ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#የዓለም_ንግሥት

የዓለም ንግሥት የሆንሽ
ድንግል ማርያም እናቴ
ታመስግንሽ አንቺን ሁል ጊዜ ህይወቴ
ማርያም ባርኪኝ እመበቴ እሰግድ ለኪ

እንዳልንገላታ ጠብቂኝ
በኃጢአት ዓለም ጎዳና
ደግሞም እንድመገብ ሰማያዊ መና
ማርያም የአዳም ጤና

ተሽጬ ስኖር ልጅሽ
በኃጢአት ዓለም ከተማ
የሚያወጣኝ ጠፍቶ የእናት ልጅ ወንድም
ወጣሁኝ በልጅሽ ደም እሰግድ ለኪ

ከቅድስት ቦታ ሀገር
ከቤተልሔም ተነስተሽ
ምድረ ግብጽ አውራጃ ፈጥነሽ ስትደርሽ
ማርያም መከራን አየሽ እሰግድ ለኪ

ያ ምቀኛ ሰይጣን ንጉሥ
ተንኮል የተሞላው ሄሮድስ
ልጅሽን ሊገድለው ደሙን ለማፍሰስ
ተሯሯጠ በእግር በፈረስ እስግድ ለኪ

ያንቺ መንገለታት ሁልጊዜ
ያሳዝነኛል ሲወራ
በምድረ ግብጽ ሁሉ ያየሽው መከራ
ማርያም ነፍሴን አደራ እሰግድ ለኪ


👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit