አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_አራት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ው

በፉጨት የሚጋልብ ከባድ ንፋስ መለል ያሉትን ረጃጅም ዛፎች እየለመጠ ሰፋፊ ቅርንፎቻቸውን አያወዛወዘ ቅርንጫፍን ከቅርንጫፍ እያላተመ
አዋከበው » ቅጠል ከቅጠል እያማታ ኢስት ሊንና አካባቢውን አዋከበ

ድምፁ የሚያሳዝን አመጣጡ የሚያስፈራ ቅጽበታዊ ነፋስ ተለዋወጠ " ዝናብ አዘል ዳመናዎች ተጠረቃቀሙ » በዚያ ቅዳሜ ምሽት ብቻውን
ይጓዝ የነበረ አንድ የሩቅ መንገደኛ ዝናቡ ከመንገድ እንዳይዘው እያሰበ › በእግሩ
ይኳትናል ሰውየው የመርከበኛ ልብስ ለብሷል " ከሰማያዊው አንገትያው በላይ ያለውን አንገቱንና ፊቱን ቸምቸም ያለው ጢሙ ሸፍኖታል " ከግንባሩ ዝቅ አድርጎ የደፋው ባርኔጣው ለጢሙ ተጨማሪ ሆኖ ጋርዶታል ሰፊና ሸካራው ሱሪውን በቀበቶ አጥብቆ ታጥቆ አጭር ሰፊና ወፍራም የመርከበኛ ሱፍ ካፖርት ደርቦ እየተወዛወዘ ቢን ሌን ደረሰ » ቀደም ሲልም በዚህ ታሪክ የተወሳው ቢን ሌን ስላች
መንገድ ነው ። ከዚያ ቀጥሎ እግር በማይበዛበት በአንድ ትንሽ በር ዐልፎ ከኢስት ሊን ምድረ ግቢ
ገባ ።

የገባበትን በር መልሶ ዘጋው መወርወርያውን ቀረቀረው ከዚያ በየት በኩል
መሔድ እንደሚገባው ቆም ብሎ አሰላሰለ "ቆይ እስቲ” አለ ለራሱ » “ በዛፎቹ
የተሸፈነ መንገድ ያለችኝ በግራሮቹ አጠገብ ሳይሆን አይቀርም ስለዚህ ወደ ቀኝ
መታጠፍ አለብኝ " ለመሆኑ ከሁለቱ አንዱ እየጠበቁኝ ይሆን ?”"

አውነትም ባርባራን የምሽት አየር ለመቀበል የወጣች መስላ ስትንጐራደድ
አገኛት " የናፍቆታቸውን ተናንቀው ተሳሳሙ " ሁለቱንም ሲቃ ተናነቃቸው "
ባርባራ እንደ ትንሽ ልጅ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች " እንቅ አድርጎ ይዟት የነበረውን ለቀቃትና ትክ ብሉ አያት "

“ ታዲያስ ባርባራ ! በቃ አሁን አግብተሽ ትዳር ይዘሽ ተቀምጠሻል !”

“ አዎን በትዳሬም ደስተኛ ነኝ " ያንተ ነገር እየተደቀነብኝ ከማዘኔ በቀር
ምንም የጐደለብኝ የለም " ብታየው በጣም የሚያሳሳ ልጅ ወልጃለሁ እሱም
አሁን አንድ ዓመት ሊሞላው ነው " በቅርቡ ደግሞ ሁለተኛ ልጄን እወልዳለሁ ”

ሰዎቻችንሳ እንደ ምን ናቸው ?”

“ ደኅና ናቸው » እማማም ከቅርብ ጊዜ ወዲሀ በጎ ናት

" ዛሬ ግን ያንተን መምጣት አላወቀችም "

“ዛሬስ እሷን ማየት አለብኝ ከዚህ ቀደም ሳላያት መሔዴን ታስታውሻለሽ የለ?”

“ ሁሉም በጊዜው ይሆናል " የሊቨርፑል ኑሮስ እንዴት ይዞሃል ? እዚያ ምን
ትሠራለህ ?”

“ አጥብቀሽ አትጠይቂኝ ባርባራ " የተወሰነ ሥራ የለኝም " ያገኘሁትን
እሠራለሁ " ከዚህ በምትሰጡኝ እየተደገፍኩ እኖራለሁ " ግን ለምንድነ© ወደዚህ የጠራሽኝ ? ምን አዲስ ነገር ተገኘ ?”

“ እውን ቶርን እዚህ ብታየው ግን ታውቀዋለህ ?

“ ታውቀዋለህ ወይ ! ምኑ ይጠየቃል ? ”

“ ዌስት ሊን ላይ የሕዝብ እንደራሴነት ምርጫ በመካሔድ ላይ መሆኑን ታውቃለህ?

“ አዎን ሚስተር ካርላይልና ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን እንደሚወዳደሩ ከጋዜጣ አንብቢያለሁ።

“ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንን እንዴት ልታውቀው እንደ ቻልክ ልትነግረኝ ትችላለህ
· ሪቻርድ ? ”

“ እሱንማ ዐውዋዋለሁ ከቶርን ጋር ሁለት ጊዜ አይቸዋለሁ „ “

“ እኔ የምልህ እንዴት ልታውቀው ቻልክ ? ”🍾

“ ቶርንን ከአንድ ሰው ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ አየሁትና አጠገቤ የነበረውን
አንድ ታንኳ ቀዛፊ በእጄ እያሳየሁ ያውቀው እንደሆነ ጠየቅሁት " እኔ ያመለከትኩትን ሰውዬ እንደሚያውቀውና ካጠገቡ የነበረውን ግን ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን መሆኑን ነገረኝ

“ እንግዲያውስ ሪቻርድ አንተና ታንኳኛው አንድ የሆነ ስሕተት አድርጋችኋል " ወይ አንተ ስታሳየው ወይ ደግሞ እሱ ያልጠየቅኸውን ሰው ሲያሳይህ አስተውለህ አላየኽውም እንጂ ' ቶርን ፍራንሲዝ ሌቪሰን ራሱ ነው

“ ምን ማለትሽ ነው ... ባርባራ ” አላት ዐይኖቹን አፍጥጦ እያያት

"ነው አለችና ራሱ ሪቻርድ ቢን ሌን ላይ አየሁት ካለበት ጊዜ ጀምሮ ስትጠረጥረው እንደ ኖረችና፡ ከዚያም በመጨረሻ ይፈለግ የነበረው ቶርን ራሱ ፍራንሲዝ ሌቪስን ለመሆኑ ኦትዌይ ቤቴልና ኧበንዘር ጄምስ ለይተው እንዳወቁት አብራርታ ነገረችው

ሁለቱም ሊያወቁት ይችላሉ ” አለ ሪቻርድ " ጄምስ ራሱ ሆልጆን ዘን ይሹለከለክ ስለ ነበር ቶርንን ብዙ ጊዜ አይቶታል" ኦትዌይ ቤቴልም በፊት ቢክድም አይቶት ሊሆን ይችላል - ”

ሪቻርድ ከሩቅ አንድ ሰው ሲመጣ ሲያይ ጊዜ ጥሏት ሮጠና ከአንዱ ቁጥቋጦ
ውስጥ ድርግም አለ » ባርባራ ሣቅ አለች " ለካስ ሚስተር ካርይል ኖሯል "

“ ዛሬም ትፈራለህ ሪቻርድ ? ” አለው ሲጨብጠው „ “ ዛሬስ የመንገድ ልብስህን ለውጠሃል።

በፊት ስለብሰው የነበረው ስለ ታወቀብኝ ለብሸው ለመምጣት ፈራሁ "
ስለዚህ ይህን በሁለት ፓውንድ ገዛሁ ”

ጸጉሩንም ጢሙንም ጭምር ነው ?

ጸጉሩማ እንዳዲስ ተበጥሮና ዘይት ተቀብቶ ነው እንጂ የድሮው ነው
ጸጉር አስተካካዩም የውሸት ጢሙን አበጃጅቶ የራሱንም ጸጉር ከርክሞ አንድ ሽልንግ አስከፈለኝ ሚስተር ካርላይል ... ባርባራ አረመኔው ቶርን ሌቪሰን ሆኖተገኘ ትለኛለች "

" አዝማሚያ ይመስላል ቢሆንም አንዳች ነገር ከመደረጉ በፊት አንተም
ሊቪስንን በዐይንህ አይተህ ማረጋግጥ አለብህ " ወደ ቨን ሆቴል ብቅ ብትል ሲገባ
ሲወጣ በቀላሉ ታየዋለህ ደሞ ዛሬ ሰው ሁሉ ልቡን ወደ ምርጫው ስለ አደረገ
የሚያውቅህም የሚያስብህም አይኖርም " ስለዚህ በጥንቃቄ አስተውለህ አረጋግጠህ ና አለው ሚስተር ካርላይል "
“ ቶርን መሆኑን ካረጋጥኩ በኋላ ምን እርምጃዎች ይወሰዳሉ ?

"ችግሩ እዚህ ላይ ነው ” አለ ሚስተር ካርላይል "

“ ክሱን የሚመሠርተው ከዚያም ጉዳዬን የሚከታተለው ማን ነው ?

“ እሱንማ አንተ ራስህ ነህ... ሪቻርድ " እኔ በዚህ ነገር በጣም አስቤበታለሁ
የምትከታተለው አንተው ነህ
“ አንተ ልትይዘው አትችልም
ሚስተር ካርላይል ? ''

“አልችልም !ሌቪሰን ከሆነ እንዴት አድርጌ ?” አለው "
ዐፈር ይብላ ይህ ርኩስ ” አለ ሬቻርድ በንዴት " ግን እሱ ቢሆን ምን ቸገረህ
ሚስተር ካርላይል ? ብዙ የተበደሉ ሰዎች ጠላታቸው በአጃቸው ሲገባ ለመበቀል ሲጣደፉ አይተሃል "

“ በሆሊጆን በተፈጸመው ወንጀል ፍርዱ እስከሚፈጸምበት ሰገነት ድረስ ልክታተለው እችላለሁ ስለ ራሴ በደል ግን አልሞክረውም" ወደ ዌስት ሊን ከመጣበት ጀምሮ ራሴን ለመቁጣጠርና ለመታገሥ ኃይለኛና አስቸጋሪ ትግል ባላደርግ ኖሮ ነፍሱ እስኪ ወጣ አስገርፈው ነበር "

“ ታዲያ ነፍሱ እስኪወጣ ብታስገፈው ዋጋውን አገኘ ኮ ነው የሚባለው ” አለው ሪቻርድ "

ለግድያው ተጠያቂ መሆኑን አምናለሁ ነገር ግን እኔ እጄን አንሥቸበት ወደ አሳፋሪ ሞት ከምሰደው ያነሣሁትን እጄን ቆርጦ ብጥለው እመርጣለሁ።ምክንያቱም የሰውዬውን የነፍስ ማጥፋት ወንጀል በኔ ላይ ከፈጸመው በደል ልለየው
አልችልምና " በሆሊጆን ሕይወት ብከታተለውም የሌላም ሕይወት ያጠፋ ለመሆኑ ሊሰወር አይችልም ሁልጊዜ አዛኝ የሆነው ዓለምም ለሚስተር ካርላይል ደስታውን
የሚገልጽበት በሚስተር ሆሊጆን ገጻይ ሳላስፈረደበት ሳይሆን ለተዋለበት ግፍ ብድሩን ስለ መለስ ይሆናል" ስለዚህ ነው በዚህ ነገር አልገባም
ሪቻርድ....

“ እሺ አንተስ ተወው ባርባራ ልትከታተልልኝ አትችልም ? " አላው "
ባርባራ ክንዶቿን ከባሏ ክንዶች ጋር አቆላልፋ ቁማ ትሰማለች "
“ ባርባራማ የኔ ሚስት ናት "
“ እንግዲህ ነገሩ ለመገለጽ ተስፋ የለውም " እኔም ተስፋ ቆርጬ ልሒድ ”
👍6