በአማላጅና በመማጸኛ መካከል ያለውን ልዩነት ያውቃሉ?
ክፍል -2
በአማላጅና በመማጸኛ መካከል ያለው ትልቅ ልዩነት አማላጅ ህልውና ያለው አካል ብቻ ሲሆን ከዚህ ቀደም እንደገለጽነው መማጸኛ ደግሞ ህልውና ያለውም የሌለውም ሊሆን መቻሉ ነው።
አማላጅን ፣ መማጸኛን እና ተማላጅን በግልጽ እንድንረዳቸው የሚከተለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እንደ ምሳሌ እንመልከት።
ዘጸ 32÷1-14
በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ሙሴ አማላጅ እግዚአብሔር ደግሞ ተማላጅ (ተለማኝ ፣ ታራቂ፣ ይቅር ባይና ፈራጅ) ሆኖ ስመ አብርሃም ይስሐቅ እስራኤል የተባለ ያዕቆብ ደግሞ መማጸኛ ሆነው ቀርበዋል።
ታሪኩ እንዲህ ነው። እግዚአብሔር አምላክ እስራኤል ዘሥጋን ከግብጽ ባርነት በዘጠኝ ታላላቅ ተዓምራት በአሥረኛ ሞተ በኩር (የግብጽን ሰዎች የበኩር ልጆቻቸውን ገድሎ) በአሥራ አንደኛ ስጥመተ ባህር (ጠላቶቻቸውን በኤርትራ ባሕር አስጥሞ) ነጻ ቢያወጣቸው እነርሱ ግን እግዚአብሔርን ክደው ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስል ጣዖትን ለራሳቸው አደረጉ። ሰዉለት፣ ሰገዱለት አልፎም ተርፎ ነጻ ያወጣቸውን እግዚአብሔርን ረስተው ከግብጽ ባርነት ነጻ ያወጡን እነዚህ አማልክት ናቸው አሉ።
የእግዚአብሔርም ቁጣ በህዝቡ ላይ በነደደና ሊያጠፋቸው በተናገረ ጊዜ ግን የተመረጠው ሙሴ በመቅሰፍት ሰዓት በእግዚአብሔር ፊት ስለ እነርሱ ቆሞ ማማለድና ይቅር ይላቸው ዘንድ መለመን ጀመረ። መዝ 105÷23
የምልጃ ቃሉም መማጸኛን እየተጠቀመ ነበር።
"ሙሴም በእግዚአብሔር በአምላኩ ፊት ጸለየ ፥ አለም፦ አቤቱ ፥ ቍጣህ በታላቅ ኃይልና በጽኑ እጅ ከግብፅ ምድር ባወጣኸው በሕዝብህ ላይ ስለ ምን ተቃጠለ? ግብፃውያንስ፦ በተራራ መካከል ሊገድላቸው፥ ከምድርም ፊት ሊያጠፋቸው ለክፋት አወጣቸው ብለው ስለ ምን ይናገራሉ? ከመዓትህ ተመለስ ፥ ለሕዝብህም በክፋታቸው ላይ ራራ። ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ ይህችንም የተናገርኋትን ምድር ሁሉ ለዘራችሁ እሰጣታለሁ፥ ለዘላለምም ይወርሱአታል ብለህ በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህን #አብርሃምንና #ይስሐቅን #እስራኤልንም አስብ። እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ሊያደርግ ስላሰበው ክፋት ራራ።" ዘጸ 32÷12-14
እንደተመለከትነው እስራኤል ዘሥጋ ስለፈጸሙት ገቢረ ኃጢአት ሙሴ ስለ እነርሱ አማልዷል። በምልጃው ወቅት የተጠቀማቸው መማጸኛዎች እግዚአብሔር ለአብርሃም ፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የገባላቸውን ቃልኪዳን ነው። ስለ እነርሱ ብለህ ማራቸው ይቅር በላቸው የሚለው የሙሴ የምልጃ ጸሎት ቅዱሳኑን መማጸኛ አሰኝቷቸዋል። በአንጻሩ ደግሞ ሙሴ የእስራኤል ዘሥጋ አማላጃቸው ነው።
አማላጅ የግድ ህልውና ሊኖረው ይገባል። ዛሬ የፕሮቴስታንቱ ዓለም እንደሚያወራው ሲያሻው ክርስቶስን "አማላጄ" ሲለው (ሎቱ ስብሐት) ሲያሻው የፈሰሰው የክርስቶስ ደም እያማለደኝ ይኖራል እያለ የተምታታና ግራ የገባ ዕምነት ያራምዳል።
እርሱንም ሆነ የፈሰሰውን ደሙን መማጸኛ እንጂ አማላጅ እንድናደርጋቸው አልተፈቀደልንም። ይልቅ ቅዱሳኑ እንዲያማልዱን እነርሱንም መማጸኛ አድርገን እንድንጠቀም የታዘዝነው። "የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደ ቅዱሳን ጆሮዎቹም ወደ ልመናቸው ነው።" መዝ 33(34)÷15 ፣ 1ጴጥ 3÷12 እንዲል የእነርሱ የተሰሚነት ጸሎት የተሻለ ነውና እነርሱ ሊያማልዱን ይገባል። አልያም በእነርሱ ስም ብንማጸነው ስለገባላቸው ቃል ኪዳን ብሎ ከጭንቅ ፣ ከመከራ ፣ ከተቃጣው መዐት ፣ ከመጣው ቁጣና መቅሰፍት በቸርነቱ ያድነናል። ስለ አብርሃም ስለ ይስሐቅ ስለ ያዕቆብ ብሎ ጣዖት ላመለኩ እስራኤል ዘሥጋ ከራራላቸው በስሙ ላመንን የልጅነት ሥልጣል ለተሰጠን ከአብርሃም ከይስሐቅ ከያዕቆብ የምትበልጥ እናት እመቤታችን ላለችን ለኛ እስራኤል ዘነፍሥ ስለ እናትህ ብለህ ማረን ብንለው እንዴት አይምረንም???
ይቆየን።
ይቀጥላል…
አዘጋጅ #አቤኔዘር_ማሙሸት
👉 @AwediMeherit