አትሮኖስ
286K subscribers
117 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አትሮኖስ pinned «#ቋጠሮ_ሲፈታ ፡ ፡ #ክፍል_ሶስት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ /// በፍርድ ቤቱ የስብሰባ ክፍል ውስጥ የነበረው ትእይንት መቀበል ከምትፈልገው በላይ አንቀጥቅጧታል።ግን ደግሞ ጭንቅላቷን ወደ ላይ ቀና አድርጋ እና ደረቷን ነፍታ ነበር ቢሮውን ለቃ የወጣችው ።እራሷን ለመቆጣጠርና የድንጋጤዋንና የፍራቻዋን ቅንጣት እንኳን ለእነሱ ሳታሳይ ስብሳባውን በድል ለማገባደድ ያደረገችው ጥረት የመታፈን አይነት…»
ጥላና የሰው ልጅ ይመሳሰላሉ
አለውልህ ብለው ሲመሽ ይጠፋሉ
ጨለማ ሲወርስህ ብርሀንህ ሲጠፋ
ቅን እኮ ነው ያልከው ታያለህ ሲ'ከፋ

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍63
#ልብ_አልባው_ገጣሚ

ሰው በሞተ ቁጥር
መግደል መሸነፍ ነው የሚል ከንቱ ተረት
ሟቹን ላያነሳ
ገዳይ ላይሸነፍ
መልመድ ካስተማረን እየወጡ መቅረት

ይቅርብን ስብከቱ
የቃሬዛ ሲሳይ መሆን ይታክታል
በማይሸነፉ
ስሜት አልባ ልቦች እልፍ ሰው ይሞታል።

እናም ለገዳዩ
የሽንፈትን ፅዋ ገሎ ለማይቀምሰው
በሟቹ ልትቆምር
በማይረባ ስብከት ድፍረት አታውርሰው
በቅቶናል አንተ ሰው።

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍91
#የትል_ትዕግስት

እኔ ደቂቅ ፍጡር
በደረት ተሳቢ አካሄዴ ሁሉ የተንቀረፈፈ፤
ቅዱስ ያሬድ ብልጡ
ውድቀቴን በሙሉ
በአንክሮ አይቶ ተምሮ አተረፈ፤
በትንሽነቴ ንቆኝ አላለፈ!

በዚች እሽክርክሮሽ
ተመልከት ያሬድን
ከትል አስተሳሰብ ትዕግስትን ይወርሳል፤
በውጤቱ ማምሻ
በጥዑመ ዜማ ፈጣሪ ይወደሳል!

ተመልከታት ትሏን
የትዕግስቷ ልኬት በታሪክ ይወሳል፤
ቅዱስ ያሬድ ሲባል
የቅጠል ትል ታሪክ መች በዋዛ ይረሳል፤
ጌታ አስተምሮቱ በትልም ይገዝፋል!

ተመልከት እራስክን
ተስፋ ቤትህ ወድቆ
ትዕግስት በማጣትህ እምነትህ ይፈርሳል፤
በውድቀትህ ማግስት
ነክሽ ነካ እያለ ሰይጣን ይደግሳል!

               
🔘አብርሃም ፍቅሬ🔘
                     

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
7👍2
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

/////

አለም ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባቷ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ  አያቷ የህግ ሙያ እንድታጠና አጥብቃ ትገፋፋት ነበር..በወቅቱ ምክንያቱ አይገባትም ነበር…እንዲሁ ሰዎች.. የልጅ ልጅሽ ጠበቃ ነች ወይም ዳኛ ነች እንዲሏት ካላት ምኞት ተነስታ የምትገፋፋት ይመስላት ነበር..አሁን ነው ነገሮችን ስታገጣጥም ምክንያቱ ፍንትው ብሎ የተገለፀላት፡፡

አለም በትምህርት ቤት ጎበዝ ተማሪ ነበረች እና በመጨረሻ አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍልም ወርቅ ሜዳሊያ አጥልቃ ነበር የተመርቀችው። የህግ ትምህርት አያቷ የመረጠችለት እና በእሷ ዘንድ በልጅነቷ ያላገኘችውን ሞገስ ለማግኘት ስትል የገባችበት ሙያ ነበር፣ ግን ከተማረችው በኋላ አያቷን ደጋግማ አመሰግናታለች… ምክንያቱም በጣም የሳባት እና ያስደሰታት መስክ ነው። የማወቅ ጉጉት ያለው አእምሮዋ ወደ ውስጡ የህግ ዕውቀቷቹን መጦ ሲያስገባ በደስታ ነው፡፡ ወደስራም ስትሰማራ በሙሉ የራስ መተማመንና በከፍተኛ የስራ ንቃት ነበር፡፡

አቃቢ ህጉ የእጅ ሰዓቱን ተመለከተ.. ከዚያም ሲጋራውን በከንፈሮቹ መካከል አስገብቶ ቆመና ኮቱን ከመስቀያው አነሳ "ያለ በቂ ማስረጃ የግድያ ክስ እንደገና መክፈት አልችልም። ታውቂለሽ። ከሀያአምስት አመት በፊት ተፈፅሞ የነበረ ወንጀልን ወደኋላ ተጉዞ መረጃ ማሰባሰብ ብራንድ ልብሶችን ለብሶ በመዘነጥ የአዳም ዘርን እንደማማለል ቀላል ስራ አይደለም…..እና መጀመሪያ እኔን አሳምኚኝ..ምን አልባት ከዛ በኋላ ስለክሱ ሁኔታ መልሰን እንንጋገርበት ይሆናል››
ልቅ የሆነ ንግግሩን ችላ ብላ በብስጭት ተመለከተችው፡አጠያየቋ በጣም ድፋረት የታከለበትና እና ቅንነት የጎደለው መሆኑን ታውቃለች።እሷ በእሱ ቦታ ብትሆን ከረጂም ደቂቃ በፊት ክፍሉን ለቃ ትወጣ ነበር፡፡

"አየሽ አለም፣ ይህ የምትጠይቀኝ ጉዳይ እንደምትይው ቀላል አይደለም…እነዚህ ሰዎች በደቂቃ ውስጥ ይህንን ቢሮ ወደ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ መቀየር የሚችሉ ናቸው። አንገቴን ልታስቀነጥሺኝ ካልፈለግሽ በስተቀር ይሄንን የአያትሽን ከንቱ ጥርጣሬ መልሰሽ ታነሺብኛለሽ ብዬ አልጠብቅም››ብሎ መንገዱን ቀጠለ፡፡ወደ ቢሮው ደጃፍ ሲያመራ ተከተለችው

"ክቡር አቃቢ ህግ ይሄ ለእኔ ጥልቅ ትርጉም ያለው ጉዳይ ነው። እንዴት እምቢ ትለኛለህ..የምታስበው ስለራስህ ብቻ ነው?።"

"እውነትሽን ነው እኔ እራስ ወዳድ ነኝ።
"ሲል መለሠላት።

"በሌሎች ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረጌን እንዳለ ሆኖ ይህን ግድያ እንዳጣራ ፍቃድ ስጠኝ።"ሙጭጭ አለችበት፡፡

"እኛ ምን አይነት ውዝግብ እንዳለብን ታውቂያለሽ? መአት አንገብጋቢ ጉዳዮች እጃችን ላይ አሉ ፤ሀያ ምናምን አመት የተረሳ...መዝገብ እራሱ በአቧራ የተበላ ጉዳይን በቀላሉ ለፍርድ ማቅረብ አንችልም።"

"እሺ በትርፍ ሰዓቴ እሰራለሁ፣ ሌሎች ኃላፊነቶቼ ላይ በምንም አይነት ተፅዕኖ እንዲያሳድር እላደርግም፣ለዛ ቃል ገባልሀለው ።"

"አለም"

"እባክህ … ግርማ በቅርቡ አንድ ተጫባጭ ፍንጭ ከላገኘሁ ..ጉዳዩን እርግፍ አድርጌ ተወዋለሁ...ከዚያ በኋላ ስለ ጉዳዩ በጭራሽ ከእኔ አትሰማም.››

በትኩረት ተመለከታት እና ፊቷን አጠና ። "ለምን እንዲህ አይነት ውስብስብ ነገር ውስጥ ራስሽን ታስገቢያለሽ ..እንደማንኛውም ወጣት ዘመናዊ ሴት .ዘና ያለ የህይወት መንገድን አትመርጪም፡፡ ።"

ፊቷን አኮስታተረችበት ።

"እሺ፣ እሺ፣ ምርመራውን መጀመር ትችያለሽ፣ ነገር ግን በትርፍ ጊዜሽ ብቻ ነው። ተጨባጭ የሆነ ነገር ይዘሽ ነይ። አለበለዛ ውሳኔዬን ታውቂዎለሽ .አሁን ከቀጠሮዬ አዘግይተሽብኛል።››ብሎ በቆመችበት ጥሏት ሄደ፡፡

በእርካታ ተነፈሰች፡፡ሸክሟ ከባድ ነበር ፡፡ እያቷ በእናቷ ግድያ ላይ ያላት መረጃ የተወሰነ ነበር። በጋዜጣ ላይ እንዳገኘችው መረጃ ከሆነ እናቷን በመግደል የተወነጀለው ሰው የአእምሮ ብቻ ሳይሆን የመስማትም ችግር እንዳለበት ነው፡  ።እነሱ መሠረታዊ እና ቀላል ችግሮች ነበሩ. የአእምሮ ዝግመት ችግር የነበረው ሊቁ የተባለው ሰው በግድያው ቦታ በተያዘበት ጊዜ የሟቾ እናቷን ደም በጠቅላላ ልብሱ ላይ ተነክሮ እንደነበረ ተዘግቦ ነበር።በተጨማሪም በተያዘበት ወቅት ተጎጂዋን ገድሎበታል የተባለበትን የቀዶ ጥገና መሳሪያ በእጁ ይዞ ነበር።በዛ ምክንያት ወዲያው በቁጥጥር ስር ውሎ ታስሯል፣ ተጠየቋል
እና ተከሷል። በቀናት ውስጥ ነበር ችሎት የቀረበው። ወዲያው ዳኛው ካለበት የጤና እክል የተነሳ ለፍርድ የመቅረብ ብቃት እንደሌለው አውጀው በመንግስት የአእምሮ ሆስፒታል ውስጥ አንዲታሰር ትዕዛዝ አስተላለፉ።ተጠርጣሪው ግን ወደአእምሮ ሆስፒታል ተመዘዋወሮ ብዙም ሳይቆይ እራሱን አጠፋ ተባለ፡፡ በውቅቱ ወንጀለኛውን አሳዶ ለመያዝ
..ከዛም ፍርድ ለማስተላለፍና ፋይሉን ለመዝጋት የነበረው ጥድፊያ ያስደነግጣል፡፡ እናም ከፍተኛ ጥርጣሬም በአለም አእምሮ ውስጥ ጭሯል፡፡
በሶስተኛው ቀን ያገኘችውን ተጨማሪ መረጃ ይዛ ዋና አቃቢ ህጉ ፊት ለፊት ቀረበች፡፡መረጃዎቹን ካቀበለችው በኃላ

‹‹የእረፍት ቀን እንዴት ነበር?›››ስትል ለጫወታ መጀመሪያ ጠየቀችው፡፡

"ድንቅ ነበር. ካንቺ የበለጠ ውጤታማ ቀናቶችን አሳልፌለሁ ብዬ አስባለው። ብዙ ነገሮችን የማንበብ እድል ነበረኝ።"
ፋይሉን ገልጦ ይዘቱን መቃኘት ጀመረ። "እህም" የመጀመሪያ ንባቡ ትኩረቱን ለመሳብ በቂ ነበር። ወንበሩ ላይ ተደግፎ በጥንቃቄ በድጋሚ አነበበው።

"ይህ ዶ/ር ታደሰ የተባለው … ሊቁ የታሰረበት የነበረበት የአእምሮ ሆስፒታል ሐኪም ነው?"

‹‹አዎ ነው››

‹‹ታዲያ አግኝተሸ ማነጋገር አልቻልሺም?››

"አልቻልኩም እንዳለመታደል ሆኖ ከጥቂት ወራት በፊት ሞቷል." "አስደሳች ነው."
"አስደሳች?" አለም በንግግሩ ተበሳጨች። ወንበሯን ትታ ዞረች እና ከኋላው ቆመች
"ይሄ ታደሰ የተባለው ዶክተር ሊቁ የግድያ ወንጀል ለመፈፀም ብቃቱ እንዳለው ሙያዊ ውሳኔ ላይ ሲደርስ ለመጨረሻ ጊዜ የተከታተለው ሌላ የስነ አእምሮ ሃኪም ግን ሊቁ የተባለው ግለሰብ የአእምሮ በሽተኛ ቢሆንም ምንም አይነት ሰውን የማጥቃት ዝንባሌ አሳይቶ እንደማያውቅ በሪፖርቱ አስፍሯል.. ምንም አይነት የወሲብ ፍላጎት እንደሌለው እና
አመፀኝነትም ታይቶበት እንደማያውቅ ተናግሯል፡፡ እና በዶክተሩ ሞያዊ አስተያየት መሠረት እሱ እኔን ዋጋ እንዳስከፈለኝ አይነት የግድያ ወንጀል መስራት እንደማይችል ነው ያረጋገጠው።ገደለ በተባለው ሰው ላይ ሁለቱ ባለሞያዎች የተለያ አይነት ምልከታ ነበራቸው…ይሄም ከመዝገቡ ጋር ተያይዞል..ዳኛው የባለሞያዎቹን ውሳኔ ሚዛናዊነት ለመጠበቅ የሶስተኛ ባለሞያ አስተያየት መጠየቅ ሲገባቸው ባልታወቀ ምክንያት የአንደኛውን አስተያየት ውድቅ አድርገው የሌለኛውን ተቀብለዋል፡፡በአጠቃላይ…ሊቁ የተባለው ሰው እናቴን አልገደላትም የሚል በጣም ጠንካራ እምነት አለኝ።›› አቃቢ ህጉ ሌሎች በርካታ አጭር መግለጫዎችን አነበበ፣ ከዚያም አጉተመተመ፡-

"በአጭር ቀናት ከዚህ የበለጠ ተአምራዊ የሆነ ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ አልችልም። ጉዳዩ ሃያ አምስት አመት ያስቆጠረ ነው። ተስፋ የማደርገው ይሄ ጉዳዩን በ ዳኞች ፊት ለማቅረብ በቂ ምክንያት ነው። በተጨማሪም የዓይን እማኝ የማግኘትም ትንሽም ቢሆን እድል አለኝ
።"
አቀቢ ህጉ‹‹አለም.››ሲል ተጣራ "አቤት"
44👍5
"የቤት ስራሽን በበቂ ሁኔታ ሰርተሻል፣ ግን ግድያው የተፈፀመው በሶሌ ኢንተርፕራይዝ ንብረት በሆነው የከብት እርባታ ግዙፍ ግቢ ውስጥ ነው፡፡ የዚህ ኢንተርፕራይዝ ባለቤቶች በዚህ ከተማ ውስጥ በጣም ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ከመሆናቸው የተነሳ የአይን እማኝ ቢኖር እንኳን በእነሱ ላይ አይመሰክርም ….ምክንያቱም ወይ በገንዘባቸው ይደልሉታል..አልደለል ካለም ያጠፉታል ፡፡ ››
‹‹በየትኛውም መንገድ እነሱን ለመፋለም ቁርጠኛ ነኝ››

'እሺ አምንሻለሁ። ነገር ግን በሻሸመኔ ከተማ ቁጥር አንድ ሀብታም በሆኑትና ከተማውና በማሳደግ በሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ዋና ተሳታፊ እንደሆኑ የሚታወቁት ሰዎች ላይ ክስ መክፈት እንዲህ ቀላል አይደለም…በዛ ላይ የፖሊስ አዛዡም ቢሆን ቀላል የሚባል ባለጋራ አይደለም..እና በተለይ እዚህ ቦታ ላይ ሆነሽ ማለቴ የምክትል አቃቢ ህግ ስልጣን ይዘሽ ይሄንን ክስ መቀስቀስ ነገሩን የበለጠ ውስብስብ ያደርገዋል፡፡ምን አልባት እንዳሰብሺው ክስሽን  ሚደግፉ  መረጃዎችና  ማግኘት  የማትችይ  ከሆነ  እንደግለሰብ  ብቻ  ሳይሆን
እንደተቋምም ቢሮችንን ያስወቅሳል…እኔና አንቺም ስራችንንም ልናጣ የምንችልበት እድል ከፍተኛ ነው፡፡

እንደማኩረፍ አለችና "እሺ ከዚህ ቢሮ ስራዬን ለቅቄ በራሴ አደርገዋለሁ" አለችው። "በኢየሱስ …ንግግሬን እኮ እንድጨርስ አልፈቀድክሺልኝም።››

መጥሪያውን ተጫነና  ቡና እንዲያመጣለት ፀሐፊውን ላይ ጮኸበት። ወዲያው  ሲጋራ ለኮሰ ።

"በሌላ በኩል" ሲል ንግግሩን ጀመረ "ያንን ኩማንደር አልወደውም..እሱን ወደ ገደል ጎትቶ የሚጥል ቁራጭ እድልም ቢሆን ካገኘሁ ልጠቀምበት እፈልጋለው….. ››

የአለም እየከሰሙ የነበሩ አይኖች በሌላ ተስፋ ሲፈኩ ታዩ‹‹እና ምን እያልከኝ ነው?›› "ስለዚህ ክሱን እንደገና መክፈት ትቺያለሽ እያልኩሽ ነው?"
በደስታ ዘለለችና ከጀርባው ተጠመጠመችበት፡፡፡
" አለም አንቺ ጎበዝ ተፋላሚ ነሽ። ምርጥ የህግ ባለሞያ እንደሆንሽ በተደጋጋሚ ጊዜ አሳይተሸል ፤ይሄንንም ጉዳይ ከስር መሰረቱ በርብረሽ ውጤታማ እንደምትሆኚ አምናለው ››አለና የሰጠችውን ፋይል ሰብስቦ ወደፎልደሩ መልሶ ከተተና መለሰላት፡፡

አለምም በአቃቢ ህጉ ጠረጴዛ ላይ ተደግፋ። " ልክ እንደ ሆንኩ አውቃለሁ። እውነተኛውን ገዳይ ለፍርድ አቀርባለሁ፣ ያንን ማድረግ ካቃተኝ ኃላፊነቱን ሁሉ በግሌ እወስዳለው፡፡››አለችው፡፡

አይኖቹን በደረቷ ላይ አፈትልከው የሚታዩት ጡቷቾ ላይ ሰክቶ‹‹አይ ይሳካልሻል…ደግሞ ይሄንን አማላይ ውበትሽንና ቅንዝንዝ ሴትነትሽንም ተጠቀሚበት››አላት፡፡

‹‹ትልቅ ሰው አይደለህ እንዴ…..?ለማንኛውም በሰጠሀኝ ፍቃድ በጣም ስለተደሰትኩ የተናገርከውና እንዳልተናገርክ ቆጥረዋለው››አለችና ክፍሉን ለቃ በመውጣት ወደራሷ ቢሮ ሄደች፡፡ከዛ በኋላ ነበር ዋና አቃቢ ህጉ በዳኛ ዋልልኝ አማካይነት የጥዋቱን ስብሰባ ከእናቷ ገዳይነት ከምትጠረጥራቸው ሶስት ኃያላን ሰዎች ጋር እንድትገናኝ እና…ፊት ለፊት እንድትገጥማቸው እድሉን ያመቻቸላት፡፡እዛው አልጋዋ ላይ እየተገላበጠች በሀሳብ ከወዲህ ወዲያ ስትላጋ እኩለ ለሊት ማለፉን ልብ አላለችም ነበር…..፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
37👍10
አትሮኖስ pinned «#ቋጠሮ_ሲፈታ ፡ ፡ #ክፍል_አራት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ ///// አለም ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባቷ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ  አያቷ የህግ ሙያ እንድታጠና አጥብቃ ትገፋፋት ነበር..በወቅቱ ምክንያቱ አይገባትም ነበር…እንዲሁ ሰዎች.. የልጅ ልጅሽ ጠበቃ ነች ወይም ዳኛ ነች እንዲሏት ካላት ምኞት ተነስታ የምትገፋፋት ይመስላት ነበር..አሁን ነው ነገሮችን ስታገጣጥም ምክንያቱ ፍንትው ብሎ የተገለፀላት፡፡…»
#አዎ_ትመጣለች

ትመጣለች እያልሁ
                   ቀኔን እንደ ምግብ ስበላው አኝኬ
አዝኖልኝ ነው
መሰል አትመጣም የሚል ቃል ይልካል አምላኬ

ሰይጣን ደግሞ በጎን ቄጠማ ነስንሶ
ትመጣለች ጠብቅ
ብሎ ይነግረኛል ቃሉን አለስልሶ

አውቃለሁ እውነት ነው
ፈጣሪ ያለው ቃል አይስትም ሚዛኑን
ሰይጣን ስግብግብ ነው
ቀን እየነጠቀ ያስረዝማል ቀኑን
ቢሆንም
ቢሆንም
እውነት እንደ ኮሶ እያንገሸገሸኝ አልጠጣም ደፍሬ
ተስፋን በገሃዱ እጋታለሁ እንጂ ከውሸት ቆንጥሬ

አዎ ትመጣለች
               እውነቱን እያወቅሁ አላምንም እውነቱን
ቀን የተቀማ ሰው
ሃሰትን ተግቶ ተስፋን እየጠጣ ያረዝማል ህይወቱን
ሰይጣን ትመጣለች አይደል?

🔘✍️በላይ🔘


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍115😢1
ካልመጣህ

ባትመጣም ቅጠረኝ
ሺ ጊዜ ልገተር
ፀሀይ ቆማ ትቅር
ብርሀንም ይፈር
ጨለማ ያሸንፍ

የሰዉ ልጅ ከርታታ
እንደቆመ ይቅር
አንተ 'ስክትመጣ
የፈካዉ ይገርጣ

ግሳንግሳም አለም
የምትመካበት ቴክኖሎጂም ይክተም

ብቻ አንተ እስክትመጣ
ደርቆ መቅረት ይሁን የዚች ዓለም እጣ።

ብልህ ደስ ባለኝ
ጅል ሆኖ ባስቀረኝ

                        የኔ ተናፋቂ......

አንተ ብትመጣም
አንተ ባትመጣም
ደግሞ ብትቀርም
እኔ እንደዉ ለሴኮንድ አንተን አልጠብቅም።

ስለ ፍቅር ብለዉ የቆሙ አዉቃለሁ
ባትመጪም ቅጠሪኝ ሲሉም ሰምቻለሁ
ደግሞም ሲጠብቁ በአይኔ አይቻለሁ

ከዚ ሁሉ መሀል እኔ የተረዳሁት
አፍቃሪዉን ሳይሆን አጠባበቁን ነዉ እነሱ የወደዱት።

አረ እንደዉም ዉዴ......

በመጠበቅ ብዛት ስሙ የገነነዉ
እሷኑ ቢያሳዩት
       እየጠበቃት ነዉ።

ታዲያ ለምን ብዬ
ብትመጣም ባትመጣም ለምረሳህ ነገር
ሴኮንድ አልጠብቅህ ጥቅር ብለህ ብትቀር።

🔘ትዝታ ወልዴ🔘


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
5🔥5👏4👍2
#እውር_እና_እውር
:
:
:

«ሲመሽም ጠጣለው ባንቺ ምክንያት፣
ሲነጋም ጠጣለው ባንቺ ምክንያት፣
ግን ዛሬም አልቻልኩም አንቺን መርሳት።»
:
:

እንደዚህ ሚለውን እርባነ ቢስ ዘፈን ከሰማ በኋላ፣
አፍቃሪው በሞላ፣
ፍቅረኛዬ ባላት ገና እንደተከዳ፣
ባለጌ ወንበር ላይ እግሩን አነባብሮ ጂኑን እያስቀዳ፣
ጠዋትና ማታ መጠጣት ጀመረ፣
እንቶ ፈንቶ ሰምቶ ሱሰኛ ሆኖ ቀረ።
:
:

እውር እና እውር ተያይዞ ገደል፣
ማለት ይሄስ አይደል።
:
:

ሲመሽ እየጠጣ ሲነጋ እየጠጣ እንዲ ብሎ መቀኘት፣
«ሱሰኛ» ነው እንዳይባል ሴትን ማመካኘት፣
የራስን ደካማ በሰው ላይ መለጠፍ፣
በሴት ላይ መለጠፍ፣
እንኳን ለንጉርጉሮ ለማውራትም ሲቀፍ።
:
:

በርግጥ ሰው ይጎዳል በርግጥ ሰው ያደማል፣
በጊዜ ሂደት ውስጥ ሁሉም ይታከማል።
ያመኑት ሲከዳ ምንም ቢቆረጥም፣
ላያስችል አይሰጥም።
:
:

ላንድ ሰሞን ቁስል ቀናቶች ሲያልፉ ለሚሽር ዳግመኛ፣
ጠዋትና ማታ መጠጥ እየላፉ ከመሆን ሱሰኛ፣
ብቅልና ብሶት ሆድን ከሚፈጀው፣
ባለን መደሰቱ እሱ ነው ሚበጀው።
:
:

በዛሬ መገፋት ዛሬን የወደቁ፣
ነገ ካልተነሱ ሊያውም እየሳቁ፣
ይቺን ቀን ለመርሳት መጠጥ ቤት ከሮጡ፣
ቀን በቀን ከጠጡ፣
የነጋቸው ገዳይ የራሳቸው ዓለም፣
እራሳቸው እንጂ ትናንት የጣላቸው ገፊው እጅ አይደለም።
:
:

ሰውን አመካኝቶ ቀን በቀን መጠጣት፣
እራስን ማታለል ማንነትን ማጣት፣
ወድቆ አለመነሳት፣
በጣም ትልቅ ጥፋት፣
ከመሆን ባሻገር፣
ከቶ አያስደፍርም ጥምብዝ ብሎ ሰክሮ
እሷ ናት ምክንያቴ ብሎ ለመናገር።

🔘ሄኖክ ብርሃኑ🔘


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👏127😢1
ከሌላ እንዳትቆጥር

ይሀዉልህ ዉዴ
ትላንትና ማታ

እንባዬን አፍስሼ
አፈር ትቢያ ልሼ
ከእግርህ ወድቄ ማረኝ ተዉ ማለቴ
ታቦት እየጠራዉ መማል መገዘቴ

                 ከሌላ እንዳትቆጥር

ደግሞም ታቦታቱን ጠርቼ ጠርቼ
አንተም ዝም ብትል
የሞተች እናትህን መቃብር አዉጥቼ
በሷ ሞት እያልኩኝ ያኔ መለመኔን
አንተንም እያስማልኩ.......
ቅዱሱን መፅሐፍ በእጆችህ አስይዤ
አልተውሽም ስትል በደስታ ፈንጥዤ
ያኔ መጨፈሬን

                     ከሌላ እንዳትቆጥር

ከወትሮዉ በሌላ
ካልለመድከዉ ገላ
እራሴን ሰጥቼ ደባብሰኝ ማለቴን
ሳመኝ እቅፍ አርገኝ ብዬ መማፀኔን
ላለፈ ስህተቴ
ከእቅፍህ ገብቼ ንስሀ መግባቴን

                   ከሌላ እንዳትቆጥር

አንተን ከረሳሁኝ
ባንተ ከማገጥኩኝ
ሳት ብላኝ ነብሴ
ሌላዉን ከሻተች ሞት ይሁነኝ ዋሴ።

ስቅበዘበዝ ልሙት ልክ እንደ ይሁዳ
የሄድኩበት እግሬ ይቅር ምድረ በዳ።

ነፍሴንም አይማረዉ
እግዜሩም ይጣላኝ
እኔ አንተን ከረሳዉ
ያቀፍኩበት እጄን ለምጥ እከክ ይዉረሰዉ
ብዬ መገዘቴን
በራሴ ጨክኜ ርግማን ማዝነቤን

         አደራ እንዳትቆጥረዉ
         እባክህ በሌላ

         ሰክሬ ነዉ እንጂ
         ባሌ ትዝ ብሎኝ
         ለደቂቃም እንኳን እንዲያዉ ለቅፅበቱ
         አንተ የኔ እንድትሆን አልሻም በእዉነቱ።

🔘ትዝታ ወልዴ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍129
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///

አቶ ፍሰሀ በቀይ ቆዳ በተለበጠ መቀመጫው ላይ ተቀመጦ ስልክ እያወራ ነው። ከድሮም ጀምሮ ይህን ወንበር ይወደዋል፡፡

"ተረጋጋ ክቡር ዳኛ"

ጁኒየር በበሩ ደጃፍ ላይ ቆሞ  ተመለከተውና እና እጁን አውለበለበለት።
እያወራ የነበረውን የገመድ አልባውን ስልክ በእጁ ሸፍኖ ለልጁ በሹክሹክታ፣ ‹‹ዳኛውን እያወራሁት ነው›› አለው..ከዛ ወደስልኩ ትኩረቱን ሰብስቦ"አሁን ወደ ድምዳሜ እየዘለልክ ነው እናም እንዲሁ በከንቱ ነው እየተበሳጨህ ያለኸው " አለው

"..ፍሰሀ ነገሩን አቃለህ ልታየው አይገባም….እሷ እናቷ ተገድላበታለች።አሁን የህግ ድግሪ እና የከፍተኛ አቃቤ ህግ ስልጣን በእጇ አስገብታለች..በዚህም ምክንያት የመስቀል ጦርነት ላይ ነች። እነዚህ ወጣት ሴቶች አካሄዳቸው እንዴት እንደሆነ መገመት ከባድ ነው…. ታውቃለህ?። ››

ለአፍታ አዳመጠ። “ክብር ዳኛ ተረጋጋ፣ ምንም ሚከሰት አዲስ ነገር የለም፣አንተ ብቻ ዝም ብለህ አፍህን ዝጋ፣ ይሄ ሁሉ ነገር በቅርብ ያልፋል። የሰሎሜን ልጅ ለእኔ ተውልኝ፡፡››አለው ልጁ ጁኒየር ላይ ዓይኑን ተክሎ ንግግሩን ቀጠለ።"ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ጅራቷን በውብ እግሮቿ መካከል ሸጉጣ ወደ መጣችበት ከተማ ትመለሳለች ።ምንም አታስብ የእኔም ልጅ ምርጫውን በከፍተኛ ድምፅ አሸንፎ ፓርላማ ይገባል…፣ አንተም ጊዜህን ጠብቀህ በክብር ጡረታ ትወጣለህ፣ እና ያ እስኪሆን አንድ አመት አለን።››አለናን ተሰናብቶት ተንቀሳቃሽ ስልኩን በጠረጴዛ ላይ አስቀመጠው።

"በኢየሱስ ስም …ይሄ ዳኛ ተንበቅብቆ ሊያንበቀብቀኝ እየሞከረ ነው….እባክህ ቢራ ስጠኝ
›› አለና…መቀመጫውን ለቆ ወደ በረንዳ ወጣ…..ልጁ ጁኒዬርም ለእሱና ለአባቱ አንድ አንድ ቢራ ከፍሪጅ ውስጥ አወጣና አባቱን ተከትሎ ወደበረንዳው ወጣ…..አንዱን ቢራ ለአባቱ አቀብሎት አንደኛውን ለራሱ ያዘና ከፊት ለፊቱ የበረንዳውን ግድግዳ ተደግፎ ቆመ፡፡

ወዲያው የእንስሳት እርባታ ድርጅት ውስጥ ለ30 አመት የሰራው ሱልጣን ከፊት ለፊት የውጪን በራፍ አልፎ ተከሰተ … በጭንቀት ተወጣጥሯል፣ የሰሌን ኮፍያ በጭንቅላቱ ላይ አድርጎ አንገቱን ደፍቶ ከፊት ለፊታቸው በአራት ሜትር ርቀት ላይ ቆመ፡፡

ሱልጣን ከከተማው ጥግ ከምትገኝ አንድ የገጠር ከተማ ተወልዶ ያደገ ሲሆን እስከ ስድስተኛ ክፍል ተምሮ ያቆረጠና በአባሮ ኢንተርፕራይ ስር የሚተዳደረውን የእንስሳት እርባት ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ ከሠላሳ አመታት በላይ ያገለገለ አገልጋይ ነው ፣ ሚስት ያገባው እዛ ድርጅት ውስጥ ስራ ከጀመረ በኋላ ነው….አምስት ልጅ ወልዶ ያሳደገውም አዛው ድርጅት ተቀጥሮ ከብቶችናና ፈረሶችን በመንከባከብ በሚያገኘው ደሞዝ ነው….ከአሁን ወዲህ ባለው ቀሪ ዘመኑም ከዛ ውጭ መስራት የሚችለው ሌላ ስራ ይኖራል ብሎ አያምንም…ለዛም ነው ለሰራው ስህተት በመንቀጥቀት ይቅርታ ለመጠየቅ ጌታው ፊቱ የቆመው፡፡

አቶ ፍሰሀ እሱ ምንም ከመናገሩ በፊት "ምን እንደምትል አውቃለሁ። ምንም የማዳምጥህ ነገር የለም… በአጭሩ ከስራ ትባረሀል››አለው
ጁኒየር በቆመበት ሆኖ አባቱን በድንጋጤ ተመለከተ..እንደዛ አይነት ውሳኔ ሰማለው ብሎ አልጠበቀም…..‹‹አይ አባዬ ትንሽ ሊያስደነግጠው ፈልጎ ነው እንጂ የእውነትማ አያባርረውም››ሲል በውስጡ አሰበ፡፡

"ጋሽ ፍሰሀ እንዴት እንዲህ ታደርጋለህ ?። እዚህ ለሠላሳ ዓመት በላይ ለአንተና ለቤተሰቦችህ አገልግያለው።"አዛውንቱ ሱልጣን መለማመጡን ቀጠለ፡፡

"ጥሩ ለዛ ሚመጥን በቂ የስራ መፈለጊያና የአገልግሎት ክፍያ እንዲከፈልህ አደርጋለው "

"ግን ... አንድ የመጨረሻ እድል ብትሰጠኝ ምን አለበት? "

" መቶ ሺ ብር ልሸጠው የማስበውን ልዩ ፈረሴን እኮ ነው በእንዝላልነት እንዲሰበር ያደረከው፣በቃ ከአሁን ወዲያ ቢድን እንኳን ምን አልባት የጋሪ ጎታች ፈረስ ይሆን እንደሆን እንጂ ለውድድር የሚያገለግል የግልቢያ ፈረስ አይሆንም፡፡ከዚህ በፊትም ስንት ከብቶች ውጭ አሳድረህ በጅብ እንዳስበላህ አትረሳውም አይደል…አንተ ላይ ያለኝ ትግስት አልቋል፡፡››

አቶ ፍሰሀ አየር ወደውስጡ ሳበ ። "ጌታ ሆይ፣ እኛን ውጥንቅጥ ውስጥ የሚያስገባን ነገር ከፊታችን ተደቅኖ እያለ ስለእሱ እንኳን ተረጋግተን ማሰብ አልችልም። በቃ ከፊቴ ጥፋልኝ…ሰኞ ቼክህ እንዲዘጋጅልህ አደርጋለው፣እዎ እርባታ ድርጅቱ ፋይናንስ ክፍል ጋር አስቀምጥልሀለው…ከዛሬ ጀመሮ እዚህም ሆነ የስራ ቦታ አይንህን ማየት አልፍግም፡፡››ቁርጥ ያለውን የመጨረሻ ውሳኔውን አሳወቀው፡፡፡

"አንድ ተጨማሪ እድል ስጠኝ ጋሽ ፍሰሀ በልጆቼ እምላለው…ሁለተኛ አላሳዝንህም፡፡››

"ይህን ንግግር ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ ሰምቼዋለሁ።አሁን በጥበቃ እያስገፈተርኩ ሳላስወጣህ በክብር ጊቢዬን ለቀህልኝ ውጣ፡፡››
"ጋሽ ፍሰሀ…"

"ደህና ሁን… እና መልካም ዕድል "

አባቱን ተወና የልጁን የጁኒዬርን አይን አይን ማየት ጀመረ …ከልጅነቱ ጀምሮ የሚያውቀውና ሲንከባከበው የኖረ ልጅ ስለሆነ የአባቱን ሀሳብ ለማስለወጥ የሆነ ነገር ይላል ብሎ ነበር የጠበቀው.. ጁኒየር ግን ዓይኖቹን ወደመሬት ደፋ ፡፡ ጋሽ ሙስጠፋ በመጨረሻ
ያደረገው ቦት ጫማ ላይ የተጣበቀውን ጭቃ እያራገፈ እንገቱን እንደደፋ ጊቢውን ለቆ ወጣ።የግቢው በር መዘጋቱን እንደተሰማ ጁኒየር ወደአባቱ ተመለከተና"እንደምታባርረው አላውቅም ነበር" ሲል በቁጭት ተናገረ።

" በቃ..ከአሁን ወዲህ ከእሱ ምንም ጥቅም ማግኘት አይቻልም…እድሜው ገፋቷል ጉልበቱም ደክሞል…ዛሬ ፈረሱን እንዲሰበር ካደረገ ነገ ራሱን ይሰብርና የእድሜ ልክ ሸክም ነው የሚሆንብን።"

"ቢሆንስ!ማባረሩ አስፈላጊ ነበር? ለጥፋቶቹ ልትጮህበት..ወይንም በገንዘብ ልትቀጣው ትችል ነበር ፣ወይንም ደግሞ አንዳንድ ኃላፊነቶቹ አንስተሀው ቀላል ስራ ላይ እንዲመደብ ማድረግ ትችል ነበር ፡፡››

‹‹ነገርኩህ እኮ ከአሁን በኋላ አያስፈልገንም….ከዛፎች ትምህርት መውሰድ አለብህ..ቅርንጫፋቸው ላይ ያሉ ቅጠሎች ሲደርቁ ወዲያው ከላያቸው ላይ አራግፈው ያስወግዷቸዋል….ህይወት እንደዛ ነው….››

‹‹ቢሆንም ውሳኔ ጭካኔ የታከለበት ነው፡፡››

"ይህን ንግድ የምትሠራ ከሆነ ልጄ፣ ልብህ እንደብረት ጠንካራና ደንዳና መሆን አለበት።

ሥራው ሁልጊዜ አስደሳች አይደለም፣ ታውቃለህ። ደንበኞችን የሚያምር እራት ከመጋበዝና ከሚስቶቻቸውና ከሴት ልጆቻቸው ጋር ከመሽኮርመም የበለጠ ብዙ ነገር አለ።››በማለት ልጁን በአሽሙር ወጋው፡፡

ጁኒዬር ሱልጣን ላይ የተወሰደውን ከባድ ቅጣት ለመቀበል ከብዶት ራሱን ወዘወዘ፣ ከዛ በእጁ ከያዘው ቢራ አንዴ ተጎነጨለትና‹‹ቅድም ከዳኛው ጋር በስልክ ስታወራ ነበር….ስለሰሎሜ ልጅ መሰለኝ?››ሲል ጠየቀው፡፡

‹‹አዎ ….ዛሬ ዳኛውን ለማናገር ቢሮው ሄዳ ነበር››

‹‹ እንዴ?››

"አድርጋዋለች፣ ይህን ለማድረግ ጊዜ እንዳላጠፋች አስተውል። ዳኛው በሁኔታው በጣም ነው የተደናገጠው፡፡ ዳኛ ጡረታ በመውጫ ጊዜው እንዲህ አይነት ፈታኝ ጉዳይ ስለተጋረጠበት ለስሙ ፈርቷል።"

"አለም ከእሱ ምን ፈለጋ ነው?"
44👍7
"ሊቁ የተባለው እብድ በሳይካታሪስት ዶ/ሮች ሲመረመር ለምን ሁለት ዶ/ር ብቻ እንዳየውና ለውሳኔ ለምን እንደቸኮለ አንዳንድ ጥያቄዎችን ጠየቃችው።ምክንያቱም ሁለቱ ዶክተሮች ወንጀለኛውን በተመለከተ ሁለት የተለያየ ሙያዊ አስተያየት ነበር የሰጡት…እንደእሷ አመካከት የሁለቱን ዶ/ሮች አስተያየት ፍትሀዊ ለማድረግ ሶስተኛ ዶ/ር መጋበዝ ነበረበት ባይ ነች….ዳኛው በምን መስፈርት የአንደኛውን ዶ/ር ሞያዊ አስተያየት ውድቅ አድርጎ የአንደኛውን ዶ/ር አስተያየት ሊቀበሉት እንደቻሉ ነው ጥያቄዋ ።"

"ይገርማል….እንደእዛ አይነት ጉዳይ ነበር እንዴ?››

‹‹አዎ ነበር…እሷም ያንን ፈልፍላ በማውጣቷ የአደገኝነቷ አንድ ማሳያ ነው››

"ታዲያ… ስለ ልጅቷ ምን አሰብክ?"ጁኒዬር በጭንቀት ጠየቀ፡፡

‹‹ከዳኛው  ጋር እስማማለሁ። እሷ ለሁላችንም ስጋት ነች። ከመካከላችን አንዱ ሰሎሜን እንደገደላት ታስባለች፣ እና ማን እንደሆነ ለማወቅ ቆርጣለች።"

‹‹የምትገርም ሴት ነች"

"አዎ…የምትገርም ሴት ነች….ሆንም በእርግጥ በማናችንም ላይ ምንም አይነት መረጃ የላትም።"

"እርግጥ ነው።"ጁኒየር አባቱን በትኩረት ተመለከተ።

‹‹ግን እሷ ስል የሆነ ጭንቅላት ያላት ሴት ነች።››

"ስል ጭንቅላት ብቻ ሳይሆን አማላይ አቋምና ውብ መልክም አላት›› አባት እና ልጅ ተሳሳቁ።

"አዎ ጥሩ ነች. አብዛኛው ነገሮቾ ልክ እንደ እናቷ ነው››የጁኒየር ፈገግታው ደበዘዘ

"አዎ እስማማለሁ….አሁንም ትናፍቅሀለች አይደል?»አቶ ፍሰሀ የልጁን አጠቃላይ ሁኔታ በማጥናት ጠየቀ።

"አንዳንድ ጊዜ."

አቶ ፍሰሀ ቃተተ። "የእሷ ሞት በአንተ ላይ ዘላቂ ተጽእኖ ማሳደሩን ሳስበው ይገርመኛል..አውቃለው የቅርብ ጓደኛህን ስታጣ ማዘንህ የሚጠበቅ ነው… ያንተ ግን እነዚህን ሁሉ አመታት ለሞተች ሴት ማለቃቀስ ሞኝነት ነው..የእሷን ሀዘን እንደምንም ከውስጥህ ማስወገድ አለብህ… ያለ በለዚያ መቼም ሰው መሆን አትችልም። ።››
ጁኒየር ተቃወመ፡

“የምትለውን ያህል አልሰበረኝም››

‹‹ ሰሎሜ ከሞተች በኋላ ለረጅም ጊዜ ተበሳጭተህ ነበር. ከዛን ጊዜ በኃላ በስርአቱ እንኳን መተንፈስ አልቻልክም። ኩማንደሩን ተመልከት። የሰሎሜን ሞት በፀጋ ተቀብሎ ህይወቱን ወደፊት ቀጥሏል ።"

"እኔ…እስከዛሬም ድረስ እሷን እንዳማስብ እንዴት አወቅክ?" "

" ያ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ሰው ግልጽ ነው?"

"አባዬ ተሳስተሀል ..እሷ ከሞተች በኃላ ሶስት ሚስቶች ማግባት ችያለው…ይልቅ ይሄንን ምክር ለኩማንደሩ ብትነግረው ይሻላል…እሱ ነው በአርባአምስት አመቱም ወንደላጤ ሆኖ የሚኖረው.. የዛ ምክንያቱ ደግሞ እሷ ነች."

"ያንተ ሶስት ሚስት ማግባት ሊኮራበት የሚገባ ነገር ነው…?ካሰሎሜ ሀዘን አገግመህ ቢሆን ኖሮ ከአንድ ሚስት ጋር ነበር ፀንተህ የምትኖረው….እስከአሁን ሲያገባ የነበረው በድንህ ስለሆነ ሴቶቹ ጥለውህ ይሄዳሉ፣….መንፈስህ ከእሷ ጋር ተቀብሯል?" አባትዬው ጮኸበት፣ ንዴቱ ጨመረ። " ሴቶች እያገቡ መፍታት የጤነኝነት ምልክት አይደለም…በዚህ ምርጫ ውድድርህ አንደ አንድ ሂስ የሚቀርብብህ ይሄ ሴት አያያዝህ ነው››

‹‹አባዬ እኔ እኮ አይደለም የምወዳደረው…እኔ ለአንተ ስል ነው የምወዳደረው…በምርጫው ብሸነፍ  እኔ  አልተሸነፍኩም  ..ምክንያቱም  መጀመሪያውኑም  አልፈልገውም  ነበር
…ባሸንፍም…ህዝቡን ወይም ከተማዋን ወክዬ ሳይሆን አንተን ወክዬ ነው የምገባው››

‹‹ባንተ ቤት ንግግር ማሳመርህ ነው..በዚህ ጉዳይ ቀልድ እንደማልወድ ጠንቅቀህ ታውቃለህ…..በአንተ እንዝላልነት አንድ እንቅፋት ቢገጥመን እና ይሄ ለአመታት የለፋሁበትና ገንዘቤን የከሰከስኩበት ጉዳይ ቢሰናከል…እኔና አንተ አንተዋወቅም….ከአሁኑ ቤቴንም ኩባንያዬንም ለቀህ ለመሄድ ተዘጋጅ፡፡››

‹‹አታደርገውም አይባልም….ግን አባዬ እኔን አይደለም መፍራት ያለብህ….የሰሎሜን ልጅ ፍራ….ለአመታት የገነባሀውን ነገር ሁሉ ወደፍርስራሽ እንዳትቀይርልህ፡፡››

"አታስብ ..እኛ ንፁሀን መሆናችንን እናሳምናታለን ። እኛ የተከበረን ዜጎች ነን።" "ስለዚህ አካሄዳችን እንዴት ነው?"

"አታሏት"

"አታሏት!አልገባኝም" ጁኒየር መልሱን ለመስማት ጓጓ፡፡፡

‹‹አንደምታያት ቅንዝንዝ እና ቅንዝራም ነገር ነች..በፍቅር አይኗቾን ለመጋረድ መሞከር በጣም አዋጪው ዘዴ ይመስለኛል፡፡››

"እንዲህ ዓይነቱን ደስ የማይል ወጥመድ በቀላሉ የምትወድቅ ይመስልሀል?"ጁኒየር ፈገግ አለ።

"መሞከር ነው..ካልሞከርን እንዴት እናውቃለን…አንተም ሆንክ ኩማንደር ገመዶ ሞክሯት…ከሁለት አንዳችሁ በለስ ይቀናችሁ ይሆናል….በእናቷ ጊዜ ልምድ ስላላችሁ ለአንድ ሴት መፋለም ያን ያህል የሚከብዳች አይመስለኝም….ግን እወቅ በምንም አይነት ሁኔታ ከእሷ ጋር ወደአልጋ እንዳትሄድ…በምንም አይነት?››

‹‹እንዴ ለምን››

‹‹ነገርኩህ…ያ የሆነ ቀን ከእኔ ምንም አይነት ከለላ የለህም…ቀጥታ እጅህን ሄደህ እሰሩኝ ብለህ ለመንግስት እንደሰጠህ ቁጠረው፡፡››

‹‹እውነትህን አይደለም አይደል?››

‹‹ሚካኤልን ብያለው››

ጁኒዬር ደነገጠ..አባትዬው ሚካኤልን ብለው ከማሉ ምንም የሚቀየር ነገር እንደሌለ እና የመጨረሻ ሀሳባቸው እንደሆነ ያውቃል፡፡ግን ምናቸውም አልገባውም‹‹…በፍቅር እንድትወድቅልህ አታላት ..ግን አብረሀት እንዳትተኛ..ምን አይነት ግራ የተጋባና የተወሳሰበ ትዕዛዝ ነው››ሲል በውስጡ ይወዛገብ ጀመር፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍2826🥰2
አትሮኖስ pinned «#ቋጠሮ_ሲፈታ ፡ ፡ #ክፍል_አምስት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ /// አቶ ፍሰሀ በቀይ ቆዳ በተለበጠ መቀመጫው ላይ ተቀመጦ ስልክ እያወራ ነው። ከድሮም ጀምሮ ይህን ወንበር ይወደዋል፡፡ "ተረጋጋ ክቡር ዳኛ" ጁኒየር በበሩ ደጃፍ ላይ ቆሞ  ተመለከተውና እና እጁን አውለበለበለት። እያወራ የነበረውን የገመድ አልባውን ስልክ በእጁ ሸፍኖ ለልጁ በሹክሹክታ፣ ‹‹ዳኛውን እያወራሁት ነው›› አለው..ከዛ…»
#ታምናለህ?

“ውስኪን ከብርጭቆ
መጎንጨት አንስቶ
ጭኗን ከገለጠች…
ማውራት እንቶፈንቶ ፤
አያድርስ በደሉ !
የሀብታም ሰው ግፉ
ተናግሯል መጽሐፉ”
ብሎ የሚታዘብ…
አረቄ ቤት ያለ …
የዛ ድሀ ምኞት ፤

በሴቶች ታጅቦ...
ውስኪ መጠጣት ነው
እ’ሱም ገንዘብ ኖሮት።

🔘ሚካኤል አስጨናቂ🔘


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍75
#ተመስገን

ለውሀ ቢቀረጥ ለማየት ቢከፈል
ለጠሀይ ቢቆጠብ አየር ቢከለከል
ለመስማት ቢያስጨንቅ ለማሽተት ቢቀጣ
አቤት የእኛ እጣ!
ዋጋ ቢወጣለት እያወሩ መስማት
በደረሰኝ ቢሆን መራመድ መተኛት
እግዚኦ የኮመቴው የህግ አውጭው መዓት!
ይህን ሳይ ብቻ ነው ወደ ላይ ማንጋጥጥ
የዓለም ማጣቴን ... በስድብ የማለውጥ
ውድ መነፅር ሳጣ ከጎኔ ማተርኩኝ
መኪና አልባ ስሆን አቀርቅሬ አየሁኝ
ማየት የተሳነው እግር አልባም አለ
እንዴት ብዬ ላማር ሁሉ ኖሮኝ ሳለ?
ስድብ ከቶ አልክም ለዝምታው ዳኛ
ጤና ቢሰጠኝ ነው ሰርቼ ምተኛ
አላማርረውም ቤት ሳልገዛ ብዬ
የጎዳናውን ጉድ እያየሁኝ ባይኔ
ባለ መፅናናት ነው በፀጋው ማመስገን
ያለን ነው የሚበዛ ለእኛ ካልተሰጠን
ተመስገን ተመስገን
ይሄ ነው ክፍያው ደግሞ ለቀጣይ ቀን

🔘ሚካኤል አስጨናቂ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
14👎1
#ለካስ



ማበጠር ቸግሮኝ ገለባን ከፍሬ፣
እንዲው እንደባከንኩ መልስ አጥቼ ኖሬ፣
ለዚው ጥያቄዬ ለሚወብቅና ለሚያንቀጠቅጠኝ፣
ተመስገን ነው ዛሬ ግዜ ምላሽ ሰጠኝ።


ይኸው የግዜው መልስ ...


ስንዴን ከእንክርዳዱ የምንለይባቸው
ገንዘብና ዝናም ለካስ ወንፊት ናቸው።

🔘ሄኖክ ብርሃኑ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
9👍2👏2
#ሀገሬን_አትንኩ

ዝንጀሮ
ያኔ ጥንት ድሮ..
መጀመርያ የመቀመጪያዬን
ማረፊያ መንበሬን.. .
ብላ ተናግራለች ብለው ሲተርቱ
አልገቡኝም ነበር አበው አዛውንቱ
ዛሬ ፍቺ አገኘሁ ተፈታልኝ ቅኔ
ለካስ የሚያሞቀኝ ትንፋሹ ነበረ
የምስኪን ወገኔ !
ብሄድ ብጓዝ ብድህ ብሸሽም በርሬ
ማረፊያ ወንበሬ
መሸሸጊያ አድባሬ
እሷ ናት ኢትዮጵያ
እሷ ናት ሀገሬ !
አሁን መሯል ደሜ ..
ግራ ጉንጬን ምቱት ሰንዝሩብኝ ጡጫ
ሲሻችሁ ነርቱኝ በዱላ በርግጫ.. .
ብቻ ግን
ብቻ ግን.. .
ሀገሬን አትንኳት የኔን መቀመጫ ።

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
7👍4🥰1
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


///
ፀሐይ ከምዕራቡ አድማስ በላይ ልክ እንደ አንድ ግዙፍ ብርቱካንማ ዲስክ ተንጠልጥላ ነበር፣ ብሩህ ነሐስ ትመስላለች። ሰማዩ ቀዝቃዛ እና የሚረብሽ አይነት ነው፡፡ ከከተማ ወጣ ብሎ የሰሜኑ ንፋስ የጠነከረ ይመስላል። ተክለሀይማኖት ቤተክርሲቲያኑ በራፍ ጋር ስትደርስ መኪናዋን ጥግ አስይዛ አቆመችና መጀመሪያ ተሳለመች…ከዛ ቀጥታ ወደ መቃብር ስፍራዎች ነው ሄደችው። ወደ እናቷ መቃብር ሄዳ አታውቅም ስለዚህ የመቃብር ድንጋዬች ላይ የተጻፉትን ፅሁፎች እያነበበች መፈለግ ጀመረች፡፡ከአስር ደቂቃ አሰልቺ ሚመስል ፍለጋ በኋላ ተሳካላትና አገኘችው፡፡የእናቷ የመቃብር ድንጋዮች ላይ የበቀሉት ሣሮች ረዥም እና አረንጓዴ ናቸው፡፡
ወደመቃብሩ ለመጠጋት ፈራች …ከእናቷ መንፈስ ጋር ለማውራት ዝግጁ የሆነች አልመሰላትም፡፡አራት ማዕዘን ቅርጽ ያለው የእምነበረድ ምልክት ከመቃብሩ አናት ተተክሏል፡፡ የእናቷ ሙሉ ስም ፤ የእናቷን የትውልድ ቀን እና የሞት ቀን ተፅፎበታል፡፡እሰከዛሬ አይታ የማታውቀው ውብ የሚባል ፎቷዋ ከፅሁፎቹ በላይ አለ - ሌላ ምንም ነገር የለውም. ፡፡

‹‹ሩጫዬን ጨርሼለሁ….››የመሰለ አንድ ጥቅስ እንኳን ከስር ቢያሰፍሩበ ስትል አሰበችና ልቧ አዘነባት።መልሳ ስታስበው እርባን የሌለው ነገር እንደሆን ሲገባት ቅሬታዋን ሰረዘችው፡፡

እናቷ ሰሎሜ በጣም ወጣት እና ቆንጆ እና ሙሉ ተስፋ የነበራት ሴት ነበረች፣ነገር ግን ማንነቷ በተገቢው መንገድ እንዳይገለፅ በአጭሩ እንድትቀጭ ተደርጓል፡፡ ከመቃብር አጠገብ ተንበረከከች። በእናቷ ቀብር አጠገብ ምንም አይነት ሌላ የቅርብ ዘመድ መቃብር ባለመኖሩ ቅር አሰኛት፡፡እሷ የሚሰማትን አይነት ብቸኝነት እናቷም የሚሰማት አድርጋ ነው የወሰደችው፡፡ በውትድርና አገልግሎት ላይ እያለ የሞተ አባቷ አስከሬን እዛው በተሰዋበት ጦር ሜዳ ነው የተቀበረው፡፡ሰሎሜ ገና  ልጅ እያለች የሞተው አያቷ በትውልድ ከተማው
ኮፈሌ ነው የተቀበረው።በዚህ የተነሳ የሰሎሜ መቃብር ብቸኛ ነበር። ድንጋዩን ስተነካው ከጠበቀችው በላይ ቀዝቃዛት . የእናቷን የመጀመሪያ ስም የተቀረጹትን ፊደሎች በጣቷ እየዳበሰች መረመረች፣ ከዚያም የልቧ ምት እንደሚሰማት እጇን ከፊት ለፊቱ ባለው ሳር ላይ ጫነች።ከተፈጥሮ በላይ በሆነ መንገድ ከእሷ ጋር መነጋገር እንደምትችል ማሰቧ ሞኝነት መስሎ ተሰማት ፣ ነገር ግን የደረቀ ሳር መዳፏን ሲወጋ "እናቴ" ብላ ወደቀልቧ ተመለሰች።

"ማማ. እማዬ." ስሞቹ ለምላሷ እና ለከንፈሯ እንግዳ ነገር ሆኖ ተሰሟት። ከዚህ በፊት በየትኛውም አጋጣሚ ተጠቅማበት አታውቅም።በዚህ ጊዜ ከጎን በኩል ስሟ ሲጠራ ሰማች…ግራ ገባት..የሆነ እርኩስ መንፈስ ሊተናኮላት እየሞከረ ነው የመሰላት…፡፡
"አሌክስ….›› በድንጋጤ ዙሪያውን ተመለከተች..በዚህ ስም የአዲስአበባ አብሮ አደግ ጓደኞቾ ናቸው የሚጠሯት፡፡እንዴት እዚህ ተገኙ። ሚመታው ልቧ ላይ እጇን እየጫነች፣ በፍርሃት ተንፈሰች።ዞር ስትል ያልጠበቀችውን ሰው ነው ያገኘችው፡፡

" አስደነገጥከኝ … እዚህ ምን እየሰራህ ነው?"
ጁኒየር ፍሰሀ አጠገቧ ተንበርክኮ በመቃብሩ ቆሚ ድንጋይ ላይ እቅፍ አበባ አስቀመጠ። ለአፍታ በራሱ ጥሞና አቀረቀረና ከዛ ፊቱን ወደ አለም አዙሮ ፈገግ አለላት፡፡

"በደመ  ነፍስ  ወደ  አረፍሽበት  አፓርታማ  ደውዬ  ነበር…ነገር  ግን  ስልኩ  የሚያነሳ አልነበረም።"
"የነበርኩበትን ሆቴል ለቅቄያለው … የት እንደገባው እንዴት አወቅክ?"

"በዚች ከተማ ውስጥ ስለሚከወነው ሁሉም ነገር መረጃውን በቀላሉ ማግኘት እችላለው ." "ወደ መቃብር ስፍራ እንደምመጣ ግን ማንም አያውቅም።››

" በአንቺ ጫማ ውስጥ ብሆን የት እንደምሆን  ለመገመት  ሞከርኩኝ. በመምጣቴ እንዳላስደበርኩሽ አገምታለው."

"አይ. ምንም አይደለም…አሌክስ ስትለኝ እኮ በጣም ነው ግራ የተጋባሁት."

‹‹እንዴ ለምን?››

‹‹በዚህ ስም የተወሰኑ የቅርብ ጓደኞቼ ብቻ ናቸው የሚጠሩኝ…እዚህ እንግዳ በሆንኩበት ከተማ ይሄን ስም ተጠቅሞ የሚጠራኝ ሰው ይኖራል ብዬ እንዴት ልገምት?››

‹‹ያው እኔም ጓደኛሽ ለመሆን ካለኝ ጉጉት የተነሳ ነው ይሄን ስም የተጠቀምኩት…ባለፈው እዛ ፍርድ ቤት እራስሽን ስታስተዋውቂን ስሜ አለም ይባላል..ጓደኞቼ አሌክስ ብለው ይጠሩኛል ስትይ …እኔም አሌክስ የሚለውን ስም ስለተመቸኝ ቀለብ አድርጌ በምናቤ አስቀመጥኩት››

‹‹አይ ጥሩ ነው..ደስ ብሎኛል….ብዙ ጊዜ ወደ እናቴ መቃብር አበባ ታመጣለህ ?"ስትል ጠየቀችው፡፡

ፈጥኖ አልመለሰላትም።

" በተወለድሽበት ቀን ሆስፒታል ነበርኩ፣ ከመታጣብሽ በፊት ከነደምሽ አይቼሻለሁ።" አላት፡፡ፈገግታው ክፍት እና ሞቅ ያለ ነው፣

‹‹ጥሩ ..እሺ መጀመሪያውን ጥያቄ መልስልኝ፣ብዙ ጊዜ አበቦችን እዚህ ታመጣለህ?."

" በበዓላቶች ቀን ብቻ ነው ። እኔ ፤ አባቴ እና ኩማንደር ገመዶ በልደቷ፣ ገና፣ ፋሲካ፣ሲሆን አንድ ላይ እናመጣለን። መቃብሯን ለመንከባከብ የሚያስፈልገውን ወጪ በጋራ እንሸፍናለን።"

"ለምን ?የተለየ ምክንያት አላችሁ?"
ያልተለመደ  አይነት  አሰተያየት  አያት….ከዛ  "ሁላችንም  እናትሽን እንወዳታለን…ምክንያታችን ያ ነው፡፡›› ሲል መለሰላት፡፡

ለስለስ  ባለ  የድምፅ  ቃና  "የሚገርመው  ግን  ከእናንተ  አንደኛችሁ  እንደገደላችኋት አምናለሁ" አለችው ።

" ተሳስተሻል አሌክስ ፤እኔ አልገደልኳትም።"

"አባትህስ?

እሱ ያደረገው ይመስልሃል?"

ራሱን  በምሬት  ነቀነቀ "አባቴ  እንደ ሴት ልጅ ነበር ሚንከባከባት፡፡. እሷም እንዲሁ እንደአባቷ ነበር የምታየው."

"እና ኩማንደር ገመዶስ?"

ማብራርያ የማያስፈልግ መስሎት ትከሻውን ነቀነቀ። "ገመዶ ፈጽሞ ሊገድላት አይችልም ››
አለም በእጇ አንጠልጥላ የነበረውን ባለ ፀጉር ጃኬቷን ለበሰች ። ፀሀይዋ እየጠለቀች ነበር፣
"ዛሬ ከሰአት በኋላ በሕዝብ ቤተመጻሕፍት ውስጥ የተወሰነ ጊዜ አሳልፌ ነበር፣ የቆዩ የሀገር ውስጥ ጋዜጣ እትሞችን መለስ ብዬ ለማንበብ ሞክሬያለው።"

"ስለ እኔ የሆነ ነገር አገኘሽ?"

"ኦህ አዎ፣ ስለከነማ እግር ኳስ ቡድን ተሳትፎህ ሁሉም ነገር ተፅፏል።;;›› ተንከትክቶ ሳቀ.. ንፋሱ ቆንጆ ጸጉሩን አውለበለበለት፡

"አንተ እና ገመዶ የቡድኑ ዋና እና ምክትል አንበል ነበራችሁ።"

"በሚገርም ሁኔታ አዎ…..የማይበገሩ፣ እውነተኛ እግር ኳስ ተጫዋቾች እንደሆን ነበር የምናስበው።"

" በጊዜው ወጣት የነበረችው እናቴ ወደ ቤታችሁ የምትመጣ ንግስት ነበረች። በእረፍት ሰአት ከገመዶ ጋር ስትስማት የሚያሳይ ፎቶ አይቼያለሁ።››

ያን ፎቶግራፍ ባየች ጊዜ እንግዳ ነገር ነበር የተሰማት። በፊት አይታው አታውቅም ነበር። በሆነ   ምክንያት   አያቷ   ከብዙዎቹ   ጋር   ላለማቆየት   መርጣለች፣ ለብዙ ደቂቃዎች ፎቶግራፉን ካየች በኋላ እናቷ ሳትሆን እራሷ እንደሳመችው ይሰማት ጀመር። ወደ አሁኑ ጊዜ ስትመለስ፣ "እስከእዛን ጊዜ ድረስ ከእናቴ እና ከገመዶ ጋር ጓደኛ አልነበርክም አይደል?"ስትል ጠየቀችው፡፡

ጁኒየር የሳር ቅጠል አነሳና በጣቶቹ በመቆራረጥ ማውራት ጀመረ። "ዘጠነኛ ክፍል እስክደርስ ድረስ በኩየራ በሚገኝ አንድ አዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ ነበር የምኖረው"

"በምርጫህ?"
43👍6🔥1
"አይ፣የእናቴ ፍላጎት ነበር፡፡ ያልተፈለገ ባህሪ አንዳለምድ በማለት በውድቀት ለሊት ሻንጣዬንና የትምህርት ቁሳቁሶቼን አሸክማ ወደ አዳሪ ትምህርት ቤት ላከችኝ ።ከስምንተኛ
ክፍል ወደዘጠነኛ ከተዘዋወርኩ በኃላ ግን ጎረመስኩ መሰለኝ..በፍፅም ወደእዛ አዳሪ ትምህር ቤት አልመለሰም ብዬ አመፅኩ ..የአባቴን ድጋፍ አገኘሁና እዚሁ ሻሸመኔ ሀይእስኩል ተመዘገብኩ፡፡››

'"እናትህ ምን አለች?"

" ደስ አላላትም ነበር…በግልፅም ተቃውማ ነበር፡፡በወቅቱ ነገር ግን በወቅቱ በዚህ ጉዳይ ላይ ማድረግ የምትችለው ብዙ ነገር አልነበረም.፡፡አባዬ እኔን በእዚሁ ሀይእስኩል ማስመዝገብ ብቻ ሳይሆን  ወደ ከነማው ታዳጊዎች እግር ኳስ ቡድን እንድቀላቀል አጥብቆ ይፈልግ ነበር።በወቅቱ የነበረው አሰልጣኝ ግን እኔ ላይ ብዙም ፍላጎት አላሳየም ነበር፣ ነገር ግን አባዬ ለቡድኑ አዲስ ዩኒፎርም እንደሚገዛ ቃል በመግባት ጉቦ ሰጠው። አሰልጣኙም ተቀበለኝ ፡፡..ጁኒየር እየሳቀ ታሪኩን ቀጠለ ‹‹ስለዚህ ለእግር ኳስ ብድኑ አባል ሆንኩ፡፡ የመጀመርያው የልምምድ ቀን ሊያባረረኝ ተቃርቦ ነበር። ሌሎቹ የቡድኑ አባላትም በእንቅስቃሴዬ ደካማነት ብቻ ሳይሆን በከተማው ውስጥ በጣም ሀብታም የሆነ ሰው ሰውዬ ብቸኛ ወንድ ልጅ በመሆኔ ተበሳጩተውብኝ እንደነበረ አስታውሳለው?"

‹‹እንዴት ተቀበልከው ታዲያ?››

"የሀብታም ልጅ መሆን በጣም ከባድ ስራ ነው፣ ግን አንድ ሰው የግድ ያንን ስራ መስራት አለበት" አለ በሚስብ ፈገግታ። " ለማንኛውም፣ ወደቤት ተመለስኩና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱንም እና እግር ኳስን ቡድኑን በጣም እንደምጠላ ለአባቴ ነገርኩት። እንደ ገመዶ አይነቱን ጉልበተኞች እና ትቢተኛ ወጣቶች ጋር ከመዋል ይልቅ አዳሪትምህረት ቤት ካሉ የገረጡ ትንንሽ ፊት ያላቸውን ደካሞች ጋር መኖር እንደምመርጥ ነገርኩት።"

"በቀጣይ ታዲያ ምን ሆነ፧?"

"እናቴ ራሷን ታማ አለቀሰች። አባቴ በንዴት ራሱን ሳተ። ከዚያም ወደ ውጭ አወጣኝ እና እጆቼ ለመያዝ እስኪዝል ድረስ የኮስ ልምምድ እንዳደርግ አስገደደኝ››

"አስፈሪ ነበር?"

"በእርግጥ አይደለም። ፍላጎቶቼን በልቤ ቀብሬ እንጂ ጥሩ ተጫወች መሆን እፈልግ ነበር ። ባይሳካልኝ እንኳን እዚህ ውጭ መጫወት፣ መብላት፣ መጠጣት እና መተኛት እንዳለብኝ አውቅ ነበር።….መሄድ ትፈልጊያለሽ?"

"አይ፣ ጫወታህን እንድትቀጥል እፈልጋለሁ።" "ይህ መደበኛ ምርመራ ነው እንዴ?"

በቁጣ በታከለበት ፈገግታ።"ውይይት ብንለው ይሻላል" ስትል መለሰችለት፣

"ከዛ በእግር ኳስ ክለቡ ያለህን ተሳትፎ ቀጠልክ ?››ብላ ጀምረው ወደነበረበት የጫወታ ርዕስ መለሰችው፡፡

ጁኒየር ‹‹አዎ፣ እኔ ግን በአንድ ጨዋታ ውስጥ እንኳን አልተጫወትኩም፣ ነበር። ለአውራጃ ሻምፒዮን ሺፕ አልፈን ነበር።"አንገቱን ዝቅ አደረገ እና ፈገግ አለ። ‹‹ከዛ ዋንጫ ጫወታ ቀን ደረሰ…ቡታጅራ ነበር ጫወታው፡፡ቀድመው አገቡብን.. ልንሸነፍ ሆነ … በሰዓቱ ላይ ጥቂት ሰከንዶች ብቻ ቀሩ። ››አሰልጣኙ ወደ ቤንች ሲመለከት እኔን አየ፣ከዛ ስሜን ጮኸ ተጣራ። ከፍራቻዬ የተነሳ በሱሪዬ ላይ መሽናት ነበር የቀረኝ››

"ከዛ እንዴት ሆነ?፧"በጉጉት ጠየቀችው፡፡
እንደምንም እራሴን አጠነካክሬ ቡድኑን ለመቀላቀል ሮጬ ወጣሁ። በሜዳው ላይ ያለው ንጹህ ማሊያ የኔ ብቻ ነው።ገመዶ ሜዳ ውስጥ ነበር" አለም ከጋዜጣ ዘገባዎች ይህን ታውቅ ነበር.

"አዎ የኔ መሲህ። መምጣቴን ሲያይ አቃሰተ፣ እና አሰልጣኙ የነገረኝን የጨዋታ ታክቲክ ለውጥ ስነግረውም ጮክ ብሎ ዓይኖቼን መሀል እያየኝ ኀእንዲህ አለኝ። ፣ ከጎሉ በግራ በክል ሁን ፣ እንደምንም ብዬ ኳሷን ወደአንተ ልካታለው…ወደጎል ለጋት..እርግጠኛ ነህ ታደርገዋለህ››አለኝ…ለአፍታ ጁኒየር ዝም አለ፣ ትዝታ ውስጥ ሰጥሟል።
"የዛን ቀኑን ሁኔታ በህይወት እስካለው ድረስ መቼም አልረሳውም። ከዛ ያገኘነውን ቅጣት ምት ሲመታ ገመዶ እግር ስር ነው ያረፈው …ሁለት ተጫዋቾችን ሸውዶ አለፈና ከእኔ ተሻለ ሁለት አማራጭ እያለው ለእኔ አቀበለኝ……በደመነፍስ ወደጎሉ ላኳት …የተዘናጋውን በረኛ አለፈችና መረብ ላይ አረፈች፡፡ከዛ በኃላ የሆነውን ነገር ምን ብዬ ላስረዳሽ ››

"አባትህ ደስተኛ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ."

ጁኒየር አንገቱን ወደ ኋላ ነቀነቀና እና እንባ አስኪወጣው ሳቀ ።

"አጥሩን ዘሎ ወንበሩን ጥሎ ወደ ሜዳው ቀረበ ..ሜዳው ውስጥ መግባት ነው የቀረው፡፤

"እናትህስ?"

"እናቴ! የእግር ኳስ ጨዋታ ብትሞት እንኳን ማየት አትፈልግም ።የአረመኔዎች ጫወታ ነው ብላ ታስባለች።ግን ከአባቴ በስተቀር ማንም ስለ እኔ ምን ቢያስብ ግድ አልነበረኝም። በዚያ ምሽት በጣም ነበር የኮራብኝ ።ጥቋቁር አይኖቹ በማስታወስ ያበሩ ነበር።ከዛ በፊት ገመዶን አግኝቶ አያውቅም ነበር፣ ነገር ግን በእለቱ የእግር ኳስ አባላትን እና ሁሉንም አቀፋቸው። ያ ምሽት የጓደኝነታችን መጀመሪያ ነበር። ብዙም ሳይቆይ የገመዶ አባት ሞተ፣ እና ወደ እኛ ቤት መጥቶ እንዲኖር ምክንያት ሆነው ።››

ለተወሰነ ደቂቃ በመሀከላቸው ፀጥታ ሰፈነ….ዝም ብሎ በፅሞና ሲመለከታት ቆየና "ጌታ ሆይ፣ በዚያን ጊዜ የነበረችውን ሰሎሜን ትመስያለሽ" አለ በለሆሳስ። "በባህሪ ብዙ አትመሳሰሉም , ነገር ግን የአንቺ አገላለጽ. ከእርሷ ጋር ተመሳሳይ ነው..በዛ ላይ ሁለታችሁም ተመሳሳይ አይነት የማዳመጥ ጥራት አላችሁ." እጁን ዘርግቶ ፀጉሯን ነካ። "እሷም እንደአንቺ ማዳመጥ ትወድ ነበር።ቢያንስ የሚያወራውን ሰው እደተረዳችው እንዲያስብ ታደርጋዋለች። ዝም ብላ ለሰዓታት ማዳመጥ ትችላለች"

"መጀመሪያ ወደ እሷ የሳበህ ያ ነው?"

" አይ" አለ በሚገርም ፈገግታ። "ወደ እሷ የሳበኝ የመጀመሪያው ነገር ዘጠነኛ ክፍል እያለው የወንድ ልጅ የጉርምስና ምኞት ነበር። ሰሎሜ ለመጀመሪያ ጊዜ በትምህርት ቤት አዳራሽ ውስጥ ሳያት ቀልቤን ነበር የሰለበችው፣ በጣም ቆንጆ ነበረች።"

" አሳደድካት?"

"ሄይ፣ ደንግጬ ነበር እንጂ አላበድኩም።የገመዶ ፍቅረኛ ነበረች" አለ በማያሻማ ሁኔታ።

‹‹ስለዚህ ምንም ጥያቄ አልነበረም››

" ተነሺ። ብንሄድ ይሻለናል:: ብርዱ ኃይለኛ እየሆነ ነው:: በዛ ላይ ጨለማው እየጠነከረ ነው.››
አለም ከተቀመጠችበት ቀድማ ተነሳች…ተክትሏት ተነሳ፡፡"ጁኒየር አበቦቹን ስላመጣህ አመሰግናለሁ."አለችው

"ምንም አይደል።"

"ለእሷ ያላህን ለዘመናት የማይደበዝዝ አሳቢነት አደንቃለሁ."

"በእውነቱ ከሆነ ዛሬ ወደዚህ የመጣሁበት ድብቅ ምክንያት ነበረኝ።" "ወይ?"

"ኡህ-ሁህ"  አለ  ሁለቱንም  እጆቿን  በመያዝ"  ወደ  ቤታችን  ለእራት  ልጋብዝሽ ነበር››አላት..ሀሳቡ ቀደም ብሎ ያሰበበት ሳይሆን ድንገት የመጣለት ነው፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
32👍25