ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ዘረኝነት ራሱ ግብረ-ሰዶምነት ነው!!
የራሱን አይነት ብቻ የሚያስከጅል። ሁለቱም ጥንቦች ናቸውና አንፈልጋቸውም!!"
----
ደግ ደጉን
((ጀማል አማን ዘወሎ ))

@getem
@getem
@balmbaras
…አጊንቶ ላጣ ሰው…
(አብርሃም የሙሉ ልጅ)

ማን ያውቃል፤ የማንን ስቃይ
ሁሉም እንደ ሁሉ፤ የ'ራሱን ነው የሚያይ
የተራበ የተጠማ፤ ያልለበሰ ያልተጫማ
አይኑ የማያለቅስ፤ ልቡ ግን የደማ
አለ በየ-ቦታው፤ በየስራ-ስሩ
ጉድፍ ነው አካሉ፤ የለምና ክብሩ
የወጪ ወራጁ፤ ፊት እየገረፈው
የቃላት ግልምጫ፤ ትራፊ ሳይቀፈው
የተደፋ ሲጠጣ፤ የተተፋ ሲበላ
አይምሮው ይጋጫል፤ ሲያስብ ወደ ኋላ
"ምን ነበርኩኝ" ይላል፤ የሆነውን አይቶ
ትዝታን ይበላል፤ ትዝታ ጠጥቶ
ነበርኝ ይለብሳል፤ ነበረኝ ይጫማል
ከነበር ሲባንን፤ ተርቦ ተራቁቷል።

ይሂን ሳነበንብ፤
ይሂን ሳነበንብ፤
የአንድ ሰው ታሪክ፤ የመሰለው አለ
አንድ ሰው ግን አለ፤ ብዙ የወከለ
በዶፈ 'ልብ እንባ፤ እንዲህ የሚጠይቅ
አይንን የሚያሳቅቅ፤ ጆሮ ሚሰቀስቅ…

<ሰው…ይቆስላል እንጂ፤ ቁስልን ይሆናል?
ሰው…ይራባል እንጂ፤ እርሃብን ይሆናል?
ሰው…ይራቆት እንጂ፤ መራቆት ይሆናል?>
ባላበደ አይምሮ፤ የእብድ ጥያቄ
ሀኪም ማያክመው፤ የልብ ኑፋቄ
በየ-ቤተክርስቲያን፤ በየ-መስጂዱ ጥግ
አለ ያላበደ፤ ማበድ የሚፈልግ።
ስንቱ 'አምሮ ለባሽ'፤ ብጫቂ 'ሚያለብሰው
ስንቱ 'ጠግቦ በላ'፤ ትራፊ 'ሚያጎርሰው
በድሮ አለሙ ላይ፤ የነበረው ነበር
ፊት ነስተው ሲሰጡት፤ ቅስሙ የሚሰበር
ምነው መገላመጥ፤ በሃሜት ማላማጥ
ባጣ ሰው ትከሻ፤ ኑሮን ማቆላመጥ
የሀገር ወግ ሆነ፤
ሰው በሰው መዳፍ ላይ፤ ከሰይጣን ጨከነ

"አረ ሰው እንጠይቅ፤ ለሌለው እንርዳ
ዘግቶ አለፎች ሆንን፤ ዘመድ መስለን ባዳ
እስኪ እንጠያየቅ፤
እንዴት እንሆናለን፤ ላጣ ሰው እንግዳ!"

ብሎ ተናጋሪ፤ አስተዋይ ሲጠፋ
እንዴት አያስብልም፤ "ሰው ካውሬ ከፋ"
በድሎት አለም ላይ፤
ሁሉም እንደ ሁሉ፤ የ'ራሱን ነው የሚያይ!
ግን አንድ እውነታ አለ፤
ከፈጣሪ ፍርጃ፤ ሊሰወር ያልቻለ
ዛሬ ባጣ ስቀን፤
በንፉግ መልካችን፤ ጥርስ ብናረግፍ
ነገ አይበላንም፤ የጥጋባችን ግፍ!!።

👆አልቋል
<ባይኖረን ለሌው፤ ገንዘብ ባንሰጥም
የፊትን ፈገግታ፤ ለሰው ፊት አንነፍግም
ግልምጫ ክፉ ነው፤ ከሳት ያቃጥላል
ከሚያጠቁር ምላስ፤ ጦርነት ይሻላል!!>
፪-፱-፳፻፲፩
ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለት በራሱ መጥበብ ነው (ሰው ነኝ)

👉 @yemulu_lij

@getem
@getem
@getem
ART EXHIBITION

ሰዓሊ ዩናስ ሀይሉ
በ ኢታሊያን የባህል መአከል


ከ ግንቦት 29 እስከ ሰኔ 15 የሚቆይ
@seiloch
@seiloch
ኧረ ዘንበል በል!!!!


ኧረ ዘንበል ዘንበል ፤
ኧረ ውድቅ ውድቅ ፤ሆኗል የኛ ስራ ፤
ፈሪ እየቀደደው ፤
ቡከን እየጣለው ያገሬን ባንዲራ ።


የነ አብዲሳ አጋ ፤
የነ አሉላ ጥሪት ፤
የነ በላይ ጎፈር ፤ የብርዱ ማምለጫ ልብስና ማእረጌ፤
አለ ዘንበል ዘንበል ፤
ስድ አደግ ሲንቀው ሲረግጠው ባለጌ ።


እስቲ አንገቴ ውረድ ፤ወገቤ ተጎበጥ ፤
ካላበደ በቀር ፤
ማነው ጤነኛ ሰው፤
ያባቶቹን ርስት በዱርየ ዛቻ አሳልፎ ሚሰጥ??
የገብርየን ዳዊት ፤
የሸህ አሊን ኪታብ ፤
ሰነፍ በጠበንጃ ሁሌ እያረከሰው ፤
የሃቀኛን ጃኖ ሴረኛ በምላስ ነጥቆ እየለበሰው ፤
አይናችን እያየ ፤
ጀግና የሰራውን ሃገርና መንደር ጃሂል አፈረሰው ።


ኧረ አንገቴ ወዝወዝ ፤
በፊትም በዃላ ፤በቀኝም በግራ ፤
ዞር ብሎ መጠየቅ ፤
ዞር ብሎ ማየት ነው ጎጆ የሚቀልስ ሃገር ሚሰራ ።


አይኑን የጨፈነ ፤
የሩቅ መንገደኛ ፤እኔን ብቻ ስሙኝ ብሎ እየፎከረ ፤
ሆ ብሎ የወጣው፤
መንገደኛው ሁሉ መንገዱ እየጠፋው ገደል ገብቶ ቀረ ።


አሁንም ጭፍኖች፤
በአይናር ተጋርዳችሁ ተነስ ውጣ ዝመት እንሂድ አትበሉ ፤
ጭፍን የተለመው መውጫው አይገኝም ሩቅ ነው ገደሉ ።


አሉ ዘንበል ዘንበል፤
በጭፍን አይናቸው ተደገፉን ብለው ጠሩን እንደገና ፤
ማን ገደል ይገባል በጭፍን ተመርቶ እንዳምና ካቻምና ።


ተከተሉ አትበሉን ፤
መክት ፤
ወጥር ትከል ንቀል እያላችሁ በእሳት ከንፈራችሁ አትሞጣሞጡ ፤
ይልቅ አይናችሁን፤
ከሸፈነው ጭቃ ከዘረኝነት ድር ከግርዶው ግለጡ ።


ዘሎ እንደ ዱር አውሬ፤
ጉብ ብሎ መናደፍ ፤ የእንስስነት ኑሮ ፤
ግጠሙኝ እያሉ ፤
በባለጌ ምላስ በአውራ ጎዳና ላይ መባሸቅ ፎክሮ ፤
መች እኛስ መች ጠፋን ፤
ግደለው ፍለጠው የሚል የጅል ነገር ፤
እንዳንወርድ እንጅ ፤
ዝም ማለታችን ከጦቢያነት ዙፋን ከሰውነት መንበር ፤
እንዳይናድ እንጅ እንዳይበላላ ይኸ ትልቅ ሃገር ፤
ያለበለዚያማ ፤
አካኪ ዘራፉም ገድሎ ማሽቃረሩም በኛ ያምር ነበር ።


ተው በሉት ይህን ጅል ፤
ዋርካ አትቁረጥ በሉት ፤
ዘንበል ቅልስ ይበል ቀልብያው ይራጋ ፤
በዚች በኛ መንደር ፤
ልግደላችሁ ያለ መሬት ነው የቀረው አልወጣም ወዳልጋ ፤
ድርድም ድድድም ፤
ጎጋና ጋጋኖ ፤
ጎጆውን አፍርሶ ፤ አገርን ለማፍረስ ይዟል እሽቅድድም ፤
በባንዲራው ልማል፤
እኔ በሱ መንገድ በኮቴው አልሄድም!!"

((( ጃ ኖ )))💚💛

@balmbaras
@getem
@getem
ሀገር ማለትማ...

(ሚካኤል አስጨናቂ )

.

ሀገር ማለት ሰው ነው ብለሽ ያልሽኝ ዕለት

ሀገር ሰው አይደለም እያልኩሽ ስሟገት

ምክንያት ነበረኝ!

""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

ትዝ ይልሽ እንደሆን እንዲህ እልሽ ነበር ከመስኩ ዳር ሆነን

ተራራውን ወንዙን ሜዳውን እያየን..

.

ዓለሜ!

ሀገር ማለት እኮ ተራራ ማለት ነው

ከምድር ከፍ አርጎ ፈጣሪ ያነፀው

.

ከተራራው አናት ከላይ ተቀምጠሽ

ቁልቁል እንደምታይ መስኩን ዝቅ ብለሽ

ሀገርም ያለሽ ቀን ከፍታው ያንቺ ነው

ከማማው አናት ላይ በኩራት እንደቆምሽ

ዝቅ ብለሽ ማየት ነው!

"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

ሀገር ማለትማ!

ሀገር ማለትማ....

አዎን ተራራ ነው

ማንም እየካበ ማንም የሚያፈርሰው።

.

በቆመ ተራራ አናት የወጡ ለት

ከበላይ እንዳሉ የበታችን ማየት

አውቃለሁ ያኮራል..

እመኚኝ የኔ ውድ!

ሀገርም ያለሽ ቀን እንደዚህ ያደርጋል።

""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

የተናደስ ዕለት?...

የተናደስ ዕለት ተራራው ሲፈርስ?!

ከፍታሽ ያልፍና ይጀመራል ማነስ

ወርዶ መገኘት ነው ቁመት መለካካት

ትከሻን አስታኮ አቀብ መንጠራራት

.

አየሽው ዓለሜ?

አየሽው ዓለሜ? .... ሀገር ተራራ ነው

ማንም እየካበ ማንም የሚያፈርሰው

.

ሀገር ማለትማ ሲክቡት የሚካብ በኩራት የሚያደምቅ

ሲንዱት የሚናድ ተስፋሽን የሚያደቅ

ተራራ ማለት ነው!

እና ታዲያ ፍቅሬ...

ዕውን አንቺ እንዳልሽው ሀገር ማለት ሰው ነው?

.

አይደለም የኔ ውድ!

ሀገር ሰው አይደለም!

ሀገር ማለትማ ሜዳና መስኩ ነው

ፈጣሪ አንጣሎ ዘርግቶ የጣለው።

አዎን!

.

አዎን!

.

አዎን ሀገር ማለት ሳር ያቆጠቆጠ ለጥ ያለ ሜዳ ነው

የቤት ብቻ ሳይሆን የጫካም እንስሳ መቶ የሚግጠው።.

""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

ሀገር ማለትማ

ሀገር ማለትማ ሜዳና መስክ ነው

ከጫካ ውስጥ ወቶ በቤት እንስሳ ላይ አለቃ መሆን ነው።

.

እና ታዲያ ዓለሜ

ሀገር ማለት ሰው ነው?

እኔ ብቻ ልጋጥ የሚሉት አባባል

የሰው ባህሪይ ነው?

.

አይደለም የኔ ውድ

አይደለም ዓለሜ

እንደውም ልንገርሽ.. .

ሀገር ማለትማ

ሀገር ማለትማ ፏፏቴው ወንዙ ነው

አፈር ተሸክሞ የመጓዝን ዕጣ ፈጣሪ የቸረው

""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

ሀገር ማለትማ!

ሀገር ማለትማ..ጉቶ እየነደሉ ግንድ ይዞ መዞር ነው

ማደሪያ ዳስ አጥቶ ህልምን መናፈቅ ነው

.

ሀገር መቆለል ነው

ሀገር መደርመስ ነው

ሀገር በመስክ ላይ 

ቦርቆ መዝለል ነው

ግንድና አፈር ይዞ

ሲጓዙ እየዋሉ ሲጓዙ ማደር ነው።

.

እና አንቺ እንዳልሽ ሀገር ሰው አይደለም

ቀን እየተጓዙ ማታ በማሸለብ ሀገርነት የለም

.

እልሽ ነበር ያኔ ከመስኩ ዳር ሆነን

ተራራውን ወንዙን ሜዳውን እያየን። 


@getem
@getem
@getem
👍1
ለባዶ እግሮችህ ጉዞ
የምድር እሾህ ጋሬጣ ቢሆንብህም ፈተና
ጫማ ስላጣህ አትዘን
ወዳጄ ለመራመዱም እግር የሌለው አለና፡፡

((ልብ አልባው ገጣሚ))
@getem
@getem
@getem
#በኛ ~ኑሮ~ፍቺ

የልባችን ፎሌ
ከ'ፍቅር እንስራችን~የምንጨልፍበቱ
የ'ምነትን በረከት
ምንቋደስበት~ያ'ብሮነት ወጬቱ
እልፍ ዘመናትን
ከኔ'ና አንተ ጎጆ~ከታዛችን ጓዳ
እንደየ ችሮታው
መአዱ ቀርቦበት~ፅዋን እንዳልቀዳ
ጊዜ ባጠለሸው
ሰንኮፍ አራሙቻ~ሰርክ እየማቀቀ
ምነውሳ ዛሬ
ፎሌው ተሰባብሮ~ወጬቱ ደቀቀ?

ያ'ንተና የኔ እኮ
የምነት መቋደሻ~የፍቅር መጠጫ
የትንሽ ጎጆ'ችን
የቡራኬ መሶብ~የፅዋችን ዋንጫ
እንዲህ እንደዛሬው
በከንቱ ሽኩቻ~ደቆ ሳይሰበር
እራቤን አስታግሶ
ጥምህን ሚቆርጥ~ገመናችን ነበር፡፡

ታዲያ ለምን ይሆን
ማጀታችን ሞልቶ~ተርፎ ጥሪታችን
የፍቅርን ቀላስ
የእምነትን ትሪ~ጓዴ መስበራችን?

አላውቅም እኔንጃ!!

ብቻ ግን ሲገባኝ
መሰበር መድቀቁ
በጎጇችን ኑሮ~ለውጥ አያመጣም
ሲርበኝ መጉረሻ
ወጬት ታበጃለህ
እኔም ስትጠማ
አንተን ማጠጣበት~ሌላ ፎሌ አላጣም፡፡

(((ልብ አልባው ገጣሚ)))

@getem
@getem
@getem
ሰካራም ገጣሚ

ፎቶዬን ካየሽው
በሳቅ የታጀበ ፈገግታን አርግዟል
ልቤ ግን ሌላ ነው
ካንቺ ተለይቶ ባረቄ ደንዝዟል፡፡

የሚል አንድ ግጥም
ስንኞች አጣምረህ ጣቴን ፃፍ እንዳልኩት
የሰካራም ቅኔ
ሆድ የባው ነው ሲሉኝ መከተቤን ተውኩት፡፡

ሰካራም

((ልብ አልባው ገጣሚ))

@getem
@getem
@gebreil_19
ከማንነቴ ላይ
ነፍስያዬን ጭምር ያሻችሁን እንኩ
ግን እባካችሁን
ትፋጃለችና እንዳትቃጠሉ ሀገሬን አትንኩ፡፡

ለራሳችሁ ብዬ ነው፡፡

((ልብ አልባው ገጣሚ))

@getem
@getem
@getem
የነ ጃኖ መንደር ፤
ወሎ ማርዘነቡ ፤
አበጋሩ አጃኢብ በረካው ጎርፍ ነው ፤
ጨርቄን ልዘርጋና፤
ቱፍታ ምርቃኑን ፤ ሷህቡን ልቀበለው ።
ወንድም ሲመርቀኝ ይሁን አሁን ሲለኝ ፤
ጨርቄን ዘረጋሁኝ ቃሉ እንዲያበሽረኝ፤
ይሁን ያለኝ ጊዜ ፤
የያዘኝ በሽታ በቱፍታው ቀለለኝ ።
አሜን አሜን ልበል አሜን እወዳለሁ ፤
በዚህ በኛ ቀየ ፤
አሜን ያለ ሁላ ተጠቅሞ አይቻለሁ ።
አሜን ልበል ዛሬ ጠብቄ አሜን አሜን ፤
ይሁን ውሰድ አለ ሰማሁት ወንድሜን ፤
አሜን እያልኩ ነው ሃጃየ የወጣው ያየሁት አለሜን ።
አሜን አሜን አሜን

(( ጃ ኖ ))💚💛

ያማረ ጁምኣ ይሁንልን !!💚💛

@balmbaras
@getem
@getem
መለላ ሀሳቦች !

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።፡።።።።።።።።።።።።።

አንድ ዘመነኛ !

ጊዜ ያገነነው ፥ የወንበር ሹመኛ

እኛ ዜጋዎቹን...

በአፉ ቃል ቀድሶ ፥ ሸንግሎ ሊያስተኛ

አድገናል የሚለን ፥ የምናብ ተስፈኛ

በመስታወት መስኮት ፥ እያጨነቆረ

ውሉ 'ማይጨበጥ ...

ሆሄያት ሰድሮ ፥ ይናገር ነበረ።

.

እኔና አያቴ...

በዘመን ሰሌዳ ፥ ሁለት ዓለም ታከን

የባለ ጊዜውን ፥ ወጎች እንፈትላለን።

.

እኔ ለሱ 'ምለው.. .

ሸጋ ነው ዓመቱ 

ባለ በረከት ነው 

ቀኑና ወራቱ ...

ዘወትር ምሉዕ ነው ፥ ጓዳና ማጀቱ

ሰርክ ይታፈሳል ፥ እንጀራው ህብስቱ

ማመስገን ካለብን ፥ አሁን ነው ሰዓቱ!

.

እሱ ለኔ 'ሚለኝ

ዘለላ ቅጠሎች ፥ በግንድ ላይ ያሉ

ሥሮች በማሰኑት ፥ የተንሰላሰሉ

እኒያ አሸብራቂ!

ውበትን አድማቂ 

"የዛፍ ራስ አክሊሎች 

ተብረቅራቂ ዘውዶች"

ፈክተን ለምልመናል ፥ ተውበናል ቢሉም

የቆረቆዘ ግንድ...

ስንኩል ሥር ታቅፈው...

ሳይከስሙ ለመዝለቅ ፥ መንፈቅ አይሻገሩም።

@getem
@getem
@getem
# እውነትና ~ስሜት

ለራሴ ልብ አልባ
ቀልብ የሌለኝ ፍጡር ከንቱ ስደተኛ
ጊዜ ያሸነፈኝ
ሀኪም ያላገኘሁ ያ'ሳብ በሽተኛ፡፡

ታዲያ ለምን ተብሎ
የኔ መዘላበድ እናንተን ያናዳል
ጥሎባችሁ እንጂ
በልብ አልባ ምስኪን እንዴት ይፈረዳል?

ስለዚህ አንዳንዴ
ምቀበጣጥረው የማወራው ቃሉ
እውነት ስለማይሆን
ብዕሬን አንስቼ የምፅፈው ሁሉ
ከምትታዘቡኝ
ውስጤን ተረዱና ልብ አልባ ነው በሉ፡፡

እናም ትላንትና
ከእንግዲህ አልፅፍም
ኮመንትና ላይክ አታረጉም ብዬ ብቀበጣጥርም
እውነቴን አይደለም
እኔ በዚህ መንደር ካልፃፍኩኝ አልኖርም፡፡

ሁሌም እፅፋለሁ
በተቸረኝ መክሊት ግጥምን በርትቼ
እናንተም አንብቡ
ላይክ የለም ብዬ አልተውም ውዶቼ፡

@getem
@getem
@getem
…ሁላችንም…
[አብርሃም ሙሉ]

ሁላችንም ዘፋኝ፤ ሁላችን ዘማሪ
ሁላችንም ሌባ፤ ሁላችን መስካሪ
ሁላችንም አዳኝ፤ ሁላችን ታማሚ
ሁላችንም ደጋሽ፤ ሁላችን ታዳሚ

ሁላችን ባላገር፤ ሁላችን እንግዳ
ሁላችንም ዘመድ፤ ሁላችንም ባዳ
ሁላችን እንቅልፋም፤ ሁላችንም ንቁ
ሁላችንም ድንጋይ፤ ሁላችንም እንቁ

ሁላችንም ሳቂ፤ ሁላችን አኩራፊ
ሁላችን ዝመኞች፤ ሁላችን ለፍላፊ
ሁላችንም ተራ፤ ሁላችን ዝነኛ
ሁላችንም ደጎች፤ሁላችን ምቀኛ

ሁላችን ፀበኛ፤ ሁላችን ገላጋይ
ሁላችን የበታች፤ ሁላችን የበላይ
ሁላችንም ተጓዥ፤ ሁላችንም መጪ
ሁላችንም ቀሚ፤ ሁላችንም ሰጪ
ሁላችን ተቀጪ፤ ሁላችንም ቀጪ

ሁላችን ለሁላችን፤ ለሁላችን ሁላችን
ማኖራችን፤ መግደላችን፤ መሞታችን።

፲፱-፰-፳፻፲፩
▪️ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለት በራሱ ጠባብነት ነው (ሰው ነኝ)
@yemulu_lij


@getem
@getem
@getem
Forwarded from ᗞᝪᑎᎩ21̶ⓋⓈe ̶m ̶a ̶y ̶e
"…አምሳያ የሌላት ጥላ ነች ከለላ
በቃል ማትገለፅ: የሕይወት የፍቅር-ጥላ
ብልሃቷ ጠፍቶ ሃሳብ ተሸክማ
እንዳይሆኑ ሁና ከድካሟም ታማ
የመንትዮች እናት፥ ያልሆነችው የለም ልጄ ስትል እማ!!! …"

♦️ውድ የሩታ አርት ቤተሰቦች በእለተ እሮብ በፋና 90 ላይ የተመለከትኩት አሳዛኝ ነገር ላካፍላችሁ ነው። በድሮ ሰፈሬ የማውቃት እመቤት የምትባል የ3 መንትዮች እናት ስትሆን በጣም ጠንካራና ስራ ወዳጅ የነበረች ሴት ናት ።በመጀመሪያ የኩላሊት ኢንፌክሽን እንዳለባት ከሰማች ከአመታት በውሀላ፤ የኩላሊት ጠጠር ተገኝቶባት ኦፕሬሽን ተሰራላት በመሀል ደሞ ከስድስት አመት በውሀላ ኩላሊቶቿ ፌል አደረጉ የቤተሰቦችዋ አቅም እንደማይፈቅድ ስላወቀች አስቸኳይ ህክምና ማድረግ አልቻለችም ነበረ ህመሙዉዋም ከአቅሙዋ በላይ ሲሆንባት ለቤተሰቦቹዋ ተናግራ አስቸኩዋይ ዱያሌሲስ ጀመረች በዛን ጊዜ የሚረዳት ድርጅት ቢኖርም በአሁኑ ሰአት ግን የሚረዳት ድርጅት እርዳታውን ስላቆመ ሕይወቷ በአሁኑ ሰዐት በጣም ከብዱዋል በዋነኛነት ደግሞ የዲያሌያሲስ ህክምናዋን በገንዘብ እጥረት ልታቁዋርጥ ደርሳለች።
ይህች የሦስት መንትዮች እናት ኑሮዋ በጣም ከብዷል ለልጆጅዋም ተጨንቃለች። ፋና ቲቪም ድጋፉን አሳይቷል።

ኢትዮጵያዊነት ለመረዳዳት ነው ካልን ይሄንን ስዕል ለጫረታ አቅርቤዋለሁ ሙሉለሙሉ ገቢው ለሱዋ ስለሆነ ይሄንን ስዕል በመጫረት እናቲቱን እንድትረዱ በእግዚአብሔር ስም ጠይቃለው ።

መጫረት የምትፈልጉ እና ለበለጠ መረጃ
+251988103088

የእናትየው ስልክ +251916157712
bank account ንግድ ባንክ..1000038267403

@ruta_art16 Tg; IGg; fb;
#share
Forwarded from ᗞᝪᑎᎩ21̶ⓋⓈe ̶m ̶a ̶y ̶e
"…አምሳያ የሌላት ጥላ ነች ከለላ
በቃል ማትገለፅ: የሕይወት የፍቅር-ጥላ
ብልሃቷ ጠፍቶ ሃሳብ ተሸክማ
እንዳይሆኑ ሁና ከድካሟም ታማ
የመንትዮች እናት፥ ያልሆነችው የለም ልጄ ስትል እማ!!! …"

♦️ውድ የሩታ አርት ቤተሰቦች በእለተ እሮብ በፋና 90 ላይ የተመለከትኩት አሳዛኝ ነገር ላካፍላችሁ ነው። በድሮ ሰፈሬ የማውቃት እመቤት የምትባል የ3 መንትዮች እናት ስትሆን በጣም ጠንካራና ስራ ወዳጅ የነበረች ሴት ናት ።በመጀመሪያ የኩላሊት ኢንፌክሽን እንዳለባት ከሰማች ከአመታት በውሀላ፤ የኩላሊት ጠጠር ተገኝቶባት ኦፕሬሽን ተሰራላት በመሀል ደሞ ከስድስት አመት በውሀላ ኩላሊቶቿ ፌል አደረጉ የቤተሰቦችዋ አቅም እንደማይፈቅድ ስላወቀች አስቸኳይ ህክምና ማድረግ አልቻለችም ነበረ ህመሙዉዋም ከአቅሙዋ በላይ ሲሆንባት ለቤተሰቦቹዋ ተናግራ አስቸኩዋይ ዱያሌሲስ ጀመረች በዛን ጊዜ የሚረዳት ድርጅት ቢኖርም በአሁኑ ሰአት ግን የሚረዳት ድርጅት እርዳታውን ስላቆመ ሕይወቷ በአሁኑ ሰዐት በጣም ከብዱዋል በዋነኛነት ደግሞ የዲያሌያሲስ ህክምናዋን በገንዘብ እጥረት ልታቁዋርጥ ደርሳለች።
ይህች የሦስት መንትዮች እናት ኑሮዋ በጣም ከብዷል ለልጆጅዋም ተጨንቃለች። ፋና ቲቪም ድጋፉን አሳይቷል።

ኢትዮጵያዊነት ለመረዳዳት ነው ካልን ይሄንን ስዕል ለጫረታ አቅርቤዋለሁ ሙሉለሙሉ ገቢው ለሱዋ ስለሆነ ይሄንን ስዕል በመጫረት እናቲቱን እንድትረዱ በእግዚአብሔር ስም ጠይቃለው ።

መጫረት የምትፈልጉ እና ለበለጠ መረጃ
+251988103088

የእናትየው ስልክ +251916157712
bank account ንግድ ባንክ..1000038267403

@ruta_art16 Tg; IGg; fb;
#share
እምዬ ስላንቺ
በቀን አንድ ግጥም ሳልከትብ ከዋልኩኝ
ምኑን ባለቅኔ
ጎበዝ የብዕር ሰው ግጣሚ ተባልኩኝ?

አንቺኮ ጥበብ ነሽ
ያውም ሚስጥራዊ ያልተፈታሽ ቅኔ
እንዴት አይመርምርሽ
በየምክንያቱ ተገልጦ ድርሳኔ?

ስለዚህ ልንገርሽ
ሞት ቆርጦ እስኪጠራኝ በህይወት እስካለሁ
እመኚኝ ሀገሬ
ችዬ ባልገልፅሽም ስላንቺ ፅፋለሁ
ለምን ያልሽ እንደሆን
ምክንያት የለኝም በቃ ወድሻለሁ፡፡

ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር፡፡

መልካም ምሽት
((ልብ አልባው ገጣሚ))

@getem
@getem
@getem
#ቅኔአዊት ~ምርቃት

ከቤትህ ጣራ ስር
ኑሮን የሚፈትን ክፉ ቀን ሲመጣ
እውነት እልሀለው
ጠብሳ ምታበላ ቆንጆ ሚስት አትጣ፡፡

(ልብ አልባው ገጣሚ)

@getem
@getem
@getem