ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
ከዘመናት_በፊት.mp3
1.3 MB
#መዝሙር #ከዘመናት_በፊት

#ወንድማችን #ዳዊት_ክብሩ እና #በእህታችን #ፋሲካ_ክብሩ

#መሰንቆ #በወንድማችን #ማርቆስ_አለማየሁ

#ከዘመናት_በፊት አንተ ነበርህ
ሁሉን አሳልፈህ ትኖራለህ
እም ቅድመ ዘመናት ዘመናዊ
ድኅረ ዘመን አዲስ ኢየሱስ ናዝራዊ

ክብርህ ገናና ነው ባንተ ከብሬአለው
ዘላለማዊ ነህ ባንተ እኖራለው
ከሰልፉ መካከል አለህ ከኔ ጋራ
የሠራዊት ጌታ እጹብ ያንተ ሥራ

ከላይ ከአርያም ከዙፋንህ ግርማ
ቅዱስ አለ ኪሩብ ምስጋናው ተሰማ
ውዳሴ ከበበው መንበሩን ዕልልታ
ባርያህ ላመስግንህ ፍቀድልኝ ጌታ

የአማልክት አምላክ የሚመስልህ የለም
ዓይኔ ያየው ሁሉ ያላንተ አልሆነም
ፍጥረትና ዓለሙ ገንዘብህ ነው
አልፋና ኦሜጋ ይድረስህ ምስጋና

የምድር ኃያላን አይቆሙም ከፊትህ
ይህን ሰራህ ብሎ የለም የሚወቅስህ
ሰማይና ምድርን ፈጥረህ የምትገዛ
እናመልክሀለን የሕይወታችን ቤዛ

👇👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆👆
ሦስትነት_ባለው_በእግዚአብሔር.mp3
1.1 MB
#መዝሙር #ሦስትነት_ባለው_በእግዚአብሔር

#በእህታችን #ፋሲካ_ክብሩ

#መሰንቆ #በወንድማችን #ማርቆስ_አለማየሁ

#አጃቢዎች #ወንድሞቻችን #አቤኔዘር እና #ኢዮብ

ሦስትነት ባለው በእግዚአብሔር
ስሙን አምኜ ልዘምር
የመድኃኔዓለም ህማሙን
እንባን በማፍሰስ በሀዘን
እንደ እርሱ ታጋሽ ማንም የለም
ቸሩ አምላካችን መድኃኔዓለም
በጎልጎታ የዓለም ንጉሥ ተንገላታ
አልበደለ እውነተኛው ተሰቀለ ሰጊድ ስብሐት

ድኅነት የሚሰጥ ለፍጥረቱ
የሚገዙለት መላእክቱ
ሁሉን በፍቅር የሚያድነው
ክፉዎች ያዙት ተረባርበው
የሚያዳፉ ውሾች በዙርያው ተሰለፉ
ያለ ዕረፍት አጥንቱ እስኪታይ ገረፉት ሰጊድ ስብሐት

ትዕግስቱ የበዛ ቸርነቱ
የሚመሰገን በፍጥረቱ
ከዓለም ሊያጠፋ የክፋት መርዝ
የአዳምን እዳ ለመሰረዝ
በፈወሰው በጥፊ መታው ያ ክፉ ሰው ሰጊድ ስብሐት

ድኅነትን ሊሰጥ የወደደ
በፍቅር ተስቦ የወረደ
ዘላለማዊ ሚሰጥ ጸጋ
አዳምን ሊያድን ከአለንጋ
ግፍ ባልሰራ እየተነሱ በየተራ
ያለዕረፍት አጥንቱ እስኪታይ ገረፉት ሰጊድ ስብሐት

የሁሉ ንጉሥ የዓለም ፈራጅ
በራሱ ፈቃድ ያለ ግዳጅ
ከነገሠበት ከዙፋኑ
ሰይጣንን ሊጥል ከስልጣኑ
በፍቅር ነፍሱን ሰዋልን ሞት ሊሽር
ይቅር ባይ ተፈጸመ አለ ኤልሻዳይ ሰጊድ ስብሐት

👇👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆👆
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

"...ስቅሎ ስቅሎ..." ማቴ 27:23

በ5534 ዓ.ዓ የዛሬ 2012 ዓ.ም መጋቢት 27 በዕለተ አርብ የፀሐይ አበቅቴ/ጥንተ ኦን/ 7 :የጨረቃ አበቅቴ 14 : መጥቅዕ 16 : ወንበሩ 4: ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ/ዘመነ ማርቆስ/ ዓመቱ 34 :የአይሁድ ፍሥሕ በዋለ ማግስት አይሁድ "ስቅሎ ስቅሎ" በማለት በሲኦል ሆኖ ማዳኑን ለሚጠባበቀው አዳም ድምፅ ይሆኑ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ አፃፍቶ እርሱ ባወቀ አስጩሆ አናገራቸው በመስቀል መሰቀሉ ግድ ነበርና ይሰቀል ብለውም ጮሁ ፡ ምድርም ልተሸከመው የማትችለው የፈጣሪዋ በፍጡር መሰቀሉ ነበርና፡ሰማይንም አስደንቆ መኑ ከመ አምላክ ብለው ተደመው ተገርመው በዚች ቅድስት ቀን አምላክ በፈጠረው ፍጥረት በመስቀል ተሰቅሎ እርቃኑን በእለተ አርብ አዩት ፀሐይ ጨለመች አምላኳ ተሰቅሎ ታይዘንድ አልወደደችምና፡ ከተቸነከሩት እጆቹ እግሮቹ የሚፈሰውን ደም አይታ መቋቋም የተሳናት ጨረቃ ደም መሰለች ፡፡ከዋክብት የሰማዩ ጌጥነታቸው አልፀናም ወደምድር እረገፉ ፡ ፍጥረቱ በሚችሉት መልኩ የአምላክን መከራ በቋንቋቸው ገለጡ መቃብራት ተከፈተና በመሞቱ ህይወት የሰጣቸው ሙታን ለትንሣኤ ዘጉባኤ ምሳሌ ይሆኑ ዘንድ ከሞት አስነስቷቸዋልና ወደ ከተማ ወጥተው ለብዙዎች ታዩ በዚያኛው ወገን ደግሞ ድኅነቱን የሚጠበቀው አዳም ሱባኤ ቆጥሮ ዘመን ቀምሮ የድኅነቱን ቀን የቃልኪዳኑን መፈፀሚያ የአምስት ቀን ተኩል ኪዳን ሲፈፀም እርሱን አለሙን እንዲሁ ያድናልና ድኅነትን ያገኝ ዘንድ ከአምላክ የተሰጠውን ቃልኪዳን በተስፋ ይጠባበቅ ስለነበር በአንድ በኩል አዳም የአምላክ ሞት ያስፈልገዋል ከልጅ ልጅ ተወልጄ አድንሃለው ተብሏልና በመስቀል ተሰቅሎ መሞቱን በሶስተኛውም ቀን ከሞት መነሳቱን የሚሻ በሲኦል ሆኖ አድኅነኒ እግዚኦ ይላል፡፡እግዚአብሔር የፈጠረው ፍጥረት በአንድ በኩል ሞቱን በሌላይኛው በኩል ትህትናው በማሰብ የአምላክን መሰቀል በሁለት መንገድ ሲመለከት የነበረ ፍጥረት ሁሉ አምላክ በመስቀል ላይ በመሰቀሉ በተዋሕዶ አንድ ሆነ የሁሉም ዓይን ወደመስቀሉ ሆነ እርሱም የተስፋው ኪዳን ፍፃሜ ሆነ፡፡ ለዚህም የድኅነት መንገድ ጴላጦስ ሌላይኛው ተሳታፊ ሆነ በፈቃዱ የሚሞተው አምላክ ሞቱ የግድ ነበርና ""የ ወይቤሉ በርባንሃ ። ወይቤሎሙ ጲላጦስ ምንተ እንከ እረስዮ ለኢየሱስ ዘስሙ ክርስቶስ ። ወይቤሉ ኵሎሙ ስቅሎ ። "" ገዢውም መልሶ ፦ ከሁለቱ ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ ? አላቸው ፤ እነርሱም ፦ በርባንን አሉ ። ጲላጦስም ፦ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው ? አላቸው ፤ ሁሉም ፦ ይሰቀል አሉ ።
የማቴዎስ ወንጌል 27:22
ህዝቡ ሁሉ ይህን በማለቱ ክርስቶስን የጎዱ መስሏቸው የአዳምን የተስፋ መንገድ ጠረጉ ከአዳምም ጋር ተባበሩ አዳም በሲኦል ሱባኤ ይቆጥር ስለነበር ከአምላክ ዘንድ የተገባለት ቃል ኪዳን ስላለው ህዝቡ ሁሉ ይሰቀል አሉ የትንቢቱ መፈፀምያ የአዳም ልጇች ናቸውና
"ወይቤሎሙ መልአክ ምንተ እኩየ ገብረ ። ወአፈድፈዱ ጸሪኀ እንዘ ይብሉ ስቅሎ ስቅሎ ። ጲላጦስ ፦ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው ? አላቸው ፤ ሁሉም ፦ ይሰቀል አሉ ።
የማቴዎስ ወንጌል 27:22-23
አባቶችም ስቅለቱ ቀን ዝቅ ካለ <መጋቢት 24 ከፍ ካለ ሚያዚያ 28 >ኢይወረድ ኢየዐርግ ብለው ስርአት ሰሩልን።

እንኳን ለብርሃነ ስቅለቱ በሰላም አደረሰን

…ይቆየን…

#አዘጋጅ #መምህር #ማርቆስ_አለማየሁ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ድንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልና ?
/መኑ ይከሥታ ለነ ለእብን እምኆኅተ መቃብር/
የማርቆስ ወንጌል 16:3

ክርስቶስ ተንስአ እም ሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አጋዝኦ ለአዳም
ሰላም
እም ይዕዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሠላም።

እርዳታን መሻትና የፍቅር አስገብሮት ጎኖ ለጎን የተሰለፉበት ያላንዳች ፍርሃት የጨለማውን ዳፍንት ተጋፍጠው የጠባቂዎች ገዳይነት ሳይበግራቸው በመቃብሩ ደጃፍ የደረሱት ከቅዱሳን አንስት መካከል "፤ ሰንበትም ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም የያዕቆብም እናት ማርያም ሰሎሜ" ነበሩ። ዳሩ ግን ጌታ እራሱ ያስተማራቸውን ትምህርት ዝንጋዬ በሚመስል አኳኀን የትንሣኤውን ትምህርት ከቶም አላስታወሱትም። ያው በመከራ በጭንቅ ያለ የፊት ፊቱን ብቻ ያስታውሳልና እነሆ እነርሱም የጌታን መቃብር ለመክፈት በጌታ መቃብር ደጅ ተገኙ። እንኳንም በዚያ ለሊት ገስግሰው ተገኙ። እነርሱ የትንሣኤውን ብስራት ለዓለም ሊያበስሩ መፍጠንና በዚህ መከራ ውስጥ ማለፍ ነበረባቸው። ነገር ግን ነገረ ትንሣኤውን በመርሳታቸው እንዲህ ብለው ጠየቁ "እርስ በርሳቸውም" ይላል ቅዱስ ማርቆስ በወንጌሉ ሲጽፍ ፦ "ድንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል ? ይባባሉ ነበር።"
የማርቆስ ወንጌል 16:3
የተጨነቁ ሴቶች በበሩ ቆሙ ድንጋዩ በነርሱ አቅም አይነሳምና እንሆ በልቦናቸው የሳሉት አምላካቸው በመቃብር አለ። ሽቱም መነስነስ ፍቅራቸውን ያረሰርሰዋል ግና ሁለት ነገር ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል።
አንደኛው ፡-የመቃብሩ ደጃፍ መከፈት
ሁለተኛው፡-እነርሱ እንዳሰቡት ጌታ በቃብር አለመኖሩ ነው፡፡
በነዚህ ሁለት ነገሮች ከፊት ለፊታቸው የሚጠብቃቸው ሴቶቹ በበር ቆመው የመጀመርያውን ፈተና ለማለፍ እርዳታን ፈልገዋል ነገር ግን ማን እንደሚረዳቸው እራሳቸውን ጠይቀዋል እንጂ ሊራዳቸው የሚችል ሰው አላገኙም ነበር፡፡ ነገር ግን የልብን በጎ መሻት የሚረዳው ጌታ አስቀድሞ የጠየቁትን ጥያቄ መልስ ሰጥቶታል ወንጌላዊው ማርቆስም እንዲህ በማለት ይጽፋል "ድንጋዩ እጅግ ትልቅ ነበርና ፤ አሻቅበውም አይተው ድንጋዩ ተንከባሎ እንደ ነበር ተመለከቱ ። የማርቆስ ወንጌል 16:4
አስቀድመው ተጨንቀው ነበርና መረዳታቸውም ከእግዚአብሔር ነውና ትልቁን ሸክም ተንከባሎ አዩት ነቢዩ እንዳለሁ "፤ አቤቱ፥ እርዳታው ከአንተ ዘንድ የሆነለት፥ በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብ ሰው ምስጉን ነው።" (መዝሙረ ዳዊት 84: 5)
ሰማያዊውን መንገድ በልባቸው ፈልገዋል እና እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ ሲመሰገኑ ይኖራሉ። በዚህም የመጀመሪያውን ከፊታቸው የሚጠብቃቸውን ጉዳይ ተገላገሉ እርሱ ጌታ ተራድቷቸዋልና ፡፡
ሁለተኛው እነርሱ እንዳሰቡት ጌታችን በመቃብር አልነበረም። ወንጌላዊው ይህን ሲያስረዳ "ወደ መቃብሩም ገብተው ነጭ ልብስ የተጐናጸፈ ጕልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ።"
የማርቆስ ወንጌል 16:5
ያም ጎልማሳ መልአክ ነበር። የሚፈልጉት ማንን እንደሆነ ነገራቸው። "አትደንግጡ ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ ፤ ተነሥቷል ፥ በዚህ የለም ፤ እንሆ ፥ ርሱን ያኖሩበት ስፍራ።"
የማርቆስ ወንጌል 16:6
በማለት የምስራቹን ነገራቸው ጌታ እንደተናገረ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል ከሙታን መካከል ተለይቶ ተነስቷል በማለት የትንሣኤውን ብርሃን አበሰራቸው። ሴቶቹም ከጎልማሳው ንግግር እንዲሁም ጌታ በመቃብር አለመኖሩ አስደንግጧቸዋልና ከዚህም የተነሳ ተንቀጠቀጡ። ያም መልአክ አንድ ነገር አስታውሶ ሲገልጥላቸው እንዲህ በማለት ነበር፡፡ "ነገር ግን ፥ ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ለጴጥሮስም ፦ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል ፤ እንደ ነገራችሁ በዚያ ታዩታላችሁ ብላችሁ ንገሯቸው አላቸው።"
የማርቆስ ወንጌል 16:7
በገሊላ እንደሚቀድማቸው በዚሁ ወንጌል እንዲህ ተጠቅሷል
"ነገር ግን ከተነሣሁ በኋላ ወደ ገሊላ እቀድማችኋለሁ አላቸው።"
(የማርቆስ ወንጌል 14: 28)
እንግዲህ ይህ መልአክ ያስታወሳቸው የጌታን የትንሣኤ ትምህርት ነው፡፡
ሌላው የተገለጠው በእጃቸው የነበረው ውድ ለዓለሙ የተላከው ወንጌል ነበር "ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ራሱ ለዘለዓለም ድኅነት የሆነውን የማይለወጠውን ቅዱስ ወንጌል ከፀሓይ መውጫ እስከ መጥለቂያው ድረስ በእጃቸው ላከው።"
የማርቆስ ወንጌል 16:8
ቅዱስ ወንጌሉም በትንሣኤው ብርሃን በዓለም በራ።

…ይቆየን…

#አዘጋጅ #መምህር #ማርቆስ_አለማየሁ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
#ትንሳኤ_በባሕር_ሐሳብ

በመምህር #ማርቆስ_አለማየሁ
(ለ2010 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል የተዘጋጀ)

👇👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆👆
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

በሰሙነ ሕማማት እና በትንሳኤ ሳምንት ምክኒያት ተቋርጠው የነበሩት መንፈሳዊ የኮርስ ትምህርቶቻችን ከነገ ጀምሮ የሚቀጥሉ ይሆናሉ።

ዘውትር ማክሰኞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በመምህር #ማርቆስ_አለማየሁ

ዘውትር ረቡዕ ክብረ ቅዱሳን በወንድማችን #አቤኔዘር

ዘውትር ሀሙስ ትምህርተ ልሳነ ግዕዝ #በመሪጌታ #አምሳለ_አበበ

እንዲሁም የምን እንጠይቅልዎ አምዳችን ዘውትር ቅዳሜ በወንድማችን #ተርቢኖስ_ሰብስቤ የሚቀርብ ይሆናል።
ኢኦተቤ04_1.mp3
791.3 KB
#የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተክርስቲያን_ታሪክ

#ክፍል ሀያ ሁለት

#በመምህር #ማርቆስ አለማየሁ

#ይዘት
👉ምዕራፍ አራት
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከአጼናዖድ በኋላ (በ፰ኛው ሺህ)
ቤተክርስቲያን በዘመነ አጼ ልብነ ድንግል የቤተክርስቲያን ታላቅ ፈተና (የግራኝ ወረራ)

#ከትምህርቱ የተወጣጡ ጥያቄዎች

1 የግራኝ ወረራ ቤተ ክርስቲያናችን ላይ ያደረሰው ተጽዕኖ ምን ነበር?
2 አጼ ልብነ ድንግል ለቤተክርስቲያን ያደረጉት አስተዋጽኦ ምን ነበር?

መልሶቻችሁን እና አስተያየታችሁን
@Abenma እና @Midyam ላይ ያድርሱን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ኢኦተቤ04_2.mp3
1.3 MB
#የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተክርስቲያን_ታሪክ

#ክፍል ሀያ ሦስት

#በመምህር #ማርቆስ አለማየሁ

#ይዘት
👉 ቤተ ክርስቲያን ከአጼ ገላውዴዎስ እስከ አጼ ፋሲል

#ከትምህርቱ የተወጣጡ ጥያቄዎች

1 ቤተ ክርስቲያን በዘመነ አጼ ገላውዴዎስ የገጠማት ችግር ምንድን ነበር?
2 አጼ ፋሲል ለቤተክርስቲያን ያደረጉት አስተዋጽኦ ምን ነበር?

መልሶቻችሁን እና አስተያየታችሁን
@Abenma እና @Midyam ላይ ያድርሱን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ክርስቶስ ተንስአ እም ሙታን.mp3
778.4 KB
#መዝሙር #ክርስቶስ_ተንስአ_እም_ሙታን

#በወንድማችን #ዘማሪ #ሀብታሙ_ሽፈራው

ክርስቶስ ተንስአ እም ሙታን በዐቢይ ኃይል ወስልጣን
አማን በአማን መድኃኒዓለም(2)

መሰንቆ በወንድማችን #ማርቆስ_አለማየሁ
ክራር በዘማሪ #ሀብታሙ_ሽፈራው

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ኢኦተቤ04_2.mp3
1.3 MB
#የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተክርስቲያን_ታሪክ

#ክፍል ሀያ ሦስት

#በመምህር #ማርቆስ አለማየሁ

#ይዘት
👉 ቤተ ክርስቲያን ከአጼ ገላውዴዎስ እስከ አጼ ፋሲል

#ከትምህርቱ የተወጣጡ ጥያቄዎች

1 ቤተ ክርስቲያን በዘመነ አጼ ገላውዴዎስ የገጠማት ችግር ምንድን ነበር?
2 አጼ ፋሲል ለቤተክርስቲያን ያደረጉት አስተዋጽኦ ምን ነበር?

መልሶቻችሁን እና አስተያየታችሁን
@Abenma እና @Midyam ላይ ያድርሱን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ኢኦተቤ04_3.amr
776.1 KB
#የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተክርስቲያን_ታሪክ

#ክፍል ሀያ አራት

#በመምህር #ማርቆስ አለማየሁ

#ይዘት
👉 ቤተ ክርስቲያን በቅብዐት እና ጸጋ ኑፋቄዎች የደረሰባት ፈተናዎች

አስተያየታችሁን
@Midyam ላይ ያድርሱን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
በባተ በ 14 (መጋቢት 14 ቀን) ደብረ ዘይት ይውላል ማለት ነው ፡፡

ሆሣዕና፡- በ2012 ዓ.ም ሆሣዕና የሚውልበትን ዕለት ለማኘት የሆሣዕና ተውሳክ 2 + 4 =6 ሚያዝያ በባተ በ6 (ሚያዝያ 6 ቀን) ሆሣዕና ይውላል፡፡

ስቅለት፡- በ2012 ዓ.ም ስቅለት የሚውልበትን ዕለት ለማግኘት የስቅለት ተውሳክ 7 + 2 መባጀ ሐመር = 9 ሚያዝያ በባተ በ9(ሚያዝያ 9 ቀን) ስቅለት ይውላል፡፡

ትንሣኤ፡- በ2012 ዓ.ም የትንሣኤ ተውሳክ 9 + 2=11 ሚያዝያ በባተ በ11(ሚያዝያ 11) ትንሣኤ ይውላል፡፡

ርክበ ካህናት ፡- በ2012 ዓ.ም ርክበ ካህናት የሚውልበትን ዕለት ለማግኘት (ለማወቅ) የርክበ

ካህናት ተውሳክ 3 +2 መባጀ ሐመር = 5 ግንቦት በባተ በ5 (ግንቦት5ቀን) ርክበ ካህናት ይውላል፡፡

ዕርገት፡- በ2012 ዓ.ም ዕርገት የሚውልበትን ዕለት ለማግኘት (ለማወቅ) የዕርገት ተውሳክ18 +2 መባጀ ሐመር = 20
ግንቦት በባተ በ20 (ግንቦት 20 ቀን ) ዕርገት ይውላል፡፡

ጰራቅሊጦስ፡- በ2012 ዓ.ም ጰራቅሊጦስ የሚውልበትን ዕለት ለማግኘት (ለማወቅ)

የጰራቅሊጦስ ተውሳክ 28 + 2 መባጀ ሐመር = 30

የሰኔ መባቻ ( ግንቦት 30 ቀን ) ጰራቅሊጦስ ይውላል፡፡

ጾመ ሐዋርያት፡- በ2012 ጾመ ሐዋርያት የሚውልበትን ዕለት ለማግኘት (ለማወቅ) የጾመሐዋርያት ተውሳክ 29 +2 መባጀ ሐመር = 31-30 = 1 ሰኔ በባተ በመጀመርያው ቀንሰኔ 1 ቀን ጾመ ሐዋርያት ይውላል፡፡

ጾመ ድኅነት ፡- በ2012 ዓ፣ም ጾመ ድኀነት የሚወልበትን ዕለት ለማግኘት የፆመ ድኅነት

ተውሳክ 1 + መባጀ ሐመር 2= 3

በ3(ሰኔ 3ቀን) ጾመድኅነት ይውላል፡፡

በ2012 ዓ.ም በዘመነ ዮሐንስ የሚውሉ በዓላት አፅዋማትና የሚውሉባቸው ዕለቶች

ጾመ ነቢያት_____________ሕዳር 15
ጾመ ነነዌ ________የካቲት 2
ዐቢይ ጾም_____________ የካቲት 16
ደብረዘይት_____________መጋቢት 13
ሆሣዕና _________ሚያዝያ 4
ስቅለት _________ሚያዝያ 9
ትንሣኤ _________ሚያዝያ 11
ርክበ ካህናት_____________ግንቦት 5
ዕርገት _________ግንቦት 20
ጰራቅሊጦስ _________ግንቦት 30
ጾመሐዋርያት_____________ ሰኔ 1
ጾመድኅነት _________ሰኔ 3
ጾመ ፍልሰታ ________ነሐሴ 1

እነዚህ ከዚህ በላይ የቀረቡ በ2012ዓ.ም በዘመነ ዮሐንስ ያሉ በዓላት አጽዋማት የሚውሉባቸው ዕለታት ሲሆኑ በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ ያለ
ማንኛውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ የሆነ ቀኖና ቤተክርስቲያንን ጠብቆ በዓላትን ለማክበር አፅዋማትን ለመጾም ይጠቅማልና ጠንቅቆማወቅ ከእኛ ይጠበቃል፡፡

አዘጋጅ መምህር #ማርቆስ አለማየሁ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ከዘመናት_በፊት.mp3
1.3 MB
#መዝሙር #ከዘመናት_በፊት

#ወንድማችን #ዳዊት_ክብሩ እና #በእህታችን #ፋሲካ_ክብሩ

#መሰንቆ #በወንድማችን #ማርቆስ_አለማየሁ

#ከዘመናት_በፊት አንተ ነበርህ
ሁሉን አሳልፈህ ትኖራለህ
እም ቅድመ ዘመናት ዘመናዊ
ድኅረ ዘመን አዲስ ኢየሱስ ናዝራዊ

ክብርህ ገናና ነው ባንተ ከብሬአለው
ዘላለማዊ ነህ ባንተ እኖራለው
ከሰልፉ መካከል አለህ ከኔ ጋራ
የሠራዊት ጌታ እጹብ ያንተ ሥራ

ከላይ ከአርያም ከዙፋንህ ግርማ
ቅዱስ አለ ኪሩብ ምስጋናው ተሰማ
ውዳሴ ከበበው መንበሩን ዕልልታ
ባርያህ ላመስግንህ ፍቀድልኝ ጌታ

የአማልክት አምላክ የሚመስልህ የለም
ዓይኔ ያየው ሁሉ ያላንተ አልሆነም
ፍጥረትና ዓለሙ ገንዘብህ ነው
አልፋና ኦሜጋ ይድረስህ ምስጋና

የምድር ኃያላን አይቆሙም ከፊትህ
ይህን ሰራህ ብሎ የለም የሚወቅስህ
ሰማይና ምድርን ፈጥረህ የምትገዛ
እናመልክሀለን የሕይወታችን ቤዛ

👇👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆👆
ከአሥራ አንዱ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በፊት ስለነበረችውና መሥዋተ ኦሪት ይሰዋባት ስለ ነበረችው #መርጦ_ለማርያም ታሪክ ምን ያህል ያውቃሉ???

በቅርብ ቀን በወንድማችን መምህር #ማርቆስ_አለማየሁ ይቀርባል። ይጠብቁን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
አንድ ቀን አለ.mp3
931.8 KB
#መዝሙር #አንድ_ቀን_አለ

#በወንድማችን #ዘማሪ #ሀብታሙ_ሽፈራው

#መሰንቆ #ማርቆስ_አለማየሁ
#ክራር #ሀብታሙ_ሽፈራው

አንድ ቀን አለ የሚያስፈራ
ለጻድቃን የሚያበራ(2)
ጌታ በዚያች ቀን ይመጣል
በክበሩ ይገለጻል(2)
አብረው ከእርሱ ጋር ይመጣሉ
ቅዱሳን መላእክት ሁሉ(2)
ጌታ በዚያች ቀን ይመጣል
በዙፋን ይቀመጣል(2)
የምሕረት አዋጅ ይታወጃል
ነፍስ ሁሉ ይጨነቃል(2)
ኃጥአን ሁሉ ያለቅሳሉ
በግራው ይቆማሉ(2)
ቅዱስ ቃሉን ሰምተው ያመኑ
የጸኑ በኪዳኑ(2)
አብረው በቀኙ ይቆማሉ
ከሀዘን ይሰወራሉ(2)
መኃሪ ጌታ ፈጣሪያችን
ይድረስህ ልመናችን(2)
በዚያ ግሩም ቀን እባክህን
አቁመን በቀኝህ(2)

"በዕለተ ምጽዐት በቀኙ ያቆመን ዘንድ የአምላካችን ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን።"

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ሦስትነት_ባለው_በእግዚአብሔር.mp3
1.1 MB
#መዝሙር #ሦስትነት_ባለው_በእግዚአብሔር

#በእህታችን #ፋሲካ_ክብሩ

#መሰንቆ #በወንድማችን #ማርቆስ_አለማየሁ

#አጃቢዎች #ወንድሞቻችን #አቤኔዘር እና #ኢዮብ

ሦስትነት ባለው በእግዚአብሔር
ስሙን አምኜ ልዘምር
የመድኃኔዓለም ህማሙን
እንባን በማፍሰስ በሀዘን
እንደ እርሱ ታጋሽ ማንም የለም
ቸሩ አምላካችን መድኃኔዓለም
በጎልጎታ የዓለም ንጉሥ ተንገላታ
አልበደለ እውነተኛው ተሰቀለ ሰጊድ ስብሐት

ድኅነት የሚሰጥ ለፍጥረቱ
የሚገዙለት መላእክቱ
ሁሉን በፍቅር የሚያድነው
ክፉዎች ያዙት ተረባርበው
የሚያዳፉ ውሾች በዙርያው ተሰለፉ
ያለ ዕረፍት አጥንቱ እስኪታይ ገረፉት ሰጊድ ስብሐት

ትዕግስቱ የበዛ ቸርነቱ
የሚመሰገን በፍጥረቱ
ከዓለም ሊያጠፋ የክፋት መርዝ
የአዳምን እዳ ለመሰረዝ
በፈወሰው በጥፊ መታው ያ ክፉ ሰው ሰጊድ ስብሐት

ድኅነትን ሊሰጥ የፈቀደ
በፍቅር ተስቦ የወረደ
ዘላለማዊ ሚሰጥ ጸጋ
አዳምን ሊያድን ከአለንጋ
ግፍ ባልሰራ እየተነሱ በየተራ
ያለዕረፍት አጥንቱ እስኪታይ ገረፉት ሰጊድ ስብሐት

የሁሉ ንጉሥ የዓለም ፈራጅ
በራሱ ፈቃድ ያለ ግዳጅ
ከነገሠበት ከዙፋኑ
ሰይጣንን ሊጥል በስልጣኑ
በፍቅር ነፍሱን ሰዋልን ሞት ሊሽር
ይቅር ባይ ተፈጸመ አለ ኤልሻዳይ ሰጊድ ስብሐት

👇👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆👆
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

"...ስቅሎ ስቅሎ..." ማቴ 27:23

በ5534 ዓ.ዓ የዛሬ 2012 ዓ.ም መጋቢት 27 በዕለተ አርብ የፀሐይ አበቅቴ/ጥንተ ኦን/ 7 :የጨረቃ አበቅቴ 14 : መጥቅዕ 16 : ወንበሩ 4: ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ/ዘመነ ማርቆስ/ ዓመቱ 34 :የአይሁድ ፍሥሕ በዋለ ማግስት አይሁድ "ስቅሎ ስቅሎ" በማለት በሲኦል ሆኖ ማዳኑን ለሚጠባበቀው አዳም ድምፅ ይሆኑ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ አፃፍቶ እርሱ ባወቀ አስጩሆ አናገራቸው በመስቀል መሰቀሉ ግድ ነበርና ይሰቀል ብለውም ጮሁ ፡ ምድርም ልተሸከመው የማትችለው የፈጣሪዋ በፍጡር መሰቀሉ ነበርና፡ሰማይንም አስደንቆ መኑ ከመ አምላክ ብለው ተደመው ተገርመው በዚች ቅድስት ቀን አምላክ በፈጠረው ፍጥረት በመስቀል ተሰቅሎ እርቃኑን በእለተ አርብ አዩት ፀሐይ ጨለመች አምላኳ ተሰቅሎ ታይዘንድ አልወደደችምና፡ ከተቸነከሩት እጆቹ እግሮቹ የሚፈሰውን ደም አይታ መቋቋም የተሳናት ጨረቃ ደም መሰለች ፡፡ከዋክብት የሰማዩ ጌጥነታቸው አልፀናም ወደምድር እረገፉ ፡ ፍጥረቱ በሚችሉት መልኩ የአምላክን መከራ በቋንቋቸው ገለጡ መቃብራት ተከፈተና በመሞቱ ህይወት የሰጣቸው ሙታን ለትንሣኤ ዘጉባኤ ምሳሌ ይሆኑ ዘንድ ከሞት አስነስቷቸዋልና ወደ ከተማ ወጥተው ለብዙዎች ታዩ በዚያኛው ወገን ደግሞ ድኅነቱን የሚጠበቀው አዳም ሱባኤ ቆጥሮ ዘመን ቀምሮ የድኅነቱን ቀን የቃልኪዳኑን መፈፀሚያ የአምስት ቀን ተኩል ኪዳን ሲፈፀም እርሱን አለሙን እንዲሁ ያድናልና ድኅነትን ያገኝ ዘንድ ከአምላክ የተሰጠውን ቃልኪዳን በተስፋ ይጠባበቅ ስለነበር በአንድ በኩል አዳም የአምላክ ሞት ያስፈልገዋል ከልጅ ልጅ ተወልጄ አድንሃለው ተብሏልና በመስቀል ተሰቅሎ መሞቱን በሶስተኛውም ቀን ከሞት መነሳቱን የሚሻ በሲኦል ሆኖ አድኅነኒ እግዚኦ ይላል፡፡እግዚአብሔር የፈጠረው ፍጥረት በአንድ በኩል ሞቱን በሌላይኛው በኩል ትህትናው በማሰብ የአምላክን መሰቀል በሁለት መንገድ ሲመለከት የነበረ ፍጥረት ሁሉ አምላክ በመስቀል ላይ በመሰቀሉ በተዋሕዶ አንድ ሆነ የሁሉም ዓይን ወደመስቀሉ ሆነ እርሱም የተስፋው ኪዳን ፍፃሜ ሆነ፡፡ ለዚህም የድኅነት መንገድ ጴላጦስ ሌላይኛው ተሳታፊ ሆነ በፈቃዱ የሚሞተው አምላክ ሞቱ የግድ ነበርና ""የ ወይቤሉ በርባንሃ ። ወይቤሎሙ ጲላጦስ ምንተ እንከ እረስዮ ለኢየሱስ ዘስሙ ክርስቶስ ። ወይቤሉ ኵሎሙ ስቅሎ ። "" ገዢውም መልሶ ፦ ከሁለቱ ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ ? አላቸው ፤ እነርሱም ፦ በርባንን አሉ ። ጲላጦስም ፦ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው ? አላቸው ፤ ሁሉም ፦ ይሰቀል አሉ ።
የማቴዎስ ወንጌል 27:22
ህዝቡ ሁሉ ይህን በማለቱ ክርስቶስን የጎዱ መስሏቸው የአዳምን የተስፋ መንገድ ጠረጉ ከአዳምም ጋር ተባበሩ አዳም በሲኦል ሱባኤ ይቆጥር ስለነበር ከአምላክ ዘንድ የተገባለት ቃል ኪዳን ስላለው ህዝቡ ሁሉ ይሰቀል አሉ የትንቢቱ መፈፀምያ የአዳም ልጇች ናቸውና
"ወይቤሎሙ መልአክ ምንተ እኩየ ገብረ ። ወአፈድፈዱ ጸሪኀ እንዘ ይብሉ ስቅሎ ስቅሎ ። ጲላጦስ ፦ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው ? አላቸው ፤ ሁሉም ፦ ይሰቀል አሉ ።
የማቴዎስ ወንጌል 27:22-23
አባቶችም ስቅለቱ ቀን ዝቅ ካለ <መጋቢት 24 ከፍ ካለ ሚያዚያ 28 >ኢይወረድ ኢየዐርግ ብለው ስርአት ሰሩልን።

እንኳን ለብርሃነ ስቅለቱ በሰላም አደረሰን

…ይቆየን…

#አዘጋጅ #መምህር #ማርቆስ_አለማየሁ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ድንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልና ?
/መኑ ይከሥታ ለነ ለእብን እምኆኅተ መቃብር/
የማርቆስ ወንጌል 16:3

ክርስቶስ ተንስአ እም ሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አጋዝኦ ለአዳም
ሰላም
እም ይዕዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሠላም።

እርዳታን መሻትና የፍቅር አስገብሮት ጎን ለጎን የተሰለፉበት ያላንዳች ፍርሃት የጨለማውን ዳፍንት ተጋፍጠው የጠባቂዎች ገዳይነት ሳይበግራቸው በመቃብሩ ደጃፍ የደረሱት ከቅዱሳን አንስት መካከል "፤ ሰንበትም ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም የያዕቆብም እናት ማርያም ሰሎሜ" ነበሩ። ዳሩ ግን ጌታ እራሱ ያስተማራቸውን ትምህርት ዝንጋዬ በሚመስል አኳኀን የትንሣኤውን ትምህርት ከቶም አላስታወሱትም። ያው በመከራ በጭንቅ ያለ የፊት ፊቱን ብቻ ያስታውሳልና እነሆ እነርሱም የጌታን መቃብር ለመክፈት በጌታ መቃብር ደጅ ተገኙ። እንኳንም በዚያ ለሊት ገስግሰው ተገኙ። እነርሱ የትንሣኤውን ብስራት ለዓለም ሊያበስሩ መፍጠንና በዚህ መከራ ውስጥ ማለፍ ነበረባቸው። ነገር ግን ነገረ ትንሣኤውን በመርሳታቸው እንዲህ ብለው ጠየቁ "እርስ በርሳቸውም" ይላል ቅዱስ ማርቆስ በወንጌሉ ሲጽፍ ፦ "ድንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል ? ይባባሉ ነበር።"