#እድሜን_ያሸነፈ
እድሜ ሚሉት ቋጥኝ
በእርጅና መዳፉ አካሌን ደርምሶ
ውበቴን
አጥንቴን ስጋየን አኩስሶ
እንደ ሃር ነዶ
የጠቆረ ጠጉሬን ከበረዶ አንፅቶት
ለስላሳ አካላቴን
እሳት የገረፈው ፌስታል አስመስሎት
ባምሳሉ የተሰራ
ቁመና ወበቴን ሸብሽቦ አበላሽቶት
በጊዜ ዳኝነት ሁሉም ተበይኖ
የነበረው ሁሉ እንዳልነበር ሆኖ
ዘመን አሸንፎት ቀና ያለው ሁሉ እያቀረቀረ
ያንቺ ፍቅር ብቻ በልቤ ላይ ፀበል እየተነከረ
ዘመንን ረግጦ እንደ ፅጌሬዳ እንደፈካ ቀረ።
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
እድሜ ሚሉት ቋጥኝ
በእርጅና መዳፉ አካሌን ደርምሶ
ውበቴን
አጥንቴን ስጋየን አኩስሶ
እንደ ሃር ነዶ
የጠቆረ ጠጉሬን ከበረዶ አንፅቶት
ለስላሳ አካላቴን
እሳት የገረፈው ፌስታል አስመስሎት
ባምሳሉ የተሰራ
ቁመና ወበቴን ሸብሽቦ አበላሽቶት
በጊዜ ዳኝነት ሁሉም ተበይኖ
የነበረው ሁሉ እንዳልነበር ሆኖ
ዘመን አሸንፎት ቀና ያለው ሁሉ እያቀረቀረ
ያንቺ ፍቅር ብቻ በልቤ ላይ ፀበል እየተነከረ
ዘመንን ረግጦ እንደ ፅጌሬዳ እንደፈካ ቀረ።
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
YouTube
አትሮኖስ_ Tube
Share your videos with friends, family, and the world
❤14👍3
ቀናሁ
ለመንኩት አምላክን
አበባ እንዲያደርግሽ
ንብ ሆኜ መጥቼ
እየዞርኩ ልቀስምሽ
ማለዳ ማለዳ
በበራፋችሁ ሳልፍ
ብመለከት ጊዜ
ፀሀይ ስትሞቂ
ፈጣሪን ለመንኩት
"ፀሀይ አርገኝ "ብዬ
ውብ ሠውነትሽ ላይ
እንዳርፍ ዘና ብዬ፡፡
ያንገትሽ ማተብ
ያለ ማንም ከልካይ
ገብቶ ሲንከላወስ
በጡቶችሽ ክፋይ
ብመለከት ጊዜ...
ቀናሁ በማተብሽ
ቀናው በመስቀሉ
ጡትሽን ተንተርሶ
በመዋል በማደሩ፡፡
ቅዳሜ እረፋድ ላይ
ስትመጭ ከገበያ....
ትኩስ ለጋ ጎመን
በክንድሽ ታቅፈሽ
በሌላኛው እጅሽ
ዘንቢል አንጠልጥለሽ..
ብመለከት ጊዜ...
እንደ ጎመን መሆን
ተመኘው ለቅፅበት
በአካሌ እንዲሠራጭ
የአክናድሽ ሙቀት
ተመኘው ለቅፅበት
መሆን እንደ ዘንቢል
ውብ ለሥላሳ ጣትሽ
በገላዬ እንዲውል፡፡
ትናንትና ደግሞ..
ከኛ ቤት ፊት ለፊት
ውሐ ስትቀጂ
ከየት እንደ መጣ
ያልታወቀ ንፋስ
ቀሚስሽን ገልቦ
ጀምበር የመሠለ
ያ ውቡ ጭንሽን
ቢያሳየኝ በስሱ
እምልልሻለው
ቀናሁ በንፋሱ፡፡
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ለመንኩት አምላክን
አበባ እንዲያደርግሽ
ንብ ሆኜ መጥቼ
እየዞርኩ ልቀስምሽ
ማለዳ ማለዳ
በበራፋችሁ ሳልፍ
ብመለከት ጊዜ
ፀሀይ ስትሞቂ
ፈጣሪን ለመንኩት
"ፀሀይ አርገኝ "ብዬ
ውብ ሠውነትሽ ላይ
እንዳርፍ ዘና ብዬ፡፡
ያንገትሽ ማተብ
ያለ ማንም ከልካይ
ገብቶ ሲንከላወስ
በጡቶችሽ ክፋይ
ብመለከት ጊዜ...
ቀናሁ በማተብሽ
ቀናው በመስቀሉ
ጡትሽን ተንተርሶ
በመዋል በማደሩ፡፡
ቅዳሜ እረፋድ ላይ
ስትመጭ ከገበያ....
ትኩስ ለጋ ጎመን
በክንድሽ ታቅፈሽ
በሌላኛው እጅሽ
ዘንቢል አንጠልጥለሽ..
ብመለከት ጊዜ...
እንደ ጎመን መሆን
ተመኘው ለቅፅበት
በአካሌ እንዲሠራጭ
የአክናድሽ ሙቀት
ተመኘው ለቅፅበት
መሆን እንደ ዘንቢል
ውብ ለሥላሳ ጣትሽ
በገላዬ እንዲውል፡፡
ትናንትና ደግሞ..
ከኛ ቤት ፊት ለፊት
ውሐ ስትቀጂ
ከየት እንደ መጣ
ያልታወቀ ንፋስ
ቀሚስሽን ገልቦ
ጀምበር የመሠለ
ያ ውቡ ጭንሽን
ቢያሳየኝ በስሱ
እምልልሻለው
ቀናሁ በንፋሱ፡፡
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
Telegram
አትሮኖስ
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።
Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳

❤12👏7😁5
ድርሳነ ፍቅር!
አንቺ የእኔ ጣዖት!
እኔ ያንቺ አማኝ
የምዕመኑ ጠሎት ቅዳሴና አዛኑ
በየት በኩል ይሰማኝ?
እሳት ያንቺ ገላ መብረቅ ያንቺ መውደድ
በየት መንገድ ልጓዝ እምን ላይ ልራመድ?
ዓይኖችሽ ጉልላት
ጥርሶችሽ በረዶ
ጣቶችሽ አለንጋ....
ሠንበር የወረሰው ቁስል ልቤን ይዤ
እንደምን አልሰጋ?
እኔ
መድሀኒቴ አንቺ
በሽታዬም አንቺ
አንቺን እየዋጥሁኝ አንቺን የምታመም
ባንቺ እየታመምሁኝ ባንቺ የምታከም
ባለ አንድ ድዌያም ባለ አንድ ክኒና
ወይ አልሞት ፥ ወይ አልድን
ወይ አልኖር በደህና!
🔘ሚካኤል አስጨናቂ🔘

❤11👍9👎1
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///
አለም የሆቴሉን የተወሰነ ክፍል አገልግሎት ዝርዝር የሚያሳየውን ካርድ አንስታ ተመለከተች። የአርብ ምሽት የአካባቢው ዘመናዊና ባህላዊ ባንድ በጥምረት ከምሽቱ አንድ ሰዓት እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ የሙዚቃ ድግስ እና ትርኢት ያሳያሉ።
ክፍል 125 ተከራይታ ጓዟን አሳረፈችና ልብሷን መቀያየርና እራሷን ማስዋብ ጀመረች፡፡ የመዋቢያ እቃዎቾን ከያዘው ሻንጣ ግርጌ ላይ የጥፍር መቁረጫ አገኘች። ጥፍሯን ከሞረደች በኃላ አለባበሷን እና ጠቅላላ አቋሟን ለማየት መስታወት ፊት በመቆም ለመጨረሻ ጊዜ እራሷን ተመለከተች...።
በምትገናኛቸው ሰዎች ላይ የመጀመሪያ አስደናቂ የስሜት ትስስር ለመፍጠር ትፈልጋለች። ማንነቷን ስትነግራቸው በጣም እንደሚገረሙ እርግጠኛ ነች፣ ነገር ግን የበለጠ ጠንካራ ተጽእኖ መፍጠር ፈልጋለች።ከዚህ ቀደም ከሚያውቋት ሴት ጋር እንደሚያነፃፅሯት ጥርጥር የለውም። እሷ ያንን መከላከል አትችልም፤አትፈልግምም፡፡. እሷን በትክክል መመዘንና መገምገም ከቻሉ እርግጠኛ ነች ሰሎሜ ጎይቶምን ለማስታወስ ይገደዳሉ ።የምትለብሰውን በጥንቃቄ መርጣለች። ሁሉም መዋቢያዎችና ጌጣጌጦች በተገቢው ልኬትና መጠን ተጠቅማለች፡፡በዛም የተነሳ በጣም ጥሩ የሚባል የተለየ እይታ እና ልዩ አይነት ውበት እንደተላበሰች ተሰምቷታል ። ሴትነቷን በጥበብ አጉልቶ የሚያሳይ ልዩ አይነት ብርሀን የሚንቦገቦግባት የውበት መቅረዝ ነው የምትመስለው፡፡
ግቧ መጀመሪያ እነሱን ማስደነቅ ነበር፣ እዚህ ወደ ሻሸመኔ በመምጣቷ እንዲገረሙ ብቻ ሳይሆን በዛው ልክም እንዲደነግጡ ነው የምትፈልገው።ከመጣችበት የሀገሪቱ ዋና ከተማ አዲስአበባ ጋር ሲነፃፀር ሻሸመኔ የአንድ ክፍለከተማን ያህል እንኳን ስፋት የሌላት ከተማ ነች፡፡ግን ደግሞ በሀገሪቱ ካሉ ማንኛውም ከተሞች የበለጠ ፤ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚደረግባት…በየቀኑ በሚሊዬን የሚቆጠሩ ሰዎች ገብተው የሚወጡባት በጣም ደማቅ ከተማ ነች፡፡እና አሁን ፊት ፊት የምትጋፈጣቸው ሰዎች የዚህ ከተማ የጡት አባት ተደርገው የሚታዩ….ናቸው፡፡
አለም ያሰበችው ስራ በስኬት ካጠናቀቀች በሀገሪቱ የመገናኛ ብዙሀን ዜናዎችን በዋናነት የሚቆጣጠር ርዕሰ አንቀፅ እንደሚሆን እርግጠኛ ነች።ለበርካታ ደቂቆች መኝታ ክፍሏ ባለው መስታወት ፊት እየተሸከረከረች መልኳን ሆነ ጠቅላላ ቁመናዋን ደጋግማ ካየች በኃላ ሁለ ነገሯ እንከን ሊወጣለት እንደማይችል በመደምደም የእጅ ቦርሳዋን ትከሻዋ ላይ አንጠልጥላ ፣ የፍይል መያዣ ፎልደሯን አነሳችና እና የክፍል ቁልፍ እንደያዘች እርግጠኛ ሆና ወጣች፡፡ የክፍሉን በር ዘጋችው። የሆቴሉን ህንፃ ለቃ ወጣችና ቀጥታ ወደመኪናዋ በመግባት መሃል ከተማውን እየሰነጠቀች ወደቀጠሮ ቦታ መንዳት ጀመረች፡፡ይሄንን ስብሰባ ያዘጋጀላት የዞኑ ዋና አቃቢ ህግ ነው፣ያንንም ስላደረገላት ለእሱ ታላቅ ምስጋና አላት፡፡ የትምህርት ቤት መለቀቂያ ሰዓት ስለሆነና ..አስፓልቱን በሰዎችና በተማሪዎች ስለተጨናነቀ እንድልቧ በፈለገችው ፍጥነት ለመንዳት ከባድ ሆኗባት ነበር፡፡
አለም ወደእዚህች ውብ ከተማ የመጣችው ለጉብኝት አይደለም፡፡ወይንም ዓላማዋን ከግብ እስክታደርስ ድረስ በእንግድነት አይደለም፡፡የከተማዋ ምክትል አቃቢ ህግ ሆና በመመደቧ ምክንያት ነው የመጣችው፡፡የትምህርት ዝግጅቷን እና ብቃቷን በማየት ይህን ሹመት የተሰጣት የአካባቢውን ህብረተሰብ ፍትህ እንዲያገኝ እንድታግዝ ነው፡፡ የእሷ ተልእኮ ግን የተለየ ነው፡፡የራሷ የሆነ አላማ እና ፍላጎት ባይኖራት ኖሮ በሞያዋ ለመስራትና ለማገልገል ከአደገችበት እና እድሜዋን ሙሉ ካሳለፈችባት አዲስአበባ እግሯን አታነሳም ነበር፡፡ የእሷ ተልእኮ እና ዓላም ለህብረተሰቡ ምንም ረብ እንደሌለው ስታስብ ትፀፀታለች። እሷ ለምን ወደእዚህ እንደመጣች ባስታወሰች ጊዜ የሚሰማትን የጥፋተኝነት ስሜት ነው፤ግን ደግሞ ምርጫ የላትም፡፡
በህይወቷ ውስጥ ወደዚህ ደረጃ እንድትደርስ ገፊ ምክንያት የሆናትን ጉዳይ ለአንድ ሰከንድ እንኳን ከረሳች እና ችላ ካለች ራሷን መቼም ይቅር ለማለት አትችልም፡፡ አካባቢው ስትደርስ ወደቀኝ ታጠፈችና ወደመዘጋጃ የሚወስደውን ጠባብ የአስፓልት መንገድ ተያያዘችው፡፡መዘጋጃ ጽ/ቤት ከመድረሷ በፊት አሁንም ወደቀኝ ታጠፈችና ከቀበሌ ጽ/ቤት ጎን ካለው የፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ መኪናዋን አስገባችና ምቹ ቦታ ፈልጋ በማቆም
… ሞተሩን አጥፍታ ቦርሳዋንና የፋይል ፎልደሯና ይዛ ወረደች፡፡ በግቢው ውስጥ ያሉ የቢሮ ሰራተኞች ሆኑ የባለጉዳይ አይኖች ሁሉ እሷ ላይ ሲንከራተት ይታወቃታል…ብዙም ትኩረት ያልሰጠቻችው በማስመሰል ወደውስጥ ገባች፡፡
የፍርድ ቤቱን በር አልፋ ወደውስጥ ገባች፡፡ የተላላጠ ቀለምና የተፋፋቀ ግድግዳ እያየች ኮሪደሩን አቋርጣ ወደአንድ ክፍል ገባች፡፡
የፍርድ ቤቱ እንግዳ ተቀባይ የተለየ አይነት ሽቶ ስለሸተተው በደስታ ካቀረቀረበት ቀና አለ
…ቆንጆ መልክና ማራኪ አለባበስ የለበሰች ውብ ሴት ወደእሱ ስትመጣ ተመለከተ..ለሴቶች ስስ ልብ ያለው ወጣት ፀሀፊ በተቀመጠበት ተቁነጠነጠ፡፡
….አለም ወደፀሀፊው እየተራመደች በጎሪጥ ቀጣዩን ቢሮ በጉጉት ተመለከተች።
ስሩ ደረሰችና ‹‹ጤና ይስጥልኝ››አለችው፡፡
‹‹አቤት የእኔ እመቤት ….እንዴት ነሽ….?ይሄንን የመሰለ ውበት ይዘሽ መቼስ ተከሰሽ አይሆንም ወደዚህ የመጣሽው?››አላት፡፡
‹‹አረ በፍፅም››ስትል መለሰችለት፡፡
‹‹እና ከሰሽ ነው?››
ስለመቅለብለብ እያሰበች ‹‹እንደዛም አይደለም››ስትል መለሰችለት፡፡
‹‹እና….እኔን ፈልገሽ ብቻ እንዳይሆን?››
ከንግግግሩ በላይ ጉንጭ ውስጥ እያላመጠ ያለው ማስቲካ ሲታኘክ የሚያሰማው ድምፅ ምቾት ነሳት።ቢሆንም ፈገግ አለችለትና ሌላ ነገር ለመናገር እየተቅለበለበ እያለ፡፡"እኔ ከዞኑ አቃቢ ህግ ቢሮ ነው የመጣሁት። ዋና አቃቢ ህጉ ክቡር ግርማ ጠያቂነት ክብሩ ዳኛው የጠሩት ስብሰባ ነበር ››
ፈጎ የነበረው ፊቱ ሲኮሳተር እና ልቅ የነበረው ንግግሩ ሲሰበሰብ ታወቃት….
"ከአቃቢ ህግ ቢሮ ሰው እንደሚልኩ ተነግሮኝ ነበር…ግን ተወክሎ የሚመጣው ሰው ወንድ ይሆናል ብለን ነበር የጠበቅነው"አላት፡፡
"እንደምታየው እኔ ነኝ የመጣሁት…ምነው የክብሩ ግርማ ምክትል መሆኔ አላሳመነህም?ነው ወይስ አላስደሰተህም?፡፡››ሰውዬው ሴት አውል ከመሆኑም በተጨማሪ የወንድ ትምክት እንዳለበት ተረዳች፡፡እናም አበሳጫት፡፡
ከተቀመጠበት አሻግሮ ጉልበቷ ጋር የቀረውን አጭር ቀሚሷን እየተመለከተ…"ደህና
..በቀጠሮ ሰዓት ነው የተገኘሽው። "ስሜ ቶሌራ ይባላል። ቡና ትፈልጊያለሽ? ››አላት ፡ የእሱን ግብዣ ችላ ብላ "የተጠሩት ሁሉም እንግዶች መጥተዋል?"
ከእሱ መልስ ከመስማቷ በፊት ከተዘጋው በር የፈነዳ ተንከትካች የወንዷች ሳቅ ተሰማ ።
‹‹አዎ…ሁሉም ተገኝተዋል!!››
‹‹ለቡናው አመሰግናለው….መግባት አለብኝ ››አለችና ቦታውን ለቃ ወደክፍሉ ተራመደች…አለም በህይወቷ ውስጥ በጣም ወሳኝ ለሆነው ስብሰባ ራሷን አበርትታ ወደ ቢሮ ተጠጋች።በስሱ ስታንኳኳ ሳቁ ተቋረጠና ፀጥታ ሰፈነ፡፡ገፋ አድርጋ አንገቷን አስቀድማ ወደውስጥ ገባች ፡፡በክፍሉ ውስጥ ያሉት ወንዶች ሌላ ወንድ ሲጠብቁ እንደነበረ ከተረጋጋ መንፈሳቸው በግልፅ መረዳት ችላ ነበር። በራፉን ተሻግራ ወደውስጥ በገባች ቅጽበት በራፉ ከኃላዋ ሲዘጋ ተሰማት፡፡.የአራት ሰዎች ጥንድ ስምንት አይኖች እሷ ላይ ተተከሉ….በሁሉም ላይ ተመሳሳይ አይነት ግራ የመጋባት እና የመደነቅ ስሜት አነበበች…የፈለገችውም እንደዛ እንዲሆን ነው፡፡

❤57👍5
ቀጥታ ሄደችና ባዷቸውን ካሉት ወንበሮች አንዱን ሳበችና ፎልደሩን የጠረጴዛው ጫፍ ላይ አስቀምጣ ከላይ የለበሰችን ኮት ቀስ ብላ በቄንጥ አወለቀችና የወንባሯ እጄታ ላይ አስተካክላ ከስቀመጠች በኋላ በእርጋታ ተቀመጠች….ይሄን ሁሉ ስታደርግ እነሱ ያለምንም ንግግር ትንፋሻቸውን ውጠው በመገረም ሲመለከቷት ነበር፣እሷም የፈለገችው ያንን ነው፡፡
ጤና ይስጥልኝ..ከዞኑ ዋና አቃቢ ህግ ቢሮ ክብሩ አቃቢ ህግ አቶ ግርማን ወክዬ ነው የመጣሁት ….ስብሰባው በእኔና እና በእናንተ መካከል ይደረጋል ማለት ነው፡፡››የሚል ያልተጠበቀ አይነት አጭር ማብራሪያ ሰጠች፡፡
ከመሀከለኛው ወንበር የተቀመጡት በእድሜያቸው መጨረሻ ላይ ሚገኙት አዛውንቱ ሰው"ምንም ችግር የለውም, ለአንቺ እና ለሀለቃሽ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ፍቃደኞች ነን…እኔ ዳኛ ዋልልኝ እባላለው፡፡እሱ የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኩማንደር ገመዶ ይባላል፡፡ሁለት ሰዎች ተራ በተራ እየጠቆመ። "እሳቸው አቶ ፍሰሀ ይትባረክ ይባላሉ እሱ ደግሞ ልጃቸው ጁኒየር ይባላል።የሶሌ ኢንተርፕራይዝ ዋና እና ምክትል ስራአስኪያጅና ባለቤት ናቸው፡፡የሶሌ ኢንተርፕራይ ማለት ከተማዋ የጀርባ አጥንት የሆኑትን በጣም
በርካታ ድርጅቶችን በጥምረት የሚያስተዳድር ግዙፍ ድርጅት ነው፡፡አቶ ፍሰሀ እና ልጃቸው በከተማዋ እጅግ የተከበሩ እና የተመሰገኑ ግለሰቦች ናቸው፡፡››ሲሉ የማስተዋወቅና የመግቢያ ንግግር አድርገው ከጨረሱ በኋላ ራሷን እንድታስተዋውቅ አይን አይኗን ይመለከቷት ጀመር፡፡
አለምም የዳኛውን ማብራሪያ በፅሞና ስታዳምጥ ከቆየች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እነዚህ ከፊት ለፊቷ ያሉትን ዳኛው የዘረዘሯቸውን ሶስት ሰዎች በማየቷ እንግዳ እና ሀይለኛ የማወቅ ጉጉት በውስጧ ሲንተገተግ ተሰማት፡፡በውስጧ ለእነሱ ያዳበረችው ጥላቻም ሲገለባበጥ ይታወቃታል፡፡ እነሱ ስለእሷ እና ስለ ስብሰባው አለማ ለማወቅ እንደጓጉ ሁሉ እሷም እነሱን ለማወቅ ፈልጋለች፣
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ጤና ይስጥልኝ..ከዞኑ ዋና አቃቢ ህግ ቢሮ ክብሩ አቃቢ ህግ አቶ ግርማን ወክዬ ነው የመጣሁት ….ስብሰባው በእኔና እና በእናንተ መካከል ይደረጋል ማለት ነው፡፡››የሚል ያልተጠበቀ አይነት አጭር ማብራሪያ ሰጠች፡፡
ከመሀከለኛው ወንበር የተቀመጡት በእድሜያቸው መጨረሻ ላይ ሚገኙት አዛውንቱ ሰው"ምንም ችግር የለውም, ለአንቺ እና ለሀለቃሽ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ፍቃደኞች ነን…እኔ ዳኛ ዋልልኝ እባላለው፡፡እሱ የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኩማንደር ገመዶ ይባላል፡፡ሁለት ሰዎች ተራ በተራ እየጠቆመ። "እሳቸው አቶ ፍሰሀ ይትባረክ ይባላሉ እሱ ደግሞ ልጃቸው ጁኒየር ይባላል።የሶሌ ኢንተርፕራይዝ ዋና እና ምክትል ስራአስኪያጅና ባለቤት ናቸው፡፡የሶሌ ኢንተርፕራይ ማለት ከተማዋ የጀርባ አጥንት የሆኑትን በጣም
በርካታ ድርጅቶችን በጥምረት የሚያስተዳድር ግዙፍ ድርጅት ነው፡፡አቶ ፍሰሀ እና ልጃቸው በከተማዋ እጅግ የተከበሩ እና የተመሰገኑ ግለሰቦች ናቸው፡፡››ሲሉ የማስተዋወቅና የመግቢያ ንግግር አድርገው ከጨረሱ በኋላ ራሷን እንድታስተዋውቅ አይን አይኗን ይመለከቷት ጀመር፡፡
አለምም የዳኛውን ማብራሪያ በፅሞና ስታዳምጥ ከቆየች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እነዚህ ከፊት ለፊቷ ያሉትን ዳኛው የዘረዘሯቸውን ሶስት ሰዎች በማየቷ እንግዳ እና ሀይለኛ የማወቅ ጉጉት በውስጧ ሲንተገተግ ተሰማት፡፡በውስጧ ለእነሱ ያዳበረችው ጥላቻም ሲገለባበጥ ይታወቃታል፡፡ እነሱ ስለእሷ እና ስለ ስብሰባው አለማ ለማወቅ እንደጓጉ ሁሉ እሷም እነሱን ለማወቅ ፈልጋለች፣
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
YouTube
አትሮኖስ_ Tube
Share your videos with friends, family, and the world
👍37❤17👏1
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
/////
ጤና ይስጥልኝ..ከዞኑ ዋና አቃቢ ህግ ቢሮ ክብሩ አቃቢ ህግ አቶ ግርማን ወክዬ ነው የመጣሁት ….ስብሰባው በእኔና እና በእናንተ መካከል ይደረጋል ማለት ነው፡፡››የሚል ያልተጠበቀ አይነት አጭር ማብራሪያ ሰጠች፡፡
ከመሀከለኛው ወንበር የተቀመጡት በእድሜያቸው መጨረሻ ላይ ሚገኙት አዛውንቱ ሰው"ምንም ችግር የለውም ለአንቺ እና ለሀለቃሽ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ፍቃደኞች ነን…እኔ ዳኛ ዋልልኝ እባላለው፡፡እሱ የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኩማንደር ገመዶ ይባላል፡፡ሁለት ሰዎች ተራ በተራ እየጠቆመ። "እሳቸው አቶ ፍሰሀ ይትባረክ ይባላሉ እሱ ደግሞ ልጃቸው ጁኒየር ይባላል።የሶሌ ኢንተርፕራይዝ ዋና እና ምክትል ስራአስኪያጅና ባለቤት ናቸው፡፡የሶሌ ኢንተርፕራይ ማለት ከተማዋ የጀርባ አጥንት የሆኑትን በጣም
በርካታ ድርጅቶችን በጥምረት የሚያስተዳድር ግዙፍ ድርጅት ነው፡፡አቶ ፍሰሀ እና ልጃቸው በከተማዋ እጅግ የተከበሩ እና የተመሰገኑ ግለሰቦች ናቸው፡፡››ሲሉ የማስተዋወቅና የመግቢያ ንግግር አድርገው ከጨረሱ በኃላ ራሷን እንድታስተዋውቅ አይን አይኗን ይመለከቷት ጀመር፡፡
አለምም የዳኛውን ማብራሪያ በፅሞና ስታዳምጥ ከቆየች በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ እነዚህ ከፊት ለፊቷ ያሉትን ዳኛው የዘረዘሯቸውን ሶስት ሰዎች በማየቷ እንግዳ እና ሀይለኛ የማወቅ ጉጉት በውስጧ ሲንተገተግ ተሰማት፡፡በውስጧ ለእነሱ ያዳበረችው ጥላቻም ሲገለባበጥ ይታወቃታል፡፡ እነሱ ስለእሷ እና ስለ ስብሰባው አለማ ለማወቅ እንደጓጉ ሁሉ እሷም እነሱን ለማወቅ ፈልጋለች፣
አለም መጀመሪያ አቶ ፍሰሀን ነው የተመለከተችው….በእድሜ ከዳኛው ብዙም የሚያንስ አይመስልም…ግን እንደዳኛው ግርጅፍጅፍ አላለም፡፡ሰውነቱን በትኩረት ላየ‹‹አሁንም ገና እጅ አልሰጥም ››እያለ የሚፎክር ይመስላል፡፡ፊቱን በትኩረት ስትመለከት መሰላቸቱን ታዘበች፡፡የበጋው የከረረ ጸሀይ እና ፀሀይን ተከትሎ ያለው ሙቀት ያደከመው ይመስላል፣ የማሰብ ችሎታ ያላቸው የሚመስሉ ደማቅ ጥቋቁር አይኖቹ አፈጠጡባት።
አለም ከእሱ አይኗን ነቀለችና ቀጥሎ ወደተቀመጠው ኩማንደር አዘዋወረች፡፡ሙሉ የደንብ ልብሱን እንደለበሰ ነው፡፡ጭንቅላቱ ላይ ያጠለቀው የፖሊስ ኮፍያ ወደታች አዘቅዝቆ ብድር እንዳለበት ሰው ከፊል ፊቱን እንዲሸፍን አድርጎታል፡፡ እድሜው አርባዎቹ አጋማሽ ላይ እንዳለ ብትገምትም ሰውነቱ ግን አሁንም የጎረምሳ ነው…ከፊቱ ላይ ምንም ማንበብ አልቻለችም ፡፡ቀዝቃዛና ስሜታ አልባ ሆኖ ነው ያገኘችው፡፡ አካሉ ብቃት ያለው እና ጠንካራ ይመስላል። ማንም ሰው ከእሱ ጋር አካላዊ ፀብ ውስጥ ገብቶ መጣላትን ይጸየፋል። በዛ ላይ ጨካኝና ተንኰለኛ መሆኑን በእይታ እንኳን መገመት ያን ያህል ከባድ አይደለም፡፡ በመጨረሻ ጁኒዬርን ተመለከተች፤በእድሜ ከኩማደሩ ጋር እኩያ መሆኑ ያስታውቃል፡፡ በሌሎች ነገሮች ግን ተቃራኒ ናቸው፡፡ጁኒዬር ከሁለቱም በተለየ ገራገር ሰው ይመስላል፡፡ፈገግ ሲል ልዩ አይነት መስህብ አለው ። ቀጥ ያሉ ነጭ ጥርሶቹ ብልጭ ድርግም ሲያደርጋቸው ቀልብን ይገዛሉ፡፡ ጥቁር ደማቅ አይኖቹ ከአባቱ በተለየ የጠለቀ ሀዘን ይነበብባቸዋል፡፡ ደግሞ ውብ ነው፡፡የወንድ ቆንጆ፡፡
በሽርፍራፊ ሰከንዶች ሁሉንም ገምግማ ካጠናቀቀች በኃላ ጉሮሮዋን አሟሸችና ስሟን ለመስማት በጉጉት እየጠበቁ ወዳሉት አራት ጥንድ አይኖች እየተመለከተች ።
"እኔ አለም ጎበና እባላለሁ፣ ጎደኞቼ አሌክስ ይሉኛል፡፡የሶሎሜ ሴት ልጅ ነኝ።"አለች
ንግግሯን ተከትሎ በቤቱ ኒዩክሌር ቦንብ የፈንዳ ይመስል በሶስትም ሰዎች ላይ የታየው ድንጋጤ የተለየ አይነት ነበር፡፡ዳኛው ግን ምኑም ስላልገባቸው የሌሎቹ መደንገጥ ድንግርግራቸው እንዲወጣ ነው ያደረገው…ለተወሰኑ ደቂቃዎች በክፍሉ ፍፁም አይነት ዝምታ ተንሰራፋ።
ዳኛው ግራ በመጋባት "ሰሎሜ ማን ናት?"ሲሉ ጠየቁ።
አቶ ፍሰሀ ወንበሩ ላይ እንደ ተሰባበረ አሻንጉሊት ወደ ኋላ ተንሸራተተና
"አንቺ…የሰሎሜ ሴት ልጅ….?
አምላኬ..እኔ አላምንም." አለ፡፡
ጁኒየር በሹክሹክታ" የማይታመን ተአምር።አንድ ሰው ህልም ነው ቢለኝ ደስ ይለኛል?" ሲል ተሰማ፡፡
በጡረታ መውጫው በር ላይ ሚገኙት አዛውንቱ ዳኛ አሁንም ግራ እንደተጋቡ ነው። ሁሉም ድንጋጤ ውስጥ ስላሉ ለእሳቸው ማንም ትኩረት አልሰጠም።አባትና ልጅ ፊቷን በደንብ ለማጥናት አፈጠጡባት …አይኖቾ ከዘመናት በፊት ከሚያውቋት እናቷ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለቸው በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል።በደንብ ልብሱ ላይ የወታደር ኮፍያ ያጠለቀው ኩማንደር አሁን በትካዜ እግሯቹን እያወዛወዘ እንደሆነ አስተዋለች፡፡
"ከዚህ ሁሉ አመት በኋላ እዚህ ምን ልትሰሪ መጣሽ ?" አቶ ፍሰሀ ነው ያለይሉኝታ የጠየቋት።
‹‹ምን ልትሰሪ መጣሽ ነው..?ወይስ እንኳን ደህና መጣሽ?››በማሽሞጠጥ መልስ ሰጠች፡፡
"ስንት አመት ሆነሽ?" ጁኒየር የጠየቀው የመጀመሪያ ጥያቄ ነበር፡፡
"ሃያ አምስት." አለም ትክክለኛ እድሜዋን ነገረችው፡፡
"አያትሽ እንዴት ነች?"
"በአሁኑ ጊዜ አርጅታለች..በሜቅዶኒያ የአረጋዊያን መንከባከቢያ ተቋም ውስጥ ነው የምትገኘው…የጡረታ ደሞዟን ይዛ እዛ ገብታለች..በካንሰር በሽታ ተይዛ የመሞቻ ጊዜዋን እየተጠባበቀች ነው።
ማለቴ ኮማ ውስጥ ነች።››
"ይህን በመስማቴ አዝናለሁ."አለ ጁኒዬር፡፡
"አመሰግናለሁ።"ስትል በትህትና መለሰችለት፡፡
"ይህን ሁሉ ጊዜ የት ነበር የምትኖሪው?"አቶ ፍሰሀ ነው ጠያቂው፡፡
ህይወቴን በሙሉ አዲስ አበባ ነው የኖርኩት፡፡ቢያንስ እኔ እስከማስታውሰው ድረስ። እዚያው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን አጠናቅቄ ወደ አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍልን ተቀላቀልኩ።ከአራት አመት በፊት ነው ግራጅዌት ያረኩት..እና ሶስት አመት እዛው አዲስአበባ አንድ የውጭ ካምፓኑ ውስጥ ተቀጥሬ ስሰራ ነበር..እና አሁን ለዞኑ ምክትል አቃቢ ህግ ሆኜ ከተመደብኩ አንድ ሳምንት ሆነኝ ።"
"የህግ ትምህርት ቤት ተመርቀሽ….እዚ የእኛ ዞን አቃቢ ህግ ። ደስ የሚል ነው››ጁኒየር በፈገግታ ተውጦ ተናገረ ፡፡
በዋናው አቃቢ ህግ ጥያቄ አቅራቢነት ይህንን ስብሰባ እንዲያዘጋጁ የጠየቁትና ያዘጋጁት አዛውንቱ ዳኛ ሁኔታው ምንም አላመራቸውም… ፡፡
"እንደዚህ አይነት ልብ የሚነካ አይነት መገናኘትን እጠላለሁ፣ ግን አሁንም በጨለማ ውስጥ ነኝ..ስለሚካሄደው ነገር ምንም የገባኝ ነገር የለም፡፡››ሲሉ ብሶታቸውን ተናገሩ፡፡
‹‹ሶሎሜ ማለት የእሷ እናት ነች፡፡እሷ ከመወለዷ በፊት የጁኒዬርና የኩማንደሩ የቅርብ ጓደኛ ነበረች፡፡ከዛም አልፏ ቤተሰብ ነበርን….ነፍሷን ይማርና ፈፅሞ የማይለያዩ የልብ ጓደኛሞች ነበሩ…. ››ከዚያም ጥቋቁር አይኖቹ ደመና አጠላባቸውና በሀዘን ራሱን ነቀነቀ..እና ንግግሩን ካቆመበት ቀጠለ "ሞቷ ለሁለችንም ከፍተኛ ሀዘን ያስከተለ ነበር….ክብር ዳኛ … የገዳዩን ችሎት እኮ እርሶ ነበር ያስቻሉት…የእኔ የእርባታ ግቢ ውስጥ አንድ እብድ በቢላዎ ወግቶ ከገደላት በኋላ ራሱን እስር ቤት ውስጥ ያጠፋው…፡፡››
የዳኛው ፊት ሲጠቁር በግልፅ ተመለከተች‹‹እኔ እንጃ ትዝ አላለኝም…የሽማግሌ ነገር ስንትና ስንት ችሎት አስታውሳለው ብለህ ነው?››በማለት ሸፋፍነው ለማለፍ ሞከሩ፡፡
አቶ ፍሰሀ ራሱን ለመቆጣጠር የተወሰነ ጊዜ በፀጥታ አሳለፈና። " ለማንኛውም ስለ አለም ሆነ ስለ አያቷ የሆነ ነገር ስንሰማ ይህ የመጀመሪያ ጊዜያችን ነው።
ለማናኛውም እንኳን ወደእናትሽ የትውልድ ከተማ በሰላም መጣሽ››አላት፡፡

❤53👍3😢2🔥1
አለም"እመሰግናለው ግን….›› አለችና ከፊት ለፊቷ የተቀመጠውን ፎልደር በማንሳት ውስጡ ያለውን ፋይል አወጣች…ከዛ መናገር ጀመረች፡፡
"አቶ ፍሰሀ …እንደነገርኩህ እኔ እዚህ የተወሰነ ጊዜ ለመቆየት አይደለም የመጣሁት …እንደ እውነቱ ከሆነ እዚህ በቋሚነት የመንግስትንም ሆነ የግሌን ስራ ለመስራት ነው የመጣሁት።›› አለችና ፋይሉን ለክብር ዳኛው አቀበለች፡፡
ዳኛውም በእንቆቅልሽ እይታ ተመለከታትና እና የሰጠችውን የክስ ዶሴ ለማየት ሞከረ
.በቀላሉ ሊገባው ስላልቻለ
" ምንድነው?›› በማለት ጠየቃት፡፡
‹‹ከአመታት በፊት ስለተዘጋ ክስ እንደገና ስለመክፈት ነው …ተከሳሾቹ ሁሉም እዚህ አሉ፡፡ይዘቱን እንዲመሩትና እና ዝርዝሮቹን በደንብ እንዲያጠኗቸው ሀሳብ አቀርባለሁ።››አለች፡፡
ስለምታወራው ነገር ማንም የገባው ሰው የለም፡፡
‹‹የምታወሪው ምንም አልገባንም….››አቶ ፍሰሀ ጠየቃት፡፡
"እሺ፣ እንግዲህ፣ አብራራላችኃለው …የሃያ አምስት አመት ግድያ ጉዳይን እንደገና እየከፈትኩ ነው። ሊቁ የተባለ ሰው እናቴን እንደገደለ እና ወንጀሉን እንደፈፀመ ተወስኖ ፋይሉ ተዘግቶ ነበር …››ወደ አቶ ፍሰሀ አይን ተመለከተች… ከዛ ወደ ጁኒየር ተመለከተች። በመጨረሻም ኮማንደሩን ላይ ትኩረት አደረገች…ያለምንም የስሜት ለውጥ ሆነ የአካል እንቅስቃሴ ተቀምጧል..እሷ የምታወራውን ነገር እያዳመጠ ይሁን ወይም ጆሮውን በጥጥ ጠቅጥቆ ችላ ብሎት እንደሆነ እርግጠኛ መሆን አልቻለችም….፡፡ ንግግሯን ቀጠለች
"ነገሩን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ ከእናንተ መካከል አንዳችሁ ወይንም ሁላችሁም በመተጋገዝ እናቴን እንደገደላችኃት ጠንካራ ጥርጣሬ አለኝ።"
ማብራሪያዋ በመሀከላቸው የእጅ ቦንብ እንደወረወረች አይነት ነው ሁሉንም ያስበረገገው፡፡እስከአሁን አንድ ቃል ያልተናገረው ኩማንደር ጭንቅላቱ ላይ ያደረገውን ኮፍያ አንስቶ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠና በሚንቀለቀል ቁጠ አይኖቹ ደፍርሰው‹‹በዚህ ልክ ሰውን መወንጀል ራሱ ወንጀል መሆኑን እዛ ዩኒቨርሲቲ አላስተማሩሽም እንዴ?››ሲል አፈጠጠባት፡፡
እያንዳንዷን እስከአሁን የተናገረቻቸውን ነገሮች በጥንቃቄ እንዳዳመጠ በመረዳቷ እርካታ ተሰማት‹‹ኮማንደር እኔ ክስ ከፍቼለው ..መረጃ አቀርባለው..አንተ ደግሞ እንዳልገደልክ ፍርድ ቤቱን ታሳምናለህ…አካሄዱ እንደዛ ነው..ባይሆን ከዛ በኃላ እኔ ከተረታው በስም ማጥፋት ልትከሰኝ ትችላለህ…..ያ ደግሞ የሚሆነው ነጻ ሰው ከሆንክ ነው….››ስትል የማትበገር መሆኗን በሚያረጋግጥ በተመሳሳይ ቁጣ መለሰችለት፡፡
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
"አቶ ፍሰሀ …እንደነገርኩህ እኔ እዚህ የተወሰነ ጊዜ ለመቆየት አይደለም የመጣሁት …እንደ እውነቱ ከሆነ እዚህ በቋሚነት የመንግስትንም ሆነ የግሌን ስራ ለመስራት ነው የመጣሁት።›› አለችና ፋይሉን ለክብር ዳኛው አቀበለች፡፡
ዳኛውም በእንቆቅልሽ እይታ ተመለከታትና እና የሰጠችውን የክስ ዶሴ ለማየት ሞከረ
.በቀላሉ ሊገባው ስላልቻለ
" ምንድነው?›› በማለት ጠየቃት፡፡
‹‹ከአመታት በፊት ስለተዘጋ ክስ እንደገና ስለመክፈት ነው …ተከሳሾቹ ሁሉም እዚህ አሉ፡፡ይዘቱን እንዲመሩትና እና ዝርዝሮቹን በደንብ እንዲያጠኗቸው ሀሳብ አቀርባለሁ።››አለች፡፡
ስለምታወራው ነገር ማንም የገባው ሰው የለም፡፡
‹‹የምታወሪው ምንም አልገባንም….››አቶ ፍሰሀ ጠየቃት፡፡
"እሺ፣ እንግዲህ፣ አብራራላችኃለው …የሃያ አምስት አመት ግድያ ጉዳይን እንደገና እየከፈትኩ ነው። ሊቁ የተባለ ሰው እናቴን እንደገደለ እና ወንጀሉን እንደፈፀመ ተወስኖ ፋይሉ ተዘግቶ ነበር …››ወደ አቶ ፍሰሀ አይን ተመለከተች… ከዛ ወደ ጁኒየር ተመለከተች። በመጨረሻም ኮማንደሩን ላይ ትኩረት አደረገች…ያለምንም የስሜት ለውጥ ሆነ የአካል እንቅስቃሴ ተቀምጧል..እሷ የምታወራውን ነገር እያዳመጠ ይሁን ወይም ጆሮውን በጥጥ ጠቅጥቆ ችላ ብሎት እንደሆነ እርግጠኛ መሆን አልቻለችም….፡፡ ንግግሯን ቀጠለች
"ነገሩን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ ከእናንተ መካከል አንዳችሁ ወይንም ሁላችሁም በመተጋገዝ እናቴን እንደገደላችኃት ጠንካራ ጥርጣሬ አለኝ።"
ማብራሪያዋ በመሀከላቸው የእጅ ቦንብ እንደወረወረች አይነት ነው ሁሉንም ያስበረገገው፡፡እስከአሁን አንድ ቃል ያልተናገረው ኩማንደር ጭንቅላቱ ላይ ያደረገውን ኮፍያ አንስቶ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠና በሚንቀለቀል ቁጠ አይኖቹ ደፍርሰው‹‹በዚህ ልክ ሰውን መወንጀል ራሱ ወንጀል መሆኑን እዛ ዩኒቨርሲቲ አላስተማሩሽም እንዴ?››ሲል አፈጠጠባት፡፡
እያንዳንዷን እስከአሁን የተናገረቻቸውን ነገሮች በጥንቃቄ እንዳዳመጠ በመረዳቷ እርካታ ተሰማት‹‹ኮማንደር እኔ ክስ ከፍቼለው ..መረጃ አቀርባለው..አንተ ደግሞ እንዳልገደልክ ፍርድ ቤቱን ታሳምናለህ…አካሄዱ እንደዛ ነው..ባይሆን ከዛ በኃላ እኔ ከተረታው በስም ማጥፋት ልትከሰኝ ትችላለህ…..ያ ደግሞ የሚሆነው ነጻ ሰው ከሆንክ ነው….››ስትል የማትበገር መሆኗን በሚያረጋግጥ በተመሳሳይ ቁጣ መለሰችለት፡፡
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
YouTube
አትሮኖስ_ Tube
Share your videos with friends, family, and the world
👍39❤24
#አንቺና_ጨረቃ
መብረቅ ብልጭ ብሎ
ምስልሽን ሲፈጥር፤
ፀሀይ ስትስቅ ነው
አንቺን የምትመስል፣
ኩልል ያለ ውሃ
ሲያይሽ ይጠራል፣
ከዋክብትን አይተሽ
ስንቴ አሽኮርምመሻል።
ጨረቃ ደግሞ አይታ፣
ካንቺ ካልተዋስኩኝ ብርሃንሽን ብላ፣
እንደዘብ ጠባቂ
አንቺን ተከትላ፣
ከአጼ ቤት ጎጆ
ገባች ሰተት ብላ።
አውቀሽ ነው ቢባልም
አሁን አምኛለሁ፣
አንቺን ለመፈለግ፤
አይደለም ጨረቃ እኔም ደክሜያለሁ።
ሰአሊ እንዳይስልሽ
ቀለምሽ አይገባም፣
ገጣሚ እንዳይገጥምሽ
ያለው ቃል አይበቃም።
ሆኖብኝ ነው እንጂ
እንደ አጼ ቤት ልጆች፣
መች እዋስ ነበረ
ዋንጫና ቁልፊቶች።
አውቃለሁኝ አዎ
በዚ ውስጥ አትቆዪም፣
በፍቅርሽ ተይዤ፤
በልቤ ብልቃጥ ውስጥ
አንቺን ባስቀምጥም፣
ሰበርሽው እሱንም፣
አንቺና ጨረቃ
ጭራሽ አትያዙም፣
ድንገት ብትያዙ፤
የያዛችሁን ነገር ከመስበር አትቀሩም፣
አንቺና ጨረቃ
መስበርን አተዉም፣
አንቺም ጨረቃም
ወደኋላ አትሉም።
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
መብረቅ ብልጭ ብሎ
ምስልሽን ሲፈጥር፤
ፀሀይ ስትስቅ ነው
አንቺን የምትመስል፣
ኩልል ያለ ውሃ
ሲያይሽ ይጠራል፣
ከዋክብትን አይተሽ
ስንቴ አሽኮርምመሻል።
ጨረቃ ደግሞ አይታ፣
ካንቺ ካልተዋስኩኝ ብርሃንሽን ብላ፣
እንደዘብ ጠባቂ
አንቺን ተከትላ፣
ከአጼ ቤት ጎጆ
ገባች ሰተት ብላ።
አውቀሽ ነው ቢባልም
አሁን አምኛለሁ፣
አንቺን ለመፈለግ፤
አይደለም ጨረቃ እኔም ደክሜያለሁ።
ሰአሊ እንዳይስልሽ
ቀለምሽ አይገባም፣
ገጣሚ እንዳይገጥምሽ
ያለው ቃል አይበቃም።
ሆኖብኝ ነው እንጂ
እንደ አጼ ቤት ልጆች፣
መች እዋስ ነበረ
ዋንጫና ቁልፊቶች።
አውቃለሁኝ አዎ
በዚ ውስጥ አትቆዪም፣
በፍቅርሽ ተይዤ፤
በልቤ ብልቃጥ ውስጥ
አንቺን ባስቀምጥም፣
ሰበርሽው እሱንም፣
አንቺና ጨረቃ
ጭራሽ አትያዙም፣
ድንገት ብትያዙ፤
የያዛችሁን ነገር ከመስበር አትቀሩም፣
አንቺና ጨረቃ
መስበርን አተዉም፣
አንቺም ጨረቃም
ወደኋላ አትሉም።
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
❤9👍2
#ነዳይ ...
ውዴ....
እግዜርን ፍለጋ በዱር በተራራ
ምድሩን አታስሽው
በምናኔ ጉዞ ዋሻ ለመገስገስ
እግርሽን አታንሽው
መውረድ ከጀመረ የማይቆም እምባሽን
ይቅር አታፍስሽው
ጽድቅ ያማረሽ እንደው
ነዳይ ልቤ ፊትሽ
ደጅሽ ወድቋል አንሽው !!!
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ውዴ....
እግዜርን ፍለጋ በዱር በተራራ
ምድሩን አታስሽው
በምናኔ ጉዞ ዋሻ ለመገስገስ
እግርሽን አታንሽው
መውረድ ከጀመረ የማይቆም እምባሽን
ይቅር አታፍስሽው
ጽድቅ ያማረሽ እንደው
ነዳይ ልቤ ፊትሽ
ደጅሽ ወድቋል አንሽው !!!
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
❤14👍1🔥1
#ብዬማ+አልዋሽሽም
እኔ'ኮ ያላንቺ ምንም ነኝ ብዬ
ብዙ አልዘበዝብም
ስሚኝ አንቺ ሆዬ
ትተሽኝ ከሄድሽ
ልቤ ድንኳን ጥሎ
ደረቱን ይደቃል
ከሰው ተነጥሎም
ሀዘን ይቀመጣል
ከመኖር ተጣልቶም
ሞትን ይናፍቃል ።
ብዬማ አልዋሽሽም
ከተውሽኝ አልኖርም
ያላንቺ ምስቀዉ
ሳቄም ሳቅ አይሆንም
ስልማ አልዋሽሽም
ምን በወጣሽ ፍቅሬ
ባምላክ ትዕዛዝ እንጂ
ባንቺ አይደል መኖሬ ።
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
እኔ'ኮ ያላንቺ ምንም ነኝ ብዬ
ብዙ አልዘበዝብም
ስሚኝ አንቺ ሆዬ
ትተሽኝ ከሄድሽ
ልቤ ድንኳን ጥሎ
ደረቱን ይደቃል
ከሰው ተነጥሎም
ሀዘን ይቀመጣል
ከመኖር ተጣልቶም
ሞትን ይናፍቃል ።
ብዬማ አልዋሽሽም
ከተውሽኝ አልኖርም
ያላንቺ ምስቀዉ
ሳቄም ሳቅ አይሆንም
ስልማ አልዋሽሽም
ምን በወጣሽ ፍቅሬ
ባምላክ ትዕዛዝ እንጂ
ባንቺ አይደል መኖሬ ።
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
❤12🥰6
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///
በፍርድ ቤቱ የስብሰባ ክፍል ውስጥ የነበረው ትእይንት መቀበል ከምትፈልገው በላይ አንቀጥቅጧታል።ግን ደግሞ ጭንቅላቷን ወደ ላይ ቀና አድርጋ እና ደረቷን ነፍታ ነበር ቢሮውን ለቃ የወጣችው ።እራሷን ለመቆጣጠርና የድንጋጤዋንና የፍራቻዋን ቅንጣት እንኳን ለእነሱ ሳታሳይ ስብሳባውን በድል ለማገባደድ ያደረገችው ጥረት የመታፈን አይነት ስሜት እንዲሰማት ነበር ያደረጋት፡፡ስብሰባው ባቀደችው መሰረት ነው የተካሄደው፣ እስኪጠናቀቅ ድረስም በጣም እንደተረጋጋች ነበር።
አለም ወደ ሆቴሏ ከተመለሰች በኃላ ሱፍ ኮቷን አልጋ ላይ ወረወረች።እጆቿ በላብ ተጠምቀው ስለነበረ እርጥብ ነበሩ እና ጉልበቶቿ መንቀጥቀጣቸው አሁንም አላቆሙም
ከመደንገጧ የተነሳ የማቅለሽለሽ ስሜት ነበራት። አልጋዋ ለይ ተዘርራ ተኛችና ስለቆይታዋ በምልሰት ማሰላሰል ጀመረች፡፡
በጣም መጥፎው ጉዳይ ወደፊት የሚከሰተው እንደሆነ ብታስብም ለጊዜው ደስ ብሏታል፣ ቢሆንም ነገ ተነገ ወዲያ ስለሚሆነው ነገር መፍራቷ አልቀረም። ዛሬ ያገኘቻቸው ሶስት ሰዎች በዋናነት ዳኛው ደግሞ በተዘዋዋሪ ከእናቷ ጋር የሚያያይዝ ታሪክ ያላቸው ናቸው። ከዘመናት በኋላ እነሱን መጋፈጥ ቀላል ውሳኔ አልነበረም እና በምንም አይነት ሁኔታ እሷን በማየታቸው ደስተኞች ሊሆኑ እንደማይችሉ መጀመሪያም ግምቷ ነበር፣ እናም ካገኘቻቸው
በኃላም የተረዳችው ያንን ነው..ትንሽም ቢሆን ጁኒዬር ካልሆነ በስተቀር ኩማንደሩና አቶ ፍሰሀ ጥላቻቸው በግልፅ ግንባራቸው ላይ ይነበብ እንደነበረ ታዝባለች፡፡
አቶ ፍሰሀ በሻሸመኔ ከተማና በአካባቢው በጣም ሀብታም እና ኃያል ሰው ነው። ያንን ደረጃ ያገኘው ደግሞ በመልካም አመራር እና በስራ ትጋቱ ብቻ አይደለም። ዕድሜ ልኩን ያካበተውን ሀብት ጠብቆ ለማቆየት ባለው ኃይል ሁሉ በስውርም ሆነ በግልፅ ሲዋጋ እና ሲፋለም ኗሯል።አቶ ፍሰሀ እና ቤተሰቡ ላይ እያቀረበችውን አይነት ክስ ማቅረብ እንደእብደት እንደሚቆጠር ታውቃለች..ከዳኛው ፊት ላይ ያነበበችውም ያንኑ ስሜት ነው፡፡ አይደለም በጥርጣሬ ግድያ ቀርቶ እጅ ከፍንጅ ተኩሰው ሲገድሉ ቢታዩ እንኳን ባርቆባቸውን ነው በሚል ተስተካክሎና ለዛም ምስክርና ማስረጃ ተጠናክሮ በቀላሉ ነፃ እንዲወጡ እንደሚደረግ በቀላሉ መገመት ትችላለች፡፡ግን ከእሷ ጋር መጋፈጥም ቀላል እንዳልሆነ በሂደት እንዲረዱ እንደምታደርገቻው እርግጠኛ ነች፡፡
ስለ ጁኒየር ስታስብ የተሰማት የተለየ ነገር ነው፡፡በሴቶች ዙሪያ ያለው አመለካከት የተለየ ስለሆነ አቀራረቡም ከአባቱና ከኩማንደር ጓደኛው በመጠኑም ቢሆን የሚለይ ማራኪ ሆኖ ነው ያገኘችው። አለም በጉርምስና ዕድሜው ላይ እያለ ካያቸው ፎቶ ግራፉ ብዙም አልተለወጠም። መልከ መልካምነቱን ፍላጎቱን ለማሳካት እና እንስቶችን ለማማለል ሲጠቀምበት እንደኖረ ታውቃለች። ለእሱ ሰውን ከመግደል ይልቅ በፍቅር መውደቅ ቀላል እንደሚሆንለት አሰበች፡፡እናም በገዛ ሀሳቧ ፈገግ አለች፡፡
ቀጥሎ ወደአእምሯዋ የተሰነቀረው ኩማንደር ገመዶ ነው፡፡እስከአሁን ኩማንደሩን ለማንበብ እና እንዲህ ነው ብሎ ለመተንበይ በጣም ከበድ ነው የሆነባት.. እርግብ ይሁን እባብ… ወይንም ሁለቱንም አዳብሎ የያዘ እስስት ለመለየት ከባድ ነው የሆነባት፡፡ ስለ እሱ የነበራት ግንዛቤ ትንሽ የተለየ ነው።በስብሰባ ክፍል ውስጥ እንደሌሎቹ አይኖቹን ማየት አልቻለችም። እሱ ከአያቷ የፎቶ ማከማቸ ሳጥን ውስጥ የልጅነት ፎቶውን ካየችው ከዛ ወጣት ልጅ በእጅጉ የተቀየረ ….የበለጠ ከባድ እና ጠንካራ የሆነ መስሎ ታየት። የመጀመሪያ እይታው ተንኮለኛ፣ ወዳጃዊ ያልሆነ እና አደገኛ መስሎ ነበር የተሰማት።ከእነዚህ ሰዎች መካከል አንዱ እናቷን እንደገደለ እርግጠኛ ነች። እናቷ ሰሎሜ በተከሳሹ ሊቁ እጅ አልተገደለችም።
"አለም ክሱን ከእንደገና ማስከፈት እና የእናትሽን እውነተኛ ገዳይ ለፍርድ ማቅረብ የአንቺ ኃላፊነት ነው፡፡" በየቀኑ ለራሷ የምትነግረው ጉዳይ ነው።"ይህ ለእናትሽ ልታደርጊው የምትችይው ትንሹ ነገር ነው."
ብዙውን ጊዜ አያቷ በቤቱ ውስጥ ተበታትነው ከነበሩት ብዙ የድሮ ፎቶግራፎች ውስጥ አንዱን በተደጋጋሚ ጊዜ በጥንቃቄ ይመለከቱ ነበር።ያ ፎቶ ደግሞ እናቷ ሰሎሜ በአፍላ ወጣትነቷ ዘመን ከእድሜ እኩዬቿ ጁኒዬር እና ገመዶ መሀከል ቆማ የተነሳችው አሮጌ ፎቶ ነው፡፡ ፎቶውን መመልከት ሁልጊዜ እንድታዝንና እና በናፍቆት እንድታለቅስ ያደርጋታል፣ እና የልጅ ልጇ ምንም ነገር ብታደርግ ሊያስደስታት አይችልም ነበር።ይሁን እንጂ እስከ ጥቂት ወራት ድረስ አለም ጎበና እናቷ ሰሎሜን በመግደል ተጠርጣሪው ማን እንደነበረ አታውቅም ነበር።ያንን ሚስጥር ያወቀችበት እለት በአለም ሕይወት ውስጥ በጣም ጨለማው ቀን ነበር።
ትዝ ይላታል በወቅቱ የስራ ገበታዋ ላይ ሆና እየሰራች ሳለ….ከሜቅዶኒያ ተደውሎላት በአስቸኳይ ድረሺ ስትባል በፍጥነት ነበር የሄደችው… ፡፡ተቋሙ ጸጥ ያለ፣ በበጎ ፍቃደኞች እና በተንከባካቢ ባለሙያዎች የተሞላ ነበር። አያቷ ወደ ሆስፒታል ተወስደው ነበር…. ወዲያው ወደሆስፒታል አመራች፡፡ በሽታዋ የእርጅና በሽታ የተጫጫነው ነበረ፡፡ተስፋ መቁረጥ እና እርጅና ከካንሰር በሽታቸው ጋር ሲደመር የመጨረሻ እስትንፋሳቸውን እየሳቡ እንደሆነ ገባት፡፡ ዶክተሮቹንም ስታናግር አያቷ አስጊ ሁኔታ ላይ እንዳሉ ተነገራት። ፀጥ ወዳለው የአያቷ ክፍል ገብታ ወደ አልጋቸው ተጠጋች። የአያቷ አካል በሚታይ ሁኔታ ተዳክመው ነበር።አለም የጎበኘቻቸው ከሳምንት በፊት ስለሆነ በነዛ ጥቂት ቀናት ውስጥ እንደዛ አይነት ጉልህ ለውጥ ማየቷ አስደነገጣት።አያቷ መላ አካላቸው ድቅቅ ብሎ ቢደክምም ዓይናቸው ግን ህያው ነበር፣
"እዚህ አትግቢ" ትንፋሿቸውን አጠራቅመው ጮሁባት "አንቺን ማየት አልፈልግም
…በአንቺ ምክንያት ነው!"
"ምንድነው አያቴ?" አለም በጭንቀት ጠየቀች።
"ምንድን ነው የምታወሪው?" "እዚህ አልፈልግሽም."
አለም አያቷ እሷ ላይ ባሳዩት ብስጭት እና ጥላቻ በመሸማቀቅ ወደ ሐኪሙ እና ወደ ነርሶች ዞር ብላ ተመለከተቻቸው። "ልታየኝ ለምንድነው የማትፈልገው? ያለዋት ብቸኛ ዘመድ እኔ ነኝ…የልጅ ልጇ ነኝ፣››በእፍረት ተውጣ ልታስረዳቸው ሞከረች፡፡
አያትዬው ወቀሳቸውን ቀጠሉ"እናትሽ ባንቺ ጥፋት ነው የሞተችው፣ ታውቂያለሽ፣ ባንቺ ምክንያት ባይሆን ኖሮ ልጄ አትሞትም ነበር. . " አያቷ ማልቀስ ጀመሩ…..አለም ምታደርገው ነገር ጠፋት ፡፡
"ለእናቴ ሞት ተጠያቂዋ እኔ ነኝ እንዴ?"
የአይቷ አይኖች ከተደበቁበት ፈጠው ወጡ። "አዎ" ብላለው በቁጣ አረጋገጡላት።
"እኔ እናቴ ስትሞት ገና ሕፃን ነበርኩ እኮ፣ ጨቅላ ህፃን" ስትል ተከራከረች፣የአያቷን የአእምሮ ጤንነትም መጠራጠር ጀመረች፡፡"እንዴት በጨቅላ እድሜዬ የምትይውን ማድረግ እችላለሁ?"
" ጠይቂያቸው።"
‹‹ማንን አያቴ? ማንን ልጠይቅ?"
"የገደሏትን...ፍሰሀ… ልጁ ጁኒዬር እና ኩማንደር ገመዶን… እናም አንቺም ነበርሽ አንቺ ነሽ "አያቷ ንግግራቸውን ሳይቆጩ ጥልቅ ኮማ ውስጥ ገቡ፡፡ ከዛ በኋላ አለም ከክፍሉ በዶክተር እየተመራች ወጣች። በገዛ አያቷ የቀረበባት አስቀያሚው ክስ እስክትደነዝዝ ድረስ ነበር ያስጨነቃት፡፡ በአንጎሏ ውስጥ ተንሰራፍቶ ማሰቃየት ብቻ ሳይሆን ነፍሷ ድረስ ዘልቆ ነው ያጠቃት ።አያቷ ለእናቷ ሞት እሷን ተጠያቂ አድርገው እንደሚያስቧት ከሰማች ጊዜ በኋላ ስለእናቷም ሆነ ስለአስተዳደጓም ወደኋላ መለስ ብላ እንድታስብ ተገደደች፡፡ አያቷ ከእሷ ጋር የነበራት ግንኙነት ለምን የሻከረ እንደነበረ ሁል ጊዜ

❤42👍3🔥2
እራሷን ትጠይቅ ነበር፣አሁን ግን መልሱ ፍንትው ብሎ ተገልፃላታል፡፡
የአለም ስኬቶች ምንም ያህል አስደናቂ ቢሆኑም፣ የሴት አያቷን ውዳሴ ለማሸነፍ በቂ ሆነው አያውቁም ነበር ። አያቷ በሚያሳዝን ሁኔታ ብልህ እና ጨዋ ልጅ እንደሆነች አድርገው እንደማያዬት ታውቃለች።አለም በአያቷ አልተናደደችም። በእርግጥም ያለ ወላጅ ያደገችውን ልጅ በጭፍን ስሜት በዚህ ልክ በሆነ ጥላቻ መጥላታቸው አግባብ እንዳልሆነ ታውቃለች…ግን ደግሞ የአያቷንም የውስጥ ቁስለት ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ ስላማታውቅ ድምዳሜ ላይ መድረስ አልፈለገችም። አለም በሁሉም ነገር ጥሩ ለመሆን ብቻ ሳይሆን ብቁ ሴት ልጅ ለመሆን የአያቷን ፍቅር እና ሞገስ ለማግኘት ተስፋ ባለመቁረጥ ትለፋ ነበር።ግን አያቷን በምትፈልገው መጠን ለማሳመን ተሳክቷላት
አያውቅም ነበር፡፡ ስለዚህ ለሰሎሜ ግድያ ተጠያቂ መሆኗን ከአያቷ ከንፈር መስማቷ የሚያስደንቅ መብረቃዊ ምት ነው የሆነባት።
ስለአያቷ የጤና ደረጃ ዶክተሩ ስታናግራት "አሁን ምንም ልናደርግላት የምንችለው ነገር የለም ወይዘሪት አለም››ብላው ነበር ተስፋ ያስቆረጧት፡፡
አለም ግን ተስፋ ልትቆርጥ አልፈለገችም "እሷን በህይወት ማቆየት የሚቻልበት መንገድ መኖር አለባት ››ስትል አሰበች፡፡ከዛ ወዲያው ወደ ቤቷ ተመለሰችና የእናቷን የድሮ ማስታወሻዎች ..በተገደለችበት ወቅት የነበሩ የጋዜጣ ዜናዎቹ …የፍርድ ቤት ክስና ውሳኔዎችና በመበርበር ማጥናት ጀመረች…ከዛ አጠራጣሪ ነገሮች ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ፡፡
ከዛ ምን አደረገች ከፍተኛ ደሞዝ የምታገኝበትን ስራ ለቃ ወደሻሸመኔ ከተማ ለመሄድ የኦሮሚያ ክልል ጉምቱ ባልስልጣኖችን ደጅ መጥናት አስፈልጓት ነበር….ከዛ የዞኑ ም/ት አቃቢ ህግ ሆና ለመመደብ ቻለች፣ እዛም እግሯ እንደረገጠ የከተማዋን ፍርድ ቤት ያረጁ ፋይሎችን ለማገላበጥ ጊዜ አላጠፋችም፡፡የከተማዋ ዋና አቃቢ ህግ ጋር ጉዳዩን ይዞ ለመቅረብ ብዙ ምሽቶችን ግልባጭችን እና የፍርድ ቤት ሰነዶችን በማጥናት አሳልፋለች። የመጀመሪያ ደረጃ ምርምሯ እንደ አቃቤ ህግ እና እንደጠበቃ ፍላጎቷን አነሳስቷታል፣ እና በተጨማሪም አያቷ ስህተት እንደሰራች ለማሳየት እና ራሷን ከማንኛውም ጥፋተኝነት ለማዳን የነበራት ከፍተኛ ፍላጎት በድርጊቱ የበለጠ እንድትገፋበት ምክንያት ነበር።
ደግነቱ እግዚያብሄር ሲረዳት የእሷ ሀለቃ ሆኖ የጠበቃት ሰው ከሶስት አመት በፊት ለስድስት ወራትም ቢሆን አንድ መስሪያ ቤት አብረው ሰርተዋል….እና በደንብ ስለምትግባባው ነገሮች ቀላል ሆነውላታል፡፡ዋና አቃቢ ህጉ አቶ ግርማ የሚያጨሰውን ሲጋራ ከአንዱ የከንፈሩ ጥግ ወደ ሌላኛው አቅጣጫ እየቀያየረ ነበር ያዳመጣት። በፍርድ ቤቱ ክፍል ውስጥ ጥፋተኛ የተባሉ ተከሳሾች፣ የውሸት ምስክሮች እና ጉበኛ ዳኞችን በጣም የሚጠየፍና እነሱንም ለማስወገድ እድሜውን ሙሉ ሲጥር የኖረ የተከበረ ሰው ነው፡፡ሁሉን ነገር በፅሞና ለረጅም ጊዜ ካዳመጣት በኋላ
"ከሃያ አምስት አመት በፊት የተፈፀመ የግድያ ክስ እንደገና ፋይሉን ማንቀሳቀስ ትፈልጊያለሽ?" ሲል ባለማመን ጠየቃት፡፡
‹‹በትክክል እንደዛ ነው የምፈልገው›› "ምክንያት አለሽ?"
"ምክንያቱም.. ተጎጂዋ እናቴ ነች።"
"በእየሱስ ስም አለም፣ ይቅርታ ያንን አላውቅም ነበር።"
‹‹አመሰግናለው ..ክቡር አቃቢ ህግ››
"ግድያው ሲፈፀም ዕድሜሽ ስንት ነበር?"
"ጨቅላ ነበርኩ. አላስታውስም. ስትገደል ገና የአስራ ስምንት ወር ልጅ ነበርኩ፡፡." "ጉዳዩ በይፋ እልባት ማግኘት አልቻለም ነበር ?"
"በትክክል የሆነው እንደዛ አይደለም፣ አንድ ተጠርጣሪ ተይዞ ክስ የተመሰረተበት ቢሆንም ክሱ ለፍርድ ሳይቀርብ ተቋርጧል።"
‹‹እስቲ አጠር አድርገሽ አስረጂኝ …ከክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጋር የምሳ ቀጠሮ አለብኝ እንዳታስረፍጂብኝ አስር ደቂቃ አለሽ››
አለም እንደተባለችውም በፍጥነት ማስረዳት ጀመረች… ስትጨርስ የአቃቢ ህጉ መገረምና ድንጋጤ ይበልጥ ጨምሮ ነበር።"አምላኬ ሆይ፣ የሶሌ ኢንተርፕራይዝ ባለቤቶች አባትና ልጅ በጉዳዩ ተሳትፈዋል እያልሺኝ ነው?። አያትሽ በእርግጠኝነት ከመካከላቸው አንድ እናትሽን እንደገደላት ታምናለች?"
"አዎ የከተማዋ ፖሊስ አዛዥ ኩማደሩ ገመዶም ጭምር" "በምን ምክንያት ሊያደርጉት ይችላሉ አለችሽ?››
"እናቴ ለእነሱ የረጅም ጊዜ የቅርብ ጓደኛ ነበረች." "ታዲያ ከመካከላቸው አንዱ ለምን ይገድላታል?" " ለማወቅ የምፈልገው ይህንኑ ነው።"
‹‹ይገርማል…እና ያንን የመሰለ ቅንጡ ስራሽን ጥለሽ ወደዚህ የመጣሽው ለዚህ ነዋ?››እሱ ጋር ተመድባ ከመጣች ጀምሮ ሲገረምበት የነበረውን ጥያቄ ጠየቃት፡፡
‹‹ያው ለምንፈልገውን ነገር ስንል የሆነ መስዋዕትነት መክፈል አለብን አይደል?…አንተም እኮ ምክንያትህ ምን እንደሆነ ባላውቅም ከዚህ በጣም የተሻለ ስራ ነበረህ …ለምን እንደሆነ ባይገባኝም ያንን ጥለህ እዚህ እየሰራህ ነው››
‹‹እኔ ምንም የተለየ ምክንያት የለኝም….የተወለድኩበት ከተማ እና ቤተሰቦቼ ያሉት እዚህ ስለሆነ ነው››
‹‹እኔም እኮ እትብቴ እየተቀበረበት ከተማ ነው…..እናም የዘመዶቼ ሀገር ነው፡፡››
‹‹ጥሩ …ግን እወቂ ከኪሊማንጀሮ ተራራ ጋር ልጋፈጥ እያልሺኝ ነው..በእነዚህ ሰዎች ላይ መረጃ አነፍንፎ ማደራጀትና እነሱን ተጠያቂ ማድረግ እንዲህ ቀላል አይደለም…ቢቻል ኖሮ እኔ ከረጅም ጊዜ በፊት አደርገው ነበር›፡፡›
‹‹ግድ ለህም ..ምንም ያህል ጊዜ ይፍጅ የቱንም ያህል መስዋዕነትነት ይጠይቅ እኔ አደርገዋለው፡፡››
"ይህ የግል ቂም ብቻ እንዳልሆነ እርግጠኛ ነሽ?"
"በእርግጥ አይደለም." አለም ተቆጣች። "ይህን በጥብቅ ህጋዊ እይታ ነው የምከታተለው። ሊቁ የተባለ ሰው ለፍርድ ቀርቦ ትክክለኛው ህግ ሂደት ታልፎ በዳኞች ቢፈረድበት ኖሮ አያቴ በነገረችኝ ጥርጣሬ ላይ ብዙም ጊዜዬን አላጠፋም ነበር። ግን የሆነው እንደዛ አይደለም፤ሰውዬው ተይዞ እስር ቤት እንደገባ..የፍርድ ሂደቱ ሳይደረግና ምርመራው ሳይጠናቀቅ እራሱን አጠፋ ተባለ….የክስ መዝገቡ እንዲዘጋ ተደርጎ ጉዳዪ ተደፋፈነ››
" አያትሽ በወቅቱ...ማለቴ ግድያው ሲፈፀም እንዴት ይሄንን ጉዳይ አላነሱም?"
"እኔ ራሴ ይሄንን ጥያቄ ጠይቄያት ነበር። በወቅቱ ጉዳዩን ለመከታተል በቂ ገንዘብ አልነበራትም እና ደግሞ እንዳስፈሯሯት የራሴ የሆነ ጥርጣሬ አለኝ። በተጨማሪም በልጇ ግድያ ጉልበቷ ተሟጦ እና ቅስሟ ተሰብሮ ነበር፡፡ በዛ ላይ እኔን የመንከባከብና የማሳደግ ኃላፊነት ነበረባት ..እና በወቅቱ ማድረግ የቻለችው እቃዋን ሸክፋና እኔን ይዛ ሻሸመኔን ከተማን ለእነሱ ለቃላቸው ወደአዲስአበባ መሰደድ ነበር።››

❤31👍29
ጥላና የሰው ልጅ ይመሳሰላሉ
አለውልህ ብለው ሲመሽ ይጠፋሉ
ጨለማ ሲወርስህ ብርሀንህ ሲጠፋ
ቅን እኮ ነው ያልከው ታያለህ ሲ'ከፋ
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
አለውልህ ብለው ሲመሽ ይጠፋሉ
ጨለማ ሲወርስህ ብርሀንህ ሲጠፋ
ቅን እኮ ነው ያልከው ታያለህ ሲ'ከፋ
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
YouTube
አትሮኖስ_ Tube
Share your videos with friends, family, and the world
👍6❤3
#ልብ_አልባው_ገጣሚ
ሰው በሞተ ቁጥር
መግደል መሸነፍ ነው የሚል ከንቱ ተረት
ሟቹን ላያነሳ
ገዳይ ላይሸነፍ
መልመድ ካስተማረን እየወጡ መቅረት
ይቅርብን ስብከቱ
የቃሬዛ ሲሳይ መሆን ይታክታል
በማይሸነፉ
ስሜት አልባ ልቦች እልፍ ሰው ይሞታል።
እናም ለገዳዩ
የሽንፈትን ፅዋ ገሎ ለማይቀምሰው
በሟቹ ልትቆምር
በማይረባ ስብከት ድፍረት አታውርሰው
በቅቶናል አንተ ሰው።
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ሰው በሞተ ቁጥር
መግደል መሸነፍ ነው የሚል ከንቱ ተረት
ሟቹን ላያነሳ
ገዳይ ላይሸነፍ
መልመድ ካስተማረን እየወጡ መቅረት
ይቅርብን ስብከቱ
የቃሬዛ ሲሳይ መሆን ይታክታል
በማይሸነፉ
ስሜት አልባ ልቦች እልፍ ሰው ይሞታል።
እናም ለገዳዩ
የሽንፈትን ፅዋ ገሎ ለማይቀምሰው
በሟቹ ልትቆምር
በማይረባ ስብከት ድፍረት አታውርሰው
በቅቶናል አንተ ሰው።
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍9❤1
#የትል_ትዕግስት
እኔ ደቂቅ ፍጡር
በደረት ተሳቢ አካሄዴ ሁሉ የተንቀረፈፈ፤
ቅዱስ ያሬድ ብልጡ
ውድቀቴን በሙሉ
በአንክሮ አይቶ ተምሮ አተረፈ፤
በትንሽነቴ ንቆኝ አላለፈ!
በዚች እሽክርክሮሽ
ተመልከት ያሬድን
ከትል አስተሳሰብ ትዕግስትን ይወርሳል፤
በውጤቱ ማምሻ
በጥዑመ ዜማ ፈጣሪ ይወደሳል!
ተመልከታት ትሏን
የትዕግስቷ ልኬት በታሪክ ይወሳል፤
ቅዱስ ያሬድ ሲባል
የቅጠል ትል ታሪክ መች በዋዛ ይረሳል፤
ጌታ አስተምሮቱ በትልም ይገዝፋል!
ተመልከት እራስክን
ተስፋ ቤትህ ወድቆ
ትዕግስት በማጣትህ እምነትህ ይፈርሳል፤
በውድቀትህ ማግስት
ነክሽ ነካ እያለ ሰይጣን ይደግሳል!
🔘አብርሃም ፍቅሬ🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
እኔ ደቂቅ ፍጡር
በደረት ተሳቢ አካሄዴ ሁሉ የተንቀረፈፈ፤
ቅዱስ ያሬድ ብልጡ
ውድቀቴን በሙሉ
በአንክሮ አይቶ ተምሮ አተረፈ፤
በትንሽነቴ ንቆኝ አላለፈ!
በዚች እሽክርክሮሽ
ተመልከት ያሬድን
ከትል አስተሳሰብ ትዕግስትን ይወርሳል፤
በውጤቱ ማምሻ
በጥዑመ ዜማ ፈጣሪ ይወደሳል!
ተመልከታት ትሏን
የትዕግስቷ ልኬት በታሪክ ይወሳል፤
ቅዱስ ያሬድ ሲባል
የቅጠል ትል ታሪክ መች በዋዛ ይረሳል፤
ጌታ አስተምሮቱ በትልም ይገዝፋል!
ተመልከት እራስክን
ተስፋ ቤትህ ወድቆ
ትዕግስት በማጣትህ እምነትህ ይፈርሳል፤
በውድቀትህ ማግስት
ነክሽ ነካ እያለ ሰይጣን ይደግሳል!
🔘አብርሃም ፍቅሬ🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
❤7👍2
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
/////
አለም ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባቷ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ አያቷ የህግ ሙያ እንድታጠና አጥብቃ ትገፋፋት ነበር..በወቅቱ ምክንያቱ አይገባትም ነበር…እንዲሁ ሰዎች.. የልጅ ልጅሽ ጠበቃ ነች ወይም ዳኛ ነች እንዲሏት ካላት ምኞት ተነስታ የምትገፋፋት ይመስላት ነበር..አሁን ነው ነገሮችን ስታገጣጥም ምክንያቱ ፍንትው ብሎ የተገለፀላት፡፡
አለም በትምህርት ቤት ጎበዝ ተማሪ ነበረች እና በመጨረሻ አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍልም ወርቅ ሜዳሊያ አጥልቃ ነበር የተመርቀችው። የህግ ትምህርት አያቷ የመረጠችለት እና በእሷ ዘንድ በልጅነቷ ያላገኘችውን ሞገስ ለማግኘት ስትል የገባችበት ሙያ ነበር፣ ግን ከተማረችው በኋላ አያቷን ደጋግማ አመሰግናታለች… ምክንያቱም በጣም የሳባት እና ያስደሰታት መስክ ነው። የማወቅ ጉጉት ያለው አእምሮዋ ወደ ውስጡ የህግ ዕውቀቷቹን መጦ ሲያስገባ በደስታ ነው፡፡ ወደስራም ስትሰማራ በሙሉ የራስ መተማመንና በከፍተኛ የስራ ንቃት ነበር፡፡
አቃቢ ህጉ የእጅ ሰዓቱን ተመለከተ.. ከዚያም ሲጋራውን በከንፈሮቹ መካከል አስገብቶ ቆመና ኮቱን ከመስቀያው አነሳ "ያለ በቂ ማስረጃ የግድያ ክስ እንደገና መክፈት አልችልም። ታውቂለሽ። ከሀያአምስት አመት በፊት ተፈፅሞ የነበረ ወንጀልን ወደኋላ ተጉዞ መረጃ ማሰባሰብ ብራንድ ልብሶችን ለብሶ በመዘነጥ የአዳም ዘርን እንደማማለል ቀላል ስራ አይደለም…..እና መጀመሪያ እኔን አሳምኚኝ..ምን አልባት ከዛ በኋላ ስለክሱ ሁኔታ መልሰን እንንጋገርበት ይሆናል››
ልቅ የሆነ ንግግሩን ችላ ብላ በብስጭት ተመለከተችው፡አጠያየቋ በጣም ድፋረት የታከለበትና እና ቅንነት የጎደለው መሆኑን ታውቃለች።እሷ በእሱ ቦታ ብትሆን ከረጂም ደቂቃ በፊት ክፍሉን ለቃ ትወጣ ነበር፡፡
"አየሽ አለም፣ ይህ የምትጠይቀኝ ጉዳይ እንደምትይው ቀላል አይደለም…እነዚህ ሰዎች በደቂቃ ውስጥ ይህንን ቢሮ ወደ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ መቀየር የሚችሉ ናቸው። አንገቴን ልታስቀነጥሺኝ ካልፈለግሽ በስተቀር ይሄንን የአያትሽን ከንቱ ጥርጣሬ መልሰሽ ታነሺብኛለሽ ብዬ አልጠብቅም››ብሎ መንገዱን ቀጠለ፡፡ወደ ቢሮው ደጃፍ ሲያመራ ተከተለችው
"ክቡር አቃቢ ህግ ይሄ ለእኔ ጥልቅ ትርጉም ያለው ጉዳይ ነው። እንዴት እምቢ ትለኛለህ..የምታስበው ስለራስህ ብቻ ነው?።"
"እውነትሽን ነው እኔ እራስ ወዳድ ነኝ።
"ሲል መለሠላት።
"በሌሎች ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረጌን እንዳለ ሆኖ ይህን ግድያ እንዳጣራ ፍቃድ ስጠኝ።"ሙጭጭ አለችበት፡፡
"እኛ ምን አይነት ውዝግብ እንዳለብን ታውቂያለሽ? መአት አንገብጋቢ ጉዳዮች እጃችን ላይ አሉ ፤ሀያ ምናምን አመት የተረሳ...መዝገብ እራሱ በአቧራ የተበላ ጉዳይን በቀላሉ ለፍርድ ማቅረብ አንችልም።"
"እሺ በትርፍ ሰዓቴ እሰራለሁ፣ ሌሎች ኃላፊነቶቼ ላይ በምንም አይነት ተፅዕኖ እንዲያሳድር እላደርግም፣ለዛ ቃል ገባልሀለው ።"
"አለም"
"እባክህ … ግርማ በቅርቡ አንድ ተጫባጭ ፍንጭ ከላገኘሁ ..ጉዳዩን እርግፍ አድርጌ ተወዋለሁ...ከዚያ በኋላ ስለ ጉዳዩ በጭራሽ ከእኔ አትሰማም.››
በትኩረት ተመለከታት እና ፊቷን አጠና ። "ለምን እንዲህ አይነት ውስብስብ ነገር ውስጥ ራስሽን ታስገቢያለሽ ..እንደማንኛውም ወጣት ዘመናዊ ሴት .ዘና ያለ የህይወት መንገድን አትመርጪም፡፡ ።"
ፊቷን አኮስታተረችበት ።
"እሺ፣ እሺ፣ ምርመራውን መጀመር ትችያለሽ፣ ነገር ግን በትርፍ ጊዜሽ ብቻ ነው። ተጨባጭ የሆነ ነገር ይዘሽ ነይ። አለበለዛ ውሳኔዬን ታውቂዎለሽ .አሁን ከቀጠሮዬ አዘግይተሽብኛል።››ብሎ በቆመችበት ጥሏት ሄደ፡፡
በእርካታ ተነፈሰች፡፡ሸክሟ ከባድ ነበር ፡፡ እያቷ በእናቷ ግድያ ላይ ያላት መረጃ የተወሰነ ነበር። በጋዜጣ ላይ እንዳገኘችው መረጃ ከሆነ እናቷን በመግደል የተወነጀለው ሰው የአእምሮ ብቻ ሳይሆን የመስማትም ችግር እንዳለበት ነው፡ ።እነሱ መሠረታዊ እና ቀላል ችግሮች ነበሩ. የአእምሮ ዝግመት ችግር የነበረው ሊቁ የተባለው ሰው በግድያው ቦታ በተያዘበት ጊዜ የሟቾ እናቷን ደም በጠቅላላ ልብሱ ላይ ተነክሮ እንደነበረ ተዘግቦ ነበር።በተጨማሪም በተያዘበት ወቅት ተጎጂዋን ገድሎበታል የተባለበትን የቀዶ ጥገና መሳሪያ በእጁ ይዞ ነበር።በዛ ምክንያት ወዲያው በቁጥጥር ስር ውሎ ታስሯል፣ ተጠየቋል
እና ተከሷል። በቀናት ውስጥ ነበር ችሎት የቀረበው። ወዲያው ዳኛው ካለበት የጤና እክል የተነሳ ለፍርድ የመቅረብ ብቃት እንደሌለው አውጀው በመንግስት የአእምሮ ሆስፒታል ውስጥ አንዲታሰር ትዕዛዝ አስተላለፉ።ተጠርጣሪው ግን ወደአእምሮ ሆስፒታል ተመዘዋወሮ ብዙም ሳይቆይ እራሱን አጠፋ ተባለ፡፡ በውቅቱ ወንጀለኛውን አሳዶ ለመያዝ
..ከዛም ፍርድ ለማስተላለፍና ፋይሉን ለመዝጋት የነበረው ጥድፊያ ያስደነግጣል፡፡ እናም ከፍተኛ ጥርጣሬም በአለም አእምሮ ውስጥ ጭሯል፡፡
በሶስተኛው ቀን ያገኘችውን ተጨማሪ መረጃ ይዛ ዋና አቃቢ ህጉ ፊት ለፊት ቀረበች፡፡መረጃዎቹን ካቀበለችው በኃላ
‹‹የእረፍት ቀን እንዴት ነበር?›››ስትል ለጫወታ መጀመሪያ ጠየቀችው፡፡
"ድንቅ ነበር. ካንቺ የበለጠ ውጤታማ ቀናቶችን አሳልፌለሁ ብዬ አስባለው። ብዙ ነገሮችን የማንበብ እድል ነበረኝ።"
ፋይሉን ገልጦ ይዘቱን መቃኘት ጀመረ። "እህም" የመጀመሪያ ንባቡ ትኩረቱን ለመሳብ በቂ ነበር። ወንበሩ ላይ ተደግፎ በጥንቃቄ በድጋሚ አነበበው።
"ይህ ዶ/ር ታደሰ የተባለው … ሊቁ የታሰረበት የነበረበት የአእምሮ ሆስፒታል ሐኪም ነው?"
‹‹አዎ ነው››
‹‹ታዲያ አግኝተሸ ማነጋገር አልቻልሺም?››
"አልቻልኩም እንዳለመታደል ሆኖ ከጥቂት ወራት በፊት ሞቷል." "አስደሳች ነው."
"አስደሳች?" አለም በንግግሩ ተበሳጨች። ወንበሯን ትታ ዞረች እና ከኋላው ቆመች
"ይሄ ታደሰ የተባለው ዶክተር ሊቁ የግድያ ወንጀል ለመፈፀም ብቃቱ እንዳለው ሙያዊ ውሳኔ ላይ ሲደርስ ለመጨረሻ ጊዜ የተከታተለው ሌላ የስነ አእምሮ ሃኪም ግን ሊቁ የተባለው ግለሰብ የአእምሮ በሽተኛ ቢሆንም ምንም አይነት ሰውን የማጥቃት ዝንባሌ አሳይቶ እንደማያውቅ በሪፖርቱ አስፍሯል.. ምንም አይነት የወሲብ ፍላጎት እንደሌለው እና
አመፀኝነትም ታይቶበት እንደማያውቅ ተናግሯል፡፡ እና በዶክተሩ ሞያዊ አስተያየት መሠረት እሱ እኔን ዋጋ እንዳስከፈለኝ አይነት የግድያ ወንጀል መስራት እንደማይችል ነው ያረጋገጠው።ገደለ በተባለው ሰው ላይ ሁለቱ ባለሞያዎች የተለያ አይነት ምልከታ ነበራቸው…ይሄም ከመዝገቡ ጋር ተያይዞል..ዳኛው የባለሞያዎቹን ውሳኔ ሚዛናዊነት ለመጠበቅ የሶስተኛ ባለሞያ አስተያየት መጠየቅ ሲገባቸው ባልታወቀ ምክንያት የአንደኛውን አስተያየት ውድቅ አድርገው የሌለኛውን ተቀብለዋል፡፡በአጠቃላይ…ሊቁ የተባለው ሰው እናቴን አልገደላትም የሚል በጣም ጠንካራ እምነት አለኝ።›› አቃቢ ህጉ ሌሎች በርካታ አጭር መግለጫዎችን አነበበ፣ ከዚያም አጉተመተመ፡-
"በአጭር ቀናት ከዚህ የበለጠ ተአምራዊ የሆነ ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ አልችልም። ጉዳዩ ሃያ አምስት አመት ያስቆጠረ ነው። ተስፋ የማደርገው ይሄ ጉዳዩን በ ዳኞች ፊት ለማቅረብ በቂ ምክንያት ነው። በተጨማሪም የዓይን እማኝ የማግኘትም ትንሽም ቢሆን እድል አለኝ
።"
አቀቢ ህጉ‹‹አለም.››ሲል ተጣራ "አቤት"

❤44👍5
"የቤት ስራሽን በበቂ ሁኔታ ሰርተሻል፣ ግን ግድያው የተፈፀመው በሶሌ ኢንተርፕራይዝ ንብረት በሆነው የከብት እርባታ ግዙፍ ግቢ ውስጥ ነው፡፡ የዚህ ኢንተርፕራይዝ ባለቤቶች በዚህ ከተማ ውስጥ በጣም ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ከመሆናቸው የተነሳ የአይን እማኝ ቢኖር እንኳን በእነሱ ላይ አይመሰክርም ….ምክንያቱም ወይ በገንዘባቸው ይደልሉታል..አልደለል ካለም ያጠፉታል ፡፡ ››
‹‹በየትኛውም መንገድ እነሱን ለመፋለም ቁርጠኛ ነኝ››
'እሺ አምንሻለሁ። ነገር ግን በሻሸመኔ ከተማ ቁጥር አንድ ሀብታም በሆኑትና ከተማውና በማሳደግ በሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ዋና ተሳታፊ እንደሆኑ የሚታወቁት ሰዎች ላይ ክስ መክፈት እንዲህ ቀላል አይደለም…በዛ ላይ የፖሊስ አዛዡም ቢሆን ቀላል የሚባል ባለጋራ አይደለም..እና በተለይ እዚህ ቦታ ላይ ሆነሽ ማለቴ የምክትል አቃቢ ህግ ስልጣን ይዘሽ ይሄንን ክስ መቀስቀስ ነገሩን የበለጠ ውስብስብ ያደርገዋል፡፡ምን አልባት እንዳሰብሺው ክስሽን ሚደግፉ መረጃዎችና ማግኘት የማትችይ ከሆነ እንደግለሰብ ብቻ ሳይሆን
እንደተቋምም ቢሮችንን ያስወቅሳል…እኔና አንቺም ስራችንንም ልናጣ የምንችልበት እድል ከፍተኛ ነው፡፡
እንደማኩረፍ አለችና "እሺ ከዚህ ቢሮ ስራዬን ለቅቄ በራሴ አደርገዋለሁ" አለችው። "በኢየሱስ …ንግግሬን እኮ እንድጨርስ አልፈቀድክሺልኝም።››
መጥሪያውን ተጫነና ቡና እንዲያመጣለት ፀሐፊውን ላይ ጮኸበት። ወዲያው ሲጋራ ለኮሰ ።
"በሌላ በኩል" ሲል ንግግሩን ጀመረ "ያንን ኩማንደር አልወደውም..እሱን ወደ ገደል ጎትቶ የሚጥል ቁራጭ እድልም ቢሆን ካገኘሁ ልጠቀምበት እፈልጋለው….. ››
የአለም እየከሰሙ የነበሩ አይኖች በሌላ ተስፋ ሲፈኩ ታዩ‹‹እና ምን እያልከኝ ነው?›› "ስለዚህ ክሱን እንደገና መክፈት ትቺያለሽ እያልኩሽ ነው?"
በደስታ ዘለለችና ከጀርባው ተጠመጠመችበት፡፡፡
" አለም አንቺ ጎበዝ ተፋላሚ ነሽ። ምርጥ የህግ ባለሞያ እንደሆንሽ በተደጋጋሚ ጊዜ አሳይተሸል ፤ይሄንንም ጉዳይ ከስር መሰረቱ በርብረሽ ውጤታማ እንደምትሆኚ አምናለው ››አለና የሰጠችውን ፋይል ሰብስቦ ወደፎልደሩ መልሶ ከተተና መለሰላት፡፡
አለምም በአቃቢ ህጉ ጠረጴዛ ላይ ተደግፋ። " ልክ እንደ ሆንኩ አውቃለሁ። እውነተኛውን ገዳይ ለፍርድ አቀርባለሁ፣ ያንን ማድረግ ካቃተኝ ኃላፊነቱን ሁሉ በግሌ እወስዳለው፡፡››አለችው፡፡
አይኖቹን በደረቷ ላይ አፈትልከው የሚታዩት ጡቷቾ ላይ ሰክቶ‹‹አይ ይሳካልሻል…ደግሞ ይሄንን አማላይ ውበትሽንና ቅንዝንዝ ሴትነትሽንም ተጠቀሚበት››አላት፡፡
‹‹ትልቅ ሰው አይደለህ እንዴ…..?ለማንኛውም በሰጠሀኝ ፍቃድ በጣም ስለተደሰትኩ የተናገርከውና እንዳልተናገርክ ቆጥረዋለው››አለችና ክፍሉን ለቃ በመውጣት ወደራሷ ቢሮ ሄደች፡፡ከዛ በኋላ ነበር ዋና አቃቢ ህጉ በዳኛ ዋልልኝ አማካይነት የጥዋቱን ስብሰባ ከእናቷ ገዳይነት ከምትጠረጥራቸው ሶስት ኃያላን ሰዎች ጋር እንድትገናኝ እና…ፊት ለፊት እንድትገጥማቸው እድሉን ያመቻቸላት፡፡እዛው አልጋዋ ላይ እየተገላበጠች በሀሳብ ከወዲህ ወዲያ ስትላጋ እኩለ ለሊት ማለፉን ልብ አላለችም ነበር…..፡፡

❤37👍10
#አዎ_ትመጣለች
ትመጣለች እያልሁ
ቀኔን እንደ ምግብ ስበላው አኝኬ
አዝኖልኝ ነው
መሰል አትመጣም የሚል ቃል ይልካል አምላኬ
ሰይጣን ደግሞ በጎን ቄጠማ ነስንሶ
ትመጣለች ጠብቅ
ብሎ ይነግረኛል ቃሉን አለስልሶ
አውቃለሁ እውነት ነው
ፈጣሪ ያለው ቃል አይስትም ሚዛኑን
ሰይጣን ስግብግብ ነው
ቀን እየነጠቀ ያስረዝማል ቀኑን
ቢሆንም
ቢሆንም
እውነት እንደ ኮሶ እያንገሸገሸኝ አልጠጣም ደፍሬ
ተስፋን በገሃዱ እጋታለሁ እንጂ ከውሸት ቆንጥሬ
አዎ ትመጣለች
እውነቱን እያወቅሁ አላምንም እውነቱን
ቀን የተቀማ ሰው
ሃሰትን ተግቶ ተስፋን እየጠጣ ያረዝማል ህይወቱን
ሰይጣን ትመጣለች አይደል?
🔘✍️በላይ🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ትመጣለች እያልሁ
ቀኔን እንደ ምግብ ስበላው አኝኬ
አዝኖልኝ ነው
መሰል አትመጣም የሚል ቃል ይልካል አምላኬ
ሰይጣን ደግሞ በጎን ቄጠማ ነስንሶ
ትመጣለች ጠብቅ
ብሎ ይነግረኛል ቃሉን አለስልሶ
አውቃለሁ እውነት ነው
ፈጣሪ ያለው ቃል አይስትም ሚዛኑን
ሰይጣን ስግብግብ ነው
ቀን እየነጠቀ ያስረዝማል ቀኑን
ቢሆንም
ቢሆንም
እውነት እንደ ኮሶ እያንገሸገሸኝ አልጠጣም ደፍሬ
ተስፋን በገሃዱ እጋታለሁ እንጂ ከውሸት ቆንጥሬ
አዎ ትመጣለች
እውነቱን እያወቅሁ አላምንም እውነቱን
ቀን የተቀማ ሰው
ሃሰትን ተግቶ ተስፋን እየጠጣ ያረዝማል ህይወቱን
ሰይጣን ትመጣለች አይደል?
🔘✍️በላይ🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍11❤5😢1