#የ‘ናቴን_ቤት_ኪራይ
:
:
አግባኝ አትበዪኝ ገና ከመውጣቴ
ስንት ዐመት ተምሬ ስራ ከማግኘቴ።
:
:
ሚጨበጥ ሳይኖረን እንደው የሚረባ
ምን ሰምተሽ ነው ፍቅሬ ከጆሮሽ ምን ገባ።
:
:
እውነቱማ ይህ ነው...
...አጥንትሽ ካጥንቴ ካለው ቁርኝትህ
አምላክ ሁኚ ካለሽ አንቺን የኔ ሴትህ
ማንም ባንደበቱ ያሻውን ቢያወራ
መሆኔ ማይቀር ነው ያንቺው አባወራ።
:
:
እናምልሽ ውዴ ምማፀንሽ ቢኖር ...
...ምዬ በዚ ሰማይ
እሱ ከፃፈልን ስለማይቀር ደስታ...
...ስለማይቀር ሲሳይ
ስወድቅ ያነሱኝን ስዝል ያገዙኝን...
...ወገኖቼን እንዳይ
ባክሽን ታገሺኝ ባልጨርሰው እንኳ...
...እስክከፍል ድረስ የእናቴን ቤት ኪራይ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henokbirhanu
@getem
@getem
:
:
አግባኝ አትበዪኝ ገና ከመውጣቴ
ስንት ዐመት ተምሬ ስራ ከማግኘቴ።
:
:
ሚጨበጥ ሳይኖረን እንደው የሚረባ
ምን ሰምተሽ ነው ፍቅሬ ከጆሮሽ ምን ገባ።
:
:
እውነቱማ ይህ ነው...
...አጥንትሽ ካጥንቴ ካለው ቁርኝትህ
አምላክ ሁኚ ካለሽ አንቺን የኔ ሴትህ
ማንም ባንደበቱ ያሻውን ቢያወራ
መሆኔ ማይቀር ነው ያንቺው አባወራ።
:
:
እናምልሽ ውዴ ምማፀንሽ ቢኖር ...
...ምዬ በዚ ሰማይ
እሱ ከፃፈልን ስለማይቀር ደስታ...
...ስለማይቀር ሲሳይ
ስወድቅ ያነሱኝን ስዝል ያገዙኝን...
...ወገኖቼን እንዳይ
ባክሽን ታገሺኝ ባልጨርሰው እንኳ...
...እስክከፍል ድረስ የእናቴን ቤት ኪራይ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henokbirhanu
@getem
@getem
👍1
#የ 4 ኪሎ ተጓዥ!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
ተስፈኛ ወያላ ፥ የሹፌር ረዳት
ታክሲ ተደግፎ ፥
እንድረስ እያለ ፥ አራት ኪሎን ጠራት።
"አራት ኪሎ የሞላ !
አንድ ሰው የቀረው ...
አራት ኪሎ ሊሄድ ፥ ልቡ የከጀለው
አራት ...አራት ኪሎ
ከቤተመንግስቱ ከፓርላማው ሰፈር
ጠጋ ጠጋ ብለን በአጀብ እንብረር"
በሚል ጥዑም ዜማ በስልተኛ ቃላት
አራት ኪሎ ባሉ ተስፈኛ ፊደላት
ታክሲ ተደግፎ
በፅኑ ለፍፎ
በጩኸት ይጣራል.. .
አራት ኪሎ ሊደርስ ልቦናው የመራው ተጓዥ ይሳፈራል ።
አንድ ሰው የሞላ !
አራት ...አራት ኪሎ
ሲሻው ከጆሊ ባር
ቆንጆ ሴት ከጅሎ
እንደው ለአፉ ደንብ ማክያቶ አዝዞ
ሲሻው ከመንገድ ዳር
የወሬ ሰሌዳ ጋዜጣውን ይዞ
መቀመጥ የሚሻ ...
ሲሻው ከድልት ሀውልት
ግርጌ አረፍ ብሎ ለታሪክ ሟሟሻ
መጣፍ የሚከትብ...
አንድ ሰው የሞላ !
አራት ኪሎ እንሂድ ከመንግስቱ ግድም።"
አንድ ሰው የሞላ !
አራት ... አራት ኪሎ ...
መንጋው ይሳፈራል ለመድረስ ተቻኩሎ ።
ደግሞም ወዲያ ያለው...
የ አራት ኪሎ ተጓዥ መብዛት ያስገረመው
ጥርሱን እየፋቀ ከጠርዝ ዳር ቆሞ
የቱ ይደርስ ይሆን? እያለ ያስባል ብቻውን ቆዝሞ
አንድ ሰው የሞላ !
አራት ...አራት ኪሎ
ወያላው ይጣራል...
በየፌርማታው ላይ
መንገዱ አታክቶት
መድረስ የቸገረው አንድ ሰው ይወርዳል ።
አራት...አራት ኪሎ
ይጣራል ወያላው!
...
ኸረ መንገድ ስጡኝ ?
እያለ ይለፍፋል ሹፌሩ በተራው.. .
።።።።።
ደግሞም ሌላ ተጓዥ...
ከችኩል በራሪው ... መንጋ ተነጥሎ
በቀስ ... ቀስ እርምጃ መንደሩን አካሎ
ወያላ ሳይጠራው ካልተሳፈርህ ብሎ
ሳይዋከብ ይደርሳል.. .
የጉዞውን ማብቂያ እድሉ ላይ ጥሎ ።
ደግሞም ወዲያ ያለው ...
ከዚህ ሁሉ መንጋ የትኛው ይደርሳል? ብሎ የጠየቀው
ከ አራት ጎማ ታክሲ ቀድሞ የደረሰ
እግረኛ አለ ሲሉት ተዐምር ያፈሰ
እንዴት ሆነ ሳይል ? ጥያቄ ቀጥሎ
ፈገግ ብሎ ያልፋል መፋቂያውን ጥሎ።
አንድ ሰው የሞላ...
@getem
@getem
@getem
(ሚካኤል አስጨናቂ)
ተስፈኛ ወያላ ፥ የሹፌር ረዳት
ታክሲ ተደግፎ ፥
እንድረስ እያለ ፥ አራት ኪሎን ጠራት።
"አራት ኪሎ የሞላ !
አንድ ሰው የቀረው ...
አራት ኪሎ ሊሄድ ፥ ልቡ የከጀለው
አራት ...አራት ኪሎ
ከቤተመንግስቱ ከፓርላማው ሰፈር
ጠጋ ጠጋ ብለን በአጀብ እንብረር"
በሚል ጥዑም ዜማ በስልተኛ ቃላት
አራት ኪሎ ባሉ ተስፈኛ ፊደላት
ታክሲ ተደግፎ
በፅኑ ለፍፎ
በጩኸት ይጣራል.. .
አራት ኪሎ ሊደርስ ልቦናው የመራው ተጓዥ ይሳፈራል ።
አንድ ሰው የሞላ !
አራት ...አራት ኪሎ
ሲሻው ከጆሊ ባር
ቆንጆ ሴት ከጅሎ
እንደው ለአፉ ደንብ ማክያቶ አዝዞ
ሲሻው ከመንገድ ዳር
የወሬ ሰሌዳ ጋዜጣውን ይዞ
መቀመጥ የሚሻ ...
ሲሻው ከድልት ሀውልት
ግርጌ አረፍ ብሎ ለታሪክ ሟሟሻ
መጣፍ የሚከትብ...
አንድ ሰው የሞላ !
አራት ኪሎ እንሂድ ከመንግስቱ ግድም።"
አንድ ሰው የሞላ !
አራት ... አራት ኪሎ ...
መንጋው ይሳፈራል ለመድረስ ተቻኩሎ ።
ደግሞም ወዲያ ያለው...
የ አራት ኪሎ ተጓዥ መብዛት ያስገረመው
ጥርሱን እየፋቀ ከጠርዝ ዳር ቆሞ
የቱ ይደርስ ይሆን? እያለ ያስባል ብቻውን ቆዝሞ
አንድ ሰው የሞላ !
አራት ...አራት ኪሎ
ወያላው ይጣራል...
በየፌርማታው ላይ
መንገዱ አታክቶት
መድረስ የቸገረው አንድ ሰው ይወርዳል ።
አራት...አራት ኪሎ
ይጣራል ወያላው!
...
ኸረ መንገድ ስጡኝ ?
እያለ ይለፍፋል ሹፌሩ በተራው.. .
።።።።።
ደግሞም ሌላ ተጓዥ...
ከችኩል በራሪው ... መንጋ ተነጥሎ
በቀስ ... ቀስ እርምጃ መንደሩን አካሎ
ወያላ ሳይጠራው ካልተሳፈርህ ብሎ
ሳይዋከብ ይደርሳል.. .
የጉዞውን ማብቂያ እድሉ ላይ ጥሎ ።
ደግሞም ወዲያ ያለው ...
ከዚህ ሁሉ መንጋ የትኛው ይደርሳል? ብሎ የጠየቀው
ከ አራት ጎማ ታክሲ ቀድሞ የደረሰ
እግረኛ አለ ሲሉት ተዐምር ያፈሰ
እንዴት ሆነ ሳይል ? ጥያቄ ቀጥሎ
ፈገግ ብሎ ያልፋል መፋቂያውን ጥሎ።
አንድ ሰው የሞላ...
@getem
@getem
@getem
👍1
#የ'ሚገጥም እና የማይገጥም;
▪︎
□
■
የሚገጥም:-
የውስጡን ስሜቶች የልብና አእምሮ
የሚያወጣቸውን የሚያወርዳቸውን ሃሣቦች ደምሮ
ስንኞች ይፈጥራል ብዕሩን
ገብሮ።
✨✨✨✨✨✨✨✨✨
የማይገጥም:-
የውስጡን ስሜቶች የልብና አእምሮ
በአንጀቱ ይዞ በሆዱ ፀውሮ
ጭንቀትን ያበዛል ሃሣቦችን ቋጥሮ።
✨✨✨✨✨✨✨
የሚገጥም:-
ከጠልሰም ማህደር እስከ ራሺያ ቺኮቭ
መፃህፍት መርምሮ አልያ ቆጥሮ ኮኮብ:
ቢፈልግ በትችት አልያ በውዳሴ
ነፃነት ያገኛል ግጥሙ ሆኖ ሙሴ!
የማይገጥም፧-
መጨነቅ መጠበብ ማሠቡ መች ቀርቶ
በእጁ ይከፍትና ጥበብ ማዕድ ከ'ቶ
የልቡን ባይፅፍም መች አርፎ ዝም ይላል
•ይሄን የኔን ግጥም ተክዞ ያነባል።
○
●
٭
ዳዊት ጥዑማይ
ለ ፓሲካ
፲፩\፰\12
@getem
@getem
@yetbebmaed
ምስለ kingdome of ህንደኬ እስመ:ዳዊት :ይቤ........... :ልበ ሰብዕ
ወቅብዕ...........
▪︎
□
■
የሚገጥም:-
የውስጡን ስሜቶች የልብና አእምሮ
የሚያወጣቸውን የሚያወርዳቸውን ሃሣቦች ደምሮ
ስንኞች ይፈጥራል ብዕሩን
ገብሮ።
✨✨✨✨✨✨✨✨✨
የማይገጥም:-
የውስጡን ስሜቶች የልብና አእምሮ
በአንጀቱ ይዞ በሆዱ ፀውሮ
ጭንቀትን ያበዛል ሃሣቦችን ቋጥሮ።
✨✨✨✨✨✨✨
የሚገጥም:-
ከጠልሰም ማህደር እስከ ራሺያ ቺኮቭ
መፃህፍት መርምሮ አልያ ቆጥሮ ኮኮብ:
ቢፈልግ በትችት አልያ በውዳሴ
ነፃነት ያገኛል ግጥሙ ሆኖ ሙሴ!
የማይገጥም፧-
መጨነቅ መጠበብ ማሠቡ መች ቀርቶ
በእጁ ይከፍትና ጥበብ ማዕድ ከ'ቶ
የልቡን ባይፅፍም መች አርፎ ዝም ይላል
•ይሄን የኔን ግጥም ተክዞ ያነባል።
○
●
٭
ዳዊት ጥዑማይ
ለ ፓሲካ
፲፩\፰\12
@getem
@getem
@yetbebmaed
ምስለ kingdome of ህንደኬ እስመ:ዳዊት :ይቤ........... :ልበ ሰብዕ
ወቅብዕ...........
#የ_ሀያ_አራት_ልጆች
የኔ አድርገው ብለሽ ~ የሷ እድርገኝ ብዬ
ለማርያም ተስለሽ ~ ለጊዮርጊስ ተስዬ
በጉዞ በርትተሽ ~ በሀሳብ ደክሜ
አግብተሽ ስትመጪ ~ ስለት ተሸክሜ
መሐል ተገናኝተን
ሻይ ቡና ጠጥተን
ለመገናኛችን ~ ትንሽ ቢቀረንም
ሀያ ሁለት ማደሩ ~ ውዴ አልቀረልንም
===||===
@getem
@getem
@getem
ከሙሉቀን ሰ•
የኔ አድርገው ብለሽ ~ የሷ እድርገኝ ብዬ
ለማርያም ተስለሽ ~ ለጊዮርጊስ ተስዬ
በጉዞ በርትተሽ ~ በሀሳብ ደክሜ
አግብተሽ ስትመጪ ~ ስለት ተሸክሜ
መሐል ተገናኝተን
ሻይ ቡና ጠጥተን
ለመገናኛችን ~ ትንሽ ቢቀረንም
ሀያ ሁለት ማደሩ ~ ውዴ አልቀረልንም
===||===
@getem
@getem
@getem
ከሙሉቀን ሰ•