ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
Audio
#መዝሙር – እያለፈ ነው ዘመኔ
በወንድማችን #ዳዊት_ክብሩ

#እያለፈ ነው ዘመኔ ትዕዛዙን ሳልፈጽም ወየው ለኔ(2)
በጠራኝ ጊዜ ምን እላለው ና ብሎ ወደኔ(2)

በወጣትነቴ ሳልሰራ እያየው አለፈ ብዙ አዝመራ(2)
ከእግዲህ በመስራት ጌታ ሆይ ልኑር ካንተ ጋራ(2)

የማስብበት በየዕለቱ ንጹህ ልብን ስጠኝ አቤቱ(2)
ከትዕዛዝህ ውጪ በመሆን እንዳልቀር በከንቱ(2)

እንደየሥራው ለመክፈል በግርማ መንግሥቱ ሲመጣ(2)
ማን ይሆን የሚቆም ከፊቱ ፈተናን የወጣ(2)

እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ የተማራችሁ ከቃሉ(2)
ይመጣሉና በእርሱ ስም አምላክ ነን የሚሉ(2)

ትዕግስትን በመያዝ ሁላችሁ እስከ መጨረሻው ጠንክሩ(2)
ያንጊዜ ይሆናል በእርሱ ዘንድ የማዳን ተግባሩ(2)

👇👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆🖕
ከዘመናት_በፊት.mp3
1.3 MB
#መዝሙር #ከዘመናት_በፊት

#ወንድማችን #ዳዊት_ክብሩ እና #በእህታችን #ፋሲካ_ክብሩ

#መሰንቆ #በወንድማችን #ማርቆስ_አለማየሁ

#ከዘመናት_በፊት አንተ ነበርህ
ሁሉን አሳልፈህ ትኖራለህ
እም ቅድመ ዘመናት ዘመናዊ
ድኅረ ዘመን አዲስ ኢየሱስ ናዝራዊ

ክብርህ ገናና ነው ባንተ ከብሬአለው
ዘላለማዊ ነህ ባንተ እኖራለው
ከሰልፉ መካከል አለህ ከኔ ጋራ
የሠራዊት ጌታ እጹብ ያንተ ሥራ

ከላይ ከአርያም ከዙፋንህ ግርማ
ቅዱስ አለ ኪሩብ ምስጋናው ተሰማ
ውዳሴ ከበበው መንበሩን ዕልልታ
ባርያህ ላመስግንህ ፍቀድልኝ ጌታ

የአማልክት አምላክ የሚመስልህ የለም
ዓይኔ ያየው ሁሉ ያላንተ አልሆነም
ፍጥረትና ዓለሙ ገንዘብህ ነው
አልፋና ኦሜጋ ይድረስህ ምስጋና

የምድር ኃያላን አይቆሙም ከፊትህ
ይህን ሰራህ ብሎ የለም የሚወቅስህ
ሰማይና ምድርን ፈጥረህ የምትገዛ
እናመልክሀለን የሕይወታችን ቤዛ


👇👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆👆
Audio
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴

🌴እንኳን ለበዓለ ሆሳዕና በሰላም🌴

🌴አደረሳችሁ።🌴

🌴 #መዝሙር #ሆሳዕና_በአርያም 🌴

🌴#በወንድማችን #ዳዊት_ክብሩ🌴

🌴#ክራር #በወንድማችን
#ሀብታሙ_ሽፈራው🌴

ሆሳዕና በአርያም
ሀሌ ሀሌሉያ(2)
መድኃኒት መጣልን ለሁላችን
ሀሌ ሀሌሉያ(2)
እናከብረዋለን ከልባችን ለዘለዓለም
ሆሳዕና(2) በአርያም
ሆሳዕና በአርያም
ሀሌ ሀሌሉያ(2)

ቡሩክ ነው የመጣው በእግዚአብሔር ስም
ሀሌ ሀሌሉያ(2)
ምስጋና ይድረሰው ለአምላክ በመላው ዓለም
ሆሳዕና(2) በአርያም
ሆሳዕና በአርያም
ሀሌ ሀሌሉያ(2)


🌴 @AwediMeherit 🌴
🌴 @AwediMeherit 🌴
🌴 @AwediMeherit 🌴

🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴
Voice 001.amr
387 KB
#መዝሙር በወንድማችን #ዳዊት_ክብሩ

#ትምክህተ ዘመድነ

👇👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆🖕
ከዘመናት_በፊት.mp3
1.3 MB
#መዝሙር #ከዘመናት_በፊት

#ወንድማችን #ዳዊት_ክብሩ እና #በእህታችን #ፋሲካ_ክብሩ

#መሰንቆ #በወንድማችን #ማርቆስ_አለማየሁ

#ከዘመናት_በፊት አንተ ነበርህ
ሁሉን አሳልፈህ ትኖራለህ
እም ቅድመ ዘመናት ዘመናዊ
ድኅረ ዘመን አዲስ ኢየሱስ ናዝራዊ

ክብርህ ገናና ነው ባንተ ከብሬአለው
ዘላለማዊ ነህ ባንተ እኖራለው
ከሰልፉ መካከል አለህ ከኔ ጋራ
የሠራዊት ጌታ እጹብ ያንተ ሥራ

ከላይ ከአርያም ከዙፋንህ ግርማ
ቅዱስ አለ ኪሩብ ምስጋናው ተሰማ
ውዳሴ ከበበው መንበሩን ዕልልታ
ባርያህ ላመስግንህ ፍቀድልኝ ጌታ

የአማልክት አምላክ የሚመስልህ የለም
ዓይኔ ያየው ሁሉ ያላንተ አልሆነም
ፍጥረትና ዓለሙ ገንዘብህ ነው
አልፋና ኦሜጋ ይድረስህ ምስጋና

የምድር ኃያላን አይቆሙም ከፊትህ
ይህን ሰራህ ብሎ የለም የሚወቅስህ
ሰማይና ምድርን ፈጥረህ የምትገዛ
እናመልክሀለን የሕይወታችን ቤዛ


👇👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆👆
Audio
#መዝሙር #ድንግል_ሆይ_ስለ_አንቺ

#በወንድማችን #ዳዊት_ክብሩ

#ክራር #አቤኔዘር_ማሙሸት

ድንግል ሆይ ስለ አንቺ ነውና መሐሪ 
አማልጅን ከአንድ ልጅሽ ከፈጣሪ 

ስሙን እንዳልጠራ አንደበትም የለኝ 
ፊቱንም እንዳላይ ሥራዬ አስቸገረኝ 

ታውቆኛል ጥፋቴ ብዙ እንደበደልኩኝ 
ትእዛዙን እንደሻርኩ ሕጉን እንደጣስኩኝ 

በፊቱ እንዳላፍር የተጠራሁ ለታ 
እለምነዋለሁ ከአሁኑ ይቅርታ

አንተ ክቡር መልአክ ልደቱን አብሣሪ 
አማልደን ከጌታዬ ከፈጣሪ 
 
ጻድቃን ሰማእታት እናንተ ሁላችሁ 
አማልዱኝ ከአምላኬ ከአምላካችሁ

👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
Audio
#መዝሙር – እያለፈ ነው ዘመኔ
በወንድማችን #ዳዊት_ክብሩ

#መሰንቆ #ሀብታሙ_ሽፈራው

#እያለፈ ነው ዘመኔ ትዕዛዙን ሳልፈጽም ወየው ለኔ(2)
በጠራኝ ጊዜ ምን እላለው ና ብሎ ወደኔ(2)

በወጣትነቴ ሳልሰራ እያየው አለፈ ብዙ አዝመራ(2)
ከእግዲህ በመስራት ጌታ ሆይ ልኑር ካንተ ጋራ(2)

የማስብበት በየዕለቱ ንጹህ ልብን ስጠኝ አቤቱ(2)
ከትዕዛዝህ ውጪ በመሆን እንዳልቀር በከንቱ(2)

እንደየሥራው ለመክፈል በግርማ መንግሥቱ ሲመጣ(2)
ማን ይሆን የሚቆም ከፊቱ ፈተናን የወጣ(2)

እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ የተማራችሁ ከቃሉ(2)
ይመጣሉና በእርሱ ስም አምላክ ነን የሚሉ(2)

ትዕግስትን በመያዝ ሁላችሁ እስከ መጨረሻው ጠንክሩ(2)
ያንጊዜ ይሆናል በእርሱ ዘንድ የማዳን ተግባሩ(2)

👇👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆🖕
ሰላምሽ ዛሬ ነው
<unknown>
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴

🌴እንኳን ለበዓለ ሆሳዕና በሰላም🌴

🌴አደረሳችሁ።🌴

🌴 #መዝሙር #ሰላምሽ_ዛሬ_ነው 🌴

🌴#በወንድማችን #ዳዊት_ክብሩ🌴

🌴#መሰንቆ #በወንድማችን
#ሀብታሙ_ሽፈራው
🌴#ክራር #በወንድማችን
#አቤኔዘር_ማሙሸት

ሰላምሽ ዛሬ ነው ኢየሩሳሌም
ወደአንች መጥቷልና አምላክ ዘላአለም/2/ 

ሆሳዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ 
ሕፃናት በኢየሩሳሌም 

አንቺ ቤተልሄም የዳዊት ከተማ/2/ 
የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/2 

ኪሩቤል መንበሩን የሚሸከሙለት/2/ 
መስቀል ተሸከመ ሊሆነን መድኃኒት /2/

የኢየሱስን ሕማም ደናግልም አይተው/2/ 
እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው/2/ 

ሆሳዕና እያሉ አመሰገኑት
በኢየሩሳሌም አእሩግ ሕፃናት/2/


🌴 @AwediMeherit 🌴
🌴 @AwediMeherit 🌴
🌴 @AwediMeherit 🌴

🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴
#መዝሙር #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ

#በአርቲስት #ነብዩ_ኤርሚያስ እና #ዳዊት_ክብሩ

#ክራር #ሀብታሙ_ሽፈራው

ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘይሰርር በአክናፍ
ኀበ ዓምደ ወርቅ(2) ስሙ ጽሑፍ

እንኳን ለጻድቁ አባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሠላም አደረሳችሁ።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel
Watch "🔴 አዲስ ዝማሬ "መድኀኒታችን ነሽ" ዘማሪ ዳዊት ክብሩ @-mahtot" on YouTube https://youtu.be/O2vyMH5NbX4
ሰምቶ በማሰማት #ለብዙዎች_ማረፊያ ሁኑ !
__________    #ዳዊት በገናን በደረደረ ጊዜ በሳኦል ያደረ ክፉ መንፈስን እያራቀ ሳኦልን ያሳርፈው ነበር።     
      #ይህው ዛሬም በጥዑም ኦርቶዶክሳዊ ለዛው ዝማሬዎችን በየ ዓይነቱ እየደረደረ ጸላዔ ሰናያት የሆነ የዲያቢሎስ ማደሪያዎችን እየጎሰመ በቀናች የሃይማኖት ወደብ ያሳርፉቸው ዘንድ ይዞል።
           |1ኛ #ሳሙ 16፥23
#ድንግል ሆይ አዎን  " #መድኃኒታችን_ነሽ "
ከዕለቱ #መዝሙር

#መዝሙረ ዳዊት 69

አቤቱ፥ እኔን ለማዳን ተመልከት፤ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
ነፍሴን የሚሹአት ይፈሩ ይጐስቍሉም፥ ክፉንም የሚመክሩብኝ ወደ ኋላቸው ይመለሱ ይፈሩም።
እንኳ እንኳ የሚሉኝ አፍረው ወዲያው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።
የሚሹህ ሁሉ በአንተ ሐሤት ያድርጉ ደስ ይበላቸው፤ ማዳንህን የሚወድዱ ሁልጊዜ፦ እግዚአብሔር ታላቅ ነው ይበሉ።
እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ፤ አቤቱ፥ እርዳኝ፤ ረዳቴ ታዳጊዬም አንተ ነህ፤ አቤቱ፥ አትዘግይ።

እንኳን ለጻድቁ፣ለየዋሁ፣ለደጉ፣ለብእሴ #እግዚአብሔር ለቅዱስ #ዳዊት በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችሁ!!!የቅዱስ #ዳዊት በረከቱ ይደርብን!!!

#ታኅሣሥ 23/2017 ዓ.ም
#ኢዮብ ክንፈ
#ዛሬ #እግዚአብሔር “ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።” (ዘፍ 11፥7) ብሎ ለራሱ በብዙ ቁጥር ተናግሮ ሦስትነቱን ገልጧል።ስለዚህም ቅድስት #ሥላሴ ብለን እናከብራለን።ቅድስት #ሥላሴ ማለትም ልዩ ሦስትነት ማለት ነው።

#እግዚአብሔር ያንጻል #እግዚአብሔር ያፈርሳል

#“በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።”( ዘፍ1፥1) በሚለው ቃል የእግዚአብሔርን አናፂነቱን ተረዳን ፤“እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተው።"ዘፍ 11፥8) በሚለው ቃልም የእግዚአብሔር አፍራሽነቱን ዐወቅን።የሰናዖርን ግንብ የገነቡ ሰዎች ዓላማቸው እግዚአብሔርን ከንግሥና ዙፋኑ አውርዶ ለመንገሥ ነበር።

#እነዚህም ቅዱስ #ዳዊት"የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ። ማሰርያቸውን እንበጥስ፥ ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል። በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል። በዚያን ጊዜ በቍጣው ይናገራቸዋል፥ በመዓቱም ያውካቸዋል።"(መዝ 2:2-5) ብሎ የተናገረላቸው ዓይነት ሰዎች ናቸው።ዓላማቸውም #የእግዚአብሔር አምላክነቱን (ገዢነቱን) ከላያቸው ላይ መጣል ነው።ነገሩ ግን አስቂኝ ነው።ሰው የማይሆንለትን ነገር ሲሞክር ቂልነቱ ያስቃል።

#የሰው ፍላጎት በአጭሩ #እግዚአብሔርን መሆን ነው።የአዳም ምኞት ፣ የባቢሎን ሰዎች ፍላጎት፣ የአላውያን ነገሥታት ጉጉት ፣ አሁን ያለን ሰዎች ፍላጎትም አምላክ መሆን ነው።አምላክ የመሆን ፍላጎታችን ማሳያዎችም አሉ።መውሰድ #የእግዚአብሔር ነው እኛ እንሰርቃለን ፤ መግደል #የእግዚአብሔር ነው እኛ እንገድላለን ፤ መፍረድ #የእግዚአብሔር ነው እኛ እንፈርዳለን።

#ቅድስት #ሥላሴ በዛሬው ዕለት የባቢሎንን ግንብ እንዳፈረሰ የእኛንም የትዕቢትና የኃጢአት ግንብ በቸርነቱ አፍርሶ ፤ ሰውነታችንን ለእርሱ ማደሪያነት ያንጽልን።

#ጥር #ሥላሴ / 2017 ዓ.ም
ኢዮብ ክንፈ