ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#አላምንም!
እስኪ ተጠየቁ...!
-
የዝንጀሮ መልኳ አስቀያሚ እንደሆን
በልሳን ብ'ነግራት ትደነግጥ ይሆን?
-
ስናወራ ሰምታ - ወፍ እንደምታምር
ፉጨቷን አቋርጣ - ትለን ይሆን "ከምር??"
-
እህሳ?!.....
ታድያ የት ተለከፍን? ምን ነክቶን ነው እኛ?
ስለ አቋም መልካችን ...
እንዴት ባለው ልኬት - ሆንን እርግጠኛ??
.
የቱ ቡዳ በላን?
ምን ቀን ሰፈረብን? ተያዝን በመንፈስ
ለምን ተጠመድን?
ስለራስ በማዜም - ስለራስ በማልቀስ።
.
ቢያማልል ....
ቢያባብል...
ማር ቢሆን ቢጣፍጥ - ነገር በምሳሌ
ባለማመን የማምን -
ተጠራጣሪ ነኝ - እኔ በበኩሌ።
-
-
"ሔዋን እንደዚ ነች!"
"አዳም እንደዚ ነው!"
የሚል ጥቅስ ቢናኝ - አየሩን ቢሞላ
ማንንም አላምንም - ከእንግዲህ በኋላ!!
.
በቃ አላምንም ከቶ፣
ግርምቱን - ትዝብቱን ሳይጨምር - ሳያስቀር
"ሰው እንዲህ ነው!" ብሎ -
ሰው ያልሆነ ፍጥረት - ካልነገረኝ በቀር።
============//==========


(በርናባስ ከበደ)

@getem
@getem
@getem
#አላምንም!
እስኪ ተጠየቁ...!
-
የዝንጀሮ መልኳ አስቀያሚ እንደሆን
በልሳን ብ'ነግራት ትደነግጥ ይሆን?
-
ስናወራ ሰምታ - ወፍ እንደምታምር
ፉጨቷን አቋርጣ - ትለን ይሆን "የምር??"
-
እህሳ?!.....
ታድያ የት ተለከፍን? ምን ነክቶን ነው እኛ?
ስለ አቋም መልካችን ...
እንዴት ባለው ልኬት - ሆንን እርግጠኛ??
.
የቱ ቡዳ በላን?
ምን ቀን ሰፈረብን? ተያዝን በመንፈስ
ለምን ተጠመድን?
ስለራስ በማዜም - ስለራስ በማልቀስ።
.
ቢያማልል ....
ቢያባብል...
ማር ቢሆን ቢጣፍጥ - ነገር በምሳሌ
ባለማመን የማምን -
ተጠራጣሪ ነኝ - እኔ በበኩሌ።
-
-
"ሔዋን እንደዚ ነች!"
"አዳም እንደዚ ነው!"
የሚል ጥቅስ ቢናኝ - አየሩን ቢሞላ
ማንንም አላምንም - ከእንግዲህ በኋላ!!
.
በቃ አላምንም ከቶ፣
ግርምቱን - ትዝብቱን ሳይጨምር - ሳያስቀር
"ሰው እንዲህ ነው!" ብሎ -
ሰው ያልሆነ ፍጥረት - ካልነገረኝ በቀር።
============//==========
(በርናባስ ከበደ)

@getem
@getem
@gebriel_19
👍31