ክብረ ቅዱሳን01_09.amr
853.8 KB
#ክብረ_ቅዱሳን
#ክፍል ዘጠኝ
#በወንድማችን #አቤኔዘር ማሙሸት
#ይዘት
👉 የመንፈሳዊ ተጋድሎ መገለጫዎች
አድማጮች የምትሳተፉበት ጥያቄ
የመንፈሳዊ ተጋድሎ መገለጫዎች ምን ምን ናቸው?
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#ክፍል ዘጠኝ
#በወንድማችን #አቤኔዘር ማሙሸት
#ይዘት
👉 የመንፈሳዊ ተጋድሎ መገለጫዎች
አድማጮች የምትሳተፉበት ጥያቄ
የመንፈሳዊ ተጋድሎ መገለጫዎች ምን ምን ናቸው?
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ክብረ ቅዱሳን01_10.amr
896.2 KB
#ክብረ_ቅዱሳን
#ክፍል አሥር
#በወንድማችን #አቤኔዘር ማሙሸት
#ይዘት
👉 ቅዱሳን በመንፈሳዊ ተጋድሎ መከራን ከማን ይቀበላሉ?
አድማጮች የምትሳተፉበት ጥያቄ
ቅዱሳን በመንፈሳዊ ተጋድሎ መከራን ከማን ከማን እንደሚቀበሉ ዘርዝሩ።
መልስ እና አስተያየት መስጫ
👇👇👇👇👇👇
@Amtcombot

Audio
መዝሙር #ኢያቄም_ወሃና
በዘማሪ #ክብሮም_ግደይ
ክራር #አቤኔዘር_ማሙሸት
ኢያቄም ወሃና እናት አባትሽ
ቤተ እግዚአብሔር ወስደው ስለት የሰጡሽ
መና ከሰማያት የወረደልሽ
እጹብ ድንግል የሆንሽ ማርያም አንቺ ነሽ
ኦ እመ ክርስቶስ ማርያም አንቺ ነሽ(2)
እንኳን ለእመቤታች ቤተ መቅደስ ለገባችበት ቀን (በዓታ ለማርያም) ዓመታዊ ክብረ በዓል በሠላም አደረሳችሁ። መልካም በዓል።

"ክርስቶስን ማመን ብቻ ለመዳን በቂ ነው?"
ክርስቶስ የማዳኑን ሥራ ፈጸመልን። ተዘግቶ የነበረ ገነትን ከፈተልን። ሰው ግን ለመዳን የራሱን ድርሻ የግድ መወጣት አለበት። ክርስቶስ ከፈጸመለት የማዳን ሥራ ሊካፈል ዘንድ ያስፈልጋል። እንዴት ነው የሚካፈለው ሲባል የራሱን ድርሻ በሥራ ተወጥቶ ነው። በነገረ ድኅነት ላይ የእግዚአብሔር ድርሻ አለ። እንዲሁም የሰው ድርሻ አለ። እነዛን ድርሻዎቹን ሰው የግድ ሊፈጽማቸው ይገባል።
"፤ ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ።" ፊልጲ 2: 12 ብሎ ሰው ክርስቶስ ከፈጸመለት የማዳን ሥራ ይካፈል ዘንድ የራሱ ድርሻ እንዳለው ይናገራል። ይሁዳም በመልእክቱ ይሁዳ 1:3 "ወዳጆች ሆይ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን እጽፍላችሁ ዘንድ እጅግ ተግቼ ሳለ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠች ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኳችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።" ከማመን አልፋችሁ ተጋደሉ እያለን ነው ሐዋርያው። ሰው ከአመነ በኋላ የሚጋደለው ይጸድቅ ይድን ዘንድ አይደለምን? ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌ 6:12-18 ላይ በዓለም ሳለን እንጋደል ዘንድ የመከረን ለምንድን ነው? የእምነትን ጋሻ፣ የመንፈስን ሰይፍ ቃለ እግዚአብሔርን እንዲሁም በጸሎት ዘውትር ትጉ ብሎ የተናገረው የሰው ልጅ ይጸድቅ ዘንድ ሥራ ስለሚያስፈልገው አይደል? ሌላ 1ጴጥ 4:18 "ጻድቅም በጭንቅ የሚድን ከሆነ ዓመፀኛውና ኃጢአተኛው ወዴት ይታይ ዘንድ አለው?" በጭንቅ ይድናል ማለት ምን ማለት ነው? ከላይ ከቁጥር 12 ጀምረን ስናነብ እንደ እሳት የሚፈትን መከራን ታገሱ ይለናል። ያ መከራ እንዴት ያለ ነው? እምነት ብቻውን መከራ ሊሆን አይችልም ይልቁንስ እምነቱን ተከትሎ የሚመጣውን መከራ ሁሉ በመታገስ ጽድቅን አድርጉ ነው የሚለው። "ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል።" ሐዋ 14: 21 እንዲል ብዙ መከራ ብሎ ሥራ ለመጽደቃችን አስፈላጊ መሆኑን ይነግረናል። (NB አባቶቻችን በዚህ ኃይለ ቃል መሠረት ነው ስለ መንግሥተ ሰማይ ብለው በገዳም ሆነው ጾመው ጸልየው ድምጸ አራዊቱን ግርማ ሌሊቱን የአጋንንቱን ፈተና ሁሉ ታግሰው ለክብር የበቁት።)
ሌላው በእምነቱ ብቻ ዳነ በማለት ጥጦስን ወይም በጌታችን በቀኝ የተሰቀለውን ወንበዴ ያነሳሉ። ለዚህ መልስ እንዲሆነን ማቴ 20:1—17 ያለውን ታሪክ መመልከት በቂ ይመስለኛል። መንግሥተ ሰማያት በወይን እርሻ ተመስላለች። ሰዎች ከ3 ሰአት ጀምሮ መጥተው ሰሩ። አሥራ አንደኛውም ሰአት ተቀጥረው የሰሩ አሉ። እንደው ምሳሌው እንኳን ሥራ ውጣ ውረድ መሆኑን ልብ እናድርግ። ታዲያ 11ኛ ሰዓት ላይ ለመጡትም ጭምር የተከፈላቸው ክፍያ እኩል ነው። ጥጦስም በመስቀል ሳለ ያነባው እንባ የገባው ንስሐ የተሰበረው ልቡ ከእምነቱ ጋር ከሥራ ተቆጥሮለት ድኗል።
በማቴ 19:16 ላይ ሀብታሙ ሰውዬ ጌታችንን እጸድቅ ዘንድ ምን ላርግ ሲለው ክርስቶስ የመለሰለት መልስ ምንድን ነው ሕግጋትን ፈጽም አለው። ሕግጋትን መፈጸም ራሱ ሥራ መሆኑን ልብ እናድርግ። ደፋሩ ሀብታም በትዕቢት ፈጽሜአለው ሲል ክርስቶስ ምን ሲል መለሰለት "ኢየሱስም። ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ አለው። ጐበዙም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነ ሄደ። ኢየሱስም ለደቀ መዛሙርቱ። እውነት እላችኋለሁ፥ ለባለጠጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ጭንቅ ነው።" ማቴ 19:21—23 ወንጌሉ ግልጽ ነው። ሀብታም ሆኖ መመጽወት ካልቻለ አይጸድቅም ማለት ነው። መመጽወት የማያጸድቅ ቢሆን ኖሮ ጌታችን ይህን ባልተናገረ ነበር። ሰው ከእምነቱም በተጨማሪ ፍጹም ይሆን ዘንድ ሥራ የግድ ያስፈልገዋል። ያዕ 1:4 "ፍጹማን እና ምሉአን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ፈጽሙ።" እንዲል።
ሌላ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ላይ ጌታችን ጹሙ፣ ጸልዩ፣ መጽውቱ እያለ አስተምሯል። ይህ ሥራችን በጎ ሥራ ማድረግ ብቻ ከመሆኑም በተጨማሪ ግንኙነቱ ቀጥታ ከሰማይ ጽድቅ ጋር መሆኑን እና ክፍያው ሰማያዊ መሆኑን ጭምር ይናገራል። ለዚህ ነው "ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ።" ማቴ 6: 20 ከእምነት በተጨማሪ የምንሰራቸው ሥራዎች በሰማይ መዝገብ ተመዝግበው ያጸድቁናል። ያልሰራናቸው ሥራዎች ወይም የሰራናቸው መጥፎ ሥራዎች ያስኮንኑናል። "እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። " ራእይ 22: 12 በሌላም ቦታ "ለእያንዳንዱ እንደየሥራው መጠን ተከፈለው።" ራዕይ 20:13 ሰው በእምነቱ ብቻ ቢጸድቅ ኖሮ እንደ ሥራው ይከፈለዋል የሚለውን ቃል እንዴት እናድርገው? በአጭሩ ሰው በእምነቱ ብቻ ይጸድቃል የሚባል ከሆነ አሁንም ጌታችን በፍርድ ቀን ለምን ሥራን ሰርታችኋል ወይ ብሎ ይጠይቀናል? ሌሎቹንስ ለምን አልሰራችሁም ይላቸዋል? ሚገርመውኮ አላውቃችሁም ያላቸው እምነት ያላቸውን ሰዎች ጭምር ነው። ማቴ 25:34–46 ነገር ግን ሰው በእምነቱ ብቻ ስለማይጸድቅ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ በማያሻማ ቃል የተናገረውን ልጥቀስና ላብቃ "፤ ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?" ያዕ 2: 14
አዘጋጅ #አቤኔዘር_ማሙሸት

በአማላጅና በመማጸኛ መካከል ያለውን ልዩነት ያውቃሉ?
ክፍል -2
በአማላጅና በመማጸኛ መካከል ያለው ትልቅ ልዩነት አማላጅ ህልውና ያለው አካል ብቻ ሲሆን ከዚህ ቀደም እንደገለጽነው መማጸኛ ደግሞ ህልውና ያለውም የሌለውም ሊሆን መቻሉ ነው።
አማላጅን ፣ መማጸኛን እና ተማላጅን በግልጽ እንድንረዳቸው የሚከተለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እንደ ምሳሌ እንመልከት።
ዘጸ 32÷1-14
በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ሙሴ አማላጅ እግዚአብሔር ደግሞ ተማላጅ (ተለማኝ ፣ ታራቂ፣ ይቅር ባይና ፈራጅ) ሆኖ ስመ አብርሃም ይስሐቅ እስራኤል የተባለ ያዕቆብ ደግሞ መማጸኛ ሆነው ቀርበዋል።
ታሪኩ እንዲህ ነው። እግዚአብሔር አምላክ እስራኤል ዘሥጋን ከግብጽ ባርነት በዘጠኝ ታላላቅ ተዓምራት በአሥረኛ ሞተ በኩር (የግብጽን ሰዎች የበኩር ልጆቻቸውን ገድሎ) በአሥራ አንደኛ ስጥመተ ባህር (ጠላቶቻቸውን በኤርትራ ባሕር አስጥሞ) ነጻ ቢያወጣቸው እነርሱ ግን እግዚአብሔርን ክደው ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስል ጣዖትን ለራሳቸው አደረጉ። ሰዉለት፣ ሰገዱለት አልፎም ተርፎ ነጻ ያወጣቸውን እግዚአብሔርን ረስተው ከግብጽ ባርነት ነጻ ያወጡን እነዚህ አማልክት ናቸው አሉ።
የእግዚአብሔርም ቁጣ በህዝቡ ላይ በነደደና ሊያጠፋቸው በተናገረ ጊዜ ግን የተመረጠው ሙሴ በመቅሰፍት ሰዓት በእግዚአብሔር ፊት ስለ እነርሱ ቆሞ ማማለድና ይቅር ይላቸው ዘንድ መለመን ጀመረ። መዝ 105÷23
የምልጃ ቃሉም መማጸኛን እየተጠቀመ ነበር።
"ሙሴም በእግዚአብሔር በአምላኩ ፊት ጸለየ ፥ አለም፦ አቤቱ ፥ ቍጣህ በታላቅ ኃይልና በጽኑ እጅ ከግብፅ ምድር ባወጣኸው በሕዝብህ ላይ ስለ ምን ተቃጠለ? ግብፃውያንስ፦ በተራራ መካከል ሊገድላቸው፥ ከምድርም ፊት ሊያጠፋቸው ለክፋት አወጣቸው ብለው ስለ ምን ይናገራሉ? ከመዓትህ ተመለስ ፥ ለሕዝብህም በክፋታቸው ላይ ራራ። ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ ይህችንም የተናገርኋትን ምድር ሁሉ ለዘራችሁ እሰጣታለሁ፥ ለዘላለምም ይወርሱአታል ብለህ በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህን #አብርሃምንና #ይስሐቅን #እስራኤልንም አስብ። እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ሊያደርግ ስላሰበው ክፋት ራራ።" ዘጸ 32÷12-14
እንደተመለከትነው እስራኤል ዘሥጋ ስለፈጸሙት ገቢረ ኃጢአት ሙሴ ስለ እነርሱ አማልዷል። በምልጃው ወቅት የተጠቀማቸው መማጸኛዎች እግዚአብሔር ለአብርሃም ፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የገባላቸውን ቃልኪዳን ነው። ስለ እነርሱ ብለህ ማራቸው ይቅር በላቸው የሚለው የሙሴ የምልጃ ጸሎት ቅዱሳኑን መማጸኛ አሰኝቷቸዋል። በአንጻሩ ደግሞ ሙሴ የእስራኤል ዘሥጋ አማላጃቸው ነው።
አማላጅ የግድ ህልውና ሊኖረው ይገባል። ዛሬ የፕሮቴስታንቱ ዓለም እንደሚያወራው ሲያሻው ክርስቶስን "አማላጄ" ሲለው (ሎቱ ስብሐት) ሲያሻው የፈሰሰው የክርስቶስ ደም እያማለደኝ ይኖራል እያለ የተምታታና ግራ የገባ ዕምነት ያራምዳል።
እርሱንም ሆነ የፈሰሰውን ደሙን መማጸኛ እንጂ አማላጅ እንድናደርጋቸው አልተፈቀደልንም። ይልቅ ቅዱሳኑ እንዲያማልዱን እነርሱንም መማጸኛ አድርገን እንድንጠቀም የታዘዝነው። "የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደ ቅዱሳን ጆሮዎቹም ወደ ልመናቸው ነው።" መዝ 33(34)÷15 ፣ 1ጴጥ 3÷12 እንዲል የእነርሱ የተሰሚነት ጸሎት የተሻለ ነውና እነርሱ ሊያማልዱን ይገባል። አልያም በእነርሱ ስም ብንማጸነው ስለገባላቸው ቃል ኪዳን ብሎ ከጭንቅ ፣ ከመከራ ፣ ከተቃጣው መዐት ፣ ከመጣው ቁጣና መቅሰፍት በቸርነቱ ያድነናል። ስለ አብርሃም ስለ ይስሐቅ ስለ ያዕቆብ ብሎ ጣዖት ላመለኩ እስራኤል ዘሥጋ ከራራላቸው በስሙ ላመንን የልጅነት ሥልጣል ለተሰጠን ከአብርሃም ከይስሐቅ ከያዕቆብ የምትበልጥ እናት እመቤታችን ላለችን ለኛ እስራኤል ዘነፍሥ ስለ እናትህ ብለህ ማረን ብንለው እንዴት አይምረንም???
ይቆየን።
ይቀጥላል…

ብስራተ ገብርኤል
ገብርኤል ማለት የአምላክ አገልጋይ ማለት ነው። አባቶች ሊቃውንት ገብርኤል የሚለውን ስም ገብር (አገልጋይ፣ ሰው) ኤል አምላክ በአንድ ላይ አምላክ ወሰብ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ የሚል ነገረ ሥጋዌውን የሚያወሳ ስመ ትርጓሜ ሰጥተውታል።
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዓለመ መላእክት አምላካቸውን በመፈለግ በታወኩ ጊዜ "ንቁም በበ ህላዌነ እስክ ንረክቦ ለእግዚእነ ወአኅድኦሙ መልአክ ሰላም ገብርኤል በቃሉ ለሠራዊተ መላእክት መንፈሳዊያን። ዛሬ መልካም ጎልማሳ ጦር ሲፈታ ድል ሲመታ አይቶ አይዞህ በያለህበት ቁም ብሎ ጦሩን እንዲያጸና እንዲያራጋጋ ሁሉ ቅዱስ ገብርኤልም በመላእክት ሽብር ሲጸናባቸው ባየ ጊዜ አይዟችሁ ፈጣሪያችን ፈጥሮ አይጥለንምና እስክናገኘው እስክናውቀው ድረስ በያለንበት እንቁም ብሎ አጸናቸው አረጋጋቸው።" በዚህም መላእክት የቅዱስ ገብርኤልን ቃል ሰምተው በያሉበት ጸንተው ቆመዋል።
ይህ አጽናኝ መልአክ ጥንት ዓለመ መላእክትን እንዳጸናቸው የዘመኑ ፍጻሜ ሲደርስ ደግሞ እግዚአብሔር ለአዳም የገባውን ቃል ኪዳን በመፈጽም ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ፍጹም ሰው በመሆን ዓለሙን እንዲያድን የብስራቱን ዜና ለሰው ልጆች እንዲያበስር ወደ እመቤታችን ተላከ።
ይህ ብስራታዊ መልአክ ከስድስት ወር በፊት በመወለዱ ብዙዎች ደስ የሚሰኙበት የጌታን መንገድ የሚጠርግ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እንደሚወለድ ለካህኑ ዘካርያስ አብስሮት ነበር። ከስድስት ወር በኋላ ደግሞ እመቤታችንን አብስሯታል።
እስኪ እነዚህን ሁለት ብስራቶች እንመልከት።
መልአኩ የብስራቱን ዜና ለካህኑ ሲያበስረው "ይህ እንዴት ይሆናል? እኔ አርጅቻለው። ሚስቴም ሙቀት ልምላሜ ተለይቷታል።" በማለት ተቃውሞታል። መልአኩም "አኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው መልአኩ ገብርኤል ነኝ። የነገርኩህን አላመንክምና ሕፃኑ እስኪወለድ ድረስ ዲዳ ትሆናለህ።" በማለት መልአኩ ለእግዚአብሔር ቀንቶ ካህኑን ቀጥቶታል። በአንጻሩ እመቤታችንን በሚያበስራት ጊዜ እርሷም "ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል?" የሚል ጥያቄ ጠይቃው ነበር። መልአኩም ካህኑ ዘካርያስን እንደቀጸፈው እርሷን ግን ሊቀስፋት አልደፈረም። ይልቁንም የዘመዷ ኤልሳቤጥ ከሸመገለች ካረጀች የመውለጃ ጊዜዋ ካለፈ በዋላ የመጸነሷን ማስረጃ ማቅረብ ተያያዛ። በስተ መጨረሻም "እስመ አልቦ ነገር ዘይስሀኖ ለእግዚአብሔር። ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም።" ብሎ ሲረታት እርሷም "ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ። እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ይደረግልኝ።" በማለት የብስራቱን ዜና ተቀበለች። በዚህች ቅስፈት ከሦስቱ አካል አንዱ አካል ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ እግዚአብሔር ወልድ ከሰማያት ወርዶ በድንግል ማኅጸን አደረ። የአዳም የድኅነቱ መንገድም እነሆ ተጀመረ። ይህም የሆነው በመጋቢት 29 ቀን ነው። አባቶች በቀኖና በዓሉን ታኅሳስ 22 እንዲከበር አውጀዋል።
ከመልአኩ ከቅዱስ ገብርኤል ከእናታችን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት በረከት ይክፈለን።
መልካም በዓል።

መዝሙር - #በህበረት
#አማን_በአማን
አማን በአማን(2) ተክለሃይማኖት(2)
ተወለዱልን
የሁላችን መሪ የሃይማኖት አባት(2)
የማናውቅ እንወቅ ናቸው ተክለሃይማኖት
ጻድቁ ተወልደው በዚህች ዓለም ላይ(2)
ባለሟሉ ሆኑ የአምላክ አዶናይ
የጻድቅ ሰው ጸሎት ተሰሚ ነውና(2)
እንማጸናቸው በንጹህ ልቦና
መሰንቆ #ሀብታሙ_ሽፈራው
ክራር #አቤኔዘር_ማሙሸት
እንኳን ለብጹዕ አባታችን ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ ልደት በሠላም አደረሳችሁ። በዓሉ በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ይከበራል። እርሶም በቦታው በመገኘት ከጻድቁ ረድኤት በረከት ትካፈሉ ዘንድ በአምላከ ተክለሃይማኖት ስም ተጋብዘዋል።

ኃጢአትን ለካህን መናዘዝ ተገቢ ነውን? ኑዛዜ በመጽሐፍ ቅዱስ የተፈቀደ ነው ወይስ ኑዛዜ አያስፈልግም?
ኑዛዜ በመጽሐፍ ቅዱስ
† የሰው ልጅ ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ ለሠራው ኃጢአት ቅጣቱን ይቀበላል። የሠራውን ኃጢአት በንስሐ አባቱ ፊት እየተናዘዝ በካህኑ ፊት መገረፍ በራሱ ቅጣት ነው። ይህም ሰውዬው ዳግመኛም የካህኑን ፊት ማየት በማፈር እንደዛ ያለ ኃጢአትን እንዳይፈጽም ይረዳዋል። ኑዛዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ከጥንት ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ ሲተገበር የነበረ እና በሐዲስ ኪዳንም ተጠናክሮ የቀጠለ ንስሐን የመፈጸሚያ ሥርአት ነው።
የተወሰኑ ማስረጃዎችን እንመልከት እስኪ…
✔ ኃጢአትን አምኖ ለካህን መናዘዝ ለእግዚአብሔር መናዘዝ ነው። ኢያ 7:19 "ኢያሱም አካንን ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጥ ለእርሱም ተናዘዝ ያደረከውንም ንገረኝ አትሸሽገኝ አለው።" በዚህም መሠረት ካህናት ዐእይንተ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር ዐይኖች) ተብለው ይጠራሉ
✔ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት የንስሐ ጥምቀትን በሚያጠምቅ ጊዜ የሰሩትን ኃጢያት ይናዘዙ ነበር። ማቴ 3:5 "ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ ይጠመቁ ነበር።" ኑዛዜ ተገቢ በመሆኑ ዮሐንስ መጥምቅ እያናዘዛቸው የንስሐን ጥምቀት አጠመቃቸው። ማር 1:5
✔ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማሰር፣ የመፍታት እንዲሁም ኑዛዜን የመቀበል ጸጋን ለካህናት ሰጥቷቸዋል። ሉቃ 5:14 ማቴ 18:18 በምድር የፈቱት በሰማይ የተፈታ የሚሆነው ካህኑ የኑዛዜውን ቃል ተቀበለው ለሰውዬው የሰጡትን ቀኖና መፈጸሙን ካዩ በኋላ "እግዚአብሔር ይፍታህ" በሚለው የክህነት ሥልጣናቸው ነው።
✔ ሐዋርያት አባቶቻችንም ኑዛዜን በመፈጸም ኃጢአታችን እንደሚሰረይ አስተምረውናል። ያዕ 5:15–16 "እርስ በእርሳችሁ ኃጢአታችሁን ተናዘዙ።" እንዲል በዚህ ቃል መሠረትም ኃጢአትን ለካህን መናዘዝ ተገቢ ያደርገዋል። እርስ በእርስ መባሉ እንዴት ነው ቢሉ አንደኛ ካህኑ በሥልጣን ይብለጠን እንጂ እንደኛው ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ ከሦስቱ ባሕርያተ ነፍስ የተፈጠረ ሰው በመሆኑ እርስ በእርሳችሁ ተባለ። አንድም ካህንም ቢሆን የበደለውን በደል ለሌላ ካህን (ለንስሐ አባቱ) ይናዘዝ ዘንድ የሚያስገድድ ነው። ሀኪም ሲያመው ሌላ ሀኪም እንዲያክመው እንዲሁ ካህንም የራሱ መምህረ ንስሐ አለውና እርስ በእርስ ኃጢአታችሁን ተናዘዙ ተብሏል።
☞ በመሆኑም ኃጢአትን ለንስሐ አባታችን መናዘዝ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። ሌሎች እንደሚሉት ከተጸጸትን በቂ ነው እርሱ የልብን ያውቃል መናዘዝ ለእግዚአብሔር ብቻ ነው… በሚል ራስን ኃጢአት የሚያለማምድና ከንስሐ የሚያርቅ ኢ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮችን ልንቃወም ያስፈልጋል። ኃጢአታችንን ለንስሐ አባታችን ተናዘን በንስሐ ሳሙና ታጥበን የንስሐ ፍሬን አፍርተን አዲስ ሰው እንድንሆን አምላካችን በቸርነቱ ይርዳን።
ይቆየን!
በወንድማችን #አቤኔዘር ማሙሸት

#መዝሙር #ተፈነወ
#በሕብረት
#መሰንቆ #ሀብታሙ_ሽፈራው
#ክራር #አቤኔዘር_ማሙሸት
#ከበሮ #ዮሴፍ_ዘለቀ
ተፈነወ(2) ሀገረ ገሊላ
ሀገረ ገሊላ(4) እንተ ስማ(2) ናዝሬት ሀረገ ገሊላ
ትርጉም:
ስሟ ናዝሬት ወደምትባለው ወደ ገሊላ ሀገር ሄደ
አንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት ከተራ በሠላም አደረሳችሁ። በዚህ ቀን ጌታችን ይጠመቅ ዘንድ ከገሊላ ወደ ዮሐንስ መሄዱ የሚዘከርበት የሚታሰብበት ቀን ነው። በዚህም ምሳሌነት በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ አድባራትና ገዳማት ታቦተ ሕግጋቱን ከመንበራቸው አውጥተው ወደ ዮርዳኖስ ምሳሌ ወደ ሚሆን የተከተረ ውኃ ወዳለበት ጥምቀተ ባህር ይወርዳሉ። ሀገሩን ሁሉ ይባርካሉ።
መልካም የከተራ በዓል።

#መዝሙር #በሕብረት
#መሰንቆ
#ሀብታሙ_ሽፈራው
#ክራር
#አቤኔዘር_ማሙሸት
#ከበሮ
#ዮሴፍ_ዘለቀ
#ፈለገ_ዮርዳኖስ
ፈለገ ዮርዳኖስ የእመነታችም ጣዕሙ
ለክርስቲያን ሁሉ አንቺ ነሽ መቅድሙ
ቅድስት(3) ዮርዳኖስ ሆይ የጌታ ሀገሩ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ባንቺ ላይ አደሩ(2)
#በጥምቀት
👉 በጥምቀት መዳንን አገኘን። ማር 16:16 1ጴጥ 3:21
👉 በጥምቀት ዳግም ከመንፈስ ቅዱስ ተወልደን ልጅነትን አገኘን። ዮሐ 3:5
👉 በጥምቀት የመንግሥቱ ዜጎች ሆንን። ዮሐ 3:5
👉 በጥምቀት ሥርይተ ኃጢአትን አገኘን። ሐዋ 2:35
👉 በጥምቀት የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተካፋዮች ሆንን። ሐዋ 8:16
በጥምቀት የቤተ ክርስቲያን ዓባላት ሆንን (ክርስቲያኖች ሆንን)።
👉 በጥምቀት ፈጣሪያችን ክርስቶስን ለበስነው። ገላ 3:27
በጥምቀት ፈጣሪያችንን በሞቱ እና በትንሳኤው መሰልነው። ሮሜ 6:4
መልካም የጥምቀት በዓል።

#መዝሙር #ድንግል_ሆይ_ስለ_አንቺ
#በወንድማችን #ዳዊት_ክብሩ
#ክራር #አቤኔዘር_ማሙሸት
ድንግል ሆይ ስለ አንቺ ነውና መሐሪ
አማልጅን ከአንድ ልጅሽ ከፈጣሪ
ስሙን እንዳልጠራ አንደበትም የለኝ
ፊቱንም እንዳላይ ሥራዬ አስቸገረኝ
ታውቆኛል ጥፋቴ ብዙ እንደበደልኩኝ
ትእዛዙን እንደሻርኩ ሕጉን እንደጣስኩኝ
በፊቱ እንዳላፍር የተጠራሁ ለታ
እለምነዋለሁ ከአሁኑ ይቅርታ
አንተ ክቡር መልአክ ልደቱን አብሣሪ
አማልደን ከጌታዬ ከፈጣሪ
ጻድቃን ሰማእታት እናንተ ሁላችሁ
አማልዱኝ ከአምላኬ ከአምላካችሁ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
#በወንድማችን #ዳዊት_ክብሩ
#ክራር #አቤኔዘር_ማሙሸት
ድንግል ሆይ ስለ አንቺ ነውና መሐሪ
አማልጅን ከአንድ ልጅሽ ከፈጣሪ
ስሙን እንዳልጠራ አንደበትም የለኝ
ፊቱንም እንዳላይ ሥራዬ አስቸገረኝ
ታውቆኛል ጥፋቴ ብዙ እንደበደልኩኝ
ትእዛዙን እንደሻርኩ ሕጉን እንደጣስኩኝ
በፊቱ እንዳላፍር የተጠራሁ ለታ
እለምነዋለሁ ከአሁኑ ይቅርታ
አንተ ክቡር መልአክ ልደቱን አብሣሪ
አማልደን ከጌታዬ ከፈጣሪ
ጻድቃን ሰማእታት እናንተ ሁላችሁ
አማልዱኝ ከአምላኬ ከአምላካችሁ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
Audio
#ውይይት
#በእንተ_መጻጉዕ
በወንድሞቻችን
#ኢዮብ_ክንፈ
#ተርቢኖስ_ሰብስቤ (ምንዳዬ)
#አቤኔዘር_ማሙሸት
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#በእንተ_መጻጉዕ
በወንድሞቻችን
#ኢዮብ_ክንፈ
#ተርቢኖስ_ሰብስቤ (ምንዳዬ)
#አቤኔዘር_ማሙሸት
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
ውይይት
#በእንተ_ኒቆዲሞስ
በወንድሞቻችን
#አቤኔዘር_ማሙሸት
#ኢዮብ_ክንፈ
#ቡሩክ_መልሳቸው
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#በእንተ_ኒቆዲሞስ
በወንድሞቻችን
#አቤኔዘር_ማሙሸት
#ኢዮብ_ክንፈ
#ቡሩክ_መልሳቸው
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ሰላምሽ ዛሬ ነው
<unknown>
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴
🌴እንኳን ለበዓለ ሆሳዕና በሰላም🌴
🌴አደረሳችሁ።🌴
🌴 #መዝሙር #ሰላምሽ_ዛሬ_ነው 🌴
🌴#በወንድማችን #ዳዊት_ክብሩ🌴
🌴#መሰንቆ #በወንድማችን
#ሀብታሙ_ሽፈራው
🌴#ክራር #በወንድማችን
#አቤኔዘር_ማሙሸት
ሰላምሽ ዛሬ ነው ኢየሩሳሌም
ወደአንች መጥቷልና አምላክ ዘላአለም/2/
ሆሳዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ
ሕፃናት በኢየሩሳሌም
አንቺ ቤተልሄም የዳዊት ከተማ/2/
የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/2
ኪሩቤል መንበሩን የሚሸከሙለት/2/
መስቀል ተሸከመ ሊሆነን መድኃኒት /2/
የኢየሱስን ሕማም ደናግልም አይተው/2/
እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው/2/
ሆሳዕና እያሉ አመሰገኑት
በኢየሩሳሌም አእሩግ ሕፃናት/2/
🌴 @AwediMeherit 🌴
🌴 @AwediMeherit 🌴
🌴 @AwediMeherit 🌴
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴
🌴እንኳን ለበዓለ ሆሳዕና በሰላም🌴
🌴አደረሳችሁ።🌴
🌴 #መዝሙር #ሰላምሽ_ዛሬ_ነው 🌴
🌴#በወንድማችን #ዳዊት_ክብሩ🌴
🌴#መሰንቆ #በወንድማችን
#ሀብታሙ_ሽፈራው
🌴#ክራር #በወንድማችን
#አቤኔዘር_ማሙሸት
ሰላምሽ ዛሬ ነው ኢየሩሳሌም
ወደአንች መጥቷልና አምላክ ዘላአለም/2/
ሆሳዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ
ሕፃናት በኢየሩሳሌም
አንቺ ቤተልሄም የዳዊት ከተማ/2/
የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/2
ኪሩቤል መንበሩን የሚሸከሙለት/2/
መስቀል ተሸከመ ሊሆነን መድኃኒት /2/
የኢየሱስን ሕማም ደናግልም አይተው/2/
እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው/2/
ሆሳዕና እያሉ አመሰገኑት
በኢየሩሳሌም አእሩግ ሕፃናት/2/
🌴 @AwediMeherit 🌴
🌴 @AwediMeherit 🌴
🌴 @AwediMeherit 🌴
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴
#በኩረ_ሙታን_ወትንሳኤ
#ክፍል ሁለት
ክርስቶስ ተንስዓ ሙታን
በአቢይ ኃይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለዓዳም
ሰላም
እምይዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም
የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት ልጆች የቅዱሳን ወዳጆች እንደምን ቆያችሁ?
አሜን የትንሳኤያችን በኩር አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባሕሪይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብ ከባሕሪይ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋር ዛሬም ዘውትርም እስከ ዘለዓለም ድረስ በፍጥረቱ አንደበት የከበረ የተመሰገነ ይሁን፡፡
በመጀመሪያው ጽሑፋችን ክርስቶስ በኩር እንዲሁም በኩረ ሙታን የተባለበትን ምክኒያት በሰፊው ተመልክተን ነበር፡፡ ለዛሬ ደግሞ ክርስቶስ በኩረ ትንሳኤ የተባለበትን ምክኒያት እንመለከታለን፡፡
ትንሳኤ ማለት ‹‹ተንስአ›› ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ከሙታን ተለይቶ መነሳት ማለት ነው፡፡ ክርስቶስ በኩረ ትንሳኤ ነው ማለት ከሙታን ተለይቶ ለመነሳት ቀዳሚ የመጀመሪያ ነው ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ከክርስቶስ በፊት ከሙታን ተለይቶ የተነሳ የለም ማለት ግን አይደለም፡፡ ታዲያ ስለምን በኩረ ትንሳኤ ተባለ ቢሉ አባቶች ስለ ሁለት ምክኒያት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡
፩. ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው በሥልጣኑ በመሆኑ ነው፡፡ ሌሎች ከሙታን ተለይተው ቢነሱ ለእነርሱ አስነሺ አካል አላቸው፡፡ ለምሳሌ በዮሐ 11፡11-44 ስንመለከት ከሞተ አራት ቀን የሆነውን አልአዛርን ጌታችን ከሞት እንዳስነሳው እንመለከታለን፡፡ አልአዛር ከሞት የተነሳው በራሱ ስልጣን አይደለም፡፡ ይልቁንስ ለመነሳቱ ሌላ አስነሺ አካል አስፈልጎታል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲነሳ ግን ለእርሱ አስነሺ አካል አላስፈለገውም በስልጣኑ ተነሳ እንጂ፡፡ ነገር ግን በሐዋ 3፡15 ላይ ‹‹እግዚአብሔር ከሙታን አስነሳው፡፡›› ተብሎ ተጽፎ እናገኛለን፡፡ ይህ ቃል ለክርስቶስ ሌላ አስነሺ አካል አለው አልያም በስልጣኑ አልተነሳም ለማለት አይደለም፡፡ በመሰረቱ ክርስቶስ ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ዮሐ 1፡3 ዮሐ 5፡17 ታዲያ እግዚአብሔር አስነሳው ቢባል መለኮትነቱ በሥልጣኑ አስነሳው ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ራሱን በራሱ ማክበር ልማዱ እንደሆነ እንዲሁ እግዚአብሔር አስነሳው ቢባል መለኮትነቱ በስልጣኑ አስነሳው ማለት ነው፡፡ ጌታችን ሳይሞት ከሙታን ተለይቶ የሚነሳው በራሱ ስልጣን፤ ሌላ አስነሺ አካልም አንደማያስፈልገው በዮሐ 2፡19 ላይ ‹‹ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስት ቀንም አስነሳዋለው ፡፡›› ብሏል፡፡ መቅደስ የተባለው የራሱን ሰውነት እንደሆነም ቁጥር 21 ላይ ይመሰክራል፡፡ ከሙታን ከተነሳም በኋላ ሐዋርያት ይህን ቃል አስታውሰውት ነበር፡፡ ዮሐ 2፡22 በመሆኑም በዚህ ምክኒያት ክርስቶስ በኩረ ትንሳኤ ይባላል፡፡
፪. ሁለተኛው ምክኒያት ክርስቶስ ስለ ምን በኩረ ትንሳኤ ተባለ ቢሉ ሌሎች ቢነሱ የሥጋ ሞት ዳግመኛ ያገኛቸዋል፡፡ ክርስቶስ ግን ሞትን ድል አደርጎ ሲነሳ ሞት ዳግመኛ አያገኘውምና በኩረ ትንሳኤ ተብሏል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ መልዕክቱ 1ኛቆሮ 15፡55 ላይ ‹‹ሞት ሆይ መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል ሆይ ድል መንሳትህ ወዴት አለ?›› እንዲል፡፡
ስለዚህ ከላይ ባነሳናቸው ሁለት ምክኒያቶች አንደኛው ክርስቶስ ሲነሳ ለእርሱ አስነሺ አካል እንዳላስፈለገው ይልቁኑ በራሱ ኃይል እና ስልጣን በመነሳቱ እንዲሁም ዳግመኛ የሥጋ ሞት ክርስቶስን ስለማያገኘው ክርስቶስ በኩረ ትንሳኤ ተብሏል፡፡ መልካም ዘመነ ትንሳኤ ይሁንልን፡፡
የልዑል እግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳኑ ተራዳኢነት አይለየን፡፡ ይቆየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአሥራት የቃልኪዳን ልጆች የቅዱሳን ወዳጆች እንደምን ቆያችሁ?
አሜን በቸርነቱ እስከዚህች ሰዓት ያደረሰን የአባቶቻችን የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን፡፡
በዛሬው በምን እንጠይቅልዎ አምዳችን የደረሰንን የዶግማ ጥያቄ እንደሚከተለው እንመልሳለን፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ‹‹ሥላሴ›› የሚል ቃል ተጽፎ እናገኛለን ወይ የሚል ሲሆን መልሱም አዎ በሚገባ ተጽፎ እናገኛለን የሚል ነው፡፡
ነገረ ሥላሴ ጽንሰ ሐሳብ ብቻ ከመሆንም ባለፈ በኦሪትም ሆነ በሐዲስ ኪዳን የሚታወቅና የሚታመን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሥጢር ነው፡፡ በኦሪቱ በምሳሌ እንዲሁም እግዚአብሔር ለወደዳቸውና ለመረጣቸው ቅዱሳን አንድነቱን ሦስትነቱን ገልጦ አሳይቷዋል፡፡ ለምሳሌ በዘፍ 18 ከቁጥር አንድ ጀምሮ እግዚአብሔር ለአብርሃም በሦስትነት ተገልጦ ታይቶታል፡፡ በኢሳ 6 ላይም እንዲሁ ነቢየ ልዑል ቅዱስ ኢሳይያስም የእግዚአብሔርን ልዩ ሦስትነት ተመልክቷል፡፡ ‹‹ማንን እልካለው ማንስ ይሄድልናል›› የሚለው የእግዚአብሔር ንግግር ይህን ያጠነክርልናል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ሦስቱ አካላት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን የሚያመለክተው ሥላሴ የሚለው መጠሪያም በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ ሰፍሮ እናገኘዋለን፡፡
በመሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ የምንለው በቁጥር ተሰፍረው የምናገኛቸውን 81 መጽሐፍትን ነው፡፡ (46ቱ የብሉይ እና 35ቱ የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት) ይህን የቁጥር መጠን በቀኖና ሰፍራ የምትቀበለው ደግሞ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነች፡፡ ከ81ዱ ሳታጎድል ሳትጨምር ትቀበላለች፡፡ በነዚህ መጽሐፍት ውስጥም "ሥላሴ" የሚለው ቃል ተጠቅሶ እናገኛለን። ለአብነትም ጥቂቶቹን እነሆ።
ሄኖክ 5፡38 ‹‹ምዕመናን ለሥላሴ እንዲሰዉ እነርሱም ለአጋንንት ይሰዉ ዘንድ ሰዎችን ያስቷቸዋል፡፡››
ሄኖክ 6፡23 "ፍጹም መቻያቸውን እስተሚቀበሉባት ቀን ድረስ እስከ ጊዜያቸውም ቀን ድረስ እነሱን የሚያኖሩባቸው እነዚህን ቦታዎች ሥላሴ ፈጠሩ።"
ሲራክ 3:22 "ሥላሴ ከሰው ሁሉ ይልቅ የገለጡልህ ምሥጢር የለምና ከግብር ገብተህ የሥላሴን ባሕርይ አትመርምር።"
ሄኖክ 13:14 "በመረጥኋቸው በጻድቃንም እጅ ሥላሴ ይጥሏቸዋል።"
ዮዲት 11:18 "ሥላሴ ለእኔ እንዲህ ያለ ነገር ፈጽመው ነግረውኛ…"
ጥበብ 6: 6 "ለደኃው፣ ግን ሥላሴ ከቸርነት ሥራ የትነሣ ያቃልሉለታል። ኃይለኞች ሰዎችን ግን ጽኑ ምርመራ፣ ይመረምሯቸዋል።"
ሄኖክ 17:17 ፣ ሄኖክ 38:10፣ ጥበብ 17:10፣ ሲራክ 15:17፣ ሲራክ 39:21፣ ሲራክ 44:10 …
ጥቂቶቹ ናቸው።
እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ኃይለ ቃላት የቀኖና መጽሐፍት ተብለው ከሚመደቡት መካከል ሲሆኑ ካለነዚህ መጽሐፍት መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ ሊሆን አይችልም። ለምሳሌ ሉቃ 12:19 ከ ሲራክ 11:19 ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሀሳብ ይዘዋል። ማቴ 27:9 ላይ የተፈጸመው ትንቢት የተነገረው ተረፈ ኤር 7:3 ላይ ነው። ይሁዳ በመልእክቱ 1:14 ላይ ያለውን ቃል ቀድሞ የተናገረው በብሉይ ኪዳን ሄኖክ ነበር። ሄኖክ 1:9
የተወሰኑት ማሳያዎች ናቸው።

#መዝሙር #ሐዋርያት_ተባበሩ
#በወንድማችን_ዳዊት_ክብሩ
#መሰንቆ #ሀብታሙ_ሽፈራው
#ክራር #አቤኔዘር_ማሙሸት
ሐዋርያት ተባበሩ
በአዲስ ቋንቋ እየተናገሩ
ቃሉን አስተማሩ
ከዐረገ በኋላ በአስረኛው ቀን
ወደ ዓለም ላከው ጰራቅሊጦስን
በዝግ ቤት ውስጥ ቆዩ ቀኑን ሲጠብቁ
የተሰጣቸውን ተስፋውን እስኪያውቁ
ቀኑም ደረሰና ሃምሳኛው ዕለት
ተሰብስበው ሳሉ በአንድነት ጸሎት
መንፈስ ቅዱስ ታየ በነደ እሳት
ያ የተነገረው ያ የተስፍ ቃል
ወረደ ከሰማይ በእሳት አምሣል
ጴጥሮስ አሳመነ ሶስት ሺ ነፍሳት
ያን ጊዜ ገሊላ በሰጠው ትምህርት
ከሦስት አካል አንዱ መንፈስ ቅዱስን
ልኮ አናገራቸው ሁሉን በልሳን
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#በወንድማችን_ዳዊት_ክብሩ
#መሰንቆ #ሀብታሙ_ሽፈራው
#ክራር #አቤኔዘር_ማሙሸት
ሐዋርያት ተባበሩ
በአዲስ ቋንቋ እየተናገሩ
ቃሉን አስተማሩ
ከዐረገ በኋላ በአስረኛው ቀን
ወደ ዓለም ላከው ጰራቅሊጦስን
በዝግ ቤት ውስጥ ቆዩ ቀኑን ሲጠብቁ
የተሰጣቸውን ተስፋውን እስኪያውቁ
ቀኑም ደረሰና ሃምሳኛው ዕለት
ተሰብስበው ሳሉ በአንድነት ጸሎት
መንፈስ ቅዱስ ታየ በነደ እሳት
ያ የተነገረው ያ የተስፍ ቃል
ወረደ ከሰማይ በእሳት አምሣል
ጴጥሮስ አሳመነ ሶስት ሺ ነፍሳት
ያን ጊዜ ገሊላ በሰጠው ትምህርት
ከሦስት አካል አንዱ መንፈስ ቅዱስን
ልኮ አናገራቸው ሁሉን በልሳን
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
#ውይይት
#በእንተ_መጻጉዕ
በወንድሞቻችን
#ኢዮብ_ክንፈ
#ተርቢኖስ_ሰብስቤ (ምንዳዬ)
#አቤኔዘር_ማሙሸት
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#በእንተ_መጻጉዕ
በወንድሞቻችን
#ኢዮብ_ክንፈ
#ተርቢኖስ_ሰብስቤ (ምንዳዬ)
#አቤኔዘር_ማሙሸት
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit