ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
የሀዘን #መግለጫ
😔😔😔😔😔

#ውድ_የቻናሎቻችን ታዳሚዎች በልዮ ልዮ ጊዜ በልዮ ልዮ ምክንያት #በአካለ_ሥጋ_በሞት_ከኛ ከተለዮን #ለምናውቃቸውና_ለማናውቃቸው_ለሁሉም_የሰው_ልጆች _እልፈተ_ሕይወት የተሰማን እና የሚሰማንን #ጥልቅ ሀዘን በእኛና በቻናሎቻችን ተከታዮች ስም ለመግለጽ እንወዳለን::
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
😞😞😞😞😞😞😞😞😞😞😞

"፤ #የሰው_ዕድሜ_የተወሰነ ነው፥ #የወሩም_ቍጥር በአንተ ዘንድ ነው፥ እርሱም ሊተላለፈው የማይችለውን ዳርቻ አደረግህለት።" #ኢዮ 14÷5

😞😞😞😞😞😞😞😞😞😞😞
"፤ #የዘመኖቻችንም ዕድሜ #ሰባ ዓመት፥ ቢበረታም #ሰማንያ ዓመት ነው፤ #ቢበዛ_ግን ድካምና መከራ ነው፤ " #መዝ 88(90)÷10
😞😞😞😞😞😞😞😞😞😞
የሀዘን #መዝሙር
😞😞😞😞😞😞

#ማርያም ሀዘነ ልቡና ታቀልል(2)×
ሀዘነ ልቡና (4)× ታቀልል (2)×

#ማርያም የልብን ሀዘን ታቀላለች(2)×
የልብን ሀዘን(4)× ታቀላለች (2)×

#እግዚአብሔር_አምላክ ነፍሳቸውን #ከአብርሃም_ከይስሐቅ_ከያዕቆብም እቅፍ ያኑርልን #ለዘለዓለሙ_አሜን🙏

ዓውደ ምህረት
@AwediMeherit
የኔታ
@yenetta
መጽሐፈ ጨዋታ
@MtsafiChewata
#ዛሬ #እግዚአብሔር “ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።” (ዘፍ 11፥7) ብሎ ለራሱ በብዙ ቁጥር ተናግሮ ሦስትነቱን ገልጧል።ስለዚህም ቅድስት #ሥላሴ ብለን እናከብራለን።ቅድስት #ሥላሴ ማለትም ልዩ ሦስትነት ማለት ነው።

#እግዚአብሔር ያንጻል #እግዚአብሔር ያፈርሳል

#“በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።”( ዘፍ1፥1) በሚለው ቃል የእግዚአብሔርን አናፂነቱን ተረዳን ፤“እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተው።"ዘፍ 11፥8) በሚለው ቃልም የእግዚአብሔር አፍራሽነቱን ዐወቅን።የሰናዖርን ግንብ የገነቡ ሰዎች ዓላማቸው እግዚአብሔርን ከንግሥና ዙፋኑ አውርዶ ለመንገሥ ነበር።

#እነዚህም ቅዱስ #ዳዊት"የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ። ማሰርያቸውን እንበጥስ፥ ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል። በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል። በዚያን ጊዜ በቍጣው ይናገራቸዋል፥ በመዓቱም ያውካቸዋል።"(መዝ 2:2-5) ብሎ የተናገረላቸው ዓይነት ሰዎች ናቸው።ዓላማቸውም #የእግዚአብሔር አምላክነቱን (ገዢነቱን) ከላያቸው ላይ መጣል ነው።ነገሩ ግን አስቂኝ ነው።ሰው የማይሆንለትን ነገር ሲሞክር ቂልነቱ ያስቃል።

#የሰው ፍላጎት በአጭሩ #እግዚአብሔርን መሆን ነው።የአዳም ምኞት ፣ የባቢሎን ሰዎች ፍላጎት፣ የአላውያን ነገሥታት ጉጉት ፣ አሁን ያለን ሰዎች ፍላጎትም አምላክ መሆን ነው።አምላክ የመሆን ፍላጎታችን ማሳያዎችም አሉ።መውሰድ #የእግዚአብሔር ነው እኛ እንሰርቃለን ፤ መግደል #የእግዚአብሔር ነው እኛ እንገድላለን ፤ መፍረድ #የእግዚአብሔር ነው እኛ እንፈርዳለን።

#ቅድስት #ሥላሴ በዛሬው ዕለት የባቢሎንን ግንብ እንዳፈረሰ የእኛንም የትዕቢትና የኃጢአት ግንብ በቸርነቱ አፍርሶ ፤ ሰውነታችንን ለእርሱ ማደሪያነት ያንጽልን።

#ጥር #ሥላሴ / 2017 ዓ.ም
ኢዮብ ክንፈ