ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
ሥላሴ

#ከቸርነትህ እጅግ እጅግ እጅግ ጥቂቱን ልበል ፦

#ሥላሴ ጌታዬ አምላኬም
#ሥላሴ አባቴ እናቴም
#ሥላሴ የጠላትን ጦር መመከቻ ጋሻዬ
#ሥላሴ ጠላትን ማጥቂያ ጦሬ
#ሥላሴ ከኃዘኔ መጽናኛ ደስታዬ
#ሥላሴ በድካሜ ጊዜ ጉልበቴና ኃይሌ
#ሥላሴ የተቆረጠውን የምትቀጥል ተስፋዬ
#ሥላሴ ሳዝን ሲከፋኝ ማልቀሻዬ
#ሥላሴ ሩኅሩኅ የጽድቅ ዳኛዬ
#ሥላሴ ሃይማኖቴ ማዕተቤም

+ኃይልየ #ሥላሴ ወጸወንየ #ሥላሴ
+በስመ #ሥላሴ እቀጠቅጥ ከይሴ

+ ሁሉ #ከሥላሴ #በሥላሴ #ለሥላሴ ሆነ !!!

+ክብር #ለሥላሴ በሰማይ በምድር!!! +በባሕርና በጥልቆች ሁሉ ይሁን አሜን!!!

ታኅሣሥ #ሥላሴ / 2017 ዓ.ም

#ኢዮብ ክንፈ
#ዛሬ #እግዚአብሔር “ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።” (ዘፍ 11፥7) ብሎ ለራሱ በብዙ ቁጥር ተናግሮ ሦስትነቱን ገልጧል።ስለዚህም ቅድስት #ሥላሴ ብለን እናከብራለን።ቅድስት #ሥላሴ ማለትም ልዩ ሦስትነት ማለት ነው።

#እግዚአብሔር ያንጻል #እግዚአብሔር ያፈርሳል

#“በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።”( ዘፍ1፥1) በሚለው ቃል የእግዚአብሔርን አናፂነቱን ተረዳን ፤“እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተው።"ዘፍ 11፥8) በሚለው ቃልም የእግዚአብሔር አፍራሽነቱን ዐወቅን።የሰናዖርን ግንብ የገነቡ ሰዎች ዓላማቸው እግዚአብሔርን ከንግሥና ዙፋኑ አውርዶ ለመንገሥ ነበር።

#እነዚህም ቅዱስ #ዳዊት"የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ። ማሰርያቸውን እንበጥስ፥ ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል። በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል። በዚያን ጊዜ በቍጣው ይናገራቸዋል፥ በመዓቱም ያውካቸዋል።"(መዝ 2:2-5) ብሎ የተናገረላቸው ዓይነት ሰዎች ናቸው።ዓላማቸውም #የእግዚአብሔር አምላክነቱን (ገዢነቱን) ከላያቸው ላይ መጣል ነው።ነገሩ ግን አስቂኝ ነው።ሰው የማይሆንለትን ነገር ሲሞክር ቂልነቱ ያስቃል።

#የሰው ፍላጎት በአጭሩ #እግዚአብሔርን መሆን ነው።የአዳም ምኞት ፣ የባቢሎን ሰዎች ፍላጎት፣ የአላውያን ነገሥታት ጉጉት ፣ አሁን ያለን ሰዎች ፍላጎትም አምላክ መሆን ነው።አምላክ የመሆን ፍላጎታችን ማሳያዎችም አሉ።መውሰድ #የእግዚአብሔር ነው እኛ እንሰርቃለን ፤ መግደል #የእግዚአብሔር ነው እኛ እንገድላለን ፤ መፍረድ #የእግዚአብሔር ነው እኛ እንፈርዳለን።

#ቅድስት #ሥላሴ በዛሬው ዕለት የባቢሎንን ግንብ እንዳፈረሰ የእኛንም የትዕቢትና የኃጢአት ግንብ በቸርነቱ አፍርሶ ፤ ሰውነታችንን ለእርሱ ማደሪያነት ያንጽልን።

#ጥር #ሥላሴ / 2017 ዓ.ም
ኢዮብ ክንፈ