#የወል #አለም
ባለቤት የሌለው
የተገነባ ልብ ቆመሽ ስትጠብቂ
አለምሽን ስሪ እንጂ
አለሜን አሳየኝ ብለሽ አትጠይቂ
ብዬሽ ነበር !
ብለሽ ከምትቆሚ
እግዚአብሔር ካልሰጠ እግዚአብሔር ካላለው
እስቲ አንቺ ጀምሪ
ሜዳውም ይኸውልሽ ፈረሱም እኔ አለው
አንቺ የኔ ባልደራስ
ለወል በውል ግሪኝ በልጓምሽ ልቁሰል
ከመልክሽ አዋጂኝ ግብርሽንም ልምሰል
* * *
ሞኝ እና ወረቀት እንዲባል ተረቱ
ለጅል እኔ አላንስም ብልጥ ሁኚልኝ እቱ
አንቺ ቀለም ሁኚ ወረቀት ሆናለሁ
ከያዝኩሽ በኋላ መቼ ለቅሻለሁ
ብልሀትና ጥበብ እንድታስተምሪን
እኔና ጎጄዬ እጅሽ ላይ ነን ስሪን
* * *
ቅርፁም እንዲቀየር ግብሩም እንዲለወጥ
ብረት ከተገኘ ሲግል ነው መቀጥቀጥ
የጋለውን ልቤን እንደፈለግሽ አርጊው
ላንቺ እንደሚመችሽ እንደምትፈልጊው
* * *
ወንድ ሁሉ ትዳሩን በእሳት ቢመስልም
ማብሰሉን ዘንግቶ ማቃጠል ቢስልም
ሳትቀምሽ ከምትጥዪኝ የኑሮ ጥሬሽን
አብስለሽ ብዪበት እሳትነትሽን
ያለቀላትን ሚስት ወንዶቹ ቢመኙም
ሴቶች ሚስት ሳይሆኑ ባሎች አይገኙም
ያው እንደሰማሽኝ
ለየብቻ ከብዶን ከምንንገዳገድ
እስቲ እንጠጋጋ ግማሽ ግማሽ መንገድ
ያው እንደነገርኩሽ
አንድ ባደረግናት የኔ እና ያንቺ አለም
መመሳሰል እንጂ መመላለስ የለም
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
@getem
@getem
@getem
ባለቤት የሌለው
የተገነባ ልብ ቆመሽ ስትጠብቂ
አለምሽን ስሪ እንጂ
አለሜን አሳየኝ ብለሽ አትጠይቂ
ብዬሽ ነበር !
ብለሽ ከምትቆሚ
እግዚአብሔር ካልሰጠ እግዚአብሔር ካላለው
እስቲ አንቺ ጀምሪ
ሜዳውም ይኸውልሽ ፈረሱም እኔ አለው
አንቺ የኔ ባልደራስ
ለወል በውል ግሪኝ በልጓምሽ ልቁሰል
ከመልክሽ አዋጂኝ ግብርሽንም ልምሰል
* * *
ሞኝ እና ወረቀት እንዲባል ተረቱ
ለጅል እኔ አላንስም ብልጥ ሁኚልኝ እቱ
አንቺ ቀለም ሁኚ ወረቀት ሆናለሁ
ከያዝኩሽ በኋላ መቼ ለቅሻለሁ
ብልሀትና ጥበብ እንድታስተምሪን
እኔና ጎጄዬ እጅሽ ላይ ነን ስሪን
* * *
ቅርፁም እንዲቀየር ግብሩም እንዲለወጥ
ብረት ከተገኘ ሲግል ነው መቀጥቀጥ
የጋለውን ልቤን እንደፈለግሽ አርጊው
ላንቺ እንደሚመችሽ እንደምትፈልጊው
* * *
ወንድ ሁሉ ትዳሩን በእሳት ቢመስልም
ማብሰሉን ዘንግቶ ማቃጠል ቢስልም
ሳትቀምሽ ከምትጥዪኝ የኑሮ ጥሬሽን
አብስለሽ ብዪበት እሳትነትሽን
ያለቀላትን ሚስት ወንዶቹ ቢመኙም
ሴቶች ሚስት ሳይሆኑ ባሎች አይገኙም
ያው እንደሰማሽኝ
ለየብቻ ከብዶን ከምንንገዳገድ
እስቲ እንጠጋጋ ግማሽ ግማሽ መንገድ
ያው እንደነገርኩሽ
አንድ ባደረግናት የኔ እና ያንቺ አለም
መመሳሰል እንጂ መመላለስ የለም
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
@getem
@getem
@getem