ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
#ተአምረ ማርያም የተባለው ጉደኛ መጽሐፍ የምንወዳትን ድንግል ማርያምን ያከበረ የሚመስል ነገር ግን #ስድብ እና #ክህደት የሞላበት ስለመሆኑ እርግጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈ #ከ1400 ዓመት በኋላ በኢትዮጵያ ንጉሥ በዘርዓ ያዕቆብ የተደረሰ ሲሆን በወቅቱ የነበሩ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት እና ምእመናን ይህ ልዩ ወንጌል ከሐዋርያት ትምህርት የወጣ ስለሆነ #አንቀበለውም በማለታቸው፣ እስከ…


ታሪኩ ሲጀምር

መጽሐፉ “ #ቅምር” በሚባል አገር አንድ ሰው ነበር
#ወኢየበልዕ እክለ ወኢ ሥጋ ላሕም ወኢ ካልአ እንሥሣ አላ ይበልዕ ሥጋ ሰብእ”
ትርጉም:- እህል፥ የላም፥ ሥጋ የሌሎችንም እንሥሳ ሥጋ አይበላም ነበር የሰው ሥጋ ይበላ ነበር እንጂ” #ቁ 68።)

« #ወዘበልዖሙሰ ሰብእ የአክሉ ፸ወ፰ተ ነፍሳተ ወኀልቁ ወተወድኡ ዓርካኒሁ ወፍቁራኒሁ ወአዝማዲሁ ወመገብቱ»
ትርጉም:- «የበላቸውም ሰዎች #78 ነፍሳት ያህላሉ ባልንጀሮቹ ወዳጆቹም ዘመዶቹም ቤተ ሰቦቹም አለቁ ተጨረሱ» #ቁ 69)
ሰውየው ልጆቹን #ከበላ በኋላ ከቤት ወጥቶ ሄደ በማለት ታሪኩ ይቀጥላል። ሲዞርም ሁለንተናው #በደዌ #ሥጋ #የታመመ ሰው አገኘ።( #ቁ 92) #ሊበላው #አስቦ ነበር ነገር ግን #በደዌው ምክንያት ሰለጠላው #ሊበላው #አልወደደም። በደዌ የተያዘው ሰው ግን ፈጽሞ #የተጠማ ስለነበረ " #በላዔ ሰብን "
ስለ
#እ #ግ #ዚ #አ #ብ #ሄ #ር
ብለህ #ውሃ #አጠጣኝ አለው " በላዔ ሰብ ግን
#ተ
#ቆ
#ጣ
#ለሁለተኛ ጊዜ ስለ #ጻድቃን እና ስለ #ሰማዕታት #አጠጣኝ አለው፤ አሁንም #በላዔ ሰብእ ፈጽሞ #ተቆጣው #ሊያጠጣው #አልፈለገም#የተጠማው #ሰው #ሦስተኛ
#ፈጣሪን #ስለወለደች
ስለ #ማ #ር #ያ #ም #አጠጣኝ አለው። በዚህ ጊዜ #በላዔ ሰብእ እስኪ #ቃልህን #ድገመው አለ፤ #አምላክን #ስለወለደች #ስለማርያም ብለህ #አጠጣኝ #አለው በዚህ ጊዜ #በላዔ ሰብእ « #ስለዚህች ስም ከሲኦል #እንደምታድን ሰምቻለሁ» አለ አሁንም እኔ በሷ #ተማጽኛለሁ #በማርያም #ስም #እንካ #ጠጣ #አለው#ውሃው ትንሽ ስለነበር እጁ ላይ ፈሶ ቀረ ጉሮሮውንም አንጣጣው እንጂ ጥሙን አልቆረጠለትም በማለት ያጭውተናል።

እስቲ እንደው ይሄን ምን #ትሉታላቹ
ለነገሩ ይሄን ያነበበ ትክክለኛ ክርስቲያን ምን እንደሚል መገመት አይከብደውም።

#ነገርዬውን ስናስተውለው #በላዔ #ሰብእ #ስለ #እግዚአብሔር ተብሎ #በእግዚአብሔር #ስም #ሲለመን#እግዚአብሔርን #አላውቅም ብሏል። ይህ ሰው #እምነት #የለሽ ከመሆኑም በላይ እንዲያውም ውሃ በመስጠት ፈንታ ስሙ ሲጠራ ተቆጥቷል። #በማርያም ተብሎ ሲለመን ግን #ውሃውን #ሰጠ። የእግዚአብሔርን ይቅርታ ተጠራጥሮ በማርያም ስም #በሰጠው ውሃ #እንደሚድን ነው #ያመነው#የክህደቱ ምሥጢር፣ ምንፍቅናው፣ ኑፋቄው እዚህ ላይ ነው። ይህ ትምህርት ህዝባችንን
በሚቀቀለው #ንፍሮ
በሚጠመቀው #ጠላ
በሚዘከረው #ዝክር #እድናለሁ የሚል አጉል #ተስፋ እንዲይዝ አድርጎታል።
#ዝክርሽን የዘከረ፣ #ስምሽን #የጠራ #ይድናል #የሚለው ባዕድ ወንጌል ተቀባይነት እንዲያገኝ #የበላዔ ሰብን #ልብ ወለድ ታሪክ #እንደማስረጃ አድርጎ #ለማሳመን #ለሕዝብ #የቀረበ ነው።

ታሪኩ ይቀጥልና የምድሩን ጨርሶ በላይ በሰማይ በእግዚአብሐር የፍርድ ዙፋን የተከናወነውን በታዛቢነት ተቀምጦ ያየ ይመስል ሊነግረን ይሞክራል። #በላዔ ሰብ #አንድ #ዋሻ ውስጥ #ገብቶ #ሞተ
« #ወመጽኡ መላእክተ ጽልመት በአፍርሆ ወበ አደንግጾ ወከበብዎ ወአውጽኡ ነፍሶ በጕጸት ወበግዱድ»
ትርጉም:- « #በማስፈራትና በማስደንገጥ የጨለማ አበጋዞች አጋንንት መጥተው ከበቡት በመቀማትና በግድ ነፍሱን ከሥጋው ለዩ»
ይላል #ደራሲው ይህ ሁሉ ሲሆን ቁጭ ብሎ የሚመለከት #ይመስላል። ይህ በእንዲህ እንዳለ መላእክት ይህን ጉዳይ #ለማርያም ነገራት #ድንግል ማርያም #ግን #በስሟ #ያጠጣውን #ቀዝቃዛ #ጽዋ #ውሃ #በጎኑ #ተሸክሞ #ስላየችው ደስ አላት
« #ወርእየት እግዝእትነ ቅድስት ድንግል ወላዲተ አምላክ በገቦሁ ማየ ምልአ ሕፍን ዘአስተየ ለነዳይ ምጽዋተ ቤእንተ ስማ ወተፈስሐት ሶቤሃ»
ትርጉም:- « #እመቤታችን ስለ ስሟ ለድሀ ምጽዋት አድርጎ ያጠጣውን ጥርኝ ውሃ በጎኑ አይታ ያን ጊዜ ደስ አላት» ማለት ነው።
#ነፍሳት በምድር ላይ እንደፈለጋቸው ሲቀላውጡ ኖረው አንድ ቀን የሰጡትን #ውሃ ወደ ሰማይ ሲሄዱ ተሸክመው እንደሚገኙ የሚያስተምር #የክርስትና #ትምህርት የለም። የዚህ ነፍሰ ገዳይ ነፍስ ግን በጎኗ ጥርኝ ውሃ ተሸክማ ስትሄድ ማርያም አየችና ደስ አላት ይለናል። ነፍሳት ወደ #ማርያም ሳይደርሱ ወደ #እግዚአብሔር #እንደማይቀርቡ ( #ቁ 111) ላይ ይናገራል #ድንግል ማርያም #የበላዔ #ሰብን #ነፍስ #ውሃ ተሸክማ #ያየቻት በዚህ ምክንያት ነው።

በመጨረሻ #መላእክት #የበላዔ ሰብን #ነፍስ ወደ #እግዚአብሔር ፊት #አደረሷትና #ልቅሶና #ጥርስ ማፋጨት #ወዳለበት #ጣሏት የሚል ትእዛዝ #ከዙፋኑ ወጣ ይላል። በዚህ ጊዜ #ድንግል ማርያም #ማርልኝ #እያለች ለመነች #በስሜ #ቀዝቃዛ #ጽዋ #ውሃ ያጠጣውን #ልትምርልኝአሳየ ቃል #ገብተህልኝ #አልነበረምን? አለች። እግዚአብሔርም ፍርዱን ገልብጦ ሚካኤልን #ጥርኝ ውሃንና #78ቱን #ነፍሳት መዝንልኝ አለው። #ሚካኤልም #ውሃንና #78ቱን #ነፍሳት ሲመዝን #ውሃ ቀለለ #ነፍሳት ግን #ክብደት #አሳዩ ይላል።
#ድንግል ማርያም ግን #ፈጠን
ብላ #በውሃው ላይ #ጥላዋን #ጣለችበት #በዚህ ጊዜ #ውሃው #ከበደ #ነፍሳት #ግን #ቀለሉ
#በላዔ ሰብም በማርያም #ጥላ
ምክንያት #ለትንሽ
#ከሲኦል #አመለጠ #በማለት #አስቂኝ #ልቦለድ #ያስነብበናል#ይህም ታሪክ #እውነት ነው ተብሎ #አመታዊ በአል ሆኖ #እንዲከበር#ዜማ ተዘጋጅቶለት #መልክ #ተድርሶለት #እንዲነገር #ተብሎ #በየካቲት 16 ቀን #ታስቦ ይውላል። የየካቲት አስራ ስድስት #የኪዳነ ምሕረት በዓል ይህን ቃል ኪዳን የተመለከተ ነው።

@gedlatnadersanat
👇👇👇
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
😏😏😏😁😁😁😁 @gedlatnadersanat @gedlatnadersanat @gedlatnadersanat @gedlatnadersanat


500 ሚሊዮን ነፍስ ከሲኦል ማስመለጥ

« #ወወሐባ ኪዳነ ከመ ታውጽእ ነፍሳተ እምሲኦል ሠለስተ እልፈ ነፍሳተ በበዕለቱ»
ትርጉም " #ጌታም በየቀኑ ከሲኦል ሦስት ሺህ ነፍሳትን እንድታወጣ ሥልጣን ሰጣት ወይም ቃል ኪዳን ሰጣት»
📖/ ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘጥቅምት ቁ 61...

500 ሚሊዮን የኢትዮጵያን ህዝብ 5 እጥፍ ነው። ይህ ቁጥር ክርስቶስ ሰምራ ከኖረችበት #ከአጼ ገብረ መስቀል መንግስት ጀምሮ #ለ450 አመታት በቀን #3000 ነፍሳት #ከሲኦል እንድታወጣ #ቃል ኪዳን ተቀበለች ከተባለላት ጀምሮ የተሰላ ነው። መቼስ እሱዋ ካወጣቻቸው ቀድሞውኑ ለምን #ሲኦል #ወረዱ የሚለው አጠያያቂ ቢሆንም መጽሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረን ሲኦል ይቅርታ የሌለበት ያጠፉ የሚቀጡበት እንጂ በቃልኪዳን ስም እየተጨለፈ የሚወጣበት አይደለም።
እንዲህ አይነቱ ሰይጣን ሰዎች #ሲኦል ብወርድም #ክርስቶስ ሰምራ ታወጣኛለች ብለው፤ እንዲሁም " #ምንም እንደምድር አሽዋ ቢበዛ ሀጥአቴ፣ ታማልደኛለች #ድንግል እመቤቴ" እያሉ #በሃጢአታቸውና #በዝሙታቸው #በግድያቸው #በስርቆታቸው #እንዲገፉበትና #እንዳይጸጸቱ የሚሰራበት ሽንገላ ነው።

#ክርስቶስ ሰምራ #ባለትዳርና የ 11 ልጆች እናት ነበረች፤ ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት ባሪያዋ አበሳጨቻትና በእሳት ትንታግ ጉሮሮዋን #ጠብሳ #ገደለቻት ከዚያም #ተጸጽታ #ትዳሩዋንና #ልጆቹዋን #በትና ደብረ ሊባኖስ ገባች።

1= በዚህም እግዚአብሄር #ጋብቻ ቅዱስ ነው ያለውን ተላልፋ #መለያየትን እጠላለሁ ያለውን አልሰማም ብላ ራስ የሆነውን ባሉዋን አልሰማ ብላ፤ እግዚአብሄር በረከት ያላቸውን ልጆች #መንከባከብ #ትታ ጥላ በመጥፋት በድላለች/መጥፎ #ክርስቲያናዊ ያልሆነ #ምሳሌ ሆናለች።

2= (ወደ ጣና ሄዳ በጣና #ባሕር ውስጥ #ለ12 ዓመት ያህል ሳትነቃነቅ #ጸልያለች። በዚህ ጊዜ ሰውነቷ #አልቆ #አጥንት ብቻ #ቀርቷት ነበር። #አሳዎችም #ባጥንቶቿ ውስጥ መመላሻ መንግድ ጎጆና #መዝናኛ #ሠርተው ነበር።)
ይህ #የሰው ባህሪ ያልሆነ #ሃሰተኛና #አደገኛ #ተረት ነው። ይህ የሰው ባህሪ አይደለም። ጌታ እንኩዋን #ተርቦአል/ተጠምቶአል/ #ደክሞአል ኤሌያስም ተርቦ ደክሞት ነበር -ሰውነት ተበሳስቶ መኖር አይቻልም።

3. ክርስቶስ ሰምራ #በዲያብሎስና #በክርስቶስ መካከል ያለውን ጠላትነት ዘንግታ ዲያብሎስን ለማስታረቅ ወደ ሲኦል ወርዳ #ከዲያብሎስ ጋር #ተነጋግራለች። ይህ #ለዲያቢሎስ ፍቅር እንጂ #የእግዚአብሄር ፍቅር አይደለም።
2ኛ ቆሮ 6:15 “ ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን #መስማማት አለው? “ ይላልና #መንፈሳዊ ሰው ከሆነች ይህንን እንዴት አታውቅም….

4. « #ጌታም ተናገራት እንዲህ አላት #በአራት ወር ውስጥ በየቀኑ የሚወርደውን #የዝናብ #ነጠብጣብ ያህል #ነፍሳትን #አሥራት ሰጥቸሻለሁ» ወገኖቼ የአራት ወር #ዝናብ ነጠብጣብ ማለት ከአለም ህዝብ በላይ ነው።
ክህደቱ የሚጀምረው ገና ከመጀመሪያው ነው። #አሥራት ማለት ከአስር አንድ ማለት ሲሆን እሱም ከሰው ወደ እግዚአብሔር እንጂ ከእግዚአሃብሄር ወደ ሰው አይደለም።
#አለምና መላው ደግሞ #የኢየሱስ ክርስቶስ እንጂ የአንድ ፍጡር #የክርስቶስ ሰምራ አይደለም።

ወገኔ ዮሐ 15፥22። «እኔ መጥቼ ባልነገርኋችሁስ #ኃጢአት ባልሆነባችሁም ነበር» ይላልና ዛሬ እንዲህ አይነት አጋንንታዊ ተረት የምትከተሉ ጌታ ያስጠነቅቃችሁዋል ወደጌታ ተመለሱ።

1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4:7
ነገር ግን ለዚህ ዓለም #ከሚመችና የአሮጊቶችን #ሴቶች #ጨዋታ ከሚመስለው #ተረት #ራቅ። እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ።

#እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል/ዩሀ 8፥32/

@gedlatnadersanat @teeod