አትሮኖስ
280K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
460 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_ሦሥት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


...ሳቤላ ከማዳመጥ ሌላ አማራጭ አልነበራትም ግን ፍራንሲዝ ሌቪሰን ከሪቻርድ ሔር ጋር ምን እንዳገናኘው ገርሟት ነበር

ድሮ በልጅነቴ በጣም ልጅም አልባልም ክፍ ብዬ ነበር ሪቻርድ አፊ ዘንድ እመላለስ ነበር እሷ ከአባቷ ከጆርጅ ሆሊጆን ጋር ነበር የምትኖር » ብዙ ወጣቶች እሷ ዘንድ አይጠፉም "እሷ ግን ቶርን የተባለው የትልቅ ሰው ልጅ በመሆኑ ከሁሉ አብልጣ ትወደው ነበር " ያ ሰው በአካባቢው የሚያውቀው አልነበረም
በምስጢር ሹልክ ብሎ ፈረስ አየጋለበ ይመጣና እንዳመጣጡ ሹልኮ ይመለሳል አንድ ቀን ማታ ሆሊጆን በጥይት ተገደለ ሪቻርድ ተሸሸገ " ምስክሩ በሱ ጠነከረበት « ፍርድ ቤትም ገዳይነቱን አምኖ ወሰነበት " ሁላችንም እሱ ስለ መግደሉ አልተጠራጠርንም አሁን እናቴ የልጅዋን ነገር እያነሳች በኅዘን ልትሞት ሆነ " ማንም ሊያጽናናት አልቻለም " በዚህ ዐይነት ያለ ምንም ለውጥ አራት ዓመት ያህል ቆየ።
ከዚያ በኋላ ሪቻርድ በምስጢር ለጥቂት ሰዓቶች ወደ ዌስት ሊን መጣና ወንጀለኛው እሱ ሳይሆን ቶርን የተባለ ሰው እንደ ነበር ነግሮን ሔደ ቶርንን ለማግኘት ብዙ ጥረት
ተደረገ " ነግር ግን ማን እንደ ነበረ የት እንደ ነበረ ከየት እንደ መጣ ወዴት እንደ ሔደ የሚያውቅ ሰው ሳይገኝ ጥቂት ዓመታት ዐለፉ " አንድ ጊዜ ቶርን የተባለ ካፒቲን
ወደ ዌስት ሊን መጣ። መልኩ ሁኔታው ሁሉ ሪቻርድ ከሰጠን ምልክት ጋር አንድ ሆነ " እኔም ሪቻርድ የነገረን ነፍሰ ገዳይ ቶርን እሱ መሆን አለበት ብዬ አመንኩ አሁን ምን መደረግ እንደሚገባው እንኳን ሳይታሰብበት ካፒቴን ቶርን ወደ መጣበት ሔደ አሁንም ከዚያ በኋላ ዓመቶች ዐለፉ ”

ባርባራ ዐረፍ አለች " ማዳም ቬን ፍዝዝ እንዳለች ቀረች " ያ ሁሉ ታሪክ ለሷ ምን እንደሚያደርግላትም አልገባትም "

“ኋላ ፍራንሲዝ ሌቪሰን የኢስት ሊን እንግዳ ሆኖ በሰነበተበት ዘመን ካፒቴን ቶርን የሔርበርትን ቤተሰብ ለመጠየቅ ወደ ዌስት ሊን መጣ አሁን ሰውየው
እሱ መሆኑን ሚስተር ካርላይልና እኔ አመንበት " ቢሆንም ይበልጥ ለማረጋጥ እንሯሯጥ ጀመር። እማማ እንደ ልቧ ወዲያ ወዲህ ማለት ስለማትችልና አባባም የሪቻርድን ነገር ለመስማት ስለማይፈልግ እኔ ብቻ ነበርኩ ከሚስተር ካርላይል ጋር በየጊዜ መገናኘት የነበረብኝ " ያኔ ፍራንሲዝ ሌቪሰንን ብዙ ጊዜ አይቸዋለሁ ኢስት ሊን ውስጥ ተደብቆ ስለ ተቀመጠ ለማንም ሌላ እንግዳ አይታይም ባለ
ዕዳዎቹ እንዳያገኙኝ ፈርቸ ነው ይል ነበር " አሁን ግን ውሸቱን ሳይሆን አይቀርም ብዬ መጠርጠር ጀመርኩ ሚስተር ካርላይልም በዚያ ጊዜ ዌስት ሊን ውስጥም ሆነ በአካባቢው በዕዳ የሚፈልገው ሰው የለም ያለውም ትዝ አለኝ » "

“ ታድያ በምን ምክንያት ነበር በግልጽ የማይወጣውና ከሰው የሚደበቀው?” አለች ወይዘሮ ሳቤላ አቋርጣ እሷም በበኩሏ ዘመኑ ይራቅ እንጂ ነገሩን በደንብ
ታስታውሳለች » የሚሹሎከሎከው ባለ ዕዳዎቹን በመፍራት መሆኑን ይነግራት ነበር » አንድ ጊዜ ብቻ በኢስት ሊን አካባቢ ፈላጊዎች እንደሌሉት አጫውቷታል

“ ከባለዕዳዎቹ የባሰ ፍራት ነበረበት " አለቻት ባርባራ “ እንዳጋጣሚ ሆነና
ካፒቴን ቶርን ከሔርበርት ቤተሰብ ዘንድ አንደ መጣ ከወንድሜ አንድ መልእክት
ደረሰን " መልእክቱም ለአጭር ጊዜ ወደ ዌስት ሊን መጥቸ ለመመለስ ፈልጌአለሁ የሚል ነው "ይኸንኑ ለሚስተር ካርላይል ነገርኩት " እማማ በጣም ተጨነቀችበት "
ሚስተር ካርላይልም የሪቻርድን ንጹሕነት ይፋ የሚሆንበትን መላ ለማግኘት ብዙ
ይጠበብበትና ይጓጓበት ነበር » ስለዚህ ከምን ጊዜውም የበለጠ ከሚስተር ካርላይል
ዘንድ እየተመላለስኩ መመካከር ግዴታ ሆነብኝ " አየሽ አባባና ሚስ ካርላይል ዘመዳሞች ናቸው " ስለዚህ የሪቻርድ መከራ የኛ ብቻ ሳይሆን የካርላይል ቤት ጭምር ነበር "

ሳቤላ ትዝታና መራራ ጸጸት ወደዚያ ዘመን ይዟት ተመለሰ " የሚስትር ካርይልና የባርባራ ቶሎ ቶሎ መግናኘት' በቅናት አመለካከት ሌላ ትርጕም መስጠቱን አስታወሰች " ለምንድነው ባልተረጋገጠ ነገር ከመከራ ላይ ለመውደቅ አእምሮን ያን ያህል ያስጨነቀችው ?

“ሪቻርድ መጣ " ጸሐፊዎቹ ወደ ቤታቸው ከሔዱ በኋላ እሱ ወደ ሚስተር ካርላይል ቢሮ ሹልክ ብሎ ሔዶ ከአንድ ክፍል እንደገባና ካፒቴን ቶርንን ተደብቆ
እንዲያው አስቸኳይ ዝግጅት ተደረገ " ካፒቴኑ ሚስተር ካርላይል የሚፈጽምለት አንድ ጕዳይ ነበረው " ሚስተር ካርላይልም ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ከቢሮው ድረስ
ቀጠረው » ስለዚህ ሁኔታውን ስለ ሪቻርድ ለማመቻቸት ምንም ችግር አልነበረውም የሚስተር ካርላይል ሚስት የኮበለለችው ያን ዕለት ሌሊት ስለ ነበር ምጊዜም ከአምሮው አይጠፋም

«ሳቤላ ድንግጥ አለችና ሽቅብ ተመለከተች »

" የሆነውን ኮ የምነግርሽ እመቤት ሳቤላና ሚስተር ካርላይል የራት ጥሪ ነበረባቸው " ሚስተር ካርላይል ከጥሪው ካልቀረ የሪቻድን ጉዳይ መፈጸም የማይቻለው ሆነ " መቸም ርኀሩጎና ለሰው አሳቢ ነው " ከራሱ ጥቅምና እርካታ ይልቅ ስለ ሌላው ደኅንነት ማሰብ ደስ ይለዋል " ስለዚህ ከጥሪው ቀረ " መቸም የሽብር ሌሊት ነበር " አባቴ ወጥቶ አምሽቷል ሪቻርድ በቀጠሮው መሠረት ወደ ዌስት ሊን በጨለማ በሚጓዝበት ጊዜ የመንገድ አደጋ ሊደርስበት ስለሚችል ተጨንቀናል " ስለዚህ እማማን እያረጋጋሁና እያጽናናሁ አብሬአት አመሸሁ " ሪቻርድ
ሚስተር ካርይል ጋር ያለውን ጉዳይ እንደ ጨረሰ ከእማማ ጋር ለመገናኘት
መምጣት ነበረበት ከተለያዩ ብዙ ዓመታቸው ሆኗቸው ነበርና።

ባርባራ ነገሯን ቆም አረገችና ሐሳብ ይዟት ጭልጥ አለ " ማዳም ቬንም ቃል ሳትተነፍስ ዝም አለች " ቢሆንም የሪቻርድ የካፒቴን ቶርንና የፍራንሲዝ ሌቪሰን ግንኙነት ምን እንደሆነ አላወቀችውም "

“በመስኮት ቁሜ ስጠብቃቸው ሚስተር ካርላይልና ሪቻርድ በአትክልቱ ቦታ በር ሲገቡ አየኋቸው ሰዓቱ ከምሽቱ ሦስትና በአራት መካከል ሳይሆን አይቀርም!
እንደ ተገናኘን ካፒቴን ቶርን ሪቻርድ ያለው ቶርን አለመሆኑን ሲነግሩኝ በጣም አዘንኩ ሚስተር ካርላይል ደግሞ' ' እንኳን እሱ አልሆነ ብሎ ደስ አለው
ሪቻርድ እማማ ዘንድ ገባ አባባ ካገኘው ይዞ ለፍርድ እንደሚያቀርበው ብዙጊዜ
ተናግሯል እሱ ተጫውቶ እስኪወጣ ድረስ እኔና ሚስተር ካርላይል ከግቢው ወዲያና ወዲህ እያልን የአባባን መምጣት አንድንጠባበቅ ተማከርን ከመጣ ሚስተር ካርላይል እያዝናጋው እንዲቆይና እኔ ሮጥ ብዪ ገብቼ ሪቻርድን እንዲሸሸግ እንዳስጠነቅቀው ከማማ ጋር ተነጋገርን ሚስተር ካርይልም የእማማን ልመና ተቀብሎ ሐሳቡ ተስማምቶ አብረን ከደጅ አመሽን " ሪቻርድም አልወጣም!ብዙ ቆየ አባባም አልመጣም " እኔና ሚስተር ካርላይልን ብዙ ጌዜ አስጠበቀን - ደስ የሚል የጨረቃ ሌሊት ነበር ።

ያልታደለችው ሳቤላ እጇን እስኪያማት እያፋተገች
አዳመጠች ባርባራ ምንም ሳትጠረጥር የሆነውን ሁሉ እያስታወሰች በቅንነቷ ስትነግራት ጸጸቱ እንደ እሳት ይፈጃት ጀመር ሁለቱ እጅ ለእጅ ተያይዘው ሲንጎራደዱ
👍13👏1🤔1