አትሮኖስ
280K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
460 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


...ፍራንሲዝ ሌቪዞን ሌላ ሠረገላ እስኪመጣ መጠበቅ ፈልጎ ነበር . .
ጓደኞቹ ደግሞ እንደዚያ ሆኖ ቁሞ ከጠበቀ አደገኛ ብርድ ሊመታው ስለሚችል በእግር ማዝገም መሻሉን መከሩት በሐሳባቸው አልተስማማም " ነገር ግን መንጋጋዎቹ ክፉኛ ተንቀጫቀጩ " ሁለቱ ሰዎች ከመኻል አድርገው
ያዙትና ሳይወድ መንግድ ጀመሩ " ነገር ግን ሚስተር ካርላይልንና ደጋፊዎቹን ከመንገድ ሊያገኙዋቸ
ስለ መቻላቸው ትዝም አላላቸው " ስለ መሔድና ስለ መቆየት ሲከራከሩ የዚህ ጉዳይ አልታያቸውም ፍራንሲዝ ሌቪሰን ደግሞ ከነሱ ጋር ፊት ለፊት ከመግጠም በራሱ ፈቃድ ከኩሬው ውስጥ በጭንቅላቱ ቢተከል ይመርጥ ነበር ።

ሚስ ካርላይል በዚያ ቀን ኢስት ሊን ራት ለመብላት ከሚስዝ ካርላይል
ከማዳም ቬንና ከሉሲ ጋር መጥታ ነበር "

ሚስ ካርላይል ከመልበሻ ክፍሏ ገብታ ... ጆይስን ለመጥራት ደወለች እነዚያ ክፍሎች እስከ ዛሬም የሚስ ካርላይል ክፍሎች ይባላሉ" ምክንያቱም አንዳንድ
ጊዜ እየመጣች ለጥቂት ቀኖች እያደረች ስለምትሔድ ነው አሁንም ገብታ ጓዝዋን ስታኖር ጆይስ መጣች "

ዛሬ ከሰዓት በኋላ እንዴት ያለ አምባጓሮ ገጠመን መሰለሽ ... ጆይስ "

“ የስኳየር ስፒነር አራሾች ናቸው አሉ ኋይት እኮ መጥቶ ነገረን ይገባዋል”
ግን ከዚያው ሰጥሞ እንዲሞት ቢተዉት ኖሮ ጥሩ ነበር " ወንድ ልጅ እንደዚህ
ሲሆን አይቸ አላውቅም ። ፒተርማ ሲሰማ አለቀስ ” አለች "

“ አለቀሰ ?” አለች ኮርነሊያ
“ ፒተር እሜቴ ሳቤላን በጣም ይወዳቸው እንደ ነበር እርስዎም ያውቃሉ”
ስለዚህ ይኸን ነገር ሲሰማ ስሜቱ ተናነቀውና ከደስታው ብዛት የተነሣ ጮህ ብሎ አለቀሰ " በኋላ አንድ ብር ከኪሱ አውጥቶ ለኋይት ሰጠው " ሰውየውን ወደ ኰሬው በወረወሩት ጊዜ ኋይትም አንድ እግር ይዞ እንደ ነበር ነገረን " እርስዎ ስለማይወዷት ስሟን ስጠራብዎ አይቆጡኝ እንጂ አፊም እኮ አይታዋለች » እሷም እዚህ ስትደርስ ብርክ ያዛት "

“እሷ ደግሞ የት ሆና አየችው? አለች ሚስ ካርላይል ከጆይስ አፍ ነጠቅ አድርጋ “ እኔም ከያ ነበርኩ ግን አላየኋትም "

“ሚስዝ ላቲመር ከአንድ የጀርመን መስፍን ሚስት የደረሳትን ወሬ ለማዳም ቬን
ለመንገር ልካት ወደዚ ስትመጣ በእርሻው በኩል ከኩሬው አጠገብ ጩኸት መስማቷን ነገረችኝ " "

“ ታድያ ምን ሆንኩ ብላ ነው ብርክ የያዛት " አለች ሚስ ካርላይል ቶሎ ቀበል አድረጌ

ምን ዐውቄ መቼም አንዘፈዘፋት አለች ጆይስ "
“ እሷንም ቢያጠልቋት ኖሮ ጥሩ ነበር ” አለች ሚስ ካርላይል እየተናደደች »

" አንቺ ጆይስ ... ” አለች ሚስ ካርላይል ድንገት ርዕስ በመለወጥ ይህችን የልጆች አስተማሪ ስታያት ማንን ትመስልሻለች ?

“ እስተማሪ ? እለች ጆይስ በጥያቄው ድንተኛነት ድንግጥ ብላ !“ማዳም ቬንን ማለቶ ነው?

“ እንግዲያ አንቺን ወይስ እኔን የምል መሰለሽ አስተማሪምች ነን? አለችና
ቆጣ ብላ “ማዳም ቬን ነው እንጂ ማንን ልል ኖሯል ” ብላ ዐይን 0ይኗ እያየች
የምትመልሰውን ትጠብቅ ጀመር "

ጆይስ ድምጿን ዝቅ አድርጋ " በመልክም በጠባይም አንዳንድ ጊዜ ሟንቿን
አመቤቴን መስላ ትታየኛለች " ነገር ግን የአመቤት ሳቤላ ስም ከዚህ ቤት እንዳይነሣ የተክለከለ በመሆኑ ለማንም አልተናርኩም ” አለቻት "

“ መነጽሯን አውልቃ አይተሻት ታውቂያለሽ ?”

“ ኧረ የለም "

“ እኔ ዛሬ አየኋት " ልክ እሷን መሰለችኖ ድርቅ አልኩልሽ - መምሰል ስልሽ እኮ ልክ በአካል ቁጭ ማለት ነው ያየ ሰው የእመቤት ሳቤላ መንፈስ እንደ ገና ተመልሶ ወደዚህ ዓለም የመጣ ይመስለው ነበር "

“ኧረ እሜቴ እባክዎ አይቀልዱ ነገሩ ያሳዝናል እንጂ ለቀልድ አይመችም "
ቀልድ ? መቸ ነው ስቀልድ የምታውቂኝ ? አለችና ጥቂት ዝም ብላ ከቆየች በኋላ : “ ዊልያምን ብሶበታል ሲሉ የምሰማው እንዴት ነው?”

“ በጣም እንኳን አልጠናበትም በርግጥ በተለይ ወደ ማታ ሲሆን ድክምክም ይላል " ሕመሙ ግን የሚነገርለትን ያህል አልመሰለኝም ” አለች ጆይስ

“ በጣም ታሟል ሲሉ እሰማለሁ "

ማነው የነገረዎት ?

“ አስተማሪቱ ዛሬ ከቀትር በኋላ ነገረችኝ " እሷማ ተስፋ የሚያስቆርጥ አድርጋ ነው የነገረችኝ » ድምጿም እንደ ንግግርዋ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነበር "

“ እሷስ በጣም የታመመ እንደሚመስላት ዐቃለሁ » ለእኔም ባለፉት ጥቂት
ቀኖች እንኳን ብዙ ጊዜ ነግራኛለች "

“ ቢደካክምም አይገርመኝም ” አለች ሚስ ካርላይል “ “ ሰውነቱ ልክ እንደ እናቱ ለንቋሳ ነው "

ማታ ራት ከተበላ በኋላ ሎርድ ማውንት እስቨርንና ኮርኒሊያ አንድ ሶፋ ላይ
ቡና ይዘው ጐን ለጐን ተቀምጠው ነበር" ሰር ጆን ዶቢዴና አንድ ሁለት ሌሎች
መኳንንትም አብረው ነበሩ " ትንሹ ቬን ' ሉሲና ሚስዝ ካርላይል አንድነት እያወጉ
ይስቁ ነበር " ወጉና ጫጫታው መድመቁን አይታ ሚስ ካርላይል ወደ ኧሩሉ ዞር ብላ ወይዘሮ ሳቤላ በርግጥ ሙታለች ? አለች "

ኧርሉ በጥያቄዋ በጣም ስለ ተገረመ : የቻለውን ያህል አፍጦ ተመለከታትና
“ ነገርሽ አልግባኝም፡ ሚስ ካርላይል ... የተረጋገጠ ነው ? እንዴታ ምኑ ይጠየቃል


የአደጋው ሁኔታ በተገለጸልዎ ጊዜ ስለ ትክክለኝነቱና ስለ ዝርዝር ሁኔታው እንዲግጽልዎ እርስዎ ራስዎ ጠይቀው የነበር ይመስለኛል ”

“አዎ ያን ሁሉ መከታተል ግዴታዬ ነበር " ሌላ ሥራዬ ብሎ የሚከታተል
አልነበረማ

እና በርግጥ መሞቷን በማያጠራጥር ሁኔታ አረጋግጠዋል ?

“በደንብ አረጋግጫለሁ " አደጋው የደረሰ ዕለት ሌሊቴን ሙታ አደረች
እንክትክት ብላ ተጎድታ ነበር »

ትንሽ ዝምታ ቀጠለ " ሚስ ካርላይል ማሰላሰል ጀመረች » አሁንም ለማመን
እንደ ተቸገረች ሁሉ ወደዚያው ርዕስ ተመለሰች።

“ እርስዎ ካገኙት ማረጋግጫ ስሕተት ሊኖርበት ይችላል ብለው አይጠራጠሩም? መሞቷን በትክክል አረጋማጠዋል ?

“ አሁን እኔና አንቺ በሕይወት እንዳለን ያጠራጥራል?ልክ የዚህን ያህል እርግጠኛ ነኝ " ግን ለምን ጠየቅሽኝ ?”

“ እንዲያው በርግጥ ሙታ ይሆን ? የሚል ሐሳብ ድቅን አለብኝ »

« አየሽ ... የመሞቷ ወሬ ስሕተት ቢሆን ኖሮ በየጊዜው እንድትቀበል
ተነጋግረን ያደረጉሁላትን የዘለቄታ ተቆራጭ ገንዘብ
ትቀበልበት ከነበረው ባንክ
ሔዳ ታወጣ ነበር ግን ገንዘቡ ከዚያ ጊዜ ወዲህ አልተነካም " ከዚህም ሌላ ከኔ ጋር እንደ ተስማማ ነው እስከ ዛሬ ትጽፍልኝ ነበር የሷ ነገር ያለቀለት ነው " ምንም አያጠራርም " ጥፋቷንም ሁሉ ይዛው ተቀብራለች”

አሳማኝ ማረጋግዎች ኮርኒሊያም ከልብ አዳምጣና አጢና ተቀበለቻቸው "

በበነጋው ጧት ሕፃኑ ሎርድ ቬን ከማዳም ቬንና ከጆቹ ጋር ተጨመረ ቁርሱን አብሮ በላ " በኋላ እሱ ሎሲና ዊልያም ከግቢው መስክ ላይ የሩጫ እሽቅድድም
ገጠሙ " የዊልያም ሩጫ መቸም እንዲያው ለይምስል እንጂ እሱ ራሱም ትንፋሹም ድክም ብለው አብቅተዋል » ሳቤላ አርኪባልድን ከጫወታው ለይታ ከእናት በቀር ምናልባት በጣት የሚቆጠሩ ብቻ ሊያደርጉት በሚችሎት ጥንቃቄ ጉልበቷ ላይ አስቀምጣ ከውስጧ በሚፈልቀው የጋለ ስሜት ጥምጥም አድርጋ አቅፋ : እስረኛ አድርጋ እንደያዘችው ሚስተር ካርላይል ገባ

እንግዳ ትቀበያለሽ ... ማዳም ቬን ? አላት በረጋው ጠባዩና ደስ በሚለው
ፈገግታው።

ልጁን ሸተት አድርጋ አስቀመጠችውና ብድግ ስትል እሱም ብድግ ብሎ
ታላቆቹ ወደሚጫወቱበት የሣር መስክ እየሮጠ ሔደ።
👍18
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_አንድ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

ሚስተር ካርላይል ከታወቀው ከባክስ ሔድ ሆቴል ሰገነት ወጥቶ ለተሰበሰበዉ ሕዝብ ንግግር ያደርግ ነበር " አረንጓዴ የተቀባው ስገነት ደጋፊቹን ሁሉ አሰባስቦ ለመያዝ በቂ ስፋት ነበረው ሚስተር ካርላይል አስቀድሞ ከነበረው መልካም
ስምና ተወዳጅነት ሌላ በንግግር ተስጥዎ የታደለ ስለ ነበሮ የዌስት ሊን ሕዝብ
ወደሱ እያደላ ፍራንሲዝ ሌቪሰንን አገለለው።

ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንም በበኩሉ ሬቨን ሆቴል ሆኖ ንግግር እያስማ ነበር "
ሆቴሎ ያማሩ መስኮቶች እንጂ ሰገነት አልነበረውም " ቦታው በደንብ ቁሞ ንግግር
ለማድረግ አይመችም " ስለዚህ ከአንደኛ ፎቅ ወደ ምድር ቤት ወርዶ በሳሎኑ ቅስት መስኮት ውጪኛ ጠርዝ ላይ ቁሞ ለመናገር ተገደደ " ያም ሆኖ ቦታው በጣም በመጥበቡ ክንዱን ማወወዝ እግሩን ማንቀሳቀስ ቢሞክር ሚዛኑን መጠበቅ ተቸገረ »
እሱን ሊያዳምጥ ከቆመው ሕዝብ ላይ በጭንቅላቱ እንዳይደፋ ስለ ፈራው ' ለመጀመሪያ ቀን ብቻ በአንድ በኩል ሚስተር ድሬክ በሌላው በኩል ጠበቃው ደግፈውት
ሊወጣው ቻለ ጠበቃው ግን ቁመቱ ከሁሉ ያጠረ ፡ ጐኑ ከሁሉ የሰፋ ወደል
በመሆኑ በንግግሩ መጨረሻ ተመልሶ ለመግባት ችግር ገጠመው " ሰር ፍራንሲዝ እየጎተተ ሚስተር ድሬክ እንደ መሰላል ተሸክሞት እየገፋ የተሰበሰበው ሕዝብ እየሳቀበት በስንት መከራ በደኅና ወረደ " ላቡን ከፊቱ እየጠረገ ዳግመኛ በመስኮት ላይ
በመንጠልጠል በልቡ ማለ

ሰር ፍራንሲዝ ሊቪሰን ሲናግር ያንቀጠቅጠዋል " አንድ ቀን ከቀትር በኋላ
ንግሩን በርቱዕ አንደበቱ ሲያንቆረቁረው ጓደኞቹ አብረውት ቁመዋል " የተሰበሰበው ሕዝብ መንገዱን ሙልት አድርጎ ዘግቶ ጥቂቱ ድጋፉን በመግለጽ እጅግ
የሚበልጠው ግን በማሾፍ ይሥቃል ያፋጫል ይጮኻል ያጨበጭባል " ሚስተር ካርላይል ንግግሩን ቀድም አድርጎ ስለጨረሰ ከሱ ዘንድ የነበረው ሕዝብ ግልብጥ
ብሎ ሰር ፍራንሲዝን ለማዳመጥ መጥቷል " ስለዚህ የነበረው ሕዝብ ብዛት ይህ ነው አይባልም » መተላለፊያ ጠፍቶ በክርኑ እየተጓሸመ • በትከሻው እየተጋፋ እግር ለእግር እየተራገጠ ይርመሰመሳል " ሕዝቡ እንደዚህ ሲተራመስ አንድ ባለ አራት እግር ግልጽ ሠረገላ እንደዚህ በሚተራመሰው ሕዝብ መኻል እየጣሰ በማለፍ ሊበትነው ሞከረ የሚስቡት ፈረሶች ደማቅ ቀይና ወይን ጠጅ ምልክት አሥረዋል " ከሠረገው አንዲት መልከ መልካም ወይዘሮ ተቀምጣለች ሚስዝ ካር
ላይል ።

ጥቅጥቅ ብሎ የምላው ሕዝብ ግን በቀላሉ የሚበተን አልሆነም " ሠረገላው በጣም እያዘገመ አንድ አንድ ጊዜም ቆም እያለ ለመጓዝ ተገደደ በዚህ ላይ ትርምሱና ጩኽት በረከተ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንም ሁኔታው ስክን እስኪልለት ንግግሩን ገታ አያረገ " ባርባራን ባጠገቡ ስታልፍ አይቷታል " ነገር ግን ሚስ ካርላይልን ሰላም በማለቱ የደረሰበትን ጣጣ በማስታወስ እጅ ሳይነሣት ዝም አለ " ወደ ባርባራም ሆነ ወደ ሌላ ትኩረት ሳያደርግ ሰው እስኪረጋጋለት ዝም ብሎ ይጠብቃል

ባርባራ ዳንተል ሥራ የሆነው ጃንጥላዋን ዘርግታ ዐይኖቿን ወደሱ በመለስ በወንፊቱ ተመለከተችው " በዚህ ጊዜ የቀኝ እጁን አነሣ" ራሱን ወደ ኋላው በቀስታ ነቀነቀ ጸጉሩን
ከግንባሩ ወደ ኋላ ምልስ አደረገ " የጣቱ ያልማዘ ቀለበት
በዙርያው አንጸባረቀ " ባርባራ ይኸንን ሁኔታውን እያየች ፊቷ ተለዋወጠ "

ስለ ሪቻርድ የተናገረቻችው ምልክቶችና ድርጊቶች አንዳሉ ናቸው ሪቻርድ ፍራንሲዝ ሌቪስንን ዐውቀዋለሁ ያለው ተሳስቶ ነው " ይህ ሰው ቶርን መሆን አለበት ብላ አሰበች።

በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ሰላም ሲሏት አጸፋውን የምትመልስው ያለ ልቧ ነበር ሐሳቧ ተበጠበጠ „ “ ካርላይል ይኑር ! ምን ጊዜም ካርላይል! ብለው እየጮኹ
ባጠገቧ ሲያልፉ ባርባራ በግራም በቀኝም አጸፋውን እጅ በመንሣት ትመልስ እንጂ ሀሳቧ ከሌላ ነበር።
በመጨረሻ ሠረገላው መንገዱን ቀጠለ።

ንግግሩ አብቅቶ ሕዝቡ ሲበታተን ሚስተር ዲልና ሚስተር ኧበንዘር ተገናኙ ኧበንዘር ጀምዝ ለአሥራ ሁለትና ዐሥራ አምስት ዓመት በተለያዩ ሙያዎች በመሠማራት
የሚስተር ካርላይል ጸሐፊ ነበር ቀጠለና ሊንበራ ላይ ከነበረው ቲያትር ሮያል ከተባለው ገባ ከዚያ ሐራጅ ሻጭ ሆነ ያን ተወና ቄስ ሆነ።ከዚያ በኋላ የሕዝብ ማመላለሻ
ትልቅ ሠረገሳ ነጅ ሆነ ያ ደግሞ አላዋጣም ሲለው ቦልናትሬድማን ለተባሉ የዌስት ሊን ጠበቆች ጸሐፊ ሆነ ኧበንዘር ጀምዝ በቁም ነገር በኰል በዋልፈሰስ ቢሆንም ወግ
አዋቂ ለዛ ያለው ፈገግታ የማይለየው ጥሩ ሰው ነው " የሱ ክፋቱ ከችጋር አይወጣም " ኪሱ ባዶ ይሆናል አንዳንድ ጊዜም ከነሚላባብሰው ያጣል አባቱ በንግድ የተገኘ ብዙ ሀብት ያፈራ በሰው ዘንድ የተከበረ ነው " ነገር ግን'ሁለተኛ ሚስት አግብቶ የሁለት ቤተሰብ አስተዳዳሪ ሆነ " ስለዚህ ልጁም ገንዘብ ብሎ ወደባቱ
አይሔድም ቢሔድም ቁጣን እንጂ ገንዘብ አያገኝም "

“ ታዲያስ ኧበንዘር” አለው ሚስተር ዲል ሰላምታ ሲስጠው “ ዓለም እንዴት ይዛሃለች ?”
"አለች ታዘግማለች አንድም ቀን ሶምሶማ አትረግጥም ! ”
“ ትናንት ወደ
አባትህ ቤት ስትገባ አላየሁህም ?

ወዲያው ተባርሬ ወጣሁ ። እኔ እኮ እዚያ ቤት ከሔድኩ እንደ ውሻ ነው የምታው ቤሳ ከሚሰጠኝ ቢረግጠኝ ይወዳል ኧረ አሁን ዝም በል ! ሰዉ የውድድሩን ንግግር እንዳይሰማ እያስቸገርን ነው "

የተባለው ንግግር የስር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ነው » ሚስተር ዲል ኮስተር ብሎ ሚስተር ኧበንር ደግሞ ሣቅ ሣቅ እያላቸው ሲያዳምጡ ከመኻል አንድ ዐይነት ግፊያና እንቅስቃሴ ወደ ዳር አወጣቸው ተናጋሪውን ማየት ከማይችሉበት ቦታ ደረሱ ንግግሩን ግን ይሰሙታል • እንደዚያ ተገፋፍተው ከቆሙበት ቦታ ሆነው መንገዱ ከሩቅ ድረስ ይታያቸዋል አንድ ሰው በኋላ እግሮቹ ቁሞ የሚሔድ የሩስያ ድብ የመሰለ ነገር ድንገት ከሩቅ ሲመጣ አየ
"
“ እኔስ ያ የሚመጣው ሰውዬ ቤቴል መሰለኝ ” አለ ኧበንዘር ጀምዝ "

· ቤቴል ! ” አለ ሚስተር ዲል ወዶ ሰውዬው እየተመለከተ ” “ ምን ሲያደርግ ከርሞ ብቅ አለ ?

ኦትዌይ ቤቴል ከድብ ቆዳ የተስፋ የመንገድ ልብስ ሳይቆረጥ ከነጅራቱ እንደ ለበሰና ጸጉራም ቆብ እንደ ደፋ ገና መድረሱ ነበር" የቆቡ ልብሱም ሆነ የፊቱ ጠጉር ሁሉ የተቆጣጠረና የተጠላለፈ ነበር እውነትም የዱር አውሬ ይመስል
ነበር ወደሱ ሲጠጋ ሚስተር ዲል የእውነት አውሬ ሆኖ ታየውና እንዳይበላ የፈራ ይመስል ወደ
ኋላው አፈገፈገ "
ስምህ ማን ይባላል ?

“ቤቴል እባል ነበራ ” አለ አስፈሪው ሰውዬ እጁን ወደዲል አየዘረጋ። “ጀምስ... እስካሁን ድረስ እተንፈረጋገጥህ በዚህ ዓለም አለህ ?”

“ ወደፊትም እንደዚሁ እየተፈራገጥሁ እንደምቆይ ተስፋ አለኝ... ኧረ አሁን ከየት ብቅ አልክ ? ከአንድ የሰሜን ዋልታ መንደር ነው ?”

እዚያ ድረስ እንኳን አልሔድኩም ... የምን ግርግር ነው የምሰማው?

“ መቸ መጣሀ ሚስተር ኦትዌይ ?” አለው ሽማግሌው ዲል ።

“ አሁን በዐሥሩ ሰዓት ባቡር መድረሴ ነው ። ምን ነገር ነው የምሰማውኮ ነው የምለው ?

ምርጫ ነው ” አለ ኧበንዘር “ አትሊ ተሸኘ ፤ አራት እግሩን በላ ”

“ ስለ ምርጫው አልጠየቅሁህም ስለሱ ከባቡር ጣቢያ ሰምቻለሁ” አለ ኦትዌይ ቤቴል” “ይህ ምንድነው ?” አለ መልሶ እጁን ወደ ሕዝቡ እየዘረጋ ።ደ

" ከተወዳደሪዎቹ አንዱ የሆነው ሌቪሰን ቃላትና ትንፋሽን እየዘራ ነው ''

“ እኔ የምልህ አሁን የሱ ከሚስተር ካርላይል ጋር መወዳደር በጣም አያስገሮምም ? አለ ቤቴል
👍17
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_ሁለት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

...አንድ ቀን በሚያዝያ ወር ውስጥ ሰዓቱ መሽቶ ለዐይን ሲይዝ ዊልምና ሳቤላ ሳሎን ውስጥ ተቀምጠዋል " ቀኑ ሞቃት ሆኖ ይዋል እንጂ እነዚያ የጸደይ ምሽቶች ግን ይባረዳሉ " የምድጃው እሳት ነዲድ ባይኖረውም ፍሙ ግማሹ ጠፍቶ ግማሹ ይጤሳል ማዳም ቬን እሳቱን ልብ አላለችውም ዊልያም ከሰፋው ተጋድም እሷም ዐይን ዐይኑን ታየዋለች " መነጽሯ በእንባ እየተነከረ አስቸገራት ልጆቹ እንዳያውቁት መሥጋቱንም ትታዋለች " ስለዚህ መጽሯን አወለቀች ልጁም ሊንበራ ደርሶ የተመለሰበት የሠረገላ ጉዞ ስላደከመው ዐይኖቹን ገጥሞ ተጋደመ እሷም የተኛ ሲመስላት ወዲያው መልሶ ገለጣቸው።

“ ከመሞቴ በፊት ስንት ቀን ይኖረኛል ?” አላት "

ያልጠበቀችው ጥያቄ ሆነባትና ናላዋ ዞረባት " “ ምን ማለትህ ነው
ዊልያም ስላንተ መሞት ማን አነሣ? አለችው "

“ ዐውቃለሁ እንጂ ስለኔ የሚወራውን እሰማ የለምእንዴ በቀደም ሐና
ያለችውን ሰምተሽ የለ ?

“ ምን? መቸ ?

“ እኔ ከምንጣፉ ላይ ተኝቼ ሻይ ይዛ የገባች ጊዜ " ለናንተ ቢመስላችሁም እንቅልፍ አልወሰደኝም ነበር " አንቺ እንኳ ልነቃ እንደምችል እንድትጠነቀቅ
ነግረሻት ነበር።

“እንጃ ልጄ እምብዛም አላስታውሰውም ሐና ምን የማትለፈልፈው አርቲ
ቡርቲ አላት ብለህ ነው ?”

“ ወደ መቃብሬ እየተጣደፍኩ መሆኔን ነበር የነገረችሽ " "

"አለች ? ሐና ኮ ማንም አይስማትም የምትናገረውን አታውቅም " ሞኝ ናት " አሁን ብርዳሙ ወቅት ዐልፎ የበጋው ሙቀት ሲገባ በጐ ትሆናለ "

“ ማዳም ቬን ”

“ ምነው የኔ ዓለም ”

“ ያንቺ እኔን ለማታለል መሞከርሽ ምን ይጠቅማል ? እያታለልሽኝ መሆኑን የማይገባኝ ይመስልሻል ? እኔ ሕፃን አይደለሁም አርኪባልድ ቢሆን ኖሮ ልታዋሸው ትችይ ነበር " ግን ምን ሁኘ ነው እንደዚህ የሆንኩት ?

ምንም አልሆንክም " ሰውነትህ ደካማ ከመሆኑ በስተቀር ምንም የለብህ እንደ ገና ስትጠነክር ደግሞ በጐ ትሆናለህ "

ዊልያም ራሱን ነቀነቀ " ልጁ ያስተሳሰቡ ፍጥነትና ጥልቀት ከዕድሜው የላቀ ነው ነገሮችን በማለባበስ ሊታለል የሚችል ልጅ አይደለም " ሲነግር በጀሮው
ያልሰማውን እንኳን ይደረግለት ከነበረው ጥንቃቄ በመነሣት የተሠጋለት መሆኑን በግምት የሚያውቅበት ችሎታ አለው “ እሱ ግን የሐናን አነጋገር የመሰለ ብዙ
ነገር በጆሮው ሰምቶ እንዲጠረጥር የሚያደርጉት ምክንያቶች አጠራቅሟል ስለዚህ ልጁ ሞት እየመጣ ለመሆኑ በደንብ አድርጎ ዐወቆታል "

“ታዲያ ምንም ነገር ከሌለብኝ ዶክተር ማርቲን ለምን ከኔፊት አላነጋገረሽም?
እሱ በሳቡ የነበረውን ሲነግርሽ ለምንድነው እኔን ከሌላ ክፍል አንድቆይ ያደረገኝ?
ማዳም ቬን . . . . እኔም እንዳንቺ ዐዋቂ ነኝ ”

“ አዎን የልጅ ዐዋቂ ነህ ብቻ አንዳንድ ጊዜ ትሳሳታለህ ” አለችው ሁኔታው አንጀት አንጀቷን እየበላት "

“ እግዚአብሔር ከወደደን ኮ ሞት ምንም አይደለም ሎርድ ቬን እንደዚህ
ብሎኛል » እሱም አንድ ትንሽ ወንድም ሙቶበታል
እሱ ገና ከሕፃንነቱ ጀምሮ ተስፋ የተቆረጠበት በሽተኛ ነበር ” አለችው "
"እንዴ አንቺም ታውቂው ነበር ?
“ የሰማሁትን ነው የምነግርህ " አለችው ዝንጉነቷን በስልት አስተካክላ
“ አሁን እኔ እንደምሞት አታውቂም ?

“ አላውቅም "

" ታዲያ ከዶክተር ማርቲን ከተለየን ጀምሮ የምታዝኚው ለምንድነው ? እንዲ
ያውስ ከነጭራሹ ስለኔ ምን አሳዘነሽ ? እኔ ልጅሽ አይደለሁ ?

አነጋገሩና ሁኔታው ከምትችለው በላይ ሆነባት ከሶፋው ተንበረከከች እንባዋ ያለገደብ በአራት ማዕዘን ወረደ።

“ አየህ ዊልያም.....እኔ...እኔ አንድ ልጅ ነበረኝ የራሴ ልጅ አንተን ባየሁህ ቁጥር እሱ ይመጣብኛል " ስለዚህ ነው የማለቅለው "

“ ዐውቃለሁ ስለሱ ከዚህ በፊት ነግረሽኝ ነበር የሱም ስም ዊልያም ነበር
አይደለም?

ከላው ላይ ተደግፋ ትንፋሿን ከትንፋሹ እያቀላቀለች እጁን በእጅዋ ይዛ“ዊልያም ” አለችው " “ ፈጣሪ ከሁሉ አብልጦ የሚወዳቸውን አስቀድሞ እንደሚወስድ ታውቃለህ አንተም ብትሞት ኖሮ የዚህን ዓለም ሐሳብና ጣጣ እዚህ ትተህ መንግሥተ ሰማያት ትግባ ነበር። በሕፃንነታችን ብንሞት ኖሮ ለሁላችንም ደስታችን ነበር

“ ለአንቺም ደስ ይልሽ ነበር ?

“ አዎን ለደርሰብኝ ከሚገባኝ የበለጠ ኀዘንና መከራ ተቀብያለሁ " እንዲያው አንዳንድ ጊዜ ሳስበውስ የምችለውም አይመስለኝም"

“ አሁንም ኀዘንሽ አላለፈም ? አሁንም ብኀዘን ላይ ነሽ ?

“ሀዘኔ ሁልጊዜ ከኔ ጋር ነው " አስክሞትም አብሮኝ ይቆያል » በልጅነቴ
ሙቸ ቢሆን ኖሮ ግን ዊልያም አመልጠው ነበር " ዓለም በኀዘን የተሞላ ነው

“ ምን ዐይነት ኀዘን ?”

“ ሕመም በሽታ ሐሳብ ' ኃጢአት በደል ጸጸት ልፋት ” አለችና በሪጅሙ ተነፈሰች
“ ዓለም ከምታመጣብን መከራ ግማሹን እንኳን ልነግርህ አልችልም " በጣም ሲደክምህ ዊልያም .. ከትንሽ አልጋህ ላይ ጋደም ብለህ እንቅልፍ
እስኪወስድህ ስትጠብቅ ደስ አይልህም ?

“ አዎን እኔም እንደዚያ ድክም ይለኛል ”

“ ስለዚህ እኛም በዓለም ጣጣምች የደከምነው ተጋድመን የምናርፍበት መቃብራችንን እንናፍቃለን ቶሎ እንዲደርስ እንጸልያለን ግን አይገባህም ”

ከመቃብር ኮ አንጋደምም . ማዳም ቬን "

“ የለም የለም ሰውነታችን ከዚያ ያርፋል » በመጨረሻ ቀን በክብር በውበት ይነሣል ምነው!እንዲያው ምነው!አለች እየተኮማተረች ምነው አንተና እኔ
ሁለታችን እዚያ ብንገናኝ ! "

“ ዓለም የኀዘን ቦታ ናት ያለው ነው ... ማዳም ቬን ? እኔስ በተለይ በሙቀት ቀን ፀሐይ ስታበራ ቢራቢሮዎች ሲራወጡ ቆንጆ ትመስለኛለች " አሁን
ኢስትሊን በበጋ ብታይው በአግድመቶችና በቨርተቴዎች ሽቅብና ቁልቁል ስንሮጥ ዛፎች ከራሳችን በላይ ሲወዛወዙ • ሰማዩ ጠርቶ አበባ ሁሉ ፈንድቶ ስታይው የኅዘን ዓለም ነው አትይም ነበር "

“ እነዚያ አበቦች ኮ ከመንግሥተ ሰማያት ነው የምናያቸው »

“መቸ ጠፉኝ » ሥዕላቸውን አይቻለሁ ማርቲን ስለ ምጽአት የሳለቻቸውን ስዕሎች ለማየት ወደ ሊንበራ ሔደን ነበር የዶክተር ማርቲን አይደለም
" ነጭ ነጭ የለበሱ ብዙ ሰዎች አሉ አንድ ወንዝም አለ በወንዙ የሚያማምሩ ጀልባዎች ነፍሶችን ሲያመላልሱ ይታያሉ ከወንዙ ዳር ዳር በቅለው ሲታዩ የነበሩት አበባዎች ድምቀታቸ ደስ ይላል ”

"ሥዕሎቹን ለማየት ማን ወሰዳችሁ ?”

“ አባባ ' እኔ ሉሲ ' ሚስዝ ሔርና ባርባራ ሆነን ሔደን ነበር ባርባራ ያኔ እናታችን አልሆነችም ነበር ” አለና ድምፁን ድንገት ዝቅ በማድረግ '“ ሎሲ አባባን ምን ብላ ጠየቀችው መሰለሽ ?”

"ምን ብላ ጠየቀችው ? "

ከነዚያ ነጭ ነጭ ከለበሱት ብዙ ሰዎች ውስጥ እማማም አብራ ትኖር እንደ
ሆነ ወደ መንግሥተ ሰማያት ሒዳ እንደሆነ ጠየቀችው ያኔ በፊት እናታችን የነበረ
ችውንኮ ነው ወይዘሮ ሳቤላን ደሞ ስትጠይቀው ብዙ ሰው ነበር የሰማት

"አባትህ ምን መልስ ሰጣት ? ”

እንጃ " ምንም የመለሰላት አልመሰለኝም !ከባርባራ ጋር ወሬ ይዞ ነበር " እሷ አይገባትም ስለ ወይዘሮ ሳቤላ አባባ ፊት ምንም እንዳትናገር ዊልሰን ስንት
ጊዜ ነግራት ነበር መሰለሽ « ሚስ ማኒንግም እንደሱ ስትነግራት ነበር ከቤት እንደተመለስን ዊልሰን ሰማችና ትከሻና ትከሻዋን ይዛ አንዘፍዝፋ አንዘፍዝፋ ለቀቀቻት "

ለምንድነው የወይዘሮ ሳቤላ ስም ከፊቱ የማይነሣው ? አለችው »
👍14
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_ሦሥት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


...ሳቤላ ከማዳመጥ ሌላ አማራጭ አልነበራትም ግን ፍራንሲዝ ሌቪሰን ከሪቻርድ ሔር ጋር ምን እንዳገናኘው ገርሟት ነበር

ድሮ በልጅነቴ በጣም ልጅም አልባልም ክፍ ብዬ ነበር ሪቻርድ አፊ ዘንድ እመላለስ ነበር እሷ ከአባቷ ከጆርጅ ሆሊጆን ጋር ነበር የምትኖር » ብዙ ወጣቶች እሷ ዘንድ አይጠፉም "እሷ ግን ቶርን የተባለው የትልቅ ሰው ልጅ በመሆኑ ከሁሉ አብልጣ ትወደው ነበር " ያ ሰው በአካባቢው የሚያውቀው አልነበረም
በምስጢር ሹልክ ብሎ ፈረስ አየጋለበ ይመጣና እንዳመጣጡ ሹልኮ ይመለሳል አንድ ቀን ማታ ሆሊጆን በጥይት ተገደለ ሪቻርድ ተሸሸገ " ምስክሩ በሱ ጠነከረበት « ፍርድ ቤትም ገዳይነቱን አምኖ ወሰነበት " ሁላችንም እሱ ስለ መግደሉ አልተጠራጠርንም አሁን እናቴ የልጅዋን ነገር እያነሳች በኅዘን ልትሞት ሆነ " ማንም ሊያጽናናት አልቻለም " በዚህ ዐይነት ያለ ምንም ለውጥ አራት ዓመት ያህል ቆየ።
ከዚያ በኋላ ሪቻርድ በምስጢር ለጥቂት ሰዓቶች ወደ ዌስት ሊን መጣና ወንጀለኛው እሱ ሳይሆን ቶርን የተባለ ሰው እንደ ነበር ነግሮን ሔደ ቶርንን ለማግኘት ብዙ ጥረት
ተደረገ " ነግር ግን ማን እንደ ነበረ የት እንደ ነበረ ከየት እንደ መጣ ወዴት እንደ ሔደ የሚያውቅ ሰው ሳይገኝ ጥቂት ዓመታት ዐለፉ " አንድ ጊዜ ቶርን የተባለ ካፒቲን
ወደ ዌስት ሊን መጣ። መልኩ ሁኔታው ሁሉ ሪቻርድ ከሰጠን ምልክት ጋር አንድ ሆነ " እኔም ሪቻርድ የነገረን ነፍሰ ገዳይ ቶርን እሱ መሆን አለበት ብዬ አመንኩ አሁን ምን መደረግ እንደሚገባው እንኳን ሳይታሰብበት ካፒቴን ቶርን ወደ መጣበት ሔደ አሁንም ከዚያ በኋላ ዓመቶች ዐለፉ ”

ባርባራ ዐረፍ አለች " ማዳም ቬን ፍዝዝ እንዳለች ቀረች " ያ ሁሉ ታሪክ ለሷ ምን እንደሚያደርግላትም አልገባትም "

“ኋላ ፍራንሲዝ ሌቪሰን የኢስት ሊን እንግዳ ሆኖ በሰነበተበት ዘመን ካፒቴን ቶርን የሔርበርትን ቤተሰብ ለመጠየቅ ወደ ዌስት ሊን መጣ አሁን ሰውየው
እሱ መሆኑን ሚስተር ካርላይልና እኔ አመንበት " ቢሆንም ይበልጥ ለማረጋጥ እንሯሯጥ ጀመር። እማማ እንደ ልቧ ወዲያ ወዲህ ማለት ስለማትችልና አባባም የሪቻርድን ነገር ለመስማት ስለማይፈልግ እኔ ብቻ ነበርኩ ከሚስተር ካርላይል ጋር በየጊዜ መገናኘት የነበረብኝ " ያኔ ፍራንሲዝ ሌቪሰንን ብዙ ጊዜ አይቸዋለሁ ኢስት ሊን ውስጥ ተደብቆ ስለ ተቀመጠ ለማንም ሌላ እንግዳ አይታይም ባለ
ዕዳዎቹ እንዳያገኙኝ ፈርቸ ነው ይል ነበር " አሁን ግን ውሸቱን ሳይሆን አይቀርም ብዬ መጠርጠር ጀመርኩ ሚስተር ካርላይልም በዚያ ጊዜ ዌስት ሊን ውስጥም ሆነ በአካባቢው በዕዳ የሚፈልገው ሰው የለም ያለውም ትዝ አለኝ » "

“ ታድያ በምን ምክንያት ነበር በግልጽ የማይወጣውና ከሰው የሚደበቀው?” አለች ወይዘሮ ሳቤላ አቋርጣ እሷም በበኩሏ ዘመኑ ይራቅ እንጂ ነገሩን በደንብ
ታስታውሳለች » የሚሹሎከሎከው ባለ ዕዳዎቹን በመፍራት መሆኑን ይነግራት ነበር » አንድ ጊዜ ብቻ በኢስት ሊን አካባቢ ፈላጊዎች እንደሌሉት አጫውቷታል

“ ከባለዕዳዎቹ የባሰ ፍራት ነበረበት " አለቻት ባርባራ “ እንዳጋጣሚ ሆነና
ካፒቴን ቶርን ከሔርበርት ቤተሰብ ዘንድ አንደ መጣ ከወንድሜ አንድ መልእክት
ደረሰን " መልእክቱም ለአጭር ጊዜ ወደ ዌስት ሊን መጥቸ ለመመለስ ፈልጌአለሁ የሚል ነው "ይኸንኑ ለሚስተር ካርላይል ነገርኩት " እማማ በጣም ተጨነቀችበት "
ሚስተር ካርላይልም የሪቻርድን ንጹሕነት ይፋ የሚሆንበትን መላ ለማግኘት ብዙ
ይጠበብበትና ይጓጓበት ነበር » ስለዚህ ከምን ጊዜውም የበለጠ ከሚስተር ካርላይል
ዘንድ እየተመላለስኩ መመካከር ግዴታ ሆነብኝ " አየሽ አባባና ሚስ ካርላይል ዘመዳሞች ናቸው " ስለዚህ የሪቻርድ መከራ የኛ ብቻ ሳይሆን የካርላይል ቤት ጭምር ነበር "

ሳቤላ ትዝታና መራራ ጸጸት ወደዚያ ዘመን ይዟት ተመለሰ " የሚስትር ካርይልና የባርባራ ቶሎ ቶሎ መግናኘት' በቅናት አመለካከት ሌላ ትርጕም መስጠቱን አስታወሰች " ለምንድነው ባልተረጋገጠ ነገር ከመከራ ላይ ለመውደቅ አእምሮን ያን ያህል ያስጨነቀችው ?

“ሪቻርድ መጣ " ጸሐፊዎቹ ወደ ቤታቸው ከሔዱ በኋላ እሱ ወደ ሚስተር ካርላይል ቢሮ ሹልክ ብሎ ሔዶ ከአንድ ክፍል እንደገባና ካፒቴን ቶርንን ተደብቆ
እንዲያው አስቸኳይ ዝግጅት ተደረገ " ካፒቴኑ ሚስተር ካርላይል የሚፈጽምለት አንድ ጕዳይ ነበረው " ሚስተር ካርላይልም ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ከቢሮው ድረስ
ቀጠረው » ስለዚህ ሁኔታውን ስለ ሪቻርድ ለማመቻቸት ምንም ችግር አልነበረውም የሚስተር ካርላይል ሚስት የኮበለለችው ያን ዕለት ሌሊት ስለ ነበር ምጊዜም ከአምሮው አይጠፋም

«ሳቤላ ድንግጥ አለችና ሽቅብ ተመለከተች »

" የሆነውን ኮ የምነግርሽ እመቤት ሳቤላና ሚስተር ካርላይል የራት ጥሪ ነበረባቸው " ሚስተር ካርላይል ከጥሪው ካልቀረ የሪቻድን ጉዳይ መፈጸም የማይቻለው ሆነ " መቸም ርኀሩጎና ለሰው አሳቢ ነው " ከራሱ ጥቅምና እርካታ ይልቅ ስለ ሌላው ደኅንነት ማሰብ ደስ ይለዋል " ስለዚህ ከጥሪው ቀረ " መቸም የሽብር ሌሊት ነበር " አባቴ ወጥቶ አምሽቷል ሪቻርድ በቀጠሮው መሠረት ወደ ዌስት ሊን በጨለማ በሚጓዝበት ጊዜ የመንገድ አደጋ ሊደርስበት ስለሚችል ተጨንቀናል " ስለዚህ እማማን እያረጋጋሁና እያጽናናሁ አብሬአት አመሸሁ " ሪቻርድ
ሚስተር ካርይል ጋር ያለውን ጉዳይ እንደ ጨረሰ ከእማማ ጋር ለመገናኘት
መምጣት ነበረበት ከተለያዩ ብዙ ዓመታቸው ሆኗቸው ነበርና።

ባርባራ ነገሯን ቆም አረገችና ሐሳብ ይዟት ጭልጥ አለ " ማዳም ቬንም ቃል ሳትተነፍስ ዝም አለች " ቢሆንም የሪቻርድ የካፒቴን ቶርንና የፍራንሲዝ ሌቪሰን ግንኙነት ምን እንደሆነ አላወቀችውም "

“በመስኮት ቁሜ ስጠብቃቸው ሚስተር ካርላይልና ሪቻርድ በአትክልቱ ቦታ በር ሲገቡ አየኋቸው ሰዓቱ ከምሽቱ ሦስትና በአራት መካከል ሳይሆን አይቀርም!
እንደ ተገናኘን ካፒቴን ቶርን ሪቻርድ ያለው ቶርን አለመሆኑን ሲነግሩኝ በጣም አዘንኩ ሚስተር ካርላይል ደግሞ' ' እንኳን እሱ አልሆነ ብሎ ደስ አለው
ሪቻርድ እማማ ዘንድ ገባ አባባ ካገኘው ይዞ ለፍርድ እንደሚያቀርበው ብዙጊዜ
ተናግሯል እሱ ተጫውቶ እስኪወጣ ድረስ እኔና ሚስተር ካርላይል ከግቢው ወዲያና ወዲህ እያልን የአባባን መምጣት አንድንጠባበቅ ተማከርን ከመጣ ሚስተር ካርላይል እያዝናጋው እንዲቆይና እኔ ሮጥ ብዪ ገብቼ ሪቻርድን እንዲሸሸግ እንዳስጠነቅቀው ከማማ ጋር ተነጋገርን ሚስተር ካርይልም የእማማን ልመና ተቀብሎ ሐሳቡ ተስማምቶ አብረን ከደጅ አመሽን " ሪቻርድም አልወጣም!ብዙ ቆየ አባባም አልመጣም " እኔና ሚስተር ካርላይልን ብዙ ጌዜ አስጠበቀን - ደስ የሚል የጨረቃ ሌሊት ነበር ።

ያልታደለችው ሳቤላ እጇን እስኪያማት እያፋተገች
አዳመጠች ባርባራ ምንም ሳትጠረጥር የሆነውን ሁሉ እያስታወሰች በቅንነቷ ስትነግራት ጸጸቱ እንደ እሳት ይፈጃት ጀመር ሁለቱ እጅ ለእጅ ተያይዘው ሲንጎራደዱ
👍13👏1🤔1
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_አራት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ው

በፉጨት የሚጋልብ ከባድ ንፋስ መለል ያሉትን ረጃጅም ዛፎች እየለመጠ ሰፋፊ ቅርንፎቻቸውን አያወዛወዘ ቅርንጫፍን ከቅርንጫፍ እያላተመ
አዋከበው » ቅጠል ከቅጠል እያማታ ኢስት ሊንና አካባቢውን አዋከበ

ድምፁ የሚያሳዝን አመጣጡ የሚያስፈራ ቅጽበታዊ ነፋስ ተለዋወጠ " ዝናብ አዘል ዳመናዎች ተጠረቃቀሙ » በዚያ ቅዳሜ ምሽት ብቻውን
ይጓዝ የነበረ አንድ የሩቅ መንገደኛ ዝናቡ ከመንገድ እንዳይዘው እያሰበ › በእግሩ
ይኳትናል ሰውየው የመርከበኛ ልብስ ለብሷል " ከሰማያዊው አንገትያው በላይ ያለውን አንገቱንና ፊቱን ቸምቸም ያለው ጢሙ ሸፍኖታል " ከግንባሩ ዝቅ አድርጎ የደፋው ባርኔጣው ለጢሙ ተጨማሪ ሆኖ ጋርዶታል ሰፊና ሸካራው ሱሪውን በቀበቶ አጥብቆ ታጥቆ አጭር ሰፊና ወፍራም የመርከበኛ ሱፍ ካፖርት ደርቦ እየተወዛወዘ ቢን ሌን ደረሰ » ቀደም ሲልም በዚህ ታሪክ የተወሳው ቢን ሌን ስላች
መንገድ ነው ። ከዚያ ቀጥሎ እግር በማይበዛበት በአንድ ትንሽ በር ዐልፎ ከኢስት ሊን ምድረ ግቢ
ገባ ።

የገባበትን በር መልሶ ዘጋው መወርወርያውን ቀረቀረው ከዚያ በየት በኩል
መሔድ እንደሚገባው ቆም ብሎ አሰላሰለ "ቆይ እስቲ” አለ ለራሱ » “ በዛፎቹ
የተሸፈነ መንገድ ያለችኝ በግራሮቹ አጠገብ ሳይሆን አይቀርም ስለዚህ ወደ ቀኝ
መታጠፍ አለብኝ " ለመሆኑ ከሁለቱ አንዱ እየጠበቁኝ ይሆን ?”"

አውነትም ባርባራን የምሽት አየር ለመቀበል የወጣች መስላ ስትንጐራደድ
አገኛት " የናፍቆታቸውን ተናንቀው ተሳሳሙ " ሁለቱንም ሲቃ ተናነቃቸው "
ባርባራ እንደ ትንሽ ልጅ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች " እንቅ አድርጎ ይዟት የነበረውን ለቀቃትና ትክ ብሉ አያት "

“ ታዲያስ ባርባራ ! በቃ አሁን አግብተሽ ትዳር ይዘሽ ተቀምጠሻል !”

“ አዎን በትዳሬም ደስተኛ ነኝ " ያንተ ነገር እየተደቀነብኝ ከማዘኔ በቀር
ምንም የጐደለብኝ የለም " ብታየው በጣም የሚያሳሳ ልጅ ወልጃለሁ እሱም
አሁን አንድ ዓመት ሊሞላው ነው " በቅርቡ ደግሞ ሁለተኛ ልጄን እወልዳለሁ ”

ሰዎቻችንሳ እንደ ምን ናቸው ?”

“ ደኅና ናቸው » እማማም ከቅርብ ጊዜ ወዲሀ በጎ ናት

" ዛሬ ግን ያንተን መምጣት አላወቀችም "

“ዛሬስ እሷን ማየት አለብኝ ከዚህ ቀደም ሳላያት መሔዴን ታስታውሻለሽ የለ?”

“ ሁሉም በጊዜው ይሆናል " የሊቨርፑል ኑሮስ እንዴት ይዞሃል ? እዚያ ምን
ትሠራለህ ?”

“ አጥብቀሽ አትጠይቂኝ ባርባራ " የተወሰነ ሥራ የለኝም " ያገኘሁትን
እሠራለሁ " ከዚህ በምትሰጡኝ እየተደገፍኩ እኖራለሁ " ግን ለምንድነ© ወደዚህ የጠራሽኝ ? ምን አዲስ ነገር ተገኘ ?”

“ እውን ቶርን እዚህ ብታየው ግን ታውቀዋለህ ?

“ ታውቀዋለህ ወይ ! ምኑ ይጠየቃል ? ”

“ ዌስት ሊን ላይ የሕዝብ እንደራሴነት ምርጫ በመካሔድ ላይ መሆኑን ታውቃለህ?

“ አዎን ሚስተር ካርላይልና ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን እንደሚወዳደሩ ከጋዜጣ አንብቢያለሁ።

“ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንን እንዴት ልታውቀው እንደ ቻልክ ልትነግረኝ ትችላለህ
· ሪቻርድ ? ”

“ እሱንማ ዐውዋዋለሁ ከቶርን ጋር ሁለት ጊዜ አይቸዋለሁ „ “

“ እኔ የምልህ እንዴት ልታውቀው ቻልክ ? ”🍾

“ ቶርንን ከአንድ ሰው ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ አየሁትና አጠገቤ የነበረውን
አንድ ታንኳ ቀዛፊ በእጄ እያሳየሁ ያውቀው እንደሆነ ጠየቅሁት " እኔ ያመለከትኩትን ሰውዬ እንደሚያውቀውና ካጠገቡ የነበረውን ግን ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን መሆኑን ነገረኝ

“ እንግዲያውስ ሪቻርድ አንተና ታንኳኛው አንድ የሆነ ስሕተት አድርጋችኋል " ወይ አንተ ስታሳየው ወይ ደግሞ እሱ ያልጠየቅኸውን ሰው ሲያሳይህ አስተውለህ አላየኽውም እንጂ ' ቶርን ፍራንሲዝ ሌቪሰን ራሱ ነው

“ ምን ማለትሽ ነው ... ባርባራ ” አላት ዐይኖቹን አፍጥጦ እያያት

"ነው አለችና ራሱ ሪቻርድ ቢን ሌን ላይ አየሁት ካለበት ጊዜ ጀምሮ ስትጠረጥረው እንደ ኖረችና፡ ከዚያም በመጨረሻ ይፈለግ የነበረው ቶርን ራሱ ፍራንሲዝ ሌቪስን ለመሆኑ ኦትዌይ ቤቴልና ኧበንዘር ጄምስ ለይተው እንዳወቁት አብራርታ ነገረችው

ሁለቱም ሊያወቁት ይችላሉ ” አለ ሪቻርድ " ጄምስ ራሱ ሆልጆን ዘን ይሹለከለክ ስለ ነበር ቶርንን ብዙ ጊዜ አይቶታል" ኦትዌይ ቤቴልም በፊት ቢክድም አይቶት ሊሆን ይችላል - ”

ሪቻርድ ከሩቅ አንድ ሰው ሲመጣ ሲያይ ጊዜ ጥሏት ሮጠና ከአንዱ ቁጥቋጦ
ውስጥ ድርግም አለ » ባርባራ ሣቅ አለች " ለካስ ሚስተር ካርይል ኖሯል "

“ ዛሬም ትፈራለህ ሪቻርድ ? ” አለው ሲጨብጠው „ “ ዛሬስ የመንገድ ልብስህን ለውጠሃል።

በፊት ስለብሰው የነበረው ስለ ታወቀብኝ ለብሸው ለመምጣት ፈራሁ "
ስለዚህ ይህን በሁለት ፓውንድ ገዛሁ ”

ጸጉሩንም ጢሙንም ጭምር ነው ?

ጸጉሩማ እንዳዲስ ተበጥሮና ዘይት ተቀብቶ ነው እንጂ የድሮው ነው
ጸጉር አስተካካዩም የውሸት ጢሙን አበጃጅቶ የራሱንም ጸጉር ከርክሞ አንድ ሽልንግ አስከፈለኝ ሚስተር ካርላይል ... ባርባራ አረመኔው ቶርን ሌቪሰን ሆኖተገኘ ትለኛለች "

" አዝማሚያ ይመስላል ቢሆንም አንዳች ነገር ከመደረጉ በፊት አንተም
ሊቪስንን በዐይንህ አይተህ ማረጋግጥ አለብህ " ወደ ቨን ሆቴል ብቅ ብትል ሲገባ
ሲወጣ በቀላሉ ታየዋለህ ደሞ ዛሬ ሰው ሁሉ ልቡን ወደ ምርጫው ስለ አደረገ
የሚያውቅህም የሚያስብህም አይኖርም " ስለዚህ በጥንቃቄ አስተውለህ አረጋግጠህ ና አለው ሚስተር ካርላይል "
“ ቶርን መሆኑን ካረጋጥኩ በኋላ ምን እርምጃዎች ይወሰዳሉ ?

"ችግሩ እዚህ ላይ ነው ” አለ ሚስተር ካርላይል "

“ ክሱን የሚመሠርተው ከዚያም ጉዳዬን የሚከታተለው ማን ነው ?

“ እሱንማ አንተ ራስህ ነህ... ሪቻርድ " እኔ በዚህ ነገር በጣም አስቤበታለሁ
የምትከታተለው አንተው ነህ
“ አንተ ልትይዘው አትችልም
ሚስተር ካርላይል ? ''

“አልችልም !ሌቪሰን ከሆነ እንዴት አድርጌ ?” አለው "
ዐፈር ይብላ ይህ ርኩስ ” አለ ሬቻርድ በንዴት " ግን እሱ ቢሆን ምን ቸገረህ
ሚስተር ካርላይል ? ብዙ የተበደሉ ሰዎች ጠላታቸው በአጃቸው ሲገባ ለመበቀል ሲጣደፉ አይተሃል "

“ በሆሊጆን በተፈጸመው ወንጀል ፍርዱ እስከሚፈጸምበት ሰገነት ድረስ ልክታተለው እችላለሁ ስለ ራሴ በደል ግን አልሞክረውም" ወደ ዌስት ሊን ከመጣበት ጀምሮ ራሴን ለመቁጣጠርና ለመታገሥ ኃይለኛና አስቸጋሪ ትግል ባላደርግ ኖሮ ነፍሱ እስኪ ወጣ አስገርፈው ነበር "

“ ታዲያ ነፍሱ እስኪወጣ ብታስገፈው ዋጋውን አገኘ ኮ ነው የሚባለው ” አለው ሪቻርድ "

ለግድያው ተጠያቂ መሆኑን አምናለሁ ነገር ግን እኔ እጄን አንሥቸበት ወደ አሳፋሪ ሞት ከምሰደው ያነሣሁትን እጄን ቆርጦ ብጥለው እመርጣለሁ።ምክንያቱም የሰውዬውን የነፍስ ማጥፋት ወንጀል በኔ ላይ ከፈጸመው በደል ልለየው
አልችልምና " በሆሊጆን ሕይወት ብከታተለውም የሌላም ሕይወት ያጠፋ ለመሆኑ ሊሰወር አይችልም ሁልጊዜ አዛኝ የሆነው ዓለምም ለሚስተር ካርላይል ደስታውን
የሚገልጽበት በሚስተር ሆሊጆን ገጻይ ሳላስፈረደበት ሳይሆን ለተዋለበት ግፍ ብድሩን ስለ መለስ ይሆናል" ስለዚህ ነው በዚህ ነገር አልገባም
ሪቻርድ....

“ እሺ አንተስ ተወው ባርባራ ልትከታተልልኝ አትችልም ? " አላው "
ባርባራ ክንዶቿን ከባሏ ክንዶች ጋር አቆላልፋ ቁማ ትሰማለች "
“ ባርባራማ የኔ ሚስት ናት "
“ እንግዲህ ነገሩ ለመገለጽ ተስፋ የለውም " እኔም ተስፋ ቆርጬ ልሒድ ”
👍6
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_አምስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ስኞ ማታ ሪቻርድ ሔደና ከቦል ጋር ተግናኘ " ታሪኩን ከሥሩ ዝርዝር አድርጐ አጫወተው።

የምትለውን ሁሉ አምናለሁ .. ሚስተር ሪቻርድ ቶርንን በሚመለከት
ግን ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ነው ብሎ መቀበል በጣም ያስቸግራል »

“እኔ በተናገርኩት ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም በመጠየቅ ማረጋገጥ ትችላለህ ፍቃደኝነታቸውን እጠራጠራለሁ እንጂ ኦትዌይ ቤቴልም ሊመስክር ይችላል ኧበንዘር ጄምስም ሊመሰክር ይችላል።"

አሱም በዚያን ዘመን ቶርንን ያውቀው ነበር ። ዛሬ ደግሞ ሌቪሰን ሲባል አስተውሎ አይቶታል አለው ሪቻርድ "

ደኅና ... እንግዲያው መጀመሪያ ስለ ሰውዬው ማንነት ላረጋግጥና ከዚያ
በኋላ እቀጥላለሁ በርግጥ ልቪዞን የወጣለት ወሮበላ ነው እንደ ሊቪስንነቱ እንኳ። ይህ ሲጨመርማ እስኪ ለማንኛውም ኧበንዘር ጀምስን ጠይቄ የሚለውን ልስማ

እኔ ከዚህ እያለሁ ? ኧረ እንዳያየኝ እባክህ ካየኝ አለቀልኝ ማለት ነው...
ሚስተር ቦል „

“ ሌላ የእንግዳ መቀያ ክፍል ኮ አለን ... ሪቻርድ '

ኧበንዘር ጀሞዝ መጠራቱን እንደ ሰማ ወዲያው ደረሰና “በአስቸኳይ የሚጻፍ
ነገር አለ እንዴ ? ” አለው ሚስተር ቦልን ”

“ኧረ የለም የጠራሁህ አንድ ሁለት ጥያቄዎች እንድትመልስልኝ ብዬ ነው
ሰር ፍራንሲዝ ሌቪዞን በሌላ ስም ሲጠራ ታውቅ ነበር? ሚስተር ኧበንዘር

አዎን ባንድ ወቅት ቶርን ተብሎ ሲጠራ ዐውቅ ነበር

"ወቅቱ መቼ ነበር ? "

ሆሊጆን በተገደለበት ዘመን ነው " ሁላችንም በተመሳሳይ ምክንያት በዚው አካባቢ ስንመላለስ እሱም አፊ ሆሊጆንን በወዳጅነት ይዟት ስለ ነበር ማታ ማታ ከዚያ ቤት ጠፍቶ አያውቅም "

“ እኔ እሱን ዌስት ሊን መኖሩን አላስታውስም " የት ይኖር ነበር ?

የለም ዌስት ሊን ውስጥ አልተቀመጠም ጭልምልም ሲል ማለፊያ ፈረስ እየጋለበ ይመጣና ከአፊ ጋር ሲጫወት አምሽቶ አየጋለበ ይመለስ ነበር ።

ወዴት ነበር የሚመለሰው ? የሚመጣውስ ከየት ነበር ?”

“ ከስዌንስን አካባቢ ነበር ሁልጊዜ በደንብ ለብሶና ደማቅ ላባውን ከባርኔጣው ሰክቶ ይመጣ ነበር " እንግዲህ ይመጣ የነበረው ከሌቪሰን ፓርክ ሳይሆን
አይቀርም ያጎቱ ቤት በስዌንሰን በኩል ስለሆነ " ከዚያ መምጣቱ ምንም ሊያጠራጥር አይችልም።

“ጀምስ... ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን አንተ የምታውቀው ቶርን ስለ መሆኑ
የምትጠረጥርበት ነገር የለህም ?”

«ጌታዬ ... እርስዎ ሚስተር ቦል መሆንዎ ወይም እኔ ኧበንዘር ጄምስ
መሆኔ ያጠራጥራል ?
ሌቪሰንም የዚያን ጊዜው ቶርን ለመሆኑ የዚህን ያህል ነው እርግጠኝነቴ "

“ ይህን ነገር ከፍርድ ችሎት ቀርበህ በመሐላ ልታረጋግጥ ትችላለሀ ?

“ እኔ ነገም ቢሆን በማንኛውም ፍርድ ቤት ለመመስከር ዝግጁ ነኝ "

“ በል ሒድ I ስለዚህ ጉዳይ መነጋገራችንን ለማንም እንዳትናገር

ሚስተር ቦል የሪቻርድ ሔርን ቃል እየተቀበለ ሁለቱም እስከ ዕኩስ ሌሊት
ተቀመጡ “ ሚስተር ካርላይልም በነገሩ ላለመግባት የፈለገው በሌቪሰን ጉዳይ መነካካቱን ስለ ጠላው ነው። አይመስልህም..."ሚስተር ቦል?” አለው ሪቻርድ "

ጠበቃው ከንፈሩን አጣመመ “ አስቸጋሪ ነገር ነው " ሚስተር ካርልያል
ጥንቃቄውን ያበዛው የለ ? እኔ ብሆን አለቀውም ነበር " ዳሩ ምን ይሆናል " እኔና
ካርላይል የተለያየን ነን ”

በበነጋው ማክሰኞ ቀን የኧበንዘር ጄምስን ቃል መልክ አስይዞ ጽፎ እንዳበቃ ወደ አመሻሽ ላይ ሌቪሰን ፓርክ ሔዶ አንዳንድ ነገሮችን አጠናቅሮ ተመለሰ "

ሬቻርድ ሔር አድራሻውን ለእኅቱና ለአማቹ ሰጥቶ ወደ ሊቨርፑል ተመልሶ ሔደ።

ሮብ ጧት የማውንት እስቨርን ኧርል ተመልሶ መጣ " ልጁ ሎርድ ቬንም አብሮት ነበር » በዚያ ሰዓት ልጁ ወደ ትምህርት ቤቱ ወደ ኢተን መመለስ ነበረበት ነገር ግን ' የምርጫውን መጨረሻ ለማየት እንዲፈቅዱለት አባቱን አጥብቆ ለመነው"
“ከሁሉ ከሁሉ” አለው ቀስ ብሎ አባቱን “ያ ዲያብሎስ መሸነፉን ሲያውቅ እንዴት እንዶሚበሳጭና እንደሚያፍር ለማየት እፈልጋሁ።አባትየው የልጁን
ነገር በጣም ያከብር ስለ ነበር እሺ አለው ሌቱን ተጉዘው በቁርስ ሰዓት አካባቢ ደረሱ " በኋላም ከሚስተር ካርላይል ጋር ሆነው ወደ ዌስት ሊን ሔዱ

ዌስት ሊን ተሟሟቀች ደመቅ ደመቅ አለች " ምርጫው የሚካሔደው በዚያው ሳምንት ውስጥ ነው " ሰዎች በየግላቸውም ሆነ በኅብረት ስለ ምርጫው ሽር ጉድ ማለትን ሙያ ብለው ያዙት " የሚስተር ካርሳይል ኮሚቴ በክስሔድ ላይ ተቀመጠ " ዲያና ወዲህ ያለ የሚጐርፈው ሕዝብ ከብዛቱ የተነሣ የሚረግጠውን
ድንጋይ ማጐድጐድ የሚችል ነበር " ዳኞቹም የፍርድ ሥራቸውን ትተው ሐሳባቸውን ሁሉ ወደ ምርጫው ጉዳይ መለሱ ዘ የፍርድ ሥራቸን ቸለል ብለው ወይን ጠጅና ቀይ ጥብጣቦች በተስቀሉባቸው በበክስ ሔድ መስኮቶች እየዘለቁ ለሕዝቡ
በመታየት ትኩረታቸውን ሁሉ ከምርጫው ላይ አደረጉ "

ሚስተር ካርይል ከቢሮው ገብቶ ደብዳቤዎችን እየከፈተና አስፈላጊውን
ትእዛዝ ያሰፈረባቸው ካጠናቀቀ በኋላ ሚስተር ዲልን ጠራው ደብቤዎችን
በእጅ ሰጥቶትና አንዳንድ አስቸኳይ ትአዛዞችን ነግሮት ተነሣ "

«ትቸኩላለህ እንዴ አርኪባልድ?” አለው ሚስተር ዲል »
“ሰዎች በክስ ሔድ ይጠብቁኛል ምነው ?”

“ እኔስ ትናንት አንድ አስገራሚ ነገር አጋጥሞኝ ስለ ነበር ልነግርህ ብዬ ነው! ኦትዌይ ቤቴልና ሌቪሰን ሲጨቃጨቁ ሰማኋቸው "

“ እውነትህን ነው ?” አለው ከጠረጴዛው መሳቢያ አንድ ነገር እየፈለገ "

“በል እኔ እንግዲህ እንደዚህ ያለውን ነገር ባልሰማው እመርጣለሁ " ምናልባት የሰማኸው ነገር ለሪቻርድ ይጠቅመዋል የምትል ከሆነ ጉዳዩን ሚስተር ቦል
ሊከታተለው እያሰበ ስለሆነ ለሱ..ገባህ ለሚስተር ቦል ንገረው : '

ሚስተር ዲል ለጸሐፊዎቹ አለቃ አንዳንድ ትእዛዝ ከሰጠ በኋላ ወደ ቦልና
ትፊድማን ሔዶ ከሚስተር ቦል ጋር ለአንድ ሙሉ ሰዓት ዘግተው ተነጋገሩ ።

በዚያን ዕለት ዳኞቹ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ አልተሠየሙም ለዚያውም
ቢሆን ሔርበርትና ስፒነር ብቻ ስለ ነበሩ ከመሠየም አይቈጠርም" የሆነ ሆኖም
ሰዓት ባለማከበራቸው የሕሊና ወቀሳ እንደ ተሰማቸው ከፊታቸው እየታወቀባቸው ተከታትለው ገቡ።

ያን ጊዜ ሁለት ዐበይት ጉዳዮችን ብቻ ወሰኑ" ሁለቱም ዌስት ሊን ላይ ይካ
ፈሔድ ከነበረው ምርጫ የተፈጠሩ ነበሩ ። አንደኛው ጉዳይ አንዲት የብጫና ሁለተኛይቱ የቀይ ወይን ጠጅ ደጋፊዎች የሆኑ ሁለት ሴቶች ስለ ተወዳዳሪዎቹ ጥሩነት ሲከራከሩ በብረት ድስት የተደባቡ ነበሩ ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ ጥቂት ልጆች የሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንን ምስል በገለባ ሠርተው ከተማውን ከዞሩ በኋላ ከአንድ ሣር ከነበረበት ቦታ ወስደው ሲያቃጥሉት ፡ የሌሎች ንብረት የሆነ መጠነኛ ሣርና አዝመራ ስለ አጠፉ ተከሰው ቀረቡ » የአንዳንድ ሳምንት እስራት ልጆቹን በየግላቸው እንዲገረፉ ብለው አሰናበቷቸው ።

የመጨረሻውን ጉዳይ ወስነው እንዳበቁ ሚስተር ቦል እየተንደረደረ ገባና
ዳኞቹ አንድ ጉዳይ በዝግ ስብሰባ እንዲያዩለት ለመነ ዳኞቹም የጠበቃው አቀራረብ' “ ጉዳዩ ምን ቢሆን ነው? የሚል ጕጕት ስለ አደረባቸው እርስ በርሳቸው ተያዩና ከተመካከሩ በኋላ ጥያቄውን ተቀብለው ሊያዩለት ገቡ" ጉዳዩን እስከ አሥር ሰዓት ተኩል ሲመለክቱ ቆዩ ሲወጡ" የጠበቃው ቦል ማመልከቻ ያደናገራቸውና ያስደነገጣቸው ይመስል እነዚያ የተከበሩ ዳኞች በፊታቸው ላይ ፍራትና መቀጨም ይታይባቸው ነበር "
👍13😁1
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_ስድስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

...“ አዬ ሚስተር ካርላይል እኛ ሥጋ ለባሾች ምስኪን ሐኪሞች ታላቁ ሐኪም ብቻ ሊፈጽመው የሚችለውን ተአምር መሥራት ብንችል ፈሊያጊያችን ምን ያህል
በበዛ ነበር ? በጥቁሩ ዳመና ውስጥም ስውር ትኩረት መኖሩን አስታውስ አትርሳ በል ደህና ሁን ወንድሜ

ሚስተር ካርላይል ተመልሶ ገባ ወደ ሳቤላ ቀረበና
እንደ ተቀመጠች ቁል
ቁል ተመለከታት » ፊቷን ደህና አድርጋ በመነጽሯ ሸፍናው ስለ ነበር በጣም
ሊታየው አልቻለም የሱም ሐሳብ እሷን ለማነጋገር
እንጂ ፊቷን ለማጥናት አልነበረም “ይኸ በጣም ከባድ መርዶ ነው " አንቺ ግን ከኔ ይበልጥ የተገነዘብሺውና
ያሰብሽበት ይመስለኛል ”

ከተቀመጠችበት ድንገት ብድግ አለችና ወደ መስኮቱ ሔደች " አንድ የምትፈልገው ሰው በመንገዱ ሲያልፍ ያየች ይመስል ወደ ውጭ ትመለከት ጀመር "
ስሜቷ በሙሉ በሠራ አካላቷ ተማሰለ " ቅንጦቿ ይነዝራሉ ጉሮሮዋ ለብቻው
ይመታል ትንፋቯ ቁርጥ ቁርጥ ይላል " ምን ትሁን ? በልጃቸው ጤንነት ከሱ
ካባቱ ጋር በምስጢር መነጋገሩን እንዴት ትቻለው የእጅ ሹራቦቹን እንደ አሳት
ከሚፈጃት እጆቹ አወለቀቻቸው " ላቧን ከግንባሯ ጠረገች ለመረጋጋት ሞክረች
ለሚስተር ካርላይል ምን ምክንያት ትስጠው ?

“ልጁን በጣም ነው የምወደው ...ጌታዬ ” አለችው በከፊል ፊቷን ወደሱ መለስ አድርጋ“ ስለዚህ የሐኪሙ ግልጽና ቁርጥ አነጋገር አንጀቴን አላወሰው !የምሆነውን አሳጣኝ ለሕመም ሰጠኝ "

አሁንም ሚስተር ካርይል ወደ ቆመችበት ተጠጋና “በውነቱ ለኔ ልጅ ይህን
ያህል መጪነቅሽ ሲበዛ ደግ ሰው ነሽ ” አላት "

እሷ ግን ምንም አልመለሰችለትም "

“ በይ እንግዲህ ይህን ነገር ለሚስዝ ካርላይል እንዳትነግሪያት " አላትና
ነገሩን በመቀጠል፡“እኔው ራሴ ብነግራት ይሻላል " በአሁኑ ሰዓት በድንገት ማዘንም መደንገጥም አይኖርባትም።”

“ምን የሚያሳዝናቸው ወይም የሚያስደነግጣቸው ነግር አለ እናቱ አይደሉ?”
አለችው " አነጋገሯ በቁጭት በንዴትና በግለት ስለነበር ባርባራን የምታጥላላ መሰለባት " ልትጨምርበት ስትል የሷንና የባርባራን ያሁኑ ማንነት ትውስ አላት "
በገጽታዋ ሳታሳይ ድንግጥ አለችና መደምደሚያውን በጣም አለዘበች " ሚስተር ካርላይል ዐይኖቹን አፈጠጠ " ድምፁ ተለዋወጠ "

“ ሳታስተውይ በችኮላ ትናገሪያለሽ ... ማዳም " አላት "

በተናገረችው መልስ ደነገጠች " ማን መሆኗን አሰበች " ኃፍረትም ውርደትም ተሰማት ። እሷ ስለ ሚስቱ እንደዚህ ብላ ሳትናገር ሚስተር ካርላይል ከዕብድ የባሰች አድርጎ ሊገምታት እንደሚችል ተሰማት ትቷት ሲሔድ የልመና ከንፈሮቿን
እያንቀጠቀጠች ወደሱ ምልስ አለች "

“በትክክል ገብቶኝ ከሆነ የሚወስደው ስለሌለ ወደ ሙቀት አገር ሊሔድ አይችልም ስትባባሉ የሰማሁ መሰለኝ " ይህ ከሆነ ለምን እኔ ይዤው አልሔድም ?አደራውን ለኔ ይስጡኝ "

“ አይሔድም ዶክተር ማርቲን የረባ ዕድሜ ስለማይጨምርለት ባይሔድ
ይሻላል ማለቱን ሰምተሻል "
“እሱማ ለጥቂት ሳምንት ብቻ ነው ብሏል " ታዲያ እነሱስ ቢሆኑ ዋጋ የላቸውም አለችው።

“ሊኖራቸው ይችላል # ግን ጥቅማቸው ከምኑ ላይ ነው ? ለሱ ኮ ከቤተሰቡ
ተነጥሎ በብቸነት የሚሠቃይባቸው ሳምንቶች ይሆኑበታል" ስለዚህ ልጄ ከኔ መለየቱ የማይቀርለት ከሆነ እስከ መጨረሻው የመለያያ ቅጽበት አብሮኝ መቆየት አለበት።

ዊልያም በሩን ከፈት አደረገና ጭንቅላቱን ብቅ አድርጎ ተመለከተ "ሔደ
አይደለም እኔ ኮ የዓሳ ዘይት እንዳይሰጠኝ ካልወጣ ኤልመጣም ብዬ ነው የቆየሁት” አለ።

ሚስተር ካርላይል ተቀመጠና ዊልያምን ከጉልበቱ ላይ ቁጭ አድርጎ ግንባሩን ከልጁ ሐርማ ጸጉር አሳርፎ ሰማህ ልጄ!ዘይቱ በጎ እንዲያደርግህና እንዲያበረታህ መሆኑን ታውቃለህ?። አለው

"እኔ ግን የሚያጠነክረኝ አይመስለኝም " ዶክተር “ማርቲን እኔን ይሞታል
አለኝ ?

"ስለ መሞት ደግሞ ማን ነገረህ ?”

“ አንዳንዶቹ ያወሩታል "

“ ዝም ብለህ እንድትሞት አናደርግም " አንተን ለማዳን ምን ማድረግ እንዳለብን ለማወቅ እንሞክራለን ይኸን ታውቃለህ ዊልያም ?

“ አዎን ዐውቃለሁ ”

ሚስተር ካርላይል ተነሣና ልጁን ለማዳም ቬን ስጥቶ'“ በይ ደህና አድርገሽ
ተጠንቅቀሽ ያዥው ብሏት ወደ ኮሪደሩ ዐለፈ

“ አባባ ! ... አባባ!እፈልግሃለሁ ” አለና ማዳም ቬንን ትቶ ወደሱ እየሮጠ
በእግርህ ነው ወደ ቤት የምትመለሰው ? አብሬህ በእግሬ ልምጣ ?”

በዚያ ሰዓት በዚያ ስሜት የልጁን ጥያቄ ለመቀበል እምቢ የሚልበት አንጀት አልነበረውም “ እሺ እስክመለስ ድረስ እዚህ ጠብቀኝ ” ብሎት ወጣና
ደርሶ ተመለሰ " እሱ የዊልያምን እጅ ይዞ ማዳም ቬን ከዊልያም ቀጥላ ፈንጠር ብላ ጉዞ ቀጠሉ "

በዚህ ዐይነት እየሔዱ ሳለ ትንሹ ሰውዬ ከፖስታ ቤት እየሮጠ ወጣና ከነሱ
ጋር ፊት ለፊት ግጥም አሉ ሰውየው የተደናገጠ ይመስል ነበር መንገደኞችንም
ድንገት ድቅን በማለት ካደናገራቸው በኋላ ወደ ጐርፍ መሔጃው ዘወር አለ " ሰውየው ፍራንሲዝ ሌቪሰን ነበር !

ዊልያም በልጅነት ቅንነቱ ዞር ብሎ አይቶት እኔ እንደዚህ ሰውዬ አስቀ
ያሚና መጥፎ ሰው አልሆንም " አንተሳ . . . አባባ ?

ሚስተ ካርላይል አልመለሰለትም " ማዳም ቬንም ሳታስበው ድንገት አይታዋለች » ከዚያም መንግዳቸውን ቀጠሎና ሚስተር ጀስቲስ ሔር በር ሲደርሱ ባለቤቱንም ከዚያው ቁሞ አገኙት ዊልያም' ሚስዝ ሔርን ከአትክልቱ ቦታ ወንበር
ላይ ተቀምጣ አያትና ሊስማት ሔደ ሚስዝ ሔርን ልጆቹ ሁሉ ይወዷት ነበር "
“ እኔ የምለው ሚስተር ካርላይል ዛሬ ወደ ፍርድ ቤት አልሔድኩም ነበር "
አንድ ማመልከቻ በምስጢር እንደ ቀረበላቸው ፒነር ነገረኝ ዝም ብለው የማይታመን የማይሆን ነገርኮ ነው " አንተስ ምን የምታውቀው ነገር አለ ?

" እኔ ያወቅሁት ነገር የለም ”

ነገሩ ዲክ ሆሊጆንን ያለመግደሉን ለማሳወቅ የታሰበ ይመስላል” አለ በዛፎቹ ሥር በስውር የሚያዳምጡ እንዳይኖሩ የሠጋ ይመስል ድምፁን ዝቅ አድርጎ "
የገደለው ሌቪሰን እንጂ ... ትሰማኛለህ ? ሌቪሰን እንጂ እሱ አይደለም " የሚል
ነገር አቅርበዋል አሉ " ግን በጭራሽ የማይሆን የማይመስል ወሬ ነው”

“ ስለ ሪቻርድ ከደሙ ንጹሕነት ” አለ ሚስተር ካርላይል !“ እኔም ካመንኩበት ብዙ ዘመኔ ነው

“ስለ ሌቪስን ወንጀለኝነትሳ ? አለ ጀስቲስ ሔር ዐይኖቹን በመገረም አፍጦ።

“ ስለሱ የምሰጠው አስተያየት አይኖረኝም ” አለው ሚስተር ካርላይል ቀዝቀዝ ብሎ።

“ ሊሆን አይችልም ። ዲክ ነጻ ሊሆን አይችልም ዲክ ነጻ ሆነ ማለት ዓለም
ተገለበጠች ማለት ነው !! ”

“ አንዳንዴም አይሆንም ያሉት ይሆናል " ሪቻርድ ንጹሕ የመሆኑ ነገር በፀሐይ ባደባባይ ሊረጋገጥ ነው” አለ ሚስተር ካርላይል

“ በዚያኛው ከተመሰከረበት ደግሞ የመያዣውን ከፖሊስ ወስደህ አንተው ራስህ ትይዘዋለህ ”

“ እኔስ በእንጨትም አልነካው ሰውየው ከተቀጣ ይቀጣል እኔ ግን የቅጣቱን መንገድ ጠራጊ በመሆን አልረዳም ”

“ እና ዲክ ነጻ ሊሆን ይችላል ?” ታዲያ ለምን ጠፋ ? ለምን ቀርቦ እንደዚህ ብሎ አላመለከተም ?”

"እርስዎ አንቀው ለፍርድ እንዲያቀርቡት ነው? ለማቅረብ መማለልዎን ያውቃሉ ? አለው ሚስተር ካርላይል "

ጀስቲስ ሔር በጣም እየበረዶ ሔዶ ።

“ እንዴ ግን ካርላይል
ያቺ ከንቱ በሕይወት ቆይታ ብታይ ኖሮ አንጀትህ
እንዴት በሻረ ! ያ የተሳሳተ አድራጎቷ ምን ያህል ይቆጫት ምን ያህል ያሳርራት ነበር !”
👍14
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_ሰባት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


“ስለ ሰውዬው ወንጀል እኔ አላውቅም " ልጅዎ ግን ነጻ እንዲሚወጣ አይጠራጠሩ አይዞዎ ፤አይጨነቁ " የደስታ ዘመን እየመጣልዎ ነው” ብሎ አበራታቷትና አሳምኗት ወጣ

ሚስ ካርላይል የወንድሟን የምርጫ ቀን ምክንያት በማድረግ በሕይወቷ
አድርጋው የማታውቀውን እስከ መጨረሻው አጊጣ ለብሳ ስትንጎራደድ በነበረችበት ወቅት ዐይን አውጣዋ አፊ ሆሊጆንም በበኩሏ ከሚስ ካርላይል አሽከሮች ጋር ተመሳጥራ ሾልካ በመግባት ሚስ ካርላይል ከነበረችበት በላይ ከነበረው ፎቅ ወጣች " በተጐነጐነው ጸጉሯ ላይ ቆብ ደፍታ እስከ ሽንጧ ድረስ ደረጃ እየመጣለት የተሰፋው የነጭና የአረንጓዴ ዝንጉርጉር ቀሚስ ለብሳለች » ዐይነ ርግብና ለስላሳ ነጫጭ የጅ ጓንቲዎች አጥልቃ በዳንቴል የተከፈፈና ሽቶ የተርከፈከፈ መሐረብ ይዛ ባጠቃላይ ውድና ቀለመ ደማቅ በሆነ ሙሉ ልብስ አጊጣ እንደ ሱፍ አበባ ጐልታና ደምቃ በአደባባይ ለመላው ሕዝብ እየተጐማለለች ስትታይ ቆየች ደግነቱ ግን ሚስ ካርሳይል አላየቻትም ።

“ መልከ መልካም ነውኮ !” አለች ለሚስ ካርላይል ገረዶች ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ከፊት ለፊታቸው ሲደርስ አየችውና "

ግን መጥፎ ሰው ነው የሚል ነበር ያገኘችው መልስ ። ሚስተር አርኪባልድ ጋር ተወዳድሬ “አሸንፋለሁ ብሎ ማሰቡና እዚህ መምጣቱም ያስገርማል” አሏት"

“ምን እያደረጉ ነው?” አለችና'“እንዴ ኧረ ፖሊሶችም አሉ !” ብላ ጮኸችና'' እጁን በካቴና እያሰሩት ነው ምን አደረጋቸው ? እያለች ለፈለፈች።

ለጩኸቷ መልስ አላገኘችም ። ፊቷ ዐሥር ጊዜ እየተለዋወጠ በጭንቀት ስትመለከት ቆየችና “ አንዴ ” አለች ሰዎች ሲናገሩ ነገሩን ከአፊ ቀድማ የሰማችው
አንዷ ሠራተኛ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪስንና ኦትዌይ ቤቴል አባትሽን ሆን ብለው
ስለ ገደሉ ተይዘዋል ነው የሚባል ”አለቻት "

ምን ! ” ብላ ጮኸች አፊ "

“ ገዳዬ ሴቪሰን ነው " ሪቻርድ ሔር ከደሙ ንጹሕ ነው ይላሉ " አለቻት።

አፊ ነገሩን አዳመጠች " ምን ማለት እንደሆነ አሰበች " ከዚያ እየተንገዳገደችና እየተንቀጠቀጠች ሙሉ ለሙሉ መሬት ላይ ተዘረረች አፊ ሆሊጆን ሕሊና
ዋን ሳተች።

አፊ ሆሊጆን አቅሏን ስታ የነበረችው ለቋት ወደ ሚስ ካርይል ቤት ተሸሽጋ
እንደ ገባች ሁሉ ተሸሽጋ ወጣች " ከሚስ ካርላይል ቤት ትንሽ ራቅ ብሎ ዐይብ ያሣማ ሥጋና ልዩ ልዩ የምግብ ቅባቶች የሚሸጡበት ሱቅ አለ » ሱቁ ጥሩ ታዋቂነት እንዳለው ካጠና በኋላ ገዝቶ
የሚሠራበት አንድ ከለንደን የመጣ መልከኛ ልጅ እግር ነጋዴ ነው ሱቁ ምርጥ
ዕቃ በማቅረቡ የታወቀ ለመሆኑ የሚስ ካርላይል ደንበኛ ለመሆን መብቃቱ ብቻ መረጃ ነበር " የፊተኛው ባለቤቱ በቂ ገንዘብ ስለ አጠራቀመ ለሚስተር ጂፍን
ሲሸጠው ሰዎች እሱም ሠርቶ የሚበቃውን ያህል ገንዘብ ሲይዝ እንደ ፊተኛው
ሰውዬ ይሸጠዋል " እያሉ ተንብየውበታል "

አፊ ከሚስ ካርላይል ቤት ወጥታ ከሱቁ ፊት ለፊት ስትደርስ ሚስተር ጀፊንን ከሱቁ በር ቁሞ ታየዋለች ከውስጥ ረዳቱ ከዕንጨት በርሜል እያወጣ ቅቤ
ይሸጣል " አፊ ቆም አለች " ሚስተር ጂፊን መቸም የሷ ነገር ጭንቁ ነው " ልቡ
እስኪጠፋ ይወዳታል እሷም እሱ ሲያወዳድሳት ደስ ደስ ይላታል "

“ እንደ ምን ዋልሽ ... አፊ” አላት ነጭ ሽርጡ እንዳይታይበት ተጠንቅቆ
አጣጥፎ ከደበቀ በኋላ እጁን ወደሷ ዘረጋ ። ምክንያቱም ስለ ሽርጡ አሳፋሪነት አንድ ጊዜ ጠቆም አድርጋው ነበር "

“ ደኅና ነህ ጄፈን" አለችውና ነጫጭ ጓንቲዎቿን እንዳደረገች ራሷን ዝቅ በማድረግ ለሰላምታ የቀረበላትን እጅ በጣቷ ጫፍ ነካ አደረገችው “እኔ
ደሞ ” አለችው የጅ መሐረቧን ዐይነ ርግቧንና ( ቀለበትኛ የተሠራውን ጸጉሯን በማሳየት እየተውረገረገች “ዛሬ ሱቅህን ዘግተህ ዕረፍት ያደረግህ መስሎኝ ነበር
ሚስተር ጂፊን ” አለችው።

“ ሥራ መከበር አለበት” አላት ጂፍን ሐሳቡ በሷ ፍቅር ተይዞ ነጻ ሆነሽ በሽርሽር ላይ መሆን መቻልሽን ባውቅ ኖሮ ምናልባት ባጋጣሚ እንደማገኝሽ ተስፋ በማድረግ እኔም ዕረፍት እወስድ ነበር"

አባባሉ ከእውነተኛ ፍቅር የመነጨ መሆኑን ተገንዝባ ' “ ምንም እኮ አያውቅም ሥራው ሁሉ እንደ ከብት ነው ' አለች ' በሐሳቧ "

“ እኔ በሕይወቴ ያለኝ ታላቅ ደስታ .. ሚስ አፊ አንቺ ስታልፊ በሱቁ መስኮት አሻግሬ ማየት ነው ”

“ ኧረ ጉዴ !” አለች አፊ ገፍቶ የመጣባትን ሣቅ ለማገድ እየሞከረች : “ለምን እንደሚጠቅምህ አላውቅም "ዐይን ካለህ ከአንድ ሁለት ሰዓት በፊት ወደ ሚስ ካርላይል ዘንድ ስሔድ አይተኸኝ ይሆናል”

“ አዬ ! ዐይኖቼ የት ሔደው ኖሮ ይሆን?” አለ እየተጸጸተ “ አሃ ! ገባኝ እነዚያ የቅቤ በርሜሎችን ስመረምር ነው ይገርምሻል . . . ሚስ ሆሊጆን የተበላሹትን ስለ ላኩልኝ መልሼ ልልክላቸው ነው ”

“ አ ... ይ ! እኔ የቅቤ በርሜሎች ብሎ ነገር አላውቅም " እንዲህ እንዲህ ያለው ነገር ከክብሬ በታች ነው
“ እንዴታ እሱስ እውነትሽን ነው ... ሚስ ሆሊጆን “ ምንም እንኳን የገበያውን ጥቅም ለሚገባው ከፍተኛ ትርፍ ቢኖረሙም ካንቺ ክብር ጋር አይስማማም »

“ የምን ጩኽት ነው የምሰማው ? አለች አፊ "
"መራጮች ለሚስተር ካርላይል ሲያጨበጭቡ ነው መመረጡን ስምተሻል
ይመስለኛል

" የለም አልሰማሁም ”

ያኛውማ የገዛ ወዳጆቹ አስወጡትና ተገላገሉት » እንግዲህ እንደራሴአችን
ሚስተር ካርይል መሆኑ ነ&ዘው " ይባዋል ... መቸም እንደሱ ያለ ሰው የለም ‥

“እነዚህ ሁሉ ደንበኞችህ ናቸው እንዴ ? ሁሉንም ማስተናድ ከባድ ሥራ
ነው ሰውዬህ ብቻውን አይዘልቀውም " ስለዚህ እያወራሁ ጊዜ ልወስድብህ አልፈልግም ሔድኩልህ "
አለችውና እየተንሳፈፈች ሔደች " ጂፊን ፍዝዝ ብሎ
ሲያያት ከቆየ በኋላ ከይኑ ስትጠፋ የግዱን ደንበኞቹን ወደ ማስተናገድ ዞረ »

ጂፊን በፍቅሯ ወጥመድ መግባቱን ዐውቃና እንደሚያገባትም ተማምና አፊ በዚያ በቅባት በተባላሸው ሱቅ በኩል ሳይሆን በጓዳ በር እየገባች ጠቅላላ የቤቱንና የእቃውን አያያዝና አቀማመጥ ' ባሏንም እንዴት እንደምትንከባከበውና እንዴት አድርጋ በፍቅሯ ዐሥሬ የመሽቀርቀርያ መሣሪያ እንደምታደርገው እያሰላሰለች በምኞት አየር ላይ ሰገነት ሠርታ በሐሳቧ እየተሽሞነሞነች ስትራመድ ኧበንዘር ጀምዝ ደርሶ ለቀም አደረጋት ።

“ እንደምነሽ . . አፊ ? ዛሬ ጧት ሚስ ኮርኒ መስኮቶች ላይ አየሁሽ "

“ ያንተ ነገር እንግዲህ በቃኝ . . . ኧበንዘር ጀምዝ በቀደም ለሚስተር ጀፊን የዱሮ ወዳጄ ነበረች ማለትህን እኮ ሰምቸሃለሁ ”

“ አዎን ነበርሽና ” አላት እየሣቀ "

“ አልነበርኩም " እኔ በዚያን ጊዜ ከበላዮችህ ጋር እንጂ ካንተ ጋር ምንም ግኙነት አልነበረኝም አሁንም እኔን ለመጉዳት ብለህ በሐሰት ስሜን ለማጥፋት ብታስብ ተሳስተሃል ... ኧበንዘር ጀምዝ " እኔ በዚህ ቦታ የተከበርኩ ሰው ነኝ " ስለዚሀ ዐርፈህ ተቀመጥ ”

“ ምነው አፊ ? ለምን እንደዚህ ትሆኛለሽ ? እኔ አንቺን ለመጉዳት አልፈልግም አንቺ እንደምትይው ብሞክርም አይሆንልኝም " አላት እየሣቀ "

ይኸው ነው ይበቃሃል አሁን ከኔ ራቅ የአንተ ህዝብ መሀል መታየትህ ለስሜ ደግ አይደለም " አለችው።

ደኅና መልእክቴን ከተቀበልሺኝ እሔድልሻለሁ " በይ አሁን ለዛሬ በዘጠኝ ሰዓት ፍርድ ቤት ከችሎቱ አዳራሽ ስለምትፈለጊ እንዳትቀሪ "

ከችሎት አዳራሽ ? እኔን ? ለምን ?
👍19
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_ስምንት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


የሕግ ባሥልጣኖቹ ገብተው ቦታቸውን ያዙ " በሌላ ጊዜ ቢሆን ዌስት ሊን
የማይረግጡት የሰላም ኮሚሺን አባሎች የሆኑ ሁሉ መጥተው ስለ ነበር መቀመጫ እንኳን
ሊበቃቸው አልቻለም " ምናልባት በተቃዋሚ ወገኖች የተሸረበ ደባ ይሆናል በማለት የተመሠረተበትን ክስ ስላላመኑበት የሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ወዳጆቾ
ሁሉ ተሰባስበው ከችሎት ተገኙ " ሎርድ ማውንት
እስቨርንም ከኮሚሽኑ አባሎች ጋር መቀመጫ ተሰጠው" ልጁ ሎርድ ቬንም ከሕዝቡ መኻል ገብቶ ተቀመጠ ሰብሳቢው ሚስተር ጀስቲስ ሔር እየተጀነነ ቦታውን ያዘ" ልጁን ከስቅላት ለማዳን
ቢሆንም በይሉኝታ ይበድለዋል ወይም ባባትነቱ ይጠቅመዋል ተብሎ አይታሰብም ነበር" ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንንም ቢሆን ከሕሊናው ውጭ ጥፋተኛ ያደርገዋል ተብሎ
አይገመትም " ከጐኑ የተቀመጠው ሌላዉ ዳኛ ኮሎኔል ቤቴል ነበር " ሚስተር ሩቢኒ ለሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ጥብቅና ቆመለት።

ሚስተር ቦል ከሪቻርድ የሰማውን መሠረት በማድረግና የፍንጩ መሠረት ግን ሪቻርድ መሆኑን ሳያነሣ ጭብጡን ብቻ በማቅረብ አስረዳ። ጭብጡን ከየት እንዳገኘው ተጠይቆ 'ምንጮን ለጊዜው ለመግለጽ ነገሩን የሚያበላሽበት መሆኑን
ግለጾ ሌቪስን ቶርን መሆኑን ማረጋገጥ ስለ ፈለገ በመጀመሪያ ኤበንዘር ጄምስ ተጠራ .

“ ስለ እስረኛው ስለ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ምን ታውቃለሀ ? ” አለው ጀስ
ቲስ ሔር።

.“ ብዙ አላውቅም ” አለ ኧበንዘር ጄምስ ' “ በርግጥ ካፒቴን ቶርን ሲባል
ዐውቀው ነበር ”

“ ካፒቴን ቶርን ?”

“ አፊ '“ ካፒቴን ቶርን ትለው ነበር " ኋላ ግን መቶ አለቃ እንደ ነበር ለማመቅ ችያለሁ

“ ይኸንን ከማን ልታውቀ ቻልክ ?”

“ ከአፊ! ስለሱ ስትናገር የሰማኋት እሷ ብቻ ነበረች ”
“ እና “ ከዚያ አይጫካ ከተባለው ቦታ ሁልጊዜ ታየው ነበር ?”

“ ከዚያና ከሆሊጆን ቤት ብዙ ጊዜ አየው ነበር "

“ ቶርን ብለህ አነጋግረኸው ታውቃለህ ?

“ ሁለት ሦስት ጊዜ ቶርን ብዬ ስጠራው መልሶልኛል " እኔ ስሙ መሰለኝ እንጂ
እኔ የሽፋን ስም ነው ብዬ አልጠረጠርኩም "ኦትዌይ ቤቴልና ሎክስሌይም
በዚሁ ስም ይጠሩት ነበር“ በተለይ ሉክስሌይ ከዱሩ ተለይቶ ስለማያውቅ • ቶርን
ስለ መሆኑ በሚግባ የሚያውቀው ይመስለኝ ነበር

“ ሌላስ ማን ያቀሙ ነበር ?
"ሟቹ ሚስተር ሆሊጆንም ቶርንን ከቤቱ እንዲመጣበት እንደማይፈልግ ለአፊ ሲነግራት ሰምቻለሁ።
“ቶርን ጋር የሚተዋወቁ ሌሎችስ ነበሩ ?”
“ ትልቅ እህቷ ጆይስ የምታወቀው መሰለኝ ከሁሎ የበለጠ የሚያውቀው ግን ሪቻርድ ሔር ነበር „”

ዳኛው ሪቻርድ ሔር የልጁን ስም ሲሰማ ግብሩ ከነመልኩ በዐይነ ሕሊናው
መጣበትና ከመቀመጫው እንዳለ ፊቱን ኮሶ አስመሰለው "

“ ቶርን ወደ ጫካው ይመላለስበት የነበረው ምክንያቱ ምን ነበር ?

“ አፊን በወዳጅነት ይዟት ነበር " "

“ ሊያገባት ሐሳብ ነበረው ?

“የዚህ ሐሳብ እንኳን የነበረው አልመሰለኝም ”
ሆሊጆን የተገደለ ዕለት አይተኸው ነበር ?

ሆሊጆን የተገደለ እለት አይተኸው ነበር?

የዚያን ዕለት እኔ ራሴም በዚያ አካባቢ ስላልነበርኩ አላየሁትም „”

“ግድያውን የፈጸመው እሱ ይሆናል ብለህ ጠርጥረህ ነበር ?”

"ኧረ በጭራሽ ! ሪቻርድ ሔር በወንጀሉ ተከሰሰበት እኔም አልገደለም የሚል ጥርጣሬ አልነበረኝም ”

“ ይኸ ከሆነ ስንት ዓመት ይሆናል ? አለ ሚስተር ሩቢኒ አቋርጦ ምስክር
ነቱ ያበቃ መስሎት

“ አንድ ዐሥራ ሁለት ዓመት ይሆናል ያውም ባይበልጥ ”
ታዲያ ከዚህ ሁሉ ዘመን በኋላ ' ያ ሰው ፍራንሲዝ ቪስን ለመሆኑ ምለህ
ማረጋግጥ ትችላለህ ?

“ የሱን ማንነት የራሴን ማነት ያህል ስለማውቍው
ማረጋገጥ እችላለሁ

“ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስተ ዛሬ አንድም ጊዜ ሳታየው
እንዴት አሁን ልታውቀው ትችላለህ ? እንዲህ ያለ ምስክርም አላየንም

“ በመኻሉ አይተኸው ታውቃለህ ? አለ ዳኛው "

“ ሚስተር ሆሊጆን ከተገደለ ከአሥራ ስምንት ወር በኋላ በአጋጣሚ ለንደን ላይ አይቸዋለሁ ”

“ ያን ጊዜ ስታየው ቶርን ነበር ወይስ ሌቪሰን የመስለህ ?

ቶርን ነው እንጂ !አሁን ለሕዝብ እንደራሴነት ሲወጻደር እኮ ነው ሌቪስን መሆኑን ያወኩት።

አፍሮዳይቴ ሆሊጆንን ጥራ ” አለ ዳኛው "

ሴትዮዋ ይዟት በመጣው ፖሊስ ተደግፋ ገባች እሷ የምስክርነት ቃሏን ከመስጠቷ በፊት ሚስተር ኤበንዘር ጄምስ ከችሎቱ አዳራሽ እንዲወጣ ሚስተር ቦል ፍርድ ቤቱን ጠየቀ " ለዚሁም የራሱ የሆነ ምክንያት ነበረው "

ስምሽ ማነው ?”
"አፊ ” አለች ጀርባዋን ወደ ፍራንሲዝ ሌቬሰንና ወደ ኦትዌይ ቤቴል አድርጋ።

ሙሉ ስምሽን ” አለ ዳኛዉ"
“ አፍሮዳይቴ ሆሊጆን " ስሜን ሁላችሁም ታውቁታላችሁ የማይረቡ ጥያዎችን መጠየቅ ምን ጥቅም አለው ?

“ መስካሪቱን አስምላት " አለ ጀስቲስ ሔር "

የመጀመሪያ ቃሉን መናገሩ
ነበር "

" እኔ አልምልም ”
“ መማል አለብሽ” አለ ጀስቲስ ሔር ።
“ እኔ ምንም ቢሆን አልምልም ብያለሁ „”
“ እንግዲያሙስ ፍርድ ቤቱን በመድፈር ወሀኒ ቤት ትላኪያለሽ” አላት " ከተናግረ ወደ ኋላ እንደማይል ካነጋግሩ ገባትና ደነገጠች "
ሰር ጆን ዶቢዶም ተጨመረና “ትሰሚያለሽ ' ሴትዮ ' በአባትሽ መጠደል
ያንቺም እጅ አለበት እንዴ ?

“ እኔ !” አለች በቁጣና በድንጋጤ ከገነፈለው ስሜቷ ጋር እየተናነቀች ደ
“ እንዴት እንደዚህ የመሰለ ተግቢ ያልሆነ ጥያቄ እጠየቃለሁ ? እሱ ለራሱ ደግ አባት ነበር ” አለች እንባዋ እየተናነቃት “ ሕይወቱን በሕይወቴ ለውጨም ባዳንኩት ”

“ የሱን ገዳይ ለፍርድ ለማቅረብ የሚረዳውን ምስክርነት ለመስጠት ግን ፈቃደኛ አይደለሽም ”

“ እኔ እምቢ አላልኩም " እንዲያውም ያባቴ አጥፊ ሲሰቀል ለማየት እፈልጋለሁ " እ እናንተ የማይሆን የማይሆን ጥያቄ ካልጠየቃችሁኝ እምላለሁ” አለች ቅር እያላት " ለመማል ያልፈለገችው ዋሽታ ለመመስከር አስባ ስለ ነበር ነው " ኋላ ግን በግድ ማለች። መሓላንም ትፈራ ስለ ነበር እውነቱን ለመናግር ተገደደች

“ በዚያ ዘመን ካፒቴን ቶርን የሚባል ሰው ሁልጊዜ እየመጣ ትገናኙ ነበር »
እንዴት ተዋወቅሺው ?”

“ይኽው የፈራሁትን ነገር ጀመራችሁ " እሱ በነገሩ የለበትም አልገደለም ”
"የተጠየቅሺውን ለመመለስ ነው የማልሺው » ከዚህ ሰውዬ ጋር እንዴት
ተዋወቃችሁ ?”

“ አንድ ቀን ወደ ዌስት ሊን ሔጄ በነበረ ጊዜ አንድ ብስኩት ቤት ተግናኘን”

“ ሲያይሽ በውበትሽ ተማረከና ፍቅር ያዘው ?”

የውበቷ ነገር ሲነሣ ያሰበችውን ጥንቃቄ ሁሉ ረሳችው " “ አዎን” አለች
ክፍሉን በፈገግታ እየቃኘች "

“ ከዚያ በኋላ የት እንደምትኖሪ ነገርሺውና ማታ ማታ ፈረሱን እየጋለበ
መምጣት ጀመረ ”

“ አዎን ታዲያ ይኽ ምን አለበት

"እሱስ ምንም የለበትም ”
አላት ተዝናንታ እንድትመልስለት የፈለገው ጠበቃ" “እንዲያውም መታደል ነው » ምነው እኔም እንደሱ በታደልኩ"

ያን ጊዜ ሌቪሰን ሲባል ነበር የምታቂሙ ???

የለም ካፒቴን ቶርን እንደሚባል ነገረኝና እኔም አመንኩት ”

“ የሚኖርበትን ቦታ ታውቂው ነበር?”

ለጊዜው ስዌንስን ያረፈ መሰለኝ እንጂ እኔም ጠይቄ እሱም ነግሮኝ አያውቅም

“ እንዴ ለመሆኑ እንዴት ያለ ቆንጆ የራስ መሸፈኛ ነው ያጠለቅሺው ?
ሲላት መችም የነበራት የመወደድ ፍላጎት ላሥር ሴቶች ይበቃ ነበርና በደስታሞተች " አንዱ ትልቁ ድክመቷ ይኸው ነበር " የተመሰገነውን መሸፈኛ በዕይኗ
ጠቀስ አድርጋ አይታ ሙሉ በሙሉ ከሚስተር ቦል መዳፍ ገባች "
👍22
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


“ቶርን” የሚለውን ስም ለምን አንደ ፈለገው ነግሮሽ ያውቃል '

"እሱ እንደ ነገረኝ ካፉ ስለ ገባለት ብቻ ነበር " ስዊሰን በተገናኘን ጊዜ እውነተኛ ስሙን ሊነግረኝ ደስ ስለ አላለው ይህ ስም መጣለት ነገረኝ እሱም ለሁል ጊዜ እንዲጠራበት ሌሎችም እንዲሰሙበት አይፈልግም ነበር "

ሚስ አፌ ለጊዜው ያለኝ ይኸው ነው " ኤበንዘር ጀምስ እንዲገባ እፈልጋለሁ።

ኧቤንዘር ጀምስ ገብቶ የአፊን ቦታ ያዘ "ግድያው ከተፈጸመ ከአሥራ ስምነት ወሮች በኋላ ቶርንን ለንደን ላይ እንዳየኸው ለፍርድ ቤቱ ገልጸሃል” ብሎደ ጀመረ ጠበቃው ቦል “ ይኸም አፊ ሆሊጆን አብራው የነበረችበት ጊዜ መሆን
አለበት እሷንም አይተሃት
ነበር?።

ኤቤንር ጀምስ ዐይኖቹን አፈጠጠ "አፊ ምን ብላ እንደ መስከረች አላወቀም
እሷ ከቶርን ጋር እንደ ነበረች ከዚያ በፊት ለማንም ተናግሮት አያውቅም
እንዴት ሊታወቅ እንደቻለ ገረመው ።

" አፊን ?

“አዎን አፊን አይተሃት ነበር ወይ?” አለ ጠበቃው ኮስተር ብሎ - “ ከዌስት ሊን ስትጠፋ ሪቻርድ ሔርን ተከትላ ሔዳ ነው ተብሎ ተወርቶ ነበር“ እሷ ግን
ሪቻርድን ሳይሆን ቶርንን ፍለጋ እንደሔደች ፍርድ ቤቱ ዐውቋል " ስለዚህ
አንተ ቶርንን ባገኘኸው ጊዜ እሷንም አይተሃት ነበር ወይ ? ነው የምልህ ''

“አዎን አይቻታለሁ እንዲያውም በመጀመሪያ ያየሁት እሷን ነበር ”

“ እስኪ ሁኔታውን ለፍርድ ቤቱ አስረዳው ”

“አንድ ቀን ከሰዓት በኋላ እዛው ለንደን ፖዲንግተን ከሚባለው ቦታ በመንገድ ሳልፍ አንዲት ሴት ወደ ቤት ስትገባ አየሁ " አፊ ሆሊጆን ነበረች እሷም አየችኝና ሻይ ጋበዘችኝ " እንግዳ ስለሚመጣባት በሁለት ሰዓት መውጣት አንዳለብኝ ነግራኝ ነበር ስለ ዌስት ሊን እሷ ስትወጣ የወጣሁ ስለሆነ አዲስ ነገር
ነግራትም - እየተጫወትን የተባለው ስዓት ደርሶ ወጣሁ " ከውጭ በር ስድረስ ቶርን በሠረገላ መጥቶ ሲገባ አየሁት "

“ታድያ አፊ የኮበለችው ከሪቻርድ ሔር ነው መባሉን እያወቅህ ወደ ዌስት ሊን እንደ ተመለስክ ለምን አልተናገርክም ?”

“መጀመሪያ ይህን ነገር መናገር የኔ ተግባር አይደለም አፊ ደግሞ ' አይቻታለሁ ብዬ ለማንም እንዳልናገር ቃል አስገብታኝ ስለ ነበር ለማንም አልተናገርኩም ”

“ ቆይ ” አለ ሚስተር ሩቢኒ ምስክሩ ሊወጣ ሲል “ ስዓቱ ከምሽቱ ሁለት
ሰዓት አንደ ነበር ተናግረሃል "ጨልሞ ነበር ?”

"አዎን ”

"ታድያ ከሠረገላ ወርዳ ወደ ቤት የገባው ቶርን መሆኑን እንዴት ልታረጋግጥ ቻልክ ?”

“በደንብ አረጋግጫለሁ " ከሠረገላ ከወረደበት ላይ የጋዝ መብራት ስለ ነበር
ልክ በፀሐይ ብርሃን የማየውን ያህል አድርጌ አይቸዋለሁ " ከዚህም ሌላ ድምፁን አውቀዋለሁ " የትም ቢሆን በድምፁና በቀለበቱ ብቻ በሚገባ ልለየው እችለሁ "
ደማቁ ቀለበቱ በመብራቱ ሲፍለቀለቅ አይቸዋለሁ …”

ድምፁንስ በምን ስማኸው? አነጋግሮህ ነበር ?

« ከኔ ሳይሆን ከባለ ሠረገላው ጋር ሲነጋገር ሰምቸዋለሁ " በመካከላቸው
አንድ ክርክር ነበር " ሰውዬው ኻያ ደቂቃ ሙሎ ከመንገድ ካስጠበቀው በኋላ የሰጠው ግን እንደማይበቃው ቅሬታውን ገለጸለት ቶርንም ጥቂት ከተጨቃጨቁ በኋላ አንድ ሽልንግ ተጨማሪ ወረወረለት።

ከኧቤንዘር ጄምሰ ቀጥሎ የሟቹ የሰር ፒተር ሌሺሰን ባልደራስ የነበረ አንድ
ሰው ተጠራ“ እሱም ሆሊጆን በተገደለበት ዘመን ወደ በጋው መጨረሻ ሲል ፍራንሲዝ ሌሺስን ስር ፒተርን ለመጠየቅ መጥቶ መስንበቱን መሰከረ እዚያም ሲሰነብት ብዙ ጊዜ በተለይ ወደ ማታ ሲሆን የዌስት ሊንን አቅጣጫ ይዞ በፈረሱ ይሔድና ሦስት ወይም አራት ስዓት ያህል ቆይቶ ፈረሱ ላብ በላብ እስኪሆን ድረስ እየጋለበ ይመለስ እንደ ነበር ጨምሮ አስረዳ ከሚስተር ሌቪሰን ኪስ የወደቀ ሁለት ደብዳቤዎች በተለዩ ጊዜያት አግኝቶ እንደ ስጠው ገለጸ " የሁለቱም ደብዳቤዎች አድራሻ • ለካፒቴን ቶርን ሲል የፖስታ ቤት ምልክት አልነበራቸውም
ከተቀባዩ ስም በቀር በፖስታዎቹ ላይ ምንም ነገር አልተጻፈባቸውም ጽሕፈቱ የሴት ይመስል ነበር " ምስክሩ ተጠይቆ በሰጠው ማብራሪያ የሆሊጆን መገደል ዳር እስከ ዳር ትልቅና አስደንጋጭ ዜና ሆኖ እንደሰነበተ በደንብ ማስታወሱንና ፍራንሲዝ ሌቪሰንም ሰር ፒተር ዘንድ ቆይታውን ጨርሶ ወደ ለንደን መመለሱን ተናገረ ።

እንዴት ያለ የማስታወስ ችሎታ አለህ ! አለና ሩብኒ አፌዘበት "

ምስክሩ ሞግስ ያለው ከባድ ሰው ነበር በርግጥ ጥሩ የማስታወስ ችሎታ እንደነበረው ራሱም አልሸሸገም በተለይ ግን ሚስተር ሌቪስን ሆሊጆን እንደ ተገደለ ከዚያ አካባቢ በመልቀቁና ሌሎችም አብረው የተከሠቱ አንዳንድ ነገሮች ከአእምሮው መቀረጸቸውን ገለጸ "

“ ምን ምን ነገሮች ናቸው? አለ ፍርድ ቤቱ "

“አንድ ቀን ሰር ፒተር የፈረሶችን ጋጣ እየዞሩ ሲያዩ ሚስተር ፍራንሲዝ ሌቪሰንን ትንሽ ቀን እንዲሰነብት አጥብቀው ቢጠይቁት ባልታሰበ ጉዳይ ወደ ለንደን መጠራቱን ነገራቸው እነሱ ሲነጋገሩ ሠረገላ ነጂው እየቃተተ መጣና የዌስት ሊኑ
ሆሊጆን በሪቻርድ ሔር መገደሉን ተናገረ “ ሰር ፒተር በድንተኛ አደጋ ካልሆነ በቀር ሆነ ተብሎ የተደረገ ነው ብለው ሊያምኑ እደማይችሉ መናገራቸውን አስታውሳለሁ

ሚስተር ሌቪሰን መሔድ እንዳለበት ከነገራቸው በኋላ አንድ ዐሥር ፓውንድ እንዲሰጡት ጠየቃቸው - እሳቸውም ትናንቱን ጧት ስለ ስጡት አምሳ ፓውንድ በቁጣ ሲጠይቁት የአንድ ጓደኛው መኮንን ዕዳ ስለ ነበረበት በፖስታ እንደ ላከለት ነገራቸው እሳቸው ግን የትም ሲያብድ ካላባከነው በቀር ለሰጠው ምክንያት ማዋሎን ማመን አልቻሉም » በዚህ ጊዜ ግራ የመጋባት ምልክት ታየበት " የኔጌታ ለጊዜ ቶሎ ቢቆጡም ከለመንዋቸው ልባቸው አይጠናም ነበር እንደ ሴት ምልስ ባይ ነበሩ " በርግጥ በዐይኔ አላየሁም ' ግን የጠየቃቸውን ገንዘብ ሳይሰጡት የቀሩ አልመሰለኝም " ሚስተር ሌቪዞን የዚያን ለት ሌሊት ወደ ለንደን ሔደ።

የመጨረሻው ምስክር ሚስተር ዲል ነበር " ባለፈው ማክስኞ ማታ ሚስተር ቦሻ ቤት ቆይቶ ሲመለስ ከሚስተር ጆስቲስ ቤት ፊት ለፊት አንድ ጭቅጭቅ ሰማ የነገሩ መነሻ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንና ኦትዌይ ቤቴል ድንገት መግናኘት
ኖሯል " ቤቴል ለምን እንደሚያርቀው ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንን ሲወቅሰው ያኛው
ስለሱ ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለና ለማወቅም እንደማይፈልግ ነገረው "
.
ሆሊጆን የተግደለ ዕለት ማታ ግን ' ስለኔ አንድ ነገር በማወቅህ ደስ ብሎህ
ነበር " ሰመሆኑ ላሰቅልሀ እችል እንደ ነበር ታስታውሳለህ አንዲት ትንሽ ቃል ብናግርብህ በዲክ ሔር ቦታ ልትቆም ትችል እንደ ነበር ዘነጋኸው? አሁን ያ ሁሎ አለፈና አላውቅህም ትለኛለህ ? አለው »

“አንተ ከብት አለው ሰር ፍራንሲዝ ፡ “ የራስህን አንገት ከሸምቀቆ ሴታስገባ ልታሰቅለኝ እንደማትችል ጠፋህ ? ያፍ መዝጊያ ገንዘብ አልተቀበልክም
ይግሞ እንድጨምርልህ ትፌልጋህ ?

“ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ምነው ያንን የተረገመ አምሳ ፓውንድ ስቀበልህ እጆቼ
በረገፉ እያልኩ ነው የኖርኩት " ለጊዜው ግራ ግብቶኝ • የማደርገው ጠፍቶኝ ሳለ ባታግኘኝ ኖሮ አልነካልህም ነበር ልጃቸውን ከመሰቀል የሚያድኑበትን ምስጢር
ደብቁ በመያዜ እስከዛሬ ድረስ የሚስዝ ሔርን ፊት ማየት አልቻልኰም ”

“በሱ ገመድ ራስህን ለማስገባት " አለና አሾፈበት ሰር ፍራንሲዝ።

“የለም አንተን ለማስገባት ”
👍19