አትሮኖስ
286K subscribers
117 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
" የሚወደው ፈረሱ የጋጣው ወላል መሀል ተዘርሮ እየተንፈራፈረ ነው፣ነፍሱ እንድትወጣ በመፈለግ የሚያሰማው የሚያሰቀጥጥ ጩኸት የሰው ጣር ነው የሚመስለው። አለም ባለችበት ቆማ ወደውስጥ ተንጠራርታ ፈረሱን አየችው ..ባለፈው ከኩማንደሩ ጀርባ ላይ ተለጥፋ የጋለበችበት ፈረስ ነው። ምን ያህል ይወደው እንደነበረ በዛን ቀን በደንብ መረዳት ችላለች፡፡
አንድ ሰው ገመዶን ተከትሎ ወደ ጋጣ ውስጥ ገብቷል "ለእሱ ማድረግ የምችለው ምንም ነገር የለም፣››አለው

"ገመዶ ሰውዬው ሲናገር ዝም ብሎ ተመለከተው። የሳራ ልቅሶ ጨመረ። ፊቷን በፎጣዋ ሸፈነች።

"እናቴ እባክሽ ወደ ቤት ልመልስሽ።››አላት ጁኒዬር…ጁኒየር እጁን ወገቧ ላይ አድርጎ ቀስ ብሎ ወደ መሀል መንገድ ይዞት ይሄድ ጀመር። ድንገት ሳራ ዞር ስትል አለምን ተመለከተቻት…ከዛ ከፍ ባለ ድምፅ አወጣች እና ሌባ ጣቷን ወደእሷ እየጠቁመች።

"አንቺ ነሽ ይህን ያደረግሽው።…አንቺ ነሽ››ስትል አንባረቀችባት፡፡

አለም ደነገጠችም..ግራ ገባትም "እኔ?"

" አዎ…ጥፋቱ ያንቺ ነው፣ አንቺ ቂመኛ ሴት ነሽ!"

"እማዬ…ተይ እንጂ" አለ ጁኒየር፣ ፡፡እንዳቀፋት ከአከባቢው ይዞት ሄደ ፡፡አለም ንዴት እና እልህ እየተናነቃት እይታዋን ወደጋጣው መለሰች፡እየተሰቃየ ያለውን እንስሳ ተመለከተች። ከገመዶ ጋር ያለው ሰው የእንስሳት ዶክተር እንደሆነ ገባት፡፡

" መርፌ ወግቼው ነበር …መድሀኒቱ እየሰራ አይመስለኝም..በቃጠሎ በጣም ስለተጎዳ መኖር ቢችል እኳን ከአሁን ወዲያ የምታውቀውን አይነት ፈረስ አይሆንልህም››በማለት ለገመዶ አስረዳው፡፡

ሁሉም ከፈረሱ የሚመወጣውን አሳዛኝ ድምፆ እያዳመጡ ለአፍታ ዝም አሉ። በመጨረሻ ፍሰሀ

"እናመሰግናለን ዶ/ር ፣ የምትችለውን ሁሉ እንዳደረክ እናውቃለን።"አለው

"ይቅርታ …የሚረዳው ከሆነ ወደኪሊኒክ ሄጂ አንድ መድሀኒት አለ ….እሱን አምጥቼ ልወጋው እችላለሁ…ቢያንስ ህይወቱን ባያተርፍለትም ስቃዬን ይቀንስለታል››

"አይ… ያን ያህል ጊዜ እየተሰቃየ እንዲጠብቀው አልፈቅድለትም.
"አለ ገመዶ

"አስር ደቂቃ አይፈጅብኝም።"ዶ/ሩ መለሰ፡

"ግድ የለም…አያስፈልግም…ባይሆን ሌሎች የተጎዱ እንስሳቶች ካሉ እነሱን እይልን….እሱን ለእኔ ተውልኝ›› ሲል ትግስት የለሽ በሆነ ቃላት ተናገረ …ዶ/ሩ እቃውን ሰበሰበና ከአካባቢው ለቆ ሔደ፡፡ ገመዶ ፈረሱ ስር ተንበረከከና ይዳብሰው ጀመር›‹‹ ደህና ትሆናለህ ፣ የእኔ ጀግና
?" በማለት ያባብለው ጀመር….ከዛ ወደአቶ ፍሰሀ ቀና አለና‹‹ጋሼ አንተ ወደቤት ሄድ…እኔ አስተካክለዋለው››አለው

"አዛውንቱ ለመጨቃጨቅ የተዘጋጁ ቢመስልም በመጨረሻ ግን በኩማንደሩ ሀሳብ በመስማማት ዘወር አሉ። አለምን ጠንከር ያለ ትርጉሙ የማይገባ እይታ ተመለከታት እና
፣ ምንም ሳይናገራት በአጠገቧ አልፎ ከአካባቢው ለቆ ሄደ፡፡ ገመዶ በወለሉ ላይ ከፈረሱ ጎን ተንበርክኮ ሲተክዝ ስትመለከት ማልቀስ አማራት፡፡ ፈረሱም ሰውዬውም አንጀቷን በሏት፡፡

"ጥሩ ፈረስ ነበርክ ምርጥ" መዳበሱን ቀጠለ፡፡"ያለህን ሁሉ ሰጥተኸናል.. ከዛም በላይ ›› ስንብት የሚመስል ቃላቷችን አዝጎደጎደ ።ገመዶ ቀስ ብሎ እጁን ወደታች ላከና በጎኑ የሻጠውን ሽጉጥ አወጣ… ካዝናውን ከፈተና ጥይት መኖሩን አረጋግጦ መልሶ አስተካከለው…..አለም ምን ሊያደርግ ነው ብላ በድንጋጤ እየተመለከተችው ነው፡፡ ከዛ ሽጉጡን ፈረሱ ጭንቅላት ላይ አስጠግቶ ደቀነ…

"ገመዶ፣ አይ፣ አታድርገውም። ሌላ ሰው ያድርገው።"ተንደረደረችና ወደውስጥ ገብታ እጅን ያዘችው፡፡

እስከዛሬ ገመዶን ስታውቀው ፊቷ ላይ እንዲህ ያለ የገዳይ ሰው እይታ አይታበት አታውቅም። ዓይኖቹ እንባ ማቅረራቸው ብቻ ሳይሆን ጥላቻም ማጋታቸውን በግልፅ ማየት ይቻላል፡፡ ሽጉጡን ልትቀማው ሞከረች ። ታገለችው። በፈርጣማ ግራ እጁ አንገቷን ፈጥርቆ ያዛትና በቀኝ እጁ የያዘውን ሽጉጡን በፈረሱ ሁለት አይኖች መካከል ባለው ግንባሩ ላይ አስተካክሎ አነጣጠረ እና ምላጩን ሳበው ….ክፍሉ በተከታታይ ተኩስ ተደበላለቀ….እሷ በድንጋጤ ጮኸች። አካባቢ የነበሩ ሌሎች ፈረሶች እና ከብቶች በፍርሃት በረገጉ

ከውጪ ያሉ ሰዎች ሲጮቾሁ ተሰማ ፣ እና በርካታ የእሳት አደጋ ተከላካዮች የተኩሱን ምክንያት ለማረጋገጥ ወደአካባቢው ሮጡ።ገመዶን እና አለምን ከጋጣው አስወጣችው።

በንዴት በሚንቀጠቀጥ ድምፅ‹‹በሰው ህይወት ውስጥ ጣልቃ መግባትሽን አቁሚ…በቃ አቁሚ››ጮኸባት፡፡

‹‹አንተም በጣም የምትወዳቸው ነገሮችንም ጭምር ማጥፋትህን አቁም››ብላ በተመሳሳይ ቶን ጮኸችነት፡፡

‹‹ለምወዳቻው የሚበጃቸውን ነገር ከማድረግ ወደኃላ አልልም….ነፍሴን ምትሰቃይ ቢሆንም እንኳን ግድ የለኝም ››

ስለፈረሱ ብቻ ሳይሆን ስለእናቷም እያወራ እንደሆነ ገባትና በፍርሀት ተንቀተቀጠች፡፡እሳቱ ሙሉ በሙሉ መጥፋቱን የእሳት አደጋ ኃላፊው አረጋገጠ፡፡ አቶ ፍሰሀ ፤ገመዶና አለም ተከታትለው እዛው አካባቢ ወደሚገኘው የአቶፍሰሀ ቤት ሄዱ፡፡ሲደርሱ ጁኒዬር ሳሎን ቁጭ ብሎ እየተከዘ ነበር፡፡

ሳሎን ተከታትለው እንደገቡ "ሳራ እንዴት ነች?"ሲል አቶ ፍሰሀ ጠየቀው፡፡

" እንድትረጋጋ አድርጌታለው….አሁን መድሀኒት ወስዳ ተኝታለች."ሲል ጁኒየር መለሰ።

አቶ ፍሰሀ "እስኪነጋ ድረስ ምንም ማድረግ ስለማንችል ወደ መኝታዬ ልሂድ …. አመሰግናለሁ ገመዶ፣ ባንተ ባይሆን ኪሳራችን ከዚህም በጣም የከፋ ይሆን ነበር፡፡ ››

‹‹ጋሼ..እናንተ እኮ ቤተሰቦቼ ናችሁ ….የወደመው የእኔም ንብረት ጭምር ነው››

‹‹አውቃለው…..ስለፈረሶችህ አዝናለው…ግን ከዚህ በፊት ደጋግመን ሊጥሉን ያሉትን ሰዎች አሸንፈን እንደተነሳን ከዚህኛውም ውድቀት በድል እንነሳለን››

‹‹አዎ እንነሳለን››ሲል በሀሳቡ ተስማማ፡፡

ጁኒየር እየተንቀጠቀጠች ያለችው አለም ዞር ብሎ አያት"አሌክሶ …አሁን ወደ ቤትሽ እንዳደርስሽ ትፈልጊያለሽ አለም? ››ሲል በሀዘኔታ ጠየቃት፡፡

"የስራዋን ውጤት እንድታይ ፈልጌ ነበር ያመጣዋት " አለ ገመዶ ጣልቃ ገብቶ ።

"ከዚህ እሳት ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም!"በንዴት እየተንዘረዘረች አለቀሰች።

"ምናልባት በቀጥታ ላይኖርሽ ይችላል" ሲል ፍሰሀ ገመዶን ደግፎ በቁጣ መለሰላት፣ "ነገር ግን ይህ በእኛ ላይ የከፈትሽው የሞኝ ምርመራሽ ተስፋ ቆርጠው ትተውን የነበሩ ጠላቶቻችን እንዲነቃቁና ብርታት እንዲያገኙ ምክንያት ሆኖቸዋል፡፡ ››

"ነገሮችን በዚህ መንገድ  ካየኸው ይቅርታ ጋሽ ፍሰሀ "አየሩ በውጥረት ተሞላ ።
በመጨረሻም ጁኒየር ወደ ፊት ሄዶ ክንዷን ያዘና

" ነይ ላደርስሽ።" አላት፡፡

"እኔ እመለሳታለሁ" ገመዶ በቁጣ አንቧረቀበት።

"የራሳችሁ ጉዳይ..ለማንኛውም እኔ ሄጄለሁ።" ጁኒዬር በንዴት ለመሄድ ተንቀሳቀሰ

"በቃ ይዘሀት ሂድ።" ገመዶ ነበር

"አንተ ነህ ያመጣኋት አይደል? የአንተ ኃላፊነት ነች" በማለት ክፍሉን ሙሉ በሙሉ ለቆ ወጣ፡

ፈገግታ የሌለው ፍሰሀ ልጁን ተከትሎ ወጣ። ገመዶ እና አለም ብቻቸውን ቀሩ

"ነይ" ብሎ ወደውጭ ተራመደ….።ተከተለችው እና በጭንቀት ምክትሉ ይዞት ወደነበረው የቢሮ መኪና ውስጥ ተከትላው ገባች።በዝምታ አካባቢውን ለቀው ወደእሷ ቤት አቅጣጫ መጓዝ ጀመሩ…. አስፈሪውን ዝምታ ለመስበር የሆነ ነገር ማለት ፈለገች፣ ነገር ግን አንዲት ቃል መናገር አልቻለችም። ገመዶ እሷን ለማናገር ፍቃደኛ የሆነ አይመስልም ፡፡

በመጨረሻም በደረቷ አካባቢ እየጨመረ የመጣውን የጭንቀት ቋጠሮ ስላፈናት ለመናገር ወሰነች
36👍2🥰1
"ዛሬ ምሽት ከተፈጠረው ነገር ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም" አለችው።አንገቱን ዞር አደረገና ግራ በሚያጋባ እይታ አስተዋላት…..የሆነ ነገር ይለኛል ብላ ብትጠብቅም ምንም አላላትም፡፡

"እዚህ ጉዳይ ውስጥ እጄ እንደሌለበት ጁኒየር የሚያምነኝ ይመስለኛል" ብላ አለቀሰች።

"በአንቺ ጉዳይ ስንጨቃጨቅ ስታይን ደስታ አሰከረሽ አይደል ?።››

በንዴት ጥርሶቿን አንቀረጨጨች"በኔ ምክንያት የምትጨቃጭቁበት ምንም ምክንያት የለም …ለማንኛውም.. ዛሬ ማታ በእርባታው ቦታ ላይ ለደረሰው ጉዳት እኔ ተጠያቂ ነኝ ብዬ አላስብም."

"ወደድሽም ጠላሽም ተጠያቂዋ አንቺ ነሽ። ጠላቶቻችንን አነሳስተሺብናል።"

ጭቅጭቃቸውን እልባት ሳያበጁለት መኪናዋ እሷ ቤት ጋር ደርሳ ቆመች….ገቢናውን ከፍታ ወረደች እና ከቤቷ ፊት ለፊት ቆመች። በሩ አሁንም ተገንጥሎ ገርበብ ብሎ እንደቆመ ነው።

ወደእሱ ዞረችና"ይህን በር የሚያስተካክል ሰው ልካለው ያልከኝ መስሎኝ ነበር።"አለችው

"እስከ ጥዋት ድረስ ታገሺኝ …ለዛሬው ከውስጥ ወንበር አስደግፈሽ መኝታ ክፍልሽን በራፍ ቆልፍሽ ተኚ..ደግሞም ሊነጋ ነው…ችግር የለውም››አለና መኪናውን አንቀሳቅሶ በቆመችበት ጥሏት ተፈተለከ፡፡አለም እቤቷ ከገባች በኃላ ራሱ መረጋጋት አልቻለችም…ገመዶ እንዳላት መኝታ ቤቷ ገብታ ከውስጥ በመቀርቀር አልጋዋ ላይ ኩርምት ብላ ስታሰላስልነው ነው ሊነጋጋ ሲል እንቅልፍ የጣላት …ጥዋት አንድ ሰእት ተኩል አካባቢ ሞባይሎ ጮኸ… ከአምስት ጥሪ በኃላ ከእንቅልፏ ባና አነሳችው፡፡
በሻከረ ድምፅ "ሄሎ?"

"ወ.ሪት አለም? አልቀሰቀስኩሽም አይደል? ከሆነ በጣም አዝናለሁ።››ልስልስ የሴት ድምጽ ነው፡፡አለም የደዋዬን ማንነት በድምጻ ለመለየት እየጣረች "አይ፣ ተነስቼ ነበር ››ስትል መለሰችላት፡፡

"ሳራ ጆ ነኝ"ድንጋጤ ሰውነቷን ሲወራት ታወቃት፡፡

በምንም አይነት ተአምር ሳራ የተባለች ቀዝቃዛ ሴት በዚህ ማለዳ ትደውልልኛለች ብላ ማሰብ አትችልም… ››

"ደህና ነሽ ወ.ሮ ሳራ?ችግር አለ እንዴ?"

ጁኒዬር የሆነ ነገር ሆነ ብላ ምትነግራት ነው የመሰላት፡፡በኋላ መልሳ ስታስበው በምን ስሌት ጂኒዬር የሆነ ነገር ቢሆን ለእሷ እንደማትነግራት ገባት፡፡

"አዎ ደህና ነኝ፣ ትላንትና ማታ ስለተናገርኩሽ የብልግና ንግግሮች ሳስብ በጣም ነው ያፈርኩት ።"

አለም የሴትዬዋን ኑዛዜ መስማቷ አስደንጋጭ ነው የሆነባት። እውነት ነው ብላም አምና ልትቀብል አልቻለችም፡፡"እረዳሻለሁ….በተፈጠረው አደጋ ተበሳጭተሽ ነበር።"ስትል መለሰችላት፡፡

"ቢሆንም ራሴን መቆጣጠር ነበረብኝ….እባክሽ ይቅርታ አድርጊልኝ››

‹‹አረ ችግር የለውም››ከዚህ ውጭ ምንም ልትላት ምትችለው ነገር እልነበራትም ፡፡
‹‹ዛሬ ከሰአት በኋላ ከእኔ ጋር ሻይ መጠጣት ብንችል ደስ ይለኛል…..እባክሽ?"

‹‹አለም ተኝቼ እያለምኩ ይሆን እንዴ?››ብላ ለማሰብ ተገደደች፡፡ ".. ችግር የለውም።"ነበር መልሷ፡፡

"ደህና ዘጠኝ ሰአት አካባቢ ይመችሻል?።"

"የት?"

"ለምን ፣ እዚህ እርባታ ግቢው ውስጥ ባለው ማረፊያ ቤታችት አናደርገውም…በዛውም የወደመውን ነገር መልሰው ለመገንባት እርብርብ ላይ ያሉ ሰራተኞችን እናበረታታቸዋለን…››

‹‹ችግር የለውም ..በቃ እገኛለው››

‹‹አመሰግናለው…..እስክንገናኝ ደህና ሁኚ።››

ስልኩ ተዘጋ፡፡አለም እንደደነዘዘች ነው፡፡የዚህች ሴትዬ ሁኔታ ምኑም አላማራት፡፡፡ስልኩ ላይ ለብዙ ሰከንዶች አፈጠጠች። ሳራ ለሻይ እንድትጋብዛት ያነሳሳት ምንድነው ? ሰዓቱ ደርሶ ከዚህ ግብዣ በስተጀርባ ያለውን ሚስጥር እስክታውቅ ድረስ ቸኮለች…ከዛ በፊት ግን መሄድ የሚገባት ቦታ አለ…..ገመዶ የላከው አናጺ መጥቶ በረፉን ከጠገነላት በኋላ ቀጥታ ወደጉዳዮ ሄደች፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
48👍8
አትሮኖስ pinned «#ቋጠሮ_ሲፈታ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አንድ ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ /// ገመዶ እኩለ ለሊት ላይ ስልኩ ጮኸ…. "ምንድን ነው ነገሩ" በማለት እየተነጫነጨ በተኛበት እጁን ዘረጋና ስልኩን ከኮመዲኖ ላይ አንስቶ ጆሮው ላይ ለጠፈና ‹‹ሄሎ››አለ፡፡ ‹‹ኮማንደር መስማት አለብህ ብዬ ነው…ድንገተኛ ነገር ተከስቷል."ምክትሉ ነበር፡፡ ከመኝታው ተነሳና አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠ፡፡ "…ምንድነው የተፈጠረው?"…»
#ቀን

ሁሉንም ሞክረን ፥ ሁሉም ባይሳካ

የጨበጥነው ጥሪት ፥ ባይኖረው በረካ

ቆመን ስንጠብቀው ፥ ገፍቶን ላለፈን ቀን

ተስፋ ተሸልመን ፥ ናፍቆት ባያፀድቀን

ተቀበል ውዳሴ ፥ “ተመስገንን” እንካ

ሽሽግ አልበትን

የማልቀሻ አፀዱን ፥ በአቴን አትንካ።

🔘ኪሩቤል ዘርፉ🔘
👍128🥰2
#ጳጉሜን_ስወዳት

ተቀጥያ ሁና
ማምሻ ላይ ብትመጣም...
ልታከትም ዘመን፣
ቀናችን ጠውልጎ
አዲስ እያጓጓን ብታየንም ታመን
እሷስ ድልድይ ናት...!
ጭጋግና ፍካት ..
መሀል ያለች ቁጥር ፤
ተስፋን የምትጭር
ምን አቅም ባይኗራት
ፍዳን ልታሳጥር
እስቲ እንቁጠራት
ከአንድ ጀምረን
ጠንቅቀን አመሏን
እግዜር በቃ ካለን
3 የሚዘንበውን..
ሳንስት ጠበሏን።
🥰127
#ጳጉሜነት

ምን ባይደላህም
ቀን ቢያጥርህ አዳሜ፤
ራስህን መስለው
ልክ እንደ ጳጉሜ፤
አንሰህ ብትታይም
ግዝፍናህን ቁጠር ፤
አምስት ቀናትን ይዞ
ተስተካክሏልና ከወር!!!

🔘ሀብታሙ ወዳጅ🔘
👍15🔥21
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

////

ከኪሊንኩ ጀርባ ያለው የዶ/ር ኤሊያስ  ቢሮ ምናልባት አለም ከዚህ በፊት ካየቻቸው ቢሮዎች ሁሉ የተዝረከረከ ሆኖ ነው ያገኘችው፡፡

"ዶክተር ኤሊያስ እኔን ለማየት ስለተስማማህ አመሰግናለሁ።"

"ችግር የለም …ዛሬ ብዙም ስራ አልነበረኝም " ከቀጥታ ከጠረጴዛው አጠገብ ያለውን የእንጨት ወንበር ላይ ያሉትን መጽሔቶችን አስነሳና ጠረጴዛ ላይ በማድረግ ለአለም እንድትቀመጥበት አመቻቸላት፡፡

"አንቺን ሳይሽ ብዙም አልተገረምኩም

"አላት በቅንነት ።

"ለምን?"

"ዋና አቃቢ ህጉ ደውሎ አንዳንድ ጥያቄዎችን ልትጠይቂኝ እንደምትፈልጊ ነግሮኝ ነበር።"

"ዛሬ ከከተማ ውጭ ያለ መስሎኝ ነበር."

"አይ ከቀናት በፊት ነበር ሰሞኑን ትመጣለች ቡሎ የነገረኝ ።"

"ገባኝ…ለሊት የእሳት ቃጠሎ ቦታው እንስሳቶችን ለመርዳት ስትሯሯጥ ስለነበርክ…ዛሬ እንዲህ ንቁ ሆነህ ቢሮህ አገኝሀለው ብዬ አላሰብኩም ነበር።"

በመደነቅ‹‹እንዴ እዛ እንደነበርኩ በምን አወቅሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹እኔም እንዳጋጣሚ እዛ ነበርኩ…አሁን ጊዜህን ሳልሻማብህ ቀጥታ ወደጉዳዬ ልግባ …የእናቴ የሰሎሜን ግድያን በተመለከተ መረጃዎችን እየሰበሰብኩ ነው….እባክህ አንተ በአቶ ፍሰሀ የእንስሳት እርባታ ድርጅት ውስጥ የእንስሳት ሀኪም ሆነህ እንደመስራትህ የምታውቀው ነገር ይኖር ይሆን ?" ስትል አሳዛኝ በሆነ የድምፅ ቅላፄ ጠየቀችው፡፡

"በእርግጥ እናትሽን አውቃታለው . እሷ በጣም አስደማሚ ሴት ነበረች. በእሷ ሞት ያላዘነ ሰው የለም ››

"አመሰግናለሁ፣ በዛን ወቅት በአቶ ፍሰሀ የእርባታ ድርጅት ውስጥ የእንስሳቱን ጤንነት ሚከታተሉት አባትህ እንደነበሩ ማወቅ ችያለው፡፡ "

" ልክ ነው …በዛን ወቅት አባቴ ነበር….እሱ ከሞተ በኋላ ግን ስራውን እኔ ተረክቤያለሁ." "አባትህ ስለ ሰሎሜ ግድያ ሁኔታ የሆነ ነገር ነግሮህ ይሆን?››

"በቀዶ ጥገና ቢላዋ መገደሏን በሰማ ጊዜ እንደ ሕፃን ነበር ተንሰቅስቆ ያለቀሰው››

"አባትህ እናቴ የተገደለለችበት መሳሪያ ከየት እንደመጣ አውቋል›?›

"አዎ …ያ አባቴ እንስሳቱን ለማከም የሚጠቀምበት መሳሪያ ነበር፣እናቴ ነበረች የሸለመችው የስሙ የመጀመሪያ ፊደል ተቀርፆበት ነበር ፡፡እንዴት አድርጎ ከቦርሳው እንደወደቀበት ነው ግራ የገባው፡፡››

"እንደዛ አይነት ግድ የለሽነት ከእሱ ባህሪ ጋር አይሄድም አይደል?"

"ትክክል ነሽ….አባዬ ለህክምና እቃዎቹ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያደርግ አይነት ሰው ነው
…በቆዳ በተለበጠ የእንጨት ሣጥን ውስጥ ነበር የሚያስቀምጣቸው…ያ ስለት ከሳጥኑ እንዴት እንደወደቀ ፈጽሞ ማወቅ አልቻለም ነበር, ››

"እናቴ በሞተችበት ቀን አንተ እዚያ ነበርክ?"

"ይህን ቀድመሽ ታውቂያለሽ ብዬ አስባለሁ። አባዬን ለመርዳት ትምህርት ከሌለኝ በስተቀር እዛ እገኝ ነበር …በዛም ቀን  አብሬው ሄጄ ነበር።››

"ገመዶ እዚያ ነበር?"

"በእርግጥ ኩማንደር እዚያም ነበረ።››

"ለሊቱን ሙሉ."

‹‹እሱን እርግጠኛ አይደለሁም…በመሀል አቋርጦ የሄደ ይመስለኛል››

"አባትህ የህክምና ቁሳቁስ የሚይዝበትን ሳጥን የሆነ ቦታ አስቀምጦ ዞር ብሎ ያውቃል?" ኤሊያስ ማሰላሰል ጀመረ … መልስ መስጠት እንደማይፈልግ ነገራት፡፡

‹‹ በዚያ ቀን በዛ አካባቢ ሌላ ማን ነበር?"ስትል ሌላ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

ለማስታወስ ሲጥር ተመለከተች‹‹‹ጁኒየር፣ ገመዶ፣ ጋሽ ፍሰሀ….እናትሽ….ስርጉት."

‹‹ ማን… ስርጉት ነበረች? ››

‹‹አዎ ነበረች …ከዛ ወደ ቤት መሄድ እንዳለባት ተናገረች እና አካባቢውን ለቃ ሄደች፡፡

‹‹ከግቢው ወጥታ ስትሄድ አይተሃታል….››

‹‹አይ መሄድ አለብኝ ብላ ስታወራ እንጂ ወጥታ ስትሄድ አላየኋትም….›› " ስለ ሊቁ ምን ማለት ይቻላል? እሱ በአካባቢው ነበር?"

‹‹እሱ ሁሌ  በሁሉም ቦታ የሚዞር..በሄድሽበት ቦታ የማታጪው አይነት ንክ ነበር ፣እውነቱን ንገረኝ ካልሺን ግን በዛን ቀን እሱን እዛ ቦታ እንዳየሁት አላስታውስም››

"እርሱን ካላየኸው በሰሎሜ ደም በተሸፈነ ልብሱ በቁጥጥ ስር ሲውል አልተገረምክም?"

‹‹በእርግጥ አልተገረምኩም…. ምን አልባት እኔ ሳላየው ጊቢ ውስጥ ሲዞዞር ከአባዬ ቦርሳ የወደቀውን ቢላዋ እንዳገኘው ገምታለው፣ ከዛ እናትሽን ገድሏታል ብዬ አስባለው.››

‹‹ነገር ግን ከዛ ሁሉ የአባትህ የህክምና መሳሪያዎች መካከል አንድ ቢላዋ ብቻ ሾልኮ መውደቁ ግራ መጋባት ውስጥ አይከትም… ?››

ዝም አላት…..፡፡

ይህ ዶ.ር የሶስቱም ተጠርጣሪዎች ጓደኛ ነው። በዛ ላይ በቋሚነት ለአቶ ፍሰሀ ተቀጥሮ የሚሰራ ሰው ነው፡፡የሚያውቀው ነገር እንኳን ቢኖር በምንም አይነት ተአምር አሳልፎ ሊሰጣቸው እንደማይፈቅድ አወቀች፡፡ከዚህ በላይ ጊዜዋን ማባከን ፋይዳ እንደሌለው ስላመነች ከመቀመጫዋ ተነሳችና አመስግናው ወደ ሁለተኛ ጉዳዮ አመራች፡፡
///
የእርባታ ድርጅት የእንቅስቃሴ አልባ ሆኗል ። የጽዳት ሠራተኞች ከቃጠሎ የተረፈውን ፍርስራሹን እና አመዱን እየሰበሰቡ እና እየጠረጉ በአካባቢው የቆመው መኪና ላይ እየጫኑ ነው። ኩማንደሩ በአካባቢው ወዲህ ወዲያ እየለ የሚሰራውን እየተመለከተ ነው፡፡ አለም ከመኪናዋ ስትወርድ አይቶታል፣ ነገር ግን እሷን ለማናገር ሲሞክር በአካባቢው የነበረው የእሳት አደጋ ተቆጣጣሪ ሰለጠራው ወደእዛ ለመሄድ ከተንቀሳቀሰ በኋላ ሀሳቡን ቀይሮ ቆሞ ጠበቃት፡፡ ደረሰችበት…ሰላም ይለኛል ብላ ስትጠብቅ

"እዚህ ምን እየሰራሽ ነው?"ብሎ ጠየቃት፡፡

‹ከሳራ ጋር ሻይ ልጠጣ ነው የመጣሁት።››

በመደነቅ አፍጥጦ ተመለከታ‹‹ከእሷ ጋር ደግሞ ከመቼ ወዲህ ነው ጓደኛ የሆናችሁት?››

“ሃሳብ የእኔ ሳይሆን የእሷ ነበር” አለችው።

"እሺ ተዝናኑ" አለና ፊቱን አዙሮ ሲጠራው ወደ ነበረው ሰውዬ ሄደ፡፡

እሷም ወደማረፊያ ቤቱ ተራመደች..አቶ ፍሰሀ  በቤቱ በረንዳ ላይ ቆሞ ነበር፣ ስትጠጋ ፍርሃቷ እንዳይታይ ለማድረግ ሞክራለች።

"እንዴት ነህ … ጋሽ ፍሰሀ?"

"  ሰዓት  አክባሪነትሽ  የሚደነቅ  ነው…እናትሽም  ልክ  እንደዚህ  ነበረች››አላት፡፡ለምን እንደመጣች እንደሚያውቅ ተረዳች

‹‹አመሰግናለው››አለችው፡፡

‹‹ምንም አይደል››

"ኩማንደሩ እሳቱን ያስነሳውን ሰው  በቁጥጥር ስር እንደሚያውለው  ተስፋ አደርጋለሁ። እኔም ተገቢን ፍትህ እንድታገኙ አስፈላጊውን ሁሉ አደርጋለሁ።"ስትል ቃሏን ሰጠችው፡፡

"አዎ፣ እኔም ተስፋ አደርጋለው… ሁሉንም ነገር ችላ ማለት እችላለሁ። ነገር ግን ያን የመሰለ ተወዳጁን የገመዶን ፈረስ እንዲሞት ያደረገውን ሰው ግን ይቅር አልለውም።ያን ፈረስ በማሳደግና በመንከባከቡ ይሰማው የነበረውን ኩራት እኔ ነበርኩ የማውቀው።"

በዚህ ጊዜ ጁኒዬር ከውስጥ ወጣ…በውብ ፈገግታ ተሞልቶ የሞቀ ሰላምታ ሰጣት፡፡ አለም"ወደ ውስጥ ብገባ ይሻለኛል… እናትህን ብዙ አላስጠብቃት" አለቸው ።
ጁኒየር እጁን ትከሻዋ ላይ ጫነና "እናቴ የትላንት ማታውን ጥፋቷን ማረም ትፈልጋለች። ግብዣዋን ስለተቀበልሽ በጣም ተደስታ ነበር። አንቺን ለማየት በጉጉት እየጠበቀችሽ ነው።››አላት

‹‹ጥሩ››ብላ ወደ ውስጥ ገባች፡፡
አገልጋይዋ በራፉ ድረስ መጥታ ተቀበለቻት።‹‹ግቢ።››ብላ ወደ ውስጠኛው ክፍል እየመራች ወሰደቻትና ከሳራ ጋር አገናኘቻት፡፡

ከሳራ ጋር ተጨባበጡና ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳሙ፡፡
አለም የክፍሉን ዙሪያ ገባ እየተመለከተች"እንዴት የሚያምር ክፍል ነው?!"

"ወደድሽው?።"

‹‹በጣም እንጂ…››
42👍7👏2
ሳራ  ክፍሉ  ውስጥ  ወደ  ነበረችው  ሰራተኛ  ዞረችና  "እባክሽ  በሩን  ዝጊው።
››አለቻት፡፡ሰራተኛዋ በሩን ዘጋችና ትታቸው ሄደች ፡፡ አለም እንድትቀመጥ ባሳየቻት ቦታ ተቀመጠች፡፡

"ስለጋበዝሽ አመሰግናለሁ። በጣም ጥሩ ሀሳብ ነበር።"

"ትናንት ማታ ስለተናገርኩሽ ነገር ይቅርታ መጠየቄ ግዴታ ነበር።"

" ግድ የለም.. አሁን እሱን እንርሳው።"

በሩ ተከፈተና ሰራተኛው ሻይ የያዘ ፔርሙዝና  ኩኪሶች ያየዘ አንድ ሰሀን አምጥታ በመሀከላቸው በሚገኝ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠችና እንደአመጣጧ ወጥታ ሔደች፡፡

ሳራ ፌርሙዙን አነሳችና ሻዩን የሁለቱም ብርጭቆ ላይ ከቀዳች በኋላ..‹‹ስኳር ስንት ማንኪያ ላድርግልሽ?"በማለት ጠየቀቻት፡፡

‹‹እባክሽ..ሁለት ይበቃኛል;;››አለም መለሰች፡፡

"አመሰግናለሁ።"

ሳንድዊች አንስታ እየጎረሰች ሻዬን ጠጣችና እና መልሳ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠች፡፡
ሳራ ቀጥታ ወደጉዳዮ ገባች

"ከፍሰሀ እና ጁኒየር በስተቀር የቀረኝ ቤተሰብ የለኝም።በልጅነቴ ከጀማይካ ወደእዚህ ይዘውኝ የመጡት እናትና አባቴ ነበሩ.. አሁን ሁለቱም ሞተዋል…በስመ ጀማይካዊ ካልሆነ በስተቀር እዚህ ኢትዬጵያ ውስጥ የቅርብ ዘመድ የለኝም፡፡››

‹‹ይሄን በመስማቴ አዝናለው…ያው እንደምታውቂው ዘመድን በተመለከተ እኔም ካንቺ ብዙ አልሻልም›› ስትል መለሰችላት፡፡

"ምን መሰለሽ …ሙታን በተቀበሩበት በሰላም እንዲያርፉ መፍቀድ የተሻለ እንደሆነ እየነገርኩሽ ነው፡፡››
አለም የሳራ የንግግሯ አቅጣጫ እየገባት ነው ፡፡

"ስለእናቴን ነው የምትናገሪው?"

"በትክክል ….ይህ የአንቺ ምርመራ መላ ቤተሰቤን ሰላም እየነሳ ነው›፡፡››

"ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ እጠይቃለሁ፣ ነገር ግን  በእኔ እቅድ ላይ ምንም የሚደረግ ለውጥ የለም።"ስትል መለሰችላት፡፡

"ወንበዴዎች ንብረቴን አወደሙት፣ ዛሬ የእንስሳቱን ህይወት አደጋ ላይ ከጣሉ ነገ ደግሞ ባሌን ወይም ልጄን ለማጥቃት ከማድባት ወደኃላ አይሉም፡፡ ››

አለም "ይህ አሳዛኝ ክስተት ነበር ። በዚህ ጉዳይ ምን ያህል እንዳዘንኩ ልነግርሽ አልችልም" በማለት ሴትየዋን እንድትረዳ ተማፀነች፡፡

ሳራ ጆ በረጅሙ ተነፈሰች። "እናትሽ ከጁኒየር እና ገመዶ ጋር ስለነበራት ግንኙነት ምን ያህል ታውቂያለሽ?"

"አያቴ የነገረችኝን ብቻ፣ እዚህ ሻሸመኔ ከመጣው በኃላ ካነጋገርኳቸው  የተለየያዩ ሰዎች የሰበሰብኩት  የተወሰነ መረጃም አለ።"

"እንደ መንትያ ወፎች አይነት ነበሩ… ለራሳቸው ትንሽ ቡድን ፈጥረው ነበር. ጁኒየር ከእነሱ ጋር እንዲገናኝ አልፈልግም ነበር….ገመዶ በሁሉም ነገር የሰከረ የከተማ ልጅ ነበር። እና እናትሽም እንደዛው ...ከእነሱ ጋር እንዲጣመር የማልፈልግበት ብዙ ምክንያቶች ነበሩ።"

"አንድን ጥቀሺልኝ."

"በዋነኛነት በእሷ እና በገመዶ መካከል ስላለው ሁኔታ ጁኒየር ሁል ጊዜ ሁለተኛ ምርጫዋ እንደሆነ አውቅ ነበር። የተሻለው የቱ እንደሆነ እንኳን መለየት የማትችል ከንቱ ነበረች፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ለጁኒየር ላስረዳውና ላስጠነቅቀው ብሞክርም ስለሚወዳት ሊሰማኝ አልፈቀደም። እንደፈራሁት  አፍቅሯት ነበር።" በድንገት ዓይኖቿ በአለም ላይ አተኩሩ።የሳራ አይኖች በክፋት ጠበቡ።

"እናትሽ ተንኮለኛ ነበረች።››

"እስከዚህ ነጥብ ድረስ አለም ምላሷን በጥንቃቄ ተቆጣጥራ ነበር። ነገር ግን ጋባዦ በሟች እናቷ ላይ ምትሰነዝረውን ልቅ ንግግር መታገስ አልቻለችም፡፡

"ከዚያ የስም ማጥፋት የተለየ አስተያየት አለኝ ወይዘሮ ሳራ።››

ሳራ ግድ የለሽ በሆነ ሁኔታ እጆን አወናጨፈችን " ግድ አይሰጠኝም…የተናገርኩት እውነቴን ነው፤እሷን ባገኘኋት ጊዜ ቆንጆ ነበረች፣ በጋለ ስሜት ነበር የምታወራው። የሚወደድ አይኖች ነበሯት ። ጮክ ብላ ነበር የምትስቀው፣ ተጫወች ነበረች፣ ስትጠጣ በጣም ስሜታዊ ስለምትሆን እራሷን መቆጣጠር አትችልም ነበር፡፡ በጣም ሐቀኛ ትመስላለች ግን አልነበረችም፡- ስትናገር በኩራት ነው፡ ‹‹ሰዎች የሚሰማቸውን በግልጽ ቢናገሩ ዓለም የተሻለ ሊሆን ይችል ነበር›› ብላ የምትጎርር አይነት ሴት ነች።ወንዶች ሁሉ ያለ ልዩነት ይፈልጓት ነበር፡፡ ያገኘችውን ወንዷች ሁሉ በፍቅር እንዲወድቁላት በማድረግ እርካታ የሚሰማት አይነት አደገኛ ሴት ነበረች፡፡ ››

"እራሷን ለመከላከል የማትችልን  ሴት ከዚህ በላይ  እንድታጣጥያት  አልፈቅድልሽም. ንግግርሽ ከስርዓት ያፈነገጠ ነው ወ.ሮ ሳራ፡፡››

ስትገባ እንደ ግሪንሃውስ ንፁህ አየር የሞላው የነበረ ክፍል አሁን የታፈነ ይመስላል። ለቃ መውጣት ፈለገች፡፡

"መሄዴ ነው"አለቻት፡፡

"ገና አልጨረስንም.እናትሽ ከራሷ በላይ ኩማንደሩን ትወደው ነበር።"

"ታዲያ ይሄ ጉዳይ አንቺን  እንዴት ሊያሳስብሽ ቻለ?"

"ምክንያቱም ጁኒየርን በዚህ ጉዳይ ውስጥ ስላስገባችው ነው የሚያሳስበኝ ..አያትሽ ያቺ ደደብ ሴት በልጆቻችን መካከል መግባቷን ስላወቀች በጣም ተናደደች:: ጁኒየር ሰሎሜን እንዲያገባ የፈቀድኩኝ አስመስላ መንቀሳቀስ ጀመረች" ስትል ተሳለቀች::

‹‹አልገባኝም››

"አያትሽ አንድ ጊዜ ደውላልኝ የወደፊት አማቶች እንደመሆናችን መጠን በደንብ እንድንተዋወቅ ሀሳብ አቀረበችልኝ፣ በእግዚአብሔር ስም.. በዛኑ ጊዜ መሞት ነበር የፈለኩት
›› አለችና .. በንቀት ሳቀች።

‹‹ከዛ ምን አልሻት?››አለም በንዴት እየተንተከተከች ጠየቀች፡፡

"አለም ምራቴ የምትሆንበት ምንም አይነት እድል አልነበረም። ይህንንም ለአያትሽ በግልፅ ነበር የነገርኳት።እና ምን ለማለት ፈልጌ መሰለሽ …ከቅርብ ጊዜ ወደዚህ እሱ ስለ አንቺ ብቻ ነው የሚያስበው፤ ልክ ከእናትሽ ጋር እንደነበረው."

"ወ.ሮ ሳራ አትስጊ…በመካከላችን የፍቅር መጠላለፍ በፍፁም ሊኖር አይችልም። ምናልባት ይህ ምርመራ ከተፈታ በኋላ ጓደኛሞች ልንሆን እንችል ይሆናል።››

ሳራ "እናትሽም እንደዚሁ ነበር የምትለው…በኋላ ግን ጓደኝነታቸውን አላግባብ ተጠቀመችበት ፡፡ምክንያቱም ጓደኝነታቸው ወደጋብቻ ያድጋል የሚል ስውር ተስፋ ነበራት፡፡

አንቺም እንደ እናትሽ ምርመራውን እንደሰበብ አድርገሽ ከእሱ ለመቀራረብ እና ልቡን ለመስረቅ እየተጠቀምሺበት ነው።››አለቻት

"ይህ በበፍጹም እውነት አይደለም."

"እውነት ካልሆነ ለምን ወደዚህ መምጣት አስፈለገሽ?"ሳራ በመንገሽገሽ ጠየቀች፡፡
"የመጣሁበት አላማማ ግልፅ ነው…እናቴ ለምን እንደተገደለች እና ማን እንደገደላት ለማወቅ እፈልጋለሁ."

ጣቷን በቀጥታ ወደ አለም ልብ እየጠቆመች"እናትሽ የተገደለችበት ምክንያቱማ አንቺ ነሽ!" አለቻት ። አለም ይህንን ንግግር ከዚህ በፊት ከገዛ አያቷም አንደበት ሰምታ ነበር …አሁን ከወ.ሮ ሳራ ለሁለተኛ ጊዜ ስትሰማው የመሬት መንቀጥቀ የተነሳ ያህል ነው መላ አካሏን የነዘራት፡፡

‹‹ምን ማለት ነው?››

"አንቺ የሰሎሜ ዲቃላ ልጅ ነሽ ››
አለም ስለታም ብረት በሆዷ ውስጥ እንደተሻጠ አይነት ህመም ተሰማት፡፡

‹‹አልገባኝም›› "

የምናገረው ግልፅ እኮ ነው…ከጋብቻ ውጭ የተወለድሽ ህገ ወጥ ልጅ ነበርሽ"

"ይህ ውሸት ነው" አለም ትንፋሿን ካደት። "እናቴ ከጎበና ጋር ተጋብታ ነበር። የሰማንያ ወረቀታቸው አይቻለው ።"ከተቀመጠችበት ተነስታ ቆመች፡፡
41👍1
"አይደለም…..ክርምት ቤተሰቦቼን ልጠይቅ ብላ ኮፈሌ ሄዳ ነበር….ግን ስትንዘላዘል አንቺን ፀንሳ ተመለሰች….አላወቀችም ነበረና ሀገር ሳላም ነው ብላ ከገመዶም ሆነ ከልጄ ጋር ያላትን ግንኙነት ቀጥላበት ነበር….በኃላ ግን ማርገዟን አወቀች….ማስወረድም አልቻለችም መሰለኝ መልሳ ወደኮፈሌ ተመልሳ ጠፋች….ዘመዶቾ ልጁን አስገድደው እንዲያገባት አደረጉ
…ግን ሰማንያውን ፈረመ እንጂ አንድ ቤት እንኳን አልገቡም ነበር…ከዛሬ ነገ እቤት ተከራይቶ እና እቃ አሞልቷ ይጠቀልለኛል ብላ ስትጠብቅ እሱ ሹልክ ብሎ ውትድርና ተቀጠረና ሄደ… እሷም የተቀበተተ ሆዷን እና የሰማንያ ወረቀቷን ይዛ አይኗን በጨው አጥባ ወደእዚህ ተመለሰች….ደጋግሜ እንደነገርኩሽ ሁሉንም ወንዶች የሚያደነዝዝ አዚም ስላለባት ሁለቱም ቢበሳጩባትም ከህይወታቸው ሊያስወግዷት አልፈቀዱም…..እስከነ ዲቃላዋ ይንከባከቦት ጀመረ…. ከዛ አንቺም ተወለድሽ.. ዲቃላ ያስታቀፋትም እዛው ወታደር ቤት እንደገባ መሞቱን መርዶ መጣላት፡

"ውሸትሽን ነው!" አለም እንዳትወድቅ ስለፈራች  የወንበሩን እጄታ ያዘች።

"ለምን እዋሻኛለሁ?ቤተሰቦቼን ከአንቺ የበቀል ጥፋት ለመጠበቅ እየሞከርኩ ነው። ፍሰሀ በአመታት ልፋት የገነባውን ሁሉ እንድታጠፊ አልፈቅድም። በቤተሰቤ ውስጥ አለመግባባት እንድትፈጥሪ አልፈቅድም። ከዚህ በፊት እናትሽ እንደዛ አድርጋ ነበር… አሁን.. ግን አልፈቅድም።

"ሴቶች… ሴቶች." ጁኒየር እየሳቀ ወደ ክፍሉ ገባ።‹‹ ይህ ጩኸት ምንድነው? ሸረሪት ተመለከታችሁ እንዴ?"

በመካከላቸው ያለውን ጥላቻ ሲታዘብ ቀልዱን አቆመና ግራ በመጋባት እያፈራረቀ ያያቸው ጀመር ። በአቅራቢያው መብረቅ የወረደ ይመስል አለም ደርቃና ገርጥታ ተመለከታ፡፡

"እናቴ? አሌክስ? ምን ተፈጠረ?"

አለም ምንም ሳትናገር ወንበሩ ላይ የተንጠለጠለውን ቦርሳዋን አነሳችና ከክፍሉ በፍጥነት ወጣች እና ሄደች ፡፡ጁኒየር አለምን ከኋላ ተከትሎ ከመግቢያው በር ጋር ደረሰባት ፡፡

"ምንድን ነው የተፈጠረው?"

አለም እንባዋን እንዳያይ ፊቷን በእጆቾ ሸፈነች።

"ምንም።"

" ሻይ ለመጠጣት እንደተቀጣጠራችሁ ስሰማ እኮ በጣም ደስ ብሎኝ ነበር››

"ሻይ? ሃ!ሻይ እንድንጠጣ አይደለም የጋበዘችኝ››

‹‹እና ለምንድነው?››

እንባዋ እንዳይወርድ ለማድረግ ብላ ዓይኖቿን ብታሽም አልተሳካላትም "ለነገሩ ስለነገረችኝ ማመስገን አለብኝ ።"

"ምንድነው የነገረችሽ?" "እኔ ዲቃላ መሆኔን ."

የጁኒየር ፊት በድንጋጤ ባዶ ሆነ።

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍4418😢1
🌼ውድ የቻናሉ ተከታዎችእንኳን ለ 2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሠላም  በጤና አደረሳችሁ

❤️በዓሉ የሠላም፣ የጤና፣ የደስታ እና የፍቅር አመት እንዲሆን  ለሁላችሁም ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኛለን !

   🌼መልካም አዲስ ዓመት ለሁላችን🌼
@atronosee
         
5🥰2
አትሮኖስ pinned «#ቋጠሮ_ሲፈታ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሁለት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ //// ከኪሊንኩ ጀርባ ያለው የዶ/ር ኤሊያስ  ቢሮ ምናልባት አለም ከዚህ በፊት ካየቻቸው ቢሮዎች ሁሉ የተዝረከረከ ሆኖ ነው ያገኘችው፡፡ "ዶክተር ኤሊያስ እኔን ለማየት ስለተስማማህ አመሰግናለሁ።" "ችግር የለም …ዛሬ ብዙም ስራ አልነበረኝም " ከቀጥታ ከጠረጴዛው አጠገብ ያለውን የእንጨት ወንበር ላይ ያሉትን መጽሔቶችን አስነሳና…»
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///

"ምንድነው የነገረችሽ?"

"እኔ ዲቃላ መሆኔን ."

የጁኒየር ፊት በድንጋጤ ባዶ ሆነ።

"እውነት ነው አይደል?"
ጁኒየር እጆቹን ዘረጋና እቅፉ ውስጥ አስገባት… እንባዋ በመጨረሻ የዐይን ሽፋኖቿን ሞልተው ያለከልካይ ፈሰሰ።

"ሰሎሜ ከኮፈሌ ተመልሳ መጣች። ከገመዶ ጋር ለመታረቅ ተዘጋጅታ ነበር።ፍቅራቸውን ለማደስ ተስማምተው ነበር …የመጋባት እድል ሁሉ ነበራቸው…በመሀል ግን ለማንኛችንም ሳትነግረን መልሳ ጠፋች….በኋላ ነው አንቺን ማረገዟን ስላወቀች እንደጠፋች ያወቅነው፡፡››ሲል አስረዳት፡፡

በእፍረት ፊቷን በእጆቿ ሸፈነች።
" ኦ አምላኬ በጣም ቢጠላኝ አይገርምም።››

ጁኒየር እጆቿን ከፊቷ ላይ አንስቶ በቅን ልቦና የሚወዳቸውን ጥቆቁር አይኖችን እየተመለከተ።

"ገመዶ አንቺን አይጠላሽም አሌክስ። ማናችንም ብንሆን አንጠላሽም…ያ ከአመታት በፊት ተጋፍጠን በይቅርታ ያለፍነው ጉዳይ ነው››

በንግግሩ በምሬት ሳቀች።‹‹ለምን አያቴ ሁሌ እኔ ላይ ጥብቅ እንደምትሆን እያሰብኩ እበሳጭ ነበር …በስንት ሰዓት ከቤት እንደወጣው? በስንት ሰዓት እንደተመለስኩ..?ከማን ጋር እንደነበርኩ ከአግባቡ ያለፈ ቁጥጥር ታደርግብኝ ነበር…ምክንያቷ አሁን ነው የገባኝ
…ለካ እናቴን ያጋጠማት ነገር እንዳያጋጥመኝ ፈርታ ነው፡፡አሁን ነው የገባኝ፡››

"ይሄ ከሃያ አምስት አመታት በፊት የሆነ ድርጊት ነው ፣ አሌክስ አሁን ስለዛ ማሰብ አቁሚ "

"አያቴ በእውነት እኔን ለምን እንደማትወደኝ የሚያብራራልኝ ታሪክ ነው… የሰሎሜን ህይወት አበላሽቻዋለሁ…እና ለዛ ፈጽሞ ይቅር ሳትለኝ ነው የሞተችው…. ሰሎሜ ገመዶን አጥታለች …ፍቅራቸው እንዳይሆን ሆኖ ተሰባብሯል … እና ሁሉም የሆነው በእኔ ምክንያት ነው››.

‹‹ኦህ፣በእግዚአብሔር !ተረጋጊ እንጂ!"
አለም ከእቅፉ ወጣችና ወደ መኪናዋ ሮጠች…መኪና ውስጥ በመግባት አስነሳችና አካባቢውን ለቀቀች።

."ምንድነው ነገሩ?" አለም ወደ መኪናዋ አቅጣጫ ስትሮጥ ያያት አቶ ፍሰሀ ጠየቀው።

"ሁለታችሁም እሷን ተዋት" ሳራ ከውስጥ እየወጣች ለባሏ መለሰች፡፡

ጁኒየር ወደ እናቱ ዞረና።

"እማዬ እንዴት እንዲህ ታደርጊያለሽ? እንዴት ልጅቷን እንዲህ ትጎጂያታለሽ?"

"ልጎዳት አስቤ አይደለም የነገርኳት፡፡››

"ምን ነግራት ነው?" አቶ ፍሰሀ ጠየቀ ፡፡

ጁኒየር “በእርግጥ ጎድተሻታል። ደግሞ አቅደሽበት ነው ያደረግሽው… ለምን ነገርሻት?"

‹‹ምክንያቱም እሷ ማወቅ ስላለባት። አለምን የምትጎዳት እራሱ አለም ብቻ ነች። ሸቅዠቷን እያሳደደች ነው። የምትፈልጋት አይነት ቅድስት የሆነች እናት በሰሎሜ ውስጥ አልነበረችም። ሰሎሜ ምትባል ድንቅ እናት እንደነበረቻት በማይረባ ጭንቅላቷ ደምድማለች። እናቷ ምን ያህል ተንኮለኛ እና ሀጥያተኛ እንደሆነች ልጅቷ ማወቅ አለባት.. እናቷ ስትማግጥ እሷን ዲቃላ እንዳረገዘቻት የማወቅ መብት አላት››

" አንቺ እኮ ጤነኛ አይደለሽም!" አቶ ፍሰሀ ተበሳጨባት፡፡

አቶ ፍሰሀ በጸጥታ ወደ መኝታ ቤት ገባና ከኋላው በሩን ዘጋው፡፡ሳራ በአልጋዋ ላይ ያሉትን ትራስ ደራርባ ተደግፋ መፅሃፏን እያነበበች ነበር…እሱን ስታይ መፅሀፉን ከደነችና አጠገቧ ያለው ኮመዲኖ ላይ አስቀመጠች ።

ወደአልጋው ቀረበና " ላናግርሸ እፈልጋለሁ።"አላት፡፡

"ስለ ምን?"

‹‹ዛሬ ከሰአት በኋላ ስለተፈጠረው ነገር።››
"ራስ ምታት እየፈለጠኝ ነው…ለእራት ወደታች ያልመጣሁትም ለዛ ነው"

‹‹የሆነ መድሀኒት አልወሰድሺበትም?"

"አዎ ወስጄለሁ…አሁን በመጠኑ እየተሻለኝ ነው ።"የሳራ የራስ ምታት በትዳራቸው ልክ አብሯት የቆየ ህመም ስለሆነ የተለመደ ነው፡፡

በአልጋው ጫፍ ላይ ተቀመጠ እና አቀርቅሮ ሀሳብ ውስጥ ገባ፡፡

" ምንድነው ፍሰሀ ?አሁንም የሚያሰጋን ችግር አለ እንዴ?››ጠየቀች፡፡

"አይ..ሁሉም ነገር ሰላም ነው።"

"ታዲያ ለምን ታስባለህ…?እግዚአብሔር ይመስገን ብቸኛው የሞተው ፈረስ የገመዶ ነው
።››
አቶ ፍሰሀ ምንም አስተያየት መስጠት አልፈለገም ። ሳራ ጆ ለገመዶ ያላት ስሜት ፈጽሞ አይለወጥም፤በዚህ ጉዳይ ከእሷ ጋር መነጋገር ጥቅም አልባ እንደሆነ እርግጠኛ ነው፡፡ከእሷ ጋር ሊወያይ የመጣው ስስ ስለሆነ ጉዳይ ነው። ቃላቱን በጥንቃቄ ለመምረጥ ትንሽ ጊዜ ወሰደበት.

"ሳራ ዛሬ ከሰአት በኋላ -……" "በጣም ተበሳጭቼ ነበር" አለችው፣ ፡፡

" ተበሳጭተሽ ነበር?" ፍሰሀ ትዕግሥተኛ ሆኖ ጠየቃት፡፡ወደ ድምዳሜው ከመዝለሉ በፊት ከእሷ ወገን ያለውን የታሪኩን ገጽታ መስማት ፍልጓል።

"የአለምን ስሜትስ የጎዳሽ አይመስልሽም…?"

"ዲቃላ መሆኗን ስላወቀች ብቻ አይደለም የተናደደችው….እሷ በተፈጥሮዋም ብስጩ ነች:: "

"እኔ በእሷ ቦታ ብሆን አይገርመኝም… ወላጆቼ የጋብቻ ሰርተፊኬት እንዳላቸው በጭራሽ አጣርቼ አላውቅም.., እና ባይኖራቸውም ምንም አይመስለኝም ነበር.››

" ሁሉም ሰው ለነገሮች ያለው ምላሽ የተለያየ ነው››

‹‹ አለም ግን ስሜታዊነት የሚያጠቃት ወጣት ሴት ነች።"

"እሷ ይሄን ታሪክ ለመቀበል የሚያስችል ጥንካሬ እንዳላት አምናለው."ስትል መለሰችለት

"በእርግጥ የምትይውን ያህል ጥንካሬ እንዳላት እርግጠኛ አይደለሁም።በረንዳ ላይ ቆሜ እያየችኝ እኔን እንኳን ሀሳትሰናበተኝ ነው ገፍትራኝ ሮጣ የሄደችው፡፡››

የሳራ ፈገግታ ተሰበረ። "ስለነገርኳት ትወቅሰኛለህ? ስህተት የሰራው  ይመስልሃል?"ስትል ጠየቀችው፡፡

በዛ ልብን በሚሰረስር የግሏ የሆነ ልዩ እይታ ስታየው፣ ልቡ ቀለጠ። ሁል ጊዜም የዚህ አይነት አስተያየት ስታየው የሚሆነው እንደዚሁ ነው። ፍሰሀ በስሱ ይዳብሳት ጀመር፡፡

‹‹ውዴ ስለነገርሻት አልወቅስሽም። ግን የነገርሽበት መንገድ እንደዚህ ባይሆን ጥሩ ነበር፡፡ እንደዛ ከማድረግሽ በፊት ከጁኒዬር እና ከእኔ ጋር መመካከር ነበረብሽ…በህይወቷ ሙሉ ባታውቀው የሚሻል ታሪክ ነበር፡፡››

"አልስማማም" ስትል ሳራ ተከራከረች።
አቶ ፍሰሀም "እናቷ እና አባቷ አብረው ከተኙ በኃላ አለመጋባታቸው ወይ መጋባታቸው በእሷ ልጅነት ላይ አሁን ምን ለውጥ ያመጣል? ይህ በቡዙ ወጣት ሴቶች ህይወት ላይ የሚያጋጥም በጣም የተለመደ ነገር ነው..››አላት፡፡

"ልጅቷ ስለ ሰሎሜ ያላት አመለካከት ላይ ግን ለውጥ ያመጣል። ››

‹‹እንዴት?››

‹‹ሰሎሜ ልጅቷ የምታስባትን አይነት ቅድስት ሴት አይደለችም…ይሄን ማወቋ የእሷን የግድያ ጉዳይ ለማወቅ የምታደርገውን ልፋትና ጥረት ቆም ብላ እንድታይ ያግዛት ይሆናል….ይልቅ ከአሁን በኃላ ሁላችሁም ከአለም ጋር መገናኘቱን እና መወያየቱን ማቆም አለባችሁ፡፡››

"ለምን?"ግራ ገብቶት ጠየቀው፡፡

"ለምን? ምክንያቱም እሷ እኛን ለማጥፋት እየሞከረች ነው…ለዚህ ነው. እሷን ለመፋለም የወሰንኩ…. ያለኝን ጥይት ነው የተጠቀምኩት….አንተን እና ጁኒየርን ለመጠበቅ እየሞከርኩ ነበር."

በእውነቱ፣ ፍሰሀ እንደ አለም ያለ በራስ መተማመን የነበራትን ሴትን ለመጋፈጥ ለሣራ ትልቅ ድፍረት እንደሆነ አሰበ። ያደረገችው ስህተት ቢሆንም ሳራ ያደረገችውን ነገር ያደረገችው ቤተሰቧን ልትጠብቅ እንደሆነ ተረድቷታል። የጀግንነት ጥረቷ ከትችት የተሻለ ነገር ይገባዋል ብሎ አሰበ እና ጎንበስ ብሎ ግንባሯን ሳመ።

ለስለስ ባለ ንግግር" የትግል መንፈስሽን አደንቃለሁ… ግን ማናችንም ያንቺን ጥበቃ አንፈልግም ።"አላት፡፡
46👍3
በሃሳቡ ሳቀች። "እንዴት እንደ አንቺ ያለች ደካማ ሴት ከመካከላችን ትልቅ እና የታጠቁ ወንዶችን ልትጠብቅ ትችላለች ለማለት ነው?አታስተውልም እንዴ ጁኒየር እኮ ከእሷ ጋር ፍቅር እየያዘው ነው."

"ታዲያ ቢይዘው ምን ችግር አለው ?" አለ በሚያብረቀርቅ ፈገግታ። ሳራ "እናቷ ልቡን ሰብራው ነበር ፣ ያ አያስጨንቅህም?"።
ፍሰሀ ፊቱን አኮሰታትሮ፣

"ያ ከረጅም ጊዜ በፊት የሆነ ነው። እና አለም እንደ እናቷ አይደለችም።"

"በዛ እርግጠኛ መሆን አልችልም." አለችና ሳራ ወደ ኮርኒሱ ተመለከተች።

"አለም እንደ ሰሎሜ ተለዋዋጭ እና ?ገራሚ ሴት አይደለችም….እንደውም እሷ በጣም ጎበዝ ሴት ነች ፣ ምናልባት ለጁኒየር የምታስፈልገው እንደእሷ አይነት ሴት ልትሆን ትችላለች
… እስከአሁን ብዙ ሴቶች ለማግባት ሞክሮ አንዱም ትዳር ሊሰምርለት አልቻለም፤እንደ እሷ  ምን እንደሆነ የምትነግረው ሴት ይፈልጋል ።"

"በነገራችን ላይ አሁን የት ነው ያለው? አሁንም እንደተናደደብኝ ነው?" ብላ በጭንቀት ጠየቀች።

" ተበሳጨቷል … ነገር ግን እንደ ሁልጊዜውም በመስከር ብስጭቱን ሊረሳ ሄዷል ." ሁለቱም ተሳሳቁ።

" ተጠንቅቆ እንደሚነዳ ተስፋ አደርጋለሁ።"
‹‹ምን አልባት …ሌሊቱን እዛው የሚያሳልፍ ይመስለኛል ." "ወይ ተው እንጂ ?"
"እንደዛ ቢያደርግ …አይገርመኝም" አለ ፍሰሀ

"አለም እራሷን ለማስተካከል የተወሰነ ጊዜ ያስፈልጋታል። ዛሬ ማታ የሚፈልገውን መጽናኛ የምትሰጠውን ሌላ ሴት ያገኛል።››
የአቶ ፍሰሀ አይን  ወደ ሚስቱ ዳሌ  ዝቅ አለ፣ …እጁ ሰውነቷን ሲዳብሳት  በድካም ቃተተች።

"እናንተ ወንዶች ! ስለእዛ ጉዳይ ብቻ ነው የምታስቡት? -"ተነጫነጨች "እንዲህ አይነት ቋንቋ አትጠቀሚ። ጭካኔ ነው።››
‹‹ ዛሬ ማታ ይህን ማድረግ አልፈልግም። ራስ ምታቴ እየተመለሰ ነው።››
የእሱ መሳም ተጨማሪ ተቃውሞዎችን አስነሳ. ። እሷ ሁል ጊዜ መቃወሟ የማይቀር ነው፡፡ ግን በጭራሽ አይቀበላትም። ከስሜታዊነት ይልቅ በግዴታ ስሜት ለእሱ ምላሽ መስጠቱ እሷን ከመፈለግ አግዶት አያውቅም። እንደውም በተቃራኒው ፍላጎቱን ከፍ ያደርግለት ይሆናል ። ፈጥኖ ልብሱን አውልቆ አንሶላውን ገልጦ ገባ ፡፡

ሳራ የሌሊት ልብሷን ጫፍ ወደላይ ሲሰበስባ እጁን ያዘችና ከለከለችው፡፡ አቶ ፍሰሀ ወደእሷ ተጠጋና ጉንጯን ሳመ እና አቀፋት። ለስላሳ እና፣ ጥሩ መዓዛ ያለው ቆዳዋን መዳበስ ክፉኛ ፈልጎ ነበር … ከእሷ ግር ፍቅር መስራት አምሮታል፡፡

"ፍሰሀ አሁን ተኛ … ይህን የጀመርኩትን ምዕራፍ መጨረስ እፈልጋለሁ" አለችው።

እንደ ፍቅሯ ደረቅ እና ህይወት የሌለውን ልቦለድዋን እንደገና ከፍታለች። ፍሰሀ ከማንበቢያዋ መብራት ርቆ ወደ ሌላኛው የአልጋው ጠርዝ ተጠጋና ፊቱን አዞሮ ተኛ ፡፡ እንደፍላጎቱ ስላልሆነችለት ተበሳጭቶ ነበር፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍3217
አንቺ ?
አንቺ እንቁጣጣሽ
ምናባሽ ልትሰሪ መጣሽ?


አሁንም ግፍ አይበቃሽም
ዘንድሮም ለምለም ትያለሽ
ካቀፍሽው ቅጠል ባለፈ
የለመለመ ምን አለሽ?

ካቻምናም አምናም መተሻል
አቅፈንሽ አጥነን ደግሰን
አመትሽ ውበቱ ላይቆይ
እያደር ሊያተራምሰን

አንቺ ?
አንቺ እንቁጣጣሽ
ምናባሽ ልትሰሪ መጣሽ?

አምና ተስፋ አስደረግሺኝ
ደክሜ ቤቴን ሰራሁኝ
አልቅሼ ልገባበት ስል
ይፈርሳል ሁሉ ሰማሁኝ
አሁንም ተስፋ አልቆረጥኩም
ቃልሽን ስመላልሰው
አመትህ ተባርኳል ብለሽ
የላክሺኝ እንደ ሞኝ ሰው
ስታገል ከማይሽር ህይወት
መቀመቅ ነፍሴን ሲውጣት
ወደፊት ፈቀቅ እያልኩኝ
ሞት ልቤን እንዳይለውጣት

"አበባ አየሆሽ" አትበዪኝ
አበባ አልቸገረኝም
ዘፈንሽ አንገሽግሾኛል
ጨዋታሽ አይሰማኝም
በያመት ደምቀሽ ስትመጪ
ህፃን ልጅ ለምትመስዪው
ግጥሙን በምነግርሽ ቃል
ስትዘፍኚ አስተካክዪው

"የሀገሬ ልጆች ውጡ በተራ
ቅስም ሰብሬ  ሰው እስክሰራ
እንኳን ሰውና  የለኝም እድል
ሁሌ መጣለው አመት ላጎድል
አመት አጉድዬ ስገባ ቤቴ
ደስታ ይሰማታል የእንጀራ እናቴ"
አደዪ
የሞት ጉዳዪ
"ኡኡ" በዪ

እንደዚህ ብለሽ ዝፈኚ
ግጥሙን አስተካክለሽው
በቃ አንቺም እንዳገሬ ሰው
ጊዜን ነው የተማመንሽው?

"ሆ ብለሽ መጣሽ
ሆ ብለሽ
ሆ ብለሽ መጣሽ
ሆ ብለሽ"

ሆሆሆሆ!

አታፍሪም ደግሞ
ልክ እንደ ንፁህ እንዳልበደለ
ተስፋሽ ምስኪኑን እየገደለ
ከዘመን ዘመን ማትለወጪ
ጉድ ያዘለ አመት አቅፈሽ ምትሰጪ
ሆ ብለሽ መጣሽ?
ሆ ብለሽ ውጪ!

ለተድላ ሳይሆን
ለሞት ዋዜማ ፡ እያስጨፈርሺኝ
በመጣሽ ቁጥር
ሆ የምልልሽ ፡ ሞኝ አደረግሺኝ?

አሁን ንገሪኝ
ስለ አመትሽ
ይብስብኛል ወይስ ድናለው?
ዘፈኑን ተዪ ፡ ያንቺን ስሞታ ለምጄዋለው

ባለእንጀሮችሽ በተራ ገቡ
አዝማች አባትሽ ሌላ አገቡ
እንጨቱን ሰብረሽ ቤት እስክትሰሪ
ለእንጀራ እናትሽ ሳትናገሪ
እድጅ አድረሻል ኮከብ ስትቆጥሪ

እኔ ምስኪኑ

ምን ያገባኛል ስላንቺ ኮከብ
ምን ያገባኛል የእንቅልፍሽ ማጠር
የኔ ችግር ነው ወሰን የሌለው
የኔ ስቃይ ነው  የማይቆጠር

እህት አበባ  ፡ እህት አበባ
እህት አበባ  ስትልሽ ከርማ፤
ጥላሽ ብትሄድም በሀምሌ ጭለማ
እኔ ላይ "አዬዬ".. አትበዪብኝ፡
ለኔ አመቱ ነው  የጨለመብኝ።

ተይ ባለጊዜ..
ተይ እንቁጣጣሽ..
ሀገር ጉድ አቅፈሽ ፥
ሁሌ እየመጣሽ፦

እንኩ አትበዪን፡

ሀዘን ቁስላችን ፡ ድኖ ሳይገግም፤
ካምናው የሚብስ
ሌላ አዲስ አመት ..አንፈልግም!

🔘ሚኪያስ ፈይሳ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😢128👏3
መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም አፄ ኃይለሥላሴ ከዙፋናቸው የወረዱት 48ተኛ ዓመት!

#ጃንሆይ_ያቺን_ሰዓት!
=============================
መስከረም 2, 1967 ዓ.ም የደርግ አባላት 13 ሆነው ወደ ቤተ-መንግሥት ሄዱና ጃንሆይ የአገዛዝ ዘመናቸው ማብቃቱን አረዷቸው፡፡ የደርግ አባላት ቤተ-መንግሥት ደርሰው ንጉሱን አስጠሯቸው፡፡

ንጉሱም በዝግታ ከፎቅ ላይ ወርደው በዙፋናቸው ላይ ሲቀመጡ የደርግ አባላት ደነገጡ፡፡ ሻምበል ደበላ ዲንሳ ደርግ የወሰነውን የውሳኔ ሃሳብ አነበቡ …

"ለሀገርና ለህዝብ ደህንነት ሲባል በዛሬው ዕለት ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ከስልጣን ወርደዋል፤ ለደህንነትዎ ሲባልም አስተባባሪው ኮሚቴ ወዳዘጋጀልዎ ቦታ እንዲሄዱ ተወስኗል …" የሚል ይዘት ያለው ደብዳቤ አነበቡ፡፡

ሻምበል ደበላ ውሳኔውን አንበበው ሲጨርሱ ንባባቸውን ሲጀምሩ የሰጡትን ወታደራዊ ሰላምታ ደገሙ፡፡ ንጉሱም ዝም ብለው ቆዩና መናገር ጀመሩ፡፡

"ያነበባችሁትን ሰምተናል፤ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት ስንሆን ስም ብቻ አይደለም፡፡ ቢሆንም በየጊዜው የሚለዋወጠው ነገር ደግሞ ላገር የሚጠቅም ነገር እስካለበት…

የኢትዮጵያን ታሪክ ጠብቃችሁ ማልማት ከቻላችሁ የእኛ ታሪክ እዚህ ላይ ያበቃል፤ ካልቻላችሁ የእናንተ ታሪክ ያበቃና የእኛ ይቀጥላል ፤ አገራችንንና ሕዝባችንን በምንችለው አገልግለናል ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ እድል የእኛን መወገድ የሚጠይቅ ከሆነ ስራችንን አቁመን ማንኛውንም ነገር ለመቀበል ዝግጁ ነን፤ ‹አሁን ተራው የእኛ ነው› ካላችሁ ኢትዮጵያን ጠብቁ›› በማለት ተናገሩ፡፡

… ከዚያም ንጉሱ ውብ በሆነችው ሮልስ ሮይስ መኪናቸው ሳይሆን ባረጀች ሰማያዊ ቮልስ ዋገን መኪና ተጭነው ወደ አራተኛ ክፍለ ጦር ግቢ ተወሰዱ፡፡
"ወደ ዋገን ወርደው ሲተኩ በሌላ" እንዲል ቴዲ አፍሮ ሰላም ዋሉ!!
12😢6😱2
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
ስርጉት እኩለ ለሊት ቢያልፍም ኪችን ውስጥ ስራ እየሰራች ስለነበር አልተኛችም..ድንገት ግን የውጭ በራፍ ሲንጎጎ ስትሰማ እጇ ላይ የነበረውን የሸክላ ሰሀን ለቀቀችውን ወለል ላይ አርፎ ፍርክስክስ ብሎ ተሰበረባት፡፡የበሩ መንኳኳት እንደቀጠለ ነው..ቶሎ ብላ ኪችኑን ለቃ ወጣችና ወደሳሎን ሄደች ...

" በፈጣሪ ማን ነው ?" ጠየቀች፡፡

"ስርጉት… እኔ ነኝ ..ክፈቺ."

የሰማችውን ድምፅ ልታምን አልቻለችም  ….ለማሰብ ጥቂት ሰከንድ እንኳን ሳታቅማማ
ተንደርድራ ወደበሩ ሄደችና ከፈተችው፡፡

በረንዳው ላይ ተገትሯል…ለደቂቃዎች በራፉን አንደያዘች በትኩረት ተመለከተች፣

‹‹በሰላም ነው ጁኒዬር?››

‹‹ሰላም ነው››መለሰላት፡፡

‹‹ግባ …››አለችና ከበራፉ ዞር አለችለት..ሰተት ብሎ ገባ፡፡

"እዚህ ምን እየሰራህ ነው?"

"አንቺ ጋር መጥቼ ነዋ…ክብር ዳኛ ተኝቶ እንደሚሆን እገምታለው››

"አዎ አባዬ በጊዜ ነው የተኛው።››

የቀድሞ ባለቤቷ በዚህ እኩለ ለሊት እሷን ብሎ የሚመጣበት አንድም አሳማኝ ምክንያት ሊመጣላት አልቻለም፡፡ ቢሆንም ግን….ግድ አልነበራትም። እዚህ መገኘቱ በቂ ነበር። አባቷ ካገመሰው ቦድካ በብርጭቆ ቀዳችና ሰጠችው፡፡ተቀበላትና በቆመበት አንዴ ተጎነጨለት፡፡

"ይህ የሌሊቱ የመጀመሪያ መጠጥህ አይደለም አይደል?"

"አይ..አይደለም." ድምፁን ዝቅ አድርጎ መለሰላት ፡፡

"ወደእኔ እንድትመጣ ለወራት ስጠብቅ ነበር ። ከዚህ ሁሉ ጊዜ በኋላ አሁን ወደእኔ ስትመጣ ደግሞ ለምን የሚል ጥያቄ በአእምሮዬ እየተመላለሰ ነው፡፡››አለችው፡፡

" ፈልጌ ነበር." አላት፡፡

ለጁኒየር አእምሮ ያ በቂ ምክንያት እንደሆነ ታውቃለች። ሶፋው ላይ ተቀመጠና ጎትቶ ከጎኑ አስቀመጣት።ከበርካታ ደቂቃ ፀጥታ በኋላ " በእርባታ ድርጅቱ ውስጥ ስለተፈጠረው ችግር ሰምቻለሁ" አለችው.

"አሁን ሁሉ ነገር ሰላም ሆኗል….እሳቱ በጊዜው ነው የተደረሰበት…በጣም የከፋ ሊሆን ይችል ነበር."

እያመነታች እጇን እጁ ላይ አሳረፈች፡፡
‹‹አንተ ግን ራስህን ጠብቅ…ንብረታችሁን ለማቃጠል የደፈረ ጠላት በእናንተም ላይ ቀጥታ ጥቃት ከመፈፀም ወደኃላ ላይል ይችላል፡፡››

"አሁንም ለደህንነቴ ትጨነቂያለሽ?"

"ሁልጊዜ።"አለችው፡፡

‹‹ሰሎሜ እንዳንቺ ጣፋጭ ሆኖልኝ አታውቅም። ››

"የደከመህ እና የተቸገርክ ትመስላለህ?።"

"አዎ ደክሞኛል!!።"

ሶፋው ላይ ሙሉ በሙሉ ወጣና ትራሱን ተንተርሶ አረፈ። "በሰሎሜ ግድያ ላይ ያለው ውዥንብር እየበጠበጠን ነው።ሁሉም ነገር እንደ ገሃነም ተስፋ አስቆራጭ ነው።››አላት፡፡ከትራሱ ቀና አለና እሷ ትከሻ ላይ ተንተራሰ"እህ…ጥሩ መዓዛ አለሽ…ይህ ሽታ ናፍቆኝ ነበር. በጣም ንጹህ. ነው፡፡

"ስለዚህ ምርመራ በጣም የሚያስጨንቅህ ምንድን ነው?"

"ምንም የተለየ ነገር የለም። አለም ነች ። እሷ እና እናቴ ዛሬ ተፋጠው ነበር። እናቴ ስለሰሎሜ አንዳንድ መጥፎ ነገሮችን ነገረቻትና በጣም እንድታዝን አደረገቻት… ያ ጥሩ ትእይንት አልነበረም።››

ክንዱ በወገቧ ዙሪያ ላከውና አቀፋት ..እጇን አነሳች እና ጭንቅላቱ ላይ አሳርፋ እንደህፃን ልጅ ታሻሸው ጀመር፡፡

"ዋሻተኋታል እንዴ?"

"የማጣት ፍርሀት የወለደው ውሸት"ጁኒየር ፍላጎት በማጣት አጉተመተመ።

"እናቷ በተገደለችበት ቀን በረንዳ ላይ እንደነበርኩ አልነገርኳትም።ለምን እንደዛ አደረክ ?"

" በተከታታይ ጥያቄዎች እንድታጣድፈኝ አልፈለኩም።አንዳንድ መመለስ የማልችላቸውን ጥያቄዎች ብትጠይቀኝ እንዴት አደርጋለው?›››

‹‹ ጁኒየር ዳግመኛ ችግር ስለፈጠረችብህ ጠላኋት።"

"አለም ሁኔታውን ልትረዳ አትችልም….ያም የእሷ ጥፋት አይደለም.››

ጁኒየር ስለ ሶለሜ ብዙ ጊዜ ተመሳሳይ ነገር ተናግሮ ነበር። የቱንም ያህል ብታበሳጨውም ስለእሷ ጠንከር ያለ ቃል ተናግሮ አያውቅም።ስርጉት በሹክሹክታ

‹‹ይህችን የሰሎሜን ልጅ ልክ እንደእናቷ በጣም እጠላታለሁ››ስትል አንሾካሾከች፡፡

"አሁን ስለዛ አታስቢ። ይህ ጥሩ ስሜት እንዲሰማኝ አያደርግም" አላት፡

እጁን አነሳና እርጥበታማ ከንፈሯ ላይ አሳርፉ ዳበሳት …ከለበሰችው ጋወን ያፈነገጡ ጡቶቾን ተመለከተ።እጁን ከከንፈሯ አነሳና ጡቷ ላይ አስቀመጠ…

‹‹እንደዚህ ሳደርግ ሁል ጊዜ ደስ ይልሽ ነበር ።››

"አሁንም አድርገው።››

‹‹እውነት? ››

"ጡቷን ወደ አፉ አቀረበችለት…ጎረሰው…. እጁን በጭኖቿ መካከል ሰነቀረው፡፡እርጥበት ያለውን ፀጉር እየዳበሰ ወደውስጥ መጓዙን ቀጠለ … ስሙን እየጠራች አቃሰተች።

‹‹ካልፈለግሽ ይገባኛል››አላት

"አይ" አለች በፍጥነት "እፈልጋለው እባክህ።›››ተማፀነችው፡፡፡

"ስርጉቴ ያንቺ በርህራሄ የበለጸገ ፍቅራዊ እንክብካቤ ዛሬ ማታ ያስፈልገኛል። ጥሩ ስሜት እንዲሰማኝ ሁልጊዜም በአንቺ ልተማመንብሽ እችላለሁ።››ሲል ተናዘዘላት፡፡

ጎንበስ አለችና ከንፈሩን ሳመችው፡፡

"ሁልጊዜ ጥሩ ስሜት እንዴሰማኝ እንደጣርሽ ነው…አይደል እንዴ?" ብሎ ጠየቃት፡፡

"አዎ ።"አለችና አጎንብሳ ተመለከተችው። ልክ እንደ መልአክ ፈገግ አለላት ። እንደዚያ ሲያያት ምንም ልትከለክለው አቅም አይኖራትም በጭራሽ።
///
"ወ/ሪት አለም…ወ.ሪት አለም?አለሽ እንዴ?››

አለም ድክምክም ብላ ተኝታ ነበር። ጥገና የተደረገላት በሯን በተደጋጋሚ ሲንኳኳ ነው ከእንቅልፎ የነቃችው፡፡ ስትነቃ… ደንዛዛ እና ቀዝቃዛ ነበር።ከመተኟቷ በፊት ለረጅም ሰዓት ከማልቀሷ የተነሳ ዓይኖቿ አብጠው ነበር።

"ምን ፈለክ?" ድምጿ ለጩኸት የቀረበ ነበር።

" ክፈቺልኝ እትዬ…መልዕክት አለሽ?።"
እንደምንም ከአልጋው ወረደችና ጋወኗን ለብሳ ወደሳሎን በመሄድ በራፉን ከፈተች፡፡የተከራየችበት አፓርታማ ዘበኛ ነው

"እትዬ ስልክሽ ከአገልግሎት መስጫ ውጭ ነው ይላል?"

"አዎ…ዝግ ነው….ለምን ፈለከኝ?" ግራ በመጋባት ጠየቀችው፡፡

‹‹እኔ አይደለውም…አቶ ግርማ የሚባሉ ሰውዬ መጥተው ነበር›› ደነገጠች‹‹የት ነው..?አሁን አለ?››

‹‹አይ ሄደዋል …መልዕክት ንገርልኝ ብለዋል….ነገ ጥቃት ዝዋይ ስብሰባ ስላለ እንድትገኚ ብለዋል››

‹‹ዝዋይ..?የምን ስብሰባ?››

‹‹አላውቅም እትዬ …ሰውዬው ናቸው ያሉት››

‹‹ማለት ተሳስተህ እንዳይሆን?››

‹‹አይ  ይሄው  ማስታወሻ  ላይ  አስፍሬዋለው…››ብሎ  በተወለጋገደ  ፅሁፍ  የተፃፈውን ማስታወሻ አሳያት፡፡

‹‹እሺ በቃ አመሰግናው››ብላ ሸኘችውና ወደ መኝታ ቤቷ ተመለሰች፡፡ከዛ ስልኳን ፈለግችና አበራችው…ዋናው አቃቢ ህጉ ጋር ደወለች….ስልኩ አይሰራም፡፡፡ስልኳን አስቀመጠችና ጋወኗን አውልቃ ቢጃማ መልበስ ጀመረች፡፡እንደጨረሰች ከእንደገና ስልኳን አነሳችና ደወለች፡፡

"ፖሊስ መምሪያ ነው…ምን እንርዳዎት?."

"እባክህ ኩማንደር ገመዶን ፈልጌ ነበር፡፡"

"እሱ የለም። ሌላ የሚረዳሽ ሰው ጋር እናገናኝሽ?"

"አይ፣ አመሰግናለሁ፣ በቀጥታ ከእሱ ጋር መነጋገር አለብኝ…ምክትል አቃቢ ህግ አለም ጎበና ነኝ።"

‹‹ክብርት አቃቢ ህግ እንዴት ነሽ….አሁን የት ነሽ?፧"

"እቤቴ ነኝ …ለምን ጠየቅከኝ?"

"ኩማንደር ወደአንቺ እየመጣ ነው….እስከአሁን ይደርሳል››

‹‹ምነው በሰላም…..?››መልሱን ሳይመልስላት በራፏ ሲንኳኳ ሰማች‹‹ እሺ …በል ደህና ሁን…ደርሶል መሰለኝ ››አለችና ስልኩን በመዝጋት ወደሳሎን ሄዳ በራፉን ከፈተችለት፡፡

‹‹እሺ ኩማንደር ?››

‹‹ዞር በይልኝ እንጂ ልግባ።››

‹‹መግባትህ አስፈላጊ ነው?››እያለች በራፉን ለቀቀችለት፡፡
83👍15
አትሮኖስ pinned «#ቋጠሮ_ሲፈታ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አራት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ /// ስርጉት እኩለ ለሊት ቢያልፍም ኪችን ውስጥ ስራ እየሰራች ስለነበር አልተኛችም..ድንገት ግን የውጭ በራፍ ሲንጎጎ ስትሰማ እጇ ላይ የነበረውን የሸክላ ሰሀን ለቀቀችውን ወለል ላይ አርፎ ፍርክስክስ ብሎ ተሰበረባት፡፡የበሩ መንኳኳት እንደቀጠለ ነው..ቶሎ ብላ ኪችኑን ለቃ ወጣችና ወደሳሎን ሄደች ... " በፈጣሪ ማን ነው ?"…»
#ሲያጋጥም

ልቤ በግኖ ነዶ ራሴን በፎከትኩት
ሌላኛ ጠላቴን ቅማሌን ገደልኩት፡፡


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😁8👍3😢1
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ከሰፍል_ሀያ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
የዝዋዩን ስብሰባ ተሳትፈው በተመለሱ በማግስት ዋና አቃቢ ህጉና አለም በቢሮቸው ፊት ለፊት ተፋጠው ተቀምጠዋል፡፡

እሱ እጁ ላይ አንድ ደብዳቤ በትኩረት እየተመለከተ ትካዜ ውስጥ ገብቷል …

‹‹ክብሩ አቃቢ ህግ…ምነው ችግር አለ እንዴ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ወደስራ ስትመጪ ከተማው ውስጥ የታዘብሽው ነገር የለም?››

‹‹ምንን በተመለከተ…?››

‹‹የምታሳድጃቸውን ሰዎች በተመለከተ፡፡››
‹‹እ..የጁኒዬር ፍሰሀ ምስል የያዘ የምርጫ ቅስቀሳ ፖስተር ከተማውን ሞልቶታል፡፡ገዢውን ፓርቲ ወክሎ ለተወካዬች ምክር ቤት መወዳደሩ እርግጥ ሆኗል….ያንን ነው የታዘብኩት›››

‹‹አዎ…የዚህ ትርጉም ገብቶሻል ብዬ አስባለው….ጠላቶችሽ ከቀን ወደቀን የማይነኩ አይነት ኃያል እየሆኑ ነው፡፡››

"ምንም ሆነ ምንም …እኔ የጀመርኩትን ወደፊት ከመቀጠል አያስቆመኝም››
‹‹አይ የግድ ለማቆም ትገደጂያለሽ…..››

‹‹ለምን ተብሎ››

እጁ ላይ ያለውን ደብዳቤ ወረወረላት፤ግራ ከመጋባት ውስጥ ሳትወጣ ተቀበችውና አነበበች..ማመን ነው ያቃታት….ከመቀመጫዋ ተነሳች…ተወራጨች…

‹‹ምንድነው ይሄ…››

‹‹ታላቅ እድል ነው….እንደኦሮሚያ ይህንን እድል ካገኙ ሁለት የህግ ባለሞያዎች መከካል አንዷ አንቺ ነሽ…ቀጣዩን ስድስት ወር ቻይና ሄደሽ ይህንን ስልጠና ትወስጂያለሽ…ከዛ ስትመለሺ እርግጠኛ ነኝ….ወይ እዛው ክልል ዋናው ቢሮ ካለበለዚያም ሌላ ዞን በዋና አቃቢ ህግነት ትመደቢያለሽ››

‹‹እኔ መች ፈለኩና…?በምን መስፈርት ነው እኔ የተመረጥኩት….?››

‹‹እሱን እኔ አላውቅም..››

‹‹አወቅክም አላወቅክም ..ይህ እኔን ከእዚህ ገለል ለማድረግ የተሸረበ ሴራ ነው..ለስድስት ወር ከሀገር ወጣሁ ማለት… እስከዛ ጁኒዬር ምርጫውን አሸንፎ ምክርቤት ይገባል…ስመለስም ወደእዚህ ከተማ ስለማይልኩኝ የእናቴ ገዳይ ነፃ እንደሆነ ይቀጥላል ማለት ነው…ይህን መቀበል አልችልም፡፡››

‹‹መቀበልማ የግድ ነው….በዚህ ስራ ላይ ለመቆየት ያለሽ እድል ከ15ቀን አይበልጥም……እሱም ምን አልባት ነው፡፡ደብዳቤውን አንብበሻል አይደል?ይሄ ደብዳቤ ከደረሰት ቀን አንስቶ እጇት ላይ ያለውን ስራና የመንግስት ንብረት ለተተኪው ሰው አስረክበው ለጉዞው ይዘጋጁ ነው የሚለው፡፡››

በንዴት ተንዘረዘረች‹‹አየህ የሰዎቹን ተንኮል….ይህንን ያቀናጁት አቶ ፍሰሀ እና ገመዶ እናም ዳኛው እንደሆኑ እርግጠኛ ነኝ…በዘዴ እኔን ለማስወገድ የሄዱበትን ርቀት የማይታመን ነው››

‹‹አይ የእነሱ እጅ የለበትም ብዬ ልከራከርሽ አልፈልግም….እንደውም ሁኔታውን በደንብ አንድትረጂ ነው የምፈልገው…የሰዎች አቅምና ኃይል ክልል እና ፌዴራል ድረስ ምን ያህል የተዘረጋ እና ስር የሰደደ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡አንቺ በማትጎጂበት መንገድ ከጀመርሽው መንገድ ዞር ለማድረግ የቀየሱት ጥበብ የተሞላበት ዘዴ ነው፡፡ያ ማለት እኔ እፈራው እንደነበር ቀጥታ አንቺ ላይ ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት ሊያደርሱብሽ ፍላጎቱም ሆነ እቅዱ የላቸውም ማለት ነው….ይሄንን በማወቄ አፎይታ ተሰምቶኛል፡፡››

"አንተም እንድሄድ ነው የምትፈልገው?"

"አዎ፣ ሳስበው ለአንቺም የሚበጅሽ እንደዛ ማድረጉ ነው።" በለሆሳስ መለሰላት፡፡
ዋና አቃቢ ህጉ ለእሷ ከአለቃ ይልቅ እንደ ጓደኛ ነው። ስለዚህ እሷ ደህነንት ያሳስበዋል፡፡ " እንደምንም አንድ ወር በስራዬ ላይ እንድቆይ አድርግ"ተማፀነችው፡፡

" እንደዛማድረግ አልችልም.. አልፈልግም."
‹‹እባክህ››

"አንድ ሳምንት አለሽ…ልክ የዛሬ ሳምንት የቢሮሽን ቁልፍ አስረክበሽ ወደ አዲስ አበባሽ ጉዞ ትጀምሪያለሽ።"

" አታስበው…የመጣሁበትን ከግብ ሳላደርስ ከዚህች ከተማ ንቅንቅ አልልም››

‹‹እንዳዛ ከሆነ ስራሽን ታጪያለሽ››

‹‹ስራውን በስራነቱ እንደማልፈልገው ታውቃለህ….የእናቴን ገዳይ እንዳገኝ ካረዳኝ ስራው ምን ያደርግልኛል?››

‹‹የውጭ እድሉም ይቃጥልብሻል››

‹‹አልፈልገውም …ለሌላ ሰው ስጡት፡፡››

‹‹ይሄንን ስራ ከለቀቅሽ…በራስሽ ብቻሽን ነው የምትቆሚው…የቢሮው እገዛና ጥበቃ አይኖርሽም::እንደአንድ ተራ ግለሰብ እነሱን መጋፈጥ እትችይም….››

‹‹ያንን ስሞክር ነው የማውቀው››

"በእግዚያብሄር ስም …ምን አይነት ግትር ሴት ነሽ?"

‹‹ይህ ግትርነት አይደለም…እዚ ከተማ ስመጣ አሁን እናቴን ገድለዋት ይሆናሉ ብዬ የምጠረጥራቸው ሶስት ሰዎች ነበሩ ..ወደዚህ መጥቼ ምርመራዬን ከጀመርኩ በኃላ ተጠርጣሪዎች ወደአምስት አድገዋል፡፡››

‹‹ጭራሽ ተጠርጣሪዎችሽን ቁጥር እያጠበብሽ መሄድ ሲገባሽ እያንዛዛሽው መጣሽ ማለት ነው…ለመሆኑ እነማን ናቸው የተካተቱበት?››

‹‹የአቶ ፍሰሀ ባለቤት ሳራ እና የጁኒዬር የቀድሞ ባለቤት ስርጉት››

ሲጋራውን ከፓኮው አወጣና ለኮሰ ፣ አንዴ ማገና ጭሱን በአየሩ ላይ በተነው ‹‹እንሱ ደግሞ ለምን ብለው ነው እናትሽን የሚገድሏት?››ሲል ከመገረም ውስጥ ሳይወጣ ጠየቃት፡፡

እንደውም ከወንዶቹ በተሻለ እናቴን ለመግደል በቂ ምክንያት እና ጥላቻ ያላቸው ሴቶቹ ናቸው፡፡ወ.ሮ ሳራ ልጇ ጁኒዬር እናቴን እዳያገባ ስትጥር ነበር ቆየችው....በዚህ ጉዳይ ከአያቴ ጋር ሁሉ እንተጨቃጨቁ በገዛ አንደበቷ ነው የነገረቺኝ፡፡በእሷ እምነት እናቴ በሁሉም መስፈርት ለአንድዬና ብቸኛ ልጇ ሚስት ለመሆን እንደማትመጥን ነው የምታስበው፡፡እና ልጇም ተመሳሳዪን እንዲያስብ ብዙ ጊዜ ሞክራ እንዳልተሳካላት ነግራኛለች..ይታይህ ታዲያ ድንገት እኔን ወልዳ አራስ የሆነችውን እናቴን ሊያገባ እየተዘጋጀ ነው ብለው ሲነግሯት እሷን አስወግዳ ልጇን ነፃ ለማውጣት ብትሞክር ምን ይገርማል…?በሌላ በኩል የዳኛው ልጅ የሆነችው ስርጉት ደግሞ ጁኒዬርን ለአመታት ስታፈቅረው እና የራሷ እንዲሆን ስትመኘው የነበረ ሰው ነው….እሱን የራሷ እንዳታደርገው እንቅፋት የሆነቻት እናቴ ነች..ይባስ ብሎ ከአንድ ዲቃላ ልጇ ጋር ሊያገባት እንደሆነ ስትሰማ ምንድነው የሚሰማት….?ደግሞ እናቴን እንዴት አምርራ ትጠላት እንደነበረና መሞቷን እንደግልግል እንደወሰደችው እዛ ድግስ ላይ
የተገናኘን ቀን ምንም ሳትደብቅ ነግራኛለች፡፡እና በአጠቃላይ ከእናቴ ሞት ይበልጥ ተጠቃሚ የሆነው ማን ነው? ብለን ሰንጠይቅ ለጊዜው ሁለቱ ሴቶች የሚል መልስ ነው ምናገኘው…ሳራም ልጇ የማትፈልጋትን ሴት ከማግባት ተገላገለ..ስርጉትም እናቴ ሞታ ብዙም ሳይቆይ ለአመታት ስታፈቅረው የነበረውን ሰው አሳምና ማግባት ቻለች….ምንም እንኳን ጋብቻው ረጅም እድሜ መቆየት ባይችልም ለጊዜው ግን ተጠቃሚ ነበረች፡፡››
በጥሞና ሲያዳምጣት የቆየው አቃቢ ህግ ጭንቅላቱን እየነቀነቀ‹‹ጥሩ መላ ምት ነው››አላት
፡፡
"በዚህ ጉዳይ እኔን የገረመኝን አንድ ነገር ታውቃለህ? ዳኛው። የእናቴን ግድያ በተመለከተ ተጠርጣሪዎች በጠቅላላ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ከእሱ ጋር ትስስር ያላቸው ናቸው..ታዲያ እንዴት አድርጎ ነው ትክክለኛውን ፍርድ ሊፈርድ የሚችለው?።"

በማግስቱ የአለም የመጀመሪ ስራ የዋና አቃቢ ህጉን ቢሮ ማንኳኳት ነበር፡፡ ባልተሟሸ የጥዋት ሻካራ ድምፅ፡፡‹‹ይግቡ››አላት፡፡
በራፉን ገፋ አድርጋ ገባች

‹‹የመጀመሪያ ባለጉዳይ አንቺ ትሆኜያለሽ ብዬ አልጠበቅኩም ነበር››
ለቀልዱ ምንም መልስ ለመስጠት ፍላጎት አልነበራትም…ጠረጴዛውን ተጠጋች እና ከቦርሰዋ ውስጥ አንድ ወረቀት አውጥታ ፊቱ አስቀመጠችለት፡፡ጠቅላላ አቃቢ ህጉ በሁኔታዋ ግራ ተጋብቶ‹‹ምንድነው?›› ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ስራ መልቀቂያ ነው››

‹‹ማለት ?አልገባኝም››
44👍6👎1👏1
‹‹ማለትማ ፣ስራችሁን አልፈልግም፡፡››

‹‹እስቲ ቁጭ በይ›› ቁጭ አለች፡፡

‹‹ምን እያደረግሽ ነው…?ስራውን ለቀሽስ…?››

‹‹እነሱ ማንኛውንም ዘዴ ተጠቅመው እኔን ሊያስወግዱኝ ነው አይደለ እየሞከሩ ያሉት?..እኔም ስራዬን ለቅቄ በነፃነት በማንኛውም ነገር እፋለማቸዋለው››

‹‹በማንኛውም ነገር ማለት?››

‹‹በማንኛውም ነገር ማለትማ በማንኛውም ነገር ነው››

‹‹እኔ እንደታናሽ እህቴ ነው የማይሽ…ስትጎጂ ማየት አልፈልግም…እነሱን በወንጀለኝነት ሚያስጠይቅ ምንም አይነት ተጨባጭ ማስረጃ አታገኚም…ብታገኚ እንኳን ፍርድ ቤት አቅርበሽ ፍትህ ከማስገኘትሽ በፊት መረጃውን በሆነ መንገድ ያጠፉታል!!››

‹‹አይ አሁን እነሱን ለፍትህ ማቅረብ አይደለም የምፈልገው….መበቀል ነው…እኔን ለማስወገድ እንደሞከሩት እኔም አስወግዳቸዋለው…..ስማቸውንም፤ሀብታቸውንም ኃይላቸውንም እንዲያጡ ነው የማደርገው፡፡

‹‹እንዴት አድርገሽ?››

‹‹ዝርዝሩን አልነግርህም››

‹‹ምነው እኔንም ከእነሱ እንደአንዱ አድርገሽ እያየሺኝ ነው እንዴ?››

‹‹አይ እንደዛ አላልኩም..ግን ለጊዜው እቅዴን ለማንም የመናገር ፍላጎት የለኝም››

‹‹ጥሩ …ግን ሌላ እርምጃ እንዲወስዱብሽና እንደእናትሽ አንዲያጠፉሽ ምክንያት አትስጪያቸው››

‹‹ለማንኛውም ለምክርህ አመሰግናለው…..ቢሮዬ ገብቼ የግል እቃዎቼን ልሰብስብ››

‹‹አረ እስኪ ተረጋጊ…መልቀቂያሽን እኮ ገና አልተቀበልኩም››

‹‹‹ተቀበልክም አልተቀበልክም…ሀሳቤን አታስቀይረኝም….ምን አልባት ካላሰርከኝ በስተቀር
›› አፉን እንደከፈተ  ቢሮውን ለቃ ወጣች፡፡
///
አለም ድንገት ነው የገመዶ ቤት የተገኘችው፡፡እየመጣሁ ነው ብላ ስትደውልለት በረንዳ ላይ ቁጭ ብሎ ነበር የጠበቃት፤፡፡መቆጣቷን እና ማኩረፏን ለማወቅ የእሷን ገፅታ ማየት አላስፈለገውም። እሷ ፍጹም ኩስትርትር ብላ ከረሜላ የከለከሏት ህፃን መስላለች ፡፡ ፊት ለፊቱ ኩርሲ አስቀመጠና እንድትቀመጥ ጋበዛት ፡፡እየጠለቀች ያለችው ጀንበር የምትረጨው ጨረር በፀጉሯ ላይ አርፎ የሚያበራ ደማቅ ነበልባል ፈንጥቆ ይታያል ።
"ዛሬ ጥዋት ስራ ገብተሸ ወዲያው እንደወጣሽና …ተመልሰሽ እንዳልገባሽ ነገሩኝ … ምን ሆና ይሆን ብዬ እያሰብኩ ነበር፡፡በሰላም ነው ?››አላት፡፡

"አንተ ውሸታም ፣ አታላይ ፣ ምናልባትም ነፍሰ ገዳይ ነህ።"

"ከመጀመሪያው ጀምሮ በእኔ ላይ ያለሽ አስተያየት ይህ ነበር…. የማላውቀውን አንድ አዲስ ነገር ንገሪኝ.››

ቆይ የሶሌ ኢንተርፕርይዝ 30 ፐርሰንት ድርሻ ያንተ እንደሆነ ለምን ሳትነግረኝ?››
ያልጠበቀው  ወቀሳ  ነው  የገጠመው"  ለምን  ብዬ  ነግርሻለሁ…..አግብቼሽ  ንብረት ሳልቆጥርልሽ ያታለልኩሽ እኮ ነው ያስመሰልሽው?።"

‹‹ነገሩን አታደባብሰው…እዛ እንስሳት እራባታ ውስጥ ጥቂት ፈረሶች እንዳሉህ  አይነት እድርገህ ነበር የነገርከኝ….ግን አንተ የጠገበ ሚሊዬነር ነህ፡፡››

‹‹እና ምነው ?ከፋሽ?››

‹‹ደሞዝህ 15 ሺ ብር አይሞላም…ይሄንን ሁሉ ብር ከየት አገኘህ?››

‹‹እንዴ ምርመራሽን ከግድያ ወንጀል ወደሙስና ልታዞሪው አሰብሽ እንዴ?…በንግድ ስራዬ ውስጥ ጣልቃ ለመግባት ምንም መብት የለሽም። ይህ ከአንቺ የግድያ ጉዳይ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም።"

"ይህን ምርመራ ወደ ውጤት ያደርሰኛል ብዬ ባመንኩበት ባሻኝ መንገድ የማስኬድ ሙሉ መብት አለኝ."

‹‹ወደሌሎች ነገሮች ጠልቀሽ ለመግባት በሞከርሽ መጠን የበለጠ ወደአደጋ እየቀረብሽ መሆኑን ልንግርሽ እፈልጋለው፡፡››

‹‹በዚህ መልኩ ስታስፈራራኝ ይሄ የመጀመሪያ ቀንህ አይደለም…ይህን ምርመራ እንዳይሳካልኝ በየደረጃው እንቅፋት ስታስቀምጥብኝ ነበር። ባጅህን ተጠቅመህ ገዳዩን ማንም ይሁን ማን እንዳላገኘው እየተከላከልክ ነው… ምክንያቱም የትኛውም የእናንተ ክበብ ውስጥ ባለ ሰው ላይ ክስ ቢመሰረት የሶሌን ኢንተርፕራይዝ የአክሲዬን ድርሻ ሆነ የገበያ ተቀባይነት ገደል ይገባል፡፡

‹‹እንዴት ማለት?፡፡››

‹‹የሶሌ ኢንተርፕራይዝ 10 ፐርሰንቱ የስርጉት ድርሻ ነው….ጁኒዬር የ15 ፐርሰንት አለው፣ እናቱ ሳራ 10 ፐርሰንት አላት…አቶ ፍሰሀ 35 ፐርሰንት ሲኖረው አንተ ደግሞ 30 ፐርሰንት አለህ፡፡››
ውስጡ በንዴት ሲንቀለቀል ታወቀው….ግን እንዲህ ተበሳጭቶባት እንኳን ዘለህ እነቃት የሚል ስሜት ሳይሆን እየተናነቀው ያለው ዘለህ ከንፈሯ ላይ ተጣበቅ የሚል ስሜት ነው፡፡ ግን እንደምንም እራሱን ተቆጣጥሮ
‹‹ለመሆኑ ይሄንን መረጃ ከየት አገኘሽው?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ዋናው መረጃው ትክክል መሆኑ ነው ፡፡ምንጮቼንማ ለምን ብዬ አጋልጬ እሰጣለው፡፡››

‹‹ይሄ እኮ ምንም ሚስጥር የለውም…››

ከት ብላ ሳቀች…….

‹‹ምን ያስቅሻል?››

‹‹አለው እንጂ….ተመልከት….በምንም አይነት ስሌት አንተ እና ስርጉት የዚህ ኢንተርፕራይዝ የአክሲዬን ድርሻ ባለቤቶች ትሆናላችሁ ብዬ አስቤ አላውቅም..እርግጥ አንተ ከቤተሰቡ ጋር ባለህ ቤተሰባዊ ግንኙነት አንዳንድ ነገሮችን እየሰራህ ጠቀም ያለ ገንዘብ እንደምትቀበላቸው ግምቱ ነበረኝ…..ግን ተመልከት ከአቶ ፍሰሀ ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቁ
አክሲዬን የማን ነው…?ያንተ፡፡ 30 ፐርሰንት…. ከልጁ ጁኒዬር በእጥፍ የሚበልጥ የአክሲዬን ድርሻ አለህ››

‹‹ምኑ ይገርማል….ጁኒዬር እኮ እድሜ ልኩን በየመዝናኛ ቦታው እየትሽከረከረ ሲዝናና እና ከሴቶች ጋር አለሙን ሲቀጭ የኖረ ሰው ነው….እኔ ደግሞ ድህነት ስፀየፍ የኖርኩና ያንንም ለማሸነፍ ቀን ከሌት የምለፋና የምጥር ሰው ነኝ…..የእኔ ከእሱ እጥፍ የአክሲዬን ባለድርሻ መሆኔን ነው የሚገርምሽ? በአባቱ ባይሆን አይደለም 15 ፐርሰንት አንድ ፐርሰንትም አይኖረውም ነበር››፡፡

‹‹እሺ ስርጉትስ?››

‹‹ስርጉት ምን ሆነች?››

‹‹ድርሻው በእሷ ስም ይሁን እንጂ ንብረትነቱ የዳኛው ነው አይደል?››

‹‹ያምሻል እንዴ…የራሷ ነው…የጁኒዬር ሚስት እኮ ነበረች፡፡››

‹‹አይ የአክሲዬን ባለድርሻ የሆነችው አናቴ በሞተች ከ15ተኛ ቀን በኋላ ሲሆን ሁለት ወር ቆይቶ ደግሞ ጁኒየርን አገባች፡፡››

‹‹እሱን አላውቅም››

‹‹አይ በደንብ ታውቃለህ….ከማግባቱ ከወር ከአስራአምስት ቀን በፊት የመቶ ሚሊዬን ብር ዋጋ ያለው የአክሲዬን ድረሻ በጥሎሽ መልክ የሚሰጥ ሰው በምድር ላይ የለም፡፡››

‹‹እንግዲህ ስለዚህ ጉዳይ እራሳቸውን ጠይቂያቸው››

‹‹ጠይቃቸዋለው….በደንብ ነው የምጠይቃቸው….እሺ አንተስ?››

‹‹እኔስ ምን?፡፡››

‹‹እናቴ ከመሞቷ በፊት ድርጅቱ ውስጥ ያለህ ድርሻ 10 ፐርሰንት ነበር…ግን ልክ እንደስርጉት ሁሉ እናቴ ከሞተች ከ15 ቀን በኃላ 20ፐርሰንት ተጨምሮ ከአቶ ፍሰሀ ቀጥሎ የድርጅቱን ትልቅ ድርሻ ባለቤት ሆንክ፡፡››

‹‹እና ?››

‹‹እናማ ሁሉ ነገር ግልፅ ምስል እየሰጠኝ ነው…ከእናቴ ሞት ማግስት ለሞቷ ምክንያት ናቸው ብዬ የምጠረጥራቸው ሰዎች ሁሉ በህይወት ውስጥ ከፍተኛ ትርምስ ተከስቷል….ግማሹ ከስሯል ግማሾቻችሁ ደግሞ በልፅጋችሃኃላ…….በእናቴ ሞት ሰበብ የሚፍልገውን ያገኘ አለ…ያለውንም ያጣም አለ….እና ምንድነው ሚስጥሩ?››

በሚሰረስሩ ደማቅ ጥቋቁር አይኖቹ ትኩር ብሎ አፈጠጠባት፡፡እይታው ውስጧን አሸበራት፡፡ጡቶቿ ከሹራብዋ ስር ሲንቀጠቀጡ ተሰማት…. ባልተስተካከለ የተቆራረጠ ትንፋሽ‹‹ከመካከላችሁ ማን ነው የገደላት?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አላውቅም››
38👍6