ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
****ፀሎት****


ጠዋት ቁርሴን በላሁ
ምንም አልጠገብኩም
ከዛ ምሳ በላሁ
ምንም አልጠገብኩም
ቀጥሎም እራቴን
ምንም አልጠገብኩም
ለካስ ትዝ ሲለኝ
ከመብላቴ በፊት በስመ አብ አላልኩም።።

በስመአም
ቢስሚላ
((አስታዎሰኝ እረጋሳ))


@getem
@getem
@getem
👍2
🇪🇹🇪🇹🇪🇹አምስተኛው የብርሃን ዕለት የመጀመሪያው ማክሠኞ ነው። ይምጡና አብዝተው ያትርፉ እንድቅትዮን ዕንቁላል ፋብሪካ በሚገኘው #ገነት_መናፈሻ ሠኔ 4/2011

እማይቀርበት!


@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
#ቅዳሜ- ገበያ-ይሸጣል-ሸንኳራ፤
#ይመጣብኝ-ጀመር፤
#በሽታ-ሚያሽረው-ጥርስና-ከንፈሯ።

#የወሎ-ገበሬ-ሽርጥ-አገልድሞ-ይሄዳል-ወለጋ፤
#አለም-አይደለም-ወይ-ደርሶ-ሲገጣጠም-ቅዳሜና-ሸጋ።

ሃበከው!!!!

((( ጃኖ በፎክሎርኛ ))💚💛

ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ !!💚💛

@balmbaras
@getem
@getem
።።። ታማሚ ሀኪም መድኃኒት።።።


በሽታ ያጠቃው የታወከ ስጋ
ከህመሙ እንዲድን ተንፏቆ ይሄዳል መድኃኒት ፍለጋ
መዳንን የሚሻ ሀኪም ዘንድ ይቀርባል ከመድኃኒት ቀድሞ
ሀኪም ባዘዘለት መድኃኒት መስራት ይድናል ታክሞ
ለፈውስ ነው ብሎ ያገኘውን ሁሉ ከመሰልቀጥ ይፁም
ባኪም ያልታዘዘ መድኃኒት የዋጠ አይድንም በፍፁም
በሽተኛ ትውልድ
ሀኪም ባዘዘልህ በሽታህ ቢሆን ሰድል
መድኃኒቱን ስትይዝ ሃኪሙን አትበድል
ብታውቅማ ኖሮ
ከመድኃኒት ይልቅ ሀኪም ነው ትልቁ
ለያዘህ በሽታ መድኃኒት ማወቁ
ብታወቅ ኖሮ
ከመድኃኒት በፊት ሀኪሙ ነው ውዱ
ፈውስ እንዲሆንህ መድኃኒት አምጦ መዳኒት መውለዱ
መዳኒት ልጅዋ ነው ሀኪሟም እማምላክ
መዳንን ከፈለክ ሁልጊዜም ወደሷ በሽቶችህን ላክ


አስታውሰኝ እረጋሳ
ከተስፋ የግጥም መድብል


@getem
@getem
@getem
👍2
* አጎቱን አልገልም *
-- @Johny_Debx -- ገጣሚ

የምር ገዳይ ብትሆን እንኳ
አስር 'ቀላ ... አትያዝ ፤
በውሸት ዐለም ላይ
መውደድ አደል' ... መዘዝ ?

ግና ... ለአላሚ ?
አንድ ይበቃ ነበር
ለመግደል ተኩሶ ፤
መቼስ ማገር ታስሮ
ወድቆ የለ' ምሶሶ ፤

ብቻ ማለም' ነው !
ካናቱስ ህልሙን ፤
ሲገባ ኢላማ'
የሳትክ ተዋልደን ፤

እነሱማ ቢሉህ ~
ዘርህን ገድሏል ... ?
ዘሩን አግብተህ ፤
የልጅህን አጎት
ሳትገለው ቀረህ ፤
***********

@getem
@getem
@getem
👍1
ተማጥኖ ለገመድ
(ልዑል ሀይሌ)

እንፈራገጣለሁ
ያሰረኝን ገመድ ታግዬ ለመፍታት፤
የማሠሪያ ዕጣ ነው
በነፃነቱ ልክ
እስረኛዋን ነፍሴን ነፃ የሚያወጣት፤
.
ነፃ ውጣ ገመዱ!
አትገደብ በኔ በገላዬ ልኬት፤
የኔ ስቃይ አይሁን
ያንተ ጥጋት ስኬት፤.
.
የውልህ ገመዴ!...
ኑሮን እወቅበት ክንድህን አበርታ፤
ስንት ልብስ መሰለህ
ታጥቦ ሚጠብቀው ከላይህ ሊሰጣ፤
ስንት ስጋ አለልህ
ቋንጣነትን ብሎ አንተን የሚማጠን፤
ሂድ መከታ ሁነው
እስራቴን ለቅቀህ
ጀግን በፍጥረትህ በመክሊትህ መጠን፤
.
የውልህ ገመዴ!...
አትያዘኝ ጨምድደህ አትፍቀድ እስራት፤
አሳሪውን ትተህ
ውስጥህን አድምጠው ፍርቱናህን ኑራት፤
.
ገመድ ሆይ ልቀቀኝ!!
አታብዛው ጭንቀቴን ነፃ ሁን ተፈታ፤
አንተም እስረኛ ነህ
ዕድሜህን ከፈጀህ
ለአሳሪው ትዕዛዝ ገላህ ከተረታ፤
ነፃ ሁን ገመዴ!!.


@getem
@getem
@gebriel_19
…ተመስገን…
[አብርሃም ሙሉ]

አረ አለን ተመስገን፤
ተመስገንን አመስግነን፤
ምንስ እንሆናለን!!

ተመስገን ባይኖርማ፤
አይናችን አያይም፤ ጆሯችን አይሰማ
ክፉ ሰማን፤ "ምስጋና"
ጥሩ አየን፤ "ምስጋና"
ባይደላንም፤ ችጋር ኑሮ
ተመስገናችን ይኑር ከብሮ
ይመስገን ተመስገን
ስናንስ #ያስበለጠን
ስንበልጥ ያሳነሰን።

አረ አለን ተመስገን።

▪️ሰው መሆን ከባድ ነው!!
[አብርሃም ሙሉ]
፩-፲-፳፻፲፩
@getem
@getem
@getem
ጀንበሩን ተግኖ ፣
ባቲ ከተማው ላይ ፣
ልቡን ልቡን የሚል ፣ ጩኸቱ በርክቷል ፣
ያቺው ጉድ ጀሚላ ፣ ሰው ገላ ይሆናል ።

((( መሀመድ ሙፍቲ )))

እኔ ግን ይቺ የኛዋን ጀሚላ ሳያት አንድ የአብዲ ሰኢድ ግጥም ነው ግጥም😁 የሚልብኝ...እንደውም ይቺኛዋን ጀሚላ አይቶ ሳይሆን አይቀርም የገጠመው ያሰኘኛል.....በሉ ወደ ግጥሙ ላንደርድራቹ.....



ጀ – ሚ – ላ !


የዓይንን አሰራር ጥበብ ያላወቀ፣
የጥርስን ተፈጥሮ ልክ ያላደነቀ፣
የቁመናን ልኬት ሚዛን ያልጠበቀ፣
ጀሚላን ቢያገኛት አወቀም ፀደቀ።


ቁም ነገር ወዴት ነው በማን ተወሰነ?
መልካምነት የታል እንዴት ተከወነ?
እውቀትስ ምንድን ነው የት ተተነተነ?
ከጀሚላ ወዲያስ ይህ ሁሉ ባከነ።


አልሐምዱሊላሂ ደርሶናል በረካ
በጀሚላ ፍቅር ቀልባችን ተነካ።


የቀሚሷ ፀዳል፣ የሂጃቧ ግርማ
የእርምጃዋ ስክነት፣ የገጿ ከራማ
የአንደበቷ ለዛ፣ የቃሏ ጥፍጥና
ማር ተምር ቢሏትስ መች ይበቃትና።


በዚህ ቁንጅና ላይ የአምላክ ፍራቻ
ተጣጥባ ተጣጥና ወደ መስጅድ ብቻ
ባያት አልሰለቻት አይነቀል ዓይኔ
የፍቅር ዓለም ሱሴ የነፍስ ኹረልዓይኔ።


አልሐምዱሊላሂ ደርሶናል በረካ
በጀሚላ ፍቅር ልባችን ተነካ።


እይዋት ስትመጣ . . .


ሽውው አለ ነፋሱ ሞገዱም ረገበ፣
ቀሚሷም ለአመል ያው ተርገበገበ፣
(ሸርተት አለ ሻሿ መልሰችው በእጇ
አምባሯን አየሁት ሲገለጥ ግዳጇ)
አትሞቅም አትበርድም ፀሐይዋም ልከኛ፣
ዛፎች ቅጠሎቹ ሆነዋት ምርኮኛ።


አበባውም ፈካ፣ ችግኙም ፀደቀ፣
ያገር ሽማግሌው በስሟ አስታረቀ፣
እናቶች ለክብሯ አወጡላት ዜማ፣
የጓዳ እድርተኛው ለቅሶውን ተቀማ።


ጀሚላ መኣረይ፣ ጀሚላ በሬዱ
ጀሚል ሸኮሪና፣ ጀሚል የውዱዱ
ጀሙ ጀሚላዬ፣ የሰው መጨረሻ
በፍቅር የሰራሽ፣ የውብ መዳረሻ።


አልሐምዱሊላሂ ደርሶናል በረካ
በጀሚላ ፍቅር ልባችን ተነካ።


እዪዋት ብቅ ስትል


’ሚያላዝነው ውሻ ብሶቱን አቆመ
ጭራውን ቆላና ፊቷ ተጋደመ።
ድመት ተንጠራራች ስስ እግሯ ረዘመ
‘አጃኢበ ረቢ’ ፍጥረት ተደመመ።


እርግቦች በዜማ እርግብኛ አወሩ
ጎጆአቸውን ረስተው በሽቶ ሰከሩ
ደነሱ ዘመሩ፣
ጨፈሩ ፎከሩ፣
ክንፋቸው ተማታ፣ ወደ ላይ በረሩ
”ምን አይነት ውበት ነው?!”
”ምን አይነት ሽታ ነው?!” እያሉ እያወሩ።


ጀሚላ መኣረይ፣ ጀሚላ በሬዱ
ጀሚል ሸኮሪና፣ ጀሚል የውዱዱ
ጀሙ ጀሚላዬ፣ የሰው መጨረሻ
በፍቅር የሰራሽ፣ የውብ መዳረሻ።


አልሐምዱሊላሂ ደርሶናል በረካ
በጀሚላ ፍቅር ስስ ልባችን ተነካ።


ምነው ባደረገኘ ቁርአን ማስቀመጫ
በስስ እጇ ዳብሳኝ ባገኝ መተጫጫ
ኧረ ምነው በሆንኩ ምንጣፍ ወይ ስጋጃ
ግንባሯ እንዲነካኝ ስታስገባ ምልጃ።


እንደመታጠቢያሽ እንደ ውዱእ ውኃ
ልቤ ፈሰሰልሽ በፍቅርሽ በረሃ
እስቲ በይ ቁጠሪኝ ልክ እንደ ሙስበሃ
በሚፈትለኝ ጣትሽ እንዳገኝ ፍሠሐ።


ጀሙ ጀሚላዬ፣ የሰው መጨረሻ
በፍቅር የሰራሽ፣ የውብ መዳረሻ።
ስለፍቅር ብለሽ፣ በአላህ በነቢ
የኒካውን ቀልቤን፣ ከቀልብሽ አስገቢ፤
አቤት ያንቺስ ውበት …
አቤት ያንቺስ ፍቅር …
. . . አ
. . . . . . ጃ
. . . . . . . . . ኢ
. . . . . . . . . . . . በ
. . . . . . . . . . . . . . . ረቢ።


/አብዲ ሰዒድ/
ተፃፈ 2005 E.C

እንደ ጀሚላ ያማረ ቀን ተመኘው!!!💚💛

@getem
@getem
@balmbaras
1👍1
#ከጥበብ በላይ !!

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።።።።።።።።።።።

አጃኢብ ያረቢ!

አጃኢብ ያ ጎፍታ !

መገን ያንቺ ውበት

መገን ያንቺ ዝና...

የገላሽ ፍምነት ፥ የቁንጅናሽ ፋና

ደግሞ ተለኮሰ!

ጠዳል ብርሀንሽ ፥ ባገር ተዳረሰ።

ይኸው መጣን ደግሞ!

ጠበብት ተሰብስበን 

ብዕር ተሸክመን...

ቀለማት በጥብጠን..

አንደኛው ሊፅፍሽ

ሌላኛው ሊስልሽ

ውበት ቃኙ ብለን ፥ ልናውጅ ለ'ዓለሙ

ነጋሪት ልንጎስም ፥ ስላንቺ ላልሰሙ።

እንችል ይመስል.. .

በብራና ጥራዝ ፥ በቅርፆች ማህደር

ስላንቺ መናገር!

እንችል ይመስል.. .

በሸራ ላይ ስዕል ፥ በሙዚቃ ቃና

መንገር ያንቺን ዝና!

እንዲያው ለሙከራ

እንዲያው ስለደንቡ

እንያዝ ብለን ወጉን

የገጣሚ ልኩን...

ስንኝ ልንቋጥር ፥ ሆሄ ልናስመታ

እንገልፅሽ ይመስል ፥ በቃላት ጋጋታ

እንዲያው ለሙከራ

እንይ ብለን ወጉን

የአዝማሪ ልኩን...

ቀይ የወደደና ፥ እባብ የነደፈው

እያልን በዜማ ፥ ውበትሽን ልንገልፀው

እንዲያው ለሙከራ

እንዲያው ስለደንቡ

እንያዝ ብለን ወጉን 

የሰዓሊ ልኩን...

በውድር ሸራ ላይ ፥ ስለናታል ልንል

ገፅታሽ በቀለም ፥ ይገለፅ ይመስል

ይኸው መጣን ጠበብት!

ይኸው መጣን ሊቃን !

ሞልቶልን ባንገልፅሽ...

ሞከሩ ለመባል ፥ የፈጠረሽ ያብቃን ።

አሜን 🙏

@getem
@getem
@getem
በንፁህ ልቦና
ስለ ሰው መኖርን ከ'ግዜር ብታደልም
ለምን እንደው እንጃ
ሴትን ማፍቀር እንጂ ማባበል አልችልም፡፡

ስለዚህ ደህና ሁኝ
አልለማመጥም አትሂጂብኝ ብዬ
ኑሮውም ከብድኛል
ሸክም አልጨምርም አንቺን አባብዬ፡፡

(ልብ አልባው ገጣሚ)

@getem
@getem
@gebriel_19
#ይድረስ~ለእናቴ~ልጅ

ደምህ እና ደሜ
ከገነቱ ጠበል ከጊዮን ተቀድቶ
ስጋዬ እና ስጋህ
ከበረከት አፈር ከኤደን ተቦክቶ
ያውም በእግዜር ቃል
በተስፋዋ ምድር ሰው ሆኖ እነዳልኖረ
ያ ሁሉ ፍቅራችን
በትንሽ የዘር ክር ስለምን ታሰረ?
:
አንተ'ኮ ክብሬ ነህ
የመጎሴ ሚስጥር ህመሜን ታማሚ
እኔ'ኮ ደስታህ ነኝ
ከባድ ሀዘንህን ቀሎኝ ተሸካሚ፡፡

ያ'ንተ ዘር የኔ ዘር
ትሁፊቴ ትሁፍትህ ባህልህ ባህሌ
ዘመናት ስንኖር
ሳቄ ሳቅህ ነበር በደልህ በደሌ፡፡

ግሸን ስታስቀድስ
ለዱኒያ ዱአ ነጃሽ ካድሜአለሁ
እዛ'ና እዚህ ሆነን
በቁልቢ ስትምል በፂሆን ምያለሁ፡፡

ባ'ክሱም ስመፃደቅ
በ'ላሊበላ አለት ኩራት ተሰምቶሀል
በጀጎል ሳቅራራ
በፋሲለደስ ጌጥ አምረህ ሸልለሀል፡፡

ታዲያ ምነው ዛሬ
ዘመን ባጎደፈው በማይድን ነቀርሳ
በዘር አቅላሚዎች
አንድነትን ጠልተን ተለየን በጎሳ?
:
እባክህ ወንድሜ
ለባለቀን ብለህ ከፍቶህ አታስከፋኝ
አንተ ነህ ደስታዬ
ሲረግጡን ተረግጠህ ሲገፉን አትግፋኝ፡፡

ባይሆን ከረገጠን
ከገፋን ባለቀን ደም እየጨለጠ ከሰከረ ነፍሱ
በአንድነት ጠበል
ተጠምቀን እንዳን
ለለከፈን ሴጣን ፋቅራችን ነው ምሱ፡፡

[ልብ አልባው ገጣሚ]

@GETEM
@GETEM
@GEBRIEL_19
1
የጨለማ ጥግ (ልዑል ሀይሌ)
ተስፋ አትስጪኝ ንጋቴ
መጨለም መምሸቱ ካልቀረ
ውሰጂው የነገ ጥጋቴን
በልብሽ መደብ ያደረ
ዘመናት ባደረ ተስፋ
እንድቋደስሽም አልሻ
አንቅሬ ተፋሁሽ ንጋቴ
ዳግም ሄድኩኝ በጨለማ
ዳግመኛ ታመምኩ በግርሻ
..
ይመስገነው!
ካንቺ አርቆ ከጨለማ ላዛመደኝ
ይመስገነው!
ካንቺ ሽሽት ወደ ወህኒ ላወረደኝ
ላመስግነው ተንበርክኬ
ለዚህ ላበቃኝ ፈጣሪ
ጨለማውን ባይፈጥርልኝ
ምን ይሆን ነበር እጣዬ
ንጋቴ ክደሺኝ ስትቀሪ

@getem
@getem
@gebriel_19
አፈር
.
ፈጣሪ
ከመሬት ላይ ዘግኖ መክበሪያን ፈጠረ
ህያው ያሏትን ነፍስ ከውስጧ ቀበረ
ወርቁን ውስጡን ቀብሮ ሰሙን አከበረ
የትዬለሌዋን ህያው ያሏትን ነፍስ በአፈር አሰረ።

በውሀ ተላውሶ
በእሳት ተጠብሶ
በእስትንፋስ ተናፍሶ
አፈር ስጋ ሆነ
ነፍስን ተዋህዶ
ሰውም ተከሸነ

በእጅ ላይ ሲሆን አሞሌው ይቀላል
የሰው ልጅ ላመሉ አፈርን ይረግማል
ሰውንም ሲያቀሉት አፈር ነህ ይባላል
ነፍስ ስትለየው ሰው አፈር ይሆናል
ግን ከዘመናት በፊት በእግዜር እስትንፋስ አፈር ሰውን ሆኗል።
*
ሞሲሳ ደምሴ

@getem
@getem
@gebriel_19
ለአባቴ
(ቡሩክ ካሳሁን)

ከጥንት ጀምሮ ከወንድ የዘር ግንዱ
ሀያላን ነበሩ ተራራ ’ሚንዱ
ጠቢቦች ነበሩ ጥበብ የሚወዱ
ምን ያደርጋል ታዲያ
አንተን የሚመስሉ መቼ ተወለዱ?
ባልሆን ሙታን ቀስቃሽ
ወደኋላ ገስጋሽ በእውነት ታሪክ ጋሪ
ባልሆን እንኳን ነቢይ ትንቢት ተናጋሪ
በቁንፅሏ እድሜዬ የተገለጠልኝ ያወቅኩት ሀቂቃ
ለራሴ ብነግረው
ምንም ’ማይሰለቸኝ ብደጋግመውም በየሩብ ደቂቃ
አንዳ’ንተ አይነቱ የተመረጠ አባት ህሩየ ህሩያን
ካንተ ኋላ የለ ወደፊት አይመጣ ልክ እንደ ሰለሞን*።

* ጠቢቡ ሰለሞን ከሱ በፊትም ሆነ ከሱ በኋላ እንደሱ ያለ ጠቢብ "እንደሌለ"፤ "እንደማይኖርም"!!!

👇
@burukassahunc


@getem
@getem
@getem
እንዳሉት ከሆነ
ካዲሳባ ውጪ ክፍለ ሀገር ጠፍቶ
ከቀናት በኀላ
ኔቱም ተመለሰ ሲያሽቃብጥ ሰንብቶ፡፡

የፈተና ሌቦች
አውቀው ተመራምረው ሀገር ላይለውጡ
ነገ ብዕር ጥለው
ካንፓስ እንደገቡ ዲንጋይ ሊጨብጡ
ከወዳጅ ሊያርቁን
ከቴሌ ጋር ሆነው ቆዩን ሲያሽቃብጡ፡፡

ይሁና


@getem
@getem
@getem
#አላምንም!
እስኪ ተጠየቁ...!
-
የዝንጀሮ መልኳ አስቀያሚ እንደሆን
በልሳን ብ'ነግራት ትደነግጥ ይሆን?
-
ስናወራ ሰምታ - ወፍ እንደምታምር
ፉጨቷን አቋርጣ - ትለን ይሆን "ከምር??"
-
እህሳ?!.....
ታድያ የት ተለከፍን? ምን ነክቶን ነው እኛ?
ስለ አቋም መልካችን ...
እንዴት ባለው ልኬት - ሆንን እርግጠኛ??
.
የቱ ቡዳ በላን?
ምን ቀን ሰፈረብን? ተያዝን በመንፈስ
ለምን ተጠመድን?
ስለራስ በማዜም - ስለራስ በማልቀስ።
.
ቢያማልል ....
ቢያባብል...
ማር ቢሆን ቢጣፍጥ - ነገር በምሳሌ
ባለማመን የማምን -
ተጠራጣሪ ነኝ - እኔ በበኩሌ።
-
-
"ሔዋን እንደዚ ነች!"
"አዳም እንደዚ ነው!"
የሚል ጥቅስ ቢናኝ - አየሩን ቢሞላ
ማንንም አላምንም - ከእንግዲህ በኋላ!!
.
በቃ አላምንም ከቶ፣
ግርምቱን - ትዝብቱን ሳይጨምር - ሳያስቀር
"ሰው እንዲህ ነው!" ብሎ -
ሰው ያልሆነ ፍጥረት - ካልነገረኝ በቀር።
============//==========


(በርናባስ ከበደ)

@getem
@getem
@getem