መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም አፄ ኃይለሥላሴ ከዙፋናቸው የወረዱት 48ተኛ ዓመት!
#ጃንሆይ_ያቺን_ሰዓት!
=============================
መስከረም 2, 1967 ዓ.ም የደርግ አባላት 13 ሆነው ወደ ቤተ-መንግሥት ሄዱና ጃንሆይ የአገዛዝ ዘመናቸው ማብቃቱን አረዷቸው፡፡ የደርግ አባላት ቤተ-መንግሥት ደርሰው ንጉሱን አስጠሯቸው፡፡
ንጉሱም በዝግታ ከፎቅ ላይ ወርደው በዙፋናቸው ላይ ሲቀመጡ የደርግ አባላት ደነገጡ፡፡ ሻምበል ደበላ ዲንሳ ደርግ የወሰነውን የውሳኔ ሃሳብ አነበቡ …
"ለሀገርና ለህዝብ ደህንነት ሲባል በዛሬው ዕለት ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ከስልጣን ወርደዋል፤ ለደህንነትዎ ሲባልም አስተባባሪው ኮሚቴ ወዳዘጋጀልዎ ቦታ እንዲሄዱ ተወስኗል …" የሚል ይዘት ያለው ደብዳቤ አነበቡ፡፡
ሻምበል ደበላ ውሳኔውን አንበበው ሲጨርሱ ንባባቸውን ሲጀምሩ የሰጡትን ወታደራዊ ሰላምታ ደገሙ፡፡ ንጉሱም ዝም ብለው ቆዩና መናገር ጀመሩ፡፡
"ያነበባችሁትን ሰምተናል፤ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት ስንሆን ስም ብቻ አይደለም፡፡ ቢሆንም በየጊዜው የሚለዋወጠው ነገር ደግሞ ላገር የሚጠቅም ነገር እስካለበት…
የኢትዮጵያን ታሪክ ጠብቃችሁ ማልማት ከቻላችሁ የእኛ ታሪክ እዚህ ላይ ያበቃል፤ ካልቻላችሁ የእናንተ ታሪክ ያበቃና የእኛ ይቀጥላል ፤ አገራችንንና ሕዝባችንን በምንችለው አገልግለናል ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ እድል የእኛን መወገድ የሚጠይቅ ከሆነ ስራችንን አቁመን ማንኛውንም ነገር ለመቀበል ዝግጁ ነን፤ ‹አሁን ተራው የእኛ ነው› ካላችሁ ኢትዮጵያን ጠብቁ›› በማለት ተናገሩ፡፡
… ከዚያም ንጉሱ ውብ በሆነችው ሮልስ ሮይስ መኪናቸው ሳይሆን ባረጀች ሰማያዊ ቮልስ ዋገን መኪና ተጭነው ወደ አራተኛ ክፍለ ጦር ግቢ ተወሰዱ፡፡
"ወደ ዋገን ወርደው ሲተኩ በሌላ" እንዲል ቴዲ አፍሮ ሰላም ዋሉ!!

❤12😢6😱2