ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
😏😏😏😁😁😁😁 @gedlatnadersanat @gedlatnadersanat @gedlatnadersanat @gedlatnadersanat


500 ሚሊዮን ነፍስ ከሲኦል ማስመለጥ

« #ወወሐባ ኪዳነ ከመ ታውጽእ ነፍሳተ እምሲኦል ሠለስተ እልፈ ነፍሳተ በበዕለቱ»
ትርጉም " #ጌታም በየቀኑ ከሲኦል ሦስት ሺህ ነፍሳትን እንድታወጣ ሥልጣን ሰጣት ወይም ቃል ኪዳን ሰጣት»
📖/ ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘጥቅምት ቁ 61...

500 ሚሊዮን የኢትዮጵያን ህዝብ 5 እጥፍ ነው። ይህ ቁጥር ክርስቶስ ሰምራ ከኖረችበት #ከአጼ ገብረ መስቀል መንግስት ጀምሮ #ለ450 አመታት በቀን #3000 ነፍሳት #ከሲኦል እንድታወጣ #ቃል ኪዳን ተቀበለች ከተባለላት ጀምሮ የተሰላ ነው። መቼስ እሱዋ ካወጣቻቸው ቀድሞውኑ ለምን #ሲኦል #ወረዱ የሚለው አጠያያቂ ቢሆንም መጽሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረን ሲኦል ይቅርታ የሌለበት ያጠፉ የሚቀጡበት እንጂ በቃልኪዳን ስም እየተጨለፈ የሚወጣበት አይደለም።
እንዲህ አይነቱ ሰይጣን ሰዎች #ሲኦል ብወርድም #ክርስቶስ ሰምራ ታወጣኛለች ብለው፤ እንዲሁም " #ምንም እንደምድር አሽዋ ቢበዛ ሀጥአቴ፣ ታማልደኛለች #ድንግል እመቤቴ" እያሉ #በሃጢአታቸውና #በዝሙታቸው #በግድያቸው #በስርቆታቸው #እንዲገፉበትና #እንዳይጸጸቱ የሚሰራበት ሽንገላ ነው።

#ክርስቶስ ሰምራ #ባለትዳርና የ 11 ልጆች እናት ነበረች፤ ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት ባሪያዋ አበሳጨቻትና በእሳት ትንታግ ጉሮሮዋን #ጠብሳ #ገደለቻት ከዚያም #ተጸጽታ #ትዳሩዋንና #ልጆቹዋን #በትና ደብረ ሊባኖስ ገባች።

1= በዚህም እግዚአብሄር #ጋብቻ ቅዱስ ነው ያለውን ተላልፋ #መለያየትን እጠላለሁ ያለውን አልሰማም ብላ ራስ የሆነውን ባሉዋን አልሰማ ብላ፤ እግዚአብሄር በረከት ያላቸውን ልጆች #መንከባከብ #ትታ ጥላ በመጥፋት በድላለች/መጥፎ #ክርስቲያናዊ ያልሆነ #ምሳሌ ሆናለች።

2= (ወደ ጣና ሄዳ በጣና #ባሕር ውስጥ #ለ12 ዓመት ያህል ሳትነቃነቅ #ጸልያለች። በዚህ ጊዜ ሰውነቷ #አልቆ #አጥንት ብቻ #ቀርቷት ነበር። #አሳዎችም #ባጥንቶቿ ውስጥ መመላሻ መንግድ ጎጆና #መዝናኛ #ሠርተው ነበር።)
ይህ #የሰው ባህሪ ያልሆነ #ሃሰተኛና #አደገኛ #ተረት ነው። ይህ የሰው ባህሪ አይደለም። ጌታ እንኩዋን #ተርቦአል/ተጠምቶአል/ #ደክሞአል ኤሌያስም ተርቦ ደክሞት ነበር -ሰውነት ተበሳስቶ መኖር አይቻልም።

3. ክርስቶስ ሰምራ #በዲያብሎስና #በክርስቶስ መካከል ያለውን ጠላትነት ዘንግታ ዲያብሎስን ለማስታረቅ ወደ ሲኦል ወርዳ #ከዲያብሎስ ጋር #ተነጋግራለች። ይህ #ለዲያቢሎስ ፍቅር እንጂ #የእግዚአብሄር ፍቅር አይደለም።
2ኛ ቆሮ 6:15 “ ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን #መስማማት አለው? “ ይላልና #መንፈሳዊ ሰው ከሆነች ይህንን እንዴት አታውቅም….

4. « #ጌታም ተናገራት እንዲህ አላት #በአራት ወር ውስጥ በየቀኑ የሚወርደውን #የዝናብ #ነጠብጣብ ያህል #ነፍሳትን #አሥራት ሰጥቸሻለሁ» ወገኖቼ የአራት ወር #ዝናብ ነጠብጣብ ማለት ከአለም ህዝብ በላይ ነው።
ክህደቱ የሚጀምረው ገና ከመጀመሪያው ነው። #አሥራት ማለት ከአስር አንድ ማለት ሲሆን እሱም ከሰው ወደ እግዚአብሔር እንጂ ከእግዚአሃብሄር ወደ ሰው አይደለም።
#አለምና መላው ደግሞ #የኢየሱስ ክርስቶስ እንጂ የአንድ ፍጡር #የክርስቶስ ሰምራ አይደለም።

ወገኔ ዮሐ 15፥22። «እኔ መጥቼ ባልነገርኋችሁስ #ኃጢአት ባልሆነባችሁም ነበር» ይላልና ዛሬ እንዲህ አይነት አጋንንታዊ ተረት የምትከተሉ ጌታ ያስጠነቅቃችሁዋል ወደጌታ ተመለሱ።

1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4:7
ነገር ግን ለዚህ ዓለም #ከሚመችና የአሮጊቶችን #ሴቶች #ጨዋታ ከሚመስለው #ተረት #ራቅ። እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ።

#እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል/ዩሀ 8፥32/

@gedlatnadersanat @teeod