አስሼ፣
ካለሽበት ወንበር አይኖቼን ማተርኩኝ

ታድያ የዛን እለት
ከወንድ ልጅ እቅፍ ተቀምጠሽ አየሁኝ

ቢዘገይ ነው መስል
ፍቅራችን ይታደስ ቶሎ ና ማለትሽ

ለደቂቅ ለአፍታ
አስፈርቶሽ ነበር ብቻሽን መሆንሽ


ታድያ በዛ ቅስፈት

አይንሽ ሲንከራተት ከአይኖቼ አረፈ፣ በቅዢብር
ስሜትሽ ባይንሽ አስተዋልሺኝ

መምጣቴን ብታውቂም፣ ፊትሽን አዙረሽ
በአይኖችሽ ከዳሽኝ ..



.....ግና........
በእዝህ መሀል
በጠለቀው ጀንበር ነብስሽን ቃኘሁት

ካንቺነት አልፌ
ውስጥሽን አየሁት

የገፋሽወ ልቤ፣ ክፋትሽን እረስቶ ብርታትሽን
አውቀው

በንቀት ትብታቦ፣ ካነጠፍሺኝ ቦታ ልብሽን
አገኘው


ታድያ በእዝህ ስሜት ብዙ ነገር ቃኘሁ

በጥላቻሽ
መሀል አንቺም የማታውቂው መውደድሽን አየሁ።


thomas
@getem
@getem
@gebriel_19
ሙሾ

©በታመነ መንግስቴ ዘ_ብሄረ ኢትዮጵያ

እንባ እንባ ይለኛል
ዝም ብሎ መሞራት፤
ለአገር የተሰዋ
የሞተ "ሰው" መጥራት፡፡

ጥፋቷን በሚመኝ
በጨካኝ ጠላቷ
አገሬ ተቀብራ፣
የናቴን ጎጆ ቤት
በአፉ የሚነግድ
ሲያፈርሰው አሞራ፡፡
የት ሆኘ ላልቅሰው
እንዴትስ ልሞራ?


ታጭዶ ቢከመርም
በቄስ ቢሠፈርም
የተዝካሬ ስንዴ፤
ከአንድነት አርማ ላይ
ከኢትዮጵያ ማማ
ዝቅ አልልም ለአንዴ፡፡

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ህዳር ስምንት ቀን ፪ሺ፲፪ ዓ.ም

@getem
@getem